የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጥሪ
ምዕመኑ የከተራና ጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስተያን ጥሪ አቀረበች፡፡
በዓሉን በሰላማዊ ሁኔታ ለማክበር ቤተክርስትያኒቱ ከመንግስት የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበርና ኮሚቴ በማደራጀት ዝግጅት ማጠናቀቋን አሳውቃለች፡፡
በዓሉን በምናከብርበት ጊዜ አገራዊ ሁኔታን በመጠቀም በዓሉን ለማውክ የሚያስቡ አካላት ሊኖሩ ይችላሉ ሲሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስተያን የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በዚህም ምዕመኑ ግጭት ቀስቃሽ ፅሁፎችን ጨምሮ ተገቢነት የሌላቸዉ መልዕክቶችን ከማስተላለፍ፣በህግ ከተፈቀደዉ ባንዲራ ዉጭ ከመያዝ እንዲቆጠብም ጠይቀዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም በዓሉን ለማክበር ቤተክርስቲያኗ ካለፉት ሦስት ወራት ጀምሮ የተለያዩ ስራዎች ስታከናውን እንደነበር ጠቅሰው ፤ በተለይም ለረጅም ዓመታት ሲያገለግል የቆየውን የጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት ቦታ ግንባታ እንደተደረገለትም ጠቁመዋል፡፡
ለእድሳቱም ከ 10 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት ሲሆን 6 የዉሀ መሳቢያ ሞተሮች ፣ ጀነሬተሮች ጭምር መሟላታቸውን ነው የገለፁት፡፡
በተጨማሪም እድሳቱ ሌሎች መንፈሳዊ መርሃ ግብሮች እንዲከወንበት ታስቦ የተዘጋጀ ነዉ ብለዋል፡፡
አሐዱ ቴሌቪዥን!
@Yenetube @Fikerassefa

በሱማሌ ክልል በተከሠተው ድርቅ የዱር እንስሳት ለአደጋ መጋለጣቸው ተገለጸ!
በሱማሌ ክልል በተከሠተው ድርቅ ምክንያት በክልሉ የሚገኙ የዱር እንስሳት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ተገለጸ።
የክልሉ ማኅበረሰብ በብዛት አርብቶ አደር በመሆኑ ግጦሽ ፍለጋ የዱር እንስሳቱ ወደሚኖሩበት ቦታ ከብቶችን ይዞ በመግባቱ፣ እንስሳቱ እየተረበሹ መሆኑን የገራሌ ብሔራዊ ፓርክ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መልካሙ አይቸው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
በዚህም ምክንያት በተለይ በገራሌ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚኖሩ የዱር እንስሳት ቦታቸውን ጥለው ከመሰደድም ባሻገር፣ ከፍተኛ መረበሽ እንደሚያጋጥማቸው ነው ኃላፊው የጠቆሙት።
ኃላፊው አክለውም፣ ድርቁ በዚህ ወር ያበቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸው፣ ያ የማይሆን ከሆነ በፓርኩ ውስጥ ለሚገኙ የዱር እንስሳት ውኃ በቦቴ ለማቅረብ መታሠቡን ጠቁመዋል።
Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa

ኢትዮጵያ በታሪክ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ወደ ውጪ መላኳን ገለጸች!
ኢትዮጵያ በታሪክ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ወደ ውጪ ሀገራት መላኳን ገለጸች።
የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አንደገለጸው ባለፉት ስድስት ወራት 123 ነጥብ 6 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጪ ሀገራት ለመላክ ታቅዶ 148 ነጥብ 8 ሺህ ቶን ቡና ተልኳል።
የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር ለአል ዐይን እንዳሉት ባለፉት ስድስት ወራት ወደ ውጪ ሀገራት ከሚላክ ቡና 405 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 578 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።የተገኘው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ274 ሚሊየን ዶላር ወይም በ60 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አክለዋል።በተጠቀሱት ወራት ወደ ውጭ ሀገራት የተላከው ቡና እና የተገኘው ገቢ በኢትዮጵያ የቡና ንግድ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑንም አቶ ሻፊ ተናግረዋል።
ጀርመን፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ቤልጂየም፣ ጃፓን እና አሜሪካ የኢትዮጵያ ቡና በብዛት ከተላከባቸው አገራት መካከል ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ ቻይና ከዚህ በፊት የኢትዮጵያን ቡና በመቀበል ረገድ 33ኛ ደረጃ ላይ ከነበረችበት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ወደ ስምንተኛ ደረጃ መጥታለች ተብሏል።በቡና ንግዱ ላይ የኮሮና ቫይረስ እና በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት ቀጥታ ተጽዕኖ እንደሚፈጥሩ ስጋት ቢቀመጥም ምንም አይነት ተጽዕኖ እንዳላሳደሩም አቶ ሻፊ ኡመር ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ በቡና አቅራቢ እና ላኪ መካከል የነበረውን የተንዛዛ አስራር በማሳጠር፣ ከዚህ በፊት በቡና ድለላ ላይ የነበሩ አሰራሮችን በማስወገዱ፣ የቡና ምርት ጥራት የሚያሳድጉ አሰራሮችን በመከተሉ፣ የግብይት ስርዓትን የሚያዘምኑ የበይነ መረብ ግብይቶችን በመከተሉ ኢትዮጵያ ከቡና ንግድ የተሸለ ገቢ እንድታገኝ ያስቻሉ ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸውም ብሏል።አሁንም ኢትዮጵያ ከቡና ንግድ ማግኘት ያለባትን ገቢ እያገኘት አይደለም የሚሉት አቶ ሻፊ ሩሲያ እና የምስራቅ እስያ ሀገራት ቡናችንን ለመግዛት ከፍተኛ ፍላጎት በማሳየት ላይ በመሆናቸው እነዚህን ሀገራት በሰፊው እንጠቀማለንም ብለዋል።
ባለስልጣኑ የቡና ጥራትን በዘላቂነት ለማስጠበቅ የበይነ መረብ ግብይትን የበለጠ ማዘመን፣ የቡና ጥራት ስልጠና ማዕከላትን ማስፋፋት፣ ከዩንቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር በቡና ላይ ስፔሻላይዝ ያደረጉ ባለሙያዎችን ማፍራት እና ቡና አምራች ክልሎችን ማብዛት ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑንም ገልጿል።
ኦሮሚያ፣ ደቡብ ፣ሲዳማ፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልለ ጋር የሚዋሰኑ እና በሶማሌ ክልል ስር ያሉ ወረዳዎች ቡና በማምረት ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ገልጿል።
Via Alain

የከተራ በዓል በደሴ ከተማ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው!
የከተራ በአል በደሴ ከተማ በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል። ህዝበ ክርስቲያኑ ታቦታቱን ከመንበራቸው አጅቦ በመነሳት ሆጤ የሚገኘው ጥምቀተ-ባህር ድረስ በመሸኘት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ አዳሩን የከተራ በዓል ተከብሮ ነገ ማለዳ የጥምቀት ስነ-ስርአቱ የሚጀመር ይሆናል።
በደሴ ከተማ ብቻ የሚከበረው የሰባራፅሙ ጊዮርጊስ ጥር 17 የሚከበር ሲሆን ጥር 21 የአስቴርዮ ማርያም በዓልም በተለመደው ታቦታትን በማጀብና በተለምዶ ሆጤ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚካሄድ የጥምቀት ስነ-ስርአት የሚከበሩ ይሆናል፡፡
በዓላቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበሩ የከተማ አስተዳዳሩ ዝግጅት ማድረጉን ተናግሯል። ወጣቶችም ከጽዳት ጀምሮ የፀጥታው አጋር በመሆን በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ ትብብር እያደረጉ ነው።
Via Addis Zeybe

የከተራ በዓል በአዲስ አበባ በድምቀት እየተከበረ ነው!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በየዓመቱ የሚከበረው የከተራ በዓል በአዲስ አበባ በድምቀት እየተከበረ ነው።በአሁኑ ወቅት ታቦታቱ ከየመንበረ ክብራቸው ወጥተው በሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና በበርካታ ምዕመናን ታጅበው ወደማደሪያቸው እያመሩ ይገኛሉ።
ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ምዕመናን በመንፈሳዊ ዝማሬ ታቦታቱን አጅበው ወደ ጃንሜዳ በመሄድ ላይ ናቸው።
በበዓሉ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ወደ አገራቸው የመጡ ዳያስፖራዎችና ሌሎችም የውጭ አገር ጎብኝዎች እየተሳተፉ ነው።
[EPA]

ፌደራል መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ለሚገኙ አርሶ አደሮች አዲስ ፖሊሲ ለመዘርጋት ረቂቅ ሕግ እንዳዘጋጀ ፎርቹን ጋዜጣ አስነብቧል።
ረቂቅ ሕጉ በከተማዋ ስር ያሉ የገበሬ እርሻ መሬቶችን ጨምሮ የከተማ መሬት ይዞታዎችን ከአየር ላይ ካርታ ለማንሳት፣ በካርታና መሬት ላይ ድንበሮችን ለማሰመር፣ ቋሚ መለያ ምልክቶችን ለመትከል እና ወጥ የሆነ የከተማ መሬት አስተዳደር ለመዘርጋት ያስችላል።ረቂቅ ሕጉ ጸድቆ ሥራ ላይ ከዋለ፣ ባለ ይዞታዎች የእርሻ መሬታቸውን በአዲሱ የመሬት ምዝገባ ሥርዓት እንዲያስመዝገቡ፣ መሬታቸውን እንዲጠቀሙ፣ በገበያ ዋጋ እንዲሸጡ ወይም ለልማት ሲነሱ ከፍተኛ ካሳ እንዲያገኙ ያደርጋል።የእስካሁኑ አሠራር በከተማዋ ስር ላሉ የገበሬ እርሻ መሬቶች የባለቤትነት ማረጋገጫ አይሰጥም።
[Wazema/Fortune]

ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሁሉን አሣታፊ ብሔራዊ ምክክር ምንድነው?
• ሃገር አቀፍ ተሣታፊ ጉዳዮች ሁሉም
• ግልፅ እና ገንቢ አካሄዶች ብቻ የሚከተል ስርዓት
• መደማመጥ፤ መከባበር የሚያዳብር፤ የሌሎችን ጥያቄ እይታ መረዳት ፤ አዲስ እይታ
ምን እንጠብቅ፦
• በሃገራችን ያሉ ግድያዎች፤ ግጭቶችና የእርስበርስ ጦርነትን መከላከል፤ ካሉም ማስቆም
• በታሪካችን ያልታረቁ የፖለቲካ ፍጥጫዎችን የምናስተነፍስበት
• የኢትዮጵያ ማህበረሰብን በሚያግባቡት ጥቂት መሠረታዊ እሴቶች ላይ መገንባት
• አሽናፊና ተሸናፊ የሌላት የጋራ ኢትዮጵያ በጋራ መገንባት
እንዴት እጩ ኮሚሽነሮችን እንጠቁም
- ከላይ የተያያዘውን ቅጽ ፕሪንት ማድረግ
- ቅጹ ላይ ያለውን መጠይቅ መሙላት
- ስካን አድርጎ ለ dialoguecommission@gmail.com እና info@hopr.gov.et ኢሜል አድራሻ መላክ
ማሳሰቢያ
- አንድ ሰው መጠቆም የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን ተገንዝበን ብቃት ፣ታማኝነት፣ እና ቅንነት አላቸው የምናላቸውን ሰዎች በሐቅ እንጠቁም።
- በአግባቡ ቅጹን ሞልተን በመላክ ዕድሉን እንጠቀም።

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በዓል በተለያዩ አካባቢዎች እየተከበረ ይገኛል።
የእምነቱ ተከታዮች በትናንትናው የከተራ በዓል፣ ከየአድባራቱ ታቦታትን በማጀብ ሀይማኖታዊው የጥምቀት በዓል ወደሚከወንበት ጥምቀተ ባህር አድርሰዋል፡፡የጥምቀት በዓል፣ የእየሱስ ክርስቶስን በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅን ለማስታወስ የእምነቱ ተከታዮች የሚያደርጉት ስነ-ሥርአት ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
የእምነቱ ተከታዮች በትናንትናው የከተራ በዓል፣ ከየአድባራቱ ታቦታትን በማጀብ ሀይማኖታዊው የጥምቀት በዓል ወደሚከወንበት ጥምቀተ ባህር አድርሰዋል፡፡የጥምቀት በዓል፣ የእየሱስ ክርስቶስን በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅን ለማስታወስ የእምነቱ ተከታዮች የሚያደርጉት ስነ-ሥርአት ነው።
@YeneTube @FikerAssefa
ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የንግድ ባንክ ሕንፃ ተጠናቀቀ!
በርዝማኔውና በአገሪቱ የሕንፃ ግንባታ ታሪክ ከፍተኛ ወጪ የወጣበት፣ እንዲሁም በዘመናዊ ጥበብ የታነፀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ ግንባታ በመጠናቀቁ በይፋ ሊመረቅ ነው፡፡
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በምሥራቅ አፍሪካ ረዥሙ በመሆን የሚጠቀሰው የባንኩ ሕንፃ በይፋ የሚመረቀው ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው፡፡ ጥር 21 ቀን 2007 ዓ.ም. 48 ፎቆች ያሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ሕንፃ ግንባታ ሲጀመር ግንባታው 5.2 ቢሊዮን ብር እንደሚጠናቀቅ ታሳቢ ተደርጎ ቢሆንም፣ በአሁኑ ጊዜ ግን አጠቃላይ ወጪው ከሰባት እስከ ከስምንት ቢሊዮን ብር ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል፡፡
የሕንፃው ግንባታ ከተያዘለት ጊዜ በላይ መውሰዱ፣ የግንባታ ዕቃዎች መጨመር፣ የምንዛሪ ተመን ጭማሪና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች የግንባታውን ወጪ ከታሰበው በላይ እንዲሆን እንዳደረጉት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የዲዛይን ለውጥ ተደርጎ አዳዲስ ሥራዎች የታከሉ በመሆናቸው፣ መጀመርያ ከተያዘው ዋጋ በላይ ጭማሪ ማስከተሉ ተጠቁሟል፡፡
Via Reporter