የሲዳማ ክልል ባለሥልጣናት የክልሉን ሕዝብ ሰብአዊ መብቶች ይጥሳሉ፣ የመልካም አስተዳደር ጉድለት ይታይባቸዋል፣ በሙስናም ተዘፍቀዋል በማለት የክልሉ ወጣቶች ወቀሱ።
ወጣቶቹ ትናንት ሐዋሳ ወስጥ ከፌደራሉ መንግስትና ከገዢው የብልጽግና ፓርቲ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ዉይይት እንዳሉት ባለስልጣናቱ ለወጣቶች መገልገያ የተገነቡ ተቋማትን ለዘመዶቻቸዉና ለቤተሰቦቻቸዉ ሰጥተዋል፣ዉሳኔዎችንም የሚያሳልፉት ለነሱና ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ በሚጠቅም መልኩ ነዉ። የክልሉና የገዢው ፓርቲ ተወካዮች ወጣቶቹ ባቀረቡት ቅሬታ ላይ ተመስርተዉ ስህተቶችን ለማረም እንደሚጥሩ ቃል ገብተዋል፡፡
[DW]
@YeneTube @FikerAssefa

የአዋሽ – ኮምቦልቻ – ሃራ ገበያ የባቡር መስመርን የሚገነባው የቱርክ ኩባንያ የሰራተኞቹን ውል አቋረጠ!
የአዋሽ– ኮምቦልቻ – ሃራ ገበያ (ወልዲያ) የባቡር መስመር ፕሮጀክትን ግንባታ የሚያከናውነው “ያፒ መርከዚ” የተሰኘው የቱርክ ኩባንያ የሰራተኞቹን ውል አቋረጠ።ኩባንያው ውሉን ማቋረጡን ያስታወቀው ከአስር ቀናት ገደማ በፊት ለሰራተኞቹ በጻፈው ደብዳቤ ነው።
በ“ያፒ መርከዚ” የኢትዮጵያ ቅንርጫፍ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ሰርካን ኮርክማዝ ተፈርሞ በወጣው ደብዳቤ ላይ፤ የሰራተኞቹ ውል የተቋረጠው ከመጋቢት 22፤ 2014 ጀምሮ እንደሆነ ተገልጿል። ኩባንያው የሰራተኞቹን ውል ያቋረጠው የባቡር መስመር ፕሮጀክቱ ባለቤት ከሆነው ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ጋር የገባው ውል በመቋረጡ ሳቢያ መሆኑን በደብዳቤው ላይ አስፍሯል።
የቱርኩ ኩባንያ ከኮርፖሬሽኑ ጋር ያለው ውል የተቋረጠው ከሁለት ወር ገደማ በፊት ከጥር 25፤ 2014 ጀምሮ መሆኑን በደብዳቤው ገልጿል።በኢትዮጵያ የባቡር ትራንስፖርት መሰረተ ልማቶችን የመገንባት እና የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የመስጠት ዓላማ አንግቦ የተቋቋመው ኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፤ የአዋሽ– ኮምቦልቻ– ሃራ ገበያ የባቡር መስመር ፕሮጀክትን ለ“ያፒ መርከዚ” የሰጠው በ2006 ዓ.ም ነበር።
ፕሮጀክቱን የተረከበው የቱርኩ ኩባንያ የባቡር መስመር ግንባታውን በ1.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ በሶስት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ውሎ ገብቶ ነበር።ይሁን እንጂ የባቡር መስመር ግንባታው አምስት ዓመታት ዘግይቶም ቢሆን መጠናቀቅ አልቻለም።ፕሮጀክቱ ለዓመታት ከመጓተቱ በተጨማሪም በሰሜን ኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ላለፉት ሰባት ወራት ያህል ተቋርጦ መቆየቱን የኩባንያው ሰራተኞች ይናገራሉ።
Via Ethiopia Insider

https://tttttt.me/sabinavisa1
😳በድጋሚ የወጣ የስራ ማስታወቂያ 🙄
🇬🇧 የስራ ጉዞ ወደ #UK 🇬🇧
👉 የሚሰራበት አገር - UK
👉 የስራው አይነት - Vegetables and fruits picker
👉 የስራ ቀናት - 5 - 6 ቀናት/ week
👉 የስራ ሰዓት - ከ8 - 10 hr/day
40/60 working hrs per week
👉 ደሞዝ - £8.91 per hr + bonuses for OT
👉 ፆታ - ወንድ እና ሴት
👉 ዕድሜ - 20 እስከ 45
👉 OT - ይቻላል
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ 2 _3 ወር
Accommodation is provided by the employer (~£55 per week)
#Requirements
👉 Passport
👉 Photo
#Urgent
የምንፈልገው የአመልካች ብዛት 20 ሰው ብቻ::
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
info@sabinaadvisor.com
https://tttttt.me/sabinaadvisor

👍1
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ እና ምክትላቸው ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተገለጸ!
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ እና ምክትል ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ፔይቶን ኖፕፍ ዛሬ ሚያዝያ 5 ቀን 2014 አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።ልዩ መልዕክተኛው የአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ እና የምክትላቸው ፓይተን ኖፍ በጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት፣የሰብአዊ ድርጅቶች ተወካዮች እና የዲፕሎማቲክ አጋሮች ጋር በመገናኘት ይወያያሉ ተብሏል።
በተጨማሪም በዚህ ጉብኝት ጦርነትን ለማስቆም፣ ያልተገደበ የሰብአዊ አገልግሎት አቅርቦት እንዲኖር፣የሰብአዊ መብት ረገጣ እና የኹሉም ተዋናዮች ጥሰቶች ላይ ግልፅ ምርመራ እንዲደረግ እና በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በድርድር ለመፍታት አሜሪካ የምታደርገውን ጥረት ያስቀጥላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።የቀድሞውን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማንን በቅርቡ የተኩት ሳተርፊልድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም።
አምባሳደሩ መጋቢት 12 እና 13/2014 አዲስ አበባ ገብተው ለኹለት ቀናት ባደረጉት ቆይታ ከአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆን፣ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ውይይት አድርገው እንደነበር ይታወሳል።በተያያዘም የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው ዴቪድ ሳተርፊልድ ከክረምት በፊት ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ጉዳዩን በቅርብ ከሚያውቁ ምንጮች ሰምቻለሁ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።ዛሬ አብረዋቸው አዲስ አበባ እንደሚገቡ የሚጠበቁት ምክትላቸው ፔይቶን ኖፕፍ ቦታውን እንደሚረከቡ እንደሚጠበቅም በዘገባው ተመላክቷል።
@YeneTube

ህወሓት ከአፋር ክልል ኤሬብቲ አካባቢ ተዋጊዎቼን አስወጥቻለሁ አለ!
ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ጦርነት ውስጥ የገባው ህወሓት በአፋር ክልል ኤሬብቲ ተብሎ የሚጠራ ስፍራን ተቆጣጥረው የነበሩ ተዋጊዎቼ አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ አድርጊያለሁ አለ።
ህወሓት ሠራዊቱን ኤሬብቲ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ ለማስወጣት ከውሳኔ የደረሰው ለሰብአዊነት ሲባል የተደረሰው ስምምነት ተከብሮ ያልተገደብ ሰብአዊ እርዳት ትግራይ እንዲደርስ ነው ብሏል።
ዛሬ ሚያዚያ 5/2014 ዓ.ም. በክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ በተላለፈው መግለጫ፤ "የትግራይ መንግሥት የሰላም ውይይቱን ለማሳለጥ በተለይም ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ሚያዚያ 4/2014 ዓ. ም. የትግራይ ሠራዊት ተቆጣጥሮት ከነበረው ኤሬብቲ ተብሎ ከሚጠራው የአፋር አካባቢ ሠራዊቱ እንዲነሳ ተደርጓል" ብሏል።
ህወሓት ይዟቸው ከነበራቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች ለቅቆ ስለመውጣቱ ከአፋር ክልል መንግሥት ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት ስልክ ባለመሳነቱ ሳይሳካ ቀርቷል።የህወሓት ኃይሎች በአፋር ክልል ዞን ሁለት የሚገኙ ወረዳዎችን በቁጥጥራቸው ስር ያዋሉት በጥር ወር አጋማሽ ላይ ነበር።
Via BBC

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት የሚውል የ300 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ!
የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ለተዘጋጀ ፕሮጀክት የሚውል የ300 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አፀደቀ።ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባንኩ ላከልኝ ባለው መግለጫ፥ ይህ ዓለም አቀፍ የልማት ድጋፍ በኢትዮጵያ ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች የተጎዱ ሰዎችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት እንደሚውል አስታውቋል።
በተለይም ድጋፉ የመሰረታዊ አገልግሎት አቅርቦትን ለማሻሸል እና ለዓየር ንብረት ለውጥ የማይበገር መሰረተ ልማት ለመገንባት እንደሚውል በመጠቆም፥ በግጭት የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንደሚያስቀድም ነው ባንኩ ያመለከተው።
በዚህም መሰረት አፋር፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም አስታውቋል።ውጤታማ እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠትም በማሰብ የገንዘብ ድጋፉ በፌደራል መንግስት፣ በክልል መንግስታት እና በአካባቢዎቹ በሚንቀሳቀሱ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በኩል እንደሚቀርብም ገልጿል።
Via FBC

ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ጎርፍ ባስከተለው አደጋ ቢያንስ 60 ሰዎች ሞቱ።
ደርባን ከተማ እና በኩዋዙሉ ናላት ክፍለ ሀገር አካባቢ በሚገኙ ቦታዎች ወጀብ የቀላቀለበት ዝናብ ያስከተለው የመሬት መናድ ለሰዎቹ ሞት ምክንያት መሆኑን ባለሥልጣናት ተናግረዋል። የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር እንደሚችል የአካባቢው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው። ከገጠር አንስቶ እስከ ከተማ በርካታ ቤቶች እና መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳትም መድረሱም ተነግሯል።
የሜቲሪዎሎጂ ትንበያ ትናንት ሌሊቱንም ተጨማሪ ኃይለኛ ዝናብ እንዲሁም ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል አሳስቧል። የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ደርባን ላይ በጎርፍ የተጎዱ አካባቢዎች ነዋሪዎችን ዛሬ ጎብኝተዋል። ራማፎሳ በተለይም በኮረብታ አካባቢ በተገነቡት ቤቶች ከሚኖሩት መካከል የመሬት መናዱ ቤታቸውን ባፈረሰበት ወቅት አራት ልጆቻቸው የሞቱባቸውን ቤተሰቦችም አጽናንተዋል። ከዚህ በፊት ተመሳሳይ የጎርፍ አደጋ በሌሎች እንደ ሞዛምቢክ እና ዚምባብዌ ሲደርስ መመልከታቸውን የተናገሩት ፕሬዝደንቱ ዛሬ ደግሞ ይኽ አደጋ በሀገራቸው መከሰቱን አውስተዋል። ኃይለኛው ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ የከተማዋ የትራፊክ መብራቶች አናት ብቻ በሚታይበት ደረጃ ድረስ እንዳጥለቀለቃት ነው የተገለጸው።
የኳዙሉ ናታል ክፍለ ሀገር የአደጋ መከላከል ዘርፍ የደርባን ከተማ ሰዎች ከቤት እንዳይወጡ ያስጠነቀቀ ሲሆን በዝቅተኛ አካባቢ የሚኖሩ ደግሞ ባስቸኳይ ወደ ከፍተኛ አካባቢዎች እንዲወጡ አሳስቧል። እስካሁን ከሁለት ሺህ በላይ ቤቶች ፤ አራት ሺህ የሚሆኑ ደግሞ መጠለያ መሰል መኖሪያዎች መጎዳታቸው ተገልጿል። 140 በላይ ትምህርት ቤቶች ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተዘግቧል።

የፌደራል መንግስትና የደቡብ ክልል መንግስት የዜጎችን ደህንነት እንዲያከብሩ እና እንዲያስከብሩ ኢሰመጉ ጠየቀ!
የፌደራል መንግስት እና የደቡብ ብሄር ብሔረሰቦች ክልላዊ መንግስት የዜጎችን በህይወት የመኖር፣ አካላዊ እና የንብረት ደህንነት እንዲያስከብሩ እና እንዲያከብሩ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ጥሪ አቀረበ።
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን አሪ ወረዳ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ኢሰመጉ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ “የአሪ ወጣቶች ነን” በሚል ሽፋን ‘ሸኮን’ የተባሉ የተደራጁ ቡድኖች በወረዳው በሚገኙ በጋዘር (ደቡብ አሪ ከተማ) አንዲሁም በሌጠር፣ ሺሸር፣ ሆሊታ፣ በርካማማ እና ቲቲ ቀበሌዎች ቤቶችን ማቃጠል፣ ንብረት ማውደም እና ዘረፋ መፈፀማቸውን ገልጿል። ከመጋቢት መጨረሻ የጀመረውን ክስተት ለመቆጣጠር በአሁኑ ወቅት የፀጥታ ኃይል ወደ አካባቢው መግባቱን ኢሰመጉ አረጋግጫለሁ ብሏል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ባሰባሰባቸው መረጃዎች የችግሩ መነሻ የአሪ ወረዳ የዞን አደረጃጀት ጥያቄውን ለደቡብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት ቢያቀርብም ጥያቄያቸው ለክልል ምክር ቤት አለመላኩ ሲሆን ለብዙ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት መሆኑን ገልጿል።ኢሰመጉ ችግሩ በአፋጣኝ እንዲቆም፣ በድርጊቱ ፈፃሚዎች ላይ መንግስት ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንዲሁም ለተፈናቀሉ ሰዎች ተገቢ ጥበቃ እና ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል። ጉባኤው በቀጣይ ሰፊ የምርመራ ሪፖርቶችን እንደሚያወጣም አስታውቋል።
[Addis Zeybe]

👉ሴት እህቶቻችንን ዋጋችን ከ 300 እስከ 1,000 ብር ብቻ!!!
😱 3 ልብስ ለገዛ 1 በነፃ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ልዩ ቅናሽ።
ሰላም ውድ ደንበኞቻችን ጥራት ያላቸውን የሴት አልባሳት እና ጫማዎችን እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል።
👉የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ምርጥ ምርጥ ልብሶችን በቅናሽ ዋጋ ይግዙ።
https://tttttt.me/CITYFASHION321
📞ስ.ቁ
0975798585
አድራሻ: ከ 22 ወደ ቦሌ መድሃኒአለም (ኤድና ሞል) በሚወስደዉ መንገድ(New day) ኒው ዴይ ሆቴል አጠገብ ባማ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ሱቅ ቁጥር 108 ላይ ያገኙናል።

ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቀድሞው የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ሞሐመድ ኡመር ክስ የዛሬውን የምስክር መስማት ሂደት ወደ ዓርብ ማስተላለፉን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።
ችሎቱ የዛሬውን ቀጠሮ ያዛወረው፣ ለተከሳሹ አስተርጓሚ ሆነው የተመደቡት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ አብዱላሂ ረሚ ችሎት ሳይቀርቡ በመቅረታቸው ነው። ችሎቱ አስተርጓሚው በ24 ሰዓት ውስጥ ታስረው እንዲቀርቡ አዟል። ተከሳሾቹ የክሳቸው ሂደት እየተጓተተ መሆኑን በመጥቀስ፣ ችሎቱ ከሌላ መንግሥት መስሪያ ቤት ተተኪ አስተርጓሚ እንዲፈልግ ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ፤ ሱዳን ያልከፈለቻትን ውዝፍ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ እንድትከፍላት መጠየቋን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የ2014 ስድስት ወራት አፈጻጸሙን ለገንዘብ ሚኒስቴር ባስገመገመበት ወቅት፤ ሱዳን ውስጥ ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት አገሪቱ ለኢትዮጵያ መክፈል የነበረባትን የስድስት ወራት ክፍያ መፈጸም አለመቻሏን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ሞገስ መኮንን ለአል ዐይን አማርኛ እንደገለጹት፤ ሱዳን ያልከፈለችው የኤሌክትሪክ ክፍያ መኖሩን ገልጸው፤ ይህ ግን ከዚህ ቀደምም የሚያጋጥም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ከዚህ በፊትም ሱዳን የተጠቀመችውን የኤሌክትሪክ ውዝፍ ክፍያ ትከፍል እንደነበር የገለጹት ሞገስ የአሁኑም ከቀደመው ጊዜ የተለየ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል፡፡ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተገኘው መረጃ መሰረት፤ ኢትዮጵያ ለሱዳንና ጂቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበች ትገኛለች፡፡ሁለቱም አገራት ውዝፍ ክፍያ ቢኖርባቸውም ቀደም ሲል ባለው አሰራር መሰረት ውዝፍ ክፍያውን እንደሚከፍሉ ተገልጿል፡፡
[Alain]

የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ተጨማሪ ጥቃት ሳትከፍትብን ድረሱልን ሲሉ ለአውሮጳ ሃገራት ጥሪ አቀቡ።
ለኢስቶኒያ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር አውሮጳ ሩሲያ ላይ ተጨማሪ ርምጃ እንዲወስድ የተማጸኑት ፕሬዝደንት ዘለንስኪ አውሮጳ ርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ጊዜ የሚያጠፋ ከሆነ ሩሲያ የጦርነት ቀጣናውን ወደሌሎች ሃገራትም ታስፋፋዋለች በማለት አስጠንቅቀዋል። የዘለንስኪ ጥሪ የተሰማው የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ውጤት ከሌለው ያሰቡትን እስኪያሳኩ ወታደራዊ ዘመቻውን እንደሚገፉበት ከተናገሩ በኋላ ነው።
የሩሲያ ኃይሎችም የሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ወታደራዊ ዘመቻውን እያጠናከረች ነው ያላት ኪየቭ የሰላም ንግግሩን እያጓተተች ነው በሚል ከሷል። የሩሲያ ኃይሎች ትናንት ምሽቱን ማሪዎፖል ከተማን መደብደባቸውን የዩክሬን ባለሥልጣናት መግለጻቸው ተዘግቧል። ይኽ በእንዲህ እንዳለም የብሪታንያ ፍርድ ቤት የሩሲያዊውን ባለሃብት ሮማን አብራሞቪችን 7 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረት ማገዱን ሮይተርስ ከሎንደን ዘግቧል።
አብራሞቪች ከሰሞኑ በብሪታንያ እና በአውሮጳ ሕብረት ማዕቀብ ውስጥ ከተካተቱ የሩሲያ ባለጸጎች አንዱ ነው። እስካሁንም የአውሮጳ እና የብሪታንያ መንግሥታት የሩሲያውያናኑን ባለሀብቶች መርከቦች እና የተቀናጡ ሌሎች ንብረቶችን እያገዱ ነው። በተያያዘ ዜናም ዩክሬን ላይ በከፈተችው በዚህ አውዳሚ ጦርነት ሩሲያን ማውገዝ ያቃታቸው ሃገራት ማስተዋል የጎደላቸው ናቸው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት የሊን ተቹ።ሚኒስትሯ አክለውም የምዕራባውያንን ማዕቀብ ችላ የሚሉ ከሆነም መዘዝ ይከተላቸዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ለኢትዮ ከቴሌኮምና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ
ከስምምነት ላይ ደረሱ!
እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሰረተ ልማት መጋራት እና ትስስር ላይ ያደጉት ዘርፈ ብዙ ድርድሮች በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቃቸውን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።ኩባንያዎቹ በቅርቡ ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@YeneTube @FikerAssefa
ከስምምነት ላይ ደረሱ!
እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሰረተ ልማት መጋራት እና ትስስር ላይ ያደጉት ዘርፈ ብዙ ድርድሮች በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቃቸውን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።ኩባንያዎቹ በቅርቡ ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@YeneTube @FikerAssefa
"አንበሳ ፋርማሲ እና ኒዮን አዲስ እንዲፈርሱ ተወሰነ ተብሎ የሚናፈሰው መረጃ ፍጹም ከእውነታው የራቀ ነው"፦ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
አንበሳ ፋርማሲ እና ኒዮን አዲስ እንዲፈርሱ ተወሰነ ተብሎ የሚናፈሰው መረጃ ፍጹም ከእውነታው የራቀና መሰረተ ቢስ መረጃ ነው ሲል የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አስታወቀ።ኮርፖሬሽኑ የቅርስ ቤቶቹ ይዘታቸው እና ቅርጻቸው ሳይቀየር፤ ባሉበት ሳይነኩ አካባቢው እንዲለማ ተደረገ እንጂ፤ እንዲፈርሱ አልተወሰነም ብሏል።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በትላንትናው ዕለት የቅርስ ቤቶቹን መፍረስ አስመልክቶ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ሲናፈስ ስለነበረው መረጃ ማብራሪያ ሰጥቷል።በማብራሪያውም አንበሳ ፋርማሲ እና ኒዮን አዲስ የተባሉ ድርጅቶች በኪራይ ሲገለገሉበት የነበሩበት እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ንብረት የሆኑ ቤቶች፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቅርስነት ይዘታቸው ሳይቀየር፣ ባሉበት ምንም ዓይነት የቅርጽና የይዘት ለውጥ ሳይደርግባቸው በአካባቢው ከሚገነባው አዲስ ግንባታ ጋር ለአልሚው ባለሀብት እንዲተላለፉ መደረጉን ገልጿል።
በዚህም በቅርሶቹ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማይደርስባቸው በኮርፖሬሽኑ እና በከተማ አስተዳደሩ መካከል ሥምምነት ላይ መደረሱንም አስታውቋል፡፡በተለይ ከቅርብ ዓመታት በፊት ኮርፖሬሽኑ የሚያስተዳድራቸው በርካታ ቤቶቹ እና የቅርስ ቤቶች በልማት ምክንያት በከተማ አስተዳደሩ መፍረሳቸውን ተከትሎ፤ የተፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታትና የቤቶችን ደህንነት በጋራ በመጠበቅ እንዲሁም ከተማዋን በጋራ ለማልማት ኹለቱ አካለት ሥምምነት ላይ በመድረሳቸው፤ ከአሁን በፊት በተለየ ሁኔታ ልዩ ትኩረት ለቅርስ ቤቶች ደህንነት እንደተሰጠም ገልጿል፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያሉንን ቅርሶች በመጠበቅ እና በመንከባከብ፤ ቅርስ ጥበቃ እና ልማት ሚዛኑን አስጠብቆ እንዲሔድ ማድረግ ሌላኛው ከድህነት መውጫ መንገድ ሊሆን እንደሚገባ ገልጿል፡፡ሆኖም በእርጅና ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን እና ቤቶችን ደግሞ ለኹላችን ጥቅምና እድገት በሚያስገኝ መልኩ ማልማትም ተጊቢ ነው ብሎ እንደሚያምንም አስታውቋል፡፡
በዚህም ልማት እና ቅርስ ጥበቃ ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዲሔዱ ማድረግ ተጊቢ እንደሆነ ህብረተሰቡ በውል እንዲረዳ ያሳሰበው ኮርፖሬሽኑ፤ ከዚህ አውድ ውጭ ሌላ ትርጉም ሰጥተው ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት የተሳሳተ መረጃ እየሰጡ መሆኑንም ገልጿል፡፡የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ እና በድሬደዋ ከተማ የሚገኙ የፌደራል መንግስት ቤቶችንና ይዞታዎችን የሚያስተዳድር እንዲሁም በቤት ልማት ዘርፍ የተሰማራ የመንግስት የልማት ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሦስት ወረዳዎች የአቮካዶ ምርትን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ውጤታማነታቸው መረጋገጡን ማኅበሩ አስታወቀ!
ጥራት ያለው የአቮካዶ ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ሦስት አካባቢዎች ውጤታማነታቸው በተግባር መረጋገጡን የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማኅበር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማኅበር የፕሮጀክት ማናጀር አቶ ዋለ ጌታነህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ምሥራቅ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ፤ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ቡታጂራ አካባቢና በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ጥራት ያለው የአቮካዶ ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ ውጤታማነታቸው በተግባር ተረጋግጧል።
እስካሁን በተከናወኑ ሥራዎች በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ለወጪ ንግድ የሚውሉ ጥራት ያላቸው የአቮካዶ ምርቶችን ማዘጋጀት ቢቻልም በኢትዮጵያ በርካታ ቦታዎች ላይ ጥራት ያለው የአቮካዶ ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም መኖሩን ጠቁመዋል።
[EPA]

"ብልፅግና፣ ብሔር ተኮር ፓርቲ መሆኑን አረጋግጧል" - ኢዜማ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ሚያዚያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም በአምስት አገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት ይመስገን መሳፍንት "ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ህብረ ብሔራዊ ነኝ ይበል እንጂ ብሔር ተኮር ፓርቲ መሆኑን አረጋግጧል።" ብለዋል።
የፓርቲው አመራሮች እርስ በእርሳቸው አውራ ለመሆን የሚፎካከር መሆኑን ያነሱት ይመስገን፤ "የራሱ የብልፅግና ሰዎች የሀገሪቱ ስጋት ሆነዋል።" ሲሉ ገልፀዋቸዋል።"ለእያንዳንዱ ድርጊታቸው ተጠያቂ እንደሚሆኑ ሊያወቁ ይገባል።" ሲሉ አሳስበዋል።
በኑሮ ውድነት፣ የመሬት ወረራ፣ በተለይ በደቡብ ክልል ያሉት "የፀጥታ ችግሮች"፣ ሀይማኖት ነክ ጉዳዮችና በመንግስት መካከል ያሉት የእርስ በእርስ እሰጣ ገባዎች የሚሉት አምስቱ ኢዜማ ትኩረት ሰጥቶ መግለጫ የሰጠባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።
Via Asham

በደቡብ ክልል ለወራት ታስረው የነበሩ ከአንድ ሺህ በላይ የትግራይ ተወላጆች መፈታታቸው ተነገረ!
በደቡብ ክልል ሃድያ ዞን ሾኔ በተሰኘች ከተማ ለወራት ታስረው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች መፈታታቸውን ቢቢሲ ከተፈቱ ግለሰቦች ሰምቷል።ወደ 1 ሺህ 300 የሚሆኑ እስረኞች በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ በአውቶብስ ተጭነው አዲስ አበባ መድረሳቸውን መረሳና አይናለም የተሰኙና በስፍራው ታስረው እንደነበር የገለጹ የትግራይ ተወላጆች ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ለዘጠኝ ወራት ያህል ክስ ሳይመሰረትባቸውና የተጠረጠሩበት ወንጀል ሳይነገራቸው እንደቆዩ የሚናገሩት መረሳና አይናለም ሲለቀቁም ምንም መረጃ እንዳልተሰጣቸው ለቢቢሲ አስረድተዋል።ከትናንት በስቲያ ከነበሩበት እስር ቤት ውጡ እንደተባሉና በየእያንዳንዱ አውቶብስ ሁለት ፖሊሶች ተመድቦ እንደመጡና በአዲስ አበባ ቃሊቲ እንዳወረዷቸውም መረሳ ተናግሯል።"የት እንደሚወስዱን፣ ወደ የት እንደምንሄድ አናውቅም። ብንጠይቅም፣ አናውቅም የሚል ምላሽ ተሰጠን" ሲለ መረሳ ያስረዳል።
በእስር ላይ ያሉ የትግራይ ተወላጆችን ቢቢሲ ከሰሞኑ ባናገራቸው ወቅት በብሔራቸው ምክንያት በቂ የምግብ፣ የውሃና የመድኃኒት አቅርቦት በሌለበት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ታስረናል ሲሉ ተናግረው ነበር።

የሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ 47 የጭነት ተሸከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እየተጓዙ ነው!
እየተጓጓዘ ያለው የሰብዓዊ ዕርዳታም ምግብ፣ ዓልሚ ምግቦችን እና ሌሎች ሕይወት አድን ቁሳቁሶችን እንዳካተተ ነው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ያስታወቀው።ከምግብ እና መሰል አቅርቦቶች በተጨማሪ 3 የነዳጅ ቦቴዎች በማጓጓዝ ሂደቱ ለተሸከርካሪዎቹ ለጥቅም እንዲውሉ ታስቦ አብረው ወደ ትግራይ ክልል እየተንቀሳቀሱ እንደሆነም ነው ድርጅቱ በትዊተር ገጹ ያመላከተው፡፡

በአማራ ክልል በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ ግንባታውን በጨረታ አሸንፈው የተረከቡት የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች አስጠንቅቀዋል።
300 አባላት ያሉት የአማራ ክልል የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ማኅበር እንዳስታወቀው የማኅበሩ አባላት የሆኑ ተቋራጮች ከመንግሥት በጨረታ የተረከቧቸውን የግንባታ ፕሮጀክቶች ማከናወን አለመቻላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለአማራ ክልል ር/መስተዳደር እንዲሁም ለሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት ማለትም ለአማራ ክልል ማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ፣ ለገንዘብ ቢሮ፣ ለከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ ለፍትሕ ቢሮ እና ለአማራ ብልፅግና ጉዳዩን የሚያብራራ እና ምላሽ እንዲሰጥበት የሚጠይቅ ደብዳቤ አስገብተዋል።
የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮቹ እንደሚሉት የግንባታ ቁሳቁሶች ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን በመናሩ ቀድሞ በጨረታ አሸንፈው ስራውን በተረከቡበት ዋጋ ግንባታውን ማከናወን እንዳይችሉ እንቅፋት ሆኗል። በመሆኑም የዋጋ ማሻሻያ የማይደረግ ከሆነ ስራቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዲያቋርጡ ይገደዳሉ።
ሙሉውን ያንብቡ
https://bit.ly/3EgJ8O5

በአዲስ አበባ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጣለ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ እገዳ ተጥሏል፡፡
ወቅቱ የፋሲካ በዓል በመሆኑ ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ ስለሚኖር፣ ግርግር እና ስርቆት እንዳይፈጠር በማሰብ፤ አዲሱ ጥናት ተጠናቆ እስኪጠናቀቅ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከአሽከርካሪዎች ውጭ ሌላ ተሳፋሪ እንዳይጭኑ ቁጥጥር እንዲደረግ እገዳ ተጥሏል፡፡
በዚህም እርምጃ እንዲወሰድ ቢሮው ለሚመለከተው አካል የስራ ትዕዛዝ ማስተላለፉም ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡