YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ሰብስቤ ዋሻ በሚባል አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉን ኦቢኤን ዘግቧል።አደጋው የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሮቤ ከተማ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ በስፍራው በመገልበጡ የደረሰ ነዉ።

@YeneTube @FikerAssefa
የመርከቦች የወደብ ቆይታ ከ12 ቀናት ወደ 9 ቀናት መቀነሱ ተገለጸ!

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የመርከብቦችን የወደብ ቆይታ ከነበረበት 12 ቀናት ወደ 9 ቀናት ለመቀመስ መቻሉን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሰታወቀ።

በሎጂስቲክሰ ዘርፍ ባለፉት 9 ወራት የመርከብቦችን የወደብ ቆይታ ከነበረበት 12 ቀናት ወደ 9 ቀናት መቀነስ መቻሉን የኢፌዴሪ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከሚኒስቴሩ ያገኘነዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ምርቶችን በኮንቴነር አሽጎ ከመላክ አንጻር አፈፃፀሙን በማሻሻል ድርሻዉን ወደ 62 ነጥብ 5 በመቶ ማድረስ መቻሉ ፤ እንዲሁም አንድ ነጥብ 34 ሚሊየን ቶን ካርጎ በባቡር ማጓጓዝ መቻሉን ተችሏል፡፡

በአቪየሽን ዘርፍ ለማሳካት የታቀደዉን የብቃት ማረጋገጫ የመስጠት አገልግሎት ማሳካት የተቻለ ሲሆን የበረራ ደህንነትን ከአለም አቀፍ ደረጃ አንጻር ማስጠበቅ ተችሏል፡፡ የፐብሊክ ሰርቪስ የትራንስፖር አገልግሎት ለአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች የሚሰጠዉን አገልግሎት በተጠናከረ መልኩ በማከናወን እንደሚገኝም ተመልክቷል፡፡ በዘርፉ ለ71 ሺህ 300 ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ62 ሺህ 420 ጎጎች የስራ እድል ተፈጥሯል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ጥቃት መፈጸሙን ተመድ አስታወቀ!

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ዳባት ከተማ በሚገኘው የኤርትራውያን ስደተኞች መጠለያ በታጣቂዎች ጥቃት እንደደረሰበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገለፀ።የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) በምስራቅ አፍሪካ እና በግሬት ሌክስ የስደተኞች ተጠሪ ቃል አቀባይ ፌይዝ ኪሲንጋ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ምሽት ታጣቂዎቹ አዲስ በተከፈተው መጠለያ በመግባት በፈፀሙት ጥቃት ስምንት ስደተኞች በጥይት እንደተመቱ እና እንደቆሰሉ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ስደተኞች ሕክምና እንደተደረገላቸው እና በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ኃላፊዋ ጨምረው ገልፀዋል።ታጣቂዎቹ በቁጥር ስድስት እንደነበሩ የገለፁት ኃላፊዋ ዓላማቸው ምን እነደነበር ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) በትግራይ መጠለያ ጣብያዎች ውስጥ የሚገኙትን ስደተኞች የተሻለ ሰላም ወዳለባቸው አካባቢዎች ለማዘዋወር በሚል ነበር ይህንን መጠለያ ጣብያ ያቋቋመው።ከዚህ ቀደም በማይጸብሪ በሚገኙት ማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች ያሉ ስደተኞችን በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ዳባት ከተማ ወደተገነባው አዲስ ጣቢያ እንደሚዘዋወሩ ተቋሙ ገልፆ ነበር።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍21
በጅንካ እና አካባቢው በሚገኙ ከተሞች የተከሰተው ምንድን ነው?

ደቡብ ኦሞ ዞን በደቡብ ክልል ካሉ ዞኖች መካከል አንዷ ስትሆን፤ ጅንካ ከተማ ደግሞ የዚህ ዞን አስተዳድር ዋና መቀመጫ ነች።በዚህ ዞን ስር ባሉ ወረዳዎች ውስጥ ከሚኖሩ ማህበረሰቦች መካከል ደግሞ የአሪ ማህበረሰብ አንዱ ሲሆን፤ ይህ ማህበረሰብ በራሱ ዞን እንዲተዳደር የዞንነት ጥያቄ ለደቡብ ኦሞ ዞን እና ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ጥያቄ አቅርቦም ነበር።

ይሁንና ይህ የዞንነት ጥያቄያችን አልተፈታም በሚል የአሪ ማህበረሰብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች ግጭት መቀስቀሱን አል ዐይን አማርኛ ከነዋሪዎች አረጋግጧል።ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የጅንካ ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው፤ የአሪ ማህበረሰብ የሚገኙባቸው ወረዳዎች ወደ ዞን ይደግ በሚል መነሻነት በደቡብ ኦሞ ዞን ሁከት መከሰቱን ተናግረዋል።

ሁከቱ ጅንካን ጨምሮ የአሪ ማህበረሰብ በሚኖሩባቸው ሶስት ወረዳዎች ላይ ከትናንት 9 ሰዓት ጀምሮ ማንነቶችን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መሰንዘራቸውን የተናገሩት ነዋሪው፤ ለብዙ ዓመታት የተለፋባቸው ንብረቶች የዘረፋ እና በእሳት ማውደምን ጨምሮ ድብደባ ተፈጽሟልም ብለዋል።

ሙሉ ዘገባው: https://am.al-ain.com/article/identity-based-attacks-have-been-reported-in-four-cities-including-jinka-ethiopia

@YeneTube @FikerAssefa
https://tttttt.me/sabinavisa1

😳በድጋሚ የወጣ የስራ ማስታወቂያ 🙄

🇬🇧 የስራ ጉዞ ወደ #UK 🇬🇧

👉 የሚሰራበት አገር - UK
👉 የስራው አይነት - Vegetables and fruits picker
👉 የስራ ቀናት - 5 - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - ከ8 - 10 hr/day
40/60 working hrs per week
👉 ደሞዝ - £8.91 per hr + bonuses for OT
👉 ፆታ - ወንድ እና ሴት
👉 ዕድሜ - 20 እስከ 45
👉 OT - ይቻላል
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ 2 _3 ወር

Accommodation is provided by the employer (~£55 per week)

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo

#Urgent
የምንፈልገው የአመልካች ብዛት 20 ሰው ብቻ::

Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com

https://tttttt.me/sabinaadvisor
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግል ባንኮች የከፈቷቸው የባንክ ሒሳቦች በሙሉ እንዲዘጉ ታዘዙ!

የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች በተለያዩ የግል ባንኮች የከፈቷቸውን ሒሳቦች በአስቸኳይ እንዲዘጉ፣ ይህንንም ማድረጋቸውን የሚያረጋግጥ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ታዘዙ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር በግል ባንኮች ውስጥ አካውንት ከፍተው ገንዘብ እያንቀሳቀሱ ነው ለተባሉ መሥሪያ ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ፣ በግል ባንኮች ውስጥ ያላቸውን ሒሳብ ካልዘጉ ዕርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቋል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተጻፈው ይኼው ደብዳቤ፣ በመንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ መሠረት፣ የመንግሥት ገንዘብ ወይም ገቢ የሚደረገው በብሔራዊ ባንክ ወይም ብሔራዊ ባንክ በሚወክለው ባንክ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በዚህ ድንጋጌ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለጊዜው የሰየመው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ብቻ መሆኑን የሚኒስትር ዴኤታው ደብዳቤ ያመለክታል፡፡

ሆኖም በአሁኑ ወቅት በርካታ የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች የመንግሥት ገንዘብ ለማንቀሳቀስ በግል ባንኮች ሒሳብ በመክፈት ላይ መሆናቸውንና ይህንን ማቋረጥ እንደሚኖርባቸው በመታመኑ ዕርምጃው እንደተወሰደ ታውቋል፡፡

በመሆኑም ይህንን ተግባር የፈጸሙ፣ እንዲሁም በዚህ በሒደት ላይ የሚገኙ መሥሪያ ቤቶች የከፈቱትን የባንክ ሒሳብ በመዝጋት ለገንዘብ ሚኒስቴር ሪፖርት እንዲያደርጉም አሳስቧቸዋል፡፡

መሥሪያ ቤቶቹ ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ግን በሚደረገው ማጣራት፣ በግል ባንኮች ውስጥ የተከፈተ የባንክ የሒሳብ ቁጥር ከተገኘባቸው፣ ዕርምጃ እንደሚወስድባቸውም የሚኒስትር ዴኤታው ደብዳቤ አመልክቷል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
👍2
ሩሲያ ወደ ውጭ በምትልከው ስንዴ ላይ በታሪክ ከፍተኛ የተባለ የታክስ ጭማሪ አደረገች!

የሩሲያ መንግስት ወደ ውጭ በሚላከው ስንዴ ላይ የታክስ ጭማሪ ማደረጉን የሀገሪቱ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።ሚኒስቴሩ፤ ከሀገሪቱ ወደ ውጭ በሚላክ ስንዴ ላይ የታክስ ጭማሪ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን ይህም በዚህ ሳምንት ተግባራዊ ይደረጋል ብሏል፡፡ በዚህም መሰረት አንድ ቶን ስንዴ ወደ ውጭ ሲላክ 101 ነጥብ 4 ዶላር እንዲከፈል መንግስት ወስኗል።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
በጂንካ ከተማ እና በዙሪያዋ በሚገኙ ወረዳዎች ከትናንት ጀምሮ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ!

ከሰሞኑ በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ እና በዙሪያዋ ባሉ ወረዳዎች በተነሳ አመጽ ምክኒያት ከትናንትናዉ እለት ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ የጀመረ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተቋቋመው ኮማንድፖስት እንደታወጀ የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰይፉ አየለ ተናግረዋል።

በትናንትናው እለት የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል የጸጥታ አካላት ወደ ዞኑ እንደገቡም አረጋግጠዋል። በዚህም በከተማዋ በሚገኙ ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንደታገደ ገልጸዋል። በተጨማሪም ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ ማንኛቸዉም እንቅስቃሴዎች ለጊዜዉ እንደታገዱ አብራርተዋል።

በተነሳዉ አመጽም እስከአሁን ድረስ የአንድ ሰዉ ህይወት እንዳለፈም ሀላፊዉ አረጋግጠዋል።በአመጹ መኖሪያ ቤታቸዉ እና የንግድ ሱቆቻቸዉ የወደመባቸዉ ዜጎች መከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ጸጥታ አካላት በሚገኙበት አካባቢዎች ተጠልለው እንደሚገኝም ተናግረዋል። በጂንካ ከተማ የሚገኘው የቀይመስቀልም ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም ገልጸዋል።

በከተማዋ በዛሬዉ እለት አንጻራዊ ሰላም እንደሚታይባት እና አንዳንድ ባንኮች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲሁም የነዋሪዎች እንቅስቃሴ እየተመለሰ መሆኑን የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ሰይፉ አየለ አክለዉ ተናግረዋል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
“ከአማራ ክልላዊ መንግስት በመነሳት የጦር መሳሪያ የታጠቁ ኃይሎች በኃይል በመጣስ ጦርነት አውጀው የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት ተግባር ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ “ ኦፌኮ

ኦፌኮ መንግስት ሰሞኑን በአዲስ መልኩ ያወጀው ዘመቻ በጥቂቱ ፈንጥቆ የነበረውን የሰላም ጭላንጭል መልሶ የሚያደበዝዝ፤ኦሮሚያና አገሪቱን ለተጨማሪ አደጋ የሚያጋልጥ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ የማይሰጥ ነው ብሏል።

በሁለቱ አካላት መካከል ያለው ግጭት ፖለቲካዊ መንስዔ ያለው ሲሆን መፍትሄውም ፖለቲካዊ መሆን አለበት ብሎ እንደሚያምንም አሳውቋል፡፡ በአጎራባች የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች መካከል የሰላምና ፀጥታ ችግር እየተባባሰ ነው ያለው መግለጫው፣ ከሰሞኑ ይፋ እየተደረጉ ካሉ ዘገባዎች መረዳት እንደሚቻለው ከአማራ ክልላዊ መንግስት በመነሳት የጦር መሳሪያ የታጠቁ ኃይሎች በተለያዩ ስፍራዎች በኩል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትን የታወቀ ወሰን በኃይል በመጣስ ጦርነት አውጀው የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት ተግባር ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ ብሏል ኦፌኮ በመግለጫው፡፡

እነዚህ ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል፤አርሷደሮችን ከመሬታቸው በማፈናቀል ክልሉን ወደማያባራ የግጭት ቀጠና እየለወጡት እንደሚገኙ፣ በተለይም ይህ የጦር ዘመቻና የመሬት ወረራ በምስራቅ ወለጋ፤ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፤ሰሜን ሸዋ፤ ምዕራብ ሸዋና በምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ በተቀናጀ አኳኋን እየተካሔደ እንደሚገኝ ከአባሎቻችን እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ለመረዳት ችለናል ብሏል፡፡

ታጥቀው ወረራ እያካሔዱ ባሉ የአማራ ክልል ኃይሎች በሚዲያ የሚሰጡት መግለጫም ይህንኑ ያረጋግጣል ብሏል፡፡ ይህን ወረራ የሚያካሂዱት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጪ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ “ጽንፈኛ” ኃይሎች ናቸው ቢባልም ይህ እውነት እንዳልሆነ የሚያመላክቱ ማስረጃዎች አሉ ካለ በኃላ፣ እንዲህ ያለው አሰራር ህገመንግስቱን ከመፃረር አልፎ የሁለቱ ክልሎች ወንድማማች ህዝቦች ወደለየለት ጦርነት እንዲገቡ በር የሚከፍት መሆኑን ኦፌኮ አበክሮ ያስጠነቅቃል፡፡

ይህ በጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እየታገዘ የሚካሔደው የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት ዘመቻ ቀድሞውንም ባልሻረ ቁስል ላይ ጨው በመነስነስ የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት ወደከፋ የመጠፋፋት ጦርነት ሊገፋ እንደሚችል ሁለቱም ወገኖች ሊገነዘቡ ይገባል ሲል ገልጿል፡፡

በሁለቱ ክልሎችና እነዚህ ትልልቅ ህዝቦች መካከል የሚደረገው ጦርነት አገሪቱንም ለብተና፤ የአፍሪካን ቀንድ ደግሞ ለከፋ አለመረጋጋት የሚያጋልጥ መሆኑ ታውቆ ይህ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም ኦፌኮ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
👎9👍8
👉ሴት እህቶቻችንን ዋጋችን ከ 300 እስከ 1,000 ብር ብቻ!!!

😱 3 ልብስ ለገዛ 1 በነፃ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ልዩ ቅናሽ።

ሰላም ውድ ደንበኞቻችን ጥራት ያላቸውን የሴት አልባሳት እና ጫማዎችን እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል።

👉የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ምርጥ ምርጥ ልብሶችን በቅናሽ ዋጋ ይግዙ።

https://tttttt.me/CITYFASHION321

📞ስ.ቁ
0975798585

አድራሻ: ከ 22 ወደ ቦሌ መድሃኒአለም (ኤድና ሞል) በሚወስደዉ መንገድ(New day) ኒው ዴይ ሆቴል አጠገብ ባማ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ሱቅ ቁጥር 108 ላይ ያገኙናል።
👍2
ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር ክልል መብረር ይችላሉ ሲል የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እገዳ ተጥሎባቸው የቆዩትን ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር ክልል መብረር እንደሚችሉ አስታዉቋል፡፡

ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በረራ ቁጥር ኢ ቲ-302 ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ላይ የደረሰውን አደጋ መሠረት በማድረግ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ሥሪት ተለዋጭ መመሪያ እስካልወጣ ድረስ በኢትዮጵያ አየር ክልል እንዳይበር እገዳ መጣሉ ይታወሳል።

ይሁንና አውሮፕላኑ የተፈበረከበት አገር የአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር አውሮፕላኑ ለአደጋው መንስኤ የሆኑ ችግሮችን በመለየት አደጋውን ሊቀርፍ የሚያስችል አስገዳጅ መመሪያ በማውጣት መመሪያዎቹ ተግባራዊ እንደሆኑ አውሮፕላኖቹ ወደ በረራ መመለስ እንደሚችሉ ገልጿል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በአውሮፕላኖቹ ላይ የተደረገውን የዲዛይን ማሻሻያ እና የአየር መንገዱን የበረራ መመሪያዎች እና ሥልጠናዎች በተገቢው ሁኔታ በመፈተሽ አየር መንገዱ መመሪያዋቹን ተግባራዊ ማድረጉን በማረጋገጥ ከዛሬ ጀምሮ ጥሎት የነበረውን የበረራ እገዳ ማንሣቱን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍3
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ ከፊንላንዱ ኖኪያ ኩባንያ ጋር በቴሌኮም መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ዙሪያ የግማሽ ቢሊዮን ዶላር የረጅም ጊዜ ስምምነት እንደተፈራረመ ካፒታል ዘግቧል።

ስምምነቱ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶችን እና ኔትዎርኮችን ለማስፋፋት የሚያስችል ነው። ሳፋሪኮም በቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎቱን እንደሚጀምር ይጠበቃል። ኩባንያው ቀደም ሲል ከቻይናው ሁዋዌ ኩባንያ ጋር ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉት የአገሪቱ ክፍሎች ኔትዎርክ ለማስፋፋት ውል ገብቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍26
https://tttttt.me/sabinavisa1

😳በድጋሚ የወጣ የስራ ማስታወቂያ 🙄

🇬🇧 የስራ ጉዞ ወደ #UK 🇬🇧

👉 የሚሰራበት አገር - UK
👉 የስራው አይነት - Vegetables and fruits picker
👉 የስራ ቀናት - 5 - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - ከ8 - 10 hr/day
40/60 working hrs per week
👉 ደሞዝ - £8.91 per hr + bonuses for OT
👉 ፆታ - ወንድ እና ሴት
👉 ዕድሜ - 20 እስከ 45
👉 OT - ይቻላል
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ 2 _3 ወር

Accommodation is provided by the employer (~£55 per week)

#Requirements
👉 Passport
👉 Photo

#Urgent
የምንፈልገው የአመልካች ብዛት 20 ሰው ብቻ::

Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com

https://tttttt.me/sabinaadvisor
👍1
በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ ትላንት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች ወደሙ!

በአፋር ክልል ሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ በትላንትናው ዕለት በድንገት በተከሰተ የእሳት ቃጠሎ በግምት ከ160 በላይ የሚጠጉ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን የወረዳው አስተዳድር ገለፁ። የሰሙሮቢ ገልዐሊ ወረዳ አስተዳድር ሀሰን ሀንዲ ለአፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት በስልክ እንደገለፁት የእሳት ቃጠሎ አደጋው የደረሰው ትናንት ወደ 10 :00 ሰዓት አካባቢ በድንገት ከቢንዝል መሸጫ ቤት በተነሳ መሆኑን ጠቁመዋል።

በደረሰው ድንገተኛ የቃጠሎ አደጋም ወደፊት የሚጣራ ሁኖ፤ በግምት ግን ከ80 በላይ መኖሪያ ቤቶች እንደዚሁም ወደ 80 ሊጠጋ የሚችል የተለያዩ የንግድ ሱቆች በእሳት አደጋው የወደሙ ሲሆን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ አደጋ ግን የለም ብለዋል።በአካባቢው ከነበረው ከፍተኛ ንፋስ መኖሩ የተነሳ እና የውሀ እጥረት በመኖሩ ቃጠሎው በፍጥነት በመባባሱ ምክንያትም እሳቱን ለመቆጣጠር ባለመቻሉ ከፍተኛ ውድመት ተከስቷል ሲሉ የወረዳው አስተዳደር አስታውቀዋል።

ስለሆነም በቅድሚያ እሳቱን ማጥፋት እና ተጎጂዎቹ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። የወረዳው አስተዳደር አክለውም፤ በብዛት የቢንዚል ሽያጭ ከሚከናወንበት ቦታ በቀላሉ የእሳት አደጋ እየተፈጠረ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቂ ሊደረግ ይገባል ሲሉ ማሳሰባቸውን የአፋር መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍6
ወደ ሶማልያ የሚሄድ ጫት ዋጋ ላይ እጥፍ ጭማሪ ተደረገ!

ከወጪ ሸቀጦች በግምባር ቀደምትነት የሚካተተው የጫት ዘርፍ የተሻለ ገቢ ማስገኘት እንዲቻል በግብይቱ ላይ በርካታ ማሻሻያዎች እየተደረገ ነው፡፡

ከነዚህም መካከል ለ41 አመታት ሲሰራበት የነበረውንን የግብይት መመሪያ ማሻሻል ይጠቀሳል፡፡በተጨማሪም የጫት ግብይት አሰራር እና የድርጊት መርሃግብር ተዘጋጅቶ እንዲፀድቅ ለብሄራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ቀርቧል፡፡

ከተደረጉ ለውጦች መካከል የጫት ወጪ ምርት ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረግ ይጠቀሳል፡፡በዚህም መሰረት ከጥር 15 አንስቶ ወደ ሶማልያ የሚላክ ጫት ዋጋ ላይ በኪሎግራም ቀደም ሲል ከነበረው ዝቅተኛ 5 ዶላር ወደ 10 ዶላር እንዲያድግ መደረጉ ይጠቀሳል፡፡

ጫት በበጀት አመቱ 8 ወራት 280 ሚሊየን ዶላር ያስገኘ ሲሆን ይህም ከወጪ ሸቀጦች በገቢ ቡና እና ወርቅን ተከትሎ 3ኛ ደረጃን እንዲይዝ አስችሎታል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍3
የሽንኩርት ዋጋ ሊወደድ የቻለው በህገወጥ ደላሎች መበራከት መሆኑን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት የሽንኩርት እጥረት የለም ሲል ቢያስታውቅም በተለያዩ የከተማዋ የገበያ ስፍራዎች አላአግባብ የዋጋ ጭማሪ ይስተዋላል።ይህ ሊሆን የቻለው የህገወጥ ደላሎች መበራከት ያመጣው ችግር መሆኑን በቢሮው የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ሚኤሶ በተለይ ተናግረዋል፡፡

በተለምዶው ሽንኩርት ከሚያዚያ ወር በኋላ ከነበረበት ዋጋ የተወሰነ ጭማሪ የሚያሳይ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱም አጠቃላይ ሃገር ውስጥ የሚገኘው የሽንኩርት ምርት እየቀነሰ የሚሄድበት ወቅት በመሆኑ ነው።ካለው የሃገር ውስጥ የሽንኩርት ምርት በተጨማሪ ከሱዳን የሚመጣውን ሽንኩር በማቅረብ ፍላጎቱን ለማርካት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ቢሮው በሸንኩርት ዋጋ ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታየ ያለውን የዋጋ መወደድ ተከትሎ አሉ በተባሉ ህብረት ስራ ማህበራት ጋር ያለውን ሁኔታ ለማጣራት የተሞከረ ቢሆንም ምንምን አይነት የምርት እጥረት እንደሌለ ማወቃቸውን አስረድተዋል፡፡

ችግሩ ያለው ሂደቱ ላይ ነው የሚሉት አቶ ዳንኤል ህገወጥ ደላሎች የገበሬው ማሳ ድረስ በመሄድ ገበሬዎቹ ኪሳራ ውስጥ እንዲገቡ በሚያደርግ መልኩ ዋጋውን የማራከስ ሂደቶችን እየተጠቀሙ መሆናቸውን አንስተዋል።

ችግሩን ለመፍታት ገበሬው ቀጥታ ከህብረት ስራ ማህበራት ጋር ትስስር እንዲፈጥር እና እዚሁ በመምጣት በማከፋፈል እንዲሰራ የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡በዚህም ኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበራት ጨምሮ የሽንኩርት አምራቾች እና ሌሎች ዩኒየኖችን በመጪው በአል እና በእሁድ ገበያዎች ላይ በስፋት ማቅረብ እንዲችሉ ታሳቢም በማድረግ ከአዲስ አበባ ከሚገኙ የህብረት ሰራ ማህበራት ጋር የማስተሳሰር ስራ እየተሰራ ነው ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል፡፡ብስራት ሬዲዮ አከናወንኩት ባለው የገበያ ቅኝት አንድ ኪሎ ሽንኩርት በ 42 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

[Bisrat FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ማብራሪያ፡-

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ጉዳዩን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በማገናኘት ሲሰራጭ ቆይቷል።

እንደዚህ ያሉ ቅሬታዎች የሀገሪቱን የፌደራል ስርዓት አሰራር በውል ካለመረዳት የመጣ ሊሆን እንደሚችል በመገመት በፌደራል የትምህርት ሚኒስቴርና በክልሎች በሚተዳደሩ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሰራር የግንኙነት ማዕቀፍ መረዳት ለሚፈልጉ ወገኖቻችን በአጭሩ ገለፃ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግንተንዋል፡፡

የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባራት ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀፅ 34 ለትምህርት ሚኒስቴር የተሰጡ ስልጣንና ተግባራትን ያከናውናል እንጂ የስልጣን ተዋረዱን ጠብቆ ላልመጣና ከክልሉ ትምህርት ቢሮ አቅም በላይ ባልሆነ ጉዳይ ትምህርት ሚኒስቴር ጣልቃ የሚገባበት ምንም አይነት አሰራር የለም፡፡::

ስለሆነም ከሰሞኑ ከሀይማኖታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተነሱ ቅሬታዎች በህገ መንግስቱ መሰረት የሚስተናገዱ ሆነው ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው ግን የአዲስ አበባ ት/ቢሮን እንጂ የትምህርት ሚኒስቴር አለመሆኑን እየገለፅን የትምህርት ሚኒስቴር ስልጣንና ተግባራት እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡-

ሀ/ የአጠቃላይና የከፍተኛ ትምህርት፣ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎች፣ ህጎችና እና ፕሮግራሞች ይቀርጻል፣ ለአፈጻጸሙ ከሀገራዊ የልማት አቅጣጫ ጋር የተጣጣመ ዝርዝር መርኃ ግብር ያዘጋጃል፤ በሚመለከተው አካል ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤

ለ/ የአጠቃላይና የከፍተኛ ትምህርት የሥርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍ ያዘጋጃል፣ የትምህርት እና የትምህርት ተቋማትን ስታንዳርድ ያወጣል፣ ሀገራዊ የብቃት ማዕቀፍ ያዘጋጃል፣ በሥራ ላይ መዋሉንም ያረጋግጣል፤

ሐ/ የአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲና ሥርዓተ-ትምህርት መሠረት ያደረጉ ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ዝግጅት፣ ሪከርድ መያዝና የምስክር ወረቀት የመስጠት ሂደቶችን በበላይነት ያስተባብራል፤

መ/ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጥናትና ምርምር የጎለበቱ እንዲሆኑ የሚያስችል ስልት ይነድፋል፣ ይተገብራል፤ የጥናትና ምርምር ውጤቶች በሥራ ላይ የሚውሉበትን መንገድ ያመቻቻል፤

ሠ/ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በከፍተኛ ትምህርትና የምርምር ተቋማት እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ መካከል ለምርምርና ቴክኖሎጂ ልማት እንቅስቃሴ የሚያግዝ ምቹ የእርስበርስ ትስስርና ቅንጅታዊ አሠራር እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤

ረ/ የመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አፈጻጸም ይከታተላል፤
ሰ/ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላና ምደባ አፈጻጸም ፍትሃዊ መሆኑን ያረጋግጣል፤ ሸ/ የአጠቃላይ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሊያሟሉ የሚገባቸውን ደረጃ መውጣቱን ያረጋግጣል፤ በተቋማቱ ጥራትና አግባብነት ያለው ትምህርት መሠጠቱን ይከታተላል፤
ቀ/ ጥራቱን የጠበቀ የከፍተኛ ትምህርት እንዲስፋፋ ያደርጋል፣ በበላይነት ይመራል፤ በ/ትምህርትን በተመለከተ አገራዊ የአህዝቦት ተግባራትን ያከናውናል ፡፡

ከህገ መንግስቱ አንፃር፡-

የብሄራዊ ፖሊሲ መርሆችና አላማዎች አንቀፅ 90 ንዑስ አንቀፅ 2 መሰረት ትምህርት በማንኛውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከትና ከባህላዊ ተፅዕኖዎች ነፃ በሆነ መንገድ መካሄድ አለበት የሚል የህገ-መንግስቱ አስገዳጅ ድንጋጌዎች ውስጥ ተካትቶ እንደሚገኝ መረዳት ያስፈልጋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
ወደ ቻይና የተላከ ሰሊጥ መንገዱን ቀይሮ እየተመለሰ ነው!

ቻይና በገቢ የግብርና ምርቶች ላይ አዳዲስ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጧን ተከትሎ ወደ ቻይና መንገድ ጀምሮ የነበረ ሰሊጥ እየተመለሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡ካለፈው ታህሳስ አንስቶ የሩቅ ምስራቋ አገር ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችው ቅድመ ሁኔታ በወቅቱ ባለመታወቁ ወደ አገሪቱ ተልኮ የነበረ የሰሊጥ ጭነት መንገድ እንደጀመረ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ገልጸው አዲሱ አሰራር ዘግይቶ በአገሪቱ ከተገለፀ በኋላ ምርቱ እንዲመለስ መደረጉን እና የመልስ ጉዞ ላይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በአዲሱ አሰራር የግብርና ምርቶች ወደ ግዙፏ ገዥ ማስገባት የሚችሉ የየትኛውም አገር ላኪዎች የራሳቸው ማቀነባበሪያ እና ማበጠሪያ ያላቸው እና ይሄንንም ማረጋገጥ የሚችሉ ብቻ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡በኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ ያሉ ላኪዎች ቁጥር እጅግ ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት መንግስት ከቻይና ኢምባሲ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ቅድመ ሁኔታውን ማሟላት የማይችሉ ላኪዎች አቅሙ ባላቸው እና ፈቃድ ቁጥር በያዙ ላኪዎች በኩል እንዲልኩ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
👉ሴት እህቶቻችንን ዋጋችን ከ 300 እስከ 1,000 ብር ብቻ!!!

😱 3 ልብስ ለገዛ 1 በነፃ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ልዩ ቅናሽ።

ሰላም ውድ ደንበኞቻችን ጥራት ያላቸውን የሴት አልባሳት እና ጫማዎችን እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል።

👉የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ምርጥ ምርጥ ልብሶችን በቅናሽ ዋጋ ይግዙ።

https://tttttt.me/CITYFASHION321

📞ስ.ቁ
0975798585

አድራሻ: ከ 22 ወደ ቦሌ መድሃኒአለም (ኤድና ሞል) በሚወስደዉ መንገድ(New day) ኒው ዴይ ሆቴል አጠገብ ባማ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ሱቅ ቁጥር 108 ላይ ያገኙናል።
ኦፌኮ የአማራ ክልል ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብ ሸዋ እና ምሥራቅ ሸዋ ዞኖች የመሬት ወረራ እያካሄዱ ነው በማለት መክሰሱን አብን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አውግዟል።

ኦፌኮ የጠቀሳቸው አብዛኞቹ አካባቢዎች የአማራ ብሄር ተወላጆች በማንነታቸው ተለይተው በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚጨፈጨፉባቸው እንደሆኑ አብን ገልጧል። ኦፌኮ ይህን አደገኛ መግለጫ ያወጣው፣ በኦሮሞ ፖለቲካ ኃይሎች መካከል ያለውን የፖለቲካ ሽኩቻ እና ከኦነግ ሸኔ ጋር የሚደረገውን ግጭት ለማርገብ ሲል ነው ሲል ከሷል። በአገሪቱ ያሉ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት ተቀራርቦ በመስራት ብቻ እንደሆነ ፓርቲው ጨምሮ ገልጧል።

@YeneTube @FikerAssefa