YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ከ100 በላይ ሰዎች ከሞሮኮ በዉሃ ዋና ወደ ስፔን የወደብ ከተማ ሲዉታ መግባታቸዉ ተሰማ

የስፔን መንግስት እንዳስታወቀዉ ከ100 በላይ የሆኑ ስደተኞች በአንድ ሌሊት ከሞሮኮ ወደ ስፔን ሲውታ አከባቢ በባህር ዳርቻ ተንሳፋፊ አካል በመጠቀም እና በዋና መግባታቸዉን ይፋ አድርጓል፡፡

የስፔን የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ከሆነ የሞሮኮ ድንበር ጠባቂዎች ይህ ሁኔታ ሲፈጠር በአጠገባቸው ቆመው ስደተኞቹ ራሳቸውን ለአደጋ ሲያጋልጡ እየተመለከቱ ነበር ሲሉ ዘግበዋል፡፡

አብዛኛዎቹ ስደተኞች የመጡት በሰሜናዊው የቤንዙ ዳርቻ አካባቢ ሲሆን የተወሰኑት በስተደቡብ በኩል ታራላል በተባለዉ የባህር ዳርቻ ነወ፡፡

በትላንትናዉ እለት ብቻ 5000 ያህል ስደተኞች ወደ ስፔን መግባታቸዉን ተከትሎ የስፔን መንግስት ወታደራዊ ሀይሉን ድንበሩን እንዲጠብቅ ማድረጓ ተሰምቷል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa