YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ስድስት ቅርንጫፎች ሠራተኞች በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ስድስት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቅርንጫፍ ሠራተኞች በወንጀል ተጠርጥረው በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ዛሬ ሚያዚያ 20 ቀን 2014 ዓም በቁጥጥር ስር ውለው መታሰራቸው ታወቀ።

ቅርንጫፍ መስሪያቤቶቹ በአዳማ፣ነቀምት፣ ጅማ፣ጊምቢ፣በደሌ፣መቱ ሲሆኑ ሁሉም መታሸጋቸው ታውቋል።የቅርንጫፍ ሠራተኞቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና መታሰራቸውን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለሪፖርተር ያረጋገጠ ቢሆንም የታሰሩትን ሠራተኞች ብዛትና የታሰሩበትን ቦታ ከመግለጽ ተቆጥቧል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
በሃይማኖት ሽፋን ግጭት በመቀስቀስ ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ሃይሎችን ፍላጎት ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የፌደራል የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ!

ሚያዝያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ ከቀብር ስፍራ ጋር በተያያዘ በክርስትናና በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የተቀሰቀሰውን ግጭት መነሻ በማድረግ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎችም በሃይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ሃይሎችን ፍላጎት ለማሳካት በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የፌደራል የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቋል፡፡

የጋራ ግብረ ኃይሉ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ጸረ ኢትዮጵያ አቋም የሚያራምዱ የተለያዩ የውስጥና የውጭ ኃይሎች ብሔርን መሰረት ያደረገ የጥላቻ አጀንዳ በማሰራጨት ሃገሪቱን ወደ ቀውስ ለማስገባት ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡

ህብረተሰቡ ለአመታት በገነባው ጠንካራ የሆነ የጋራ እሴት ይህ ሙከራ የከሸፈባቸው ኃይሎች፣ቀሪውን የሃይማኖት ካርድ በመምዘዝ በተለያዩ እምነት ተከታዮች ዘንድ መጠራጠርና ጥላቻ እንዲፈጠር ብሎም ወደ ግጭት እንዲያመራ በተለያዩ መንገዶች ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል፡፡

በጎንደር የተከሰተው ግጭት በተለያዩ ዕምነቶች መካከል ግጭት በመቀስቀስ ወደ ሃገራዊ ቀውስ እንዲያመራ የሚደረገው ሴራ አካል መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ በዚህ ድርጊት በተሳተፉ አካላት ላይ ተገቢ እርምጃ መወሰደ መጀመሩን ጠቁሟል፡፡

በዚህ መሰረት በጎንደር በተከሰተው ግጭት የተሳተፉና ሁከቱን ለማባባስ የተንቀሳቀሱ 280 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን አመልክቷል፡፡

እንደ መግለጫው፤ በጎንደር የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በሌሎች አካባቢዎችም በተለያዩ እምነት ተከታዮች መካከል ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር የሚጋብዙ ቅስቀሳዎች እንዲሁም ሃሰተኛ መረጃዎችም በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎችም የእምነት ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ጥቃት በመፈጸም ግጭቱ ሃገራዊ ቅርጽ እንዲኖረው ሙከራ እየተደረገ ነው፡፡

የፌደራል የደህንትና የጸጥታ መዋቅር በድርጊቱ በሚሳተፉት ላይ ብቻ ሳይሆን ከኋላ በመሆን በሚዘውሩት ላይ በቂ መረጃና ማስረጃ ያለው በመሆኑ ተከታታይ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ያስታወቀው መግለጫው፤ ችግሩ ወደ ሌሎች አካባቢዎችም እንዲስፋፋ በየትኛውም የመገናኛ ዘዴ የሚቀሰቅሱ፤ በተለይም ደግሞ የማህበራዊ ትስስር ገፆችን በመጠቀም ሃሰተኛና የጥላቻ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት በህግ የሚጠየቁበት አግባብ መኖሩን የጠቆመው መግለጫው፤ በዚህ ህግወጥ ድርጊት የሚሳተፉ ባስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም በጥብቅ አሳስቧል፡፡

ኢትዮጵያውያን ለዓመታት የገነቡት በአብሮነትና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እኩይ ዓላማ ባነገቡ የውስጥና የውጭ ፀረ ሰላም ሃይሎች እኩይ ሴራ ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ አካላት በሚፈጥሩት የግጭት አጀንዳ አይሸረሸርም ያለው መግለጫው፤ ህብረተሰቡ ለዘመናት ባዳበራቸው መልካም እሴቶች እንደዚህ አይነት የፈተና ወቅቶችን በውይይትና በሰከነ መንፈስ በመፍታት እንደሚያስመሰክር የጋራ ግብረ ኃይሉ እምነት መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

ዛሬም ኢትዮጵያን ሌላ የግጭት አጀንዳ በመስጠት ለማተራመስ ሙከራ ቢደረግም በደኀንነትና በጸጥታ መዋቅሩ ከፍተኛ ጥረት በቁጥጥር ስር ውሏል ያለው የፌደራል የደህንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል፤ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሆን ችግሩ እንዳይስፋፋ ያደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመልክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የጎንደሩን ግድያ የፈፀመዉ ማን እንደሆነ እየተጣራ ነዉ!

የአማራ ክልል መንግስት የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ዛሬ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት የፀጥታ ኃይሉ አጥፊ ግለሰቦችንና ቡድኖችን እያደነ እንደሆነም ኃላፊ አመልክተዋል፡፡

ማክሰኞ ዕለት በጎንደር ከተማ በአንድ ታዋቂ አባት መቃብር ላይ የተፈጠረውን የህይወት ማጥፋት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት መውደምን ተከትሎ የነበረው አለመረጋጋት እየተሻሻለ መምጣቱን የአማራ ክልል መንግስት አስታውቋል።

በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፉ ወገኖች የቀብር ሥነ-ስርዓትም እየተከናወነ እንደሆነ ተመልክቷል።አንድ የዓይን እማኝ ዛሬ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቢከፈቱም አንዳንድ የንግድ ተቋማት እንደተዘጉ ናቸው ብለዋል፡፡የአማራ ክልል የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰሞኑን በጎንደር የተካሄደውን ግድያ አውግዟል፡፡

ማክሰኞ ዕለት በጎንደር ከተማ የአንድ ታላቅ አባት የቀብር ሥነ-ስርዓትን ተከትሎ በንፁሐን ላይ የሞት የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ተፈፅሟል፣ ያን ተከትሎ በከተማዋ አለመረጋጋት ሰፍኖ መቆየቱን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል መንግስት የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ዛሬ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ከሁለቱም የሐይማኖት አባቶች ጋር ውይይቶች ተካሂደው የቀብር ሥነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡የፀጥታ ኃይሉ አጥፊ ግለሰቦችንና ቡድኖችን እያደነ እንደሆነም ኃላፊ አመልክተዋል፡፡

የጉዳቱ መጠን ገና እየተጠና መሆኑን የተናገሩት አቶ ደሳለኝ ጉዳቱ ከሁለቱም ወገን ነው ብለዋል፡፡መንግስቱ የተባሉ የዓይን እማኝ በስልክ እንዳብራሩት ዛሬ በከተማዋ የተረጋጋ ሁኔታ ቢኖርም ሥራ ያልጀመሩ ሱቆችን ተመልክተዋል፡፡መሐመድ የተባሉ ሌላ የዓይን እማኝ “ቀብር አናስቀብርም” የሚል ጥያቄ ያነሱ ወገኖች እንደነበሩ ጠቁመው መጨረሻ ግን በተደረሰ ውይይት ቀብር ተፈፅሟል ነው ያሉት፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጎንደር ከተማ የተፈፀመው ድርጊት እንደሚያወግዘው የአማራ ክልል የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታወቋል፡፡ጉባዔው ትናንት ለአገር ውስጥ ብዙኃን መገናኛ ብቻ በሰጠው መግለጫ «በከተማዋ የተፈፀመው ድርጊት የማንንም ሐይማኖት አይወክልም ፣ የሐይማኖቶችን አስተምሮምሆነ እሴት ያልተከተለ ነው» ብሏል፡፡መንግስት አጥፊዎችን ተከታትሎ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርብ፣ ህዝቡም እንዲተባበር ነው የጉባዔው አባላት ያመለከቱት፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በነገው እለት በአዲስ አበባ ለሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር ፕሮግራም ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች

ሚያዚያ 21 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከቅዱስ ኡራኤል አካባቢ ጀምሮ እስከ መስቀል አደባባይ እና በዙሪያዋ የሚገኙ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል።
በዚህም መሰረት፦

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሀያ ሁለት ወይም ዘሪሁን ህንፃ አካባቢ ዝግ ይደረጋል፣
- ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ወሎ ሰፈር ኦሎምፒያ፤
- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች አጎና ሲኒማ፤
- ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ እና ከሜኪሲኮ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚጓዙ ሜክሲኮ አደባባይ፤
- ከጌጃ ሰፈርና ከጎማ ቁጠባ በሰንጋ ተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ የቀድሞው ደሳለኝ ሆቴል መስቀለኛ ላይ፤
- ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ለሚጓዙ ጎማ ቁጠባ ላይ እና ከሜክሲኮ ወደ ፖስታ ቤት ለሚሄዱ ሚትሮሎጂ አካባቢ እንዲሁም ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢሚግሬሽን ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በር አካባቢ፤
- ከተክለኃይማኖት በጎላ ሚካኤል ለሚመጡ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ላይ እና ከተክለኃይማኖት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ለሚመጡ ተክለኃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከተክለ ኃይማኖት በሶማሌ ተራ ወደ ባንኮ ዲሮማ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሸዋ ሱፐር ማርኬት ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል።
- ከቀድሞ አትክልት ተራ አካባቢ በአሮጌው ፖስታ ቤት ወደ ቸርችል ጎዳና የሚወስደው መንገድ አሮጌው ፖስታ ቤት፤
- ከደጎል አደባባይ ወደ እሪ በከንቱ ደጎል አደባባይ ላይ እና ከአራት ኪሎ በፓርላማ ወደ ውጭ ጉዳይ የሚወስደው መንገድ ሸራተን ሆቴል መውረጃ ላይ፤
- ከአራት ኪሎ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛ ላይ የሚዘጋ ሲሆን ከካዛንቺስ ሼል ወደ ፍል ውሀና ወደ ባምቢስ የሚወስዱት መንገዶች ካዛንስ ሼል ላይ ከቀኑ7፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጠር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል።

በተጨማሪም በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ሲሆን ህብረተሰቡ ፕሮግራሙ በሠላም ተጀምሮ በሠላም እንዲጠናቀቅና ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🥳መልካም የትንሳኤ በአል እያልን የበአል ልዩ ቅናሽ ይዘን መጥተናል🥳
https://tttttt.me/getitonlinee
የወንድም የሴትም
🎯ኦርጂናል ጥሩ ሽታ ያላቸው ሽቶዎች
🎯የስጦታ ጥቅሎች(package)🎁
🎯ኦርጂናል ሰአቶች
🎯 ቦርሳዎች እና የውበት መጠበቂያዎች
🎯 አልባሳት እና ጫማዎች

🎯ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ በ0929011031

🎯አድራሻ፣ ቦሌ መድሀኒያለም
ያሉበት ቦታ ድረስ በነጻ እናደርሳለን
የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ቤተሰብ ይሁኑ https://tttttt.me/getitonlinee
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
ትናንት የጀመረው የሲዳማ ብሔር አዲስ ዓመት መቀበያ (ፊቼ ጨምበላላ) በዓል በዛሬው ዕለትም በሀዋሳ ከተማ በድምቀት መከበሩን ቀጥሏል።

በዓሉ በትናትናው ዕለት በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የሲዳማ ባህል አዳራሽ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ ከፌዴራልና ከተለያዩ አከባቢዎች የተጋበዙ እንግዶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች በተገኙበት በድምቀት የተከበረ ሲሆን፤ የበዓሉ አካል የሆኑ የተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከናውበታል።

በዓሉ በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ከፍተኛ የክልል እና የፌዴራል ባለሥልጣናት የአገር ሽማግሌዎች ፣ አባገዳዎች፣ አደ ሲቂዎች እንዲሁም ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ከተለያዩ ዞኖች የመጡ ተወካዮች በተገኙበት በጉዱማሌ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅቦ በመከበር ላይ ነው።

ከንጋት ጀምሮ እየተከበረ በሚገኘው በዚህ በዓል ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የተገኙ የባህሉ ባለቤቶች በባህላዊ አልባሳት ደምቀው በቄጣላ ክዋኔና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች አጅበው በዓሉን እያከበሩ ይገኛሉ።

የሲዳማ ብሔር አዲስ ዓመት መቀበያ (ፊቼ ጨምበላላ) ልጅ አዋቂው የሚደሰትበት ባህላዊ ክዋኔዎች በስፋት የሚታዩበት ልዩ በዓል ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የዩክሬን ፕሬዝዳንት በአፍሪካ ህብረት ንግግር ለማድረግ በድጋሚ ጠየቁ!

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በአፍሪካ ህብረት ንግግር ለማድረግ በድጋሚ ጠየቁ፡፡ዜሌንስኪ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ዲሜትሮ ኩሌባ በኩል ነው ጥያቄውን በድጋሚ ያቀረቡት፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ከዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሜትሪ ኩሌባ ጋር በስልክ ማውራታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ለሙሳ ፋኪ የደወሉት ኩሌባ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ለአፍሪካ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች ንግግር ለማድረግ ከአሁን ቀደም ያነሱትን ጥያቄ ደግመው አንስተዋል፡፡ከህብረቱ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ለመመስረት እንፈልጋለን ስለማለታቸውም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

ሙሳ ፋኪ በበኩላቸው ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ለገባችበት ጦርነት ሰላማዊ መፍትሔዎች ሊፈለጉለት እንደሚገባ አስረግጠው መናገራቸውን ገልጸዋል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
ከጎንደር ከተማ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ቁጥራቸው ያልተገለፁ ሰዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መንግስት ገለፀ!

በጎንደር ከተማ ከግጭቱ መከሰት በኋላ የአማራ ክልል እና የፌደራል መንግስት የፀጥታ አካላት በሰሩት ስራ በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ሲል የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ።ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ በቁጥጥር ስር ስለዋሉት ተጠርጣሪዎች ብዛት “በርካታ” ከማለት ባለፈ ቁጥራዊ መረጃ አልገለፁም።

በጎንደር ከተማ ያለው አለመረጋጋት “በተወሰኑ ግለሰቦች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት” የተከሰተ ግጭት ነው ሲልም የመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ገለጿል።የፌደራል መንግስቱ አሁንም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ ይገኛል ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በጎንደር ከተማ የተከሰተውን ችግር “የተናበበ በሚመስል ሁኔታ” ወደተለያዩ አካባቢዎች በተለይም ወደ ወራቤ አካባቢ ለማስፋፋት የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚወገዝ ነው ሲል የመንግስት ኮምኒኬሽን መግለጫ አስታውቋል።

“የአማራ ክልል ነዋሪዎች ከሌሎች ህዝቦች ጋር ግጭት ውስጥ እንዲገባ አልመው የሚሰሩ ፅንፈናኛ እና አክራሪ የፖለቲካ ልሂቃን እና የማህበረሰብ አንቂዎች ሚና አላቸው። ክልሉን የህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር መናኸሪያ ለማድረግ ሆን ብለው የሚሰሩም አሉ” ያለው መግለጫው እነዚህ ኃይሎች የተሰጣቸውን የመጨረሻ የእርምት እድል ተሰጥቷቸዋል ብሏል።

[@AddisZeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በጎንደር በተከሰተው የፀጥታ ችግር ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ 373 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል - የአማራ ክልል ሰላም ግንባታ እና የሕዝብ ደህንነት ቢሮ

በጎንደር በተከሰተው የፀጥታ ችግር ከፍተኛ ሚና የነበራቸው 373 ግለሰቦች በፀጥታ መዋቅሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአማራ ክልል ሰላም ግንባታ እና የሕዝብ ደህንነት ቢሮ አስታወቀ።

ግለሰቦቹ በቡድን በመንቀሳቀስ ለዝርፊያ እና ለቃጠሎ ተሰማርተው በመገኘት እና የግጭቱ ፊትአውራሪ በመሆን ለተፈጠረው ግጭት ምክንያት መሆናቸውን የቢሮው ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ገልጸዋል።

[AMC]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በስልጤ ዞን በቤተክርስቲያናት እና በቤተአምልኮዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት ጉባኤው አወገዘ!

መንግስት ሕግና ስርአትን ለማስፈፀም ቀደም ብሎ ያወጣቸውን ህጎችን ሁሉ ተፈፃሚ ሊያደርግ ብሏል የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናት እና በፕሮቴስታንት ቤተ አምልኮዎች ላይ ተፈጽሟል ያለውን የወንጅል ድርጊት አውግዟል፡፡

ጉባኤው ወንጀልን በሌላ ወንጀል ለማረም መሞከር ሕገ ወጥነት ብሏል፡፡ተግባሩ በየትኛውም ሃይማኖት ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑም በላይ ደረቅ ወንጀልና በህግ ሊያስጠይቅ የሚገባው ተግባር ነው ብሎ በጽኑ ያምናልም ብሏል ጉባኤው፡፡

ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ የተፈፀመወን አስነዋሪ ተግባርን አስመልክቶ ተግባሩን የሚያወግዝ መግለጫ መውጣቱን ያስታወሰው ጉበኤው፤ ትናንት በወራቤ በሆነው እጅጉን እንዳዘነም ገልጿል፡፡

“ሁሉም ሃይማኖቶች ሰላምን የሚሰብኩ፣ ትህትናን የሚስተምሩና ለሌሎች ስለመኖርና መስዋዕት ስለመክፈል የሚገዳቸው እንደሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም በሃይማኖት ስምና ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሚፈፀመው ሁሉ ሕገ ወጥና ደረቅ ወንጀል እንደሆነ ታውቆ መንግስት ሕግና ስርኣትን እንዲያስጠበቅ ጉባኤያችን አበክሮ ይጠይቃል”ም ብለዋል ጉባኤው፡፡መንግስት ሕግና ስርአትን ለማስፈፀም እንዲችል ቀደም ብሎ ያወጣቸውን ህጎችን ሁሉ ተፈፃሚ ሊያደርግ ይገባል ሲልም አክሏል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
Forwarded from YeneTube
**ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦች

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-

- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።


አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ0917040506
0912718883
ይደውሉ።

መሪጌታ ጥበቡ ባህላዊ መድሀኒት መስጫ

ለጤናወ መፍትሄ👇

https://tttttt.me/meritibe
ላልተወሰነ ጊዜ አዲስ መታወቂያ መስጠት ማቆሙን የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ አስታወቀ!

ላልተወሰነ ጊዜ አዲስ መታወቂያ የመስጠት አገልግሎት ማቆሙን የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ የመታወቂያ፣ የልደት፣ የጋብቻ እና የሞት ማስረጃዎችን ይመዘግባል፤ ዜጎች በሚፈልጉበት ወቅትም አገልግሎቱን ይሰጣል፡፡

በአገልግሎት አሰጣቱ ውስጥ በተለይም የመታወቂያ አገልግሎቱ ላይ በተቋሙ ውስጥ እና ከተቋሙ ውጭ ባሉ ሃሰተኛ ማስረጃን በሚያድሉ ግለሰቦች የተነሳ ለማይገባቸው ሰዎች መታወቂያ አላግግባብ እየተሰጠ መሆኑን የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክትር ዶክተር ታከለ ነጫ ገልጸዋል፡፡

ህገ ወጥ ድርጊቱን ሲፈጽሙ የተያዙ ግለሰቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡የነዋሪነት መታወቂያ ለማግኘት ሲባል ህገወጥነት እየተባባሰ በመምጣቱ ችግሩን በሚገባ ለማጥራት እንዲቻል በከተማ አስተዳደሩ ደረጃ በተላለፈ ውሳኔ መሰረት አዲስ መታወቂያ እንዳይሰጥ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱን ዋና ዳይሬክተሩ ዶክተር ታከለ ገልጸዋል፡፡

አገልግሎቱ ላልተወሰነ ጊዜ ታግዶ የሚቆይ መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሪክተሩ፤ በህወጥ ድርጊቱ ውስጥ የተሳተፉ አካላትን ወደ ህግ የማቅረብ እና ተቋሙ ውስጥ ያሉ ህገ-ወጥነቶችን የማጥራት ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡የመታወቂያ እድሳትም ሆነ ሌሎች የወሳኝ ኩነት አገልግሎቶች ባሉበት ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ዛሬ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው!

በአዲስ አበባ ዛሬ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው። የአዲስ አበባን የአውራ ጎዳና መንገዶችን ተከትሎ እየተካሄደ ባለው የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተሳተፉበት ነው።

የተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ታላላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር ሲያዘጋጁ ቆይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ኢድን በአገር ቤት እናክብር በማለት “ታላቁ የኢድ ሰላት በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወዳጆች ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ የገቡ እንግዶችም በዛሬው የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ እየተሳተፉ መሆኑም ተገልጿል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን የምርመራ ጋዜጠኝነትን በሥርዓት የሚመራ መመሪያ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት እንደተናገረ የዋዜማ ሪፖርተር ዘግቧል።

የምርመራ ጋዜጠኝነት በስነ ምግባር ካልተመራ፣ ማኅበራዊ ፍትህን በማስፈን ፋንታ የግለሰብ ጥቅሞች አስከባሪ እንደሚሆን ባለሥልጣኑ ተናግሯል። መመሪያውን የሚያዘጋጀው ከባለሥልጣኑ፣ ከስነ ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን እና ከእንባ ጠባቂ ተቋም የተውጣጣ ኮሚቴ ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን በቅርቡ የምርመራ ጋዜጠኝነት እንደሚጀምሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረው ነበር።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
የሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር አሰራጭተዋል የተባሉ ስድስት መገናኛ ብዙኃን በፌደራል ፖሊስ ምርመራ ሊደረግባቸው ነው!

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር አሰራጭተዋል ባላቸው ስድስት መገናኛ ብዙኃን ላይ ምርመራ እንዲካሄድባቸው ሰነዶች አደራጅቶ ለፌደራል ፖሊስ መላኩን አስታወቀ። ባለሥልጣኑ ምዝገባ ሳያከናውኑ በበይነ መረብ አማካኝነት በህገወጥ መልክ የሚዲያ ስርጭት ላይ የተሰማሩ 25 ድርጅቶችን በህግ ተጠያቂ የማድረግ ሂደት መጀመሩንም ገልጿል።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ይህን ያስታወቀው ዛሬ አርብ ሚያዝያ 21፤ 2014 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለህግ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ነው። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ለቋሚ ኮሚቴው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ እንዳሉት፤ መስሪያ ቤታቸው ባለፈው ዘጠኝ ወር ባከናወነው የሞኒተሪንግ ስራ በስድስት መገናኛ ብዙሃን በተሰራጩ 10 ፕሮግራሞች ላይ የህግ ጥሰቶች ተስተውለዋል።

“ከሐሰተኛ [መረጃ] እና ጥላቻ [ንግግር] ጋር ተያይዞ አስር ፕሮግራሞች ላይ የህግ ጥሰት በመስተዋሉ ፋይሉን አደራጅተን ለህግ አስፈጻሚ አካላት፣ ለፌደራል ፖሊስ ጥቆማ አቅርበናል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የህግ አስፈጻሚ አካላት በሚያደርጓቸው ምርመራዎች ላይ የተቋሙን ሙያዊ ድጋፍ በሚፈልጉበት [ጊዜ] ሁሉንም የጠየቁትን ጥያቄ በህጉ እና በህጉ ብቻ መሰረት አድርገን ሙያዊ ድጋፍ ሰጥተናል” ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ አስረድተዋል።

አቶ መሐመድ የመገናኛ ብዙኃኑን ማንነት በስም ከመጥቀስ ቢቆጠቡም፤ በንግድ መገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የተሰማሩ እንደሆኑ ግን በሪፖርታቸው ላይ አመልክተዋል። እነዚህ መገናኛ ብዙኃን “ሚዛናዊነት የጎደላቸው እና የአንድ ወገን ሀሳብና ፍላጎትን የሚያንጸባርቁ አድሏዊ ዘገባዎችን በማቅረብ” የህግ ጥሰቶችን መፈጸማቸውንም ጠቁመዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa