YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ 446 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 617 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 111 የላቦራቶሪ ምርመራ 446 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 130 ሺህ 772 ደርሷል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 617 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 116 ሺህ 045 ሆኗል።ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 029 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 12 ሺህ 696 ሰዎች መካከል 219 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በአዲስ አበባ ሊያካሂድ የነበረውን ሕዝባዊ ስብሰባ እንደተከለከለ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡ ፓርቲው በከተማዋ ሕዝባዊ ውይይት ለማድረግ ቀተሮ የያዘው ለጥር 9 እንደነበር ገልጧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራዩ ግጭት ጉዳት ደርሶብናል ያሉ ግብጻዊያን ባለሃብቶች ከኢትዮጵያ መንግሥት ካሳ እንደጠየቁ የግብጽ ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡በትግራይ ኢንዱስትሪ ዞን ልማት የተሠማሩት ባለሃብቶች ከመንግሥት የጠየቁት የጉዳት ካሳ 2 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡የኢትዮጵያ መንግሥት ለችግሩ መፍትሄ ካልሰጣቸው፣ ባለሃብቶቹ ጉዳዩን ወደ ዐለማቀፍ ግልግል መድረክ እንደሚወስዱት ዝተዋል፡፡ባለሃብቶቹ ስንት እንደሆኑ እና ፋብሪካዎቻቸው በክልሉ የት እንደሚገኙ ዘገባው አላብራራም፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ፋግታ ለኮማ ወረዳ ትናንት በደረሰ የትራፊክ አዳጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በጽህፈት ቤቱ የመንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር የስራ ሂደት ቡድን መሪ ኢንስፔክተር ለዓለም ጥላሁን እንደገለፁት÷ የትራፊክ አዳጋው ከአዲስ ቅዳም ወደ አዲስ አበባ ከሰል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ኤፌሰር የጭነት መኪና ከሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ የተከሰተ ነው፡፡በዚህም ኤፌሰር የጭነት መኪና ውስጥ የነበሩ ሁለቱ ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በ2 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እና በንብረት ላይም ውድመት መድረሱን አስረድተዋል።ሌሎች ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም ህክምና ተደርጎላቸው ወደቤታቸው መመለሳቸውን ከፋግታ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከምርጫው በፊት የተቋማትን ቁመና ሊቀይሩ የሚችሉ አዋጆች ለፓርላማ እንዳይመሩ ትዕዛዝ መተላለፉ ተሰማ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከመጪው ምርጫ በፊት የመንግሥት ተቋማትን የሚያቋቁሙና የኃላፊነት ሽግሽግ ሊያደርጉ የሚችሉ አዋጆችም ሆኑ ደንቦች፣ ለፓርላማ ተመርተው እንዳይፀድቁ መመርያ መተላለፉ ተሰማ።በ1997 ዓ.ም. ምርጫ ወቅት በተለይ ገዥው ፓርቲ (ኢሕአዴግ) በአዲስ አበባ ከተማ መሸነፉን ሲሰማ በአስተዳደሩ ሥር የነበሩ ሥልጣንና ኃላፊነቶችን ሰብስቦ ወደ ፌዴራል መንግሥት የወሰደበት ዓይነት አሠራር አንዳይፈጠር በሚል ሥጋት፣ የቀረቡ አዋጆችና ደንቦች ከምርጫ በኋላ ይደረጉ የሚል አቋም መያዙን፣ ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ተስፋዬ ዳባ ለሪፖርተር አስረድተዋል።

በመሆኑም ተመሳሳይ ዓይነት ስህተትና ችግር እንዳይፈጠር ተብሎ፣ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለአስተያየት የሚመጡ የማቋቋሚያ አዋጆችና ደንቦች ባሉበት እንዲቆዩና ለፓርላማ እንዳይተላለፉ እየተደረገ ነው ብለዋል።እንደ ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ ገለጻ፣ በአሁኑ ጊዜ በጣም አስፈላጊና በልዩ ሁኔታ መታየት ካለባቸው እንደ የኢትዮ ቴሌኮም ማቋቋሚያ አዋጅ ዓይነት ካልሆኑ በስተቀር፣ ሌሎች አዋጆችና ደንቦችን የማየት ዕደሉ ጠባብ ነው፡፡ይህም ሊሆን የቻለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊተላለፉ የነበሩ በርከት ያሉ አዋጆች፣ ከምርጫ በኋላ የሚቋቋመው አዲሱ መንግሥት ይያቸው በሚል አቋም እንደሆነ አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል።

በመሆኑም ማንኛውም ዓይነት ተቋም ባለው ቁመና ሥራውን እያከናወነ እንዲቆይ ተደርጎ፣ የምርጫ ሥራ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።መሥሪያ ቤቶችን ማሻሻል፣ ሥልጣንን የማስፋት ወይም የማጥበብ፣ ስም የመቀየር፣ እንዲሁም ተጠሪነትን የመቀየር ዓይነት አዋጆች ከምርጫ በኋላ የሚቋቋመውና አዲሱ መንግሥት ያስፈጽማቸው ተብለው በይደር መቀመጣቸውን አክለው ገልጸዋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም.፣ የድምፅ መስጫ ቀን እንዲሆን የምርጫ ሰሌዳውን ማፅደቁ የሚታወስ ነው።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
8ኛው ‘ጉዞ ዓድዋ’ “ዓድዋ - የአፍሪካ ድል” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለተጓዦቹ አሸኛኘት አደርገውላቸዋል።መሪ ቃሉ የተመረጠው የዓድዋ ድል የአፍሪካም ድል መሆኑን ለማስታወስ እንደሆነ የጉዞ ዓድዋ መሥራች እና አስተባባሪ ያሬድ ሹመቴ ተናግሯል።125ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ለመዘከር ወደ 125 የሚሆኑ ተጓዦች ወደ ዓድዋ ለመሔድ ተዘጋጅተው የነበረ ቢሆንም 5ቱ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው በመሆኑ መቅረታቸውን ያሬድ ገልጿል።

ከተጓዦቹ መካከል 18ቱ ሴቶች መሆናቸው ነው የተነገረው። የዘንድሮው ጉዞ ዓላማ እየተቀዛቀዘ የመጣው የሀገር ፍቅር ስሜት እንዲለመልም እና የድሉ ተምሳሌት የሆነው አንድነት እና ኅብረት በሕዝቡ ዘንድ እንዲጠናከር የማድረግ እንደሆነ ተጓዦች ተናግረዋል።በእግር የሚደረገው ጉዞው ከአዲስ አበባ እስከ ዓድዋ ወደ 1 ሺህ 10 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ይሆናል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር በተከሰተው ግጭት የሟቾች ቁጥር ወደ 48 ከፍ ብሏል።ሐኪሞች የአል ጂኔይና ሆስፒታሎች ደህንነት እንዲጠበቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡የሰላም አስከባሪዎች አካባቢዉን ለቀው በመውጣት ላይ መሆናቸው ለከፍተኛ ቀውስ እንዳያጋልጥ ተሰግቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢዜማ የክልል ልዩ ኃይል ወደ መከላከያ ወይም ፖሊስ ሊካተት ይገባል ሲል ጠየቀ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የክልል ልዩ ኃይል ከመከላከያ ሠራዊት ወይም ከፖሊስ ኃይል ጋር እንዲቀላቀል መንግሥትን ጠየቀ።በአንዳንድ አካባቢዎች የአንድ ክልል ልዩ ኃይል ከሌላው ክልል ልዩ ኃይል ጋር ሲጋጩ እየታየ ዝምታው የት እስኪደረስ እየተጠበቀ እንደሆነ ኢዜማ ግራ መጋባቱን የፓርቲው የምርጫ ስትራቴጂና ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ከውሰር እንድሪስ ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ ከውስር ይኽንን የተናገሩት ሐሙስ ጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም. የፓርቲውን የምርጫ ዝግጅትና ወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክቶ በነበረው መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡

‹‹መንግሥት በራሱ አካላት እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን በአስቸኳይ ማቆም አለበት›› ያሉት ወ/ሮ ከውሰር፣ በየክልሉ ያሉ የብልፅግና ፓርቲ አካላት እርስ በርሳቸው በሚፈጥሩት ግጭቶች የዜጎች ደኅንነት አደጋ ውስጥ መግባት የለበትም ብለዋል።‹‹መንግሥት ሰላማችን እንዲጠብቅ እንጂ የባሰ ሥጋት ውስጥ እንዲከተን አንፈልግም፤›› ሲሉ አክለው ገልጽዋል፡፡

በተመሳሳይ የፓርቲው ብሔራዊ የሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ተክሌ በቀለ፣ የክልል ልዩ ኃይል ምንም ዓይነት ሕገ መንግሥታዊ መሠረት የሌለውና ብሔርን ብቻ ለማገልገል የተፈጠረ ተቋም ነው ብለዋል፡፡በራሱ ክልል የሚኖርን የሌላ ብሔር ተወላጅ እንኳ እንደ ዜጋ የማይቆጥር እንደሆነ የገለጹት አቶ ተክሌ፣ የክልል ልዩ ኃይል ይፍረስ ባይባልም ችግሩ ተስተካክሎ ሕዝቡን ማገልገል እንዳለበት አስረድተዋል፡፡በመሆኑም ብቃቱ እየታየ ወደ ፖሊስና ወደ አገር መከላከያ ሊመደብ እንደሚገባ የጠቆሙት አቶ ተክሌ፣ ይህ ኃይል እያለ ምርጫ እንዴት ይካሄዳል የሚለው አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡

በቅርቡ የሰላም ሚኒስተሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ከሚል ከፓርላማ አባላት ጋር በነበራችው ውይይት፣ የክልል ልዩ ኃይል ምንም ዓይት ሕጋዊ መሠረት እንደሌለው መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ክልሎች እያሠለጠኑ ማስመረቁን ቀጥለዋል።በሌላ በኩል ወ/ሮ ከውሰር ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያሉ እስረኞችን አስመልክተው ሲናገሩ፣ ‹‹በታሪካችን ያገኘነውን ዴሞክራሲን የማዋለድ ዕድላችን ፍርድ ቤቶችም ጭምር እንዲያደናቅፉት አንፈልግም፤›› ብለው፣ ሕጉን ጠብቆ ጉዳያቸው ማለቅ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሮፌሰር በየነ 3.2 ሚሊዮን ብር የተገዛ የቤት መኪና ተበረከተላቸው!

በውጭ አገሮች የሚኖሩ የሀድያ ዞን ተወላጆች ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ በተለያየ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የቤት መኪና በሽልማት መልክ አበረከቱላቸው።የዞኑ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ለፕሮፌሰሩ 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የተገዛ የ2020 ሞዴል ሃዩንዳይ መኪና በሽልማት ተበርክቶላቸዋል።ሽልማቱ ትናንት በሆሳዕና ከተማ በተካሔደ ዝግጅት ነው የተበረከተው፡፡

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
የአጭር ጊዜ የተሃድሶ ስልጠና የተሰጣቸው የትግራይ ክልል ተወላጅ ፖሊስ አባላት በትግራይ ክልል ህዝብን እንዲያገለግሉ ስምሪት መስጠቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ሕግ ማስከበር ዘመቻውን ተከትሎ በክልሉ ሰላምና መረጋት እንዲሰፍን፣ የክልሉን ጸጥታ ተቋማት ለማደራጀትና ቀሪ የህወሓት አመራሮችን አድኖ ለፍርድ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ኮሚሽኑ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ሰላምና ጸጥታን ለማስፈንና ወንጀለኞችን የማደን ተልዕኮ በአገር መከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ የሕይወት መስዋዕትነት በተቀናጀ መንገድ በብቃት እየተወጡ መሆኑንም በመግለጫው አመልክቷል።

በዚህም ህዝቡን በሰላምና በፍትህ ለማርካት የክልሉ ተወላጅ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ ክልሉ ስምሪት እንደተሰጣቸው ኮሚሽኑ ጠቁሟል።“በአፍ መፍቻ ቋንቋ ተናጋሪ ፖሊስ አባላትን አሰልጥኖ ወደ ክልሉ ማሰማራቱ ህብረተሰቡ ያጋጠሙትን ችግሮች በፍጥነት ለመቅረፍና የተበታተነውን የጥፋት ቡድን ለማጽዳት ስምሪቱ ወቅቱን የጠበቀ ነው” ብሏል።

በህወሓት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ የተጎዳ ህዝብ ወደቀደመ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅሰቃሴው በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲመለስ የፖሊስ አባላቱ ግዳጃቸውን በጥንቃቄና ትኩረት በተሞላበት አግባብ እንዲወጡ ሃላፊነት እንደተጣለባቸው ኮሚሽኑ ገልጿል።

[ENA]
@YeneTube @FikerAssefa
ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተወሰደበት ሥልጣንና ኃላፊነት እንዲመለስለት ጥያቄ አቀረበ!

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እስከ በ2008 ዓ.ም. ድረስ ተሰጥተውት የነበሩ የሙስና ወንጀልን የመመርመርና ክስ የመመሥረት ኃላፊነቶች እንዲመለሱለት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቤቱታውን አቀረበ።ኮሚሽኑ ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት እንደ ዋንኛ መሣሪያ የነበሩ በተለይም የሙስና ወንጀልን የመመርመርና ተጠርጣሪ ላይ ክስ የመመሥረት ኃላፊነቶች፣ በ2008 ዓ.ም. በአዋጅ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ለፌዴራል ፖሊስ በመሰጠቱ ምክንያት ተቋሙን ጥርስ የሌለው አንበሳ እንዳደረገው ተጠቁሟል።

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም የነበሩት ኃላፊነቶች እንዲቀሩ በመደረጉ የነበረውን ተደማጭነቱን ከመቀነስ ባለፈ፣ ጀምሯቸው የነበሩ የክስና የምርመራ ሥራዎች ሳይቋጩ በመቅረታቸው፣ አሁን ሊኖረው የሚገባው ቁመና ላይ እንዳይገኝ እንዳደረጉት የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር አቶ ፀጋ አራጌ ለሪፖርተር አስረድተዋል።ኮሚሽኑ ሦስት ዋና ዋና ዓላማዎችን ይዞ መቋቋሙን የገለጹት ኮሚሽነሩ በተለይም የሥነ ምግባር ግንባታ፣ የቅድመ ሙስና መከላከልና ከእነዚህ አልፎ የሚመጣውን በሕግ መከላከል ተግባር የነበረ ቢሆንም፣ ከኮሚሽኑ ያላግባብ እንዲቀማ መደረጉን ተናግረዋል።ይሁን እንጂ ሦስተኛውን ኃላፊነት በመነጠቁ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን የሙስና ትግል ውጤታማ ማድረግ እንደተሳነ፣ መንግሥትም አስፈላጊውን ጥናት አድርጎ እንዲመልስላቸው መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ከሰሞኑ ኮሚሽኑን እንደ ገና በማቋቋም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የነበረውን ተጠሪነት፣ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማድረግ የሚያሻሽለው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ተደርጓል።የምክር ቤቱ የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሜቴ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ጥር 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ውይይት አካሂዷል።በውይይቱ የተሳተፉት ፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ የምሥራች ከተማ፣ ኮሚሽኑ እስከ 2008 ዓ.ም. ድረስ የነበረው ሥልጣንና ኃላፊነት በተለይም ጥቆማ መቀበል፣ ምርመራ ማድረግ፣ ክስ መመሥረት፣ ንብረት ማስመለስና እስከ መውረስ ድረስ የሚያሠራውና የተደራጀ እንደነበር ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ እነዚህ ሥልጣንና ኃላፊነቶች በመውሰዳቸው፣ በኮሚሽኑ ግርማ ሞገስና ትግሉ ላይ ጥላ እንዳጠላበት በግልጽ መመልከት ይቻላል ብለዋል።ኮሚሽኑ ራሱን ችሎ አገራዊ የፀረ ሙስና ትግሉን በመሪነት እንዲቀጥል የማይደረግ ከሆነ፣ አሁን ተሻሽሎ በወጣው ረቂቅ አዋጅ እነዚህ ኃላፊነቶች ካልተመለሱ ምንም ዓይነት መሻሻል አይኖረውም ብለዋል።አቶ የምሥራች አክለውም እነዚህ ኃላፊነቶች ካልተመለሱ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግም ሆነ የፌዴራል ፖሊስ፣ ለሙስና ከባለቤቱ የበለጠ ለወንጀሉ ትኩረት እንደማይሰጡና የሚቀርቡ ጥቆማዎች መስመራቸውን ጠብቀው እንደማይሄዱ አስረድተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ተስፈዬ ዳባ፣ ለኮሚሽኑ ተሰጥተው የነበሩት የምርመራና ክስ የመመሥረት ኃላፊነትና ሥልጣን ከመጀመሪያም ከተቋሙ የተወሰደበት መንገድ አግባብና ትክክል አልነበረም ብለዋል።በወቅቱ ኮሚሽኑ ድፍረት አብዝቶ ይደፈራሉ ተብለው የማይታሰቡ አመራሮችንና ጄኔራሎችን መነካካትና መመርመር በመጀመሩ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን እንደሚወሳው ቀላል ጉዳይ አልነበረም ሲሉ ተናግረዋል።ቢሮዎች ተሰብረው መረጃ ተወስዶ የጠፋበት ጊዜ እንደነበር የጠቆሙት ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ፣ ተቋሙ እጁ ተጠምዝዞ ኃላፊነቱ መወሰዱን ገልጸዋል።ይሁን እንጂ አሁን ተሻሽሎ የመጣው ረቂቅ አዋጅ ከኢንዶኔዥያ አሠራር ልምድ በመውሰድ የተዘጋጀ እንደሆነ አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል።

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
በትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በምዕራብ ጎጃም ዞን በጃቢ ጠህናን ወረዳ በሆዳንሽ ቀበሌ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ (ዶልፊን) ከፍኖተ ሰላም ወደ ጅጋ ሰርገኞችን ይዞ እየተጓዘ እያለ ተገልብጦ ከሙሽራው ጋር የነበሩ የ7 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን ሙሽራውን ጨምሮ 12 ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን የወረዳው የትራፊክ አደጋ ንዑስ ክፍል ሀላፊ ዋና ሳጅን አብባ ዋሴ ገልፀዋል።

ምንጭ: Amhara Police Commission
@YeneTube @FikerAssefa
ከሚመለከተው ህጋዊ አካል ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት በጥምቀት በዓል ድሮን መጠቀም እንደማይችሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችን ለመከላከል ከሚመለከተው አካል ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ድሮን ማብረር ወይንም ማንቀሳቀስ እንደማይችሉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታዉቋል።

ኮሚሽኑ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ሁሉም የፀጥታና የደህንነት ተቋማት ከከተራ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በድምቀት የሚከበረዉ የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር በቂ ዝግጅት አድርገዋል።

ከፀጥታ አጠባበቅ ጋር ተያይዞ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከልም የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል።

ከተገቢው አካል ፈቃድ ሳይኖራቸው ድሮኖችንም እንዳያበሩ ወይንም እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን ድሮንን ለተለያዩ አገልግሎቶች ለማዋልም ህጋዊ ስልጣን ካለዉ አካል ፈቃድ ማውጣት እንደሚቻል ተገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ ለጥምቀት በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በኢንዶኔዢያ ሱላዌሲ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 73 ደረሰ!

በኢንዶኔዢያ ሱላዌሲ ግዛት ምዕራባዊ ክፍል በተከሰተው የመሬት መንቀጥቅ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 73 መድረሱን የሀገሪቱን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘ ኒው ዴይሊ ዘግቧል፡፡ በሩክተር ስኬል 6.2 ማግኒቱድ በተመዘገው ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ 820 በላይ ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን 27800 ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡ በዚሁ የሱላዌሲ ደሴት ግዛት እ.ኤ.አ በ2018 ተከስቶ ከ2,000 በላይ ሰዎችን የቀጠፈውን የመሬት መንቀጥቀጥ ጨምሮ ኢንዶኔዢያ መሰል አደጋዎችን ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ አስተናግዳለች፡፡

Al-ain
@YeneTube @FikerAssefa
በህገ ወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ ከ4 ሺህ 600 በላይ ተተኳሽ የክላሽ ጥይት ተያዘ፡፡

በትላንትናው ዕለት ከመቐለ ወደ ባህር ዳር ከተማ ሲጓጓዝ ከነበረ አይሱዙ ኤፍኤስአር መካከለኛ የጭነት ተሽከርካሪ በወልደያ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በጉምሩክ ሰራተኞች አማካኝነት በተካሄደ ፍተሻ ብዛቱ 4 ሺህ 615 የሆኑ ተተኳሽ የክላሽ ጥይቶች ተይዘዋል።

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹን በመደበቅ ለማሳለፍ የሞከሩ አሽከርካሪውን ጨምሮ  አራት ተጠርጣሪዎች  በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ማጣራት እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

በወልደያ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ አንድ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ10 ሺህ 600 በላይ ተተኳሽ የክላሽ ጥይቶች በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ከፅህፈት ቤቱ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from Delivery Hawassa
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ
#ዴሊቨሪ_ሀዋሳ

በሀዋሳ ከተማ ላይ የስልክ አገልግሎት ባለመኖሩ ምክኒያት Order በSMS በእየተቀበልን መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

ስልክ :- 0952626262

#Deliveryhawassa #hawassa
በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ95 ሚሊየን አለፈ!

በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 95 ሚሊየን 488 ሺህ 091 መድረሱን የወርልዶሜትርስ ዶት ኢንፎ መረጃ አመለከተ።በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሁለት ሚሊየን 39 ሺህ 706 ሲሆን፣ 68 ሚሊየን 196 ሺህ 088 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል ተብሏል።

ከዚህ ቁጥር ውስጥ አሜሪካ 24 ሚሊየን 482 ሺህ 050 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ዜጎች በማስመዝገብ በዓለም ደረጃ በቀዳሚነት ተቀምጣለች። ከዚህ ቁጥር ውስጥ 407 ሺህ 202 ዜጎቿ ሕይወት ሲያልፍ፣ 14 ሚሊየን 428 ሺህ 351 ዜጎቿ ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

ሕንድ 10 ሚሊየን 572 ሺህ 672 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች በማስመዝገብ በዓለም ደረጃ በሁለተኛነት ስትቀመጥ፣ 152 ሺህ 456 ዜጎቿ ሕይወት አልፏል።

ብራዚል 8 ሚሊየን 488 ሺህ 99 በቫይረሱ የተያዙ ዜጎች ስታስመዘገብ፣ ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሦስተኝነት አስቀምጧታል፤ 210 ሺህ ገደማ ዜጎቿ ሕይወት ደግሞ አልፏል።

ሩስያ እና ዩናይትድ ኪንግደም እያንዳንዳቸው ከሦስት ሚሊየን በላይ ዜጎቻቸውን እንዲሁም ፈረንሳይ፣ ቱርክ፣ ጣልያን ስፔን እና ጀርመን እያንዳንዳቸው ከሁለት ሚሊየን በላይ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች በማስመዝገብ ከአራተኛ እስከ ዐሥረኛ ደረጃዎች ይዘዋል።

EBC
@Yenetube @Fikerassefa
ጎንደር ለከተራ ዝግጅት አድርጋለች፡፡

በከተማዋ የአስፖልት ፅዳት በወጣቶች ተከናውኗል፡፡በባህረ ጥምቀቱ ግቢ ውስጥ ያለውን ሁነት የሚያሳይ ስክሪን ተዘጋጅቷል፡፡ከተማዋን በልዩ ልዩ መልኩ የማስዋብ ሥራም ተሠርቷል፡፡

[AMMA]
@YeneTube @FikerAssefa