በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ዞኖች በፀጥታ ችግር ምክንያት ከሁለት ዓመት በላይ ምንም አይነት የመብራት አገልግሎት እንዳላገኙ ተነገረ፡፡
የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መለሰ በየነ ለአሐዱ እንዳሉት ባለፉት ዓመታት በመተከል እና ካማሽ ዞኖች በታጣቂዎች የተስተጓጎለው የመብራት አገልግሎት መፍትሔ ሳያገኝ እስካሁን ድረስ ዘልቋል ብለዋል፡፡
በዚህም ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት ተዳርጓል፤በተለይም በከተሞች አካባቢ በመብራት ኃይል ብቻ ስራቸውን የሚሰሩ ዜጎችን ለስራ አጥነት ተጋላጭ አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡
ችግሩ መቼ መቋጫ ይሰጠዋል ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄም በቀጣይ የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ሲስተካከል እግር በግር በመከተል ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመመለስ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
[አሐዱ]
@YeneTube @FikerAssefa

ህወሓት በድጋሚ በኪልበቲ ረሱ ዞን ጦርነት መክፈቱን የአፋር ክልል አስታወቀ!
አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ውስጥ ገብቶ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ አሁንም በኪልበቲ ረሱ ዞን ጦርነት መክፈቱን የክልሉ መንግስት አስታቋል፡፡የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፥ የሸብር ቡድኑ በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ ዞን በኩል በአብአላና በመጋሌ ወረዳ የከፈተውን ውጊያ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡ምንም አይነት ሰብዓዊነትና ርህራሄ ፈፅሞ የሌለው አሸባሪ ቡድኑ በንፁሀን ዜጎች ላይ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ እያሸበረ ይገኛል ነው ያለው መግለጫው፡፡
ሁሌም ከትንኮሳ አርፎ የማያውቀው የሽብር ቡድኑ ለዘመናት የቆየውን በድንበር የሚዋሰኑ የአፋር እና የትግራይ ክልልች ህዝቦችን ግንኙነት ከምንም ሳይቆጥረው ሁለቱን ህዝቦች በማጋጨት የማይረባ ትርፍ ለማግኘት ሌት ተቀን እየጣረ ይገኛል፤እያደረሰ ባለው ጥቃትም የአፋር ንፁሃን ኢላማ በማድረግ የሽብር ተግባሩን በማስፋት ላይ ነው ብሏል፡፡
በዛሬው እለት እንኳን በኪልበቲ ረሱ ዞን በተለያዩ ቦታዎች የአፋር ክልልን ወሰን ጥሶ በመግባት በአብአላ፣ በመጋሌ እና በበራህሌ በኩል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት በመክፈት በርካታ ንፁሃንን ለጉዳት ዳርጓልም ነው ያለው መግለጫው።
ይሁንና ሁሌም በማጭበርበርና በውሸት ፕሮፖጋንዳ እድሜውን የሚያራዝመው ጁንታው በአፋር ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በኩል ዘልቆ በመግባት ንፁሀን የጎዳ ቢሆንም ጥቃት እንደተፈፀመበት አስመስሎ በማቅረብ አሁንም ማደናገሪያውን እየነዛ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
Via FBC

የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አመራር ቦርድ የኢትዮጵያ መንግሥት በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም ላይ ያቀረበውን አቤቱታ ላለማየት መወሰኑን ተዘግቧል።
የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ አመራር ቦርድ ዛሬ አልወያይበትም ብሎ ወደ ጎን የገፋው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴዎድሮስ የአማጺው ሕወሃት ደጋፊ እንደሆኑ እና በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ሐሰተኛ መረጃ እንደሚያሰራጩ ጠቅሶ የድርጅቱ የበላይ ቦርድ ምርመራ እንዲያደርግባቸው ያቀረበውን አቤቱታ ነው። ቦርዱ ይህን ያሳወቀው፣ በዶ/ር ቴዎድሮስ ሁለተኛ ዙር የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዕጩነት ላይ ለመወያየት ዛሬ በጀኔቫ ባደረገው ስብሰባ ላይ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል። ጉዳዩ እጅግ ውስብስብ፣ ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው እና ከቦርዱ አሠራር ውጭ እንደሆነ ኬንያዊው የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ አሞት 34 አባላት ላሉት ቦርድ የተናገሩ ሲሆን፣ ጉዳዩን ከቦርዱ ይልቅ ሌላ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ቢመለከተው ይሻላል በማለት ያቀረቡትን ሃሳብ ቦርዱ ያለ አንዳች ተቃውሞ ተቀብሎታል።
[ዋዜማ ራዲዮ]

Forwarded from YeneTube
Free Online Courses with Free Certificates 😳
To Get the links join our Telegram channel 👇🏾
https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk
To Get the links join our Telegram channel 👇🏾
https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk
Forwarded from YeneTube
🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦
በአሜሪካ ና ካናዳ በስኮላርሺፕ የመማር ዕድል!
ያለ ቅድመ ክፍያ ለመመዝገብ ቴሌግራም ቦት ላይ አፕላይ ያድርጉ! 👇
@marakischolarshipbot
አድራሻ: ቦሌ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
ለበለጠ መረጃ @marakiconsultant
ቴሌግራም ቻናል👇
@marakiconsultancy

👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አህመድ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን ለመጎብኘ ጅግጅጋ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጂግጂጋ ሲደርሱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው የልዑካን ቡድን በክልሉ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን በመጎብኘት የሰብዓዊ ድጋፍ ክንውኖችን ይገመግማል ይጠበቃል።
በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ230 ሺህ በላይ እንስሳት ሲሞቱ፣ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አርብቶ አደሮች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ከክልሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

❤1
በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ሌሊት ከወልድያ ወደ አዲስ አበባ 22 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ አጣዬ ከተማ ሲደርስ በቦታው ቆሞ ከነበረ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።
የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሀላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ግዛቸው እንደገለጹት፥ በአደጋው የ5 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ 12 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳትና 5 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።
በደረሰው አደጋ በውስጡ ያሉ 6 ህጻናት ምንም ጉዳት አልደርሰባቸውም።የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ቢሆን፥ ምናልባትም ከአቅም በላይ መጫንና ፍጥነት ሊሆን ኮማንደር ተስፋዬ ገልፀዋል።

ስፖርት!
የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች እና ኮከብ ግብ አግቢ አቡበከር ናስር ወደ ደቡብ አፍሪካ ማምራቱ ተረጋግጧል።
የደቡብ አፍሪካን ሊግ እየመራ የሚገኘው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ በጥር ወር የዝውውር መስኮት አቡበከር ናስርን ለማስፈረም ከክለቡ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው ድርድር መሰረት የድቡብ አፍሪካው ክለብ ተጨዋቹን ለሙከራ መጥራቱን ተከትሎ ትላንት ማምሻውን አቡበከር ናስር ወደ ደቡብ አፍሪካ አቅንቷል።በሙከራው ወቅት የትራንስፖርት እና ደቡብ አፍሪካ በሚቆይበትም ጊዜ የሚኖረዉን ሙሉ ወጪውን ክለቡ እንደማሸፍንም ታዉቋል።
📷Hattrick Sport
[Ethiopian Coffee Sport club]

የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አርቲስት አሊ ቢራን በመኖሪያ ቤቱ በመገኘት ጎብኝተዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት "በኦሮሞ እና በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያሳረፈዉን፣ ተወዳጁን የጥበብ ሰው እና የነፃነት ታጋዩን የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራን በመኖሪያ ቤቱ በመገኘት በመጎብኘቴ ደስታ ተሰምቶኛል" ብለዋል።ለተወዳጁ አርቲስት መልካም ጤንነትን እመኛለሁ ሲሉም ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በጊዜያዊነት ታግዶ የነበረው መሬት ነክ አገልግሎት አሁን እግዱ ተነስቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
የከተማ አስተዳደሩ ከቀን 07/12/2013 ዓ.ም ጀምሮ መሬት ነክ አገልግሎትን አግዶ መቆየቱ ይታወቃል።ጊዜያዊ እግዱ አሁን የተነሳ በመሆኑ አገልግሎቱን ከቀን 13/05/2014 ዓ.ም ጀምሮ በየክ/ከተማው ማግኘት ይቻላል።
ታግደው ከነበሩ አገልግሎቶች መካከል ጊዜያዊ እግድ የተነሳላቸው አገልግሎቶች ዝርዝር ከዚህ በታች የተገለጹት ናቸው ፦
1. ህጋዊ ሰነድ ላላቸው ይዞታዎች ብቻ ዋስትና እዳ መመዝገብ
2. የፍርድ ቤት እና የባንክ እግድ የመመዝገብና የመሰረዝ አገልግሎት
• የእዳና እገዳ የማጣራት አገልግሎት
3. የስመ ንብረት ዝውውር ስራ
• በባንክ ሐራጅ የተሸጠ
• በፍ/ቤት አፈፃፀም የተሸጠ
• የኮንዶሚኒየም ቤት የስም ዝውውር አገልግሎት
• በውርስ የተላለፈ ንብረት
• በReal estates አልሚ የተፈፀመ የቤት ሽያጭ
4. ለነባር ይዞታዎች የቦታ ኪራይና የቤት ግብር ተመን
5. የንብረት ግመታ
6. በይዞታ ይገባኛል ክርክር በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማስረጃ መስጠት
7. የወሰን ይመላከትልኝ /የወሰን ችካል/
8. በከተማ አስተዳደር የሚታወቅ እና ቅድሚያ የሚሰጥ የልማት ተነሺ አገልግሎት
• ካሣ ክፍያ
• ምትክ ቤት
• ምትክ ቦታ አሰጣጥ አገልግሎቶች
9. የቦታ ዝግጅት
10. የወሰን ማስከበር ተግባራት
11. በሊዝ በተላለፈ ቦታ ላይ የግንባታ ክትትል
12. የለማ መሬት በምደባ ወይም በጨረታ ማስተላለፍ
13. አዲስ ካርታ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
• የምትክ ኮንዶሚኒየም ቤት ለተወሰነላቸው
• ለአመራር የሚሰጡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች፣
• የReal estates ተጠቃሚዎች /ቤት ገዥዎች የተናጠል ካርታ

መገናኛ ብዙኃን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ማስታወቂያዎች ከማስተላለፋቸው ቀድመው ትክክለኛ መረጃ መያዛቸውን እንዲያረጋግጡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አሳሰበ፡፡
በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አማራጮች የሚተላለፉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስታወቂያዎች ክፍተት እየታየባቸው መሆኑን ባለስልጣኑ ተናግሯል፡፡
ማስታወቂያዎቹ በማህበረሰቡና በተማሪዎች ዘንድ የቅሬታ ምንጭ መሆናቸውን የተናገሩት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛው ተስፋዬ ትክክለኛ መረጃ ያልያዙ ማስታወቂያዎች ተማሪዎች ጊዜና ገንዘባቸውን በማባከን የተለያዩ ጫናዎች እንዲጋለጡ ምክንያት ሆነዋል ብለዋል፡፡
የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከትምህርት ስልጠና ባለስልጣን ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሥምምነት ተፈራርሞ እንዲህ ያሉ የችግር መነሻ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለመቆጣጠር መንገድ መጀመሩንም አቶ ግዛው ተናግረዋል፡፡
የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንዱዓለም አድማሱ በበኩላቸው መገናኛ ብዙኃን የሚያስተላልፏቸውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስታወቂያዎች ትክክለኛነት የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ አለን የሚሉትን እውቅና በተመለከተ የት ካምፓስ? በምን የትምህርት መስክ? በየትኛው መርሃ ግብር? የሚሉትን ጉዳዮች አጣርተው እንዲያስተላልፉም አሳስበዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ከ324 በላይ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ከ55 በላይ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኢትዮጵያ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑ የተናገሩት ዶ/ር አንዱዓለም እነዚህን ተቋማት በመቆጣጠር ጥራት ያለው ትምህርት እንዲሰጡ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመገናኛ ብዙኃን የሚተላለፉ አሳሳች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስታወቂያዎችን ለመቆጣጠር ያግዘኛል ያለውን ምክክር ከሚመለከታቸው ጋር እያካሄደ ሲሆን የመገናኛ ብዙኃን ሀላፊዎች፣ የማስታወቂያ ባለሙያዎችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀላፊዎች እየተሳተፉበት ነው።
[Sheger]

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ባሳየችው ደካማ አቋም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይቅርታ ጠየቀ፡፡
በመሠረተችው መድረክ ያልተሳካላት፣ የባለቤት እንግዳ፣ በራስ ድግስ ተመልካች የኾነችው ኢትዮጵያ ከዓመታት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መድረክ ብትቀርብም ሳይሳካላት ቀርቷል፡፡
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ታላቅ ሠንደቅ ወክለው ካሜሮን የደረሱት ዋልያዎቹ ውጤቱ ባልጠበቁት መንገድ ኾኖ በጊዜ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሰናብተዋል፡፡
በአፍሪካ ዋንጫ የዋልያዎቹን መድመቅ ለማየት የጓጉና የተመኙ ኢትዮጵያውያንም ከምድብ ጨዋታዎች በኋላ ብሔራዊ ቡድኑን በካሜሮን ሰማይ ሥር መመልከት አልቻሉም፡፡
በካሜሩን አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ይዞ በጊዜ መሰናበቱ ይታወሳል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ከ8 ዓመታት በኋላ ወደ ውድድር ከተመለሰበት መድረክ ሳይቀናው ተመልሷል።
ገና በመጀመሪያው ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ወሳኙን ተከላከይ በቀይ ካርድ ያጡት ዋልያዎቹ የእቅዳቸው መሰናክል እንዲጀምር አድርጓል፡፡ በምድብ ጨዋታዎች ሁለት ግብ ያስቆጠሩት ዋልያዎቹ በአንጻሩ 6 ግቦች ተቆጥረውባቸዋል፡፡ በኬፕቨርዲ 1ለ0 ፣ በካሜሩን 4 ለ1 ሲሸነፉ ከቡርኪናፋሶ ጋር 1አቻ ተለያይተዋል።
የብሔራዊ በድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎና ውጤትን አስመልክቶ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን በመግለጫቸው የፌዴሬሽኑ እቅድ ከምድብ ማለፍ እንደነበር ገልጸዋል። ይህ መሳካት ባለመቻሉም የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀዋል።
የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የተጫዋቾች በኮሮናቫይረስ መጠቃትና ከኬፕቨርዲ ጋር በነበረው ጨዋታ የተከላካዩ ያሬድ ባየህ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣት የታሰበው ውጤት እንዳይመጣ ዋና ምክንያት አድርገው ጠቅሰዋል። ብሔራዊ ቡድኑ ከውድድሩ በፊት በርከት ያሉ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ አቅዶ እንዳልተሳካም አስታውሰዋል። ይህም ለውጤቱ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩም ነው የገለፁት።
ብሔራዊ ቡድኑ የተገኙትን የግብ እድሎች በመጠቀም በኩልም ክፍተት እንደነበረበት የተናገሩት አሰልጣኝ ውበቱ ይህ ደግሞ ከተጨዋቾች የልምድ ማነስ የመጣ ነው ብለዋል።የአፍሪካ ዋንጫ መሥራቿ ኢትዮጵያ ከካሜሮኑ ድግስ በጊዜ ተሰናብታ ሌላ የአፍሪካ ዋንጫ እንድትጠብቅ ተገድዳለች፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ሥራ አመራር ቦርድ በጀኔቫ እያደረገው ባለው ስብሰባ ለድርጅቱ ዋና ዳይሬክተርነት በድጋሚ ዕጩ ሆነው በቀረቡት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኻኖም ላይ ዛሬ በሚስጢር ድምጽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። ዶ/ር ቴዎድሮስ የዓለም ጤና ድርጅትን ለሁለተኛ ሥልጣን ዘመን ለመምራት ብቸኛው ዕጩ ሆነው እንደቀረቡ ዓለማቀፍ ዜና ወኪሎች ዘግበዋል። የዕጩ ዋና ዳይሬክተሩ ምርጫ የሚጸድቀው ግን ሁሉም የድርጅቱ አባል ሀገራት በመጭው ግንቦት በሚሰጡት ድምጽ ነው። 28 የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት እና ኬንያ እና ሩዋንዳን ጨምሮ ጥቂት የአፍሪካ ሀገራት ዶ/ር ቴዎድሮስ በድጋሚ እንዲመረጡ ቀደም ሲል ድጋፋቸውን የሰጡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ግን ድጋፉን ነፍጋቸዋለች።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ቦርድ በድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ንግግር እንዳያደርጉ መከልከሉ ተቀባይነት እንደሌለው የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ!
ሚኒስቴሩ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፥ ኢትዮጵያ የድርጅቱን ዋና ዳይሬክተርን የስነ ምግባር ጥሰት በተመለከተ ቦርዱ እንዲመረምር በይፋ ቅሬታ ማቅረቧን አስታውሷል።ምንም እንኳ ቀደም ሲል የአፍሪካ እና ሌሎች ወዳጅ ሀገራትን በማስተባበር ዋና ዳይሬክተሩን እጩ አድርጋ በማቅረብ ብታስመርጣቸውም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በህወሓት ጦርነት ሲከፈት ግን የግለሰቡ ትክክለኛ ማንነት መገለጡንና ከሀገራቸው ይልቅ የሽብር ቡድኑን መምረጣቸውን አመልክቷል ።
የተመረጡበትን ሀላፊነት የቡድኑን ፕሮፓጋንዳ ለማሠራጨት እንደተጠቀሙበት ነው መግለጫው ያብራራው።ይህን ከድርጅቱ የስምግባር መርህ ጋር የሚጣረስ ድርጊትን ስራ አስፈፃሚ ቦርዱ እንዲመረምር በይፋ ብታመለክትም ቦርድ ጥያቄውን ተቀብሎ ከመመልከት ይልቅ ይብስኑ የኢትዮጵያ ተወካይ ይህን ጉዳይ እንዳያብራሩ መከልከሉን ነው ያስታወቀው።በአባል ሀገር ላይ እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት መፈፀሙ ተቀባይነት እንደሌለው ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

#አስበህ_ሀብታም_ሁን!
THINK & GROW RICH
#በሶስት_የአሜሪካ_ፕሬዚዳንቶች_የተገመገመ_የዓለማችን_ብቸኛ_መጽሐፍ!!
መጽሐፍዎ በየትኛውም የሕይወት ዘርፍ ላለ ማንኛውም መሪ ማወቅ ያለበትን እጅግ ጠቃሚ መረጃ ይዟል፡፡ በዚህ አስደናቂ የተፈጥሮ “እውቀት ፍልስፍና” ትምህርት ዝግጅትዎ ወቅት የተወሰነ ድጋፍ ለማድረግ ዕድሉን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ፡፡
#ፍራንክሊን_ሩዝቬልት
32ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ፍ/ቤት ዋና ዳኛ
በእርግጥ የጠየቅከውን መረጃ እሰጥሃለሁ፡፡ ይህ ግዴታ ብቻ ሳይሆን ደስታም እንደሆነ አስባለሁ፡፡ የውድቀት ወይም የስኬት ምክንያቶችን ለማወቅ ጊዜም፣ ፍላጎትም ለሌላቸው ሰዎች ተወካይ በመሆን እየደከምክ ነው፡፡
#ቴዎድር_ሩዝቬልት
26ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
በትክክል በገለጡት “የላዕላይ አእምሮ” መርህ ትርጓሜዎ እጅግ በጣም ተደስቻለሁ፡፡
#ውድሮው_ዊልሰን
28ተኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት
የስኬት ሕግን ዋናውን ረቂቅ ጽሁፍ በመላክ ስለ ሰጡኝ ምስጋና አድናቆቴን እንድገልፅ ይፍቀዱልኝ፡፡ በዝግጅቱ ብዙ ጊዜ እና ጉልበት እንዳሳለፉ እረዳለሁ፡፡ ፍልስፍናዎ ትክክል ነው፡፡ በስራው ለረጅም አመታት ስለደከሙ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡
#ቶማስ_ኤድሰን
የዓለም እጅግ ታላቁ የፈጠራ ባለቤት
አራተኛው ዕትም በገበያ ላይ።
https://tttttt.me/teklu_tilahun

⚡️ምንም ቢሆን ምንም ⚡️
አላማችንን ለማሳካት ወደፊት እንራመድ ✊🏾
.
.
.
⚡️No matter what⚡️
We must move forward to achieve our goals ✊🏾
Join Our telegram
👉 https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk
አላማችንን ለማሳካት ወደፊት እንራመድ ✊🏾
.
.
.
⚡️No matter what⚡️
We must move forward to achieve our goals ✊🏾
Join Our telegram
👉 https://tttttt.me/+qtDDnplBq9UzZGRk
🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦🇨🇦
በአሜሪካ ና ካናዳ በስኮላርሺፕ የመማር ዕድል!
ያለ ቅድመ ክፍያ ለመመዝገብ ቴሌግራም ቦት ላይ አፕላይ ያድርጉ! 👇
@marakischolarshipbot
አድራሻ: ቦሌ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
ለበለጠ መረጃ @marakiconsultant
ቴሌግራም ቻናል👇
@marakiconsultancy
በአሜሪካ ና ካናዳ በስኮላርሺፕ የመማር ዕድል!
ያለ ቅድመ ክፍያ ለመመዝገብ ቴሌግራም ቦት ላይ አፕላይ ያድርጉ! 👇
@marakischolarshipbot
አድራሻ: ቦሌ ጌቱ የንግድ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቁጥር 102
ስልክ: 0960612222
ለበለጠ መረጃ @marakiconsultant
ቴሌግራም ቻናል👇
@marakiconsultancy
በኦሮሚያ ክልል ስምንት ዞኖች በተከሰተው ድርቅ ከ800 ሺ በላይ ሰዎች ለተረጂነት ተጋልጠዋል!
በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ስምንት ዞኖች በዝናብ እጥረት በተከሰተው ድርቅ ምክንያት 800ሺ 244 ሰዎች ለተረጂነት መጋለጣቸውን የኦሮሚያ አደጋ ስጋትና ልማት ተነሺዎች አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።ኮሚሽኑ በመኖ እጥረት ምክንያት ከብቶች እየሞቱ መሆኑን ገልጿል።
ኦሮሚያ አደጋ ሥጋትና ልማት ተነሺዎች አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙስጠፋ ከድር ጉዳዩን አስመልክተው ለኢትዮጵያ ፕሬስ እንደገለጹት፤ በዝናብ እጥረት ምክንያት በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ስምንት ዞኖች በተከሰተው ድርቅ 800 ሺህ 244 ሰዎች ለተረጂነት ተጋልጠዋል።እንደ ኮሚሽነር ሙስጠፋ ገለጻ፣ ድርቁ ለሶስት ወራት እንደሚቆይ ተረጋግጧል።
መንግሥት የሰውን ሕይወት ከማዳን ጎን ለጎን በድርቁ ምክንያት ከብቶች እንዳይሞቱ እየሰራ ቢገኝም ከ6 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ እንስሳት መኖ ማቅረብ በመንግሥት አቅም ብቻ የሚቻል ባለመሆኑ ችግሩ ኣሳሳቢ መሆኑን ጠቁመዋል።መንግሥት ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ መፍትሄዎችን ወስዷል። እስካሁን ድረስ የሰውን ሕይወት ለማዳን 197 ሺ 896 ኩንታል እህል በድርቅ ለተጎዳው ለቦረና ዞን ብቻ እንዲደርስ ተደርጓል።