ሁለት ጊዜ ለኢትዮጵያ የተዋጉት ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ
በደርግ ዘመነ መንግስት የጦር አውሮፕላን አብራሪ የነበሩት ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ እየተዋጉ ሳለ በኤርትራ ሕዝብ ነጻነት ግምባር ሰራዊት ተይዘው ኤርትራ መቆየታቸው ይታወሳል።
የደርግ መንግስት በ1983ዓ.ም ከወደቀ በኋላ ኮሎኔሉ ተይዘው ከነበረበት ኤርትራ ወደ ሀገራቸው ቢመለሱም ኢትዮጵያና ኤርትራ በ1990ዓ.ም ዳግም ወደ ጦርነት ሲያመሩ በድጋሚ የጦር አውሮፕላን አብራሪ በመሆን ጦርነቱ ላይ ዘምተው ነበር።
ኮሎኔል በዛብህ በዉጊያ ወቅት በኤርትራ ኃይሎች ከተያዙ በኋላ በህይወት አሉ ወይስ የሉም የሚል ድምዳሜ ላይ እስካሁን አለመደረሱን ቀደም ሲል ቤተሰቦቻቸው ሲገልጹ ቆይተዋል።
የኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሐውልት በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የቆመላቸው ሲሆን፤ ሐውልት 17.5 ሜትር ቁመት ያለው ሲሆን፤ በ5 መቶ 30 ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈ ነው።
https://am.al-ain.com/article/statue-of-colonel-bezabh-peter-who-has-fought-twice-for-ethiopia

የሲዳማ ክልል በዘንድሮ ዓመትም ዞን ማዋቀር እንደማይችል አስታወቀ
ከሁለት አመት በፊት 10ኛ የፌደራል ክልል ሆኖ በሕዝበ ውሳኔ የተቋቋመው የሲዳማ ብሄራዊ ክልል በያዝነው 2014 ዓመት የዞን የአስተዳደር መዋቅር መዘርጋት እንደማይችል አስታወቀ።
ዞን ማዋቀር ከወጪ ጋር የሚያያዝና የራሱን በጀት የሚፈልግ በመሆኑ፣ የሚመደቡ አመራሮች ፣ ባለሙያ፣ ተሽከረካሪዎች እና ሎሎች ውጪዎችን በመቀነስ ፣ ቅድሚያ በጣም ወሳኝ ለሆኑ ለህዝብ አገልግሎት የሚውሉ የልማት ስራዎችን መስራት እንደመረጠ ክልሉ ይናገራል። የሲዳማ ክልል ባለፈው ዓመትም የዞን አደረጃጀቱን ይዘረጋል ተብሎ ይጠበቅ ነበር።
የዞን አስተዳደር ማዋቀር እንዲዘገይ ቢደረግም በሂደት የዞን መዋቅር የሚዘረጋበት አካሄድ ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ የኮምዩኒኬሽን ፅ/ቤት/ሃላፊ አቶ ፊልጶስ ናሆም ለዋዜማ ተናግረዋል ።
በሲዳማ ክልላዊ መንግስት ህገ መንግስት እንደተቀመጠው፣ ክልሉ በፈለገው ጊዜ የዞን እና የወረዳ መዋቅሮች እንደሚያቋቁም ደንግጓል።
በዚህም መሰረት በሲዳማ ከአምስት ያልበለጠ ዞን ሊዋቀር እንደሚችል መቀመጡን አቶ ፊሊጶስ ነግረውናል።
በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፌደራሊዝም መምህር ሰለሞን ንጉሴ (ዶ/ር) እንደሚሉት ከሆነ ሲዳማ የዞን መወቅሮችን ለመትከል መዘግየቱና እንደ መንገድ፣ ጤና ኬላ እና ትምህርት ቤት ያሉ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ቅድሚያ መስጠቱ መልካም ነው።
ምናልባትም ለሌሎች ክልሎች በአርአያነት የሚወሰድ ሊሆን ይችላል ይላሉ።
እንደ አቶ ፊልጶስ ከሆነ ሲዳማ ራሱን የቻለ ክልል ሲሆን “ኑሯችን ይለወጣል” የሚጠብቁ የክልሉ ተወላጆች መኖራቸውንና ቅድሚያ የሚሰጠውም የክልሉን መስረታዊ የልማት ችግሮች ማቃለል መሆኑን አስረድተዋል።
ለአብነትም በ2013 ዓ.ም በመንግስት ብቻ 1.5 ቢሊየን ብር ካፒታል በጀት ተይዞ መንገድ፣ ጤና ኬላዎች፣ የንፁህ ውሃ አቅርቦት እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
የፀጥታ ሁኔታን በተመለከት ክልሉ 1,100 የደቡብ ብሄር ብሄረሰብ ክልል ውስጥ የነበሩ የሲዳማ ክልል ተወላጆችን ጨምሮ ዘንድሮ ደግሞ 1,000 የሚደርሱ አዲስ የልዩ ኋይል አባላትን ማስመረቁን ፣ ነባር ፖሊስን ሳይጨምር በድምሩ 2,100 የሚደርሱ አባላት እንዳሉት ነግረውናል።
Via:- [ዋዜማ ራዲዮ]
@Yenetube @Fikerassefa

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት 10.1 ሚሊዮን ደንበኞችን አፍርቻለሁ አለ!
ዛሬ የ2014 በጀት አመት የመጀመሪያ መንፈቅ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ ለመገናኛ ብዙሀን አቅርበዋል፡፡ወ/ት ፍሬህይወት ባለፉት ስድስት ወራት የኩባንያው እቅዶች በአመዛኙ ሙሉ በሙሉ የተሳኩ ቢሆንም በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት መቶ በመቶ አፈጻጸም ያልተመዘገበባቸው እቅዶች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡
የደንበኞች ቁጥር 60.8 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተጨማሪ 10.1 ሚሊዮን ደንበኞች ማፍራት ተችሏል፡፡በሪፖርቱ የገመድ አልባ ተጠቃሚዎች ቁጥር 58.7 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን የመደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 443 ሺ የደረሰ ሲሆን የ43 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
133 ሺ አዲስ የመደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ባለፉት ስድስት ወራት ማፍራት መቻሉን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አስታውቀዋል፡፡ባለፉት ስድስት ወራት ኩባንያው 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን የእቅዱን 86.4 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡
ኩባንያው በውጭ ምንዛሬ ገቢ ከሚያገኝባቸው አገልግሎቶች 74.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያገኘ ሲሆን የእቅዱን 89.3 ማሳካት መቻሉ ተገልጿል፡፡በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተቀሰቀሰው ጦርነት ወደ አማራ እና አፋር ክልል መስፋፋቱ በተጨማሪም በኮቪድ 19 አለም አቀፋዊ ተጽእኖ ምክንያት ከውጭ የሚመጡ ግብአቶች እና ቁሳቁሶች በወቅቱ መግባት አለመቻላቸው ኩባንያው ከገቢ አንጻር በስድስት ወራት ውስጥ ለማግኘት ያቀደውን ያህል እንዳያሳካ ያደረጉ ምክንያቶች መሆናቸውን ወ/ት ፍሬህይወት አስታውቀዋል፡፡
መንግሥታዊው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ኢትዮ ቴሌኮም፣ በአጠቃላይ ካሉት 8 ሺ የሞባይል ጣቢያዎች መካከል 3 ሺ 473 የሚሆኑት በጦርነቱ ምክንያት አገልግሎት አለመስጠታቸውን አብራርተዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በዛሬው መግለጫቸው ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቀዋል፡፡ሆኖም ተቋሙ ያገኘው ገቢ በዕቅድ ከያዘው 86 ነጥብ 4 በመቶውን ያሳካ መሆኑን ፍሬሕይወት ገልጸዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በዕቅድ ያስቀመጠውን ያህል ገቢ ማግኘት ያልቻለው በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት እንደሆነ ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አመልክተዋል።ለዚህ በማሳያነት በሚል ተቋሙ ካሉት ስምንት ሺህ የሞባይል ጣቢያዎች ውስጥ 3 ሺ 473 ያህሉ በጦርነቱ ምክንያት አገልግሎት አለመስጠታቸውን ነው ያነሱት፡፡
Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa

በ6 ወራት ብቻ 16 ዝሆኖች በሕገወጥ አዳኞች ተገድለውብኛ ሲል የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ የመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው የዱር እንስሳት መካከል ዝሆን አንዱ ነው ብሏል፡፡
ሕገወጦችን ማስቆም ካልተቻለ በኢትዮጵያ ዝሆን የሚጠፋበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን አስታውቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከ 1800 የማይበልጡ ዝሆኖች እንዳሉ በዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የዱር እንስሳት ሕግ ማስከበር ዳይሬክተር ዳንኤል አሰፋ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በዋናነት በጥበቃ ስፍራዎች ላይ የሚደረጉ የሕገወጥ ሰፈራዎች፣ ሕገወጥ አደን ፣ደን ምንጣሮ እንዲሁም እርሻ ለዱር እንስሳቱ ዛሬም ድረስ አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ነው የተናገሩት፡፡
[አሐዱ]

ሙስጠፌ መሃመድ በተመድ የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ልዑካን ጋር ተወያዩ!
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ዳንኤል እንድሪስ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱም በክልሉ አሁን ላይ በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ሙስጠፌ ለልዑካን ቡድኑ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በዚህም በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልግ እና በቀጣይ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሥምምነት ላይ መደረሱን ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

የአንጋፋው ሀገር ፍቅር ቴአትር ዕድሳት ሥራ ተጠናቀቀ!
በ1927 አገርን ከጠላት ወረራ ለመታደግ ይቻል ዘንድ ሀገር ፍቅር ማህበር ተብሎ የተመሰረተውና ኋላ ላይ በ1960 ሀገር ፍቅር ቴአትር ተብሎ እንደተቋቋመ የሚነገርለት አንጋፋው ቴአትር ቤት ታሪካዊ ይዘቱንና የምህንድስና ጥበቡን ሳይለቅ ዘመኑን እና የቴአትር ቤቱን ሥም በሚመጥን መልኩ ዕድሳቱ ተጠናቆ የመጀመሪያ ርክክብ ተደርጓል፡፡
ላለፉት 20 ዓመታት አንዳችም ዕድሳት ያልተደረገለት ቴአትር ቤቱ የዕድሳት ሥራው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተከናውኖ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ ርክክብ ተደርጓል፡፡
610 መቀመጫዎች የሚኖሩት ዋናው የቴአትር ማሳያ አዳራሽን ጨምሮ አርት ጋለሪ፣ አነስተኛ የቴአትር አዳራሽ፣ ዘመናዊ የሙዚቃ መከወኛ ክፍል፣ ካፊቴሪያ፣ የአስተዳደር ህንፃ እና ሌሎችም አገልግሎቶች ተካተውበታል፡፡
በዚህም ቴአትር ቤቱ ለተደራሲው ከፍ ያለ ምቾትን ከማጎናፀፉ በተጨማሪ የጥበብ ሰዎችንም ለተሻለ የፈጠራ ሥራ የሚያነሳሳ ምቹ እና ፅዱ የኪነጥበብ ቤት ሆኖ የዕድሳት ሥራው መጠናቀቁን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአማራ ክልል የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ለመፍታት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ!
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የአማራ ክልልን የነዳጅ እጥረትን በዘላቂነት ለመፍታት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና፣ የከተማ አስተዳድር ኃላፊዎች በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡
የኢትዮጵ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታደሰ ሀይለማሪያም በክልሉ የነዳጅ እጥረት የሚከሰተው የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያው ለክልሉ ማድረስ ያለበት ነዳጅ ለማደያዎች በትክክል መድረስ አለመድረሱ ክትትልና ቁጥጥር ባለመደረጉና በኮንትሮባንድ ወደ ጎረቤት አገራት በመውጣት እየተሸጠ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡፡
አክለውም በክልሉ የነዳጅ እጥረትን በዘላቂነት ለመፍታት በኮንትሮባንድ ከአገር የሚወጣውን ነዳጅ ለማስቀረት የተጀመረውን ሥራ አጠናክረን በመስራት፣ የማደያዎችንና የዲፓ ቁጥር መጨመር ህግወጥ ነጋዴዎችን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግና የመረጃ ቅብብሎሹን በማዘመን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አማካሪ አይናለም በበኩላቸው በኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ድልድሉ ፍትሃዊ እንዲሆን ማድረግ፣እንደ ክልል በባህር ዳር ከተማ ለመገንባት የታቀደው የዲፖ ግንባታ እንዲፋጠን ማድረግና ህገወጥ ነጋዴዎችን በመቆጣጠር በክልሉ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ በኩል በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የክልሉ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ቀለምወርቅ ምህረቴ በበኩላቸው፣ በክልሉ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ለመፍታት መንግስት ከሌሎች መሰረታዊ ምርቶች ጋር አቀናጅቶ ከፍተኛ ድጎማ እያደረገባቸው ቢሆንም አንዳንድ ባለሀብቶች በህገ ወጥ መንገድ ለመበልጸግ ችግሩ እንዲባባስ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም የትራንስፖርቱ ዘርፍ በተገቢው መንገድ በማንቀሳቀስ ኢኮኖሚውን ማስቀጠል ስለሚገባ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን እንዲወጣ፤ በተለይም ባለሀብቱ በማደያ ግንባታ እንዲሳተፍ መጠየቃቸውን ከአማራ ኮምዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ታስረው እንዲቀርቡ ትዛዝ ተሰጠ!
ከህዳር 4 ቀን 2011ዓ/ም ጀምሮ በስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሜቴክ ዳሪክተር ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ከዕርሻ መሳሪያ ግዢ ጋር ተያይዞ በዓቃቢህግ በቀረበባቸውባቸው የሙስና ክስ የመከላከያ ማስረጃ ማሰማት መጀመራቸው ይታወሳል።
በዚህም መሰረት በሀምሌ 11ቀን 2013 ዓ/ም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ፍርድ ቤት ቀርበው እ.ኤ. አ በ2014 ዓ/ም በተደረገ በዝቅተኛ ወለድ ስምምነት ኢትዮጲያ ከፖላንድ መንግስት ባገኘችው 50 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ እዛው ፖላንድ ሀገር ለሚገኙ የዕርሻ መሳሪያ መለዋወጪያ ኩባንያዎች መከፈሉን እና ገንዘቡ ወደ ሀገር ውስጥ አለመምጣቱን በማብራራት የመከላከያ የምስክርነት ቃላቸው ተሰምቶ ነበር።
በዚሁ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ትዛዝ ተሰቶባቸው የነበሩት የቀድሞ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ናቸው።
ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መጥሪያ እንዲያደርስ የታዘዘው የፌደራል ፖሊስ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በኩል አፈላልጌ ላገኛቸው አልቻልኩም ሲል መልስ ሰቶ ነበር።
የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በግላቸው የሮማን ፉውንድሽን እንደሚሰሩና በመንግስ ፖሊስ እጀባ እየተደረገላቸው እንደሚቀሳቀሱ ጠቅሰው ይህ በሆነበት ሁኔታ ፖሊስ ላገኛቸው አልቻልኩም በማለት የሰጠው ምላሽ አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ በድጋሚ ትዛዝ እንዲሰጥላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ፖሊስ አቶ ሀይለማርያምን ደሳለኝን ካሉበት አፈላልጎ አስሮ እንዲያቀርባቸው ትዛዝ ሰቷል።
Via Tarik Adugna

ማሊ ባማኮ የሚገኙት የፈረንሳይ አምባሳደር በ72 ሰዓታት ውስጥ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች፡፡
አምባሳደሩ የፈረንሳይ ባለስልጣናት ያልተገባ ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው ባማኮን በ3 ቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት፡፡በኮሎኔል አሲሚ ጎይታ የሚመራው የማሊ ወታደራዊ የሽግግር መንግስት ከሰሞኑ ከፈረንሳይ ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን አስታውቆ ነበር፡፡ውሳኔውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ፈረንሳይኛን ከብሔራዊ ቋንቋነት መሰረዙንና ባምባራ ኦፊሴላዊ ቋንቋ ሆኖ እንዲያገለግል መወሰኑን አስታውቋል፡፡በሃገሪቱ የሚገኘው የፈረንሳይ ጦር በ72 ሰዓታት ውስጥ ማሊን ለቆ እንዲወጣ ሲልም አሳስቦ ነበር በመግለጫው፡፡ማሳሰቢያው የፈረንሳይ ኤምባሲን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት በ72 ሰዓታት እንዲዘጉ የሚያዝም ነው፡፡
Via Alain

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለካርድ ከኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ማውጣት የሚያስችል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡
ደንበኞች ከሲቢኢ ብር ሒሳባቸው ያለካርድ ከኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ማውጣት የሚችሉበትን አሠራር ባንኩ ተግባራዊ ማድረጉ ተገልጿል፡፡በዚህ አገልግሎት ደንበኞች ከራሳቸው በተጨማሪ ለሚፈልጉት ሌላ ግለሰብ ያለካርድ በኤቲኤም ማሽን አማካይነት ከሲቢኢ ብር ሒሳባቸው ገንዘብ እንዲያወጣ ማድረግ ይችላሉም ነው የተባለው፡፡የአገልግሎቱን አጠቃቀም መመሪያ ከተቋሙ የድረ-ገጽ አድራሻ መመልከት እንደሚቻል ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Forwarded from YeneTube
#አስበህ_ሀብታም_ሁን!
THINK & GROW RICH
#በሶስት_የአሜሪካ_ፕሬዚዳንቶች_የተገመገመ_የዓለማችን_ብቸኛ_መጽሐፍ!!
መጽሐፍዎ በየትኛውም የሕይወት ዘርፍ ላለ ማንኛውም መሪ ማወቅ ያለበትን እጅግ ጠቃሚ መረጃ ይዟል፡፡ በዚህ አስደናቂ የተፈጥሮ “እውቀት ፍልስፍና” ትምህርት ዝግጅትዎ ወቅት የተወሰነ ድጋፍ ለማድረግ ዕድሉን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ፡፡
#ፍራንክሊን_ሩዝቬልት
32ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ፍ/ቤት ዋና ዳኛ
በእርግጥ የጠየቅከውን መረጃ እሰጥሃለሁ፡፡ ይህ ግዴታ ብቻ ሳይሆን ደስታም እንደሆነ አስባለሁ፡፡ የውድቀት ወይም የስኬት ምክንያቶችን ለማወቅ ጊዜም፣ ፍላጎትም ለሌላቸው ሰዎች ተወካይ በመሆን እየደከምክ ነው፡፡
#ቴዎድር_ሩዝቬልት
26ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
በትክክል በገለጡት “የላዕላይ አእምሮ” መርህ ትርጓሜዎ እጅግ በጣም ተደስቻለሁ፡፡
#ውድሮው_ዊልሰን
28ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
የስኬት ሕግን ዋናውን ረቂቅ ጽሁፍ በመላክ ስለ ሰጡኝ ምስጋና አድናቆቴን እንድገልፅ ይፍቀዱልኝ፡፡ በዝግጅቱ ብዙ ጊዜ እና ጉልበት እንዳሳለፉ እረዳለሁ፡፡ ፍልስፍናዎ ትክክል ነው፡፡ በስራው ለረጅም አመታት ስለደከሙ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡
#ቶማስ_ኤድሰን
የዓለም እጅግ ታላቁ የፈጠራ ባለቤት
አራተኛው ዕትም በገበያ ላይ።
https://tttttt.me/teklu_tilahun

አሜሪካ በአዲስ አበባ ለሚገኘው ኢምባሲዋ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰንን ዛሬ ጉዳይ አስፈጻሚ አድርጋ ሾማለች። አምባሳደር ጃኮብሰን ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር የሆኑት ጌታ ፓሲ ጡረታ ሊወጡ በመሆኑ እንደሆነ የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። አዲሷ ጉዳይ አስፈጻሚ የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ባስቸኳይ እንዲቆሙ እና ግጭቱ በድርድር እንዲፈታ አሜሪካ የጀመረችውን ግፊት እንደሚቀጥሉበት የመስሪያ ቤቱ መግለጫ አመልክቷል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤድ) በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍና የልማት ፕሮግራም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ።
በኢትዮጵያ የድርጅቱ ዳይሬክተር ሲን ጆንስ ላለፉት በርካታ ዓመታት ዩ ኤስ ኤድ በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ተኮር የልማት ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።የእናቶችና ህፃናት ሞት ቅነሳ፣ በትምህርት፣ በዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ፣ በጤና እና በንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ውጤታማ ሥራዎች ማከናወኑን ተናግረዋል።
ድርጅቱ በግብርና፣ በምግብ ዋስትና ፕሮግራሞችና በሌሎችም መሰል ሰብኣዊ ድጋፎችና የልማት ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያ ሁነኛ አጋር ሆኖ ሲሰራ ቆይቷል፤ አሁንም ይቀጥላል ብለዋል፡፡በዚህ ዓመትም በኢትዮጵያ ድርቅ በተከሰተባቸው ደቡብ ኦሮሚያ፣ በደቡብ ክልል እና በደቡብ ሶማሌ አካባቢዎች ድጋፍ ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
በአማራ፣ ትግራይ እና አፋር ክልሎች እርዳታ ለሚሹ ሰዎች ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰው በልማት ፕሮጀክቶች ላይ የሚኖረውን አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።ዩ ኤስ ኤድ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በኢትዮጵያ ከሰብዓዊ ድጋፎች በተጨማሪ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን የማከናወን እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

በአማራ ክልል ከ37 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ!
በአማራ ክልል ህወሓት በፈፀመው ወረራ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ሳይወስዱ ለቆዩ 37 ሺህ 55 ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ፈተናው እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።የቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ተወካይ ቡድን መሪ አቶ ኃይሉ ታምር እንደገለጹት÷ ፈተናው የሚሰጠው ከነገ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት ነው።ፈተናው በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደርና በደሴ ከተማ አስተዳደር ሙሉ በሙሉ እንደሚሰጥ አሳውቀዋል፡፡
ፈተናው በዋግ ኽምራ ዞን ከአበርገሌ ወረዳ በስተቀር በሁሉም ወረዳዎች፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ሶስት ወረዳዎች እና በሰሜን ጎንደር ዞን በአንድ ጣቢያ ፈተናው እንደሚሰጥ አስረድተዋል።
በኦሮሚያ ክልል ከምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ተፈናቅለው ለመጡ 220 የክልሉ ተወላጅ ተማሪዎችም በቡሬ ከተማ በተዘጋጀ የፈተና ጣቢያ ፈተናው እንደሚሰጥ አቶ ኃይሉ ተናግረዋል።ለብሔራዊ ፈተና ከሚቀመጡት ተማሪዎች መካከል 34 ሺህ 970 የሚሆኑት መደበኛ ተማሪዎች ሲሆኑ÷ ቀሪዎቹ የግል ተፈታኞች ናቸው ተብሏል።ፈተናው በአጠቃላይ በ129 ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ጠቁመው÷ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች ቀደም ሲል በፀጥታ ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ለፈተናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና የመፈተኛ ወረቀቶች ወደተዘጋጁ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተጓጉዘው አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን ያስረዱት ተወካዩ÷ለ ፈተናው ከ1 ሺህ 330 የሚበልጡ ፈታኝ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮችና ተቆጣጣሪዎች መመደባቸውን መናገራቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።ፈተናው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄድም በተዘጋጁ የፈተና ጣቢያዎች የፀጥታ አካላት እንዲመደቡ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡
@YeneTube

ሁሌም ወደተሻለ ሰው የመለወጥ ምርጫ በእጃችን ላይ ነው📈
.
.
.
The choice to be a better person is always in our hands 📈
JOIN our channel Telegram
https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk
.
.
.
The choice to be a better person is always in our hands 📈
JOIN our channel Telegram
https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk
Forwarded from YeneTube
ላለፉት አምስት አመታት በከተማችን የ ሴትና የወንድ ሠዓቶች ቦርሳዎች ሽቶዎች እና ቀበቶና ዋሌት ቦርሣዎችን በማስመጣት የሚታወቀው brand watch and bag shop .. በ አዲስ መልክ ከ አዳዲስ እቃዎች ጋር እነሆ
አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
አድራሻችን 22 ጎላጎል አጠገብ ሀናን ኬ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ 0993014846/ 0938042570
እዚህ ይጎብኙን 👉 https://tttttt.me/+Q1fJRNqbpYxXr-Ga
Forwarded from YeneTube
#አስበህ_ሀብታም_ሁን!
THINK & GROW RICH
#በሶስት_የአሜሪካ_ፕሬዚዳንቶች_የተገመገመ_የዓለማችን_ብቸኛ_መጽሐፍ!!
መጽሐፍዎ በየትኛውም የሕይወት ዘርፍ ላለ ማንኛውም መሪ ማወቅ ያለበትን እጅግ ጠቃሚ መረጃ ይዟል፡፡ በዚህ አስደናቂ የተፈጥሮ “እውቀት ፍልስፍና” ትምህርት ዝግጅትዎ ወቅት የተወሰነ ድጋፍ ለማድረግ ዕድሉን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ፡፡
#ፍራንክሊን_ሩዝቬልት
32ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ፍ/ቤት ዋና ዳኛ
በእርግጥ የጠየቅከውን መረጃ እሰጥሃለሁ፡፡ ይህ ግዴታ ብቻ ሳይሆን ደስታም እንደሆነ አስባለሁ፡፡ የውድቀት ወይም የስኬት ምክንያቶችን ለማወቅ ጊዜም፣ ፍላጎትም ለሌላቸው ሰዎች ተወካይ በመሆን እየደከምክ ነው፡፡
#ቴዎድር_ሩዝቬልት
26ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
በትክክል በገለጡት “የላዕላይ አእምሮ” መርህ ትርጓሜዎ እጅግ በጣም ተደስቻለሁ፡፡
#ውድሮው_ዊልሰን
28ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
የስኬት ሕግን ዋናውን ረቂቅ ጽሁፍ በመላክ ስለ ሰጡኝ ምስጋና አድናቆቴን እንድገልፅ ይፍቀዱልኝ፡፡ በዝግጅቱ ብዙ ጊዜ እና ጉልበት እንዳሳለፉ እረዳለሁ፡፡ ፍልስፍናዎ ትክክል ነው፡፡ በስራው ለረጅም አመታት ስለደከሙ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡
#ቶማስ_ኤድሰን
የዓለም እጅግ ታላቁ የፈጠራ ባለቤት
አራተኛው ዕትም በገበያ ላይ።
https://tttttt.me/teklu_tilahun
THINK & GROW RICH
#በሶስት_የአሜሪካ_ፕሬዚዳንቶች_የተገመገመ_የዓለማችን_ብቸኛ_መጽሐፍ!!
መጽሐፍዎ በየትኛውም የሕይወት ዘርፍ ላለ ማንኛውም መሪ ማወቅ ያለበትን እጅግ ጠቃሚ መረጃ ይዟል፡፡ በዚህ አስደናቂ የተፈጥሮ “እውቀት ፍልስፍና” ትምህርት ዝግጅትዎ ወቅት የተወሰነ ድጋፍ ለማድረግ ዕድሉን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ፡፡
#ፍራንክሊን_ሩዝቬልት
32ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ፍ/ቤት ዋና ዳኛ
በእርግጥ የጠየቅከውን መረጃ እሰጥሃለሁ፡፡ ይህ ግዴታ ብቻ ሳይሆን ደስታም እንደሆነ አስባለሁ፡፡ የውድቀት ወይም የስኬት ምክንያቶችን ለማወቅ ጊዜም፣ ፍላጎትም ለሌላቸው ሰዎች ተወካይ በመሆን እየደከምክ ነው፡፡
#ቴዎድር_ሩዝቬልት
26ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
በትክክል በገለጡት “የላዕላይ አእምሮ” መርህ ትርጓሜዎ እጅግ በጣም ተደስቻለሁ፡፡
#ውድሮው_ዊልሰን
28ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
የስኬት ሕግን ዋናውን ረቂቅ ጽሁፍ በመላክ ስለ ሰጡኝ ምስጋና አድናቆቴን እንድገልፅ ይፍቀዱልኝ፡፡ በዝግጅቱ ብዙ ጊዜ እና ጉልበት እንዳሳለፉ እረዳለሁ፡፡ ፍልስፍናዎ ትክክል ነው፡፡ በስራው ለረጅም አመታት ስለደከሙ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡
#ቶማስ_ኤድሰን
የዓለም እጅግ ታላቁ የፈጠራ ባለቤት
አራተኛው ዕትም በገበያ ላይ።
https://tttttt.me/teklu_tilahun
በአማራ ክልል አሸባሪው ህወሓት በፈፀመው ወረራ ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሳይወስዱ የቆዩ ተማሪዎች ዛሬ ፈተና መውሰድ ጀመሩ፡፡
[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa