YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሃይማኖትና የመንግስት ግንኙነትን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሰጡት ምላሽ፤-

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስድስት ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከአዲስ አበባ ምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡

የሃይማኖትና የመንግስት ግንኙነትን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሰጡት ምላሽ፤-

👉ሃይማኖትና መንግስት የተለያዩ ናቸው፤ የሚኖራቸው ግንኙነት በህገመንግስት በግልጽ ተቀምጧል፡፡

👉በሃይማኖት እያዳሉ ሀገር መምራት አይቻልም

👉የብልጽግና አመራር በየትኛውም ሃይማኖት ተቋም የወከለው ሰው የለውም፡፡

👉ግንኙነታችን ተቋማዊ ነው፤በሰላምና በልማት ጉዳይ በትብብር እንሰራለን፡፡

👉የመንግስትን ድንበር ሳናልፍ ድጋፍ እናደርጋለን፤ በበአላት አከባበር ላይ ለሀገር ገጽታ ግንባታ ጠቃሚ ስለሆነ እንደጋገፋለን፡፡

👉መንግስት ነጻነቱን ጠብቆ ስራውን እንዲያከናውን ሊጠበቅ ይገባል፤ሃይማኖት ተቋማትም በነጻነት ኃይማኖታዊ ስርዓታቸውን ማከናወን አለባቸው፡፡

👉ባለፉት 3 አመታት ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ያለን ግንኙነት እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡

👉በኣላት በትብብር እንዲከበሩ ስንሰራ ቆይተን ውጤታማ ሆነናል::

👉የተለያዩ ሃይማኖት ተቋማት ሀገር ችግር ላይ ስትወድቅ አብረው ቆመው ፈጣሪን ለምነዋል::

👉የመረጠንን ህዝብ በማክበር ለሃይማኖት ተቋማት ድጋፋችንን ስናደርግ ቆይተናል::

👉ባለፉት 3 አመታት 2014ን ሳይጨምር ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ በአጠቃላይ 1ሚሊዮን ካሬሜትር የሆነ 89 የቦታ ጥያቄዎችን አስተናግደናል

👉ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች 260ሺህ 938 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው 85 ቦታዎችን አስተናግደናል

👉ለወንጌል አማኞች 98 ሺህ 290 ካሬሜትር የሆነ 47 የቦታ ጥያቄዎችን አስተናግደናል

👉ለ7ተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን 3 ቦታ በአጠቃላይ 6ሺ 812 ካሬ ሜትር የሆነ የቦታ ጥያቄዎችን አስተናግደናል

👉ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በአጠቃላይ 7700 ካሬሜትር ስፋት ያለው 3 የቦታ ጥያቄዎችን አስተናግደናል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከመስቀል አደባባይ፤ ወይብላ ማርያም እና ባንዲራ ጋር ተያይዞ ለተነሱት ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ:-

👉በመጀመርያ በመስቀል አደባባይ የፕሮቴስታንት አማኞች የጠየቁት የገቢ አሰባሰብ ፕሮግራም ፍቃድ ሰጥተናል፡፡

👉ፕሮግራሙ ሊካሄድ አንድ ቀን ሲቀረው አንድ ከፕሮግራሙ ጋር ግንኙነት በሌለው ሰው እንወርሳለን የሚል ሃሳብ ተንፀባረቀ፡፡

👉ይህም በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ቁጣ የፈጠረ በመሆኑ ግንኙነት ስናደርግ ይህን ያለው ከፕሮግራሙ ጋር ግንኙነት የሌለው ሰው መሆኑን ነግረናቸው ፤ ነገር ግን በዚህም ወገን ያለው አባባልና እሱን መሰረት አድርጎ የተፈጠረውን ስሜት ሁለቱም ሃይ ሊባሉ ይገባል አልናቸው፡፡

👉ነገር ግን ጉዳዩ ጠንከር እያለ ሲሄድ በፕሮግራሙ እለት ተገኝተን ይሄ አደባባይ የሁላችንም ነው በማለት ማንም ወራሽ እና ተወራሽ እንደሌለ የሚጠቁም መልእክት አስተላለፍን

👉ይህ አባባል በዛ መድረክ ሲነገር የመጀመርያ አልነበረም፤ ሌሎችም ተናግረዋል፡፡እኔ ራሴ ደጋግሜ በተለያዩ ፕሮግራሞች ተናግርያለሁ፡፡

👉ስለዚህ ጉዳዩን አሁን እንዲባባስ ያደረገው የተጫጫኑ ስሜቶች በመኖራቸው ምክንያት ነው፡፡

👉ስለዚህ ጥያቄው ሲገፋ ያልነው በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ እንፍታ ነው ያልነው፡፡ በመረጃና በማስረጃ መፍታት የሚቻልባቸው ብዙ አማራጮች አሉ፡፡

👉ከአደባባይ ጋር በተያያዘ የውጪ ብቻ ሳይሆን የራሷ የራሷ የኢትዮጵያ ልምድም ጭምር አለ፡፡

👉ግንኙነት ለማድረግ ከመጀመርያው አንስቶ ብዙ ጥረት ተደርጓል ፤ከመጀመርያው የፓትርያርኩ መታመም አንስቶ በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሟል፡፡

👉እኔ በግሌ ፓትርያርኩ ጋር በመሄድም ጉዳየን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ እንፍታ ብዬ አነጋግርያለሁ፡፡ ልዩነት አልነበራቸውም፡፡ ይህንን ሃሳባችሁን በደብዳቤ አስገቡልን አሉን ይህንንም አድርገናል፡፡

👉ከዚህ ቀደም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ እኛ ወደነሱ እሄዳለን፤ እነርሱም ወደእኛ እየመጡ በርካታ ጉዳዮችን ፈትተናል፡፡

👉ዛሬ እንኳን ግንኙነት ቀጠሮ አለ ስለተባለ የተወሰነው እዚህ ሆነን ጉባኤውን እናስኪድ ሌሎቻችን ደግሞ እዛ እንሂድ ብለን ተከፋፍለን ነው የሄዱት፡፡ እኛ ከሃይማኖት ጋር ፉክክር የምናደርግ መሪዎች አይደለንም!!

👉ወይብላ ማርያም ጋር የተከሰተው ክስተት አሳዛኝና መሆን ያልነበረበት ጉዳይ ነበር፡፡እኛም ከልባችን አዝነናል።

👉በምንም መንገድ ታቦት ውጪ ማደር አልነበረበትም፡፡ ጉዳዩ አሁን በህግ ተይዟል፡፡ እውነታውን አውቀን በህግ ተጠያቂ እስካላደረግን ድረስ ይቅርታ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡

👉ከባንዲራ ጋር ተያይዞ የሚነሱ የተለያዩ ሃሳቦች አሉ፡፡ ይህ ጉዳይ የብሄራዊ ምክክር አጀንዳችን ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት ጥልም ግጭትም በፍፁም አንፈልግም፡፡ ሰውም እንዲሞት አንፈልግም!! ጉዳዮችን ሁሉ ከፖለቲካ ዝንባሌ ጋር ማያያዝም ተገቢ አይደለም ማለታቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ጤና ድርጅት 33.5 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ ጀምሬያለሁ አለ!

የዓለም ጤና ድርጅት 33 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የሚገመት አስፈላጊ የሆኑ መድሃኒቶችን እና የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ መጀመሩን አስታወቀ።የድርጀቱ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት በትዊተር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ፤ “በቀን 10 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል ይገባል” ብሏል።በዚሁ መሰረት በዛሬው እለት 10 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁሶችን በአውሮፕን ወደ ትግራይ ክልል መግቱን አስታውቋል።የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ የተመድ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ከፍተኛ የሆነ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት እንዳለ ሲገልጹ መቆየታቸው አይዘነጋም።

Via Alain
@YeneTube @FikerAssefa
ፌደራል መንግሥቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተጠሪነትን ወደ ከተማዋ አስተዳደር ሊያዛውር እንደሆነ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ተጠሪነቱን ለመረከብ ጥናቶችን አጠናቆ ለመንግሥት እንዳቀረበ የከተማዋ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ቀንዓ ያዴታ ትናንት ለከተማዋ ምክር ቤት ጉባዔ ተናግረዋል። በተለያዩ አዋጆች ላይ የተደረጉ ጥናቶች የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለከተማዋ አስተዳደር መሆን እንዳለበት የሚያመለክቱ እንደሆኑ ቀንዓ አብራርተዋል። ከንቲባ አዳነች ከቀንዓ ማብራሪያ ቀደም ብለው፣ የፖሊስ ኮሚሽኑ ተጠሪነትና አደረጃጀት እንደገና መስተካከል እንዳለበት ለምክር ቤቱ ተናግረው ነበር። የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ተጠሪነት ሙሉ በሙሉ ለፌደራል መንግሥቱ የተሰጠው በ1997 ዓ.ም ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከዚህ (shein.com) website ላይ ያሉ ለሴት እና ለወንድ በተጨማሪም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን
Contact
@kiru04
0931607806

https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Kdamie.com ንግድ እና አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ፡፡
#ጅምላና ችርቻሮ ንግዶችን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ከጨረታና ፐርፎርማ እንዲሁም የስራ ማስታወቂያዎች እና መረጃዎች ጋር፣
#በጉዞዎ መዳረሻዎችን ከነ አስጎብኚዎች እና የጉዞ ወኪሎች ጋር
#የእንግዳ ማረፊያ ሆቴልና ሪዞርቶችን ፈርኒሽድ አፓርታማዎችን ገሰት ሀውሶችን እና ፔንሲዮኖችን
ለመኖሪያ የሚሆኑ ቪላ እና ኮንዲሚኒየሞችን
#በሁሉም የገበያ ማዕከላት ለሱቅ እና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎችን ሳይዞሩ ሳይደክሙ የሚያገኙበት Kdamie.com
#በንግድ በቱሪዝም እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ለሆኑ ድጅቶችም ኑ አብረን እንስራ ይሎታል Kdamie.com

ከኛ ጋር መስራት ንግድና አገልግሎቶን ማዘመን፣ደንበኞችዎን ባሉበት ማግኘት ነው!! Kdamie.com
#በሁሉም የማህበራዊ ገፆች
Telegrame እና whatsup - +251-911705126
Kdamie.com - https://tttttt.me/+K7sPcHhHYy44NDI0
facebook - https://www.facebook.com/Kdamie-107188781818909
Instagram - https://www.instagram.com/p/CZkVH-FAd11/?utm_source=ig_web_copy_link
Email - kdamiesells@gmail.com
phone:- +251911705126/+251916821091 ያገኙናል፡፡
💕💕Valentine Day Special Gift Packages💕💕
የፍቅረኞችን ቀን ምክንያት በማረግ የወንዶች, የሴቶች እና የጥንዶችየተለያዩ የስጦታ ጥቅሎችን አዘጋጅተናል
❤️ብራንድ የእጅ ሰዓት ከስጦታ ሳጥን ጋር (የወንዶች የሴቶች እና የጥንዶች)
❤️ አሻንጉሊት (የተለያዩ ምርጫዎች የሚገኙበት)
❤️ የአንገት ሐብል (ለወንዶች ቀበቶ)
❤️ የእጅ ጌጥ (የወንዶች እና የሴቶች)
❤️ የጆሮ ጌጥ
❤️ ቀለበት (የወንዶች እና የሴቶች
🎁 ከነፃ ስጦታ መያዣ ጋር

❤️ ሁሉንም በአንድ ያግኙ
Contact @be_liye 0941573710
ተጨማሪ የስጦታ እቃዎችን ለማግኘት Telegram Channel ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/simplysellerstore
https://tttttt.me/simplysellerstore
🎁 #ArtLand_gifts 🎁

✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው" 🎁

❤️❤️HAPPY VALENTINE'S DAY❤️❤️

✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት(MDF) እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን 👌

እንዲሁም የተለያዩ GIFT PACKAGES🎁 አዘጋጅተናል❤️

🔘☎️contact us: 0931465618
🔘For Order @Artlandgifts

🚚 ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን🏍🏍

ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ደንበኞቻችን በ EMS / DHL እናደርሳለን 📦

Join👇
@artlandengraving
#የኢትዮጵያ_ታሪክ_ከንግስተ_ሳባ_እስከ_አዲስ_አበባ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የኢትዮጵያን ታሪክ ከንግስተ ሳባ እስከ አዲስ አበባ የሚቃኘውና በአማዞን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃን የተቆናጠጠው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ፡፡

ይህ አለም በጣም ያደነቀው መጽሐፍ ኢትዮጵያን በትናንት፣ በዛሬና በነገ መነጽር የሚያሳይ የ30 ዓመታት ምርምር ውጤት የሆነ በቅጡ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡

የአጼ ኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አስፋ ወሰን አስራቴ ስለመጽሐፉ እንዲህ ነው ያሉት፡-

“አንብቤ ለመጨረስ ሶስት ሌሊቶች ብቻ ነው የወሰደብኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ ላይ ባልተለመደና ቀልብን በሚያነሆልል ሁኔታ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በአፍሪካ ምድር ከሚገኙ መሳጭ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለንን ግንዛቤ የሚያፋፋ እጽ ነው፡፡”

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
ሲአይኤ አሜሪካውያንን በሚስጥር እየሰለለ ነው ሲሉ ሴናተሮች ከሰሱ!

ሁለት የአሜሪካ ሴናተሮች ሲአይኤ አሜሪካውያንን በሚስጥር እየሰለለ ነው ሲሉ ወነጀሉ።የአሜሪካው የስለላ ተቋም ሲአይኤ ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ዜጎቹን እየሰለለ ነው ብለዋል።ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ሲአይኤ ዜጎች እየሰለለ እንደሆነ የተናገሩት ሴናተሮች ሮን ዋይደን እና ማርቲን ሄይንሪች ናቸው።ሁለቱ ዴሞክራቶች ሲአይኤ ስለዘረጋው የዜጎች የስለላ መረብ ለደኅንነት አመራሮች በደብዳቤ ገልጸዋል።

አሜሪካ ውስጥ መንግሥት የዜጎችን የግል መረጃ በስለላ ይሰበስባል የሚል ክስ ሲሰማ የመጀመሪያው አይደለም።
ሲአይኤ እና ብሔራዊው የደኅንነት ተቋም ኤንኤስኤ አገር ውስጥ ስለላ እንዳያካሂዱ እአአ በ1947 የወጣው ሕግ ያግዳቸዋል።ከአሜሪካ ውጭ ግን መረጃ መሰብሰብ ይችላሉ።እአአ በ2013 የቀድሞው የሲአይኤ ሠራተኛ ኤድዋርድ ስኖውደን ሲአይኤ የአሜሪካውያንን የግል መረጃ ከተንቀሳቃሽ ስልካቸው እና ከበይነ መረብ እንቅስቃሴያቸው እየሰለለ እንደሆነ ለዓለም አጋልጧል።

ስለላ ይደረግባቸው ከነበሩት 90 በመቶው ተራ የአሜሪካ ዜጎች መሆናቸውን የስኖውደን የዋሽንግተን ፖስት ሐተታ ይጠቁማል።የወቅቱ ከፍተኛ የደኅንነት አመራሮች ሲአይኤ አሜሪካውያንን እየሰለለ እንደሆነ አናውቅም ሲሉ በምክር ቤት ፊት መካዳቸው ይታወሳል።ኋላ ላይ ግን በአሜሪካ ፍርድ ቤት ፕሪዝም የተባለው የሲአይኤ የዜጎች ስለላ ሕገ ወጥ ተብሏል።ሁለቱ ሴናተሮች እንደሚሉት ሲአይኤ አሁንም በተራ አሜሪካውያን ላይ ሁለት የመረጃ መሰብሰቢያ መዋቅሮች ዘርግቷል።

ይህንን ስለላ የሚያከናውነውም ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ነው።ሲአይኤ ከዘረጋቸው ሁለት መዋቅሮች አንደኛውን ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ይፋ ቢያደርገም ሁለተኛውን የደኅንንት መረጃ ለመጠበቅ ሲል ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል።ሁለቱ የኒው ሜክሲኮ ሴናተሮች ሲአይኤ ሁለተኛውን መዋቅር ይፋ አለማድረጉ "ኢ-ዴሞክራሲያዊ የሆነና የስለላ ተቋሙን ተአማኒነት የሚያሳጣ ነው" ብለዋል።አሜሪካውያን ለምን እንደሚሰለሉ፣ የተሰበሰበው መረጃ ምን ያህል እንደሆነም ይፋ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብ ግንባታን በፍጥነት እንድታጠናቅቅ ግብፅ ማበረታታት አለባት ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለፁ።

ሚኒስትር ዴኤታው ከአል-አረቢያ ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ የግድቡ መገንባት ግብፅን በድርቅ ወቅት እንኳ የውሃ ቋት ሆኖ የሚያገለግል ፕሮጀክት በመሆኑ ፕሮጀክቱን ልትደግፈው እንደሚገባ ተናግረዋል።ሱዳን በአነስተኛ ግድቦቿ ላይ ይደርስብኛል ብላ የምታነሳውን የደኅንነት ስጋት በሚመለከት መደበኛ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ ኢትዮጵያ ዝግጁ እንደሆነች አቋሟን አስርድታለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሀገሪቱ ግን አሁን ላይ የራሷን ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ይልቅ የሶስተኛ ወገን ጉዳይ አስፈፃሚ አየሆነች መምጣቷን አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ አንድ ወገን ብቻ ከዓባይ ሀብት ተጠቃሚ ሲሆን ዘላለም አለሟን መጠበቅ አትችልም ያሉት አምባሳደር ሬድዋን በመሆኑም ሱዳን እና ግብፅ አሁን ከያዙት ግትር አቋም መላቀቅ አለባቸው ብለዋል።ሚኒስትር ዴኤታው ተቀመጫነቱን ዱባይ ካደረገው የአል-አረቢያ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ በሚመለከት ብዙ አዎንታዊ የሆኑ እድሎችን አቅርባ እንደነበር ገልጸው ግብፅና ሱዳን ባለመቀበላቸው ምክንያት ሳይሳኩ እንደቀሩ ጠቁመዋል። የኅዳሴ ግድብ ከጭቅጭቅ ይልቅ የቀጣናዊ ኅብረትና አንድነት ማሳያ እንደሆነና ኢትዮጵያ በታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ ምንም አይነት የጎላ ጉዳት ሳታደረስ የራሷን ሀብት መጠቀም እንደምትችል ገልጸዋል።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ባለፉት ሁለት ሳምንታት 86 በረራዎችን በማድረግ ከ110 ሚሊየን በላይ የአበባ ዘንግ ወደተለያዩ ሀገራት ማጓጓዙን አስታወቀ።

እንደ ዓየር መንገዱ ገለፃ የአበባ ዘንጎቹን በዋናነት ከኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ ሀገራት ቢያጓጉዝም፥ በተጨማሪም ምርቱን ከኬንያ፣ ኢኳዶር፣ ኮሎምቢያና ሚያሚ (ዩናይትድ ስቴትስ) ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት አጓጉዟል።አየር መንገዱ “የፍቅረኞች ቀን” (የቫለንታይን ደይ) በሚውልበት በዚህ ወር የሙቀት መቆጣጠሪያ በተገጠመላቸው ዘመናዊ እቃ ጫኝ አውሮፕላኖቹ ነው የአበባ ምርቶችን ወደተለያዩ የዓለም ሀገራት በማጓጓዝ ላይ የሚገኘው።

@YeneTube @FikerAssefa
ብሉምበርግ ራሺያ ዩክሬይንና እስከ ማክሰኞ ድረስ ልትወርር ትችላለች ብሏል። እንደ ጣቢያው ትንበያ የጥቃቱ መጠን ወትሮውንም ውጥረት የነገሰባትን ዶነባስ ክልልን ከመተንኮስ የዩክሬን መዲና ኪዬቭን እስከማጥቃት ሊዘል ይችላል።

ባለፈው ሳምንት የቴሌቪዥን ጣቢያው "ራሺያ ዩክሬይንና ወረረች" የሚል ጽሑፍ ለ24 ደቂቃ ካስነበበ በኋላ በማጥፋት ቀደም ብለን የተዘጋጀንበት አርዕስት በስህተት ተለቆ ነው የሚል ማብራሪያ መስጠቱ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችን ማሳ በመጎብኘት ላይ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበጋ መስኖ የለሙ የስንዴ ማሳዎችን እንዲሁም የቡና ልማትን ነው በመጎብኘት ላይ የሚገኙት።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋርም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመስክ ጉብኝቱ ላይ መገኘታቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሱማሌ ክልል በተከሠተው ድርቅ ከ683 ሺሕ በላይ የቤት እንስሳት ሞተዋል!

በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በተከሠተው ድርቅ ምክንያት እስካሁን ከ683 ሺሕ በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የክልሉ አደጋ ሥጋት አመራር ቢሮ ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።በዚህም እስከ ጥር 30/2014 ባለው ጊዜ ብቻ 683 ሺሕ 465 የቤት እንስሳት መሞታቸውን ነው ቢሮው ያሳወቀው። የቢሮው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን ኃላፊ በሽር አረብ እንደገለጹትም፣ 32 ሺሕ 729 ግመሎች፣ 188 ሺሕ 242 ከብቶች፣ 442 ሺሕ 628 ፍየሎች፣ እንዲሁም 19 ሺሕ 866 አህያዎች በድርቁ ሳቢያ በክልሉ የሞቱ የቤት እንስሳት ናቸው። የቦረና ዞን አጎራባች በሆነው ዳዋ ዞን የሞቱት የቤት እንስሳት ብቻ ከ447 ሺሕ በላይ ሲሆኑ፣ በአፍዴራና ሸበሌ ዞኖችም እንዲሁ ብዙ የቤት እንስሳት ማለቃቸውን ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ፣ ኢትዮጵያን በተመለከተ አዲስ ረቂቅ ህግ ያወጣ ሲሆን ረቂቅ ህጉ በኢትዮጵያ ግጭትን እያባባሱ በሚገኙ አካላት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚያዝ ነው ተብሏል።

“የኢትዮጵያ የመረጋጋት፣ የሰላምና የዲሞክራሲ ህግ” በሚል ስያሜ የተዘጋጀው ረቂቅ ህግ፤ በዋናነት በአሜሪካ የኒውጀርሲና ካሊፎርኒያ ግዛት ተወካዮች በጋራ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ ለሀገሪቱ መንግስት የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ እንዲቋረጥና አሜሪካን ለኢትዮጵያ የምታደርገው የደህንነትና ፀጥታ ትብብር እንዲቆም ይደነግጋል።በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የፀደቀው ረቂቅ ህጉ በቀጣይ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ከፀደቀ ብቻ ነው ተግባራዊ የሚደረገው፤ ህጉ ለኢትዮጵያ ምንም አይነት እርዳታም ሆነ ብድር እንዳይሰጥ የሚጠይቅ ነው።

ይህ ረቂቅ ህግ በኢትዮጵያ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ድርድሩን በማይቀበሉና ግጭቱ እንዳይቆም በሚፈልጉ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት በሚፈጽሙ፣ መከራን በሚያስፋና በማናቸውም ጠብ አጫሪ ወገኖች የጦር መሳሪያ በሚሸጡ አካላት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ያስችላል ተብሏል።ለሰብአዊ እርዳታዎች ካልሆነ በስተቀር እንደ የአለም ባንክና አለማቀፍ የገንዘብ ድርጅትን የመሳሰሉ አለማቀፍ ተቋማት ለኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት የገንዘብ እርዳታዎችንም ሆነ ብድሮችን እንዳይሰጡ፤ የአሜሪካ መንግስትም ጫና እንዲያደርግ ረቂቅ ህጉ ይጠይቃል።

በዚህ ረቂቅ ህግ ላይ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰብአዊ ወንጀሎች ጦር ወንጀልና ዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ መካሄድ አለመካሄዱን መርምሮ እንዲያሳውቅ፤ ግጭቱን የሚያባብሱ ማናቸውም አካላት ተጠያቂነት ያለባቸው መሆኑን እንዲያውቁ እንዲደረግም በረቂቅ ህጉ ተመልክቷል።

[Addis Admass]
@YeneTube @FikerAssefa
ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በትግራይ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ጠየቀ!

በትግራይ የሚንቀሳቀሰው ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፖርቲ በክልሉ ሁሉን አካታች የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ጠየቀ።አሁን ላይ በትግራይ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የህዝቡን ድህንነት እና ህልውና ማረጋገጥ አልቻለም የሚለው ዓሲምባ ዴሞክራስያዊ ፖርቲ፥ በትግራይ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግር ለመፍታት ሁሉም የፖለቲካ ፖርቲዎች፣ ሲቪክ ማሕበራት እና ሌሎች ያካተተ ሁሉን አቀፍ የሽግግር አስተዳደር እንዲመሰረት ጥሪ አቅርቧል።በቅርቡ የትግራይ ነፃነት ፖርቲ እና ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የተሰኙ ሁለት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲዎች በተመሳሳይ በትግራይ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ጠይቀው እንደነበር ይታወሳል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከዚህ (shein.com) website ላይ ያሉ ለሴት እና ለወንድ በተጨማሪም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን
Contact
@kiru04
0931607806

https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
#የኢትዮጵያ_ታሪክ_ከንግስተ_ሳባ_እስከ_አዲስ_አበባ
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

የኢትዮጵያን ታሪክ ከንግስተ ሳባ እስከ አዲስ አበባ የሚቃኘውና በአማዞን የምንጊዜም የኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ሽያጭ ከፍተኛ ደረጃን የተቆናጠጠው መጽሐፍ በአማርኛ ተተርጉሞ ቀረበ፡፡

ይህ አለም በጣም ያደነቀው መጽሐፍ ኢትዮጵያን በትናንት፣ በዛሬና በነገ መነጽር የሚያሳይ የ30 ዓመታት ምርምር ውጤት የሆነ በቅጡ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡

የአጼ ኃይለስላሴ የልጅ ልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አስፋ ወሰን አስራቴ ስለመጽሐፉ እንዲህ ነው ያሉት፡-

“አንብቤ ለመጨረስ ሶስት ሌሊቶች ብቻ ነው የወሰደብኝ፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ጥንታዊ፣ ኃይማኖታዊ ልምምድ ላይ ባልተለመደና ቀልብን በሚያነሆልል ሁኔታ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ በአፍሪካ ምድር ከሚገኙ መሳጭ ስልጣኔዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለንን ግንዛቤ የሚያፋፋ እጽ ነው፡፡”

በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun