YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አምባሳደር ድሪባ ኩማ እና ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ ሊያሰሙት የነበረው የመከላከያ ምስክርነት መብታቸው እንዲታለፍ ፍርድ ቤቱ አዘዘ።

የመከላከያ ምስክርነት መብታቸው እንዲታለፍ ትዛዙን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ሁለቱ ባለስልጣናት በሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው የመርከብ ግዢ ሙስና ክስ ላይ ምስክርነታቸውን ለማሰማት ጠኋት በነበረው ቀጠሮ ችሎት ተገኝተው የነበረ ሲሆን በድጋሚ ከሰዓት በኋላ እንዲቀቡ ተነግሯቸው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

ይሁንና ሁለቱ ባስልጣናቱ ከሰዓት በኋላ በድጋሚ ፍርድ ቤት የተገኙ ቢሆንም በተከሳሽ ጠበቆች በኩል ግን ጊዜው አጭር መሆኑን ጠቅሰው ተዘጋጅተው መከላከያ ምስክርነት ለማሰማት እንዲችሉ ለሌላ ጊዜ እንዲሰሙላቸው ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ከሳሽ ዓቃቢህግ በበኩሉ በጠበቆቹ የተጠየቀው ጥያቄ ምክንያታዊና አሳማኝ አለመሆኑን በመግለጽ ለምስክር በቂ ጊዜ ተሰቷል በተሰጣቸው ጊዜ የመከላከያ ምስክርነት ማሰማት እንዳልፈለጉ ተቆጥሮ የምስክርነት መብታቸው እንዲታለፍ ይታዘዝልኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የጠበቆችን ጥያቄና የዓቃቢህግን መቃወሚያ መልስ የመረመረው ፍርድ ቤቱ ጠበቆቹ መከላከያ ምስክር ለመስማት በተሰጠው ቀጠሮ ምስክር ለማሰማት እንዳልፈለጉ ተቆጥሮ የአንባሳደር ድሪባ ኩማ እና ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ ምስክርነት መብት ታልፎ ምስክርነታቸው ሳይሰማ እንዲቀር ፍርድ ቤት ትዛዝ ሰቷል።

Via Tarik Adugna
@YeneTube @FikerAssefa
ዩክሬን ሩሲያ ለዓመታት አጥብቃ ስትጠይቅ የነበረውን ጥያቄ ለማክበር መስማማቷ ተገለፀ!

የሩሲያ ልዑካን ቡድን መሪ ቭላድሚር ሜዲንስኪ እንዳሉት ዩክሬን የወደፊቱን ስምምነት ዋና መርሆች የያዘውን ረቂቅ አስረክባለች።

"ዩክሬን ማንኛውንም ህብረት ከመግባት ትታቀባለች።የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እና የውጭ ወታደራዊ ቡድንን አትተባበርም።የትኛውም  ወታደራዊ ልምምድ የምታደርገው የሩሲያ ፈቃድ ሲኖር ብቻ ነው።" ብለዋል።

"ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኪየቭ ባለስልጣናት ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል" ሲሉ መናገራቸውን ራፕትሊ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
#ወርቃማ_ሕጎች
የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

#አእምሮህ_ማግኔት_ነው!

ሁልጊዜም አእምሮህ ማግኔት መሆኑን አስታውስ፡፡ አንተን የተቆጣጠሩህን ሃሳቦች እና በውስጥ የሰረፁትን እምነቶች የሚያምኑ እና የሚያስቡ ሌሎች ሰዎች ወዳንተ እንደሚያቀርብም ልብ በል፡፡

በትክክለኛ መንገድ የስበት ህግ (law of attraction) ብለን የምንጠራው አንድ ህግ አለ፡፡ ውሃ ከፍታውን የሚፈልግበት፣ በህዋ ውስጥ ያሉ ነገሮች ሁሉ የየራሳቸውን አምሳያ የሚፈልጉበት ህግ፡፡ ፕላኔቶችን በትክክለኛ ቦታቸው ጠብቆ እንደሚያቆየው የስበት ህግ፡፡

ይህ ህግ የሚለዋወጥ ቢሆን ኖሮ የማንጎ ፍሬ ከአበባው ውስጥ በርራ በፓፓያ አበባ ውስጥ በመግባት በከፊል ማንጎ፣ በከፊል ደግሞ ፓፓያ የሆነ ዛፍ ይፈጥሩ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ግን ሰምተን አናውቅም፡፡ ይሄንን የስበት ህግ ትንሽ በመከተል በሴቶች እና በወንዶች መካከል እንዴት እንደሚሰራ ማየት እንችላለን፡፡

ውጤታማና ሃብታም ወንዶች የሚፈልጓት ሴት የእነሱኑ አይነት ሴት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለ ወንድም እንደዚያው፡፡ ይህ የሚሆነው በተፈጥሮ ነው - ልክ ውሃ ወደ ታች እንደሚፈሰው፡፡

“ሁሉም አምሳያውን ይስባል” የሚለው አባባል የማይገሰስ ሀቅ ነው፡፡ አንድ ወንድ የሚፈልጋት ሴት በብዙ መልኩ እሱን የምትመስለውን ሴት መሆኑ እውነት ከሆነ፣ የምትፈልጋቸውን ሰዎች ለማሰብ የእነዚህን ሰዎች ሀሳቦች እና እምነቶች በመቆጣጠር እና በማዳበር ማግኔት የመስራትን ጥቅም ማየት አትችልም?

#ወርቃማው_ሕግ መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና አዟሪዎች እጅ ይገኛል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram- https://tttttt.me/teklu_tilahun
ከሳኡዲ አረቢያ በሁለተኛ ዙር 438 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመለሱ!

በሳኡዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለሱ ሥራ ሙሉ በሙሉ መጀመሩን ተከትሎ፤ ዛሬ ከሰዓት በሁለተኛው ዙር በረራ 438 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ተመላሾቹ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል የሥራ ኃላፊዎች አምባሳደር ሲራጅ ረሺድ፣ መስፍን ገ/ማርያም፣ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አራርሳ ቢቂላ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሀና የሺንጉስ፣ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።ዛሬ ማለዳ በመጀመሪያ ዙር 498 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መግባታቸው ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች እና የአስተዳደር ሠራተኞች ዛሬ በአበል ክፍያ ላይ ቅሬታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመግለጽ ሲወጡ ጸጥታ ኃይሎች ወደ ግቢያቸው እንደመለሷቸው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ሠራተኞቹ ሰልፍ የወጡት፣ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ላደረጉት አስተዋጽኦ ቃል ከተገባላቸው አበል 34 በመቶው ስላልተከፈላቸው እንደሆነ ተናግረዋል። ቅሬታ አቅራቢዎቹ የ3 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ጭምር እንዳልተከፈላቸው እና የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት እንዳማረራቸው ገልጸዋል። ሚንስትሮች ምክር ቤት ለጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሠራተኞች ተጨማሪ አበል እንዲከፈላቸው በግንቦት 2012 ዓ፣ም ወስኖ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የአውሮፕላን ነዳጅ እጥረት መከሰቱ ተሰማ!

የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለ ሥልጣን የአውሮፕላን ነዳጅ ክምችት መጠን አስተማማኝ እንዳልሆነ ዋዜማ ሰምቻለሁ ብላለች። ይህንኑ ግምት ውስጥ በማስገባት ባለሥልጣኑ ሌሎች አየር መንገዶች ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከመብረራቸው በፊት ከሌላ አገር ነዳጅ እንዲቀዱ በመምከር ላይ ነው። ባለሥልጣኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች እንዳይስተጓጎሉ የተለያዩ ርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፣ ሆኖም ችግሩ በአጭር ጊዜ ይፈታል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል። በተያዘው ሩብ በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ካስገባችው 1 ሚሊዮን ቶን ነዳጅ ውስጥ የአውሮፕላን ነዳጅ 12 በመቶ ብቻ ነው።ሰሞኑን በበርካታ ከተሞች ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ተከስቷል።

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
አፋር ክልል ውስጥ የቀጠለው ጦርነት ባለፈው ሳምንት በታወጀው «የግጭት ማቆም» ውሳኔ ላይ አደጋ መደቀኑን ዲፕሎማቶች ተናገሩ።

ሮይተርስ የዜና ምንጭ እንደዘገበው ከሆነ አፋር ውስጥ ጦርነቱ መቀጠሉን ሁለት የሰብአዊ ርዳታ ሠራተኞች አረጋግጠዋል።በአፋር ክልል ስድስት ወረዳዎች በትግራይ ኃይላት መያዛቸውን ሮይተርስ አክሎ ዘግቧል።አቶ ሠዒድ ሙሳ ኢብራሒም የተባሉ የአፋር ኤሬፕቲ ጎሣ መሪ፦ «አፋር ውስጥ ጦርነቱ ቀጥሎ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ሠላም ሊኖር አይችልም» ሲሉ ለዜና ምንጩ ተናግረዋል። የአፋር ፖሊስ ኮሚሽነር አህመድ ሐሪፍ በበኩላቸው በትግራይ ኃይላት ተይዘዋል ካሉት ስድስት ወረዳዎች ሁለቱ ውስጥ ጦርነቱ መቀጠሉን፤ በክልሉ መዳረሻ ላይም «በከፍተኛ ኹኔታ» የትግራይ ኃይላት እየተበራከቱ መሆናቸውን አክለው ተናግረዋል።

የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ፦ በተጠቀሱት አካባቢዎች ውጊያ የለም ሲሉ ማስተባበላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። በአፋር ክልል አቅራቢያ ተዋጊዎቻቸውን እያሰፈሩ ነው ስለመባሉ ግን ማስተባበያ አልሰጡም ብሏል የዜና ምንጩ።ለሰብአዊ ርዳታ በሚል «የግጭት ማቆም» ውሳኔ በፌዴራል መንግሥት የታወጀው፤ ሕወሓትም ለዚያ ተገዢ እንደሚሆን የወሰነው ባለፈው ሳምንት ነበር። የፌዴራል መንግሥት ሰብአዊ ርዳታ ወደ ትግራይ ክልል እንዳያልፍ ሕወሓት መሰናክል ኾኗል ሲል ይከሳል። ሕወሓት በበኩሉ የተባለው የሰብአዊ ርዳታ አንዳችም ወደ ክልሉ አልገባም ሲል የፌዴራል መንግሥትን ተጠያቂ አድርጓል። በአፋር፣ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች በርካቶች ለብርቱ ረሐብ አደጋ መጋለጣቸው ይነገራል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
https://tttttt.me/sabinaadvisor

የስራ ጉዞ ወደ # Europe
#Schengen_visa

👉 የሚሰራበት አገር - geneva, Swaziland
👉 የስራው አይነት :- accounting
👉 የስራ ቀናት - 6 ቀናት/ week

👉 የወር ደሞዝ - €10000_13000 and more
👉 ፆታ - አይጠይቅም
👉 ዕድሜ - 25እስከ 45
👉 መኖሪያ ቤት - በነፃ
👉 ፕሮሰሱ የሚፈጀው ግዜ ከ 2 - 3 ወር ነው

#10 persons
#Requirements
👉 Passport
👉photo
👉Degree documents
👉Work experience
Contact:
@Sabinavisa
+251118683939
0936363639
0936363680
#ወደ_ሀብት_ጉዞ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

ቲንክ ኤንድ ግሮው ሪች በሚለውና #አስበህ_ሐብታም_ሁን በሚል በተተረጎመው መጽሐፉ የምናውቀው የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ።

#ወደ_ሀብት_ጉዞ

ይህ ወደ ሀብት ጉዞ የተሰኘው መጽሐፍ እያንዳንዱን ሕልማችንንና ዓላማችንን ለማሳካት ያግዘናል፡፡

ብልፅግና በገንዘብና ዝና ብቻ የተገደበ ትርጉም እንደሌለው ያሳየናል፡፡ እውነተኛ ባለጸጋ ለመሆን በሁሉም የሕይወት ዘርፎች መበልፀግ ያስፈልጋል- በአካል፣ በመንፈስ፣ በገንዘብ፡፡

ለዚህም ደግሞ ከ25 ሺ በላይ ሰዎች የውድቀት ምክንያት፣ ከ500 በላይ ስኬታማ ሰዎች ምስጢርና የሀያ አምስት አመታት የምርምር ውጤት... ወደ #ሀብት_ጉዞ መጽሐፍን ፈጥሯል።

ከ60 ሚሊየን ኮፒ በላይ ከተሸጠው አስበህ ሀብታም ሁን መጽሐፍ ቀጥሎ ከፍተኛ ሽያጭን የተቀዳጀ መጽሐፍ።

እነሆ በሁሉም መልክ ወደ ሀብት ጉዞ!!
የናፖሊዮን ሂልን መጽሐፍ ይዞ!!!

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram-
https://tttttt.me/teklu_tilahun
ለረጅም ጊዜ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር የነበሩት ኦቦ ገላሳ ዲልቦ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በገላሣ ዲልቦ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።ርዕሰ መስተዳድሩ በሀዘን መግለጫቸው “ኦሮሚያ ጠንካራ ሰው አጥታለች” ብለዋል።

“ገላሣ ዲልቦ የኦሮሞ ነፃነት ታጋይ ነበሩ” ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ ሙሉ ህይወታቸውን ለኦሮሞ ሕዝብ የገበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።በሀዘን መግለጫቸው ለኦሮሞ ሕዝብ በሙሉ ብርታትን እመኛለሁ ብለዋል።ኦቦ ገላሳ ዲልቦ የ1983 ሽግግር ወቅትን ጨምሮ ለረጅም ጊዜ የኦነግ ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሚስጥራዊና አገር አፍራሽ ስብሰባ አድርጓል ተብሎ ፈቃዱ የተሰረዘው የሰላምና ልማት ማዕከል ወደ ሥራ ተመለሰ!

ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተገናኘ በኅዳር ወር ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመተላለፍ የድርጅቱ የቦርድ አባላት፣ ‹‹በድብቅ አገርን ለማፍረስ›› ተንቀሳቅሰዋል በሚል ፈቃዱ ተሰርዞበት የነበረው በእነ ኤፍሬም ይስሃቅ (ፕሮፌሰር) የሚመራው ‹‹የሰላምና ልማት ማዕከል›› የተሰኘ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት፣ ፈቃዱ ታድሶለት ወደ ሥራ መመለሱ ታወቀ፡፡

ሪፖርተር ከኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰቦች ባለሥልጣንና ከሰላምና ልማት ማዕከል ያገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው፣ የድርጅቱ ፈቃዱ ከአንድ ወር በፊት ተመልሶለት ሥራውን ጀምሯል፡፡

በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰቦች ባለሥልጣን ተመዝግቦ በዴሞክራቲክ ግንባታ ሥራዎች ላይ እንደሚሠራ የተገለጸለት ይህ ተቋም፣ እንዲዘጋ ያደረገው ዋነኛ ምክንያት፣ የድርጅቱ ኃላፊዎች አገር አፍራሽ የሆነ ሚስጥራዊ ስብሰባ እንዳካሄዱ ከተገለጸ በኋላ ነበር፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ: http://bit.ly/3tPiqsp

@YeneTube @FikerAssefa
ለሀይማኖት ተቋማት የብሮድካስት ፈቃድ መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታወቀ!

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ከመጋቢት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሃይማኖት ተቋማት የብሮድካስት ፈቃድ መስጠት እንደሚጀመር የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መሀመድ እድሪስ አስታዉቀዋል።በ2012 ዓ.ም ማጠናቀቂያ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ላይ የዋለው የመገናኛ ብዙሀን ፖሊሲ የሀይማኖት ድርጅቶች ከሬዲዮ ሞገድ በስተቀር በሌሎች ማሰራጫ ዘዴዎች ፈቃድ አግኝተው አስተምህሮታቸውን ለተከታያቸዉ ማድረስ እንደሚችሉ አቅጣጫ ማስቀመጡን ተከትሎ ባለስልጣኑ ፈቃድ መስጠት መጀመሩ ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።ቀደም ብሎ የነበረው የብሮድካስት አዋጅ ለሀይማኖት ድርጅቶች የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ መስጠትን ይከለክል እንደነበር ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
በመቐለ የሚገኘው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በሳምንት ከ1 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች በነጻ ስልክ የማስደወል አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገለፀ!

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኘው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ቡድን በሳምንት ከ1 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች በነጻ ስልክ የማስደወል አገልግሎት በመስጠት ቤተሰቦቻቸውን ማናገር እንዲችሉ እያገዘ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኮሚቴው ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ ከጥር 2021 እስከ ጥር 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ በትግራይ ክልል ከቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው ለተነጣጠሉ 41 ሺህ 326 ሰዎች ነጻ የስልክ ማስደወል አገልግሎት መስጠቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ1,227 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ!

በኦሮሚያ ክልል በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 1,004 የትራፊክ አደጋዎች መከሰታቸውን በክልሉ ፖሊስ የትራፊክ ደህንነት እና ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ ሳጅን የባሌወርቅ ደጀኔ በተለይ ተናግረዋል፡፡

በደረሰዉ አደጋ 1,227 ሰዎች ህይወታቸዉን ሲያጡ፣1,019 ሰዎች ላይ ከባድ እና 850 ቀላል የአካል ጉዳት ተመዝግቧል፡፡፡እንዲሁም 3,096 የንብረት ውድመት የደረሰ ሲሆን ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ570 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚገመት ተገልፆል፡፡

ከደረሰዉ አደጋ ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበው በምስራቅ አርሲ፣ ምእራብ ባሌ፣ምስራቅ ሀረርጌ ፣ሰሜን ሸዋ ፣ ምስራቅ ወለጋ ዞኖች እና አዳማ፣ዱከም ፣ቡራዩ ፣ሰበታ ፣ ሱሉልታ፣ አምቦ እና ገላን ከተሞች ናቸው፡፡ 95 በመቶ የተከሰተው አደጋ የደረሰው በወንድ አሽከርካሪዎች መሆኑ ተገልፆል፡፡ እንዲሁም 90 በመቶ የሚሆነው አደጋ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የደረሰ ሲሆን 10 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሌሊቱ ያጋጠሙ መሆናቸው ተገልፆል።

ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ከፍጥነት ወሰነ በላይ ማሽከርከር እና የአሸከርካሪዎች ጥንቃቄ ጉድለት፣ ያለ እረፍት ማሸከርከር የአደጋዎቹ መንስኤዎች ስለመሆናቸዉ ሳጅን የባሌወርቅ ደጀኔ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
የነዳጅ ትራንስፖርት ባለንብረቶች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ የጊዜ ገደብ አስቀመጠ!

የማህበሩ አባላት ዛሬ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ባደረጉት ጠቅላላ ስብሰባ፣ በተደጋጋሚ መንግስት ቸልተኛ በመሆኑ የነዳጅ አመላላሽ ቦቴ ቁጥር ከ3500 በ20 እጅ ቀንሷል።ጅቡቲ ደርሶ መልስ 25000 ብር እየከሰሩ መሆኑንና ይኸም የሆነውም የብር ዋጋ በመውረዱና መለዋወጫ በመወደዱ መሆኑንም ተናግረዋል።በመሆኑም መንግስት በአስር ቀናት ውስጥ መፍትሄ የማይሰጣቸው ከሆነ የሥራ አድማ እንደሚጠሩ አስታውቀዋል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ፖሊስ በኹለቱ የአሶሴትድ ፕሬስ ጋዜጠኞች ላይ የጠየቀው ይግባኝ ውድቅ ተደረገበት!

የአሶሴትድ ፕሬስ ዘጋቢ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያ ቶማስ እንግዳ ላይ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን ይግባኝ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ። ፍርድ ቤቱ ይግባኙን ውድቅ ያደረገው “መርማሪ ፖሊስ ሥራውን በትጋት እያከናወነ ስለመሆኑ ጥርጣሬ ስላደረበት” መሆኑን ገልጿል።

የፌደራል ፖሊስ ይግባኝ የጠየቀው፤ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ መጋቢት 20 የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ነው። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ኹለቱ ጋዜጠኞች በ60 ሺህ ብር የዋስትና ገንዘብ ከእስር ወጥተው ጉዳያቸውን በውጭ እንዲከታተሉ ውሳኔ ሰጥቶ ነበር። ሆኖም ፖሊስ በውሳኔው ላይ ይግባኝ በመጠየቁ ጋዜጠኞቹ ከእስር ሳይፈቱ ቀርተዋል።

ምርመራውን እያከናወነ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ “ቀሪ ሥራዎች እያሉን ተጠርጣሪዎቹ በዋስትና እንዲወጡ መወሰኑ አግባብ አይደለም” በሚል የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሻር ያመለከተው ትላንት ረቡዕ መጋቢት 21 ነው። ፖሊስ በዚሁ ማመልከቻው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንዲፈቅድለትም ጠይቆ ነበር።

የጋዜጠኞቹ ጠበቆች በበኩላቸው፤ ፖሊስ ለተጨማሪ የምርመራ ቀናት መጠየቂያ የሚያቀርባቸው ምክንያቶች ተመሳሳይ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ፍርድ ቤቱም ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያጸና ጠይቀዋል።የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 22 በጽህፈት ቤት በኩል በሰጠው ውሳኔ የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።

“ተጠርጣሪዎቹ ከአራት ወራት በላይ በእስር ላይ ቆይተዋል ተብሎ ነው የሚታመነው” ያለው ፍርድ ቤቱ፤ ውሳኔውን የሰጠው “[በፖሊስ] ለተጨማሪ ጊዜ መጠየቂያ የሚቀርበው ምክንያት ተመሳሳይ ነው። ይህ መርማሪ ፖሊስ ሥራውን በትጋት እያከናወነ መሆኑን አጠራጣሪ ያደርገዋል” በሚል ምክንያት ነው።

ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔውን ከሰጠ በኋላ ጉዳዩን ከውጭ ሆነው ሲከታተሉ የነበሩ የጋዜጠኞቹ የትዳር አጋሮች እና ቤተሰቦቻቸው ደስታቸውን በእንባ ጭምር ሲገልጹ መስተዋላቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። በፍርድ ቤቱ በአካል ተገኝተው ሂደቱን የተከታተሉት ኹለቱ ጋዜጠኞችም ከውሳኔው በኋላ እርስ በእርስ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በደስታ ስሜት ተውጠው ሲተቃቀፉ መታየታቸውንም በዘገባው ተገልጿል።

አሚር አማን እና ቶማስ እንግዳ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ከአራት ወራት ህዳር 19፤ 2014 ነበር። የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት “የአሸባሪውን ሸኔ ቡድንን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ሥራ ሲሰሩ ነበር” በሚል ተጠርጥረው እንደሆነ ፖሊስ በወቅቱ ማስታወቁ ይታወሳል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል በአብኣላ መንገድ የሰብአዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዝ ተጀምሯል!

በዓለም ምግብ ድርጅት አማካይነት 21 ከበድ የጭነት መኪናዎች የእርዳታ እህል በመጫን በአፋር ክልል በአብኣላ መንገድ የሰብአዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ መጀመሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሰታወቀ። የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም የሰብአዊ እርዳታን ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩ የሚታወስ ነዉ፡፡

ዉሳኔዉ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ የመድኃኒት፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ገንዘብና አልሚ ምግቦችን ረጂ ድርጅቶች በቻሉት መጠን በአየር ትራንስፖርት በየእለቱ መጓጓዝ መጀመራቸዉንም ማሰወቃችን ይታወሰል፡፡በዛሬዉ ዕለት ደግሞ በዓለም ምግብ ድርጅት አማካይነት 21 ከበድ የጭነት መኪናዎች የእርዳታ እህል በመጨን በአፋር ክልል በአብኣላ መንገድ የሰብአዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዝ ተጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በተሟላ ሁኔታ ለማስኬድ ከተባበረና ባለድርሻ አካላት ጋር ለመስራት ዛሬም ቁርጠኛ መሆኑን በድጋሚ ያሳውቃል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#ወርቃማ_ሕጎች
የናፖሊዮን ሂል አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

#አእምሮህ_ማግኔት_ነው!

ሁልጊዜም አእምሮህ ማግኔት መሆኑን አስታውስ፡፡ አንተን የተቆጣጠሩህን ሃሳቦች እና በውስጥ የሰረፁትን እምነቶች የሚያምኑ እና የሚያስቡ ሌሎች ሰዎች ወዳንተ እንደሚያቀርብም ልብ በል፡፡

በትክክለኛ መንገድ የስበት ህግ (law of attraction) ብለን የምንጠራው አንድ ህግ አለ፡፡ ውሃ ከፍታውን የሚፈልግበት፣ በህዋ ውስጥ ያሉ ነገሮች ሁሉ የየራሳቸውን አምሳያ የሚፈልጉበት ህግ፡፡ ፕላኔቶችን በትክክለኛ ቦታቸው ጠብቆ እንደሚያቆየው የስበት ህግ፡፡

ይህ ህግ የሚለዋወጥ ቢሆን ኖሮ የማንጎ ፍሬ ከአበባው ውስጥ በርራ በፓፓያ አበባ ውስጥ በመግባት በከፊል ማንጎ፣ በከፊል ደግሞ ፓፓያ የሆነ ዛፍ ይፈጥሩ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ግን ሰምተን አናውቅም፡፡ ይሄንን የስበት ህግ ትንሽ በመከተል በሴቶች እና በወንዶች መካከል እንዴት እንደሚሰራ ማየት እንችላለን፡፡

ውጤታማና ሃብታም ወንዶች የሚፈልጓት ሴት የእነሱኑ አይነት ሴት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለ ወንድም እንደዚያው፡፡ ይህ የሚሆነው በተፈጥሮ ነው - ልክ ውሃ ወደ ታች እንደሚፈሰው፡፡

“ሁሉም አምሳያውን ይስባል” የሚለው አባባል የማይገሰስ ሀቅ ነው፡፡ አንድ ወንድ የሚፈልጋት ሴት በብዙ መልኩ እሱን የምትመስለውን ሴት መሆኑ እውነት ከሆነ፣ የምትፈልጋቸውን ሰዎች ለማሰብ የእነዚህን ሰዎች ሀሳቦች እና እምነቶች በመቆጣጠር እና በማዳበር ማግኔት የመስራትን ጥቅም ማየት አትችልም?

#ወርቃማው_ሕግ መጽሐፍ

በየመጽሐፍት መደብሩና አዟሪዎች እጅ ይገኛል።

*
ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram- https://tttttt.me/teklu_tilahun