#ወደ_ሀብት_ጉዞ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች በሚለውና #አስበህ_ሐብታም_ሁን በሚል በተተረጎመው መጽሐፉ የምናውቀው የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ።
#ወደ_ሀብት_ጉዞ
ይህ ወደ ሀብት ጉዞ የተሰኘው መጽሐፍ እያንዳንዱን ሕልማችንንና ዓላማችንን ለማሳካት ያግዘናል፡፡
ብልፅግና በገንዘብና ዝና ብቻ የተገደበ ትርጉም እንደሌለው ያሳየናል፡፡ እውነተኛ ባለጸጋ ለመሆን በሁሉም የሕይወት ዘርፎች መበልፀግ ያስፈልጋል- በአካል፣ በመንፈስ፣ በገንዘብ፡፡
ለዚህም ደግሞ ከ25 ሺ በላይ ሰዎች የውድቀት ምክንያት፣ ከ500 በላይ ስኬታማ ሰዎች ምስጢርና የሀያ አምስት አመታት የምርምር ውጤት... ወደ #ሀብት_ጉዞ መጽሐፍን ፈጥሯል።
ከ60 ሚሊየን ኮፒ በላይ ከተሸጠው አስበህ ሀብታም ሁን መጽሐፍ ቀጥሎ ከፍተኛ ሽያጭን የተቀዳጀ መጽሐፍ።
እነሆ በሁሉም መልክ ወደ ሀብት ጉዞ!!
የናፖሊዮን ሂልን መጽሐፍ ይዞ!!!
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።
*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun

ሁለት ህፃናትን አግተው ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ በጠየቁ ወንጀለኞች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው።
በምስራቅ ጎጃም ዞን ብቸና ከተማ አስተዳደር መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ሁለት ታዲጊ ህፃናትን አግተው ከቤተሰቦቻቸው 400,000/አራት መቶ ሽህ ብር/ እንዲከፍሉ በመጠየቅ ሲደራደሩ የነበሩ ሁለት ወንጀለኞች በፖሊስ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወቃል።
በዚህም መሰረት የወንጀለኞችን የምርመራ መዝገብ የተመለከተው የእነማይ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሾች ጥፋተኛ መሆናቸውን በቀረቡ ማስረጃወች በማረጋገጡ መጋቢት 23 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ተሾመ ሀብቴ የተባለውን በ7 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት፣ 2ኛ ተከሳሽ በሀይሉ ይዘንጋውን ደግሞ በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዋና ኢንስፔክተር የሽዋስ አከለ ገልፀዋል።
[የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ]
@YeneTube @FikerAssefa

👍1
ከመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ሊወስዱ መሆኑ ተገለጸ!
ከሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚመረቁ ተማሪዎች በሰለጠኑባቸውና በተማሩባቸው ሙያዎች ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ ከዚህ ቀደም ሲደረግ የነበረው ጥረት ወደ ተግባር እንዲገባ ዝግጅት መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል::የመውጫ ፈተነውን በተመለከተ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምክክር እየተደረገ ይገኛል::
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የምክክር መድረክ ባዘጋጀው ውይይትም የመውጫ ፈተናው አስፈላጊነት፤ የፈተና አወጣጥና አፈታተን እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እየተደረገበት ነው::የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የምክክር መድረክ ፕሬዚዳንት እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና የመውጫ ፈተናው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የምሩቃንን ክህሎትና እውቀት ለመፈተሽ የስራ ገበያንም ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል::
በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ሚኒስትር ደዔታ ዶ/ር ሳሙዔል ክፍሌ በበኩላቸው፤ መንግስት በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ጠንካራ ትግበራና ርምጃዎችን እንደሚወስድ አንስተዋል::
አዲስ የመንግስት ዩኒቨርስቲ እንደማይኖርና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አቅምና ጥራት ማሻሻል ላይ በትኩረት እንደሚሰራና መውጫ ፈተናው እንዲወሰድ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል::የመውጫ ፈተናው በእያንዳንዱ ዩንቨርስቲ በየሙያውና ትምህርት ዘርፍ ተዘጋጅቶ የሚሰጥ ሲሆን ለዚህም ትግበራ ፖሊሲና ዝርዝር ማስፈፀሚያ መመሪያ መዘጋጀቱን ገልፀዋል::በህግና በህክምና ሙያ የሚሰጠው የመውጫ ፈተናና የብቃት ማረጋገጫ ፍተሻ እንደ ልምድ ይወሰዳልም ነው የተባለው::
[AMN]

የጥቁር አንበሳ ስፔሻይዝድ ሆሰፒታል የተኝቶ ህከምና አግልግሎት ለማግኘት የሚያስችል አዲስ የገንዘብ የማስያዣ ተመን አወጣ!
በጥቁር አንበሳ ስፔሻይዝድ ሆሰፒታል የድንገተኛ ህክምና ክፍል ከፍተኛ የአልጋ እጥረት መኖሩ እንዳለ ሆኖ አሁን ላይ ደግሞ ባሉት አልጋዎች ላይ ተኝቶ መታከም ለሚፈልጉ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ የክፍያ ስርአዓት በተጫማሪ በቂ አይደለም ባላቸው አገልግሎች ላይ አዲስ ተመን ማውጣቱ ተሰምቷል፡፡
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡን በሆስፒታሉ የድንገተኛ ክፍል ሃላፊ የሆኑት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የድንገተኛ እና ጽኑ ህሙማን ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ደመላሽ ገዛሃኝ ማንኛውም ህብረተሰብ የድንገኛ ክፍል የህክምና አገልግሎትን ጨርሶ ለጽኑ ህሙማን አልጋ ተኘቶ ለመታከም ቢፈልግ ቅደሚያ 10ሺህ ብር ማስያዝ ሲኖርበት በልብ ህሙማን ክፍል ለመተኛት እስከ 25 ሺህ ብር ማስያዝ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም በመደበኛ አልጋ የውሰጥ ደዌ 2000 ብር ፣ በመደበኛ አልጋ ቀዶ ህክምና 4000 ብር ፣ በመደበኛ አልጋ የማህጸን ቀዶ ጥገና 2000 ብር ለቀን ማስያዝ ያለበት ሲሆን በሁሉም አገልግሎቶች ላይ ደግሞ የማእረግ አልጋ ማግኘት ለሚፈልግ ተገልጋይ ከ 500 ብር እስከ 1000 ብር ተጨማሪ መክፈል ይኖርበታል ብለዋል፡፡ዶ/ር ደመላሽ አክለውም ይህ የተመን ማሻሻያ ከላይ የወረደ ይሁን እንጂ ዝቅተኛውን የህብረተሰብ ክፍል ያማካለ አለመሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
Via Bisrat FM

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄዴው 7ኛ መደበኛ ስብሰባው ውሳኔዎችን አሳለፈ!
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 7ኛ መደበኛ ስብሰባ በማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ምክር ቤቱ በመካከለኛ ዘመን (2014-2019) የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ የተወያየ ሲሆን የማዕቀፉ ዋና ዓላማ የ2015 የፌዴራል መንግስት ዝርዝር በጀት የሚዘጋጅበትና ጥቅል የገቢ ትንበያ፣ የወጪ ጣሪያ፣ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት የበጀት ድጋፍ ጣሪያ እና የፊሲካል ጉድለት መጠንን በማዕቀፍነት መወሰን ነው፡፡
ማዕቀፉ በዋናነትም ለተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች፣ ለተከሰቱ የሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ሰብዓዊ ድጋፍ፣ ለመልሶ ግንባታና ማቋቋም፣ ለአገር መከላከያ፣ ለእዳ ክፍያ እና ለአዳዲስ ፐሮጀክቶች ማስፈጸሚ የሚያስፈልገውን የወጪዎች መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡ምክር ቤቱም በማዕቀፉ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል በማጽደቅ ስራ ላይ እንዲውል መወሰኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#ወርቃማ_ሕጎች
የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
#አእምሮህ_ማግኔት_ነው!
ሁልጊዜም አእምሮህ ማግኔት መሆኑን አስታውስ፡፡ አንተን የተቆጣጠሩህን ሃሳቦች እና በውስጥ የሰረፁትን እምነቶች የሚያምኑ እና የሚያስቡ ሌሎች ሰዎች ወዳንተ እንደሚያቀርብም ልብ በል፡፡
በትክክለኛ መንገድ የስበት ህግ (law of attraction) ብለን የምንጠራው አንድ ህግ አለ፡፡ ውሃ ከፍታውን የሚፈልግበት፣ በህዋ ውስጥ ያሉ ነገሮች ሁሉ የየራሳቸውን አምሳያ የሚፈልጉበት ህግ፡፡ ፕላኔቶችን በትክክለኛ ቦታቸው ጠብቆ እንደሚያቆየው የስበት ህግ፡፡
ይህ ህግ የሚለዋወጥ ቢሆን ኖሮ የማንጎ ፍሬ ከአበባው ውስጥ በርራ በፓፓያ አበባ ውስጥ በመግባት በከፊል ማንጎ፣ በከፊል ደግሞ ፓፓያ የሆነ ዛፍ ይፈጥሩ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ግን ሰምተን አናውቅም፡፡ ይሄንን የስበት ህግ ትንሽ በመከተል በሴቶች እና በወንዶች መካከል እንዴት እንደሚሰራ ማየት እንችላለን፡፡
ውጤታማና ሃብታም ወንዶች የሚፈልጓት ሴት የእነሱኑ አይነት ሴት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለ ወንድም እንደዚያው፡፡ ይህ የሚሆነው በተፈጥሮ ነው - ልክ ውሃ ወደ ታች እንደሚፈሰው፡፡
“ሁሉም አምሳያውን ይስባል” የሚለው አባባል የማይገሰስ ሀቅ ነው፡፡ አንድ ወንድ የሚፈልጋት ሴት በብዙ መልኩ እሱን የምትመስለውን ሴት መሆኑ እውነት ከሆነ፣ የምትፈልጋቸውን ሰዎች ለማሰብ የእነዚህን ሰዎች ሀሳቦች እና እምነቶች በመቆጣጠር እና በማዳበር ማግኔት የመስራትን ጥቅም ማየት አትችልም?
#ወርቃማው_ሕግ መጽሐፍ
በየመጽሐፍት መደብሩና አዟሪዎች እጅ ይገኛል።
*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram- https://tttttt.me/teklu_tilahun

በመጅሊስ የመተዳደሪያ ደንብ ላይ የጋራ መግባባት ተደረሰ!
በመጅሊስ የመተዳደሪያ ደንብ ላይ የተደረገው ውይይት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።በመጅሊሱ የመተዳደሪያ ደንብ ላይ ለአንድ ሳምንት ሲያካሂድ የቆየውን ውይይት በማስመልከት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ መግለጫ ሰጥተዋል።
በውይይቱ 23 ዑለማዎች መሳተፋቸውን ጠቅሰው በጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር በማድረግ የጋራ ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።በውይይቱም በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የክልል ዑለማ ተወካዮችና ከመጅሊስ ውጪ ያሉ ዑለማዎች እንዲወያዩበት ይደረጋል ብለዋል።
የዳዒ ተወካዮች፣ ወጣቶችና ሴቶች ጭምር በውይይቱ እንዲሳተፉ የሚደረግ መሆኑንም የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።ከረመዳን ፆም በኋላ ውይይቱ እንዲካሄድ ከስምምነት ላይ መደረሱን ጠቅሰው ከውይይቱ ቀጥሎ አስመራጭ ኮሚቴ በማቋቋም የመጅሊስ አባላት ምርጫ ይካሄዳል ብለዋል።በዚህም ለአንድነትና ለሰላም የሚሰሩ ተወካዮች መጅሊሳቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲረከቡ ይደረጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
"ሰላምና አንድነት ለሁላችንም ይበጃል" ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስ፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በመካከላችን ልዩነት አለመኖሩን ሊያውቀው ይገባል ብለዋል።ታላቁን የረመዳን ፆም በፍቅር፣ በእዝነት እና አብሮነት በመፆም ለማሳለፍ ሁላችንም ልንዘጋጅ ይገባል ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

አረብ ኢሚሬትስ 30 ቶን የምግብ እርዳታ ወደ ትግራይ ላከች!
አረብ ኢሚሬትስ እስካሁን 220 ቶን እርዳታ የጫኑ አውሮፕላኖች ወደ ትግራይ መላኳ ይታወቃል፡፡እርዳታው ጦርነቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል ያለውን ፍላጎት ለማሟላት ያለመ ነው፡፡
[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
አረብ ኢሚሬትስ እስካሁን 220 ቶን እርዳታ የጫኑ አውሮፕላኖች ወደ ትግራይ መላኳ ይታወቃል፡፡እርዳታው ጦርነቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል ያለውን ፍላጎት ለማሟላት ያለመ ነው፡፡
[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
ኤርትራ በኢትዮጵያ ላላት ኢምባሲ ቢኒያም በርሄን ጉዳይ አስፈጻሚ አድርጋ ሾማለች። በኤርትራ ኢምባሲ ለዓመታት ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት ቢኒያም የሹመት ደብዳቤያቸውን በዚህ ሳምንት ለውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አቅርበዋል። ኤርትራ ላለፉት 3 ዓመታት አምባሳደር ሠመረ ርዕሶምን በባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ወክላ የቆየች ሲሆን፣ በወሩ መጀመሪያ ላይ ግን አምባሳደሩ ቆይታቸውን አጠናቀዋል ተብለው ወደ አገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል። ኤርትራ የዲፕሎማቲክ ውክልናዋን ለምን ከአምባሳደር ወደ ጉዳይ አስፈጻሚ ዝቅ እንዳደረገች ወይም የጉዳይ አስፈጻሚው ሹመት ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ የኤርትራ መንግሥት ያለው ነገር የለም። ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ርምጃ ትወስድ እንደሆነ ዋዜማ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን ጠይቃ፣ ሚንስቴሩ በጉዳዩ ላይ ገና ውሳኔ አልተላለፈም ብሏል።
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
የጀጎል ግንብ አደጋ እንደተጋረጠበት የሐረሪ ክልል የባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ!
በሐረሪ ክልል የሚገኘው የጀጎል ግንብ እና በዙሪያው ያሉ በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶች ላይ አደጋ እንደተጋረጠ የሐረሪ ክልል የባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።
በዓለም ዐቀፍ የሳይንስ የትምህርት እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው እና አምስት መቶ ዓመት ገደማ ዕድሜ ያስቆጠረው የጀጎል ግንብ እና በዙሪያው የሚገኙ ቤቶች፣ በክረምት ወራት እንዲሁም በየወቅቱ በሚጥል ዝናብ ሳቢያ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው። እንዲሁም በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች በየወቅቱ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በሚያደርሱት ጉዳት ምክንያት ቅርሶቹ አደጋ እንደተጋረጠባቸው የክልሉ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ተወለዳ ሀዱሽ ገልጸዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ:
https://bit.ly/3K5xBU3

የፓኪስታኑን ፕሬዝዳንት ኢምራን ካሃንን ከስልጣን ለማንሳት የቀረበውን የመተማመኛ ድምጽ ማጣት (Vote of no confidence) ፓርላማው ውድቅ አድርጐታል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️
በኤሊያስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 350 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል!
ቃሊቲ ኢንዱስትሪ መንደር በኤሊያስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 350 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ላይ ውድመት መድረሱ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ትናንት ምሽት 3:15 ሰአት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታዉ ቃሊቲ ኢንዱስትሪ መንደር በኤሊያስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል።
“ከባለንብረቶቹ በደረሰን መረጃ መሰረት 350 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ላይ ወድመት ደርሷል” ብለዋል።
በፋብሪካዉ ያሉት የጨርቅ ማቅለሚያ ኬሚካሎችና በመጋዘን ዉስጥ የሚገኙ ጥሬ እቃዎች እሳቱ ፈጥኖ እንዲስፋፋ ከማድረጋቸዉም በላይ በፋብሪካዉ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ለመግባት አመቺ አለመሆኑ እንዲሁም ፋብሪካዉ ህንጻ ላይ መሆኑ እሳቱን በቀላሉ መቆጣጠር እንዳይቻል አድርጎታል ብለዋል።
በተከናወነው የአደጋ መቆጣጠር ርብርብ ከሌሊቱ 7 ሰዓት እሳቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ገልጸዋል።
የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር 15 የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች 6 ውሃ የጫኑ ቦቴዎች እንዲሁም 154 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተዋል፤ እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋትም 500 ሺህ ሊትር ውሃና 7 ሺህ 800 ሊትር ኬሚካል ፎም ጥቅም ላይ ውሏልም ብለዋል።
የእሳት አደጋዉ በአካባቢዉ ባሉ ሌሎች ፋብሪካዎች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል በዚህ ሂደትም 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የተገመተ ንብረት ማዳን መቻሉን ገልጸዋል።
አቶ ንጋቱ እንዳሉት፤ በአደጋ መቆጣጠሩ ሂደት የአየር መንገድና የደብረዘይት እሳት አደጋ ባለሙያዎች እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ የአዲስ አበባ መንገዶችና ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን 6 የውሃ ቦቴ በማቅረብ ተባብረዋል።
በሌላ በኩልም የጸጥታ አካላት አስፈላጊዉን ትብብር ማድረጋቸውን ገልጸው፤ በስራ ላይ በነበሩ ሦስት የፋብሪካዉ ሰራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰ መሆኑን ገልጸዋል።
Via EPA

ከአዋሽ 2 ወደ አሰላ የተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ በተፈፀመበት ዝርፊያ የኤሌክትሪክ ኃይል በከፊል ተቋርጧል።
በዶዶታ ወረዳ እና ጌራ ከተማ አቅራቢያ በተፈፀመው የምሰሶ አካላት ዝርፊያ ሁለት ምሰሶዎች በመውደቃቸው አሰላ ከተማን ጨምሮ በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች በከፊል ኤሌክትሪክ የኃይል ተቋርጧል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጥገና ቡድን ዝርፊያ ወደተፈፀመበት አካባቢ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ጥገናውን በፍጥነት ለመጀመር የሚያስችል አሰሳ እያካሄደ ነው፡፡ ጥገናው ከሳምንት ያላነሰ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተገምቷል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ዝርፊያ እየተደጋገመ ሲሆን ይህም ለኃይል መቋረጥ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ ያመለክታል።