የተደራጀ ቡድን ድንገተኛ ተኩስ ከፍቶ የሕግ ታራሚዎች ማስመለጡን እና ዝርፊያ መፈጸሙ ተገለጸ።
ጥር 30 ለየካቲት 1 አጥቢያ ሌሊት 7 ሰዓት ጀምሮ በላይ ጋይንት ወረዳ ነፋስ መውጫ ከተማ በሚገኙ የወረዳ ማረሚያ ቤት፣ ፖሊስ ጣቢያ እና ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ላይ ጥቃት መድረሱ ተገልጿል።ጉዳዩን አስመልክቶ የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫውም በፋኖ ስም የሚነግድ የተደራጀ ቡድን ድንገተኛ ተኩስ ከፍቶ የሕግ ታራሚዎችን ማስመለጡን እና ከፍተኛ ዝርፊያ መፈጸሙ ተመላክቷል።
የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን መረጃው እንደደረሰው ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር የጸጥታ ኀይሎች ስምሪት በመስጠት ጉዳዩን እየተከታተለ መሆኑን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ውቤ ወንዴ ተናግረዋል። የችግሩን መንስኤ እና ውጤት በማጣራት በአጥፊዎች ላይ ሕጋዊ ርምጃ ለመውሰድ ጥረት እየተደረገ እንደሆነም ገልጸዋል።የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ “ድርጊቱን የፈጸሙት ፋኖ ያልሆኑ ነገር ግን ፋኖ ነን የሚሉና በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ አካላት ናቸው” ብለዋል። እነዚህ አካላት ታራሚዎች እንዲያመልጡ ማድረጋቸውን እንዲሁም በፖሊስ ጣቢያ እና በሚሊሻ ጽሕፈት ቤት የነበረን ትጥቅ ዘርፈው መውሰዳቸውን አመላክተዋል።
ኮሚሽኑ መረጃ እንደደረሰው ከዞኑ የጸጥታ አካላትና እና የፖለቲካ መሪዎች ጋር በመተባበር የኦፕሬሽን እና የወንጀል ምርመራ ቡድን በማሰማራት የተፈጸመውን ወንጀል የማጣራትና አጥፊዎችን የመቆጣጠር ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል። በዚህም ያመለጡ ታራሚዎችን መልሶ በሕግ ቁጥጥር ስር የማዋልና አጥፊዎችን ለሕግ የማቅረብ ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ ነው የተናገሩት። ከተዘረፈው የጦር መሳሪያ መካከል የተወሰነውን መቆጣጠር እንደተቻለም አመላክተዋል።
የኦፕሬሽን እና የወንጀል ምርመራ ቡድኖቹ ቀሪ ሥራዎችን በትኩረት እየሠሩ ነውም ብለዋል።በሂደቱ የዞኑ ሕዝብና የጸጥታ ኀይሉ ተቀናጅቶ አጥፊዎችን ለመቆጣጠር ርብርብ ማድረጉን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። የሕዝብ ብሶት የሚያንገበግበው እውነተኛ ፋኖም አጥፊዎችን ከገቡበት ገብቶ ለመያዝ እየተረባረበ ነው ብለዋል።ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል።
ከዚህ በዘለለ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነሩ በሌሎች የግልና የመንግሥት ተቋማት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን አረጋግጠዋል።በሌሎች አካባቢዎች መሰል ችግር እንዳይከሰት ሁሉም በንቃት አካባቢውን እንዲጠብቅም መልዕክት አስተላልፈዋል።ሕዝቡም ከመላው የጸጥታ ኀይል ጋር በመሆን የክልሉ ሰላምና ደኅንነት እንዲረጋገጥ ርብርብ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል።
@YeneTube @FikerAssefa

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከዚህ (shein.com) website ላይ ያሉ ለሴት እና ለወንድ በተጨማሪም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ
አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga

Kdamie.com ንግድ እና አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ፡፡
#ጅምላና ችርቻሮ ንግዶችን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ከጨረታና ፐርፎርማ እንዲሁም የስራ ማስታወቂያዎች እና መረጃዎች ጋር፣
#በጉዞዎ መዳረሻዎችን ከነ አስጎብኚዎች እና የጉዞ ወኪሎች ጋር
#የእንግዳ ማረፊያ ሆቴልና ሪዞርቶችን ፈርኒሽድ አፓርታማዎችን ገሰት ሀውሶችን እና ፔንሲዮኖችን
ለመኖሪያ የሚሆኑ ቪላ እና ኮንዲሚኒየሞችን
#በሁሉም የገበያ ማዕከላት ለሱቅ እና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎችን ሳይዞሩ ሳይደክሙ የሚያገኙበት Kdamie.com
#በንግድ በቱሪዝም እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ለሆኑ ድጅቶችም ኑ አብረን እንስራ ይሎታል Kdamie.com
ከኛ ጋር መስራት ንግድና አገልግሎቶን ማዘመን፣ደንበኞችዎን ባሉበት ማግኘት ነው!! Kdamie.com
#በሁሉም የማህበራዊ ገፆች
Telegrame እና whatsup - +251-911705126
Kdamie.com - https://tttttt.me/+K7sPcHhHYy44NDI0
facebook - https://www.facebook.com/Kdamie-107188781818909
Instagram - https://www.instagram.com/p/CZkVH-FAd11/?utm_source=ig_web_copy_link
Email - kdamiesells@gmail.com
phone:- +251911705126/+251916821091 ያገኙናል፡፡

በኢትዮጵያ እስካሀሁን 10 ሚሊየን ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባት መውሰዳቸውን በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ ግብረ ኃይል ዋና አስተባባሪ ገለጹ፡፡
10 ሚሊየን ያህል ዜጎች መከተባቸውን የገለጹት አስተባባሪው÷ በቀጣይ የክትባት ዘመቻዎች እስከ 20 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ክትባት እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል ዋና አስተባባሪው ዶክተር መብራቱ ማሴቦ።እስካሁን እድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ ለሆኑት ሲሰጥ የነበረው ፋይዘር ክትባት በዚህ ዘመቻ በትምህርት ላይ ለሚገኙ፣ በሁለተኛ ደረጃ እና በዩኒቨርሲቲ ላሉ ተማሪዎች ጥቅም ላይ እደሚውልም ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ ሲኖፋርም እና በአንድ ዙር የሚሰጠውን ጆንሰን በበርካታ ቁጥር ሀገር ውስጥ እንዲገባ መደረጉን ጠቁመዋል።ማህበረሰቡ በስራ ምክንያት ክትባቶቹን ሳይወስድ እንዳይቀር በእርሻ ቦታዎች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በገበያዎችና በመሳሰሉት ቦታዎች ክትባቱን እንዲያገኝ ዘመቻ የሚካሄድ መሆኑንም ጠቁመዋል።በቅርቡ የሰሞኑ ጉንፋን ሲባል የነበረው አራተኛው ማዕበል መሆኑን የገለጹት አስተባባሪው÷ በዓለም ጤና ድርጅት ስያሜ የተሰጣቸው አራቱ ማዕበላት አልፋ፣ ቤታ፣ ዴልታ እና አሁን ኦሚክሮን ናቸው ብለዋል።
በሁለተኛው ማዕበል ክትባቱ ከመጀመሩ በፊት አብዛኛው ሰው ሆስፒታል ይገባ ነበር፤ በቀን የሚሞተው ሰው እስከ 50 ደርሶ እንደነበር አስታውሰው በአራተኛው ማዕበል የተያዘው ሰው ቁጥር በእጥፍ ጨምሮ በቀን በአማካይ የሚሞተው ሰው ቁጥር ከ20 እንደማይበልጥና በዚህም በዋነኝነት ክትባቱ ከፍተኛ የሞት ቁጥር መቀነሱን አመላክተዋል።በመሆኑም ክትባቱ በቂ የመከላከል አቅም መፍጠሩን በአገራችን በጥናት የተረጋገጠ ነው ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በድንጋይ ከሰል ዕጥረትና በተለያዩ የግብዓት ችግሮች የተነሳ ማምረት እያቆሙ መሆኑን የሲሚንቶ አምራቾች ማኀበር አስታወቀ። ለችግሩም መፍትሄ ለመስጠት ማዕድን ሚኒስቴር እንዳልቻለ ማኀበሩ ገልጿል።
የማዕድን ሚኒስቴር በበኩሉ ወደ ማኀበሩንም ሆነ ወደ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ደብዳቤ በመላክ የትኞቹ ግብዓቶች ላይ እጥረት አለባችሁ የሚል ዝርዝር መጠየቁን መልኩን ገልጾ፤ እስካሁን መልስ ባለመገኘቱ ችግሩን አላወቅኩም፤ መፍትሄም መስጠት አልቻልኩም ብሏል።
የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በግብዓት ዕጥረትና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የተነሳ ማምረት እያቆሙ ነው፤ አንዳንዶችም ችግሩን ተቋቁመው በግማሽ አቅማቸው እያመረቱ ይገኛል ሲሉ ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የሲሚንቶ አምራቾች ማኀበር አመራር ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል።
ኢስት ሲሚንቶ፣ ኢትዮ ሲሚንቶ፣ ሃበሻ ሲሚንቶ ከችግሩ ተጠቂዎች መካከል መሆናቸውን በመጠቆም፤ ይህን ችግር መፍታት ካልተቻለም እንደ አገር ያለው የሲሚንቶ ምርት ይበልጥ እያሽቆለቆለ መሄዱ እንደማይቀር ተናግረዋል።
አንዳንዶች የተሻለ አቅም ስላላቸው የግብዓት ክምችት ይዘው ችግሩን ለማለፍ ጥረት እያደረጉ ነው። በተለይም ዳንጎቴ ሲሚንቶ በቂ የግብዓት ክምችት ስለያዘ በጥሩ ሁኔታ እያመረተ ይገኛል። ሙገርን ጨምሮ በርካታ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ግን የድንጋይ ከሰል ጨምሮ የተለያዩ የግብዓት ዕጥረት እየፈተናቸው በመሆኑ የሲሚንቶ ምርት በሙሉ አቅማቸው እያመረቱ አይደለም ብለዋል።
@YeneTube

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች በየጊዜው ጦርነት እየተከፈተበት የሚገኘውን የአፋር ሕዝብ እንዲደግፉ ጥሪ አቀረቡ።
በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ የተመራ የልዑካን ቡድን ከርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና ከተለያዩ የጎሳ መሪዎች ጋር ወቅታዊ የክልሉን ሁኔታ በተመለከተ ውይይት አድርጓል።
@YeneTube @FikerAssefa
በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ የተመራ የልዑካን ቡድን ከርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና ከተለያዩ የጎሳ መሪዎች ጋር ወቅታዊ የክልሉን ሁኔታ በተመለከተ ውይይት አድርጓል።
@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች በኤሌክትሪክ ሀይል መሰረተ ልማት ላይ ያደረሰዉን ጉዳት ለመተካት ከ23 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል ተባለ!
በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የህወኃት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች በኤሌክትሪክ ሀይል መሰረተ ልማት ላይ ያደረሰዉን ጉዳት መልሶ ለመተካት ከ 23 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልገዉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን እንዳስታወቁት ህወሓት በሁለቱ ክልሎች ላይ ያደረሰዉ የመሰረተ ልማት ዉድመት ሰፊ እንደነበር መናገራቸውን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።
ቡድኑ ባደረሰዉ ውድመት እና ዝርፊያም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ከ 1.6 ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበትም አስታዉቀዋል ። እንደ አቶ ሞገስ መኮንን ማብራሪያም ይህን ዉድመት ለመተካት ከ 23 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በአፋር ክልል አዲስ ባገረሸዉ ጦርነት ከ300 ሺህ በላይ ንፁሃን መፈናቀላቸዉን ተገለጸ!
ህወሃት አዲስ ጦርነት በከፈተበት በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ ዞን የሚገኙ ስድስት ወረዳዎችን መቆጣጠሩና በነዚህ ወረዳዎችም ከ300 ሺህ በላይ ንፁሃን አርብቶ አደሮች መፈናቀላቸዉን የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አወል አርባ መግለጻቸዉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን አስታወቀ።
አቶ አወል አርባ ይሄን ያሉት በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና በተመድ ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሀመድ ከተመራው ልኡክ ጋር በተወያዩበት ወቅት ህወሀት በአፋር ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት የጅምላ ግድያ ግፍና ሰቆቃ አስመልክቶ ለልኡኩ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል።
በእነዚህ አካባቢዎች ህፃናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ የዘር ማጥፋት የፈፀመ እንደሚገኝ እና ዜጎች ከባድ ለሆነ ስቃይና እንግልት መዳረጋቸውን የገለጹት ፕሬዝዳንት አወል አርባ በከበደ ችግር ውስጥ ላለው የአፋር ህዝብ አስቸኳይ የሰብአዊ ድገፍ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸውም ተሰምቷል።
ፕሬዝዳንቱ በማብራሪያቸው አሸባሪው ህወሀት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በአፋር ንፁሀን አርብቶ አደሮች ላይ እያደረሰ ያለው የዘር ማጥፋት እንዳልቆመና አርብቶ አደሩ ህዝብን ከጅምላ ግድያ የዘር ማጥፋት ጀምሮ ስቃይ እና እንግልት እያደረሰ መሆኑን ገልፀዋል ነዉ የተባለዉ። ፕሬዝዳንቱ "አለም የገዳዮችን ድምፅ የሚሰማበት የሟቾችን ድምፅ የማይሰማበት ምክንያት ምን ይሆን?" ሲሉ በመጠየቅ የአለም መንግስታትና ሚዲያዎች የሟቾችን ድምፅ ሊሰሙ ይገባል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።
ከውይይቱ በኋላም ልኡካን ቡድኑ አሸባሪዉ ህወሀት በቅርቡ በኪልበቲ ረሱ ዞን በከፈተው ጦርነት በከባድ መሳሪያ ባደረገው ድብደባ የተጎዱ ህፃናትን በዱብቲ ሆስፒታል በመገኘት የጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸው ባዩት ነገር በጣም ማዘናቸውንና ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ እንደሚሰሩም መገለጹን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
Via Addis Zeybe

የሀገር ውስጥ ቢራ ፋብሪካዎች በግብዓት የዋጋ ጭማሪ ምክንያት በምርታቸው ላይ የዋጋ ማስተካከያ ማድረጋቸው ተሰማ።
በኢትዮጵያ በብዛት ከሚጠጡት የቢራ ዓይነቶች መካከል ሁለቱ ድራፍት እና የታሸገ ቢራ በዚህ ሳምንት ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ተደርጎበታል።ከቢራ ፋብሪካዎቹ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ከፍተኛ የግብአት ዋጋ መጨመር የመጨረሻ ምርታቸውን መጠን እንደገና እንዲያስተካክሉ አስገድዷቸዋል።"በቅርብ ጊዜ የተከሰተው የምንዛሪ ዋጋ መናር እና የነዳጅ ዋጋ መጨመር በምርት ዋጋ ላይ ማስተካከያ ለማድረግ አስገድዶናል" ብለዋል ምንጮች።በቢራ ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ማስተካከያ በሁለት ዓመታት ውስጥ ሁለተኛው ነው።
Via Capital

አብን በወለጋው ግድያ የመንግስት አመራር በከፊል ቀጥተኛ ተሳታፊ ነው አለ!
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ባወጣው የአቋም መግለጫ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ለተፈጸመው ዘግናኝ ግድያ የመንግስት አመራር በከፊል ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆኑን ገለጠ።አብን በመግለጫው፦ «በከፊሉ የመንግስት አመራር ደንታ ቢስነት እና በከፊሉ ቀጥተኛ ተሳትፎ የመሆኑ ጉዳይ ችግሩን ውስብስብ ያደርገዋል» ብሏል። አብን፦ አሸባሪ ያለው «የሸኔ ቡድን በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ከሰሞኑ በፈፀማቸው ጭፍጨፋዎች በወረዳው በተለያዩ አካባቢዎች 81 ወገኖቻችን ተግድለዋል፣ እንዲሁም በጅምላ ተገድለው አስከሬናቸው አንድ ቦታ የተገኙ 87 ሰዎች በድምሩ 168 ወገኖች መገደላቸው ተረጋግጣል» ብሏል። ግድያውንም «የዘር ተኮር ጥቃት» ብሎታል።
«የአማራ ሕዝብ ፍላጎት በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በሰላምና በእኩልነት መኖር ብቻ ነው» ያለው አብን ጥቃት ፈጻሚዎች ላይ «ፈጣንና አስተማማኝ ርምጃ ሊወሰድባቸው» እንደሚገባ አሳስቧል።
አብን በመግለጫው፦ መላው ሕዝብ «በአፋር በኩል ላለው ግጭት ትኩረት እንዲያደርጉ፣ ከአፋር ሕዝብ ጎን እንዲቆሙ»ም ጥሪ አስተላልፏል። «የፌድራሉ መንግስት ለአፋር ሕዝብ አስፈላጊውን ትኩረት እንዲሰጥና እገዛ እንዲያደርግ» ጠይቋል።
«በራያና ጠለምት ሕዝብ ላይ» እየተፈጸመ ነው ያለው «ድርብርብ ቀውስ አፋጣኝ መንግስታዊ ትኩረት» እንደሚሻም አጥብቆ ጠይቋል።
የአብን መግለጫ፦ «በሕዝባችን ላይ ጥቃቱን የፈፀሙ አካላት በአስቸኳይ ለሕግ እንዲቀርቡ እና ለተበዳዮች ካሳ እንዲከፈል ስንል እንጠይቃለን» ሲል ይጠናቀቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል።
ምክር ቤቱ በጉባኤው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።የምክር ቤቱ ጽ/ቤት የፕሬስና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስአለም እንቻለው የጉባኤው አጀንዳዎችን አስመልክክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ ምክር ቤቱ የአስተዳደሩን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምን ይገመገማል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ፍርድ ቤቶች የስድስት ወራት አፈጻጸም፣ የመሬት ይዞታ ማስለቀቅ እና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ ተወያይቶ ማጽደቅ እንዲሁም ልዩ ልዩ ሹመቶችን ማጽደቅም የምክር ቤቱ አጀንዳዎች ናቸው።የአዲስ አበባ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የመዋቅር ማሻሻያ አዋጅም ለጉባኤው ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበትም ነው የተገለጸው።

ሳፋሪኮም-ኢትዮጵያ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ሥራ እንደሚጀመር ተነገረ።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የቁጥጥርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማቲው ሃሪሰን ሃርቬይ ለካፒታል እንደነገሩት ከመንግስት ጋር ያላቸው ስምምነት እንደሚያሳየው የፍቃድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በዘጠኝ ወር ወደ ስራ መግባት እንደሚኖርባቸው ገልፀው ከመጪው ሚያዝያ 9,2021 /እ.ኢ.አ/ጀምሮ በይፋ የንግድ ሥራ ለመጀመር እየሰራን ነው በለዋል።ከሐምሌ 9 2021 ጀምሮ የሚቆጠር የመሥሪያ ፍቃድ ያገኘው ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽን ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የቴሌኮም ማስፋፊያ ስራዎችን ጀምሯል።
ባለፈው ወር የኩባንያው የመጀመሪያ የመረጃ ማዕከል ስራ የጀመረ ሲሆን ኩባንያው የኔትወርክ ዝርጋታውን እየሰራ ነው።ሁለት የኔትወርክ አቅራቢዎች ማለትም ኖኪያ እና ሂዋዌ ጋር እየሰራ መሆኑን የገለፁት ሀላፊው በአዲስ አበባ እና አካባቢው ያለውን የኮር ኔትወርክ መሠረተ ልማት ኖኪያ ኩባንያ የሚሠራ ሲሆን ሁዋዌ ቀሪውን የአገሪቱን ክፍል ይሸፍናል ብለዋል።የመሰረተ ልማት መጋራት በተመለከተም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እስካሁን ስምምነቱ የለንም ነገር ግን በድርድር ደረጃ ላይ ነን ብሏል።ከመሰረተ ልማት ጎን ለጎን የሳፋሪ ኮም ደንበኞች እና የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች እንዲገናኙ ለማድረግ ስራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልጿል።

ሕወሓት በአፋር ክልል የጅቡቲ መስመርን ለመቁረጥ ቢሞክርም አልተሳካለትም ተባለ!
ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)በአፋር ክልል ሰርዶ የፍተሻ ኬላን ለመቁረጥ ጥረት ቢያደርግም እንዳልተሳካለት የአፋር ክልል ዛሬ ዐስታወቀ። የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ፦ አቶ አህመድ ኮሎይታ ለዶይቸ ቬለ (DW) ዛሬ ከሰአት አካባቢ እንደተናገሩት ሕወሓት «እስካሁን ድረስ ሰርዶን አልቆረጠም» ብለዋል።«ከተሳካለት ግን ያንን አካባቢ ቆርጦ አሁንም መጀመሪያ ያልተሳካለትን ሕልም የማሳካት ዓላማ አለው» ሲሉም አክለዋል። የአፋር ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ የመከላከል ሥራ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት በክልሉ በዞን 1፤ 4 እና 5 በኩል ሕወሓት ሚሌን ለመቁረጥ ከፍተኛ ጥረት አድርጎ የነበረ ቢሆንም፤ እንዳልተሳካለት ኃላፊው ገልጠው «ያ ሳይሳካለት ሲቀር እና እዚያ አካባቢ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ የበቀል ርምጃ ነው አሁን ዞን 2 ላይ መልሶ እየወሰደ ያለው» ብለዋል።
አቶ አህመድ፦ «በአፋር አካባቢ በተለይ በሰሜናዊ ዞን፤ በዞን 2፤ ኪልቤት ራሱ በሚባለው አካባቢ» ጦርነቱ እየተካኼደ መሆኑን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።
አካባቢው ከትግራይ ክልል አዋሳኝ ዞኖች አንዱ ነው። ከመጋሌ ወረዳ ጀምሮ እስከ ኮነባ ድረስ ጦርነት በአሁኑ ወቅት እንዳለም ተናግረዋል።«በመጋሌ፣ አብአላ፣ ኢሬብቲ፣ በራህሌ እና ኮነባ ወረዳዎች ላይ የሕወሓት ኃይል በከባድ ጦር መሣሪያ በተለይ ሕጻናት እና ሴቶች ሕይወታቸው እንዲጠፋ» አድርጓል ብለዋል። በጦርነቱ ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው፤ የሟቾችን ቁጥር ለመለየት ግን ጦርነት ስላለ አዳጋች መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም ከ430 ሺህ በላይ ሕዝብ በአካባቢው ተፈናቅሎ ነበር ያሉት ኃላፊው «ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ማኅበረሰብ ደግሞ በዚሁ ጉዳት ሰለባ ነበር» ብለዋል።በተጠቀሱት ወረዳዎች ካለፉት ሁለት ሳምንታት አንስቶ ተደጋጋሚ ጥቃቶች መሰንዘራቸውም ተገልጧል።ሕወሓት በኢትዮ-ጀቡቲ አዉራ መንገድ ላይ ወደምትገኘዉ ሰርዶ የፍተሻ ኬላ መቃረቡን የአፋር ክልል መስተዳድር ትናንት ዐስታውቆ ነበር። ሰርዶ ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያን ከጅቡቲ ወደብ ጋር በሚያገናኘዉ አዉራ መንገድ ላይ የምትገኝ የፍተሻ ኬላ ናት።
Via DW

የሰሜን ኢትዮጵያውን ግጭት በሰላም ለመጨረስ የሚደረጉ ጥረቶች እንደቀጠሉ መሆናቸውን የመንግስታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ጸሃፊ አሚና መሃመድ አስታውቀዋል።
ምክትል ዋና ጸሃፊዋጨይህን ያሉት የ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከተሳተፉ በኋላ በትግራይ በአማራ በአፋርና በሶማሌ ክልል ያደረጓቸውን ጉብኝቶች አጠናቀው አጠር ያለ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ጊዜ መሆኑን የዋዜማ ሪፖርተር ዘግቧል። የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ማሳሰባቸውን የጠቀሱት ምክትል ዋና ጸሃፊዋ በቆይታቸው ከፌደራልና ከክልሎች አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በአገሪቱ ሰላም በሚሰፍንበትና የሰብዓዊ ድጋፎች ተደራሽነት ዙርያ መምከራቸውን ገልጸዋል ። በጉብኝታቸው በሁሉም ወገን በግጭቱ የተፈጸሙ አሳዛኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መመልከታቸውን የጠቀሱት ምክትል ዋና ጸሃፊዋ አሁን በኢትዮጵያ ከተወሰኑ ወራቶች በፊት ከነበረው አንጻር አነስተኛ ግጭቶች መኖራቸውንና ይህም ነገሮች በተሻለ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ማሳያ ነው ብለዋል። አክለውም ተመድ በአገሪቱ በብሔራዊ ምክክር ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ እንደሚደፍ ገልጸው መንግስት ሁሉን አካታች የሰላም ውይይት እንዲያደርግ እናበረታታለን ብለዋል።
[Wazema]

Forwarded from YeneTube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከዚህ (shein.com) website ላይ ያሉ ለሴት እና ለወንድ በተጨማሪም ለህጻናት የሚሆኑ እቃዎችን ትዕዛዝ መቀበል ጀምረናል ይዘዙን
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
Contact @kiru04
0931607806
https://tttttt.me/onlinesaleandbuystore
Forwarded from YeneTube
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ
አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Forwarded from YeneTube
Kdamie.com ንግድ እና አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ፡፡
#ጅምላና ችርቻሮ ንግዶችን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ከጨረታና ፐርፎርማ እንዲሁም የስራ ማስታወቂያዎች እና መረጃዎች ጋር፣
#በጉዞዎ መዳረሻዎችን ከነ አስጎብኚዎች እና የጉዞ ወኪሎች ጋር
#የእንግዳ ማረፊያ ሆቴልና ሪዞርቶችን ፈርኒሽድ አፓርታማዎችን ገሰት ሀውሶችን እና ፔንሲዮኖችን
ለመኖሪያ የሚሆኑ ቪላ እና ኮንዲሚኒየሞችን
#በሁሉም የገበያ ማዕከላት ለሱቅ እና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎችን ሳይዞሩ ሳይደክሙ የሚያገኙበት Kdamie.com
#በንግድ በቱሪዝም እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ለሆኑ ድጅቶችም ኑ አብረን እንስራ ይሎታል Kdamie.com
ከኛ ጋር መስራት ንግድና አገልግሎቶን ማዘመን፣ደንበኞችዎን ባሉበት ማግኘት ነው!! Kdamie.com
#በሁሉም የማህበራዊ ገፆች
Telegrame እና whatsup - +251-911705126
Kdamie.com - https://tttttt.me/+K7sPcHhHYy44NDI0
facebook - https://www.facebook.com/Kdamie-107188781818909
Instagram - https://www.instagram.com/p/CZkVH-FAd11/?utm_source=ig_web_copy_link
Email - kdamiesells@gmail.com
phone:- +251911705126/+251916821091 ያገኙናል፡፡
#ጅምላና ችርቻሮ ንግዶችን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ከጨረታና ፐርፎርማ እንዲሁም የስራ ማስታወቂያዎች እና መረጃዎች ጋር፣
#በጉዞዎ መዳረሻዎችን ከነ አስጎብኚዎች እና የጉዞ ወኪሎች ጋር
#የእንግዳ ማረፊያ ሆቴልና ሪዞርቶችን ፈርኒሽድ አፓርታማዎችን ገሰት ሀውሶችን እና ፔንሲዮኖችን
ለመኖሪያ የሚሆኑ ቪላ እና ኮንዲሚኒየሞችን
#በሁሉም የገበያ ማዕከላት ለሱቅ እና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎችን ሳይዞሩ ሳይደክሙ የሚያገኙበት Kdamie.com
#በንግድ በቱሪዝም እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ለሆኑ ድጅቶችም ኑ አብረን እንስራ ይሎታል Kdamie.com
ከኛ ጋር መስራት ንግድና አገልግሎቶን ማዘመን፣ደንበኞችዎን ባሉበት ማግኘት ነው!! Kdamie.com
#በሁሉም የማህበራዊ ገፆች
Telegrame እና whatsup - +251-911705126
Kdamie.com - https://tttttt.me/+K7sPcHhHYy44NDI0
facebook - https://www.facebook.com/Kdamie-107188781818909
Instagram - https://www.instagram.com/p/CZkVH-FAd11/?utm_source=ig_web_copy_link
Email - kdamiesells@gmail.com
phone:- +251911705126/+251916821091 ያገኙናል፡፡
💕💕Valentine Day Special Gift Packages💕💕
የፍቅረኞችን ቀን ምክንያት በማረግ የወንዶች, የሴቶች እና የጥንዶችየተለያዩ የስጦታ ጥቅሎችን አዘጋጅተናል
❤️ብራንድ የእጅ ሰዓት ከስጦታ ሳጥን ጋር (የወንዶች የሴቶች እና የጥንዶች)
❤️ አሻንጉሊት (የተለያዩ ምርጫዎች የሚገኙበት)
❤️ የአንገት ሐብል (ለወንዶች ቀበቶ)
❤️ የእጅ ጌጥ (የወንዶች እና የሴቶች)
❤️ የጆሮ ጌጥ
❤️ ቀለበት (የወንዶች እና የሴቶች
🎁 ከነፃ ስጦታ መያዣ ጋር
❤️ ሁሉንም በአንድ ያግኙ
Contact @be_liye 0941573710
ተጨማሪ የስጦታ እቃዎችን ለማግኘት Telegram Channel ይቀላቀሉ
https://tttttt.me/simplysellerstore

#NEAEA
" ... አሁን የመቁረጫ ነጥቡ ( የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ) ይለያል አይለይም የሚለውን ኤጀንሲው ሊወስን አይችልም፤ የኤጀንሲውም ስልጣን አይደለም " - አቶ ተፈራ ፈይሳ
በሁለተኛው ዙር የሀገር አቀፍ ፈተና በፀጥታ ችግር ምክንያት ፈተና ላይ መቀመጥ ያልቻሉ ተማሪዎች ከጥቂት ቀናት በፊት ፈተናቸውን ወስደዋል።
በአጠቃላይ በአማራ፣ አፋር፣ኦሮሙያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከ60 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተና ወስደዋል።
ፈተናውም የወሰዱ ተማሪዎች እና የትምህርት ባለሙያዎች " ተፈታኞች ያሳለፉትን የስነልቦ ጫና እና አስቸጋሪ ሁኔታ ከግምት ያስገባ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ሊኖር " ይገባል እያሉ ይገኛሉ።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክታ ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል ይህንን የመወሰን ስልጣን የኤጀንሲው እንዳልሆነ ገልፀዋል።
አቶ ተፈራ ፈይሳ ፥ " ... ያሉ ጥያቄዎች አሉ፤ ይሄን ኤጀንሲው አሁን ላይ የሚለውም ምንም ነገር የለም። በዚህ ደረጃ ኤጀንሲው አይወስንም ፤ ይህ ትልቅ ጉዳይ ስለሆነ። ዞሮ ዞሮ ችግሩ እንዳለ እንረዳለን። ችግሩን ለመፍታት እኛ የተወሰነ ጊዜ ከመስጠት ባሻገር አሁን የመቁረጫ ነጥቡ ይለያል አይለይም የሚለውን ኤጀንሲው ሊወስን አይችልም የኤጀንሲውም ስልጣን አይደለም። ...ይሄን የሚወስነው መንግስት ነው "
በሌላ በኩል ፤ ኤጀንሲው በትግራይ ክልል ካሉ ተማሪዎች ጋር በተያያዘ የታሰበ ነገር ያለ እንደሆነ ከሬድዮ ጣቢያው የተጠየቁት አቶ ተፈራ ፥ " በእኛ በኩል የሚፈታ አይደለም። ከአጠቃላይ ከሀገራዊ ፀጥታ ጋር የሚታይ ስለሆነ ሀገራዊ ፀጥታው ሲረጋገጥ ፣ ትግራይም እንደማንኛውም ክልል ሰላም ሲሆን ፈተና የምንፈትነው " ሲሉ መልሰዋል።
Via VOA
@Yenetube @Fikerassefa

❤1