YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሽኝት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሽኝት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡

በሽኝት መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፣ ብፁዓን አባቶች እና የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እጅግ አሰቃቂና ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ መንግስት ገለፀ!

ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ እጅግ አሰቃቂ እና ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ መንግስት ገለፀ።
 
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ሰሞኑን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ እጅግ አሰቃቂ እና ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ ድርጊት መፈጸሙን አንስቷል።
 
በማህበራዊ ትስስር ገፆች በተንቀሳቃሽ ምስል ሲዘዋወር በቆየው እጅግ አሰቃቂ ድርጊት ንፁሃን ዜጎች በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ ሲደረግ መታየቱ በመግለጫው ተመላክቷል።
 
ይህ ድርጊት ከኢትዮጵያዊነት ባህል፣ እሴትና ከማንኛውም የሰብዓዊነት እሳቤ ያፈነገጠና እጅግ አሰቃቂ ወንጀል ነው ያለው አገልግሎቱ፥ ይህ እኩይ ድርጊት መጠፋፋትን ያፈጥን ካልሆነ በቀር ሰላምንም ሆነ ፍትህን እውን ሊያደርግ እንደማይችልም አስገንዝቧል።

በመሆኑም ድርጊቱ ሊኮነንና ሊወገዝ ይገባል፤መነሻቸውም ሆነ ማንነታቸው ምንም ይሁን ምን መንግስት ይህን አይነት ፍፁም ከሰብዓዊነት የራቀና ጭካኔ የተሞላበትን ድርጊት የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።
 
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ህገወጥነት ለመቆጣጠርና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከልም ከክልሉና ከመላው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን እየተሰራ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
 
የንፁሃን ዜጎችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላትን መንግስት ከዚህ በኋላ አይታገስም ያለው መግለጫው÷እነዚህ በወንጀል ስራ ላይ የተሰማሩና የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላት ከወዲሁ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም በጥብቅ አሳስቧል።
 
@YeneTube @FikerAssefa
የሕንድ ጦር በስህተት ወደ ፓኪስታን ሚሳየል መተኮሱን አመነ፡፡

የሕንድ የመከላከያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሚሳየሉ በስህተት በመተኮሴ አዝኛለሁ ማለቱን ዴይሊ ሞኒተር ፅፏል፡፡ቀደም ሲል የፓኪስታን ጦር ወደ አገሪቱ የተወነጨፈውን ተምዘግዛጊ በሚመለከት ሕንድን ማብራሪያ ለመጠየቅ እንዳላረፈደ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ሕንድ እና ፓኪስታን ግንኙነታቸው በቋፍ ላይ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡አነስተኛዎቹን ቁርቋሶዎች ሳይጨምር ሁለቱ አገሮች በመካከላቸው ቢያንስ 3 ታላላቅ ጦርነቶችን ማድጋቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡በተለይም በካሽሚር ግዛት ጉዳይ ስሜተ ስሱዎች ናቸው ይባላል፡፡

Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ከነ ቀኖናዋ፣ ከነ ትውፊቷ እና ማንነቷ ለትውልድ እንድትሸጋገር በታማኝነት አገልግለዋል-ጠ/ሚ ዐቢይ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚያምኑትን አምላክ እና የሚወዷትን ቤተክርስቲያን በታማኝነት ያገለገሉ አባት ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
 
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስክሬን የሽኝት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።በሽኝት መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፣ብፁዓን አባቶች እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሽኝት መርሃ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት፥ “አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እንደ ጥሩ አባት ሩጫቸውን ጨርሰው ወደ ሚወዱት አባታቸው ሄደዋል” ብለዋል፡፡“አባታችን እድለኛ ናቸው፤ እድሜያቸውን በሙሉ የሚወዷት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን በታማኝነት አገልግለዋል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡
 
ብፁዕነታቸው መናገር ሲገባቸው ተናግረው፤ መጸለይ ሲገባቸው ጸልየው፤ መምከር ሲገባቸው መክረው ፤ በአርምሞ እና በጸጥታ መኖር ሲገባቸው እንዲሁ አድርገው በብዙ ያስተማሩን አባት ናቸውም ብለዋል፡፡“አባታችን በጸሎት እና በምክር ያግዙኝ ነበር” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፥ ሃሳባቸውንም በጹሑፍ በተደጋጋሚ ልከውልኛል ብለዋል፡፡
 
“ከአባታችን ልንማር የሚገባን ኦርቶዶክስ ከነ ቀኖናዋ፣ ከነ ትውፊቷ እና ማንነቷ ወደ ትውልድ እንድትሸጋገር ከግጭት እርስ በርስ ከመሰዳደብ ወጥተን በመተባበር መንፈስ አብርን መስራት እንዳለበን ነው” ሲሉም መክረዋል፡፡አሁን ወቅቱ የጸሎት ጊዜ መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ ምዕመናን ለአገራቸው ኢትዮጵያ ሰላም እና ለአባታችን እረፍት እንዲጸልዩም ጠይቀዋል፡፡
 
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ እና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም መመሪያን ተግባራዊ ለማድረግ የአሰራር መመሪያ ጥናት እየተዘጋጀ ነው!

የነዳጅ ውጤቶች መሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም እና የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሠራር መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ስርጭት ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።

ከነዳጅ ግብይት ጋር በተያያዘ በዋናነት ኹለት መመሪያዎች ተዘጋጅተው ታኀሣሥ 20/2014 በሚኒስትሮች ምክርቤት የጸደቁ ሲሆን፣ መመሪያዎቹ የተዘጋጁት ከአንድ ዓመት በላይ በፈጀ ጥናት መሆኑንና ጥናቱ የተጠናው ከተለያዩ ሰባት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች እንደሆነ የባለስልጣኑ ኮሚኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ቁምነገረ እውነቱ ተናግረዋል።

ሙሉ ዘገባው : https://bit.ly/3J5YgQf

@YeneTube @FikerAssefa
ከህወሓት ጋር ያለውን ችግር በየትኛውም የሰላም አማራጭ ለመፍታት መስማማቱን ብልጽግና አስታወቀ!

የትኛውንም የሰላም አማራጭ ተጠቅሞ ከህወሓት ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት መስማማቱን ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ፡፡አንደኛ ድርጅታዊ ጉባዔን በማካሄድ ላይ ያለው ፓርቲው የትግራይ ህዝብ በህወሓት ጸብ አጫሪ ድርጊት ምክንያት ያልተገባ ዋጋ እየከፈለ ነው ብሏል፡፡የትግራይ ህዝብ ጉዳት የሌላውም ኢትዮጵያዊ ጉዳት ነው ሲሉ የድርጅታዊ ጉባዔውን የመጀመሪያ ቀን ውሎ የተመለከተ መግለጫን የሰጡት የፓርቲው የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)ህዝቡ እያጋጠመው ያለውን ችግር ለመቅረፍ የሰላም አማራጮችን ተጠቅሞ መስራት እንደሚጠበቅ ተስማምተናል ብለዋል፡፡

ህወሓት እያደረገው ካለው ትንኮሳና ዳግም ወረራ አንጻር በተለይም የሃገርን ሉዓላዊነትና ክብርን ለመቀልበስ ለመጉዳት የነበረው ፍላጎት የተቀለበሰ ቢሆንም በድጋሚ የመውረር ፍላጎቱ ዜሮ ሆኗል ለማለት አይቻልም ያሉት ኃላፊው ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጅት ማድረግና ራስን ማጠናከር ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ይህን በማድረግ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ክብር እንዲሁም ህልውና ዳግም አደጋ ላይ የሚጥል ነገር በሚያጋጥምበት ጊዜ አስፈላጊው እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም ነው የገለጹት፡፡የብልጽግና አመራርና አባላትም ይህን በአንክሮ እንዲከታተሉና ንቁ ሆኖ ለመጠበቅ የሚያስችል ዝግጅት እንዲያደርጉ ስምምነት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል ዶ/ር ቢቂላ፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሩፒያህ ባንዳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ሩፒያህ ባንዳ በ85 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ሩፒያህ ከፈረንጆቹ 2008 እስከ 2011 የዛምቢያ ፕሬዚዳንት በመሆን ሃገራቸውን መርተዋል። ከዚያ ቀደም ብሎ በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ህይወታቸው ያለፈው የሃገሪቱ መሪ ሌቨየ ምዋንዋሳ ምክትል በመሆን አገልግለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር በራሺያ ላይ የሚጣሉ ማዕቀቦች የአለምን ኢኮኖሚ እንዲያገግም ያደርጋሉ አሉ!

የቻይናው ጠ/ሚር ሊ ኬኪያንግ በራሺያ ላይ የሚጣሉ እቀባዎች ቀድሞውንም በኮቪድ ምክንያት ችግር ውስጥ የገባውን የአለም ኢኮኖሚ እንዲያገግም ይጫነዋል ብለዋል። ቀጥለውም ቻይና አለምአቀፍ ሰላም በሚረጋገጥበት መንገድ በመሥራት እድገት እና ብልፅግና እየመጣ ትሰራለች ብለዋል። ለዚህም ጦርነት ውስጥ ያሉትን ራሺያ እና ዩክሬን ተኩስ አቁመው ወደ ድርድር እንዲመጡ እናበረታታለን ብለዋል። ዘገባው የራፕትሊ ነዉ

@YeneTube @FikerAssefa
The dates are getting closer to witness one of Largest Global Hybrid Expo, which shall be taking place at the newly built state of the art library, Abrehot Library.

Exhibitors can take part either Onsite or Virtual, form any part of the globe.

List of Exhibitors:

Schools & Colleges/Universities
School Management Solution Providers
Software developers
App developers & Coders
Start-ups & TECH Entrepreneurs
Education Consultants
STEM Education Incubators,
Digital Service Providers
Education Material Producers & Suppliers
Digital Libraries
NGOs & related.

To Reserve Your Booth:
Call us:
+251 974 0820 36
+251 974 0820 37
Book online via:
www.backtoschoolafrica.com
👍1
ሩሲያ፤ ኪቭን ለመክበብ የሚያስችል ግዙፍ ወታደራዊ ኮንቮይ በማንቀሳቀስ ላይ መሆኗ ተገለጸ

እንቅስቃሴው የሩሲያ ወታደሮች ወደ ዩክሬን ዋና ከተማ ኪቭ መጠጋታቸውን የሚያሳይ ነው ተብሏል ሩሲያ፤ ኪቭን ለመክበብ የሚያስችል ግዙፍ ወታደራዊ ኮንቮይ በማንቀሳቀስ ላይ መሆኗ ተገለጸ፡፡

በእንቅስቃሴው የዬክሬን ዋና ከተማ ኪቭ ዳግም በሩሲያ ወታደሮች ከበባ ስር ልትወድቅ ትችላለች ተብሏል፡፡

60 ያህል ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍን አንድ ግዙፍ የሩሲያ ወታደራዊ ኮንቮይ ወደ ዩክሬኗ መዲና ኪቭ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ወታደራዊ የሳታላይት ምስሎች አመልክተዋል፡፡
ኮንቮዩ ወደ በቀላሉ ወደ ከተማዋ ለመግባት የሚችል ከሆነ ፕሬዝዳንት ዜለንስኪን ጨምሮ ሌሎች የሃገሪቱ በለስልጣን አለን የሚሉባት ኪቭ ሙሉ በሙሉ በሩሲያ ኃይሎች እጅ የምትወድቅ ይሆናል፡፡

የሩሲያ ወታደሮች በተለያዩ አቅጣጫዎች ማጥቃት መጀመራቸውም ነው የተነገረው፡፡ ሊሰነዘር የሚችልባቸውን የትኛውንም ዐይነት ጥቃት ለመከላከል ይችሉ ዘንድ በስብጥር መሰማራታቸውም ነው የተገለጸው፡፡

የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎች በቁልፍ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ እንዲቀመጡ መደረጋቸውን የሚያሳዩት ምስሎቹ ኪቭ ደም አፋሳሽ ጦርነትን ልታስተናግድ የመጨረሻው ሰዓት ላይ ለመድረሷ ሁነኛ ማሳያዎች ናቸው ተብሏል፡፡

የሩሲያ የእግረኛ ጦር አባላት ከኪቭ በ25 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ እንደሚገኙም የብሪታኒያ የደህንነት መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
ከሳምንት በፊት ተመሳሳይ የወታደራዊ ኮንቮይ እንቅስቃሴዎችን የሚያሳዩ ምስሎች ይፋ ሆነው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ይህ በአዲስ መልክ የተነቃቃ የሚመስለው የሩሲያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ያለ ስኬት ከተጠናቀቀው የአንታልያው ውይይት በኋላ የሆነ ነው፡፡

በቱርክ አንታልያ ከተማ የተገናኙት የሃገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተኩስ ለማቆም ከሚያስችል ስምምነት መድረስ ሳይችሉ መቅረታቸው ይታወሳል፡፡

Via Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
ብልፅግና ፓርቲ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን የፓርቲው ፕሬዘዳንት አድርጎ የመረጠ ሲሆን አቶ አደም ፋራ እና አቶ ደመቀ መኮነንን ምክትል ፕሬዘዳንት አድርጎ መርጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ጫንጮ ከተማ የኦኑግ ሸኔ ታጣቂዎች ካገቷቸው የኢትዮ ስሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች 18 ኢትዮጵያዊያን ሐሙስ ዕለት በአገር ሽማግሌዎች ጥረት እንደተለቀቁ ዋዜማ ሰምታለች። ታጣቂዎቹ ካገቷቸው የፋብሪካው ሠራተኞች መካከል 6ቱ ሕንዳዊያን ሲሆኑ፣ ሕንዳዊያኑ እና ሦስት አስተርጓሚዎቻቸው አሁንም በታጣቂዎች እገታ ስር ናቸው። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ታጋች ባልደረቦቻቸውን ገንዘብ ከፍለው ለማስለቀቅ ከታጣቂዎቹ ጋር የተደራደሩ 4 የፋብሪካው ሠራተኞችን አስሯል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ግን 18ቱ ታጋቾች ስለመለቀቃቸው እንዳልሰሙ ለዋዜማ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ገዢው ፓርቲ ብልጽግና መተዳደሪያ ደንቡን አፀደቀ!

የብልጽግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ማሳተፍ የሚችል ሆኖ መጽደቁን የፓርቲው የሕዝብና ዓለም ቀአፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ገለጹ።

ዶክተር ቢቂላ የፓርቲው አንደኛ ጉባኤ የዛሬ ከሰዓት በኋላ ውሎውን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው እንዳመለከቱት ጉባኤው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ማጽደቅ፣ የፓርቲውን ፕሮግራም እና የፓርቲውን ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ምርጫ ማካሄዱን አመልክተዋል።

መተዳደሪያ ደንቡ ፓርቲው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ማሳተፍ የሚችል ሆኑ መዘጋጀቱን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ህብረ ብሔራዊ ፓርቲና ዴሞክራሲን፣ አሳታፊነትንና አካታችነትን ለመለማመድ በሚያስችል ሁኔታ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

የፓርቲው ፕሮግራም በጉባኤው ውይይት ተደርጎበት መጽደቁን የገለጹት ዶክተር ቢቂላ፤ ፕሮግራሙ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚረዱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ጉዳይ፣ የውጭ ጉዳይና የዲፕሎማሲ ጉዳዮችን የያዘ መሆኑን አብራርተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ወደ ባሕር ዳር የሚያደርገውን በረራ መሰረዙን አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ሥራ አስኪያጅ ተስፋዬ ቀለሙ ከመጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በተከሰተ አቧራ መሰል ጭጋግ ምክንያት መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ሊደረጉ የነበሩ 11 በረራዎች መሰረዛቸውን ገልጸዋል።

እንዲህ አይነቱ ክስተት ባለፈው ዓመትም በተመሳሳይ ወር ተከስቶ እንደነበር አስታውሰው የአየር ሁኔታው እንደተስተካከለ የበረራ አገልግሎቱ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

ክስተቱ ዛሬ 11:00 ላይ በጎንደርም ያጋጠመ ቢሆንም የአየር ሁኔታው በመስተካከሉ አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ሥራ አስኪያጁ መግለፃቸውን አሚኮ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
#ጋምቤላ በደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ በተከሰተ ግጭት ከ9 ሺህ 500 በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል!

የክልሉ መንግስት እንደገለጸው በግጭቱ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በስድስት ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ታጣቂዎቹ የኢትዮጵያን እና የክልሉን ሰንደቅ ዓላማዎች እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶችን ዘርፈው ወስደዋል።

የተፈናቀሉት በኑዌር ዞን በላሬና በጂካዎ ወረዳዎች ሥር የሚገኙ የአራት ቀበሌ ነዋሪዎች መሆናቸው ተመልክቷል። የጋምቤላ ክልልና ደቡብ ሱዳን ሰፊ ድንበር የሚጋሩ ከመሆናቸዉ ጋር ተያይዞ በድንበር አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ድንበር አቋርጠው የገቡ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ተገልጿል።

Via Gambella Region Press Secretariat

@Yenetube @Fikerassefa
⬆️
ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋዜጣዊ መግለጫ!

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎችና በርካታ ተመልካቾች በተሰበሰቡበት አስክሬኖች እና አንድ በሕይወት የነበረ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ እሳት ውስጥ ሲጨመር የሚያሳይና በማኅበራዊ ሚድያ በተሰራጨ የቪድዮ ምስል በደረሱት ጥቆማዎች መሰረት ስለሁኔታው አፋጣኝ ማጣራት አድርጓል።

ኢሰመኮ ምስክሮችን በማነጋገር እንዳጣራው ክስተቱ የተፈጸመው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ ውስጥ የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. መሆኑን፣ ከዳኝነት ውጪ የተፈጸመ ግድያ (extra-judicial killing) እና አስከሬኖችን አንድ በሕይወት ከነበረ ሰው ጭምር የማቃጠል ድርጊቱ የተፈጸመው በመንግሥት የፀጥታ አባላትና ሌሎችም ሰዎች ተሳትፎ ጭምር የነበረ መሆኑን አረጋግጧል። እንዲሁም ለዚህ ክስተት መነሻ ስለሆነው ድርጊቱ ከተፈጸመበት አንድ ቀን በፊት ቢያንስ በ 20 የመንግሥት ፀጥታ አባላት እና በሲቪል ሰዎች ላይ በታጣቂዎች ስለተፈጸመው ግድያ ሁኔታም አረጋግጧል፡፡

የካቲት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በመተከል ዞን፣ በጉባ ወረዳ፣ አይሲድ ቀበሌ፣ አፍሪካ እርሻ ልማት ማኅበር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ገደማ፣ ከግልገል በለስ ከተማ በመኪና ተሳፍረው፣ በአካባቢው ካለው የደኅንነት ስጋት አንጻር በተለመደው አሰራር መሰረት በመከላከያ ሠራዊት ታጅበው ወደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ፤ ወደ ማንኩሽና ወደ አሶሳ ከተማ ሲጓዙ የነበሩ ሰዎች ላይ ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ፈጸሙ። በጥቃቱም 1 መኪና አሽከርካሪ፣ 1 በንግድ ሥራ የሚተዳደሩ ሰው እና 1 መምህር በአጠቃላይ 3 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል፤ መንገደኞቹን አጅቦ በመጓዝ ላይ የነበሩት የመከላከያ ሠራዊት አባላት መኪና በከባድ መሳሪያ ተመትቶ ሻለቃ አመራሩን ጨምሮ ቢያንስ 20 የመከላከያ ሠራዊት አባላት ሞተዋል፣ እንዲሁም 14 የመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በዕለቱ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና እና ጥቃቱን በፈጸሙ የታጠቁ ኃይሎች መካከል የተደረገው ውጊያ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እስከ ረፋዱ 12፡00 ሰዓት የቆየ ሲሆን፣ በማግስቱ የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ተጨማሪ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በቦታው ደርሰው ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ በቆየ የተኩስ ልውውጥ ከታጣቂዎቹ መካከል ወደ 30 የሚሆኑ መገደላቸውንና ቀሪዎቹ ታጣቂዎች መሸሻቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡

ይህንን ተከትሎ የመከላከያ ሠራዊት የመንግሥት ፀጥታ አባላቱና የሲቪል ሰዎች መንገደኞች መኪኖች የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት አካባቢ አይሲድ ከተማ ደረሱ። በተከሰተው አደጋም የከተማው ፀጥታ ሁኔታ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ያስረዳሉ።

የመንግሥት የፀጥታ አባላቱ አግኝተናል ባሉት ጥቆማዎች መሰረት በአካባቢው በነበሩ ተሽከርካሪዎችና በመኖሪያ ቤቶች ላይ እንዲሁም ከግልገል በለስ ከተማ ወደ ማንኩሽና ባምዛ የሚጓዙ የነበሩ ሲቪል ሰዎች ላይ ፍተሻ ማካሄድ ጀመሩ።

በፍተሻው ሂደት ውስጥ በቅርቡ ከእስር ተፈትተው ከመተከል ዞን ማረሚያ ቤት የይለፍ ወረቀት በመያዝ ወደ መኖሪያቸው የተመለሱና የአካባቢው ነዋሪዎች የነበሩ 8 የትግራይ ተወላጆችን “እናንተ ናችሁ መረጃ ሰጥታችሁ ጥቃቱን ያስፈጸማችሁት” በማለት ከተሳፈሩበት መኪና እንዳስወረዱና በፍተሻውም አንድ የወታደራዊ መገናኛ ሬዲዮ፣ የተለያዩ ፎቶግራፎች እና ከ40,000 ብር በላይ ገንዘብ እንደተገኘ ተገልጿል። የመንግሥት ፀጥታ አባላቱም ተጠርጣሪዎቹን እየደበደቡ ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ ጀመሩ።

ከዚህ ተከትሎም ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አንዱ “በአካባቢው በተፈጸመው ጥቃት ላይ እጃችን አለበት፤ ባምዛ በሚባለውና በግልገል በለስ ቦታዎች ሰዎች አሉን” ማለቱን ተከትሎ፣ የመንግሥት የፀጥታ ኃይል አባላቱ ሁኔታውን የተቃወሙ ሁለት የጉሙዝ ተወላጆችን ጨምሮ 10 ሰዎችን ተኩሰው ገድለዋል።

ከዚህ በመቀጠልም የፀጥታ ኃይል አባላቱ የተገደሉትን ሰዎች አስከሬኖች ከከተማዋ ወጣ ብሎ ወደሚገኝ ጫካ ስፍራ በመውሰድ አስክሬናቸውን ማቃጠል መጀመራቸውን የዓይን ምስክሮች አስረድተዋል። በዚህ መካከልም ከተጠርጣሪዎቹ ተገዳዮች ጋር ግንኙነት አለው የተባለን አንድ ሌላ የትግራይ ተወላጅ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተሳፈረበት መኪና ውስጥ ተደብቆ በጥቆማ ካገኙት በኋላ በገመድ አስረው በመውሰድ ቀድሞ በመቃጠል ላይ ከነበሩት አስክሬኖች ላይ እንደጨመሩት እና በእሳት ተቃጥሎ እንደሞተ ምስክሮች ለኮሚሽኑ አስረድተዋል፡፡

በአካባቢው የነበሩት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የአማራ ክልል ልዩ ፖሊስ አባላትና የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ልዩ ፖሊስ አባላት ሲሆኑ፤ በአጠቃላይ ሁኔታው በቀጥታ ድርጊት በመፈጸም ወይም አስገዳጅ ተግባሮችን ባለመፈጸም (by commission or omission) የነበራቸው የተለያየ የተሳትፎ መጠን በተጨማሪ የወንጀል ምርመራ ሊጣራ የሚገባው ነው፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እንደገለጹት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እጅግ ፈታኝ በሆኑ አካባቢዎች በከፍተኛ መስዋዕትነት የሕዝብ ደኅንነት የሚጠብቁ መሆኑ የማይዘነጋ ሕዝባዊ አገልግሎት መሆኑ እንደሚታወቅ ገልጸው፤ ሆኖም ግን በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎችን ከዳኝነት ሂደት ውጭ መግደል እና በተለይም በእሳት አቃጥሎ መግደል ፈጽሞ ከሕግ አስከባሪ አባሎች የማይጠበቅ ግፍና ጭካኔ የተሞላበት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በመሆኑ የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በተጠርጣሪዎች ላይ ተገቢውን የወንጀል ምርመራ በአፋጣኝ
እንዲደረግ አሳስበዋል።

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አክለውም “የመንግሥት ሕግ አስከባሪ አባሎች እራሳቸው በግልጽ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ፈጻሚዎች ሆነው መታየታቸው፤ ሰዎች በሕጋዊ ሥርዓት ላይ የሚኖራቸውን እምነት የሚሸረሽርና ለተጨማሪ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሚያጋልጥ በመሆኑ፤ መንግሥት የምርመራውን ሂደትና ውጤት በተመለከተ የተሟላ መረጃ
ለሕዝብ ይፋ ሊያደርግና ፍትሕን ለማረጋገጥም የሟች ቤተሰቦችን ሊክስ ይገባል” ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት (መጋቢት 4/2014 ዓ.ም ) የቤተክርስቲያኗ ሥርዓተ ቀኖና በሚያዘው መልኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ተፈጽሟል።

@YeneTube @FikerAssefa
በዩክሬን ያሉ ኢትዮጵያውያን "ለዩክሬን እንድንዋጋ እየጠየቁን ነው፣ በቅርቡ በግዳጅ ወደ ጦርሜዳ ሊወስዱን ይችላሉ ብለን ሰግተናል" ብለውኛል ሲል ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት ጽፏል።

ጋዜጠኛው በአንድ ዩክሬን ውስጥ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከዩክሬን ጦር ጋር ሆነው እንዲዋጉ መጠየቃቸውን፣ ወደፊት ደግሞ በአስገዳጅነት እንዲዋጉ ሊደረጉ እንደሚችሉ ስጋት እንዳላቸው ዛሬ በስልክ ነግረውኛል ብሏል።

ለደህንነታቻው ሲባል ስማቸው እና ያሉበት ካምፕ እንዳይጠቀስ የጠየቁ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ቢያንስ ሰባት የሚሆኑ ናቸው፣ በካምፑ ውስጥ ባጠቃላይ የሌሎች ሀገራት ዜጎችን ጨምሮ ከ100- 120 የሚደርሱ ሰዎች አሉ ብለዋል። ጋዜጠኛው ሰጡኝ ያለው መረጃ የሚከተለውን ይመስላል:

"ብዙዎቻችን ዩክሬን ለትምህርት ሄደን ከዛም ስራ ስንሰራ (አንዳንዶች ደግሞ ድንበር አቋርጠው ሲሄዱ) ተይዘን በኢሚግሬሽን ህጋቸው መሰረት እንደ እስር ቤት ያለ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ መኖር ከጀመርን አስር ወራት ሆኖኗል። ይህ ጫካ ውስጥ ያለ ካምፕ ውስጥ ሆነን የፍርድ ቤት ቀጠሮ እየጠበቅን እያለ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ጀመረ። ካምፑ ዝግ ነው፣ ለመውጣት ስንሞክር በጣም ደብድበው መለሱን። ከሰሞኑ የዩክሬን ወታደሮች ወደካምፑ መጥተው ነበር።ለዩክሬን ከተዋጋችሁ ዜግነት እንሰጣችኋለን አሉን።አሁን ያቀረቡት ጥያቄ ቢሆንም በግድ ተዋጉ እንዳይሉን ከፍተኛ ስጋት አለን።ጦርነቱ ካምፑ ጋር ቢደርስ ምን እንደሚፈጠር እና ወዴት እንደምንሄድ አናውቅም።ጉዳያችንን ጀርመን ያለው ኤምባሲ ያይልናል ብለን እየጠበቅን ነበር፣ የሚቻለውን ሁሉ እናረጋለን ብለውን ነበር። ከዛ ወዲህ ለውጥ የለም። ያለንበት ሁኔታ መጥፎ ነው፣ ስልክ እንኳን ቀምተውን በድብቅ በገባ ስልክ ነው የምናወራው። በቀን ሁለቴ የሚሰጡን ምግብ እንኳን ጥሩ አይደለም። ከዛ በላይ ደግሞ ለጥቁሮች ያላቸው አመለካከት ደስ አይልም።"

" በዚህ ጉዳይ ዙርያ ጀርመን ያለውን ኤምባሲ ለማናገር ሞክሬ ለግዜው አልተሳካም።አዲስ አበባ የሚገኘውን የዩክሬን ኤምባሲም በማናገር ተጨማሪ መረጃ ሲደርሰኝ እመለስበታለሁ።" -ኤልያስ መሠረት

@YeneTube @FikerAssefa
👍1