ባሳለፈው ሳምንት ምግብና ነዳጅ ጭነው ወደ ትግራይ የተንቀሳቀሱ ከ20 በላይ ተሽከርካሪዎች በገጠማቸው ችግር ምክንያት መመለሳቸውን ተገለፀ!
ባሳለፈው ሳምንት ምግብና ነዳጅ ጭነው ወደ ትግራይ ተንቀሳቅሰው የነበሩ ከ20 በላይ ተሽከርካሪዎች በገጠማቸው ችግር ምክንያት መመለሳቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ዶ/ር ለገሠ ቱሉ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የትግራይ ኃይሎች በተቆጣጠሯቸው የአፋር ወረዳዎች በኩል የእርዳታ አቅርቦት ይዘው ወደ ትግራይ እንቅስቃሴ ጀምረው የነበረ ቢሆንም በህወሓት ኃይሎች ጉዟቸው መደናቀፉን ገልጸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሳለፈው ሳምንት ማብቂያ ማለትም ሐሙስ መጋቢት 8 ቀን 2014 የእርዳታ ምግብ እና ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ከሰመራ ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቀለ እየተጓዙ መሆናቸውን መግለፁ ይታወሳል።
በዚህም ወደ ትግራይ የተንቀሳቀሱት 20 የእርዳታ ምግብ እንዲሁም ሦስት ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መሆናቸውንና፣ በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ለማሟላትም በየቀኑ 40 መኪኖች የሰብዓዊ አቅርቦቶችን እንዲያጓጉዙ እንደሚደረግም ጨምሮ ገልጾ ነበር።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ኃላፊው ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከረዥም ጊዜ በኋላ ባለፈው ሣምንት 23ቱ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እንዲጓዙ የተደረገው፤ የህወሓት አማፂያን በአገር መከላከያ ሠራዊትና በአፋር ክልል ኃይሎች ስለተዳከሙ "መንገዱን ሊከፍቱ ይችላሉ የሚል ተስፋ ስለነበረ" ነው ብለዋል።
ምግብና ነዳጅ የጫኑት ተሽከርካሪዎች ሐሙስ ዕለት ወደ መቀለ ጉዞ ጀምረው እንደነበር ያስታወሱት ዶክተር ለገሠ፣ አብአላ - መቀለ ኮሪደር በሚባለው መስመር ላይ የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ከሄዱ በኋላ ተኩስ ስለተከፈተባቸው ለመመለስ መገደዳቸውን ገልፀዋል።
ዶክተር ለገሠ የህወሓት ኃይሎች በተደጋጋሚ መንገድ በመዝጋት ወደ ክልሉ እርዳታ እንዳይገባ ያደርጋሉ በማለት የከሰሱ ሲሆን፣ አክለውም "በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ሕዝብ የእርዳታ አቅርቦት ስላላገኘ በረሃብ አደጋ ላይ ነው በማለት ክስ ያሰማሉ" ብለዋል።
ኃላፈው አክለውም ለትግራይ ክልል ሕዝብ እርዳታ ለማቅረብ የህወሓት ኃይሎች መንገድ እንቅፋት መሆኑን አመልክተዋል።
"በተጨባጭ የእርዳታ መኪኖች ወደ ክልሉ እንዲገቡ መንገዱን ክፈቱ ሲባል አይከፍቱም" በማለት ለእርዳታ አቅርቦቱ መሠረታዊ ችግር የመንገድ መዘጋት መሆኑን አስረድተዋል።
ዶክተር ለገሠ ቱሉ ወደ መቀለ እንዲሄዱ ጉዞ ጀምረው የነበሩት የእርዳታ አቅርቦት የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመነጋገር በዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች አማካኝነት የቀረቡ መሆናቸውን አመልክተዋል።መንግሥት ለእርዳታ አቅርቦቱ መስተጓጎል ምክንያት ነው ካለው ህወሓት በኩል ቢቢሲ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ማድረጉን ገልፆ፤ ጥረቱ እንዳልተሳካለትም በዘገባው አመላክቷል።
[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa

👍1
የብልፅግና ፓርቲ ድህር ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎች መድረክ መካሄድ ጀምሯል።
በፕሮግራሙ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ እንዲሁም የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሣህሉ ተገኝተዋል።
በመድረኩ የከተማና የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች የሚሳተፉበት ሲሆን ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ህዝብ መዝሙር በመዘመር ተጀምሯል።
መረጃው በብልጽግና ፓርቲ የባህር ዳር ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ነው

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለከተሞችና ወረዳዎች ህዝባዊ ውይይት ተጀምሯል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በ120 ወረዳዎች በ11 ክ/ከተሞችና በከተማ ደረጃ አንድ መድረክ በሁሉም የከተማዋ የአስተዳደር እርከኖች የህዝብ ውይይት መድረኮች ጀምረዋል፡፡
በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚካሄደው ህዝባዊ ዉይይት ህዝቡ በቀጥታ ፊት ለፊት ከፓርቲና ከመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር የሚገናኝበትና ስለአዲስ አበባ ችግሮች የሚመክርበት መድረክ ነው፡፡
በአጠቃላይ በዛሬው ዕለት በከተማችን በሚከናወነው ህዝባዊ ውይይት ከሚወሰደው ግብአት መነሻነት በመጪው ግዜ መንግስት በማህበራዊ፤ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች በቅደም ተከተል መተግበር የሚኖርባችወ የከተማችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚረዱ በርካት ግብአቶች ከህዝብ ይሰበሰባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የከተማውን መድረክ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባና ብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እንዲሁም አቶ አደም ፋራህ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳንት በጋራ እየመሩት ይገኛል፡፡
(ከንቲባ ፅ/ቤት)

የመገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ለ ‘ዘ ኢኮኖሚስት’ ዘጋቢው ቶማስ ጋርድነር ማስጠንቀቂያ ሰጠ!
የኢፌዲሪ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን ‘ዘ ኢኮኖሚስት’ ለተሰኘው ጋዜጣ የኢትዮጵያ ዘጋቢ ቶማስ ጋርድነር የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሰጠ።
“መጋቢት 10 ቀን በትዊተር ገፁ ያሰፈረው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሕወሓት መሪ ጋር ተነጋገሩ” በማለት በግል የትዊተር ገፁ ያሰራጨውን መረጃ የተመለከተው ባለስልጣኑ፤ የቶማስ ጋርድነር መረጃ ጥንቃቄ የሚፈልግ ሀገራዊ ጉዳይ ሲሆን ተገቢውን የመረጃ ምንጭ ያልጠቀሰ እና በሚመለከተው ባለስልጣን ያልተደገፈ ነው ብሏል።
ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው “ይህ ተግባር የጋዜጠኛነትን ሙያ እና ንቃት የማይመጥን” በመሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል። በቀጣይ ዘገባዎቹም ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጋዜጣኛውን አስጠንቅቋል።
[Addis Zeybe]

ከትግራይ ወደ አማራ ክልል በመግባት ላይ ያሉ ተፈናቃዮች በአንድ መጠለያ እንዲሰፍሩ ሊደረግ ነው!
ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው ወደ ሰሜን ወሎ ዞኖች በመግባት ላይ ያሉ ዜጎችን በአንድ መጠለያ ለማስፈር እንቅስቃሴ መጀመሩ ተነገረ፡፡ ተፈናቃዮቹን በአንድ መጠለያ ጣቢያ ለማስፈር ቦታ መረጣው ተጠናቆ ዝግጅቱ በመገባደድ ላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለሪፖርተር እንደተናገረው ከሆነ ለረድዔት አቅርቦት አመቺነትና ለፀጥታ ሥጋት ሲባል በራያ ቆቦ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች የተጠለሉ ከ56 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮችን በአንድ መጠለያ አሰባስቦ ለማስፈር፣ ቦታ መረጣው ተጠናቆ ዝግጅት በመደገባደድ ላይ ይገኛል ብሏል፡፡
አቶ ደበበ ዘውዴ የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እንደገለጹት ከሆነ፣ ከትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በርካታ ቁጥር ያለው ተፈናቃይ እየገባ ይገኛል፡፡ ለእነዚህ ተፈናቃይ የኅብረተሰብ ክፍሎች አሁን ላይ ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕርዳታዎችን፣ የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እያቀረበ እንደሚገኝ ነው የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ያመለከቱት፡፡ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ እንደሚሄድ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ለረድዔት አቅርቦት አመቺነት እንዲሁም ለሚፈጠር የፀጥታ ሥጋት ሲባል ተፈናቃዮቹን በአንድ መጠለያ አሰባስቦ ማስፈር አማራጭ ሆኖ መቅረቡንና ወደ ሥራ መገባቱን ነው ኃላፊው ያመለከቱት፡፡
Via Reporter

በዋግኽምራ በምግብ እጦት የተነሳ ህፃናት ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸው ተሰማ!
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሁለት ወረዳዎች እና የተለያዩ ቀበሌዎች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪው ተብሎ የተፈረጀው የህወኃት ቡድን ባደረሰው ጥቃት ወደ ሰቆጣ እና ዝቋላ ከተማ በርካታ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል።
በዚህም የተነሳ ህፃናቶች ተጨማሪ ምግብ በበቂ ሁኔታ ባለማግኘታቸው በከፍተኛ ደረጃ በምግብ እጦት እየተሰቃዩ መሆኑን የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የኮምኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ ከፍያለው ደባሱ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡በአሁኑ ሰዓት በአቅራቢያው በሚገኝ ጤና ጣቢያ ውስጥ በበሽታ እና በምግብ እጥረት ጉዳት ደርሶባቸው ህፃናት ህክምና እተደረገላቸው ይገኛል።
ከግጭት ነፃ ባልሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ ህፃናትን ያሉበትን ሁኔታ መመልከት እንዳልተቻለ አንስተዋል።እስካሁን በቁጥር ምንያህል ህፃናቶች እንደተጎዱ ባይገለፅም ከ5 ዓመት በታች ያሉ 1,230 ህፃናት በልዩ ሁኔታ እንክብካቤ ማግኘት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ በዋግ 61,668 ተፈናቃዮች ያሉ ሲሆን በእድሜ ከፍ ላሉ ሰዎች የተለያዩ የምግብ እርዳታ እየተደረገ ይገኛል፡፡ሆኖም ተፈናቃዮቹ በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን መብራት ባለመኖሩ የሚያገኙት አብስለው፣ ፈጭተው ለመብላት በመቸገራቸው ለረሀብ አደጋ እየተጋለጡ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
እንጀራ በመግዛት ለወር የተሰጣቸውን እህል ለቀን እንዲጠቀሙ ማስገደዱን አንስተዋል።በመሆኑም መንግስትም ሆነ መንግሰታዊ ያልሆነ ማንኛውም አካል ድጋፍ ማድረግ አለበት ሲሉ አቶ ከፍያለው ደባሱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Via Bisrat FM/ዳጉ ጆርናል

የአፍሪቃ ቀንድን በመታዉ ድርቅ ለረሐብ ለተጋለጠዉ ሕዝብ መርጃ የሚዉል ገንዘብ ካልተገኘ ከፍተኛ ሰብአዊ ድቀት ሊከሰት እንደሚችል ኦክስፋም አስጠነቀቀ።
ኢትዮጵያን፣ ሶማሊያንና ኬንያን በመታዉ ድርቅ 13 ሚሊዮን ሕዝብ ለረሐብ መጋለጡን የተባበሩት መንግስታት የምግብ ድርጅት (WFP) ካስታወቀ ሁለት ወር ሊደፍን ነዉ።ድርጅቱ እንዳስታወቀዉ ለረሐብ ለተጋለጠዉ ሕዝብ መርጃ የሚዉል የምግብ እሕል መግዢያ 6 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገዋል።የብሪታንያዉ ግብረ ሰናይ ድርጅት ኦክስፋም ትናንት እንዳስታወቀዉ ለርዳታ ከተጠየቀዉ ገንዘብ እስካሁን የተገኘዉ 3 ከመቶ ብቻ ነዉ።የኦክስፋም የበላይ ኃላፊ ጋብርኤላ በቸር እንዳሉት ባሁኑ ወቅት ምስራቅ አፍሪቃ በዓለም አቀፉ መድረክ ርዕስ አለመሆኑ «ጨካኝ» ሐቅ ነዉ።
ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በተለይም ምዕራቡ ዓለም ሙሉ ትኩረቱን በዩክሬኑ ጦርነት ላይ በማድረጉ ሌሎች በርካታ ሰብአዊና ፖለቲካዊ ቀዉሶች እየተዘነጉ ነዉ።የኦክስፋም የበላይ ኃላፊ እንደሚሉት ምሥራቅ አፍሪቃን የመታዉ ድርቅ በመዘንጋቱ በያዝነዉ የጎርጎሪያኑ 2022 በብዙ መቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች በረሐብ ሊሞቱ አይገባም።
በቸር እንደሚሉት ባሁኑ ወቅት ድፍን ዓለም «የተቃጠለች» ያክል ስሜት ቢኖርም ለጋሾች ሰብአዊ መብትንና ሰብአዊ ቀዉስን በመከላከሉ ረገድ አንዱን ከሌላዉ ሊመርጡ አይገባም።በተለይ ሶማሊያ ዉስጥ ከተደጋጋሚዉ ድርቅና ዓመታት ካስቆጠረዉ የፀጥታ መታወክ ያላገገመዉ አካባቢ በመራቡ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ገበሬዎችና አርብቶ አደሮች ከየቀያቸዉ ሲፈናቀሉ፣ ሕጻናትና አቅመ ደካሞች በረሐብ እየተሰቃዩ ነዉ።እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ2011 የአፍሪቃ ቀንድን በመታዉ ረሐብ ሶማሊያ ዉስጥ ብቻ ከ250 ሺሕ በላይ ሕዝብ አልቋል።
Via DW

ሰነድ አልባ ስደተኞችን እንዳይቀጥሩ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ትእዛዝ ሰጠ::
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት በሀገሪቱ የሚገኙ ኩባንያዎች ሰነድ አልባ ስደተኞችን እንዳይቀጥሩ፣እንዲሁም የሰራተኞቻቸውን ሰነድ በጥንቃቄ መመርመር እና መያዝ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡በደቡብ አፍሪካ ከ2.9 ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች እንደሚኖሩ የተነገረ ሲሆን ከነዚህ መካከል 10 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው የተሟላ ሰነድ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡
ከሰሞኑ በሀገሪቱ ጽንፍ የረገጡ ደቡብ አፍሪካዊያን ” መጤ “ ናቸው ባሉዋቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች ከሀገራችን እንዲወጡ ሲሉ ተቃውሞ ማሰማት መጀመሩ ይታወሳል፡፡በሀገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት አላቸው የሚባሉት እነዚህ ዜጎች “ዱዱላ ንቅናቄ” እና “ዱዱላ ጆሀንሰበርግ “የሚል ቡድን አደራጅተው ተቃውሞአቸውን በመንግስት ላይ እያሰሙ የሚገኙት፡፡
እነዚህ ቡድኖች ዋነኛ ፍላጎታቸው በመጤዎች የተያዘው የንግድ ስርአት ለደቡብ አፍሪካ ዜጎች ይመለስ የሚል ነው፡፡እንደዚሁም ” መጤዎች” ቀጥረው የሚያሰሩ በአነስተኛ ዋጋ ነው የሚሉት እነዚህ ቡድኖች በሀገራችን ሀብት የበይ ተመልካች መሆን የለብንም ይላሉ፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት የቡድኖችን እንቅስቃሴ ለመቀልበስ እና ጥያቄያቸውንም በተወሰነ መልኩ መመለስ እንዲያስችላቸው የወሰኑት ውሳኔ ግን በበርካቶች ዘንድ ተቃውሞ ተነስቶበታል፡፡አፍሪካ ሀገር ሆና ለአፍሪካዊያን ያልተመቸች ሀገር እያሉ በሀገሪቱ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ስደተኞች ተቃውሞአቸውን የገለጹ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ በሀገሪቱ የተጀመረውን ተቃውሞ ለማብረድ የወሰኑት ውሳኔ ሳያስቡት ሌላ መዘዝ አስከትሎባቸዋል ሲል የዘገባው አፍሪካ ኒውስ ነው፡፡
✍️Ethio FM

የሮታ ቫይረስ በኩርሙክ ፤በሸርቆሌ ወረዳ እና አሶሶ ከተማ መከሰቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቫይረሱ በአብዛኛው ህጻናት ላይ የሚከሰትና ለሞት የሚዳርግ በመሆኑ ህብረተሰቡ የአካባቢውንና የግል ንጽህናውን በአግባቡ መጠበቅ እንዳለበት ቢሮው አሳስቧል፡፡በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች አስተዳደር ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ፍቃዱ አያሌው እንዳሉት የሮታ ቫይረስ በክልሉ ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ መከሰቱን ገልጸው ቫይረሱ ትኩሳት፣ ማስመለስ ምልክት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
የሮታ ቫይረስ ከግል እና ከአካባቢ ንጽህና ጉድለት ጋር ተያይዞ የሚከሰት በመሆኑ ህብረተሰቡ የግሉንና የአካባቢውን ንጽህና እንዲጠብቅ የሚያስችል የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን በጤና ባለሙያዎች እየተከናወነ ነው ብለዋል።በሽታው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያጠቃ ቢሆንም ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናትን ለከፋ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን ያስታወቁት አቶ ፈቃዱ በንክኪ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ቫይረሱ በክልሉ ሞቃታማ በሆኑ አካባቢዎች ላይ በየዓመቱ እየተከሰተ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ቢሮው በሽታው የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ህመምተኞች የከፋ ጉዳት እንዳይደርስባቸው በጤና ተቋማት አስፈላጊ ግብዓቶችን የማሟላት እና በጤና ባለሙያዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የገለጹት ተወካዩ አብዛኞቹ ከህመማቸው እያገገሙ መሆኑ ታውቋል፡፡በሽታው ጥንቃቄ ካልተደረገ ለሞት የሚዳርግ በመሆኑ ህብረተሰቡ የህጻናትንና የራሳቸውን ንጽህና በአግባቡ በመጠበቅና በሽታው ሲከሰት ቶሎ ወደ ህክምና መሄድ እንዳለባቸው ቢሮው አስታውቋል ሲል የዘገበው ከክልሉ መገናኛ ብዙሀን ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ!
አቶ ተወልደ ከኃላፊነታቸው በይፋዊ መንገድ የለቀቁት ከጤናቸው ሁኔታ ጋር በተገናኘ እንደሆነ ታማኝ ምንጮች ለኢትዮ ንግድና ኢንስትመንት መድረክ ተናግረዋል፡፡
ከስድስት ወራት ላለፈ ጊዜም አቶ ተወልድ ህክምናቸውን በአሜሪካ እየተከታተሉ እንደሆነም ይታወቃል፡፡አቶ ተወልደ አየር መንገዱን በዋና ሥራ አስፈፃሚ አሥፈፃሚነት የመሩ ሲሆን፤ ለ37 አመታትም አየር መንገዱን አገልግለዋል፡፡
ምንጭ- ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ

ትምህርት ሚኒስቴር የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ቅሬታን ተቀብሎ እንዲፈታ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ!
ትምህርት ሚኒስቴር የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ቅሬታን ተቀብሎ እንዲፈታ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ።የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን አስመልክቶ ከተፈታኝ ተማሪዎች ቅሬታ እንደቀረበለት ገልጿል።
ተቋሙ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን አስመልክቶ ለተቋሙ የቀረቡ ጥቆማዎች እና በተለያዩ ሚዲያዎች ጉዳዩን አስመልክቶ የቀረቡ ዘገባዎችን መነሻ በማድረግ ጉዳዩን መርምሬያለሁ ብሏል።
በተደረገው ምርመራ መሰረትም የፈተናዎች ኤጀንሲ የፈተና እርማትን አስመልክቶ ተማሪዎች ያቀረቡትን ቅሬታ በመቀበል ምላሽ መስጠቱን የገለጸ ቢሆንም የተቋሙ መርመሪዎች ለምርመራ ስራ በኤጀንሲው በተገኙበት ወቅት በርካታ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለማቅረብ በኤጀንሲው ቢገኙም ወደ ውስጥ ገብቶ ቅሬታን ለማቅረብም ሆነ ቅሬታቸውን ተቀብሎ ሊያስተናግዳቸው አልቻለም ተብሏል።

Forwarded from YeneTube
The Right Time,
The Right Moves!
Join The Global Education Expo Today.
www.backtoschoolafrica.com
List of Exhibitors:
Schools & Colleges/Universities
School Management Solution Providers
Software developers
App developers & Coders
Start-ups & TECH Entrepreneurs
Education Consultants
STEM Education Incubators,
Digital Service Providers
Education Material Producers & Suppliers
Digital Libraries
NGOs & related.
To Reserve Your Booth:
Call us:
+251 974 0820 36
+251 974 0820 37

⬆️⬆️
#NewsAlert
የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንትና ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ።
የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት የቀድሞው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ተነስተው በምትካቸው የአየር መንገዱ ቦርድ አባል የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ ተሹመዋል።አቶ ግርማ ዋቄ ከቦርድ ሰብሳቢነታቸው በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ መመደባቸውንም ምንጮቹ ገልጸዋል።
አቶ ግርማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመደቡት ለአንድ ዓመት ብቻ እንደሆነና ዋና ተልእኳቸውም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የተረጋጋ የማኔጅመንት ቡድን መገንባት እንደሆነ ታውቋል።በአዲሱ የድርጅቱ አወቃቀር መሠረት፣ ከፕሬዚዳንቱ ስር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስፈጻሚ ሊኖር እንደሚችል ምንጮቹ ገልጸዋል።
አቶ ግርማን የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አድርጎ የመደባቸው በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እንደሆነ ምንጮች ገልጸዋል።የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ማሞ ምህረቱ መረጃውን እንዲያረጋግጡ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
የአቶ ግርማ ዋቄ ሹመት ከመሰማቱ አስቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን መዘገቡ ይታወሳል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡
አቶ ተወልደ በህክምና ላይ ባሉበት አሜሪካን አገረ ሆነው ለተቋሙ ማኔጅመንት በላኩት የኢሜል መልእክት፣ በገጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በኃላፊነት መቀጠል እንዳልቻሉ ጠቅሰው፣ በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው በጡረታ መገለላቸውን አሳውቀዋል።
አቶ ተወልደ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚነትን የተረከቡት ከአቶ ገርማ ዋቄ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ በአየር መንገዱ በተለያዩ ኃላፊነቶች ለ37 ዓመታት አገልግለዋል፡፡በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ አባላት ስብሰባ ላይ መሆናቸውን የጠቀሱት ምንጮቹ ፣ በዚህ ስብሰባ ለአየር መንገዱ አዲስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ምደባ ሊወሰን እንደሚችል ጠቁመዋል።