YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
**ኣቡነ ኣንጦንዮስ ማረፋቸው ተሰማ።

3ኛው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የነበሩት ኣቡነ ኣንጦንዮስ ማረፋቸውን የቢቢሲ ትግርኛ አገልግሎት ዘግቧል።**

ኣቡነ ኣንጦንዮስ ለበርካታት አመታት በቁም እስር ላይ ነበሩ።

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን 3ኛው ፓትሪያርክ አቡነ ኣንጦኒዮስ እስከ 1998 ዓ.ም ድረስ ቤተክርስቲያኒቱን ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ከሀይማኖቱ ተቃራኒ የሆነ አመለካከት ያራምዳሉ ተብለው ሲከሰሱ ነበር።

ኣቡነ ኣንጦንዮስ ለረጅም ጊዜ የአገሪቱ መንግሥትን ሲተቹ የቆዩ ሲሆን፤ በዚህም ለ15 ዓመታት ከመንበራቸው ተነስተው በቁም አስር ላይ መቆየታቸው ይነገራል።

ከዓመታት በፊት የኤርትራ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ፓትሪያርኩን አውግዘው ከመንበራቸው በማንሳት የእምነቱ ተከታዮች "እውቅና እንዳይሰጧቸውና ስማቸውንም እንዳያነሱ" አዘው ነበር።

ፓትሪያርኩ ከቤተክርስቲያኗ አባልነት የተገለሉ ቢሆንም በቤተክርስቲያኗ ባለቤትነት ስር በሆነ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ ተፈቅዶላቸዋል ነበር።

ኣቡነ ኣንጦንዮስ አስመራ ውስጥ ህይወታቸው እንዳለፈ ነው ዛሬ የተሰማው።

@Yenetube @Fikerassefa
በአማራ እና አፋር ክልሎች አሁንም ድረስ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ያላገኙ አካባቢዎች በርካታ መሆናቸው ተገለፀ!

ከሃምሌ 2013 ዓ.ም ጀምሮ የህወሓት ታጠቂዎች ተቆጣጥረዋቸው በነበሩ የአማራና የአፋር ክልሎች የሚገኙ በርካታ አካባቢዎች የፌደራል መንግስቱ ሃይሎች ከታህሳስ 2014 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ነጻ መውጣታቸውን ተከትሎ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማድረስ ቢቻልም አሁንም በርካታ ከተሞች አገልግሎቱን ማግኘት አልቻሉም፡፡

ሁለቱ ክልሎች የኤሌክትሪክ ሃይል ምንጫቸው በህወሃት ቁጥጥር ስር ካሉት የተከዜ ሃይል ማመንጫና የአላማጣ ማሰራጫ ጣቢያ በመሆኑ ነጻ ለወጡት በርካታ አካባቢዎች አገልግሎቱን ማቅረብ እንዳልተቻለ የሁለቱ ተቋማት የኮሚዩንኬሽን ሃላፊዎች ለዋዜማ ተናግረዋል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ፡፡

የምክር ቤቱ ጉባኤ አፈ ጉባኤ ቡዜና አልቃድር በመክፈቻ ንግግር በይፋ አስጀምረዋል።ምክር ቤቱ በሁለት ቀን ቆይታው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከከንቲባ ጽሕፈት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የከተማ የአስተዳደሩን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምን ቅድሚያ ሰጥቶ የሚገመግም ሲሆን የአዲስ አበባ ፍርድ ቤቶች የስድስት ወራት አፈጻጸም፣ የመሬት ይዞታ ማስለቀቅ እና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ ተወያይቶ ማጽደቅ እንዲሁም የተለያዩ ሹመቶችን ማጽደቅ የምክር ቤቱ አጀንዳዎች ናቸው ተብሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ስደተኛ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ተገለጸ!

በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት በዲማ ስደተኛ ካምፕና በጎግ ወረዳ ጥቃት ማድረሳቸውን የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ እንደገለጡት ፥ በጥቃቱ የአንድ ሠው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሠዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና ሶስት ህፃናት ታፍነው ተወስደዋል።

ክልሉን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያጋራው ድንበር ሰፊና ክፍት ስለሆነ ታጣቂዎች በተለያየ ጊዜ ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱ ይገኛሉ ብለዋል።ከዚህም በተጨማሪም በጎግ ወረዳ ከፑኝዶ ከተማ ወደ ቴዶ ቀበሌ በሚንቀሳቀስ ሞተር ሳይክል ላይ ባደረሱት ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ነው የተናገሩት።በቅርቡ መነሻውን ከጋምቤላ ከተማ አድርጎ ወደ ኑዌር ዞን በመጓዝ ላይ ባለ የጭነት መኪና ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ባደረሱት ጥቃት የመኪናው አሽከርካሪ እና ረዳቱ ህይወታቸው እንዳለፈም ገልጸዋል።

ጥቃት ያደረሱትን ግለሰቦች የክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻዎች ተከታትለው አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ጠንካራ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።ህብረተሰቡም ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ አቶ ኡገቱ ጠይቀዋል።የክልሉ መንግስት በአሁኑ ሰዓት ልዩ ኃይሉንና ሚሊሻውን በመጠቀም ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በየቦታው ሾልከው ሊገቡ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ ሊጠብቅ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ምከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤቱ የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የነአብዲ መሀመድ ኡመር አቤቱታን ውድቅ አደረገ!

አብዲ መሀመድን ጨምሮ 17 ተከሳሾች ከኛ ጋር ተከሰው የነበሩ ዕስረኞች ክስ ተቋርጦ እኛ ብቻ የምንታሰርበት ምንም ምክንያት የለም።በህገመንግስቱ የተሰጠንን በእኩል የመታየት መብታችን የተነፈገ በመሆኑ ፍርድ ቤት አንቀርብም ሲሉ ተከሳሾቹ ባሳለፍነው ማክሰኞ አቤታታ ማሰማታቸው ይታወሳል።በአቤቱታው ላይ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ለዛሬ በተያዘው ቀጠሮ ችሎቱ ተሰይሟል።

ሆኖም ዛሬ አብዲ መሀመድን ጨምሮ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ 14 ተከሳሾች ችሎት አንቀርብም በማለት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።ነገር ግን በቂሉንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ ሙሴ እንድሪስ፣ ሼክ ሙክታር፣ ሼክ መሀመድ እና ሙስጠፋ ሀቢብ የተባሉ ሦስት ተከሳሾች በችሎት ቀርበው በአስገዳጅ ሁኔታ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ወደ ፍርድ ቤት እንዳመጣቸው አቤቱታ አቅርበዋል።በተጨማሪም ከሌሎች ታራሚዎች ጋር ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲዛወሩ አንድ ላይ ጉዳያቸው እንዲታይላቸው ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም የደረሰባቸው የመብት ጥሰት ካለ በጽሁፍ እንዲያቀርቡ አስተያየት ሰቷል።የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አብዲ መሀመድ ኡመር ጨምሮን አጠቃላይ ተከሳሾች ሌሎች ዕስረኞች ተፈተው እኛ ፍርድ ቤት የምንቀርብበት ምክንያት የለም ሲሉ ያቀረቡትን አቤቱታ በተመለከተ መርምሮ አቤቱታውን ማቅረብ ያለባቸው ክስ ላቋረጠው መንግስታዊ አካል እንጂ ለዚህ ችሎት አደለም። ጥያቄው የህግ መሰረት የሌለው ነው ሲል አቤቱታቸውን ውድቅ ማድረጉን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ዘግባለች።

ስለዚህ ፍርድ ቤቱ በያዘው ቀጠሮ የምስክር አሰማም ሂደት ይቀጥላል ሲል፣ የዓቃቢህግ ቀሪ ምስክርን ለመስማት ለየካቲት 14 ቀን 2014 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዛሬ ያልቀረቡ 14 ተከሳሾችን በቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርብም አዟል።

@YeneTube @FikerAssefa
“ስዋሂሊ” የአፍሪካ ህብረት ተጨማሪ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ተወሰነ!

የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ስዋሂሊ ቋንቋ ተጨማሪ የህብረቱ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ወሰኑ።መሪዎቹ ውሰኔው ያሳለፉት ላለፉት ቀናት በአህጉሪቱ መዲና አዲስ አበባ በተካሄደው 35ኛ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ መሆኑም ታውቋል።

መሪዎቹ ከውሳኔው ላላ የደረሱት የታንዛንያው ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ፊሊፕ ምፓንጎ ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ እንደሆነም ነው የተገለጸው።ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ የስዋሂሊ ቋንቋ በአፍሪካ ከ100 ሚልየን በላይ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ መሆኑን በ35ኛው የህብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለተሳተፉ መሪዎች ገልጸዋል።

35ኛ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተሳተፉ የሀገራት መሪዎችም ስሃዋሂሊ ቋንቋን 5ኛ የህብረቱ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ወስነዋል።የአፍሪካ ህብረት እስካሁን አረብኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረነሳይኛ፣ ፖርቹጋል እና ስፓኒሽ ቋንቋዎችን የስራ ቋንቋ አድርጎ በመጠቀም ላይ ይገኛል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
ማንኛውም ሰው ፈቃድ ሳይወስድ የበጎ አድራጎት ኮሚቴ በማቋቋም ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ እንዳይሰራ ተከለከለ!

ማንኛውም ሰው ፈቃድ ሳይወስድ የበጎ አድራጎት ኮሚቴ በማቋቋም ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ እንዳይሰራ መከልከሉን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አስታወቀ።ከዚህ ቀደም ፈቃድ ሳይኖራቸው የበጎ አድራጎት ኮሚቴ አቋቁመው በገንዘብ ማሰባሰብ ላይ የሚገኙ ግለሰቦችና ቡድኖች ከባለስልጣኑ ፈቃድ በመውሰድ ወደ ህጋዊ አሰራር መግባት እንዳለባቸውም አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በጥር ወር ብቻ የትራንስፖርት ህጉን ተላልፈው በተገኙ 12 ሺህ 976 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ከታሪፍ በላይ በማስከፈል፣ መስመር በማቆራረጥ፣ ትርፍ ሰው በመጫን እና በሌሎች የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን ቢሮው ገልጿል፡፡ከህግ ጥፋቶች መካከል ታፔላ ባለመስቀል የተቀጡ አሽከርካሪዎች 4 ሺህ 31 ሲሆኑ፥ ከመጠን በላይ በመጫን በ3 ሺህ 949 እንዲሁም ከታሪፍ በላይ በማስከፈል በ163 እና መስመር በማቆራረጥ በ112 አሽከርካሪዎች እርምት ተወስዷል፡፡

በመዲናዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በመደረግ ላይ ይገኛል ያለው ቢሮው በተወሰደው እርምጃም ከ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ መንግስት ካዝና ማስገባት ተችሏል፡፡በየቀኑ ስምሪት ውስጥ የገቡ ተሽከርካሪዎች መረጃ መሰረት በማድረግ በሁሉም አገልግሎት መስጫ መስመሮች ላይ በሁለት ሽፍት ቁጥጥር ስራ እየተካሄደ ይገኛል ያለው ቢሮው በመዲናዋ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ አሽከርካሪዎች ህግ አክብረው እንዲሰሩ አሳስቧል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መደንገግ ተከትሎ በእሥር ላይ ከነበሩ የትግራ ተወላጆች መካከል «በአሥራዎቹ የሚቆጠሩት በእናንተ ቦታ ሌላ ሰው ተመድቦበታል» የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው መስማቱን እናት ፓርቲ ተናገረ።

በሕግ ጥላ ሥር የነበሩ እንዲሁም በቁጥጥር ሥር ሳይውሉ ከሥራ ታግደው በቤት እንዲቆዩ ተደርገው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ወደሚሠሩባቸው መሥሪያ ቤቶች ሲመለሱ በእናንተ ቦታ ሰው ተተክቶበታል የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ጌትነት ወርቁ ለዶቼ ቬለ እንደነገሩት እንዲህ ያለው ችግር በዋናነት በአዲስ አበባ መፈፀሙን መረጃ እንዳላቸው ገልፀው፣ እሥሩ ፣ ከሥራ ማሰናበቱ ፣ ደሞዝ መከልከሉ ግን በክልሎች ውስጥ ባሉ ትልልቅ ከተሞች ላይም ታይቷል። ይሁንና የትኛው መሥሪያ ቤት ይህንን እንዳደረገ ከመግለፅ ተቆጥበዋል።ጉዳዩ በመታየት ሂደት ላይ መሆኑንም ገልፀዋል። በቅርቡ ከእሥር የተፈታው የአረና ትግራይ ለዲሞክራሲ እና ሉዓላዊነት ፓርቲ ሊቀመንበር እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባል የነበሩት አቶ አብርሃ ደስታ ይህንን እሥር ተቃውመው በመፃፋቸው ታስረው መፈታታቸውን ገልፀው ፣ መንግሥት ያልተገባ በደል መፈፀሙን፣ ለድርጊቱም ይቅርታ ቢጠይቅ ጥሩ ነው ብለዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ሁለት ህፃናትን ይዛ የተሰወረችው የቤት ሰራተኛ ከነግብረ-አበሮቿ በቁጥጥር ስር ዋለች!

በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማ ሶስት ወለቴ ቀበሌ 03 በተለምዶ ስላሴ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለፈው ሰኞ ሁለት ህፃናትን ይዛ የተሰወረችው የቤት ሰራተኛ ከነግብረ-አበሮቿ በቁጥጥር ስር ውላለች።በሰበታ ከተማ መስተዳድር የክፍለ ከተማ ሶስት ፖሊስ ጽ/ቤት ምርመራ ክፍል ኃላፊ ሳጅን ሀብታሙ ፀጋዬ እንደተናገሩት የቤት ሰራተኛዋ የ4 ዓመት ሴትና የ9 ወር ወንድ ህፃን ልጆችን ይዛ ነበር ባለፈው ሰኞ በባጃጅ ከቤት የጠፋችው።

የኦሮሚያ ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዲሁም ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከህብረተሰቡ ጋር እጅና ጓንት በመሆን በሰሩት ስራ ግለሰቧን ጨምሮ አምስት ተጠርጣሪዎችን በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር አውለዋል።ተጠርጣሪዋ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ዘነበ ወርቅ አለርት ሆስፒታል አካባቢ ከአንድ ተባባሪዋ ጋር በአንድ ግለሰብ ቤት እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር መዋሏን ሳጅን ሀብታሙ በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

የቤት ሰራተኛዋ አቶ ዘይኑ ሽኩር በተባሉ ግለሰብ ቤት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ስትሰራ ከሌሎች ሰዎች ጋር ለጥቅም በመመሳጠር የአሰሪዋን ልጆች ይዛ መሰወሯን እስካሁን በተደረገው ምርመራ መረጋገጡን ሳጅን ሀብታሙ ተናግረዋል።በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት ሁለቱም ህፃናት በተደረገላቸው የሕክምና ምርመራ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል ብለዋል።ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኞችን ሲቀጥር ሕጋዊ ተያዥ (ዋስ) ያላቸውን ለይቶ መቅጠር እንዳለበትም ነው ሳጅን ሀብታሙ ያሳሰቡት።አራቱ ተጠርጣሪዎች ከቤት ሰራተኛዋ ጋር ተመሳጥረው ሁለቱን ሕፃናት ያገቱት ከቤተሰባቸው ገንዘብ ለመጠየቅ እንደነበረ ነው ፖሊስ ያስታወቀው።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከዚህ (shein.com) website ላይ ያሉ ለሴት እና ለወንድ በተጨማሪም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን
Contact
@kiru04
0931607806

https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ

አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
💕💕Valentine Day Special Gift Packages💕💕
የፍቅረኞችን ቀን ምክንያት በማረግ የወንዶች, የሴቶች እና የጥንዶችየተለያዩ የስጦታ ጥቅሎችን አዘጋጅተናል
❤️ብራንድ የእጅ ሰዓት ከስጦታ ሳጥን ጋር (የወንዶች የሴቶች እና የጥንዶች)
❤️ አሻንጉሊት (የተለያዩ ምርጫዎች የሚገኙበት)
❤️ የአንገት ሐብል (ለወንዶች ቀበቶ)
❤️ የእጅ ጌጥ (የወንዶች እና የሴቶች)
❤️ የጆሮ ጌጥ
❤️ ቀለበት (የወንዶች እና የሴቶች
🎁 ከነፃ ስጦታ መያዣ ጋር

❤️ ሁሉንም በአንድ ያግኙ
Contact @be_liye 0941573710
ተጨማሪ የስጦታ እቃዎችን ለማግኘት Telegram Channel ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/simplysellerstore
https://tttttt.me/simplysellerstore
🎁 #ArtLand_gifts 🎁

✿ "እማይረሱ ስጦታዎችን ለሚወዷቸው" 🎁

❤️❤️HAPPY VALENTINE'S DAY❤️❤️

✔️የወደዱትን "ፎቶ ወይም ምስል" እንጨት(MDF) እና ቆዳ(ሌዘር) ላይ እንሰራለን 👌

እንዲሁም የተለያዩ GIFT PACKAGES🎁 አዘጋጅተናል❤️

🔘☎️contact us: 0931465618
🔘For Order @Artlandgifts

🚚 ይዘዙን ያሉበት ድረስ እናደርሳለን🏍🏍

ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ደንበኞቻችን በ EMS / DHL እናደርሳለን 📦

Join👇
@artlandengraving
ሥራ ፈጣሪዎችን ከባለሀብቶች ጋር የሚያገናኝ መተግበሪ ይፋ ሆነ።

መተግበሪያው ''ስሙኒ'' የሚል ስያሜ ተሰጥቷል። በኮካ ኮላ ቢቬሬጅስ አፍሪካ -ኢትዮጵያ ትብበር የተሰራው በድረ ገፅ የታገዘ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዲጂታል ስራ ፈጣሪ እና ባለሀብቶች አገናኝ መተግበሪያ መሆኑ ተነግሮለታል።

ስሙኒ የሥራ ፈጠራ ባለቤቶችንና ባለሃብቶች ማገናኛ በስራ ፈጠራ ስነምህዳር ውስጥ ያሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚገናኙበት እና የሚተሳሰሩበት፣ የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን ኢንቨስትመንት እድገት በቀላሉ ለመገንባት፣ ለመደገፍ እና ለመጠቀም የሚያስችል የኦንላይን መድረክ መሆኑን ሰምተናል።

ስሙኒ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ዝግጁ የሆኑ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎችን (Startups) ማግኘት የሚችሉበት መተግበሪያ ሲሆን  በዛሬው እለትም  ወደ ሥራ ገብቷል።

መተግበሪያው የውጭ ሀገር  ባለሀብቶች  በሀገር ቤት ስራ ፈጣሪዎች  ላይ መዋዕለ ንዋይ እንዲያፈሱ በማስቻል ምንዛሪ በማስገኘት እና የውጭ ኢንቨስትመንት በመሳብ ለኢትዮጵያ የምጣኔ ሐብት እድገት ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎም ተስፋ ተደርጓበታል።

ኮካኮላ በስሙኒ መተግበሪያ በኩል በዚህ ዓመት ለ10 ስራ ፈጣሪዎች ለእያንዳንዳቸው 100,000 ብር ስራ ማስጀመሪያ  እሰጣለሁ ብሏል። በተጨማሪም የስሙኒ መድረክን በመጠቀም 10,000 የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን፣ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን እና አነስተኛ የንግድ ባለቤቶችን አቅም ለመገንባት በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ የክህሎትና የዕውቀት ድጋፍ በማድረግ ከሌሎች ኢንቨስተሮችን የማገናኘት ስራ እንደሚሰራ ተነግሯል።

የኮካ ኮላ ካንፓኒ የአፊሪካ-ኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዳረል ዊልሰን  ከሱሙኒ ጋር መተባበራች እና  ለወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር በመቻላችን ደስተኛ ነን ብለዋል።

የስሙኒ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ብሩክ ግርማ “ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አንድ ላይ በማሰባሰብ እና ውጤታማ የሆነ አጋርነት እና ትብብር በመፍጠር የአፍሪካን ኢኮኖሚ በአዳዲስ የስራ ፈጣራዎች ለማሳደግ አስበናል ”ሲሉ ተደምጠዋል።

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
ግሎባል አሊያንስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በ10 ሚሊዮን ብር ወጪ በሎጊያ ከተማ የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ሊያካሂደ ነው!

(አዲስ ዘይቤ፡አዲስ አበባ)ግሎባል አሊያንስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በ10 ሚሊዮን ብር ወጪ በአፋር ክልል ሎጊያ ከተማ የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ለመጀመር ትናንት የመሰረተ ድንጋይ ዛሬ አስቀምጧል።እስከ 7ኛ ክፍል ድረስ የሚያስተምረው የሎጊያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ወይዘሮ ህይወት ሽመልስ በስነሰርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፤ ትምህርት ቤቱ በአንድ ክፍል እስከ 120 ተማሪዎች በተጨናነቀ ሁኔታ እያስተማረ ይገኛል።

ትምህርት ቤቱ የመማሪያና አስተዳደር ክፍሎች ጥበት በተጨማሪ የውሃና የመጸዳጀ ቤት ችግሮች ያሉበት መሆኑን ጠቁመው፤ ይህ ችግር ተማሪ የመቀበል አቅሙን እንደገደበበት ገልጸዋል።ትምህርት ቤቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ትውልድ ለመቅረጽ የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታ ነው ያለው የግሎባል አሊያንስ ቦርድ ሰብሳቢ አርቲስት ታማኝ በየነ፤ የትምህርት ቤቱን ችግሮች ለመፍታት የድርጅቱን አባላት በማስተባበር በቀጣይ ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግሯል።

ግንባታው እስከ 10 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚፈጅና ስራው በአፋር ልማት ማህበር በኩል የሚከናወን መሆኑን ተናግረው 8 የመማሪያ ክፍሎች ያሉት ባለሁለት ብሎክና የአስተዳደር ህንጻን ጨምሮ ሌሎች ግንባታዎችን ያካትት መሆኑን ጠቅሰው፤ ግንባታው በ8 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል።

"በውጭ የምትኖሩ ወንድሞቼና እህቶቼ ወገናችሁ ለሀገሩ እየከፈለ ያለውን መስዋእትነት በመረዳት በምንችለው ሁሉ ከአፋር ህዝብ ጎን ልንቆም ይገባል" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።የአፋር ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኑረዲን ሰዲቅ በኩላቸው "ግሎባል አሊያንስና አርቲስት ታማኝ በየነ ከአፋር ህዝብ ጎን በመቆም እያደረገ ያለው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ የሚደነቅ ነው" ብለዋል።

Via @AddisZeybe
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ አስተዳደር ለህገወጥ ተግባራት የተጋለጡ ከ400ሺ በላይ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎችን ማምከኑን አስታወቀ!

የአዲስ አበባ አስተዳደር ለህገወጥ ተግባራት የተጋለጡ ከ400ሺ በላይ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታዎችን ማምከኑን የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ አስታወቀ፡፡አቶ ጥራቱ በየነ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት የከተማ አስተዳደሩ ወቅታዊ ጉዳይን መሰረት በማድረግ በመሬት ነክ ዙሪያ የሚሰጡ አገልግሎቶች እንዲቆሙ አድርጎ ቆይቷል። ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት ህገወጥነትን መከላከል በጣም አስፈላጊ ስለነበር ነው።በተለይም መሬት፣ ህንጻና ቤት ያላቸው አካላት ንብረታቸውን በመሸጥና በማሸሽ ለጦርነት ግብዓት እንዲውል በማድረግ ሽብርተኛውን ቡድን ሲደግፉ ተደርሶባቸዋል፤ አገልግሎቱ መቋረጡም ይህንን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራና በአፋር ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ሆቴሎች እና የቱሪዝም መዳረሻዎች ዳግም ወደ ሥራ ለመመለስ የሚያግዝ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይፋ ተደረገ፡፡

"በሙያዬ ለሀገሬ" በሚል መሪ ሐሳብ የተጀመረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ሆቴል እና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሠሪዎች ፌደሬሽን በበላይነት የሚመራው መሆኑን ሰምተናል፡፡የመርኃ ግብሩ ዋና ዓላማ በሁለቱ ክልሎች በጦርነቱ ተጎድተው ሙሉ በሙሉና በከፊል ሥራ ያቆሙ ሆቴሎችን፣ እንዲሁም የቱሪዝም መዳረሻዎችን መለየት፣ ማደራጀት፣ ማማከር፣ የሥልጠና እና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ ነው ተብሏል።

በዚህ የድጋፍ ሐሳብ ቅድሚያ ትኩረት ያገኛሉ የተባሉት ደግሞ ደብረ ብርሃን፣ ሸዋ ሮቢት፣ ከሚሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ወልድያ፣ ላሊበላ፣ ጭፍራና ካሳጊታ ከተሞች ናቸው።የድጋፍ አገልግሎቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነው የዳሰሳ ጥናት በቅርቡ እንደሚጀመር አዘጋጆቹ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ከዳሰሳ ጥናቱ ግኝት በኋላ ለሆቴሎች የሚደረገው ድጋፍ ተለይቶ ወደ ተግባር አንደሚገባ ተነግሯል፡፡የኢትዮጵያ ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሠሪዎች ፌደሬሽን በበላይነት በሚመራው የድጋፍ መርኃ ግብር ላይ ለመሳተፍ ከ270 በላይ የሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎችና 72 የሆቴል አማካሪዎች በበጎ ፈቃድ መመዝገባቸውን ሰምተናል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስድስት ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከአዲስ አበባ ምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች የከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ምላሽ እየሰጡ ነው!

የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮችን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሰጡት ምላሽ፤-

👉ሰላምና ጸጥታ ለሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ አዲስ አበባ ከተማ ሰላም ናት፤የመዲናችን ሰላም መሆን ለሀገሪቱ ሰላም ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

👉አዲስ አበባ ላይ ለመፈጸም ታቅደው የከሸፉ እኩይ ተግባሮችን መነሻ በማድረግ ነው ከተማዋ በአንጻራዊ ሰላም ላይ ናት የምንለው፡፡

👉ህዝቡን በማሳተፍ፤ አመራሩ ተቀናጅቶ በመስራትና ለጥቆማዎች ዋጋ በመስጠት ክትትል በማድረግ የከተማዋን ሰላም ቀጣይነት ያለው ማድረግ ተችሏል፡፡

👉የህግ የበላይነትን ከማስከበር፤ የወንጀል ስጋቶችን ከማስቀረት እና ወንጀልን ከመቀነስ አኳያ ብዙ ስራ ይቀረናል፡፡

👉ሰላማችንን ሊያደፈርሱ የሚችሉና ደህንነታችንን ስጋት ውስጥ ሊከቱ የሚችሉ ሁኔታዎች እና ምክንያቶችን በጥናት ላይ በመመስራት መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

👉የህዝብ ተሳትፎን በማስፋት ዘላቂ ሰላም ማምጣት ይጠበቅብናል፡፡

👉ለሰላምና ደህንነት መደፍረስ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ የተባሉ ጉዳዮችን በጊዜ ምላሽ በመስጠት የደህንነት ስጋቶችን እየቀነስን መሄድ እንችላለን፡፡

👉ለከተማዋ ሰላም መረጋገጥ የጸጥታ አካላት ትልቅ ስራ ሰርተዋል፤ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

👉ፖሊስ ተቋማዊ ሪፎርም ያስፈልገዋል፤አዲስ አበባ ከተማ እራሱን የቻለ ጠንካራ የፖሊስ ሃይል ያፈልጋታል፡፡

👉የአዲስ አበባ ፖሊስ በሎጂስቲክ፤ በብቃት፤ በስነምግባር; በቁጥር ሪፎርም ማድረግ ይገባዋል፡፡

👉ህብረተሰቡ ተደራጅቶ ለከተማዋ ሰላምና ደህንነት ያደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ ዜጎች አሁኑኑ ዩክሬንን ለቀው እንዲወጡ ጆ ባይደን አሳሰቡ!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ ሩሲያ በማንኛውም ሰአት ጥቃት ልትጀምር እንደምትችል ጠቅሰው፤ በዩክሬን የቀሩ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሁሉ ባስቸኳይ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ሩሲያ ዩክሬንን ስትወር አሜሪካውያንን ለማዳን ወታደር አንልክም፣ ስለዚህ በፍጥነት ዩክሬንን ለቃችሁ ውጡ ብለዋል ባይደን፡፡ነገሮች በፍጥነት እየተቀየሩ እደሆነ የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ ያ አካባቢ ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ ቀውጢ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ከ100 ሺህ በላይ ወታደሮችን በዩክሬን ድንበር ያሰፈረችው ሩሲያ ባንድ በኩል በተደጋጋሚ የወረራ እቅድ እንደሌላት እየገለፀች ቢሆንም በሌላ በኩል ከጎረቤት ሀገር ቤላሩስ ጋር ገዘፍ ያለ ወታደራዊ ልምምድ ጀምራለች

ዩክሬን የኔቶ አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ታቁምልኝ አበለዚያ ቀይ መስመሩን አረግጠዋለሁ እያለች ነው፡፡ለዚህኛ የሩሲያ ጥያቄ የምዕራባውያኑ ምላሽ ቀድሞ ነገር ምን አግብቶሽ የሚል ሆኗል፤ አንዲት ሉአላዊ ሀገር የፈቀደችውን ማህበር የመቀላቀል መብት አላት በሚል፡፡የኔቶ አባል ሀገራት የምድር ጦርና የባህር ሀይላቸውን ወደ አካባቢው አስጠግተዋል፡፡ ዩክሬንም የ 10 ቀን ያለችውን ልዩ ወታደራዊ ልምምድ ለብቻዋ ጀምራለች፡፡

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ትናንት አውሮፓ ከአስርት አመታት በኋላ ትልቁን የፀጥታና ደህንነት ቀውስ ተጋፍጣለች ብለዋል፡፡የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርም፤ በአለማችን ግዙፍ የጦር ሀይል ካላት ሀገር ጋር ነው ችግር ውስጥ የገባነው ያለ ሲሆን ሁሉም አሜሪካውያን ባስቸኳይ ዩክሬንን ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል፡፡በጣም በአደገኝነቱ ለየት ስላለ ሁኔታ ነው እየተናገርን ያለነው ያሉት ባይደንም ያ አካባቢ በፍጥነትና ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ ቀውጢ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa