YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን በተመለከተ ተጨማሪ ሰነዶች እና መረጃዎችን እንዲያቀርብ ምርጫ ቦርድ ጠየቀ!

ብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን በተመለከተ ተጨማሪ ሰነዶች እና መረጃዎችን እንዲያቀርብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠይቋል።ቦርዱ ሚያዝያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ፓርቲው ያቀረባቸውን የጠቅላላ ጉባኤ ሰነዶች እና ጠቅላላ ጉባኤውን በታዘቡት የቦርዱ ተወካዮች የቀረበውን ሪፖርት መመርመሩን አስታውቋል።ይሁንና የጠቅላላ ጉባኤውን ሂደት፣ በጉባኤው የተላለፉ ውሳኔዎች እና የተደረጉ ምርጫዎችን በተመለከተ ከሕጉ አንጻር ለወሰን ተጨማሪ ሰነዶች እና መረጃዎችን ማየት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁሟል።

በሆኑም ፓርቲው ምርጫ ቦርድ በዝርዝር ያስቀመጣቸውን ጉዳዮች ከሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በፊት ለቦርዱ እንዲያቀርብ አሳውቋል።ቃለ ጉባኤን በተመለከተ፣ በጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤው ላይ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባው ምልአተ ጉባኤ ተሟልቷል ቢባልም በግልፅ የጠቅላላ ባኤው ተሳታፊ አባላት ብዛት ስላልተቀመጠ ተገልፆ እንዲቀርብ፤ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የተጠቆሙበት ሂደት፣ እነማን እንደተጠቆሙ፣ ከተጠቆሙት ውስጥ የተመረጡት አባላት እያንዳንዳቸው በስንት ድምፅ እንደተመረጡ በጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ውስጥ ያልተገለፀ በመሆኑ ይሄው ተካትቶ እና ተረጋግጦ እንዲቀርብ፤ በፓርቲው የቀረበው ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ በፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተፈርሞ እንዲቀርብ፤ የማዕከላዊ ኮሚቴው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን የመረጠበትን ሂደትየሚያሳይ የማዕከላዊ ኮሚቴ ቃለ ጉባኤ ስላልቀረበ እንዲቀርብ ጠይቋል።

የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብን በተመለከተ ደግሞ በመተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 18/3 መሠረት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ብዛት እና ስብጥርን በተለከተ የወጣ የአፈፃፀም መመሪያ ካለ የመመሪያውን ኮፒ ማዕከላዊ ኮሚቴው መመሪያውን ካፀደቀበት ቃለ ጉባኤ ጭምር እንዲቀርብ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሴንትራል አፍሪካን ሪፐብሊክ ቢትኮይንን ህጋዊ ምንዛሪ አድርጋ ለመጠቀም መወሰኗን የሀገሪቱን የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ጠቅሶ ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
"የተፈጠረው የፀጥታ ችግር አሳዛኝና የከተማዋን ሕዝብ አብሮነት ታሪክ የማይገልፅ ነው" የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር)

በጎንደር ከተማ ትናንት የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር አስመልክቶ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር) ውይይቱ ችግሩን በሰከነ መንገድ ለመፍታት ያለመ ነው ብለዋል።

ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ "ትናንት የተፈጠረው የፀጥታ ችግር አሳዛኝና የከተማዋን ሕዝብ አብሮነት ታሪክ የማይገልፅ ነው" ብለዋል።የፀጥታ ችግር የፈጠሩ አካላትን በመለየት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የክልሉ መንግሥት ከከተማው ነዋሪዎች ጋር በጋራ እንደሚሠራም ገልጸዋል። ነዋሪዎች ለከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቃሴ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልክት አስተላልፈዋል።

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው የተፈጠረው ችግር ለጠላት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመኾኑ ችግሩን በውይይት ለመፍታት ሕዝቡ ባለቤት መኾን አለበት ብለዋል። በየደረጃው ያለው የመንግሥት መዋቅርም ያሉትን ክፍተቶች ለማስተካከል ጠንካራ ሥራ ይሠራል ብለዋል።የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎችም ከመንግሥት ጋር በመኾን እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ ችግሩን ለመፍታት በስክነት መወያዬት ይገባል ብለዋል።የውይይቱ ተሳታፊዎችም የቆየውን አብሮነት ለመሸርሸር የሚሠሩ አካላትን ተከታትሎ በቁጥጥር ሥር በማዋል ሕግ የማስከበር ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

[AMC]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ሁለት ም/ዋና ዳይሬክተሮችን ሾመዋል።

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ሁለት ም/ዋና ዳይሬክተሮችን ሾመዋል፡፡ በዚህም መሰረት አቶ ዳንኤል ጉታ እና አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ ከሚያዚያ 17/2014 ዓ/ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች በመሆን ተሹመዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
**ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦች

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-

- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።


አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ0917040506
0912718883
ይደውሉ።

መሪጌታ ጥበቡ ባህላዊ መድሀኒት መስጫ

ለጤናወ መፍትሄ👇

https://tttttt.me/meritibe
ህወሓት ከተቆጣጠራቸው የአፋር ክልል ወረዳዎች “ሙሉ በሙሉ ወጥቻለሁ” ማለቱ ውሸት ነው ሲል የአፋር ክልል ገለጸ!

የህወሓት ሃይሎች ከጎረቤት አፋር ክልል ሙሉ በሙሉ መውጣታቸውን ሮይተርስ የህወሓትን ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳን ጠቅሶ ከሁለት ቀናት በፊት መዘገቡ ይታወሳል፡፡አቶ ጌታቸው ከአፋር ክልል መውጣት ማለት በጣም አስፈላጊ የሆኑ የምግብ እርዳታ በርሃብ ውስጥ ላለችው ትግራይ ይደርሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡

ነገርግን የአፋር ክልል መንግስት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የህወሓት ኃይሎች ከያዟቸው የአፋር ክልል ቦታዎች አለመውጣታቸውን አስታውቋል፡፡“አሸባሪው ህወሀት በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ከወረራቸው በአፋር ክልል የኪልበቲ ረሱ ዞን ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ ወጥቻለሁ በማለት ከሰሞኑ ከእውነት የራቀ የሀሰት የማደናገሪያ ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት ላይ ይገኛል።” ብሏል የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
በሐረሬ ክልል ሐረር ከተማ ዕሁድ'ለት ከፈነዳው ቦምብ ጋር በተያያዘ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ የክልሉ ፖሊስ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሆቴል ውስጥ በፈነዳው ቦምብ ሌሎች 8 ሰዎች ቆስለዋል ተብሏል። ለቦምብ ጥቃቱ ሃላፊነት የወሰደ አካል የለም። የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት ተቋም ግን ከጥቃቱ ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ፣ በአዲስ አበባ እና ሌሎች ቦታዎች የሽብር ጥቃት ሲያሴሩ የነበሩ 34 የአልሸባብ አባላትን በቁጥጥር ስር አውያለሁ ብሎ ነበር።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ አፋር ክልል የተጣሉ ፈንጂዎች በሚገርም ሁኔታ ህጻናትን አካል ጉዳተኛ እያደረጉ ወይም እየገደሉ እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች ለሮይተርስ ተናገሩ።

እንደ ባለሙያዎቹ ገለፃ በሳምንት 25 ያህል የተጎዱ ህፃናት ወደ ሆስፒታል ይመጣሉ። አንዳንድ ህፃናቱ ታካሚዎች ከመሬት ላይ የእጅ ቦምቦቹን እንዳነሱ ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ የተቀበሩ ፈንጂዎችን መርገጣቸውን ተናግረዋል። ካሳጊታ የሚባለው አካባቢ ነዋሪዎች ለዜና ምንጩ እንደገለፁትም ባለው ሁኔታ ምክንያት ከምንጭ ውኃ ለማምጣት ወይም ወደ እርሻ ቦታዎች መሄድ አስግቶዋቸዋል።

በአጭር ጊዜ በአፋር ክልል እንደዚህ አይነት ተመሳሳይ ጉዳቶች የደረሰበት ምክንያት አልተገለፀም። ይሁንና በትግራይ ክልል በጀመረው እና ወደ አማራ እና አፋር ክልል የተስፋፋው የሀገሪቱ ጦርነት በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል። ሚሊዮኖችን ከቀያቸው አፈናቅሏል። በፈንጁ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ጎልማሶች እንዳሉ ነገርግን አብዛኞቹ ተጠቂዎች ምን እንደሆነ የማያውቁ ህፃናት እንደሆኑ የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል። የህክምና ባለሙያዎቹ በጠቅላላ ምን ያህል ሰዎች በፈንጅ ጥቃት በሆስፒታል እንደታከሙ ቁጥር ባይጠሩም በታህሳስ እና የካቲት መካከል በአፋር ትልቁ፣ የዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል፣ በሳምንት 25 የሚጠጉ ተጎጂዎች ይገጥሙት እንደነበር ታመር ኢብራሂም የተባሉ የቀዶ ህክምና ክፍል ዋና ነርስ ለሮይተርስ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሊያ ታደሰ ለሮይተርስ እንደተናገሩት፤በአፋርም ሆነ በሌሎች ክልሎች በፈንጂ ምክንያት ተጎጂ እየሆኑ ስላሉ ሕፃናት የሚያውቁት ክስተት የለም። ሮይተርስ ዜና ምንጭ ምን አይነት ፈንጂዎች ጉዳቱን እንዳደረሱ ማረጋገጥ እንዳልቻለ ዘግቧል። የህውኃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ሃይሎች ምንም አይነት የተቀበሩ ፈንጂዎችን አልተውም ብለዋል።ተጠያቂ ነው ብለው የጠቀሱትም አካል የለም።ሮይተርስ ከፌዴራል መንግስት የሰብአዊ እርዳታ ቢሮ እና ከጦሩ ቃል አቀባይ ለጥያቄዎቹ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሰካቱንም አክሎ ዘግቧል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🥳መልካም የትንሳኤ በአል እያልን የበአል ልዩ ቅናሽ ይዘን መጥተናል🥳
https://tttttt.me/getitonlinee
የወንድም የሴትም
🎯ኦርጂናል ጥሩ ሽታ ያላቸው ሽቶዎች
🎯የስጦታ ጥቅሎች(package)🎁
🎯ኦርጂናል ሰአቶች
🎯 ቦርሳዎች እና የውበት መጠበቂያዎች
🎯 አልባሳት እና ጫማዎች

🎯ለተጨማሪ መረጃ ይደውሉ በ0929011031

🎯አድራሻ፣ ቦሌ መድሀኒያለም
ያሉበት ቦታ ድረስ በነጻ እናደርሳለን
የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ቤተሰብ ይሁኑ https://tttttt.me/getitonlinee
👍1
Forwarded from YeneTube
አስደሳች ዜና 12ኛ ክፍል ለጨረሳቹ እና በመማር ላይ ላላቹ!!!

ማራኪ አማካሪ በ ካናዳ 🇨🇦 አሜሪካ 🇺🇸 እና ፖላንድ 🇵🇱 የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የምትችሉበትን ዕድል አዘጋጅቶ በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዛሬዉኑ ያለ ቅድመ ክፍያ ይመዝገቡ!

በቡድን ለሚመዘገቡ ቅናሽ አዘጋጅተናል

የተማሪዎቻችንን ምስክርነት ለመመልከት የ ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
@marakiconsultancy

አድራሻ: ቦሌ ሸዋ ዳቦ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222
0118345171

ለበለጠ መረጃ @marakiapplication
ከትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈናቀሉ ተማሪዎች ዲግሪ እንደማይሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ!

ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ተፈናቅለው በአደራ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተምረው ለተመረቁ ተማሪዎች፣ መደበኛ ዲግሪ ሚኒስቴሩ ለመስጠት እንደሚቸገር ተገለጸ፡፡ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ሚኒስቴር ዋስትና ገብተው የተመረቁ ከትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች የተፈናቀሉ ከ4,000 በላይ ተማሪዎች መደበኛ ዲግሪ ስለተከለከልን ሥራ ለመቀጠርና ለመወዳዳር አልቻልንም ሲሉ ለሪፖርተር ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡

የእነዚሁ የተማሪዎች ቅሬታ የቀረበላቸው ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ (ፕሮፌሰር) እንደተናገሩት፣ ‹‹የተማሪዎቹ ሙሉ መረጃ ሳይገኝ መደበኛ ዲግሪ ለመስጠት እንቸገራለን፡፡ ጦርነቱ ሲቆምና ሰላምና መረጋጋት በሰሜን ኢትዮጵያ በአስተማማኝ ሁኔታ ሲሰፍን ከመጡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ያቆሙበት መረጃ ተሟልቶ ሲቀርብ ዲግሪው ይሰጣቸዋል፡፡ እስከዚያው ግን በተሰጣቸው ውጤታቸውን በሚገልጽ ሰርተፊኬት ሥራ መፈለግ ይችላሉ፤›› ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህን ቢሉም ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች በጦርነት ሳቢያ ተፈናቅለው ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለመመረቅ የተገደዱ ተማሪዎች ግን፣ ትምህርት ሚኒስቴር በአንድ ሴሚስተር የውጤት መግለጫ ወረቀት (በግሬድ ሪፖርት) አሰናብቶናል ሲሉ ቅሬታ ያሰማሉ፡፡ ይህ ወረቀት ደግሞ በሥራ ዓለም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠር እንደማያስችላቸው በመጥቀስ፣ ትምህርት ሚኒስቴር ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈልግላቸው እየጠየቁ ነው፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ግን አሁን ካደረኩት የተለየ አማራጭ የለኝም የሚል ምላሽ ነው የሰጠው፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ: http://bit.ly/36ZDgNi

@YeneTube @FikerAssefa
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰቡ!

ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ አካላት ከድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ አሳሰቡ።

1 ሺህ 443ኛውን የኢድ በአልና ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ፤ ያልተረጋገጠ ወሬ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ጉዳይ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ከሰሞኑ በተከሰተው ግጭት አሳዛኝ ድርጊት መፈጸሙ የሚወገዝ እና የትኛውንም ሃይማኖት የማይወክል እንደሆነ ገልጸዋል።

ለህዝቡ ቅርብ የሆኑና ተሰሚነት ያላቸው አካላት ግጭት አባባሽ መልእክቶችን በማሰራጨት እልቂት እንዲፈጠር እየሠሩ እንደሚገኙ አመልክተው፤ ህዝቡ የተነገረው ሁሉ አምኖ መቀበል ብቻ ሳይሆን መርምሮ ማረጋገጥ እንዳለበት አስረድተዋል።

ግጭቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያሉ የፀጥታ አካላት እና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ሀላፊነታቸውን መወጣት ላይ ክፍተት እንዳሉባቸው ገልፀው፤ ችግሩ ከዚህ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በቁርጠኝነት እንዲሰሩ አፅንኦት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኮሚቴ በማቋቋም እና ቦታው ድረስ በማቅናት ችግሩን ለመፍታት ጥረት ይደረጋል ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ለፊቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ የተነሳ በአራት ክፍለ ከተሞች የውሃ አቅርቦት ተቋርጧል!

በአዲስ አበባ ከተማ በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ የተነሳ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ 12 ወረዳዎች ፣በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 10 ወረዳዎች ፣በቦሌ ክፍለ ከተማ 3 ወረዳዎች እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 5 ወረዳዎች የሚገኙ ደንበኞች ከእሁድ እለት ጀምሮ ውሃ በበቂ ሁኔታ እያገኙ አለመሆኑን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው በተለይ ለብስራ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ የተነሳ ከዚህ ቀደም ውሃ በፈረቃ ያገኙ ለነበሩ አካባቢዎች አገልግሎቱን መስጠት መቸገራቸውን ያነሱት ዳይሬክተሯ በተለይ ውሃ በሳምንት አንዴ ያገኙ የነበሩ አካባቢዎች ላይ ችግሩ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ገልፀዋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግሩን ለመፍታት ከአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመናበብ በመስራት ላይ መሆናቸውን የሚናገሩት ዳይሬክተሯ በተለይ ከእሁድ ጀምሮ እስከ ድርብ ድረስ ባሉት ቀናት በርካታ ምሶሶዎች መውደቃቸውን ተከትሎ እና መሬት ውስጥ የነበረ ኬብል በመፈንዳቱ ዳግም የመጠገን ስራዎች ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አሁን ላይ የፈረቃ ሂደቱ በመዛባቱ ባለስልጣኑ ባሉት ቦቲ ተሸከርካሪዎች ውሃ ለማዳረስ እየሰራ ሲሆን ችግሩን በአፋጣኝ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል። የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ የተፈጠረው በቴክኒክ ችግር ምክንያት መሆኑን ለብስራት ሬዲዮ ያስረዱት በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ ሲሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa
የወልዲያ ከተማ አስተዳዳር ‹‹ሰርጎ ገቦች››ን ለመለየት የነዋሪዎችን መታወቂያ ሊቀይር ነው!

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር በከተማው ውስጥ የሚገኙ ‹‹ሰርጎ ገቦችን›› ለመለየት እንዲቻል፣ የከተማዋ ነዋሪዎችን በሙሉ መታወቂያ ሊቀር እንደሆነ አስታወቀ፡፡በከተማው ውስጥ ካለው ሁኔታ አንፃር እየተለዩ የሚታሰሩ ግለሰቦች እንዳሉ የገለጸው የከተማ አስተዳደሩ፣ አዲስ መታወቂያ የሚወስዱ ሰዎች ያላቸውን መታወቂያ ከከተማዋ ወሳኝ ኩነት መረጃ ጋር እንደሚያመሳክር ገልጿል፡፡

ለወራት በሕወሓት ቁጥጥር ሥር ከቆየች በኋላ በታኅሳስ ወር ላይ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሆነችው ወልዲያ፣ ‹‹ሰርጎ ገቦች›› የቀድሞውን መታወቂያ መያዛቸውን ለሪፖርተር የተናገሩት የወልድያ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ዳዊት መሰለ (ዶ/ር)፣ በዚህም ምክንያት የከተማው አስተደዳር የከተማዋን ነዋሪዎች መታወቂያ ለመቀየር ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጸዋል፡፡

እንደ ዳዊት (ዶ/ር) ገለጻ፣ ከዚህ ቀደም መታወቂያ ሲሰጥ የነበረው መረጃዎችን በመዝገብ ላይ በመጻፍ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ ይህም በቀበሌዎች መካከል የሚጣራበት ሁኔታ እንዳይኖር በማድረጉ የተለያዩ ቀበሌዎች ላይ ከአንድ በላይ መታወቂያ ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡

‹‹ሰርጎ ገብ›› የተባሉትን ሰዎች ማንነት አብራርተው ባይገልጹም፣ የከተማዋ ነዋሪዎች መታወቂያ እንዲይዙ የሚያደርጉ የቀበሌ አመራሮች አሉ የሚል ጥርጣሬ እንዳለ አስረድተዋል፡፡ አሁን መታወቂያ የማደስ አገልግሎት እንዲቆም መደረጉን አክለዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
የኩፍኝ፣ ፖሊዮና ቢጫ ወባ ወረርሽኝን ለመከላከል ያለመ የክትባት ሣምንት ሊካሄድ ነው!

የኩፍኝ፣ ፖሊዮና ቢጫ ወባ ወረርሽኝን ለመከላከል ያለመ የክትባት ሣምንት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ሊካሄድ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ በሰጡት መግለጫ ÷ የአፍሪካ የክትባት ሣምንትን ምክንያት በማድረግ የሚከናወነው የክትባት ዘመቻው በተለይም በጸጥታ ችግር ምክንያት ክትባት ባልተሰጠባቸው ቦታዎች ይሰጣል ብለዋል፡፡

የክትባት ሣምንቱ ማህበረሰቡ በክትባት ጠቀሜታ ላይ ትክክለኛውን ግንዛቤ እንዲጨብጥ ለማድረግና የክትባት ተደራሽነትን ለማስፋት መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
የክትባት ዘመቻው ዓላማ በወረርሽኝ ደረጃ ሊነሱ ይችላሉ ተብሎ የተሰጉትን ኩፍኝ፣ ፖሊዮ እና ቢጫ ወባን ለመከላከል መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ደረጄ፤ ይህም ተፈናቃይ ዜጎች ባሉባቸው አካባቢዎች በስፋት የሚሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

ከወረርሽኝ መከላከል ባለፈ ለሕጻናት የአንጀት ተወሃሲያን መከላከያ፣ ቫይታሚን ኤ እና በምግብ እጥረት የተጎዱ ሕጻናትን በመለየት ሕክምና እንደሚሰጥ መናገራቸዉን የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል መንግሥት ሽብር በሚፈጠሩ አካላት የማያዳግም እርምጃ እወስዳለው አለ!

የአማራ ክልል መንግሥት በጎንደር ከተማ በተፈጠረው ግጭት ተገቢውን ክትትል አድርጎ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።የአማራ ክልል ርዕሠ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ፤ እንደ ሀገር ከገጠሙን ችግሮች ሙሉ በሙሉ ሳንላቀቅ ሃይማኖትን ምክንያት በማድረግ የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር የሚታትሩ እኩይ አካላትን እንደማይታገሱ ተናግረዋል።

ርዕሠ መሥተዳድሩ "ክልሉን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ የሽብር ድርጊት በሚፈጠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን" ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡ይህ ሙከራ ኢትዮጵያን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ ለባሰ ቀውስ የሚዳርግ በመሆኑ ድርጊቱ ሊወገዝ ይገባዋል ያሉት ርዕሠ መሥተዳድሩ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ለሰላም ዘብ እንዲቆሙም አሳስበዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
**ጤና ይስጥልን የተወደዳችሁ ቤተሰቦች

መሪጌታ ጥበቡ የባህል ህክምና መስጫ ከአባቶቻችን በተሰጠንና ባገኘነው ጥበብ መሰረት የተለያዩ የጤና መፍትሄወችን እንሰጣለን።**

የምንሰጣቸው አገልግሎቶችም:-

- የኪንታሮት መድሀኒት በሚቀባ ታማሚው ወደቤቱ ወስዶ ሌላ ገላ ሳይነካ በመቀባት ሳያቆስል ስራወትን ሳያስተጓጉል በሽታውን ለይቶ በማውጣት ሁለተኛም እንዳይተካ አድርጎ ይፈውሳል።
-የሪህ መድሀኒት ወስዶ በመቀባት ዘላቂ ፈውስ ይሰጣል።
- የአስም
_ የስንፈተ ወሲብ
_የአይነጥላ
_የገርጋሪ
_ለመፍትሄ ስራይ
እነዚህንና ሌሎችን አገልግሎቶችን እንሰጣለን
በሁሉም አገልግሎቶቻችን ውጤቱን እንዳዩ ክፍያ ይፈፅማሉ።
የሚፈልጉትን መድሀኒት ያሉበት ቦታ መላላክ ይቻላል።


አድርሻ:-
ባህር ዳር:- ቀበሌ 11
ለበለጠ መረጃ:-በ0917040506
0912718883
ይደውሉ።

መሪጌታ ጥበቡ ባህላዊ መድሀኒት መስጫ

ለጤናወ መፍትሄ👇

https://tttttt.me/meritibe
ሀይማኖትን ሽፋን አድርገው የሚነሱ ግጭቶች በቂ ትኩረት ይሻሉ ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ አሰሰበ።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ከሰሞኑ ጎንደር ላይ የተፈጠረውን ያወገዘ ሲሆን በዚው ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል:: ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማኅበር መንግሥት የሸቀጥ አቅርቦት እና ዋጋ ንርትን የሚያረጋጋ ጊዜያዊ ቦርድ እንዲያቋቁም ጠይቋል።

ማኅበሩን ጥያቄውን ያቀረበው፣ በዋጋ ግሽበት መዋቅራዊ ተግዳሮቶች እና የፖሊሲ አማራጮች ላይ ለ6 ወራት ያስጠናውን ጥናት ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው። ቦርዱ ቢቋቋም፣ የአገራዊ ምርትና የገቢ ንግድ አቅርቦት ሚዛንን ማስጠበቅ፣ የዋጋ ግሽበትን የሚቀንስ ግብ ማስቀመጥ፣ በግሽበቱ የሚጎዱ የኅብረተሰብ ክፍሎችን መለየት እና በተለያዩ ኢኮኖሚ ዘርፎች መካከል ቅንጅት ለመፍጠር ይችላል ተብሏል።

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa