YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በህዝብ ተወካዮች ምከር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ባለስልጣን በአዋጅ የተሰጠውን ኃላፊነት እና ስልጣን በአግባቡ እንዳልተወጣ ገለጸ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ፣ ጥራት እና ቁጥጥርን በተመለከተ የ2012 እና የ2013 በጀት ዓመት በክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ኃላፊዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ክርስቲያን ታደለ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ አለመሆኑን ጠቁመው÷ መስሪያ ቤቱ እስከ ሚያዚያ 8 ቀን ድረስ የኦዲት ሪፖርት ማስተካከያ እንዲያቀርብ አሳስበዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት እና ስልጠና ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አቅጣጫ መቀመጡንም ሰብሳቢው አስታውሰዋል፡፡የፌዴራል ሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን መርምሮ በሁለት ወራት ውስጥ ማቅረብ እንዳለበትም ነው ማሳሰቢያ የተሰጠው፡፡የፍትህ ሚኒስቴርም ከኦዲት ሪፖርቱ አንፃር በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የወንጀል ምርምራ በማድረግ የሁሉንም አፈጻጸም ሪፖርት በሁለት ወራት ውስጥ ለቋሚ ኮሚቴው እንዲያቀርብ ተጠይቋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ወይዘሮ አራሪ ሞሲሳ በበኩላቸው÷ የባስልጣን መስሪያ ቤቱ ኃላፊዎች የኦዲት ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ምላሽ ያልሰጡ መሆኑን ገልጸው፥ የተሰጣቸውን ስልጣንና ኃላፊነት በአግባቡ አልተወጡም ብለዋል፡፡በሌላ በኩል ትውልድን ለመቅረጽም ሆነ ለማበላሸት እድሉ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እጅ ላይ መሆኑ ታውቆ ችግሮች በትብብር እንዲፈቱ ሁለንተናዊ ጥረት መደረግ እንዳለበት ገልጸው÷ ከተቋሙ አመራሮችም ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ በኩል በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ፣ ክትትልና ቁጥጥር ረገድ ችግሮች የሚታዩበት መሆኑንም የቋሚ ኮሚቴው አባላት አንስተዋል፡፡ በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ባለስልጣን የትምህርትና ስልጠና ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ በበኩላቸው÷ተቋሙ የሰው ኃይል፣ የአደረጃጀት፣ የተሸከርካሪ እና የቢሮ ችግሮች እንዳሉበት መግለጻቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዓለም አቀፍ ለጋሾች ችግር ውስጥ ያለውን የአፋር ህዝብ አልፈው “ትግራይን እንርዳ” ማለታቸው አግባብ አይደለም-የአፋር ክልል

“የአፋር ሕዝብ እንደፍየል እና እንደዝንጀሮ በየቦታው ፈሶ እሱን ወደኋላ አድርገን የትግራይ ሕዝብ ብቻ ይረዳ የሚል ቋንቋ ትክክል” አይደለም ሲል የአፋር ክልል በዓለምአቀፍ ለጋሾች ላይ ቅረታውን አቅርቧል፡፡

የአፋር ጤና ቢሮ ኃላፊ ያሲን ሀቢብ እንደገለጹት በአፋር ክልል በርካታ ዜጎች በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው በየቦታው ነው ያሉት፡፡ የቢሮ ኃላፊው ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች በየቦታው እየወለዱ፤ ለውኃ ጥምና ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ተናግረዋል፡፡

ይህ ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፍ ለጋሽ አካላት በአፋር አልፈው ዕርዳታ ለትግራይ ሕዝብ ማድረስ እንደሚፈልጉም የቢሮ ኃላፊ ገልጸዋል፡፡ የትግራይ ሕዝብ ዕርዳታ ማግኘት እንዳለበትና መጎዳት እንደሌለበት እንደሚያምኑ የገለጹት ኃላፊው፤ አፋር ክልል ላይ በችግር ውስጥ የፈሰሰውን ህዝብ ጥሎ ማለፍ ግን አስቸጋሪ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ: https://am.al-ain.com/article/afar-region-decries-of-partiality-of-donors

@YeneTube @FikerAssefa
የተመድ የፍልሰተኞች ድርጅት አይኦኤም ከሳዑዲ ዓረቢያ በመመለስ ላይ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን መልሶ ለማቋቋም 11 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ በድረገጹ አስታውቋል። መንግሥት ተመላሾቹን መልሶ ለማቋቋም ዓለማቀፍ ለጋሾች የዕርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ መማጸኑን ድርጅቱ ገልጧል። በሳዑዲ ዓረቢያ እንደሚኖሩ ከሚገመቱት 750 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን 450 ሺህ ያህሉ በሕገወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ እንደገቡ ይገመታል። መንግሥት ትናንት በጀመረው ዜጎችን በአውሮፕላን የማጓጓዝ ጥረት 100 ሺህ ፍልሰተኞች ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
#ወደ_ሀብት_ጉዞ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች በሚለውና #አስበህ_ሐብታም_ሁን በሚል በተተረጎመው መጽሐፉ የምናውቀው የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ።

#ወደ_ሀብት_ጉዞ

ይህ ወደ ሀብት ጉዞ የተሰኘው መጽሐፍ እያንዳንዱን ሕልማችንንና ዓላማችንን ለማሳካት ያግዘናል፡፡

ብልፅግና በገንዘብና ዝና ብቻ የተገደበ ትርጉም እንደሌለው ያሳየናል፡፡ እውነተኛ ባለጸጋ ለመሆን በሁሉም የሕይወት ዘርፎች መበልፀግ ያስፈልጋል- በአካል፣ በመንፈስ፣ በገንዘብ፡፡

ለዚህም ደግሞ ከ25 ሺ በላይ ሰዎች የውድቀት ምክንያት፣ ከ500 በላይ ስኬታማ ሰዎች ምስጢርና የሀያ አምስት አመታት የምርምር ውጤት... ወደ #ሀብት_ጉዞ መጽሐፍን ፈጥሯል።

ከ60 ሚሊየን ኮፒ በላይ ከተሸጠው አስበህ ሀብታም ሁን መጽሐፍ ቀጥሎ ከፍተኛ ሽያጭን የተቀዳጀ መጽሐፍ።

እነሆ በሁሉም መልክ ወደ ሀብት ጉዞ!!
የናፖሊዮን ሂልን መጽሐፍ ይዞ!!!

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
በጂዳ እና አካባቢዋ ባሉ እስር ቤቶች ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገር ቤት የመመለስ ሥራ ዛሬ ይጀመራል!

ከጂዳ እና አካባቢ ባሉ እስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገር ቤት የመመለስ ሥራ ዛሬ እንደሚመለሱ ተገለፀ።በተጨማሪም 1 ሺህ 831 በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የነበሩ ዜጎች ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ከሳኡዲ አረቢያ ወደ አገር ቤት ለመመለስ ከታቀደው 102 ሺህ ዜጎች መካከል ከ80 ሺህ የማያንሱት የሚገኙት በጂዳ እና አካባቢ በሚገኙ እስር ቤቶች እና የማቆያ ማዕከላት ነው።

ዛሬ በሚደረጉ አራት በረራዎች ከጅዳ 1438 በሳኡዲ አረቢያ በእስር ቤቶች እና ማቆያ ማዕከላት ውስጥ የነበሩ ዜጎች ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።ከትላንት በስቲያ በጀመረው በሳኡዲ አረቢያ እስር ቤቶች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ሥራ፤ በአንድ ቀን ከሪያድ 936 ኢትዮጵያዊን ማምጣት የተቻለ ሲሆን ዛሬ ማለዳም 393 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውም ታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ 1,200 በላይ ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው አልተመለሱም ተባለ፡፡

ኢንዱስትሪ ፓርኩ በሕወሃት ታጣቂ ቡድን ከደረሰበት ውድመት ሙሉ በሙሉ ባለማገገሙ እና የአጎአ እድል በመሰረዙ በሥሩ ያሉ ኢንዱስትሪዎች በቀደመው አቅማቸው ልክ እያመረቱ አይደለም ተብሏል፡፡

በመሆኑም 1,214 የፓርኩ ሰራተኞች አሁንም ወደ ሥራ ገበታቸው እንዳልተመለሱ የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ሰኢድ ተናግረዋል፡፡

በፓርኩ ውስጥ ሥራ ላይ ካሉ ሼዶች መካከል በተለይ ካልሲ እያመረተ ወደ አሜሪካ ገበያ ይልክ የነበረው ፍአንላይ የተባለ የቻይና ኩባንያ ከጦርነቱ በኋላ አገግሞ ሥራ ቢጀምርም በጥቂቱ ብቻ እየሰራ በመሆኑ በርካታ ሰራተኞቹ ወደ ሥራቸው እንዳልተመለሱ ተሰምቷል፡፡

የወንዶች ሙሉ ልብስ እያመረተ ለአሜሪካ ገበያ የሚልክ የቻይና አሜሪካ ኩባንያ እና የሴቶች ቦርሳ እያመረተ እንዲሁ 95 በመቶ ለአሜሪካ ገበያ የሚያቀርብ ኩባንያ ሥራቸውን የተሻለ እየከወኑ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

ይሁንና አሜሪካ ለአፍሪካ አገራት ከሰጠቸው የቀረጥና ኮታ ነፃ እድል ኢትዮጵያን ማስወጣቷ ተከትሎ ሁለቱ ኩባንያዎች የገበያ ችግር እንደገጠማቸው ሸገር ከኩባንያዎቹ የስራ ኃላፊዎች ሰምቷል፡፡

የገበያው ሁኔታ ሲስተካከልና በፓርኩ ውስጥ እየሰሩ ያሉ ኩባንያዎች በህወሃት አማካኝነት ከደረሰባቸው ውድመት አገግመው በሙሉ አቅማቸው ማምረት ሲጀምሩ አሁን የተቀነሱ ከ1,200 በላይ ሰራተኞች ወደ ስራቸው ይመለሳሉ ተብሏል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራና አፋር ክልሎች የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችና የኦፕቲካል ፋይበር የጥገና ሥራ መጠናቀቁ ተገለፀ!

በአማራና አፋር ክልሎች በህወሃት ቡድን ከፍተኛ ውድመት አጋጥሞት የነበረውን የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችና የኦፕቲካል ፋይበር ገመዶች የመጠገን ሥራ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሰታወቀ።

በክልሎች የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ለመጠገን ለመለዋወጫ አቅርቦት የወጣውን ወጪ ሳይጨምር ለሥራው ብቻ ከ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉም ተገልጿል።

የኦፕቲካል ፋይበር መስመር ጥገናው በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ለተወሰኑ ሰዓታት ኤሌክትሪክ በማቋረጥ ሲሠራ ቆይቶ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገልጿል፡፡

ከደብረሲና – ሸዋሮቢት – ከሚሴ – ኮምቦልቻ – አቀስታ – ዓለም ከተማ ባለ132 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር፤ ከደብረብርሃን – ኮምቦልቻ – ሠመራ እና ከኮምቦልቻ – አላማጣ እስከ ቆቦ ድረስ ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር እንዲሁም ከደብረታቦር እስከ ጋሸና ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር በሚያልፍበት አካባቢ የሚገኙ ከተሞችና መንደሮች ላይ ከህዳር 24/2014 ጀምሮ በተደረገው ጥገና አካባቢዎቹ ኤሌክትሪክ መልሰው እንዲያገኙ መደረጉ ይታወሳል፡፡

ከደሴ – ወልዲያ የ ባለ 66 ኪሎ ቪልት መስመር ጥገና በማካሄድ የወልዲያና አካባቢው ኃይል እንዲያገኙ ተደርገዋል፡፡

የመልሶ ጥገና ሥራውን ከተቋሙ ስምንት ሪጅኖች የተውጣጣ የጥገና ቡድን በከፍተኛ ርብርብ ሲያከናውን መቆየቱም ተገልጿል፡፡

በአማራና አፋር ክልል የደረሰውን የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ለመጠገን ለመለዋወጫ አቅርቦት የወጣውን ወጪ ሳይጨምር ለሥራው ብቻ ከ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከማለዳው ጀምሮ በተደረጉ ሶስት በረራዎች በጠቅላላው 1173 ዜጎች አዲስ አበባ እስካሁን ገብተዋል።

የጅዳ ተመላሾች ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን በርኦ፣ የስደት እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ም /ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሃሰን፣ የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ፣ የዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ም/ ዋና /ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ገምበቶ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለገጣፎ ለገዳዲ ወደ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ!

ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው የምድብ ለ ሰንዳፋ በኬን 4-0 ያሸነፈው ለገጣፎ ለገዳዲ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የፕሪምየር ሊግ ተሳትፎን አረጋግጧል።

ምንጭ: Soccer Ethiopia
@YeneTube @FikerAssefa
የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ የበጀት ኮሚቴን ውሳኔ ኢትዮጵያ አትቀበልም - የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት

የአገልግሎቱ ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) ”የድርጅቱ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ቀደም ሲል ያቋቋመውን መርማሪ ኮሚቴ አልተቀበለችውም፤ አሁንም ውሳኔውን አትቀበልም” ሲሉ ለአሻም ነግረዋታል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ”በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ተፈፅመዋል የተባሉትን የመብቶች ጥሰት” እንዲያጣራ በተባባሩት መንግስታት በሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ለተቋቋመው መርማሪ ኮሚሽን ስራ ማስኬጃ ሊመደብ የታቀደውን በጀት ለማስቆም ኢትዮጵያ ጥያቄ ማቅረቧ ይታወቃል፡፡

በዚህም የድርጀቱ ጠቅላላ ጉባዔ የበጀት ኮሚቴ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም በጥያቄው ላይ ድምፅ ተሰጥቶበታል፡፡ 27 ሀገራት የኢትዮጵያን የበጀት ክልከላ ጥያቄ ሲደግፉ፣ 66 ሀገራት ተቃውመውታል፤ 39 ሀገራት ደግሞ ድምፅ ተዓቅቦ አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ይህ መርማሪ ቡድን በመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ሲቋቋም በብርቱ ተቃውሞት ነበር፡፡

ይህን ተቃውሞ የሚያስታወሱት የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሠ ቱሉ(ዶ/ር) ”የፖለቲካ አነሳሽነት ያለው፤ በሉዓላዊ አገር ጣልቃ እንደመግባት የሚቆጠር ነው፤ የከዚህ ቀደሙን የመንግስታቱ ድርጅትና የኢሰመኮን የጋራ ሪፖርት ዕውቅና ለመንፈግ ያለመ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Via Asham
@YeneTube @FikerAssefa
በህገወጥ መንገድ በተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ የማፍረስ እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ!

ከየካና ከለሚ ኩራ የፖሊስ አካላት ጋር በመተባበር በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ከተቋሙ ዕውቅና ውጪ በህገወጥ መንገድ የተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች ማፍረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት አስታውቋል።ያለ ተቋሙ እውቅናና ፈቃድ የተዘረጉት እነዚህ ህገወጥ መስመሮች፤ በገንዘብ ሲተመኑ በአጠቃላይ 133 ሺህ 334 ብር እንደሚገመቱ በዲስትሪክቱ የህግ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ እንዳልክ አንዳርጌ ገልፀዋል፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጎሮ ሰፈራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 6፣ አያት ፋኑኤል ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ 15፣ አያት ተክሉ ጋረዥ 3 እና አያት ዞን አካበቢ 1 በድምሩ 25 ምሶሶዎች መተከላቸውና በዚህም 960 ሜትር የሚረዝም የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመር መዘርጋቱን አቶ እንዳልክ ጠቁመዋል፡፡

ህገወጥ ድርጊቱ በምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ቁጥር 4 እና 9 ለቁጥጥር ስራ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እንደተገኘ የገለፁት ሥራ አስኪያጁ፤ እነዚህ ህገ-ወጥ ዝርጋታዎች በማን እንደተፈፀመ በግልፅ እንዳማይታወቅና የአካባቢው ነዋሪዎችም አናውቅም የሚል ምላሽ እንደሰጡ ተናግረዋል፡፡

ህገ-ወጥ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ዝረጋታ ማከናወን ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት ከማደናቀፍ በተጨማሪ ድረጊቱ ወንጀል መሆኑንና ከ5 አመት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት እንደሚያስቀጣ ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡

አቶ እንዳልክ አክለውም ደንበኞች አዲስ ቆጣሪ ለማግኘትም ሆነ ሌሎች አገልግሎቶችን ሲፈልጉ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉና መሰል አገልግሎት መስጠት የሚችለውም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ብቻ መሆኑን እንዲገነዘቡ እንዲሁም ራሳቸውንም ከህገ-ወጥ ደላሎች እንዲጠብቁ አሳስበዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
500 ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ የሰበአዊ ድጋፍ ትግራይ ክልል ደርሷል!

500 ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ በዛሬው እለት ትግራይ ክልል መድረሱን የአለም ምግብ ድርጅት ገለጸ።

ወደ ክልሉ በየብስ የሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ እንቅስቀሴ መጀመሩን ተከትሎ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል።

በዛሬው እለትም 500 ሜትሪክ ቶን አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ በድረጅቱ እና አጋር አካላቶች አማካኝነት ወደ ክልሉ መድረሱን እንዳስታወቀ ኢዜአ ዘግቧል።

መንግስት በትግራይ ክልል ያለው የሰብአዊ ድጋፍ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥል የግጭት ማቆም ውሳኔ ማድረጉና በየብስ የሚደረገው ድጋፍም እንዲቀጥል መወሰኑ ይታወቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#ወርቃማ_ሕጎች
የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

#አእምሮህ_ማግኔት_ነው!

ሁልጊዜም አእምሮህ ማግኔት መሆኑን አስታውስ፡፡ አንተን የተቆጣጠሩህን ሃሳቦች እና በውስጥ የሰረፁትን እምነቶች የሚያምኑ እና የሚያስቡ ሌሎች ሰዎች ወዳንተ እንደሚያቀርብም ልብ በል፡፡

በትክክለኛ መንገድ የስበት ህግ (law of attraction) ብለን የምንጠራው አንድ ህግ አለ፡፡ ውሃ ከፍታውን የሚፈልግበት፣ በህዋ ውስጥ ያሉ ነገሮች ሁሉ የየራሳቸውን አምሳያ የሚፈልጉበት ህግ፡፡ ፕላኔቶችን በትክክለኛ ቦታቸው ጠብቆ እንደሚያቆየው የስበት ህግ፡፡

ይህ ህግ የሚለዋወጥ ቢሆን ኖሮ የማንጎ ፍሬ ከአበባው ውስጥ በርራ በፓፓያ አበባ ውስጥ በመግባት በከፊል ማንጎ፣ በከፊል ደግሞ ፓፓያ የሆነ ዛፍ ይፈጥሩ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ግን ሰምተን አናውቅም፡፡ ይሄንን የስበት ህግ ትንሽ በመከተል በሴቶች እና በወንዶች መካከል እንዴት እንደሚሰራ ማየት እንችላለን፡፡

ውጤታማና ሃብታም ወንዶች የሚፈልጓት ሴት የእነሱኑ አይነት ሴት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለ ወንድም እንደዚያው፡፡ ይህ የሚሆነው በተፈጥሮ ነው - ልክ ውሃ ወደ ታች እንደሚፈሰው፡፡

“ሁሉም አምሳያውን ይስባል” የሚለው አባባል የማይገሰስ ሀቅ ነው፡፡ አንድ ወንድ የሚፈልጋት ሴት በብዙ መልኩ እሱን የምትመስለውን ሴት መሆኑ እውነት ከሆነ፣ የምትፈልጋቸውን ሰዎች ለማሰብ የእነዚህን ሰዎች ሀሳቦች እና እምነቶች በመቆጣጠር እና በማዳበር ማግኔት የመስራትን ጥቅም ማየት አትችልም?

#ወርቃማው_ሕግ መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና አዟሪዎች እጅ ይገኛል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram- https://tttttt.me/teklu_tilahun
ባልደራስ የታሰሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዋስትና መሻሩን ገለጠ!

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ሥር የዋሉና ትላንት ዋስትና ተፈቀዶላቸው የነበሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ ዋስትናቸው መሻሩን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ገለፀ።
ፓርቲው እንዳስታወቀው፦ ከአድዋ ድል ክብረ በዓል አከባበር ጋር በተገናኘ በእሥር ላይ ካሉት ወጣቶች መካከል የተወሰኑት ትናንት የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው የነበረ ቢሆንም፤ ዛሬ ተጨማሪ 10 ቀናት በእስር ቤት እንዲቆዩ ተወስኗል ብሏል።

በእነ ደረጀ ይበይን መዝገብ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩት የአዲስ አበባ ወጣቶች ትናንት በነበረው ችሎት የ7 ሺህ ብር ዋስ ተፈቅዶላቸው የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስ ከሰዓት በኋላ ይግባኝ በማቅረቡ ጉዳዩ ዛሬ ጠዋት መታየቱን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ተናግሯል።

ፖሊስ ተከሳሾችን የሚመለከት ምርመራ አለማጠናቀቁን፣ በምርመራ ሂደት ያገኛቸውን ማስረጃዎች በባለሞያዎች እያስተነተነ መሆኑን፣ ይህም ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑን በመግለጽ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል ያለው ፓርቲው፣ ትናንት የነበረው ችሎት የሰጠውን የዋስትና መብት አግባብ አይደለም በማለት መቃወሙንም ገልጿል፡፡

የተከሳሾች ጠበቆች እስረኞቹ ለ1 ወር የሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ እየተንገላቱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ፖሊስ በተደጋጋሚ የሚያቀርበው ምክንያትም ተመሳሳይ መሆኑ፤ ምርመራው ከልብ እየተሠራ አለመሆኑን እንደሚያመላክት ተናግረዋል። ጠበቆቹ የተከሳሾቹን በእስር መቆየት እንደማይፈልጉና የዋስትናው መብት ሊከበር እንደሚገባ ገልፀዋል ሲልም ፓርቲው የላከው መረጃ ያሳያል።

ግራ ቀኙን የተመለከተው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የሥር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን የዋስትና መብት በመሻር፣ ተከሳሾቹ ለተጨማሪ 10 ቀናት እሥር ቤት ሆነው ፖሊስ ምርመራውን እንዲያካሄድ ትዕዛዝ መስጠቱንም ፓርቲው አክሎ ገልጿል፡፡

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
1443ኛው የረመዳን ፆም ነገ ቅዳሜ መጋቢት 24  ይጀምራል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት እንደገለፀው፥  ጨረቃ ዛሬ ማምሻውን በመታየቷ ፆሙ ነገ ቅዳሜ ይጀምራል።የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኡስማን አደም  ፆሙ ነገ እንደሚጀምር ተረጋግጧል ብለዋል።ህዝበ ሙስሊሙም ፆሙን ሲያሳልፍ በተለመደው የመደጋገፍ የመረዳዳትና ባህል ሊሆን እንደሚገባ ምክር ቤቱ ገልጿል።

በተለይ በጦርነትና በድርቅ ከባድ ጉዳት ያስተናገዱ ብሎም የተፈናቀሉ ወገኖችን ማሰብ እጅጉን ሚያስፈልግበት ወቅት ነው ብለዋል።በሂጅራ አቆጣጠር 9 ኛው ወር ረመዳን በመላው አለም የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዬች በፃም እና ፀሎት የሚያሳልፉት ወር ነው።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት የቀጠናውን የጋራ ተጠባባቂ ኃይል እንዲያጠናክሩ ማሳሰባቸውን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ይህን የተናገሩት፣ ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሱማሊያ፣ ሱዳን፣ ኡጋንዳ እና ሌሎች አገራት ለተውጣጡ ወታደሮች እና ፖሊሶች በኬንያ በተሰጠው የ15 ቀን ሥልጠና ማጠናቀቂያ ላይ ነው። ኤታማዦር ሹሙ ተጠባባቂ ኃይሉ በቀጠናው ላሉት የጸጥታ ችግሮች የሚመጥን ዝግጅት እንዲያደርግ አሳስበዋል። ባሁኑ ወቅት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተጠባባቂ ኃይሉ አባል አገራት ኤታማዦር ሹሞችን ያቀፈው የጋራ ኮሚቴ የወቅቱ ሊቀመንበር ናቸው።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢራንን ከዩናይትድ ስቴትስ እና እንግሊዝ ጋር ያገናኘው የአለም ዋንጫ ድልድል ይፋ ሆኗል።

@YeneTube @FikerAssefa