የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ሳምንታዊ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች!
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ በሳምንታዊ መግለጫው ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦
1. በጥር ወር የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ኢትዮጵያ ደምቃ እንድትታይ ያደረጉ በዓላት
• የገና በአል ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ መከበርን ተከትሎ በጥር ወር የመጀመሪዎቹ ሳምንታት የከተራ፣ የጥምቀት፣ የቃና ዘገሊላ በዓላት በመላ አገሪቱ በደማቅ ሁኔታ ተከብረዋል።
• በወይብላ ማርያም ከተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት ዉጭ ከባድ የፀጥታ ስጋት አለባቸው በሚባሉት እነ ቄለም ወለጋና በዋግ ኸምራ እንዲሁም በሌሎችም ቦታዎች በዓላቱ በሰላምና በድምቀት ተከብረዋል።
በወይብላ ማርያም አካባቢ የተፈጠረዉን ችግር ከፌደራል፣ ከአዲስ አበባና ከአሮሚያ ፖሊስ የተዉጣጣ ግብረ ሃይል ጉዳዩን በዝርዝር እየመረመረ ይገኛል፡፡ የግብረ ሃይሉ የምርመራ ዉጤትም እንደተጠናቀቀ ለህዝቡ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
እንዲህ አይነቱ ችግር በዚህ አካባቢ ለሶስተኛ ጊዜ የተከሰተ በመሆኑ በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት የአካባቢው አስተዳደር፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች በችግሩ ሥር መሰረት ላይ ተወያይተዉ የመፍትሄ አካል በማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
• በተጨማሪም አዲስ አበባ የታላቁ ሩጫን በደማቅ ቀለማት አስውባ በተሳካ ሁኔታ አስተናግዳለች።
2. የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ
• 35ተኛዉ የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የእንቅስቃሴ ገደብን ተከትሎ ከሁለት ዓመታት በላይ የቆይታ ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሪዎች በአካል በመገኘት የሚያካሂዱት ጉባኤ ነው፡፡
• በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭት መስፋፋትና በወቅታዊዉ የኢትዮጵያ ሁኔታ ምክንያት ጉባኤው የህብረቱ መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ እንዳይካሄድ ጫና ሲደረግ ቢቆይም የአፍሪካ መሪዎች ለአፍሪካ ህብረት ህገ መንግስታዊ መርሆዎች ተጓዥ በመሆናቸው፤ ለኢትዮጵያም ካላቸው አጋርነት ተቋርጦ የነበረው ጉባኤ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ መወሰኑ ለአገራችን ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል ነው፡፡
ኢትዮጵያ የራሷን ችግሮች በራሷ ፈትታ፤ አንድነቷን ጠብቃ የቀጠለች አገር መሆኗንና ሰላምና መረጋጋቷ የተጠበቀ መሆኑን አጉልተን ለዓለም የምናሳይበት ይሆናል፡፡
• የጉባኤው ተሳታፊዎች ሁሉንም አይነት ዓለም አቀፍ ጫናዎች ወደ ጎን በመተው ጉባኤው በህብረቱ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰናቸው መሪዎቹን የሚያስመሰግናቸው ነው።
• መላዉ ህዝብ በተለይም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የጉባኤው ተሳታፊዎች ደህንነት እንዲሰማቸው፣ በጎ ትውስታን ይዘው እንዲመለሱ፣ ቤታቸውና አገራቸው ያሉ ያህል እንዲሰማቸው አፍሪካዊ ባህሎች፣ ወጎች፣ እሴቶችን የሚያንፀባርቅ፣ የእንግዳ አቀባበል ሁኔታን በማሳየት ችግሮች ካጋጠሙም ለፀጥታ አካላት በመጠቆም ለጉባኤዉ መሳካት የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት፡፡
3. መልሶ ግንባታና የበጋ ልማት ስራዎች
• ከወራሪዉ ሃይል ነጻ በወጡ የአማራና የአፋር ክልሎች የኢኮኖሚና የማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አብዛኞቹ ወደ ተጨባጭ ሥራ ገብተዋል፣ ህብረተሰቡም ወደ ተሟሟቀ የበጋ የግብርና ልማት ሥራዎች በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡ የክልል መንግስታትም የፀጥታ ስጋቶችን ከመቅረፍ ጎን ለጎን ህብረተሰቡን በዘላቂነት ተጠቃሚ በሚያደርጉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ ትኩራት አድርገዉ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
በየክልሎቹ በህዝባዊ ንቅናቄ የሚፈፀሙ የተፋሳስ ልማትና የበጋ መስኖ ልማት ሥራዎች በተጠናከረ መልኩ ቀጥለዋል፣
4. የድርቅ አደጋን ለመመከት እየተደረገ ያለዉ ጥረት
• በሱማሌ ክልል በአብዛኞቹ ዞኖች፣ በኦሮሚያ ክልል በቦረና፣ በጉጂና በባሌ ቆላማ አካባቢዎች እንዲሁም በደቡብ ኦሞ ዞን የተወሰኑ ወረዳዎች የመኸርና የበልግ ወቅት ዝናብ ከመደበኛ በታች በመዝነቡና በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ምንም ዝናብ ባለመዝነቡ በአካባቢዎቹ ድርቅ ተከስቷል፡፡
• በመሆኑም በእነዚህ አካባቢዎች በእንስሳት ሃብት ላይ መጠነኛ ጉዳት እየደረሰ ነዉ፡፡ በአሁኑ ወቅት የፌደራል መንግስት ከክልል መንግስታት ጋር በመሆን ጊዜያዊ ችግሩን ለማቅለል የእለት ደራሽ እህል፣ የእንስሳት መኖ፣ መድሃኒቶችና ዉሃ እያቀረበ ነዉ። በድጋፍ አቅርቦቱ ህብረተሰቡም ሆነ ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ መንግስት ይጠይቃል፡፡
5. የትግራይ ሁኔታን በተመለከተ
• አጋር አካላት ወደ ትግራይ ክልል ለሚኖራቸው የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት የአየርና የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎትን መንግስት አመቻችቷል፡፡
• ይሁንና ከሠመራ ወደ መቀሌ በአብአላ ኮሪደር የሚደረገው የየብስ ጉዞ ወራሪው ኃይል በተደጋጋሚ በአካባቢዉ የጦርነት ትንኮሳ በመፈፀሙ ተስተጓጉሏል፡፡
ባሳለፍናቸዉ ቀናት ብቻ በርካታ የእርዳታ እህልና መድሃኒት የጫኑ ተሽከሪካሪዎች ወራሪዉ ሃይል በእነዚህ አካባቢዎች በከፈተዉ ጦርነት ምክንያት ብዙ ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ ወደ ኋላ እንዲመለሱ ተገደዋል፡፡ ይህ የሚያመለክተዉ የሽብር ቡድኑ ዛሬም ረሃብን እንደ ፖለቲካ መሳሪያ ለመጠቀም እየሞከረ መሆኑን ነው፡፡
6. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በተመለከተ
• የሽብር ቡድኑ ሕወሃትና ግብረአበሮቹ በአገራችን ህልውናና ሉአላዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ በመደቀናቸዉ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በአዋጅ ቁጥር 1264/2014 ፀድቆ በስራ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
• ይህን ተከትሎ የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስና የክልል የፀጥታ ሀይሎች፣ እንዲሁም መላ የሀገሪቱ ህዝብ በአንድነት ተቀናጅተዉ በተለያዩ የውጊያ ግንባሮች ባደረጉት የጀግንነት ተጋድሎ ቀድሞ የነበረዉ ሁኔታ የተቀየረ በመሆኑና አሁን ያለውን የጸጥታ ስጋት በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥራ መቆጣጠር የሚቻል በመሆኑ፣ ለስድስት ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትም ይህንኑ ውሳኔ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
[የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት]
@YeneTube @FikerAssefa

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋርጦ የነበረውን ወደ ዱባይ በረራ ከመጪው ቅዳሜ ጥር 21 ቀን 2014 ጀምሮ እንደሚጀምር በዛሬው ዕለት አስታውቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በትላንትናው ዕለት ከተሾሙት አምባሳደሮች የተወሰኑት፤ ተቀማጭነታቸው በሀገር ውስጥ እንደሚሆን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ!
በፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በትላንትናው ዕለት ከተሾሙ 27 አምባሳደሮች ውስጥ የተወሰኑት ወደ ተሾሙበት ሀገር ሳይሄዱ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ አምባሳደሮች (non-resident ambassadors) እንደሚሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስቴሩ ቃል አቃባይ ዲና ሙፍቲ፤ ሹመቱ “ዲፕሎማሲያዊ ሙያን መሰረት ያደረገ ነው” ብለዋል።
ቃል አቃባዩ ዛሬ ሐሙስ ጥር 19 በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫቸው፤ የአምባሳደሮች ሹመት የተከናወነው “በጥናት” መሆኑን ተናግረዋል።ሹመቱ ሶስት አሰራሮችን የተከተለ መሆኑን ለጋዜጠኞች የተናገሩት ዲና፤ ከእነዚህ መካከል አንደኛው አምባሳደሮች ወደ ተወከሉበት ሀገር ሳይሄዱ ነዋሪነታቸው በሀገራቸው ሆነው ስራቸውን እንዲያከናውኑ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
“Non-resident አምባሳደር የሚባል አለ። እዚሁ ነው የሚኖሩት፤ እዚያ ሀገር አይኖሩም። የተወከሉበት ሀገር አስፈላጊ ሲሆን እየተመላለሱ የሚሰሩ non – resident ambassadors የሚባሉ እዚህ ውስጥ አሉ ማለት ነው” ሲሉ ከትላንቱ ተሿሚዎች ውስጥ የተወሰኑት ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
በዛሬው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ወደ ተወከሉበት ሀገር የማይሄዱ አምባሳደሮች ብዛት ምን ያህል እንደሆነ ጥያቄ ቢነሳም፤ ዲና ሙፍቲ ጥያቄውን ምላሽ ሳይሰጡ አልፈውታል።አምባሳደሮቹ የተሾሙባቸው ሀገራት ዝርዝርን በተመለከተ ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተጨማሪ ጥያቄ የቀረበላቸው ቃል አቀባዩ፤ “ገና እየተሰራ ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/5696/
@YeneTube

👍1
መንግሥት በሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መፍትሄ ለማፈላለግ ያዋቀረው ከከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ከሐይማኖት አባቶች እና ታዋቂ ሰዎች የተውጣጣ ልዑካን ቡድን ሪያድ እንደገባ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ለዋዜማ ተናግረዋል። ልዑካኑ በሳዑዲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ባመቻቹት መሠረት በጉዳዩ ዙሪያ ከሳዑዲው ንጉስ ሰልማን ኢብን አብዱላዚዝ ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ ተይዞለታል። ቡድኑ በሳዑዲ እስር ላይ ያሉ ዜጎች ተገደው ወደ ሀገራቸው እንዳይመለሱ የሚጠይቅ ሲሆን፣ የልዑካን ቡድኑ መሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ደዔታ ሬድዋን ሁሴንም ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዙሪያ ይወያያሉ ተብሏል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ከኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ከ1 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ እየተጣራ መሆኑን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዐሰታወቀ።
በጦርነቱ ወቅት በብሔረሰብ አስተዳደሩ የሰብአዊ ጥሰትና የንብረት ውድመት መድረሱን የብሔረሰብ አስተዳደሩ አመልክቷል።የማኅበራዊ መስጫ ተቋማት አገልግሎት እየጀመሩ መሆኑንም አስተዳደሩ ገልጧል።ከከሚሴ ከተማ ንብረት የወደመባቸው ባለሀብት መንግሥት የሕግ ማስከበር ሲል የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ከኦነግ ሸኔ ጋር ግንኙነት ነበራቸው ተብለው የተጠረጠሩ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ ዛሬ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።በወረራው ወቅት ከ260 በላይ ንፁሐን መገደላቸውንና ከ170 በላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ያመለከቱት አቶ አህመድ በንብረትም ከ 1ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን አብራርተዋል፡፡የብሔረሰብ አስተዳደሩን ወደነበረበት ለመመለስ የተፈጥሮ ሥራን ማከናወን፣ የመልሶ ማቋቋምና ሌሎች ተግባራትን እየሰሩ እንደሆነ ነው ያስረዱት።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀማል ሐሰን በበኩላቸው፣ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች መመሪያ እንደአዲስ ተቋቁሞ በግብርናው ዘርፍ የተሻለ ለማምረት እየተሰራ መሆኑን አመልክተው፣ ሌሎች የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትም ወደ ስራ ገብተዋል ብለዋል።በከሚሴ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ ባለሀብት ከ60ና 70ሚሊዮን በላይ የሚገመት ንብረታቸው ውድመትና ዝርፊያ እንደተፈፀመበት አስታውሰው መንግስት የሕግ ማስከበር ሲል የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንዲቀጥልና በአካባቢው ሰላም እንዲያሰፍን ጠይቀዋል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ባለሀብቶች ንብረታቸው መዘረፉንና መውደሙን አረጋግጠው የተዘረፉ ንብረቶች እንዲመለሱ፣ አጥፊዎች ደግሞ በሕግ እንዲጠየቁ ይደረጋል ብለዋል።በከሚሴ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ ባለሀብት ከ60ና 70ሚሊዮን በላይ የሚገመት ንብረታቸው ውድመትና ዝርፊያ እንደተፈፀመበት አስታውሰው መንግስት የጀመረውን የሕግ ማስከበር ሥራ አጠናክሮ እንዲቀጥልና በአካባቢው ሰላም እንዲያሰፍን ጠይቀዋል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ባለሀብቶች ንብረታቸው መዘረፉንና መውደሙን አረጋግጠው የተዘረፉ ንብረቶች እንዲመለሱ፣ አጥፊዎች ደግሞ በሕግ እንዲጠየቁ ይደረጋል ብለዋል። ከአማራና ከአፋር አዋሳኝ አካባቢዎች ጋር ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ውይይቶች እየተካሄዱ መሆንንም ዋና አስተዳዳሪው አመልክተዋል። ብሔረሰብ አስተዳደሩ ቀደም ሲል ከአመራሩ ጋር ይነሱ የነበሩ ችግሮችን ለማረመረ እስከታችኛው የመንግስት መዋቅር አዲስ የአመራር አደረጃጀቶች መደረጋቸውንም አስረድተዋል።
[DW]

#አስበህ_ሀብታም_ሁን!
THINK & GROW RICH
#በሶስት_የአሜሪካ_ፕሬዚዳንቶች_የተገመገመ_የዓለማችን_ብቸኛ_መጽሐፍ!!
መጽሐፍዎ በየትኛውም የሕይወት ዘርፍ ላለ ማንኛውም መሪ ማወቅ ያለበትን እጅግ ጠቃሚ መረጃ ይዟል፡፡ በዚህ አስደናቂ የተፈጥሮ “እውቀት ፍልስፍና” ትምህርት ዝግጅትዎ ወቅት የተወሰነ ድጋፍ ለማድረግ ዕድሉን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ፡፡
#ፍራንክሊን_ሩዝቬልት
32ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ፍ/ቤት ዋና ዳኛ
በእርግጥ የጠየቅከውን መረጃ እሰጥሃለሁ፡፡ ይህ ግዴታ ብቻ ሳይሆን ደስታም እንደሆነ አስባለሁ፡፡ የውድቀት ወይም የስኬት ምክንያቶችን ለማወቅ ጊዜም፣ ፍላጎትም ለሌላቸው ሰዎች ተወካይ በመሆን እየደከምክ ነው፡፡
#ቴዎድር_ሩዝቬልት
26ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
በትክክል በገለጡት “የላዕላይ አእምሮ” መርህ ትርጓሜዎ እጅግ በጣም ተደስቻለሁ፡፡
#ውድሮው_ዊልሰን
28ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
የስኬት ሕግን ዋናውን ረቂቅ ጽሁፍ በመላክ ስለ ሰጡኝ ምስጋና አድናቆቴን እንድገልፅ ይፍቀዱልኝ፡፡ በዝግጅቱ ብዙ ጊዜ እና ጉልበት እንዳሳለፉ እረዳለሁ፡፡ ፍልስፍናዎ ትክክል ነው፡፡ በስራው ለረጅም አመታት ስለደከሙ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡
#ቶማስ_ኤድሰን
የዓለም እጅግ ታላቁ የፈጠራ ባለቤት
አራተኛው ዕትም በገበያ ላይ።
https://tttttt.me/teklu_tilahun

⚡️ምንም ቢሆን ምንም ⚡️
አላማችንን ለማሳካት ወደፊት እንራመድ ✊🏾
.
.
.
⚡️No matter what⚡️
We must move forward to achieve our goals ✊🏾
Join Our telegram
👉 https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk

🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦
በአሜሪካ ና ካናዳ በስኮላርሺፕ የመማር ዕድል!
ያለ ቅድመ ክፍያ ለመመዝገብ ቴሌግራም ቦት ላይ አፕላይ ያድርጉ! 👇
@marakischolarshipbot
አድራሻ: ቦሌ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
ለበለጠ መረጃ @marakiconsultant
ቴሌግራም ቻናል👇
@marakiconsultancy

አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
#የሕይወት_ፍልስፍና
ሁሉም ሰው አስማተኛ ነው፡፡ ቃላቶቻችንን እንዴት መጠቀም እንዳለብን ከተማርን በሌሎች ላይ ጥሩ ወይም መጥፎ አስማት ማድረግ እንችላለን፡፡
ለመሆኑ የቃላቶቻችን አስማቶች ምን ይሆኑ?
ሕይወት ልክ እንደ ዳንስ ናት፡፡ ሪትሙ ሲቀያየር ላለመናደድ የዳንሱን ጥበብ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ለመሆኑ በሕይወት ውስጥ በጥበብ መደነስ የሚቻለው እንዴት ነው?
ራሳችን ከራሳችን ጋር በትክክል አንስማማም፤ ሁልጊዜም ከራሳችን ጋር ስንጣላ ነው የምንገኘው፡፡
ለመሆኑ እንዴት ነው ከራሳችንስ ጋር መታረቅ የምንችለው?
#የሕይወት_ፍልስፍና መጽሐፍ የቃላቶቻችንን አስማት ሊያሳየን፣ ከራሳችን ጋር እንድንታረቅ ሊረዳን፣ በሕይወት ላይ በጥበብ መደነስን ሊያስተምረን በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡
ቤተሰብ ይሁኑ👇

ለትግራይ ክልል ሁለተኛ ዙር የመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ!
አርብ ጥር 20 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ለትግራይ ክልል ሁለተኛውን ዙር አስቸኳይ የመድሃኒት እና የህክምና ቁሳቁሶች አቅርቦት እና ድጋፍ ለማድረስ ዛሬ ወደ መቀሌ በረራ ተደርጓል፡፡
የመድሀኒት እና የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦቱ በአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የታገዘ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮሚቴው ከመስከረም ወር ወዲህ የመጀመሪያውን የህክምና እርዳታውን ከኹለት ቀናቶች በፊት ጥር 18 ቀን 2014 ወደ ትግራይ ክልል ማድረሱ ይታወሳል።

በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ሦስት የአንድ ቤተሰብ አባላትን በቦምብ የገደሉት አባትና ልጆች በእድሜ ልክ እና በ25 ዓመት ፅኑ እሥራት ተቀጡ።
1ኛ ተከሳሽ ዓለምነው ቀማው ወልደፃዲቅ እና 3ኛ ተከሳሽ አብርሃም ቀማው ወልደፃዲቅ በእድሜ ልክ እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ ወልደፃዲቅ ገብረማሪያም በ25 ዓመት ጽኑ እሥራት እንዲቀጡ ነው የተፈረደባቸው።በወረዳው የ07 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ተከሳሾቹ አስቀድመው ሰውን ለመግደል በማሰብ ጥር 17 ቀን 2012 በግምት ከምሽቱ 1 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በቀበሌው ጦል ጎጥ ልዩ ስሙ ሾላ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ 1ኛ ተከሳሽ ዓለምነው ቀማው ወልደፃዲቅ ከሟች ወንድወሰን ወልደፃዲቅ የሳር መኖሪያ ቤት ላይ በመስኮት ቦምብ ወርውሮ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ሟችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል ይላል የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ።
ተከሳሾቹ በሟች ወንድወሰን ወልደፃዲቅ መኖሪያ ቤት የነበሩትን የዘጠኝ ወር ነፍሰጡሯን ሟች ቡጥቃ ወንድወሰንን እና ሟች ማሚቱ ተክለሀይማኖትን በ1ኛ ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በተመሳሳይ ጨካኝነትና ነውረኝነት በተሞላበት ሁኔታ 1ኛ ተከሳሽ አለምነው ቀማው ወልደፃዲቅ በሟች ወንድወሰን ወልደፃዲቅ መኖሪያ ቤት ላይ በመስኮት ቦምብ ወርውሮ ሟቾቹን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደላቸው መሆኑን መዝገቡ ያስረዳል።
2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ የአንደኛ ተከሳሽን ሃሳብና አድራጎት በሙሉ ሃሳባቸው ተቀብለው የግል ተበዳይን ቤት በመቆለፍ ሟችን በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወቱ እንዲያልፍ በማድረጋቸው በከባድ የሰው መግደል ወንጀል የዞኑ አቃቤ ህግ ክስ መስርቷል፡፡አቃቤ ህግ በመሰረተው 4ኛ ክስ ደግሞ ተከሳሾቹ በ1ኛ ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ 1ኛ ተከሳሽ ዓለምነው ቀማው ወልደፃዲቅ ከሟች ቤት የነበረችውን የግል ተበዳይ በለጥ ወንደሰንን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በፈነዳው ቦምብ ፍንጣሪ የተለያዩ የሰውነት ክፍሏ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ክስ ቀርቧል፡፡
2ኛ እና 3ኛ ተከሳሶች የግል ተበዳይን ቤት በመቆለፍና በመያዝ የግል ተበዳይዋ ከባድ የአካል ጉዳት እንዲደርስባት በማድረጋቸው ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡
ከ2ኛ ተከሳሽ ውጪ ያሉት ተከሳሾች ያልተያዙ በመሆኑ እንዲሁም ፍርድ ቤቱ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢያደርግም ሊቀርቡ ባለመቻላቸው ጉዳያቸው በሌሉበት እንዲታይ የተወሰነ ሲሆን ፥ 2ኛ ተከሳሽ ግን ከመንግስት በተመደበለት ጠበቃ እየታገዘ የዕምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ሲል ክዶ ተከራክሯል፡፡ዐቃቤ ህግም ክሱን ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማቅረብ ለፍርድ ቤቱ አሰምቷል፡፡ግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾችን ጥፋተኛ በማለት እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡ተከሳሾች ሊከላከሉ ባለመቻላቸው ጥፋተኛ ናችሁ በማለትም ወስኗል፡፡
የግራ ቀኙን የቅጣት ማቅለያና ማክበጃ ሃሳብ የተቀበለው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር 16 ቀን 2014 በዋለው ችሎት ተከሳሾችን ያርማል ሌሎችን ያስተምራል በሚል ፥ 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሽን በዕድሜ ልክ ጽኑ አሥራት፣ 2ኛ ተከሳሽን ደግሞ በ25 ዓመት ጽኑ እሥራት እንዲቀጡ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።እንዲሁም ተከሳሾቹ ለ3 ዓመት ከህዝባዊ መብታቸው እንዲታገዱ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን፥ ፖሊስም ያልተያዙ ተከሳሾችን አፈላልጎ ለደብረ ብርሃን ማረሚያ ቤት እንዲያስረክብ ማዘዙን ከዞኑ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ባላቸው የፖለቲካ ፍላጎትን እሽቅድድም የተነሳ ከባለፈው አመት ሶስት እጥፍ የሚልቅ የሳይበር ጥቃት ሙከራ መፈጸሙ ተገለጸ፡፡
በቀጠናው እየጎላ የመጣውን ፖለቲካ ፍላጎትን ለማሳካት የሚደረግ እሽቅድድም ለማሳካት የሀገራችንን የገንዘብ ተቋማት ኢላማ ያደረገ የሳይበር ጥቃት ሙከራ መፈጸሙን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉ እንዳሉት በያዝነዉ ዓመት ካለፈዉ ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ 3 ዕጥፍ ከፍ ያለ የሳይበር ጥቃት ሙከራ መደረጉን እና ከዛም መሃል ከፍተኛ የጥቃት ሙከራ የተደረገው በገንዘብ ተቋማት ላይ እንደነበር ገልጸዋል ፡፡
የገንዘብ ተቋማቱ በዉስጣቸው ከግለሰብ እስከ መንግስት ደረጃ ያሉ መረጃዎችን የያዘ ና ከፍተኛ ሃብት ያለበት በመሆኑ በተደጋጋሚ ሙከራዎች እንዲካሄዱበት ምክንያት ሆኗል ብለዋል፡፡
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና አምራች ተቋማት ሌሎች ጥቃቱ የተሞከረባቸዉ ተቋማት መሆናቸዉንም ገልጸዋል፡፡
የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ዳይሬክተሩ ለማሳያነት በ2012 እና 2013 የነበረዉን የሳይበር ጥቃት ሙከራ ቁጥሮች በማንሳት በያዝነዉ ዓመት ግን በከፍተኛ ቁጥር መጨመሩን ይናገራሉ፡፡
በ 2012 ዓ.ም 1800 ፣ በ 2013 ደግሞ 1980 የሚሆኑ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መካሄዳቸዉን እና በ 2014 ዓ.ም ግን በ 3 ዕጥፍ አድጎ 3406 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ተካሂደዋል ብለዋል፡፡
ዋነኛዉ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደዉ ቀጠናዉ ላይ ያለ የፖለቲካ ፍላጎትን ለማሳካት የሚደረግ እሽቅድድም መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ፤ የፖለቲካ ፍላጎታቸዉን ለማሳካት ሲስተሞችን ሰብሮ መግባት ፣ አገልግሎቶችን እንዲቋረጡ ማድረግ እና ጥቃቶችን መፈጸም አላማቸዉ መሆኑ ነዉ የተነገረዉ፡፡
ሃገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ደግሞ ሌሎች ምክንያት ሲሆኑ ባለፈዉ ዓመት የተጀመረዉ የህግ ማስከበሩ ስራ ፣ 6ኛዉ ሃገራዊ ምርጫ እና የህዳሴ ግድቡ የዉሃ ሙሌት የፖለቲካ ጥቅማቸዉን ለማስጠበቅ በሚሞክሩ አካላት በተደጋጋሚ ጥቃቶች እንዲሰነዘሩ ምክንያቶች ሆነዋል፡፡
ጥቃቶቹ ደርሰዉ ቢሆን ኖሮ በርካታ ኪሳራ ያደርሱ እንደነበር ሲገለጽ የሳይበር ጥቃትን መከላከል ለኤጀንሲዉ ብቻ የሚተዉ ነገር ባለመሆኑ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ግንኙነቶችን በማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተሩ ሳይበርኛ በተሰኘው መርሃግብር ላይ ገልጸዋል፡፡ በተቀናጀ ስራም ከተሞከሩት ጥቃቶች 96 በመቶ የሚሆኑትን ማክሸፍ መቻሉን ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉ ተናገረዋል፡፡
[Ethio FM]

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በፀጥታ ችግር ማስፈተን ያልቻልኳቸውን የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን በሙሉ ለፈተና ማስቀመጥ እችላለሁ ሲል የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡
ክልሉ አሁንም ድረስ በሰሜን ጎንደር እና በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን አንዳንድ ስፍራዎች አሳሳቢ የፀጥታ ስጋት ቢኖርም ከዞኖቹ ማስፈተን አንችልም የሚል ሪፖርት ስላልደረሰኝ ለ36 ሺሕ 800 ተማሪዎች ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት አጠናቅቂያለሁ ብሏል፡፡ቀደም ሲል ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 በተሰጠው የብሔራዊ ፈተና በክልሉ 133 ትምህርት ቤቶች በፀጥታ ችግር ማስፈተን እንዳልቻሉ ያስታወሱት የትምህርት ቢሮው የስራዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክተር ካሴ አባተ ናቸው፡፡
ምን አልባት እንኳን ነገሮች ከአቅም በላይ የሚሆኑበት አጋጣሚ ከተፈጠረም ሰላማዊ ወደ ሆኑ ሌሎች ዞኖች በመውሰድ ፈተናው እንደሚሰጥም ዳይሬክተሩ ለአሐዱ ገልፀዋል፡፡በመጀመሪያው ዙር ፈተናውን ለመውሰድ በክልሉ ከ127 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ተመዝገበው እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ዳግም ይሰጣል የተባለው ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥር 24 እስከ 27 ለተከታታይ አራት ቀናት ይሰጣል፡፡
[አሐዱ]

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበለትን የፌደራል መንግስት 122 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ።
የ2014 በጀት አመት የፌደራል መንግስት የተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅን በ9 ተቃውሞ፣ በሰባት ድምፀ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።ምክር ቤቱ በዛሬው ልዩ ስብሰባዉ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በአብላጫ ድምፅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

ምክር ቤቱ ለመከላከያ ሠራዊት ተጨማሪ 90 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ!
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ዛሬ ባካሄደው 3ተኛ ልዩ ሥብሰባው ለመከላከያ ሠራዊት ተጨማሪ የ90 ቢሊዮን ብር በጀት አጽድቋል።የ2014 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት የተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጅጌ፣ ተጨማሪ በጀቱ ለሰራዊቱ ስንቅና ትጥቅ የሚውል ይሆናል ብለዋል።
ከመከላከያ ተጨማሪ በጀት ባለፈ ለዕለት ደራሽ ዕርዳታ 8 ቢሊዮን ብር፣ ለመጠባበቂያ በጀት 8 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ 7 ቢሊዮን ብር እንዲሁም የታክስ ገቢ ጉድለትን ለማካካስ በበጀት ሽግሽግ ብቻ መሸፈን ባለመቻሉ ለወጪው አሸፋፈን ማስተካከያ 9 ቢሊዮን ብር እንደሚያድስፈልግ ተገልጿል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።በአጠቃላይ 122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀትና ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀርቦ መፅደቁ ታውቋል።

ኮሚሽኑ በ150 ሚሊየን ብር የተገዙ ተሽከርካሪዎችን ለክልሎች አከፋፈለ!
የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በ150 ሚሊየን ብር የተገዙ ተሽከርካሪዎችን ለክልሎች በድጋፍ መልክ መስጠቱን ገለጸ።ድጋፉን የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሸነር ነሲቡ ያሲን ለክልል ተወካዮች አስረክበዋል።
ተሽከርካሪዎቹ የተገዙት በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን፥ በዚህም 24 መኪናዎችን ለአምስት ክልሎች አስረክበዋል።
በዚህም መሰረት አምስት ለአማራ፣ ሰባት ለኦሮሚያ፣ አራት ለሶማሌ፣ አራት ለደቡብ፣ ሁለት ለሲዳማ ክልሎች እና ሁለት ደግሞ ለብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ስራ ኮሚሽን ተከፋፍሏል።እንዲሁም 60 ሞተር ሳይክሎች 30 ለሶማሌ ፣ 24 ለደቡብና 6 ለሲዳማ ክልሎች ማስጠቱን ኢዜአ ዘግቧል።

ህወሃት ለሚያደርገው ትንኮሳ የመከላከያ ሰራዊትና የክልል ጸጥታ ሃይሎች እርምጃ የሚወስዱበት አቅጣጫ ተቀመጠ!
ሽብርተኛው የህወሃት ቡድን ለሚያደርገው ትንኮሳ የመከላከያ ሰራዊትና የክልል ጸጥታ ሃይሎች በጥናት ላይ ተመስርተው እርምጃ የሚወስዱበት አቅጣጫ ተቀመጠ።በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተመራው የፌደራል ጸጥታ ምክር ቤትና የክልል ርእሳነ መስተዳደሮች ውይይት በሀገራዊ ጸጥታ ሁኔታ ላይ የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ትኩረት አድርጓል።በምክክሩም ሀገሪቱ አሁን ያለችበት አንጻራዊ ሰላምና ጸጥታን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን ማስቆምና በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠሩ ኢመደበኛ አደረጃጀቶችን ቅርጽ ማስያዝ እንደሚገባ ከስምምነት ተደርሷል።በተለይ ሽብርተኛው የህወሃት ቡድን የሚያደርገውን ትንኮሳን ተከትሎ እርምጃዎች የሚወሰድበት አግባብ አቅጣጫ ተቀምጦለታል።
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በሀገሪቱ ቀጣይ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮች ከወዲሁ መስመር የማስያዝና የማስተካካያ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አንስተዋል።ህገወጥ የመሳሪያ ዝውውር፣ የኮንትሮባንድና መሰል እንቅስቃሴዎች የተገመገሙ ሲሆን፥ በውስጥ ያሉ ችግሮችን ከመፍታት ባለፈ ቀጠናው ላይ ሰላምን ማስጠበቅ እና ሀገራዊ ግንኙነትን ማጠናከር ላይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል ብለዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ በበኩላቸው የአሸባሪ ቡድኖችን እንቅስቃሴ በመገምግም እርምጃ መውስድ የሚቻልበት ሁኔታን ከመመልከት ባለፈ አሸባሪዎች ላይ እርምጃ መውሰድን የተመለከተ አቅጣጫ ተቀምጧል ነው ያሉት።የተቀመጡ አቅጣጫዎችም ሆነ የተደረሰባቸው ስምምነቶችን የፌደራልም ሆነ የክልል የጸጥታ አካላትና አስተዳደሮች በየደረጃው ተግባራዊ እንደሚያደርጉት ይጠበቃል።

ጤና ተቋማት በዱቤ የወሰዱት ያልተሰበበ ብር በመኖሩ የመድኃኒት አቅርቦት ችግር ፈጥሯል ተባለ!
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጤና ተቋማት በዱቤ የወሰዱትን ብር በወቅቱ ገቢ ባለማድረጋቸው የህክምና ግብቶችን ለማቅረብ ችግር እየተፈጠረ መሆኑን የአገልግሎቱ የፋይናስ ዳይሬክተር አቶ ዘውዱ ሳሙኤል ገልጸዋል፡፡
ካለፉት 5 ዓመታት ጀምሮ በአጠቃላይ 1.3 ቢሊየን ብር የዱቤ ሽያጭ ( ያልተሰበሰበ ብር) በየሆስፒታሉና ጤና ተቋማት እንደሚገኝ ነው የተነገረው::
በከፍተኛ ደረጃ ያልተሰበሰበ ገቢ በአዲስ አበባ በሚገኙ ጤና ተቋማት የሚገኝ ሲሆን 85.9 ሚሊየን ብር እዳ ያለባቸው ሆስፒታሎች አሉም ተብሏል።
በክልል ከሚገኙ ቅርንጫፎች ባህርዳር 124 ሚሊየን ፣ አዳማ 91 ሚሊየን፣ ሀዋሳ 90 ሚሊየን ፣ ደሴና ጅማ 50 ሚሊየን ተሰብሳቢ ብር ያለባቸው ቅርጫፎች ለአብነት ተጠቃሽ መሆናቸውን አቶ ዘውዱ ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ የተቋቋመበት ዓላማ ፈዋሽነታቸውና ጥራታቸው የተረጋገጠ መድኃኒቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለመንግስት ጤና ተቋማት ማቅረብ ቢሆንም የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማሳለጥ ያልተሰበሰበ የዱቤ ሽያጭ በመኖሩ ችግር እየሆነበት እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡
የህክምና ግብቶችን ቶሎ ቶሎ በማሰራጨት ብዙ ሽያጭ እንዲኖረን እንፈልጋለን ያሉት ሀላፊው ከመንግሥት ካዝና በጀት የሚበጀትላቸው ጤና ተቋማት ያለባቸውን ብድር በወቅቱ እንዲከፍሉ ማሳሰባቸውን አሻም ከኤጀንሲው የማህበራዊ ትስስር ገጽ ተመልክታለች።
Via Asham

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ(ማስክ) ያላደረጉ አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች 1 ሺሕ ብር እንደሚቀጡ ተነገረ፡፡
የኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ በትራንስፖርት ዘርፍ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ በማያደርጉ አሽከርካሪዎች ላይ ከአርብ ጀምሮ ቁጥጥር እንደሚደረግ ያስታወቀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ነው፡፡
ቢሮው የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት የተሽከርካሪዎችን ንጽህና መጠበቅ፣ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች ማስክ መጠቀም እንዲሁም ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪዎች አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግ እንደሚገባ አብራርቷል፡፡
የኮቪድ ስርጭት ለመግታት በወጣው መመሪያ መሰረት ማስክ ያላደረጉ አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ከተገኙ ብር 1 ሺህ የሚያስቀጣ ሲሆን፥ ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪ በሚጭኑበት ወቅት በአንድ ሰው 500 ብር የሚቀጡ ይሆናል፡፡