YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
"በዒድ ሰላት ወቅት የተከሰተው ክስተት በክርስቲያኑና በሙስሊሙም መካከል የተፈጠረ አይደለም።"

- የአዲስአበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት


"አንዳንድ አካላት ችግሩን ከመንግስት ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውም የተሳሳተ መሆኑን አረጋግጠናል።

በዒድ ሰላት ወቅት የተፈጠረው ችግር ምን እንደሆነ በስፍራው ከነበሩ በጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎቻችን ደርሶናል። በአንድ ፌደራል ፖሊስ ድንገት (ባርቆብኝ ነው ብሏል) በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስ ምክንያት የተፈጠረ ግርግር ነበር። የአስለቃሽ ጭሱ እንደተተኮሰ በቦታው የነበሩ የበአሉ ታዳሚዎች በከፍተኛ ደረጃ ተደናግጠዋል።ወደ ፌደራል ፖሊሱ በማቅናት ይዘውታል።ፖሊሱም ድንገት ባርቆበት እንደሆነ ተናግራል። ሆኖም ህዝቡ ከፍተኛ የሆነ መረበሽ ውስጥ ስለገባ ለመግባባት አልተቻለም።

በመጨረሻም የፌደራል ፖሊሱ በኤግዚቢሽን ማዕከል አካባቢ ወደ ሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ካንፕ እንዲገባ ተደርጓል።ይህን ተከትሎ ሌሎች ፖሊሶች ከካምፑ ሲወጡ ተኩስ የፈጠረው ግርግር ባለመረጋጋቱ ችግሩ ሊባባስ ችሏል።

ከዚህ በተረፈ ከእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ጋር ችግሩን የሚያይዘው ነገር አለመኖሩ ተረጋግጧል። በመንግስት በኩልም ሆነ ተብሎ የተፈጠረ ችግር አለመኖሩን አረጋግጠናል።በመሆኑም ህዝቡ እንዲረጋጋ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።"

የአዲስአበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
🥳መልካም የትንሳኤ በአል እያልን የበአል ልዩ ቅናሽ ይዘን መጥተናል🥳
https://tttttt.me/getitonlinee
የወንድም የሴትም
🎯ኦርጂናል ጥሩ ሽታ ያላቸው ሽቶዎች
🎯የስጦታ ጥቅሎች(package)🎁
🎯ኦርጂናል ሰአቶች
🎯 ቦርሳዎች እና የውበት መጠበቂያዎች
🎯 አልባሳት እና ጫማዎች

🎯ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ በ0929011031

🎯አድራሻ፣ ቦሌ መድሀኒያለም
ያሉበት ቦታ ድረስ በነጻ እናደርሳለን
የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ቤተሰብ ይሁኑ https://tttttt.me/getitonlinee
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
“በህዳሴው ግድብና በፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች ከሽፈዋል”

– የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

በህዳሴው ግድብና በከፍተኛ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች መክሸፋቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ገለፀ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያን መልካም ነገር ማየት በማይፈልጉ የውስጥና የውጪ ኃይሎች የሚደገፉ አካላት ህዳሴው ግድብ ላይ በተቀናጀ መልኩ የሳይበር ጦርነት ከፍተው ነበር። ጥቃቶቹ ምንም ጉዳት ሳያደርሱ እንዲመክኑ ተደርጓል።

በተመሳሳይም በኢትዮጵያ ከፍተኛ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ በርካታ የሳይበር ጥቃቶች በባለሙያዎች ጥረት እንዲከሽፉ ተደርጓል ሲሉ ተናግረዋል።

የሃገሪቱን ሰላምና ዕድገት በማይፈልጉ ሃገራት የሚደገፍ ድርጅት የህዳሴው ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል በማቀድ ‘ብላክ ፒራሚድ ወር’ በሚል ስያሜ የሳይበር ጦርነት ከፍቷል። ይሁንና የጥፋት አላማ አቅደው ሲያሴሩ የነበሩት ሁሉ እንዳሰቡት ሕልማቸው ሳይሳካ ተጨናግፏል ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ እንዳስታወቁት፤ ከህዳሴው ግድብ ውኃ ሙሌት ጋር በተያያዘ ብላክ ፒራሚድ ወር የሚባል የኮምፒውተር ቫይረስ ተሠርቶ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ተደርጓል። በተለይም የፋይናንስ ተቋማት የሚጠቀሙባቸውና እርስ በእርሳቸው የተሳሰሩ 37 ሺህ ኮምፒውተሮችን ላይ ጥቃት በመፈጸም...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=72108

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ሀዘንን ለመግለጽ በቀብር ስነ ስርዓት ላይ በተተኮሰ ጥይት የአስር ልጆች እናትን ጨምሮ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ!

በሰሜን ሸዋ ዞን ጅዳ ወረዳ ለሀዘን መግለጫ በሚል በተተኮሰ ጥይት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡በክስተቱ ህይወታቸዉን ያጡት የመጀመሪያ ሟች የ55 ዓመት እድሜ ያላቸውና የአስር ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ ሎሚ ሎሜታ ሲባሉ ሁለተኛዋ ሟች ወጣት ዲቃ ዘውዴ የሁለት ልጆች እናት ነበሩ፡፡

ሁለቱም ግለሰቦች የሰሜን ሸዋ ዞን ጅዳ ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ አደጋው ባለፈው ሳምንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ የሟቾች ዘመድ በሆኑት በአቶ እሸቱ ገለልቻ የቀብር ስነስርዓት ላይ በተገኙበት ወቅት በአካባቢው የቆየ ጥይት የመተኮስ ባህል መሰረት በቀብር ስነስርዓቱ ላይ በአቶ ሽፈራው ገለልቻ በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል፡፡

አቶ ሽፈራው ገለልቻ በባህሉ መሰረት ሀዘናቸውን ለመግለጽ በአካባቢው ከነበሩት የቅርብ ጎደኛቸው ከሆኑት አቶ ዳኜ አበራ መሳሪያ በመዋስ ፈረስ ላይ በመሆን በተኮሱት ጥይት ፈረሱ በመደንበሩ እና መሳሪያው አውቶማቲክ በመሆኑ ምክንያት በመባረቁ ህይወታቸዉን ካጡት ሰዎች በተጨማሪ አንድ ሰው ላይ ቀላል የሚባል ጉዳት እንደደረሰበት በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ፖስ የኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት ኮማንደር ታዲዮስ ዘውገ ተናግረዋል፡፡

በቀብር ስነስርዓቱ ላይ በተከሰው ያልተጠበቀ አደጋ ምክንያት የቀብር ስነስርዓቱ ለሰዓታት የተራዘመ ሲሆን የመሳሪያው ባለቤት የሆኑት አቶ ዳኜ አበራ እስካሁን ያሉበት አለመታወቁን ነገር ግን ጥይቱን የተኮሱት አቶ ሽፈራው ገለልቻ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር ታዲዮስ ዘውገ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ከሰሞኑ በጎንደር ከተማ ተከስቶ የነበረውን ግጭት አስመልክቶ የተዘጉ ሱቆች እንዲከፈቱና ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱ ተገለፀ!

ከሰሞኑ በጎንደር ከተማ ተከስቶ የነበረውን ግጭት አስመልክቶ የተዘጉ ሱቆች እንዲከፈቱና ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱን የፋሲል ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።በዛሬው ዕለት በፋሲል ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከሦስቱም ቀበሌዎች ተደማጭነት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ጥሪ በማድረግና ኮሚቴ በማቋቋም በደረሰው ግጭት የማረጋጋት እና የተዘጉ ሱቆችን ወደ ሥራ ማስመለስ ሥራን ለመስራት የሚያስችል ውይይት ተደርጓል።

በክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሚመራው ኮሚቴው በዋነኝነት 4 ጉዳዮች ላይ እንደሚሰራ የፋሲል ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዳኛቸው ቢምር ገልፀዋል።ዳኛቸው እንዳሉት በዛሬው ዕለት የተቋቋመው ኮሚቴ የተጎዱ ሰዎችን የሚያፅናና፣ የወደሙ ንብረቶችን ለይቶ ድጋፍ የሚያሰባስብ፣ የጠፋ ንብረት ካለ የሚያስመልስ እና የተዘጉ ሱቆችን የማስከፈትና ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ ማድረግ የኮሚቴው ዋነኛ ተግባር ነው ብለዋል።

በቀጣይም የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የነበረው ተከባብሮና ተደጋግፎ የመኖር እሴት ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ መገለፁን ከክፍለ ከተማው መንግስት ኮምዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።ለዚህም ይረዳ ዘንድ ኹሉም የእምነት ተቋማት ፣ የከተማው ነዋሪዎች ከመንግስት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ እና በህዝቦች መካከል ግጭትን በመፍጠር እየሰሩ የሚገኙ አካላትን በመለየት በህግ ተጠያቂ እንደሚደረጉም ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ1600 በላይ ጥንዶት ፍቺ መፈጸማቸዉን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በበጀት ዓመቱ መጀመርያ ታውጆ በነበረው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ምክንያት ዝቅ ብሎ የነበረውን ምዝገባ ለማካካስ በተሰሩ ስራዎች በ9 ወር አፈፃፀሙ የተሻለ ውጤት መገኘቱን ኤጀንሲው አስታውቋል።በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ ባለፉት 9 ወራት ከ23ሺህ በላይ ጋብቻ ፣1,695 ፍቺ፣10ሺህ 219 ሞት ፣186,986 ልደት፣ከ93 በላይ የጉዲፈቻ ምዝገባዎች መከናወናቸውን የኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለሙ ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

የወቅታዊ ምዝገባ በ2013 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር የልደት ምዝገባ በ61 በመቶ ፣ የጋብቻ ምዝገባ በ9.5 በመቶ፣ የሞት ምዝገባ በ20.3 በመቶ ብልጫ ሲያሳይ በአንፃሩ የፍቺ ምዝገባ እና የጉዲፈቻ ምዝገባ ዝቅተኛ ነዉ ብለዋል። የወቅታዊ ምዝገባ ሽፋንን ለማሻሻል በቅርቡ በጤና ተቋማት የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከከተማው ጤና ቢሮ ጋር በጋራ የጀመረው ኤጀንሲው ከአምስት የመንግስት ጤና ተቋማት ወደ 22 የግል እና የመንግስት ጤና ተቋማት ከፍ በማድረግ እየሰራ ይገኛል ሲሉም ተናግረዋል።

በጥቅሉ ኤጀንሲው በዘጠኝ ወሩ ዉስጥ ለ222,765 ነዋሪዎች እና የውጭ ዜጎች አለም አቀፍ አሰራርን በተከተለ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገልግሎት ሰጥቷል። ከ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ብልጫ ያለው አገልግሎት መስጠቱን አቶ ዮናስ ጨምረው ተናግረዋል።

[ብስራት ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦች

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-

- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።


አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ 0917040506
0912718883
ይደውሉ።

መፍትሔ ሥራይ ወአይነ ጥላ ለጤናወ መፍትሔ ከመሪጌታ ጥበቡ
ለጤናወ መፍትሄ በዚህ ስልክ ደውለው ያግኙን

0917040506
0912718883

https://tttttt.me/meritibe
https://tttttt.me/meritibe
የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ያሰራቸውን ጋዜጠኞች ደሱ ዱላ እና ቢቂላ አመኑን ባስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቋል።

ድርጅቱ የክልሉ ፖሊስ በተከሳሾቹ ላይ የመሠረተውን ክስ እንዲያቋርጥ እና ጋዜጠኞቹን ያለ ጥፋታቸው ያሰሩ ባለሥልጣናት ተጠያቂ እንዲሆኑ ጨምሮ ጠይቋል። በበይነ መረብ የሚሰራጨው የኦሮሚያ ኒውስ ኔትዎርክ ባልደረቦች የሆኑት ጋዜጠኞች፣ ከኅዳር ጀምሮ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ታስረው የሚገኙ ሲሆን፣ የተከሰሱት ከ3 ዓመት እስራት እስከ ሞት በሚያስቀጣው ሕገ መንግሥት የመናድ ወንጀል ነው።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ሁለቱ ኮሚሽኖች ሥራቸውን ለአዲሱ የምክክር ኮሚሽን አስረከቡ!

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች እንዲሁም ሀገራዊ የዕርቀ-ሰላም ኮሚሽኖች፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አፈ-ጉባዔዎች በተገኙበት፤ የሥራ ኃላፊነታቸውን እና ሰነዶቻቸውን ለአዲሱ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስረከቡ፡፡

በዛሬው ዕለት በተከናወነው በዚህ ርክክብ፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ ታገሠ ጫፎ፤ ኮሚሽኖቹ ብዙ ፈተናዎችን መሻገራቸውን ገልጸው፣ በቂ ክትትል እና ድጋፍ ቢደረግላቸው ካከናወኗቸው ተግባራት በላይ መስራት ይችሉ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በመሆኑም፤ እነርሱ ካለፉበት ሁኔታ ትምህርት በመቅሰም፣ ለአሁኑ የምክክር ኮሚሽን አስፈላጊው ክትትል እና ድጋፍ መደረግ እንዳለበት አፈ-ጉባዔው አስገንዝበዋል፡፡

ሀገርን ለማስቀጠል እና ለማጽናት ይቻል ዘንድም በቅንነት እና በማስተዋል በመመካከር፤ ሕዝቡ የሚሰጠውን ውሳኔ ሁሉም አካል መቀበል ይኖርበታል ማለታቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኦሮሚያ ክልል ውስጥ መንግስት ታጣቂዎችን ለመዋጋት በሚያደርገው ሂደት ውስጥ የንጹኃን ዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታውን መወጣት አልቻለም ሲሉ ኦፌኮ እና ኦነግ ወቀሱ።

ፓርቲዎቹ ለመገናኛ ብዙኃን በላኩት ጋዜጣዊ መግለጫ ይህንኑ ብለዋል።በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ስፍራዎች እንዲሁም በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ንጹሃንን ያልለዩ ግድያዎች ይፈጸማሉም ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ንጹሃን ዜጎችን ደኅንነት እንደሚጠብቅ በመግለጥ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ አባላት ጭምር ከተገደሉት ውስጥ ይገኙበታል ብሏል። 

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🥳መልካም የትንሳኤ በአል እያልን የበአል ልዩ ቅናሽ ይዘን መጥተናል🥳
https://tttttt.me/getitonlinee
የወንድም የሴትም
🎯ኦርጂናል ጥሩ ሽታ ያላቸው ሽቶዎች
🎯የስጦታ ጥቅሎች(package)🎁
🎯ኦርጂናል ሰአቶች
🎯 ቦርሳዎች እና የውበት መጠበቂያዎች
🎯 አልባሳት እና ጫማዎች

🎯ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ በ0929011031

🎯አድራሻ፣ ቦሌ መድሀኒያለም
ያሉበት ቦታ ድረስ በነጻ እናደርሳለን
የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ቤተሰብ ይሁኑ https://tttttt.me/getitonlinee
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
የአውሮፓ ህብረት የሩሲያ የተፈጥሮ ጋዝን ለመተካት አፍሪካን እያማተረ ነው

ህብረቱ እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ 50 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ጋዝ ለመግዛት አቅዷል
የአውሮፓ ህብረት ከሩሲያ የሚገዛውን የተፈጥሮ ጋዝን ለመተካት ፊቱን ወደ አፍሪካ ማዞሩ ሪፖርት አመላከተ።

ከአውሮፓ ህብረት የተገኘ ረቂቅ ሰንድን ዋቢ አድርጎ በሉምበርግ ባወጣው ሪፖርት፤ በአፍሪካ ውስጥ ያሉ እንደ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና አንጎላ ያሉ ሀገራት በአብዛኛው ጥቅም ላይ ያልዋለ ከፍተኛ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አላቸው።

ቻይና ከሩሲያ የምትገዛውን የነዳጅ መጠን በ60 በመቶ አሳደገች

ለዚህም ህብረቱ ከሩሲያ በስተቀር ወደ ሌሎች ሀገራት የጋዝ ቧንቧ መስመር ጨምሮ በተለያዩ የጭነት አማራጮች የሚያስገባውን የጋዝ መጠን ለመጨመር ማቀዱም ተገልጿል።
የአውሮፓ ህብረት እቅዱን ለማሳካት ከአሜሪካ ጋር ያለውን የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ስምምነትን ሙሉ በሙሉ መተግበር እንዳለበትም ተነግሯል።

እንደሁም እንደ ግብፅ፣ እስራኤል፣ አዘርባጃን እና አውስትራሊያ ካሉ አቅራቢዎች ጋር ያለውን የንግድ ስምምነት ማጠናከር እንደሚጠበቅበትም ተመላክቷል።

ሩሲያ ከመጋቢት መጨረሻ ቀናት ጀምሮ አውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ወዳጅ ላልሆኑ ለሌሎች ሀገራት ነዳጅ በሩብል እንዲሸጥ መወሰኗ ይታወሳል።
የአውሮፓ ህብረት የሩሲያን አዲስ የነዳጅ ግዥ ውሳኔ ውድቅ ያደረገ ቢሆንም የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በበኩሉ ማዕቀቡን ሳይጥሱ የአውሮፓ የነዳጅ ኩባንያዎች ከሩሲያ በሩብል እንዲገዙ ፈቅዷል።
ጣሊያን በሩሲያ ላይ ካላት የነዳጅ ጥገኝነት ለመላቀቅ አፍሪካን እያማተረች ነው
ከ10 በላይ የአውሮፓ ሀገራት ነዳጅ በሩብል ከሩሲያ በመግዛት ላይ ሲሆኑ ፖላንድ እና ቡልጋሪያ ነዳጅ ለመግዛት ሩብል ባለማቅረባቸው ምክንያት ሩሲያ ነዳጅ መሸጥ ማቆሟ አይዘነጋም።

ቻይና ባሳለፍነው ተመሳሳይ ወራት ከሩሲያ የገዛችው የነዳጅ መጠን ከዘንድሮው ጋር ሲነጻጸር በ60 በመቶ ማደጉን በትናትናው እለት የወጣ ሪፖት ያመላክታል።

@Yenetube @Fikerassefa
አልሸባብ 170 የአፍሪካ ህብረት ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ

የአልሸባብ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ሶማሊያ የብሩንዲ ወታደሮች በሚገኙበት የአፍሪካ ህብረት ጦር ሰፈር ላይ ኢላማ በማድረግ በሰነዘረው ጥቃት ከ170 በላይ የብሩንዲ ወታደሮችን መግደሉን አስታውቋል።

ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሰሜን ምስራቅ 130 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የጦር ሰፈር ከባድ ውጊያ እንደነበር የዜና ኤጀንሲዎች የዓይን እማኞችን ጠቅሰዉ ዘግበዋል።

ትላንት ጎህ ከመቅደዱ በፊት የተካሄደው ወረራ ተከትሎ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ እንደነበር የተዘገበ ሲሆን፥ ከሄሊኮፕተሮች የተተኮሱ መሳሪያዎች መመልከታቸውን የዓይን እማኞች ጨምረው ተናግረዋል።

"አሸባሪዎቹ የቡሩንዲ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል በሁለቱም ወገኖች ከባድ ጦርነት እና ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ነገር ግን ስለዚህ ክስተት እስካሁን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ የለንም።"ሲሉ የአካባቢው ወታደራዊ አዛዥ ሞሃመድ አሊ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግረዋል።

ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ከመደረጉ በፊት ጥቃቱን የጀመሩት ታጣቂዎቹ በመኪና ላይ ያጠመዱትን ቦምብ በማፈንዳት ነው ሲሉም አክለዋል።አልሸባብ ባወጣዉ መግለጫ እንዳስታወቀው የጦር ሰፈሩን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ይፋ ቢያደርግም በገለልተኛ አካል ግን አልተረጋገጠም።

የአፍሪካ ህብረት ጦር እየተባለ የሚጠራው እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ማለትም ከኡጋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ የተውጣጡ ወታደሮችን ያቀፈ ስብስብ ነው።የሞቃዲሾን መንግስት ከአልሸባብ ታጣቂዎች ጋር የሚያደርገውን ውጊያ የአፍሪካ ህብረት ጦር እየደገፈ ሲሆን በአልሻባብ ታጣቂዎች ከዚህ ቀደምም የጥቃት ኢላማ እንደነበር ይታወሳል፡፡

Via:- Bisrat FM
@Yenetube @Fikerassefa
ለረጅም አመታት ደምበኞችን በትጋት ሲያገለግል የቆየው እና አንቱታን ያተረፈው አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ እቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ ዘመኑ ባፈራቸው ዘመናዊ በረቀቁ ማሽኖች እና በዘርፉ አንቱታን ባተረፍ ባለሞያዎቻችን በመታገዝ ለመኖሪያ ቤቶው እና ለቢሮ አዳዳስ ምርቶችን ውበትን በተላበሱ ዲዛይኖች እና በበርካታ አማራጮች ይዞላችሁ ቀርቧል።

ለቤትዎ ግርማሞገስ የሚሆኑ ለአይን ዕይታ ማራኪ የሆኑ በሌዘር እና በጨርቅ የተሰሩ ዘመናዊ ሶፍዎች! ቀን በስራ ሲደክም የዋለ ሰውነቶን እፎይ የሚሉባቸው ቅንጡ አልጋዎች በፈለጉት ዲዛይኖች !

የምግብ ወንበር እና ጠረጴዛዎች ! እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት እና ህንፆዎች የሚያገለግሉ በአይነታቸው ልዩ የሆኑ ፈርኒቸሮችን ጥራታቸውን እና ጥንካሬዎቻቸውን ጠብቀው እርሶ እኛ ዘንድ ያገኛሉ !

እርሶ ብቻ ያሻዎትን ይዘዙን ከድርጅታችን የተለያዩ እቃዎችን ሲገዙ ማጓጓዣ እና የሰራተኛ አቅርቦት ከኛ መሆኑ ወጪዎን ይቀንስሎታል የፈለጉትን ዕቃ ያለቀጠሮ መግዛት በመቻሎ ! እና ያዘዟቸውን እቃዎች በቀጠሮ ቀን ማድረስ በመቻሎ ከሌሎች ልዩ ያደርገናል አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ አድራሻ

#ቁ 1 ሀዋሳ ሞቢል ከድሮ ሸዋበር ሆቴል ፊትለፊት

#ቁ2 ሀዋሳ መናሀርያ ዙፍን ህንጳ ስር እንገኛለን

#ቁ3 ሀዋሳ መናሀርያ ኖክ ማደያ ውስጥ እንገኛለን
#ቀ4 ሀዋሳ ወልደ አማኑኤል ዱባለ አደባባይ አለፍ ብሎ 300ሜ ላይ ባለው አጠና ተራ ፊት ለፈት እንገኛለን ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥራችን
0966464646
0916107676
0916581884 ሀሎ ይበሉን

አበራ ላንጋኖ የቤትና የቢሮ እቃዎች ስራ ድርጅት ሀዋሳ
ከ33ሺ በላይ ተፈናቃዮች ከአበርገሌ ወደ ሰቆጣ መግባታቸው ተነገረ

በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሁለት ወረዳዎች እና የተለያዩ ቀበሌዎች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪው ተብሎ የተፈረጀው የህወኃት ቡድን ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከቤት ንብረታቸዉ እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል፡፡በዚህም የተነሳ በየእለቱ የተፈናቃዮች ቁጥር በመጨመሩ በርካታ ሰዎች ለእንግልት እየተዳረጉ ይገኛል፡፡

በተለይም ከ70ሺ በላይ ነዋሪዎች የሚገኙባት የአበርጌሌ ወረዳ እስካሁን ድረስ በህወኃት ሀይሎች እጅ ስር በመሆኑ አለመረጋጋቱ መባባሱ ተገልጿል፡፡በወረዳው ያለዉ የጸጥታ ሁኔታ ባለመረጋጋቱ የተነሳ በርካታ ሰዎች ለእግልት እየተዳረጉ በመሆኑ ከ33ሺ በላይ የሚሆኑ ተፋናቃዮዎች ከአበርገሌ ወደ ሰቋጣ እየገቡ ይገኛል፡፡

በአበርገሌ ወረዳ በየእለቱ ከጸጥታ ሁኔታ ባለመረጋጋቱ የተነሳ ህጻናት፣አዛውንቶች እና ሌሎችም ችግር ላይ ናቸው ሲሉ የአበርግሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አለሙ ክፍሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡መንግስታዊ የሆኑ እና ያልሆኑ ድርጅቶች የተለያዩ ድጋፎች እያደረጉ ቢሆንም ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ግን ለበርካታ ሰዎች ተደራሽ ለማድረግ እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡

በወረዳው በመድሀኒት እጥረት በረሀብ እና በጸጥታ ችግር ምክንያት ከ120 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የአበርግሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አለሙ ክፍሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡