YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በተደረገለት ድጋፍ ሙሉ አገልግሎት መስጠት ጀመረ!

በአሸባሪው ህወሓት እና ሸኔ ውድመት እና ዘረፋ የደረሰበት በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በተደረገለት ድጋፍ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሰዒድ አህመድ ለኢቲቪ እንደገለጹት የጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ በማድረጉ የሆስፒታሉን አገልግሎት ለማስጀመር ተችሏል ብለዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት እና ሸኔ በሆስፒታሉ ከፍተኛ ውድመት እና ዘረፋ እንዳይደርስበት ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ባለው አቅም ሲሰራ መቆየቱን ሜዲካል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ሆስፒታሉ ከተለያዩ አካላት በተደረገለት ድጋፍ አገልግሎቱን መስጠት እንደጀመረ የሚገልጹት የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ በርሄ ገ/ማርያም፣ አሁንም የሚቀሩ አገልግሎቶችን ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የቀዶ ህክምና ክፍል ሙሉ ለሙሉ አለመጀመሩ፣ የተሸከርካሪዎች ፣የኦክስጅን እና ደም እጥረት መፈጠሩን የገለጹ ሥራ አስኪያጁ ፣ ይህን ችግር ለመፍታት በራስ አቅም እየተሰራ ቢሆንም አሁንም ሆስፒታሉ ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት በክልሉ መስጂዶችና ምዕመኑ ላይ የሚደርሱ ትንኮሳዎችና ጥቃቶች ተባብሰዋል አለ!

የአማራ ክልል የእስልምና ከፍተኛ ጉዳዮች ምክር ቤት በክልሉ መስጂዶችና ምዕመኑ ላይ የሚደርሱ ትንኮሳዎችና ጥቃቶች ተባብሰዋል ሲል ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ምክር ቤቱ ባሰራጨው መግለጫ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተለይ በደቡብ ጎንደር እና በምሥራቅ ጎጃም በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ በጠራራ ፀሐይ 7 መስጂዶችና በውስጡ የሚገኙ ቅዱስ ቁርኣን እና ሌሎች መጻሕፍት ‹‹በሃይማኖት ሽፋን እኩይ አላማቸውን ለማሳካት›› በሚንቀሳቀሱ ባላቸው አካላት መቃጠላቸውን አስታውሷል፡፡

ይህ ሁሉ ወንጀል በሕዝብ እና በአምልኮ ቦታዎች ላይ ሲፈጸም አንድም ወንጀለኛ ለሕግ ቀርቦ ውሳኔ እንዳልተሰጠው ያመለከተው ምክር ቤቱ፣ በዐል በመጣ ቁጥር የጎንደር ከተማን ጨምሮ በሌሎችም አካባቢዎች ስጋቱና ትንኮሳው መቀጠሉን ጠቁሟል፡፡

ምክር ቤቱ ለዚህ በማሳያነት ከቀናት በፊት በተከበረው የጥምቀት በዐል ወቅት ተፈጽመዋል ያላቸውን ‹‹ሕዝብን ለግጭት የሚዳርጉ›› እና ‹‹የቆሰለች›› ያላትን ኢትዮጵያን ሰላሟን የሚያናጋ ያላቸውን ተግባራት ዘርዝሯል፡፡

ከነዚህ መካከል የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የግንብ አጥር መፍረሱን፣ በተመሳሳይ ባህር ዳር ከተማ አባይ ማዶ የሚኖሩት ትልቅ የሙስሊም አባት መኖሪያ ቤት በድንጋይ መደብደቡን፣ በደሴ ከተማ የአረብ ገንዳ መስጅድ ሙስሊሞች በስግደት ላይ ባሉበት ወቅት መስጂዱ በጥይት መደብደቡን፣ በጎንደር የሚገኘው ነስረላህ የተሰኘ መስጅድ አጥር እና ጣሪያ በጥይት መመታቱን እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም በሙስሊም መቃብር ላይ መስቀል የመትከል ድርጊት መታየቱንም ጠቅሷል፡፡

እነዚህን አና ሌሎችንም ድርጊቶች ያወገዘው የምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ ፣ በተለይ በባህር ዳር የምክር ቤቱ አጥር ግንብ ሲፈርስ ስምሪት የተሰጣቸው የፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት በዝምታ በመመልከታቸው እንዲጠየቁ ያለ ሲሆን፣ የክልሉ መንግስትና በየደረጃው ያለው አስተዳዳርም አደጋውን አርቆ በማሰብ ወንጀለኞች በሕግ አግባብ እንዲታረሙ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

ከዚሁ ጋር በተገናኘ የአማራ ክልል የእስልምና ከፍተኛ ምክር ቤት ይህ መግለጫ ሳይቆራረጥ እንዲተላለፍለት የተላከለት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን መግለጫውን ለማሠራጨት ፍቃደኛ ሳይሆን መቅረቱ ተነግሯል፡፡ኮርፖሬሽኑ መግለጫውን ላለማስተላለፉ ያቀረበው ምክንያት ስለመኖሩ የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ተባብሮ ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ካልተቻለ የኢትዮጵያ ስጋት መሆኑን ይቀጥላል ሲል የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡

ቡድኑ አሁንም በአማራ ክልል የተለያዩ ስፍራዎች ላይ በየቀኑ ጥቃቶችን እየሰነዘረ ንፁሃንን እያሰቃየና እየገደለ መሆኑን ለአሐዱ የተናገሩት የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ናቸው፡፡

ማይፀብሪ ፣ አዳርቃይ ፣ ቆቦ ፣ኮረም ፣አላማጣ በየቀኑ ጥቃት የሚሰነዝርባቸው እና ከጦርነት አርፈው የማያውቁ አካባቢዎች እንደሆኑ ተናግረው ቡድኑ በእነዚህ አካባቢዎች አሁንም ፍላጎት እንዳለው ያሳያል ብለዋል፡፡

በከፍተኛ ደረጃ ሀይል እያሰባሰበና ሊወጋ እየተዘጋጀ መሆኑን የሚያሳዩ እንቅስቃሴዎች እያደረገ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡

ሕወሓት አሁንም ልክ እንደ በፊቱ በሀሰት ትርክቱ እያሳመነ እንዲሁም እያስገደደ የትግራይ ህዝብን እያሰለጠነ እና እያዘመተ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ባለዉ ሁኔታም ወረራ ለመፈፀም የተለያዩ ሙከራዎችን ቢያደርግም እንዳልተሳካለት እና ለሌላ ጥቃት እየተዘጋጀ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ይህ ኃይል እስካልከሰመ ድርስ አርፎ የሚተኛ አይደለም ያሉት ዳይሬክተሩ እሰካሁንም ሽንፈቱን አምኖ ያልተቀመጠ እና ከስህተቱ የማይታረም መሆኑን እያሳየ ነዉ ብለዋል፡፡

በዚህም ሁሉም ተረባርቦ ቡድኑን ማጥፍት ካልተቻለ አሸባሪው ቡድን ለኢትዮጵያ ስጋት እንደሆነ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

[አሐዱ]
@YeneTube @FikerAssefa
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነሳ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለስድስት ወር ተደንግጎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ወሰነ።ምክር ቤቱ ዛሬ ረቡዕ ጥር 18 ቀን 2014 ዓም ባካሄደው ስብስባ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተፈጻሚነት ጊዜ እንዲያጥር ያደረገው አዋጁን ማውጣት “የግድ አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎ የነበረው ሁኔታ የተቀየረ በመሆኑና ስጋቱን በመደበኛው የሕግ ማስከበር ስራ መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ፣ ውሳኔውን ማስተላለፉን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ ከእስር መፈታቱ ተሰማ!

የአሃዱ ራድዮ የዜና ክፍል ኃላፊ የነበረው ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ ከእስር መፈታቱን ጣቢያው ዘግቧል፡፡ ጋዜጠኛው ዛሬ ጥር 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ ከእስር ተፈትቶ ከቤተሰቦቹ ጋር መገናኘቱን አሃዱ ራድዮ ጠበቃውን አቶ ጥጋቡ ደሳለኝን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ጋዜጠኛ ክብሮም ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም. በ15 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ቢወሰንለትም ለሳምንታት የነበረበት ሳይታወቅ ቆይቶ ዛሬ በመታወቂያ ዋስ ተፈትቷል፡፡

በፖሊስ እና በጠበቃው መካከል አካልን ነጻ የማውጣት ክርክር ሲካሄድ ቆይቶ በዛሬው ዕለት መፈታቱ ተሰምቷል፡፡ ጋዜጠኛው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ በመፈታቱ የተሰማውን ደስታ አጭር መልእክት ከቤተሰቦቹ ጋር ሲገናኝ የሚያሳይ ፎቶግራፍ ጨምሮ ከጥቂተት ደቂቃዎች በፊት አጋርቷል፡፡

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
#የሕይወት_ፍልስፍና

ሁሉም ሰው አስማተኛ ነው፡፡ ቃላቶቻችንን እንዴት መጠቀም እንዳለብን ከተማርን በሌሎች ላይ ጥሩ ወይም መጥፎ አስማት ማድረግ እንችላለን፡፡
ለመሆኑ የቃላቶቻችን አስማቶች ምን ይሆኑ?

ሕይወት ልክ እንደ ዳንስ ናት፡፡ ሪትሙ ሲቀያየር ላለመናደድ የዳንሱን ጥበብ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ለመሆኑ በሕይወት ውስጥ በጥበብ መደነስ የሚቻለው እንዴት ነው?

ራሳችን ከራሳችን ጋር በትክክል አንስማማም፤ ሁልጊዜም ከራሳችን ጋር ስንጣላ ነው የምንገኘው፡፡
ለመሆኑ እንዴት ነው ከራሳችንስ ጋር መታረቅ የምንችለው?

#የሕይወት_ፍልስፍና መጽሐፍ የቃላቶቻችንን አስማት ሊያሳየን፣ ከራሳችን ጋር እንድንታረቅ ሊረዳን፣ በሕይወት ላይ በጥበብ መደነስን ሊያስተምረን በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
ህወሓት በአፋር ዳግም በከፈተው ጥቃት ከ220 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የክልሉ መንግስት አስታወቀ

ህወሓት ከወረራቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲወጣና የከፈተውን ጦርነት እንዲያቆም የአፋር ክልል መንግስት አሳሰቧል
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ህወሓት በአፋር ክልል ላይ ዳግም በከፈተው ጥቃት ከ220 ሺህ በላይ ዜጎች ማፈናቀሉን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ፤ "ለሰላም ስል ወጥቻለሁ የሚለው ህወሓት ወሯቸው ከነበሩ አካባቢዎች እንዲወጣ ቢደረግም በማግስቱ ከታህሳስ 10 ቀን 2014 ጀምሮ በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የደረሰበትን ኪሳራ ለማካካስ እና ለመበቀል በኪልበቲ ረሱ በአብኣላ በኩል እና በተለያዩ ወረዳዎች ጥቃቶችን ማድረሱን እንደቀጠለ ነው” ብሏል።
አሜሪካ “የትግራይ ኃይሎች” በአማራና አፋር ግፍ መፈጸማቸውን አስታወቀች

“ህወሓት ከባድ መሳሪያ ወደ ንፁሀን ዜጎች በመተኮስ ህይወት እየቀጠፈ እና ሆስፒታሎች፣ የጤና ተቋማት እና ትምህርት ቤቶችን ኢላማ ያደረገ የከባድ መሳሪያ ድብደባ እየፈፀመ ነው” ሲልም የክልሉ መንግስተ አስታውቋል።

“ከሰሞኑም በተደራጀ መልኩ በአብአላ፣ በመጋሌና ኤረብቲ ወረዳዎችን በመቆጣጠር እና በራህሌ ወረዳንም ከፊል ቀበሌዎች ድረስ ዘልቆ በመግባት ከባድ ጥቃት ከፍቶ ንፁሀንን በመግደል እና በማሳደድ ወረዳዎቹን እያወደመ ነው” ሲልም አስታውቋል።
በህወሓት ዳግም ወረራም ከ220 ሺህ በላይ ንጹሃን ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውንም የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።

መግለጫው አክሎም “ህወሓት የራሱን እድሜ ከማራዘም ውጭ ጭራሽ ቅንጣት ታክል ለህዝብ ሰብአዊነት የሚሰማው አለመሆኑን በመግለፅ፤ በኪልበቲ ረሱ በኩል ለትግራይ ህዝብ ይደርስ የነበረውን ሰብአዊ ድጋፍ እንዲስተጓጎል አካባቢው የጦርነት ቀጠና እንዲሆን ተደጋጋሚ ጥቃት መፈፀሙን ለአብነት አንስቷል

“ህወሓት ርሀብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም እና የፖለቲካ ትርፍ በመፈለግ እየፈጸመ ካለው የሽብር ተግባሩ እንዲወጣ የአለም ማህበረሰብ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት እና የሽብር ቡድኑ በተደጋጋሚ የሚያወጣቸውን የውሸት ማወናበጃ መግለጫዎችን ሳይሆን መሬት ላይ ያለውን እውነታ በመረዳት ይህን ድርጊቱን በቃ እንዲል” ጥሪ አቅርቧል።

በትግራይ እንደተደረገው ሁሉ በአማራ እና በአፋርም ተመሳሳይ አይነት የጣምራ ምርመራና ሪፖርት ይደረግ ይሆን ?
የክልሉ መንግስት ከተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ጋር በቅርበት በመስራት ለትግራይ ህዝብ ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ ባለፉት ሶስት አመታት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ለአብነት ጠቅሷል።

“የክልሉ መንግስትም ሆነ የአፋር ህዝብ ለትግራይ ህዝብ በቡድኑ ወረራና ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደርስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር የሚሰራ ይሆናልም”ብሏል።

Via:- Al ain
@Yenetube @Fikerassefa
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ካለፈው መስከረም ወዲህ የመጀመሪያ ያለውን የህክምና ድጋፍ ዛሬ መቀሌ ማድረሱን አስታወቀ።

ድርጅቱ እንዳለው በአውሮፕላን ዛሬ መቀሌ የደረሱት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የህክምና አገልግሎት መስጫዎችና መድኃኒቶች በጦርነት በተመሰቃቀለችው በትግራይ በሚገኙ የጤና ተቋማት እንዲከፋፈል ይደረጋል። በኢትዮጵያ የድርጅቱ የጤና ጉዳዮች አስተባባሪ አፖሎ ባራሳ ከወራት በኋላ የመጀመሪያው የህክምና እርዳታ ትግራይ ሆስፒታሎች መድረስ መቻሉ ትልቅ እፎይታ ነው ብለዋል።ድጋፉም በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ማስቀጠል የሚያስችል ነው ሲሉም ተናግረዋል።ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ተጨማሪ የህክምና እርዳታዎችን በሚቀጥሉት ሳምንታት በአውሮፕላን ለመላክ እያቀደ መሆኑንንም አስታውቋል። ፀጥታው ሲረጋጋ ደግሞ በየብስ የመላክ ሃሳብ አለው።መቀመጫውን ጄኔቫ ያደረገው የዓለም ቀይ መስቀል ድርጅት ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው በአማራና በአፋር ክልሎች ለሚገኙ የጤና ተቋማትም የህክምና እርዳታ መስጠቱን እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
1
የጊኒው ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ማማዲ ለብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ይቅርታ አድርገዋል፣ ለሽልማት ታስቦ የነበረው ገንዘብም ወደ መንግስት ካዝና እንዲመለስ አሳስበዋል!

የጊኒው ፕሬዘዳንት ኮሎኔል ማማዲ ዱምብያ የብሄራዊ ቡድኑን አባላት ወደ ካሜሩን ሲሸኙ የአፍሪካ ዋንጫን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ለእናንተ ኢንቨስት ያደረግነው ገንዘብ ትመልሳላችሁ ብለዋቸው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

በርካታ ሚዲያዎች ትላንት እንደዘገቡት የጊኒ ብሔራዊ ቡድን በጋምቢያ ከትላንት በስቲያ 1 ለ 0 መሸነፉን ተከትሎ በውጭ ክለቦች የሚጫወቱት ተጨዋቾች ከአፍሪካ ዋንጫ መሠናበታቸውን ተከትሎ ከካሜሩን በቀጥታ ወደ አውሮፓ ክለቦቻቸው ማቅናታቸው ተዘግቧል።

የጊኒው ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ማማዲ ከውጤቱ በኋላ ንዴት በተሞላበት ንግግራቸው "በጨዋታው ለማሸነፍ ምንም ፍላጎት የሌላችሁ እና 13 ሚሊዮን ጊኒውያን ክብር ያዋረዳችሁ ናችሁ" ብለዋል

በአንፃሩ ዛሬ በተሰማው መረጃ የጊኒው ፕሬዘዳንት ኮሎኔል ማማዲ ለብሔራዊ ቡድኑ ይቅርታ አደርገው
ቀደም ሲል የተላለፈው ጠንካራ ትዕዛዝ ቡድኑን ለማበረታታት ብቻ ነው ብለዋል። ሆኖም ቡድኑ መልሶ ለመገንባት ጊዜ እንደሚያስፈልገው አምነዋል።

በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ እንዳሳሰቡት ቡድናቸው ለሩብ ፍፃሜ ፣ ለግማሽ ፍፃሜ እና ለዋንጫ ጨዋታዎች ካለፈ ተብሎ ለሽልማት ታስቦ የነበረው በጀት ወደ መንግስት ካዝና እንዲመለስ አሳስበዋል።

Via Ethio-Kickoff
@Yenetube @Fikerassefa
1
ጀነራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ 27 ግለሰቦች ሙሉ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ።

በዚህም መሠረትም፡-

1/ አቶ ተፈራ ደርበው
2/ አቶ ደሴ ዳልኬ
3/ ዶክተር ስለሺ በቀለ
4/ ጄኔራል ባጫ ደበሌ
5/ ጄኔራል ሀሰን ኢበራሂም
6/ ወ/ሮ ሽትዬ ምናለ
7/ ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ
8/ አቶ ረሻድ መሀመድ
9/ አምባሳደር ጀማል በከር
10/ አቶ ፈይሰል ኦሊይ
11/ አቶ ኢሳያስ ጎታ
12/ አቶ ፀጋአብ ክበበው
13/ አቶ ጣፋ ቱሉ
14/ ደክተር ገነት ተሾመ
15/ አቶ ዳባ ደበሌ
16/ አቶ ፍቃዱ በየነ
የባሉሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት
እንዲሁም
1/ አቶ አሳየ አለማየሁ
2/ አቶ ኃይላይ ብርሃነ
3/ አቶ አወል ወግሪስ
4/ ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት
5/ አቶ አንተነህ ታሪኩ
6/ አቶ አክሊሉ ከበደ
7/ አቶ ሰይድ መሐመድ
8/ አቶ ዮሴፍ ካሳዬ
9/ አቶ ዘላለም ብርሃን
1ዐ/ ወ/ሮ ፍርቱና ዲባኮ
11/ አቶ ወርቃለማሁ ደሰታ በአምባሳደርነት የተሾሙ መሆኑን ከፕሬዝዳንት ፅሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ከቀረቡት ዕጩዎች መካከል 42ቱን መለየቱን የም/ቤቱ አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ አስታወቁ፡፡

አፈ-ጉባኤው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አዋጅ ቁጥር 1265/14 መቋቋሙንና በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ዕጩ ኮሚሽነሮች እንዲጠቆሙ በሁሉም ሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሀን መተላለፉን አስታውሰዋል::የጥቆማ ማቅረቢያ ጊዜው እንዲራዘም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት በአካልና በጽሁፍ በጠየቁት መሰረት የሁሉም አካላት ተሳትፎ እንዲረጋገጥ ም/ቤቱ ለአንድ ሳምንታት ማራዘሙን እና ባለፉት ሳምንታትም ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የም/ቤቱ ጽ/ቤት የዕጩ ኮሚሽነሮችን ጥቆማ ሲቀበል መቆቱን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች 632 የእጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ መቅረባቸውንና አብዛኛዎቹ ስራውን ለመስራት የሚያስችል ልምድና ዕውቀት ያላቸው መሆኑን መገንዘብ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡አዋጁ ለአፈ-ጉባኤውና ለአፈ-ጉባኤው ጽ/ቤት በሰጠው ስልጣን እንዲሁም በአዋጁ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ከቀረቡት 632 ዕጩዎች መካከል 42ቱ መለየታቸውን ክቡር አፈ-ጉባኤው ተናግረዋል፡፡አክለውም በቀረቡት 42 ዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከአማካሪዎች ጋር ምክክር እየተደረገበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ሳምንትም የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች፣ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት አመራር አካላት በሚገኙበት በዕጩዎች የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ ላይ ምክክር ተደርጎ ግብአት የሚሰበሰብ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር በም/ቤቱ ድረ-ገጽና በማህበራዊ ሚዲያ የእጩዎችን ማንነት በመግለጽ በቂ ግብአት ከተሰበሰበ በኋላ ሰብሳቢና ም/ሰብሳቢን ጨምሮ 11ዱ ዕጩ ኮሚሽነሮች ለም/ቤቱ ቀርቦ ከፀደቀና ዕጩዎች ከተሰየሙ በኋላ ወደ ስራ እንደሚገባም ገልጸዋል።

በመጨረሻም አፈ-ጉባኤው ቀጣይ በሚደረገው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ከህዝብ የሚነሱ የተለያዩ ሀገራዊ ሀሳቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመው ሀገሪቱ ትልቅ ታሪክ፣ ህዝብ፣ ስነ-ልቦና እና ሀብት ያላት በመሆኑ ሁሉም አካል የሰከነ ውይይት በማድረግ እና መግባባት ላይ በመድረስ የሀገሪቱን የብልፅግና ጉዞ ማረጋገጥ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
#አስበህ_ሀብታም_ሁን!
THINK & GROW RICH

#በሶስት_የአሜሪካ_ፕሬዚዳንቶች_የተገመገመ_የዓለማችን_ብቸኛ_መጽሐፍ!!

መጽሐፍዎ በየትኛውም የሕይወት ዘርፍ ላለ ማንኛውም መሪ ማወቅ ያለበትን እጅግ ጠቃሚ መረጃ ይዟል፡፡ በዚህ አስደናቂ የተፈጥሮ “እውቀት ፍልስፍና” ትምህርት ዝግጅትዎ ወቅት የተወሰነ ድጋፍ ለማድረግ ዕድሉን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ፡፡

#ፍራንክሊን_ሩዝቬልት
32ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ፍ/ቤት ዋና ዳኛ

በእርግጥ የጠየቅከውን መረጃ እሰጥሃለሁ፡፡ ይህ ግዴታ ብቻ ሳይሆን ደስታም እንደሆነ አስባለሁ፡፡ የውድቀት ወይም የስኬት ምክንያቶችን ለማወቅ ጊዜም፣ ፍላጎትም ለሌላቸው ሰዎች ተወካይ በመሆን እየደከምክ ነው፡፡
#ቴዎድር_ሩዝቬልት
26ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት

በትክክል በገለጡት “የላዕላይ አእምሮ” መርህ ትርጓሜዎ እጅግ በጣም ተደስቻለሁ፡፡
#ውድሮው_ዊልሰን
28ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት

የስኬት ሕግን ዋናውን ረቂቅ ጽሁፍ በመላክ ስለ ሰጡኝ ምስጋና አድናቆቴን እንድገልፅ ይፍቀዱልኝ፡፡ በዝግጅቱ ብዙ ጊዜ እና ጉልበት እንዳሳለፉ እረዳለሁ፡፡ ፍልስፍናዎ ትክክል ነው፡፡ በስራው ለረጅም አመታት ስለደከሙ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡
#ቶማስ_ኤድሰን
የዓለም እጅግ ታላቁ የፈጠራ ባለቤት

አራተኛው ዕትም በገበያ ላይ።

https://tttttt.me/teklu_tilahun
⚡️ምንም ቢሆን ምንም ⚡️
አላማችንን ለማሳካት ወደፊት እንራመድ ✊🏾
.
.
.
⚡️No matter what⚡️
We must move forward to achieve our goals ✊🏾

Join Our telegram
👉 https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk
🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦
በአሜሪካካናዳ በስኮላርሺፕ የመማር ዕድል!

ያለ ቅድመ ክፍያ ለመመዝገብ ቴሌግራም ቦት ላይ አፕላይ ያድርጉ! 👇
@marakischolarshipbot


አድራሻ: ቦሌ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቁጥር 102

ስልክ: 0960612222

ለበለጠ መረጃ @marakiconsultant

ቴሌግራም ቻናል👇
@marakiconsultancy
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ 💦በሠላም አደረሳችሁ 2014ዓ.ም

የሻረግ ቅመማ-ቅመም 👌

#ምርቶቻችንን :-
👉 በሸዋ ሾፒንግ
👉 በክዊንስ
👉 በሎሚያድ
👉 በጋራ ማርት
👉 በልዊስ(ባምቢስ)
👉 በዴይሊ ሚኒማርት እና በሌሎች ሱፐር ማርኬቶች ያገኙናል።

#ጥራት እና ዋጋ ቅናሽ መለያችን ነው !!
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ
#የሕይወት_ፍልስፍና

ሁሉም ሰው አስማተኛ ነው፡፡ ቃላቶቻችንን እንዴት መጠቀም እንዳለብን ከተማርን በሌሎች ላይ ጥሩ ወይም መጥፎ አስማት ማድረግ እንችላለን፡፡
ለመሆኑ የቃላቶቻችን አስማቶች ምን ይሆኑ?

ሕይወት ልክ እንደ ዳንስ ናት፡፡ ሪትሙ ሲቀያየር ላለመናደድ የዳንሱን ጥበብ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ለመሆኑ በሕይወት ውስጥ በጥበብ መደነስ የሚቻለው እንዴት ነው?

ራሳችን ከራሳችን ጋር በትክክል አንስማማም፤ ሁልጊዜም ከራሳችን ጋር ስንጣላ ነው የምንገኘው፡፡
ለመሆኑ እንዴት ነው ከራሳችንስ ጋር መታረቅ የምንችለው?

#የሕይወት_ፍልስፍና መጽሐፍ የቃላቶቻችንን አስማት ሊያሳየን፣ ከራሳችን ጋር እንድንታረቅ ሊረዳን፣ በሕይወት ላይ በጥበብ መደነስን ሊያስተምረን በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://tttttt.me/teklu_tilahun
የኤፈርት ኩባንያዎችን በጊዜያዊነት የሚያስተዳድረው ቦርድ ተበተነ!

የህወሓት ንብረት የሆኑንት የኤፈርት የንግድ ኩባንያዎች የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ የባንክ ሂሳባቸው ታግዶ መንግስት በሰየመው ቦርድ ሲመሩ የቆዩ ሲሆን በቅርቡ ግን ስባት አባላት ያለው ቦርድ ስራውን በፈቃዱ ለቆ ተበትኗል።

ከአንድ አመት በፊት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የትግራይ ክልልን በሚያስተዳድረው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የፌዴራል መንግስት መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ጠቅላይ አቃቤ ህግ (የአሁኑ ፍትህ ሚኒስቴር) 38 የኤፈርት ኩባንያዎች የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ኩባንያዎቹ ከህወሓት ጋር ያላቸውን የወንጀል ግንኙነት ከመመርመር ጎን ለጎንም ጉዳዩ እልባት እስኪያገኝም 38ቱ የኤፈርት ኩባንያዎች በሰባት አባላት የሚመራ ቦርድ ተቋቁሞ እንዲተዳደሩ ተደርጎ ቆይቷል።

ሙሉ ዘገባው: https://bit.ly/34bokKf

@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ እየተካሄደ ነው!

የፌደራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

መድረኩ በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየመከረ ይገኛል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አህመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የሁሉም ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ሀላፊዎች በመድረኩ እየመከሩ እንደሚገኙ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የፌደራል እና የክልል መንግስታት የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ ከወር በፊት በሰመራ መካሄዱ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሳውዲ ታሳሪዎች ጉዳይ ከሳውዲው ንጉስ ሰልማን ጋር ለመወያየት ለፊታችን ቅዳሜ ቀጠሮ ተይዟል!

የኢትዮጵያንና የሳውዲ ዐረቢያን ግንኙነት ለማሻሻልና በሳውዲ ታስረው የሚገኙና ወደ ሀገራቸው መመለስ በሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግስት የላካቸው ከፍተኛ የልዑክ ቡድን የፊታችን ቅዳሜ ከንጉስ ሰልማን ኢብኑ አብዱልአዚዝ ጋር ዉይይት ያደርጋሉ።

በተጨማሪም ልዑኩ በቆታው ከሳውዲ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

የልዑካን ቡድኑ ከሚኒስትሮች፥ከሃይማኖት አባቶች፥ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በኢትዮ-ሳውዲ ጉዳይ ከፍተኛ ምርምር ያደረጉ ግለሰቦች የተካተቱበት ነው። ልዑኩ የተላከው የእስረኞችን ችግር ለመፍታትና የሀገራቱን ግንኙነት ለማሻሻል ልዑክ በመላክ ንጉሡን ማናገር እንደሚገባ በሳውዲ ዐረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ባቀረቡት ምክረ ሀሳብ መነሻነት መንግስት ልዑኩ ወደ ሳውዲ እንዲሄድ መንግስት መወሰኑን የደረሰኝ መረጃ ያሳያል። ልዑኩ በአሁኑ ሰዓት በሳውዲ ዐረቢያ ዋና ከተማ በሪያድ ከተማ ይገኛል። የልዑኩ አባላት አስር ሲሆኑ የሚከተሉት ይገኙበታል።

1) አቶ አሕመድ ሺዴ
2) አምባሳደር ሪድዋን ሁሴን
3) ዶ/ር ጄይላን ከድር
4) ፕሮፌሰር አደም ካሚል
5) ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እድሪስ
6) ቄስ ታጋይ ታደለ
7) አቶ መስፍን ገብሬ
8)አቶ ሀይደር አብደላ
9) አምባሳደር ሌንጮ ባቲ
የኢትዮጵያንና የሳውዲ ዐረቢያን ግንኙነት በተመለከተ ፕሮፌሰር አደም ካሚል በዐረብኛ ቋንቋ ለንጉሡ ገለፃ እንዲያደርጉ በልዑኩ ተመርጠዋል።

Via Ustaz Kamil Shamsu
@YeneTube @FikerAssefa
ተቋርጠው የቆዩት የንብረት ሽያጭ፣ በስጦታ የማስተላለፍና ሌሎች አገልግሎቶች ወደ አገልግሎት ሊመለሱ ነው!

ተቋርጠው የቆዩት የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭ ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልና ሌሎችም አገልግሎቶች ከሰኞ ጥር 23/ 2014 ጀምሮ ወደ አገልግሎት እንደሚመለሱ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል።

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሽያጭም ሆነ በስጦታ የማስተላለፍ ውልን የማረጋገጥ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ከሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 ጀምሮ የተቋረጡትን አገልግሎቶች መስጠት የሚጀምር መሆኑን አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት ከዚህ ቀደም በተለመደው አግባብ በተቋሙ አሰራር መሠረት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት እና የተቋሙን ድረ-ገጽ www.dars.gov.et በመጠቀም ተቋሙ ባዘጋጀው የኦንላይን አገልግሎት መጠየቂያ ፎርም በመሙላትና ሲስተሙ የሚሰጠውን የጉዳይ መከታተያ ቁጥር በመያዝ በተቋሙ በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት የሚቻል መሆኑን የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa