38 ኩንታል ካናቢስ ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ዛሬ ከሌሊቱ 7 ሰአት ላይ መነሻውን ሻሸመኔ ያደረገው ኮድ 3 አዲስ አበባ 33498 አይሲዙ መኪና በአቃቂ ቃሊቲ ቱሉዲምቱ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ 38 ማዳበሪያ ካናቢስ መያዙን ኢትዮ ኤፍ ኤም ጽህፈት ቤቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሮክ ቅንጫፍ ፅ/ቤት የቱሉ ዲምቱ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሀላፊ አቶ ዋሪዮ ጉዮ ለጣቢያው ተናግረዋል፡፡ዕፁን ሲያጓጉዙ የነበሩ ሾፌርና ረዳት ጨምሮ ስራውን በውክልና ይሰራል የተባለ ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡አቶ ዋሪዮ እንዳሉት የካናቢሱ መጠን ለማወቅ በዚህ ሰአት እየተመዘነ ይገኛል በግምት ግን ከ3ሺህ ኪሎ በላይ ነው ብለዋል፡፡
[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa

በአዲስ አበባ ከተሰማሩ 500 ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ውስጥ 200ዎቹ ስራ አቆሙ።
በአዲስ አበባ ያለውን የትራንስፖር እጥረት ለመቅረፍ በሚል ድጋፍ እንዲሰጡ 500 አውቶቡሶችን ወደ ስራ ማስገባቱ ይታወሳል።ከነዚህ ውስጥም 200 የሚሆኑት ስራ ማቆማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሚውኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ ተናግረዋል፡፡
እርሳቸው እንዳሉት ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶቹ በመኖራቸው አንፃራዊ የትራንስፖርት መጨናነቁን ቀንሰውት ነበር ያሉ ሲሆን አሁን ግን ከወቅታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለአንዳንድ ስራ በመፈለጋቸው 200 የሚሆኑት ድጋፋቸውን አቁመዋል ብለዋል፡፡
ስለዚህም አሁን ላይ እንደከዚህ ቀደሙ በዋናነት ምልልሱን እየሰሩ ያሉት 300 የሚሆኑት አውቶቡስ በመሆናቸው ከተማው ላይ እየተስተዋለ ላለው የትራንስፖርት እጥረት እንደዋና ምክንያት ሆኗል ብዋል፡፡
ከዛም በተጨማሪም ከሁለት ሳምንት በፊት ትምህርት ቤቶች መከፈታቸውም የትራንስፖርት እጥረቱ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩን ተናግረዋል።ይሁንና ካለፈው ቅዳሜ ጠዋት አንስቶ በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች ሰማያዊ ታክሲዎች ከተለመደው ባነሰ መልኩ መኖራቸው ይታያል።
አንዳንድ የታክሲ አሽከርካሪዎች ለማናገር እንደሞከርነው መንግስት በነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ ለውጥ መኖሩ መስራት እየከበዳቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ለዚህ ሀሳብ በነዳጅ መሸጫ ታሪፍ ጭማሪ ምክንያት እጥረቱ ሊከሰት ይችላል ብለው እንደማያስቡ አቶ አረጋዊ ተናግረዋል።የትራንስፖርት ቢሮው ምንአልባት የታሪፍ ለውጥ የሚያስፈልገውም ከሆነ ጥናት ተካሂዶበት በአሽከርካሪዎች ላይ እና በባለቤቶቹ ላይ ተፅዕኖ የሚያመጣ ከሆነ በሚመለከተው አካል ታይቶ ማሻሻያ ሊደረግ ይችላል ብለዋል።
Via Ethio FM

የአድዋ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዛሬ ጀመረ!
በትግራይ ክልል ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር ተጠግኖ ዛሬ የአድዋ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልገሎት አግኝቷል።በዛሬው ዕለት ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የቆየው የአድዋ የኤሌክትሪክ መስመር በመጠገኑ ከተማው የመብራት አገልገሎት አግኝቷል።የአክሱም፣ ሽሬና ሑመራ ከተሞችም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ጥር 10 ቀን የሚውለው የከተራ በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው አገሪቱ ዛሬ ተከብሯል።
በዓሉ የእምነቱ ተከታዮች የዓለማት ፈጣሪ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እጅ መጠመቁን በማስመልከት የሚያከብሩት ነው።በዚህም ትውፊት መነሻነት ታቦታት ከየሚገኙበት አብያተ ክርስቲያን መንበረ ክብራቸው ተነሥተው ለጥምቀት ወደተከተሩ ውኃዎች እንደሚወርዱ የሃይማኖቱ ሊቃውንት ያስረዳሉ።
የእምነቱ ተከታዮች ሌሊቱን በማኅሌት እና በቅዳሴ ታቦታቱ በወረዱባቸው አካባቢዎች በመሰባሰብ በጋራ እንደሚያሳልፉም ይናገራሉ።በዓሉ ከሃይማኖት እና ትውፊት ባሻገር ኢትዮጵያውያን በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በአካባቢ ሳይለያዩ በአንድነት የሚያከብሩት እና የልዩ፣ ልዩ ባሕሎቻቸው መገለጫ የሆኑ አልባሳት እና መለያዎች ይዘው በመውጣት የሚያደምቁት የክርስቶስ ጥምቀት ዋዜማ መሆኑ ይታወቃል።በማግስቱ ጥር 11 ቀን ክርስቶስ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እጅ በፈቃዱ መጠመቁን በማስመልከት የጥምቀት በዓል ይከበራል።

በትግራይ ክልል ውስጥ "በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ" አንድ የመንግሥት ባለስልጣን መናገራቸውን ከእርዳታ ሠራተኞች ጋር ከተደረገ ስብሰባ ላይ ሾልኮ የወጣ ማስታወሻ ላይ የሰፈረ ጽሁፍ አመለከተ።
በመንግሥት የሚመራው የትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል በክልሉ የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ የሚያስፈልጉ ነገሮችን በተመለከተ ጥናት ያካሄደ ነው።የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁ መገለጹ ይታወሳል።
ነገር ግን አልፎ አልፎ ውጊያ እንደሚካሄድ የተነገረ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በክልሉ ያለውን የሰብአዊ ሁኔታ "የከፋ" ሲል ገልጾታል።
ጨምሮም "ምግብ አለመኖር ወይም በገበያዎች ላይ ያለው አቅርቦት ውስን መሆን እየባሰ የሚሄድ የምግብ እጥረት አደጋን እየፈጠረ መሆኑን ሪፖርቶች እያመለከቱ ነው" ብሏል።
በተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰውና የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል እንደሚለው በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል።ታኅሣስ 30/2013 ዓ.ም በትግራይ የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል አማካይነት በተካሄደው ስብሰባ ላይ በአንድ ተሳታፊ አማካይነት የተነሱ ነጥቦች የሰፈሩበትና ሾልኮ የወጣው ማስታወሻ እንደሚያሳየው፤ የማዕከላዊ ትግራይ ክፍል የጊዜያዊ አስተዳደሪ አንድ ባለሥልጣን እንዳለው "በስፍራው ያለው ሁኔታ በጣም የከፋ ነው" ብሏል።
[BBC]

የመቀሌ ከተማ ሰላምና ፀጥታ በአንፃራዊነት እየተሻሻለ ቢሆንም፣ አሁንም በመሣሪያ የተደራጁ ዘራፊ ቡድኖች መኖራቸውን የመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አስታወቁ፡፡
እንደ አቶ አታክልቲ ገለጻ፣ አዲስ የፖሊስ ኃይል በማደራጀት በጦርነቱም ሆነ ከጦርነቱ በፊት ምንም ዓይነት ተሳትፎ ያልነበራቸውን አባላት ተመልምለው ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡ ነገር ግን ትጥቅ ከማስፈታት በኋላ በድምፅ አልባ መሣሪያዎች የተደራጁ ዘራፊ ቡድኖች በየመንደሩ ዝርፊያ እየፈጸሙ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ የዝርፊያ ወንጀሉን ለመከላከል የአገር መከላከያ ሠራዊት ታች ድረስ ወርዶ ከተቋቋመው የፖሊስ ኃይል ጋር እያስከበረ እንደሚገኝ አቶ አታክልቲ አስረድተዋል፡፡
[Reporter]

336 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ!
336 ዜጎች ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።ከተመላሾቹ መካከል 75 ሕፃናት እንደሚገኙበት የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገልጿል።ዛሬ ወደ አገር የተመለሱትን ዜጎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር በተከሰተው ግጭት የሟቾች ቁጥር 129 ደረሰ።ከሟቾቹ በተጨማሪ 198 ሰዎች ሲቆስሉ 50 ሺ ያክል ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ በምዕራብ ዳርፉር የተከሰተው ግጭት እንዳሳሰበው የተባበሩት መንግስታት ገልጿል፡፡
[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ማይጨውና አካባቢው የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዘቸው ለ3 ወራት ህል ባለመከፈሉ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጋቸውን ተናገሩ።አስተያየት ሰጪዎቹ እንደሚሉት መንግስት ደመወዝ ባለመክፈሉ ምክንያት የእለት እርዳታም ለማግኘት የመንግስት ሰራተኛ ናችሁ በመባላቸው ብዙዎቹ ለችግር ተጋልጠዋል።የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር በበኩሉ ደመወዛቸው በቅርቡ እንደሚከፈል ተናግሯል፡፡
[DW]
@FikerAssefa @FikerAssefa
[DW]
@FikerAssefa @FikerAssefa
ምርጫ ቦርድ ከክልል መስተዳድሮች አስፈላጊውን ትብብር በጊዜው እያገኘ እንዳልሆነ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡ የምርጫ ክልል ቢሮዎችን፣ የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችን እና የሥልጠና ቦታዎችን በክልሎች ለማቋቋም ከክልል መስተዳድሮች ጋር ስምምነት ተደርሶ እንደነበር የጠቀሰው ቦርዱ፣ በቀነ ገደቡ ጥር 10 ግን ከአንድም ክልል ወይም የከተማ አስተዳደር ምላሽ አላገኘሁም ብሏል፡፡ ክልሎች እና የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ሕጋዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ቦርዱ አሳስቧል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ምርጫ ቦርድ የሕወሓትን ሕጋዊ ሰውነት መሰረዙን አስታወቀ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ላይ ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ የሕወሃትን ሕጋዊ ሰውነት መሰረዙን አስታውቋል፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ ከተቋቋመባቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ፣ ቁጥጥር እና ክትትል ነው። በመሆኑም በምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሠረት ፓርቲዎች የተለያዩ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።በዚህም መሠረት ቀደም ብሎ መስፈርት አሟልተው ምዝገባቸው የተጠናቀቀ እና በሂደት ላይ ያሉ ፓርቲዎች ዝርዝርን ማሳወቁ ይታወሳል።ቦርዱ ከዚህ ቀደም ውሳኔ ያልሰጠባቸው እንዲሁም የተጠየቁትን ማብራሪያዎች ያቀረቡ ፓርቲዎችን አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል።
1. ቦርዱ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የአመፃ ተግባር ላይ ተሰማርቷል ወይ የሚለውን ሁኔታ ለማጣራት በፓርቲው የተሰጡ መግለጫዎችንና በይፋ የሚታወቁ ጥሬ ሐቆችን በማቅረብ ፓርቲው ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመፃ ተግባር ላይ መሳተፉን አረጋግጧል። በተጨማሪም ፓርቲው መልስ የመስጠት እድል እንዲኖረው በማሰብ በፓርቲው እና በቦርዱ መካከል አገናኝ በመሆን ይሠሩ የነበሩትን የፓርቲውን የአዲስ አበባ ቢሮ የቀድሞ ተወካይ ለማነጋገር ጥረት ያደረገ ሲሆን፣ ተወካዩም ፓርቲውን መወከል እንደማይችሉ ገልጸዋል። በመሆኑም፦
ሀ. በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 98/1//4/ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሰርዞታል። በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 99 መሠረት የፓርቲው ሓላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉም ውሳኔ አስተላልፏል።
ለ. የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፓርቲው እና በፓርቲው አመራሮች ላይ በሚያደርገው ምርመራ የሚገኙ በሕወሓት ሥም የተመዘገቡ ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን በተመለከተ ያገኘውን ዝርዝር መረጃ እንዲልክ ቦርዱ ጥያቄ አቅርቧል።
ሐ. የፓርቲው ንብረት በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 99/2/ መሠረት ንብረቱ ተጣርቶ ዕዳ ካለበት ለዕዳው መሸፈኛ እንዲውል፣ ይሁንና እዳውን ሸፍኖ የሚተርፍ ንብረት ከተገኘ ቀሪው ገንዘብ እና ንብረት በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 99/3/ መሠረት ለሥነ ዜጋ እና መራጮች ትምህርት እንዲውል ቦርዱ ወስኗል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የአክሱምና ሽሬ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማምሻውን አግኝተዋል!
በትግራይ ክልል ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር ተጠግኖ የአድዋ፣ አክሱምና ሽሬ ከተሞችና አካባቢያቸው ዛሬ የኤሌክትሪክ አገልገሎት አግኝተዋል።መሠረተ ልማቱን ለመጠገን በተደረገው ከፍተኛ ጥረት ቀደም ሲል አብዛኞቹ የትግራይ ኣካባቢዎች የመብራት አገልግሎት ማግኘታቸውንና የአድዋ ከተማ ደግሞ ዛሬ ከሰዓት በፊት ኤሌክትሪክ እንዳገኘ መግለፃችን ይታወሳል።ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የቆየው የአክሱምና ሽሬ ከተሞችና አካባቢያቸው የኤሌክትሪክ መስመር በመጠገኑ ማምሻውን ከተሞቹ የመብራት አገልገሎት አግኝተዋል።የሑመራ እና ወልቃይት ከተሞችና አካባቢያቸውን ኤሌክትሪክ ለማገናኘትም ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል።በዚህ አጋጣሚ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በመሆን የጥገና ስራውን በኃላፊነት ስሜት የተወጡ የተቋሙ ሠራተኞችን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ በተቋሙ ሥራ አመራርና ሰራተኞች ስም አመስግነዋል።

ጦርነት በተካሄደባቸው በትግራይ ክልል፣ ደቡባዊ ዞን፣ ጨርጨር ወረዳ በሚገኙት ኡላጋ እና ቢሶበር መንደሮች 31 ሲቪል ሰዎች ሞተዋል፣ 104 መኖሪያ ቤቶች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ተናገረ ።
ኮሚሽኑ ጦርነት በተካሄደባቸው የትግራይ ክልል እና አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው ሁኔታ፣ በቦታው ያሉ የሲቪል ሰዎች ደኅንነት እንዲሁም በጦርነቱ ምክንያት ከመኖሪያ ቦታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች በአሳሳቢና ወደ ሰብአዊ ቀውስ ሊያመራ በሚችል ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙም ተናግሯል።
ኮሚሽኑ ከታህሳስ 6 እስከ ታህሳስ 11፣2013 ዓ/ም በጎንደር እና በዳንሻ በመገኘት እንዲሁም፣ ከታኅሳስ 22 እስከ ታኅሳስ27፣2013 ዓ/ም ድረስ ደግሞ በትግራይ ክልል፣ ደቡባዊ ዞን፣ ጨርጨር ወረዳ በሚገኙት ኡላጋ እና ቢሶበር መንደሮች በመጓዝ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት እንዲሁም ተጎጂዎችና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር ያደረገውን የክትትል ሪፖርት ይፋ አድርጓል።
የአሁኑ ክትትል በዋነኛነት በተካሄደባቸው በዳንሻ፣ በሁመራ፣ በቢሶበር እና በኡላጋ ጦርነቱ የሲቪል ሰዎችን ሞትና አካላዊ ጉዳት አስከትሏል፣ የሲቪል ሰዎችን መኖሪያና የንግድ ቦታዎች ለዝርፊያና ለተለያዩ ጉዳቶች አጋልጧል እንዲሁም በመሰረተ ልማቶች ላይ የደረሰው ውድመትና የኤሌክትሪክ እና የውሃ የመሳሰሉ አገልግሎቶች አለመመለስ፣ በአካባቢዎቹ ነዋሪዎች እና በተፈናቃናዮች ላይ የበለጠ ሰብአዊ ቀውስ እንዳያስከትል የሚያሰጋ ነው ብሏል የኮሚሽኑ መግለጫ።
በቢሶበር እና በኡላጋ 31 ሲቪል ሰዎች ሞተዋል፣ 104 መኖሪያ ቤቶች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል31 ሲቪል ሰዎች ሞተዋል፣ 104 መኖሪያ ቤቶች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል እንዲሁም የአካባቢው ትምህርት ቤትና ጤና ጣቢያ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል።
በተመሳሳይ መልኩ በሁመራ እና በዳንሻ የሲቪል ሰዎች ንብረት የሆኑ መኖሪያ እና ንግድ ቤቶችን ጨምሮ የአካባቢው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ውድመት እና ዝርፊያ ደርሷል። ሲቪል ሰዎች በብሔራቸው ምክንያት ወይም በአካባቢዎቹ የፀጥታ መጓደል ምክንያት ለደኅንነታቸው እንደሚሰጉ ነግረውኛል ብሏል።
በአጠቃላይ በነዚህ 4 ከተሞች ያለው የፀጥታ ስጋትና የፍትሕ አካላት ወደ መደበኛ ስራቸው አለመመለስ፣ የሰዎችን ደኅንነት ለማስጠበቅና የሰብአዊ መብቶቻቸውን ጥበቃ ለማረጋገጥ አዳጋች አንዳደረገው ተናግሯል።
የኮሚሽኑ ምርመራ ቡድን የጎበኟቸው ተጎጂዎች በአብዛኛው በአካባቢው ነዋሪዎች ብቻ እርዳታ የተደረገላቸው አልያም አንድ ዙር ብቻ እርዳታ የተደረገላቸው መሆኑን በሪፖርቱ እንደተመለከተ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ(ዶ/ር) ተናግረው “በአካባቢዎቹና በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰው ጉዳት የሁሉንም የሚመለከታቸውን አካላት ከፍተኛና አፋጣኝ ርብርብ የሚጠይቅ ነው” ማለታቸው ተሰምቷል። በተጨማሪም የኮሚሽኑ ባለሞያዎች ከጥር 2፣ 2013 ዓ/ም ጀምሮ ለተጨማሪ ዙር የመስክ ምልከታ ወደ መቀሌ ከተማ እና ሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች በመንቀሳቀስ፣ በግጭቱ ምክንያት የተፈጠረውን የሰብአዊ ቀውስ እና የሰብአዊ መብት ጉዳዮች በመመርመር ላይ የሚገኝ ሲሆን ስራው እንደተጠናቀቀ ተጨማሪ ሪፖርቱን ይፋ የሚደረግ መሆኑን ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ ተናግሯል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህብረተሰቡን ጥቆማ መነሻ አድርጎ ባደረገው ጥናት በጥምቀት በዓል ላይ ወንጀል ለመፈፀም ተዘጋጅተው የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ከህብረተሰቡ የመጣውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ባደረገው ጥናት፣ የማስረጃ ማሰባሰብና የቁጥጥር ተግባራት በቀጥታ በወንጀል ተሳታፊ የሆኑ 205 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ቀደም ሲል በደረሱት ጥቆማዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ለወንጀል ድርጊት ያዘጋጁት ሰነድ አልባ ሦስት ተሽከርካሪዎችም ተይዘዋል፤ ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይም የምርመራ መዝገብ በማደራጀት ወደ ስራ ገብቷል፡፡
በተመሳሳይ ኮሚሽኑ በአስሩም ክ/ከተማ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማና ይህንንም ጥቆማ መሰረት አድርጎ ባደረገው የቁጥጥር ተግባራት በዓሉ በሠላም እንዳይከበርና ሁከት እንዲነሳ ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩ ከሦስት መቶ በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል፡፡ግለሰቦቹ ለወንጀል መፈፀሚያነት የሚያገለግሉ የተለያዩ ድምጽ አልባ መሳሪያዎችን ጨምሮ ህገ ወጥና ፈቃድ የሌለው ሽጉጥም ይዘው ተገኝተዋል፡፡
መላው የከተማዋ ነዋሪዎች የሠላም ጉዳይ የፖሊስ ስራ ብቻ ሳይሆን የእኛ ነው በማለት ላደረጋችሁት አጋርነት ኮሚሽኑ ልባዊ ምስጋናውን እያቀረበ አሁንም የሚኖራችሁን ማንኛውንም ጥቆማ በኮሚሽኑ የነፃ ስልክ መስመር 991 እንዲሁም በ0111 11 01 11 በመደወል ማድረስ እንደምትችሉ አሳውቋል፡፡
[የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን]

የማእከላዊ ስታቲክስ ኤጀንሲ አሃዛዊ ቁጥሮችን የማረጋገጥ ሥራ ሊሰራ ነው!
የማእከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ በአገራችን የሚታዩትን የቁጥሮች መዛበትን ለማስተካከል በማሰብ ማስከላዊነቱን በጠበቀ መልኩ ከመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች የሚወጡ ቁጥሮችን ትክክለኛነት ማረጋጋጥ የሚያስችን ሥራ ሊሰራ እነደሆነ ተነገረ።
የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እንዳሉት በአገራችን የሚታየውን ከፍተኛ የሆነ የቁጥሮች እና መረጃዎች ፍልሰት (መዛባት)ን ለማስተካልል ይረዳ ዘንድ ከመንግሥት ተቋማት የሚወጡ ቁጥርችን የማረጋገጥ ሥራ ለመሥራት ተጠሪ ተቋሙ በሆነው በማእከላዊ ስታቲክስ ኤጀንሲ አማካኝነት የ(quality assurance) ሥራ ሊሰራ እነደሆነ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋዋል።