YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢፌዴሪ መከላከያ ያሰለጥናቸውን ወታደሮች ዛሬ ያስመርቃል::

የኢፌዴሪ መከላከያ ህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በመመልመል ሲያሰለጥናቸው የቆየውን ምልምል ወታደሮቾ በዛሬው ዕለት ያስመርቃል።ሰራዊቱን የተቀላቀሉ እና መስፈርቱን ያሟሉ ተመራቂ ምልምል ወታደሮች፣ ሁርሶ ጦላይና ብርሸለቆ በሚገኙ የወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ስልጠናቸውን አጠናቀው በየማሰልጠኛ ማዕከሉ በዛሬው ዕለት ይመረቃሉ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትም ለተመራቂ ምልምል ወታደሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በምሥራቅ ወለጋ ዜጎች መንግሥት ከለላ እያደረገልን አይደለም አሉ!

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ውስጥ በሚገኑት በሆሮ ጉድሩ ወላጋ፣ ሊመ ገሊላና ኪረሙ ወረዳ የሚኖሩ ዜጎች መንግሥት ደህንነታችንን ከማስጠበቅ ይልቅ ለሚደርስብን ችግር ተባባሪ ሆኖብናል ሲሉ ቅሬታቸውን ገለጹ።

በምስራቅ ወለጋ በተደጋጋሚ በሚደርሱ የጸጥታ ችግሮች እየተንገላታን ነው የሚሉት የአካባቢው ኗሪዎች በተደጋጋሚ ችግር የማያጣቸው ሆሮ ጉድሩና ሊሙ ገሊላ ውስጥ ያሉ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች የችግሩ ተባባሪ በመሆን ችግሩ መፍትሔ እንዳያገኝ እንቅፋት መሆናቸውን ተናግረዋል። የአዲስ ማለዳ ምንጮች እንደገለጹት በአካባቢው የሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን የወረዳና የቀበሌ አመራሮች ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገው ለበላይ አካላት መረጃ እንደሚሰጡ አረጋግጠናል ብለዋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ16 ሰዓታት ውሃ እንደሚያቀርብ አስታወቀ።

በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የውሃ አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወ/ሮ ሰርካለም ንጉሴ እንደተናገሩት ከሆነ በበዓል ሰሞን ከፍተኛ የሆነ የውሃ ፍጆታ ስለሚኖር ሙሉ በሙሉ ሳይቋረጥ ማድረስ ቢከብድም ለ10 ሰዓታት ያገኙ የነበሩ አካባቢዎች ወደ 16 ሰዓት ከፍ እንዲል በማድረግ ተጠቃሚነታቸው ሊጨምር ይችላል ብለዋል፡፡ከዚህ ቀደም ሲልም ሆነ በአሁኑ ወቅት እንደሚስተዋለው የመብራት ሃይል መቆራረጥ ስራቸዉን ከባድ ሲያድርገው እንደነበረ ገልወጸዉ፣ አሁንም ለዚህ መፍትሄ ካልተገኘ ችግሩ ሊቀጥል ይችላል ብለዋል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የዲግሪ ምሩቃኑ መንትዮች ዛሬ በውትድርና ተመረቁ!

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፀጥታ ችግር ያሳለፉትን ጊዜ ማየታቸው ወታደር ለመሆን እንዳስወሰናቸው ገልጸዋል፡፡መንትዮቹ ኢትዮጵያውያን የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ነው መከላከያን የተቀላቀሉት፡፡

https://am.al-ain.com/article/two-university-graduate-ethiopian-twins-today-graduated-from-the-military-training-center

@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ.ም በአማራ ክልል የተሰጠዉ የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 96 ነጥብ 85 በመቶ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ተዛውረዋል፡፡ለተመዘገበው የተሻለ ውጤት ተማሪዎች ፣ ወላጆች እና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው ብሏል ቢሮው፡፡የፈተናዉ ውጤት ማለፊያ ነጥቡን በተመለከተ ለሁሉም ዞንና ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያዎች ተላልፏል፤ ተማሪዎችም በየትምህርት ቤታቸው ውጤታቸውን በማየት የ9ኛ ክፍል ምዝገባ ከታኅሣሥ 30/2013ዓ.ም ጀምሮ ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ እንዲያካሂዱም አሳስቧል፡፡ተማሪዎቹ ከጥር 4/2013 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ ለየዞኖቹ ትምህርት መምሪያዎቹ ቀድሞ መርኃ ግብር መላኩን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙላው አበበ ለአብመድ ገልፀዋል፡፡ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከታኅሣሥ 12 -14/2013 ዓ.ም ድረስ በ5 ሽህ 162 የፈተና ጣቢያዎች ተሰጥቷል፡፡ የመደበኛ፣ የማታ እና የግል ተፈታኞችን ጨምሮ ከ400 ሽህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደወሰዱ ተገልጿል፡፡

[AMMA]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ.ም በክልሉ የተሰጠው የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ የሆነ ሲሆን ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 93 በመቶዎቹ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ተዘዋውረዋል፡፡

በክልሉ በአጠቃላይ 446 ሺህ 907 ተማሪዎች ፈተና የተቀመጡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 417 ሺህ 411 ወይም 93 ነጥብ 4 በመቶ ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡ቢሮው ከአንድ ሳምንት በኋላ የ9ኛ ክፍል ትምህርት በኦሮሚያ ክልል ይጀመራልም ብሏል፡፡ከአጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 29 ሺህ 96 ተማሪዎች ወይም 6 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑት ወደ ቀጣይ ክፍል አለመዘዋወራቸው ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን ምርጫ ቦርድን ዋሽቶኛል ሲል ከሰሰ!

የእነ አቶ ዳውድ ኢብሳ ቡድን የሆነው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ምርጫ ቦርድ እንደዋሸው እና የወሰነውን ውሳኔ እንደማይቀበለው አስታወቀ።በኦነግ ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ተከትሎ ምርጫ ቦርድ የአመራሮቹን ልዩነት ለመፍታትና የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ኹለቱም ቡድን የተካተቱበት ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱ ባሳለፍነው ታኅሳስ 9/2013 መወሰኑ ይታወሳል። ውሳኔውን የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን እንደማይቀበለው አስታውቋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የወባ በሽታን በፈረንጆቹ በ2030 ድረስ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ብሔራዊ ወባን የማጥፋት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ እንቅስቀሴ እየተደረገ መሆኑን ተገለፀ።

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ባለፉት ዓመታት የወባ በሽታን መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ በሀገራችን አመርቂ ውጤቶች የተመዘገበ መሆኑን ጠቅሰዋል።በአሁኑ ወቅት ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሽታውን ለማጥፋት የሚደረገዉ እንቅስቃሴ አካል በመሆን የወባ በሽታን እ.ኤ.አ በ2030 ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ብሔራዊ ወባን የማጥፋት ፍኖተካርታ ተዘጋጅቶ በስድስት ክልሎች፣ 12 ዞኖችና 239 ወረዳዎች ወደ ስራ መግባትቱንና እንቅስቀሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የታችኛው ተፋሰስ አገራት በሕዳሴ ግድብ ላይ የሚያሳዩት የእግር መጎተት ግድቡ ስለሚጎዳቸው ሳይሆን ግድቡን የማስተጓጎል ወይም የማስቆም ዓላማ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በተያዘው ሳምንት የኢትዮጵያን የሕግ ማስከበር ተልዕኮ ተከትሎ የሚናፈሱ የተሳሳቱ ትርክቶች እንዲታረሙ ለአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት የማስረዳት የዲፕሎማሲ ስራዎች መከናወናቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሳምንቱን አበይት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የዲፕሎማቲክ ክንውኖች አስመልክተው ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ከአንድ ወር መቋረጥ በኋላ ባለፈው እሁድ በሶስቱ አገራት የውጭና የውሃ ሚኒስትሮች አማካኝነት ዳግም መጀመሩን ከሳምንቱ አበይት ዲፕሎማሲያዊ ክንውኖች ጠቅሰውታል።በድርድሩ በደቡብ አፍሪካ አስተባባሪነት በአፍሪካ ኅብረት በተሰየሙ የባለሙያዎች ቡድን የቀረበውን የድርድር ሰነድ ኢትዮጵያና ሱዳን ሲቀበሉት ግብፅ እንዳልተቀበለችው ተናግረዋል።እስካሁን በሶስትዮሽ ድርድሩ በተደረጉ ስምምነቶች ልዩነትና አንድነቶች በባለሙያዎች እንዲቀርቡ ስምምነት መደረሱን ገልፀው፤ ዳሩ ግን የባለሙያዎቹ ቡድን ትናንት ሊያደርገው የነበረው ውይይት የሱዳን ተሳታፊዎች ባለመታደማቸው አለመካሄዱን ገልጸዋል።

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
የሮይተርስ ባልደረባ ኩመራ ገመቹ ከእስር ተፈታ!

የሮይተርስ የምስል ቀረጻ ባለሙያ የሆነው ኩመራ ገመቹ ዛሬ ጠዋት ከእስር ተፈቷል።ኩመራ ታህሳስ 4፣2013 ላይ ፖሊሶች አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ታስሮ እንደሄደ እና ዛሬ ጠዋት ከእስር መፈታቱን ጠበቃው ለአዲስ ዘይቤ ገልጿል።የእስሩ መንሰኤ ምን እንደሆነ እንካሁን ባይታወቅም እስከዛሬ ድረስ ያለምንም ክስ ታስሮ እንደቆየ ሮይተርስ እና የኩመራ ጠበቃ ገልጿዋል።የ40 አመቱ የሮይተርስ የምስል ቀረጻ ባለሙያ በ10 የፖሊስ አባላት በቤተሰቡ ፊት ታስሮ እንደተወሰደ እና ፍርድ ቤት ቀርቦ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ እንደተፈቀደ ይታወሳል።

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ባልደራስ ያቀደዉን ሰላማዊ ሰልፍ ለጥር 23 አዛወረ!

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ጠርቶት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ።ሰላማዊ ሱልፉ የተደረገበት ቀን የከተራ ቀን ዋዜማ በመሆኑ በርካታ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ነዋሪዎች ጥሪ የተደረገበት ቀን እንዲቀየር በሰጡት አስተያየት መሰረት እንዲሁም ሰልፉ አለማቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው ከሀገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን በጉዳዩ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቀኑን መቀየር አስፈላጊ ሆኗል ብሏል።በዚህ መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ በሁለት ሳምንት ተራዝሞ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ መወሰኑን ገልጿል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት መድረሱን ለመቃወል፣ የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ሉአላዊ ግዛት ጥሶ መግባቱን፣ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ ስለሚገነባቸው ግንባታዎች እና የፓርቲው አመራሮችን እስር እና በፍጥነት ፍትሕ አለማግኘትን ለመቃወም በጥምቀት ከተራ በዓል ዋዜማ ጥር ዘጠኝ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ ነበር።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የገና ሥጦታ ሎተሪ ወጥቷል!!!

የገና ሥጦታ ሎተሪ ማክሰኞ ታህሳስ 27/ 2013 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡

ዛሬ የወጣው የገና ሥጦታ ሎተሪ ማውጫ ከላይ ተቀምጧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኤርትራ ውጭ ጉ/ሚንስትር እና የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አማካሪ የተካተቱበት የሀገሪቱ ልዑክ ዛሬ በካርቱም ጉብኝት አደረገ!

የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌ እና የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ አማካሪ የማነ ገብረአብ የተካተቱበት የሀገሪቱ ልዑክ አባላት ዛሬ በካርቱም ጉብኝት አድርጐ ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ም/ቤት ሊቀመንበር አልቡርሃን ጋር ተወያይተዋል።ሁለቱ አካላት በሁለትዮሽ እና በቀጣናዊ ሰላምና ደህንነት ዙሪያ መወያየታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚ/ር የማነ ገ/መስቀል በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል።ለነጻነት ቀናቸው እና ለአዲስ ዓመት ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ የተላከ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም ለአልቡርሃን አድርሰዋል።

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
TOP book series 📚ቶፕ የተማሪዎች አጋዥ መፅሀፍት

📌ከ 1-12 ክፍል በ ተለያዩ ቋንቋ የተዘጋጀ
📌በ ኦሮምኛ
📌በ አማርኛ
📌በ እንግሊዘኛ በሁሉም አይነት ትምህርት የተዘጋጀ
- maths chemistry biology physics ...
📌ለ 8 እና 12ኛ ክፍል ፈተና የሚያዘጋጁ
📌ለ ልጆችም 20 አይነት ተረት መጽሀፍት ታትሞዋል

❗️❗️በሁሉም መፅሀፍት ቤት ይጠይቁ
 
ዋና አከፋፋይ : ኤደን መጽሀፍት ቤት  
* * መገናኛ ሀይሌ ህንፅ ፊት ለ ፊት
📞 0911238057
0912732493

@TOPBOOkSERIES
Forwarded from YeneTube
🎓🌎✈️


📣Hope Travel Agents and Consultants📣

የውጭ ሀገር የትምህርት ዕድል ለማግኘት አቅድዋል ?
መልስዎ አዎ ከሆነ እና ህልሞን ለማሳካት የሚሹ ከሆነ HOPE የትምህርት ጉዳዮች አማካሪ የእርስዎን ህልም ለማሳካት ከጎናችሁ ነው ።

መሀል አውሮፓ አንቱታን ባተረፋ ዩኒቨርሲቲዎች በመማር አለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው ትምህርት ከ ዕውቀት ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት ከፈለጉ መፍትሄው እኛ ጋር አለ።

የብዙዎችን ህልም ዕውን አድርገናል እርሰዎም መተው ይቀላቀሉን።

አድራሻ

☎️+48 739667468
@Dagides

https://tttttt.me/studymeeurope - join our channel
Forwarded from Nadi market™️ (BT)
🏷CHEKICH
🏷TURKEY
🏷Size: 41 42 43 44
🏷️Price: 2700 ETB
🏷Free Delivery
🏷contact @babeyos
🏷call +251955352406
📞+251904180418
BABYO BRAND|always unique
ንብረት የወደመባቸው የሻሸመኔ ነዋሪዎች የግብር እፎይታ አልተሰጠንም አሉ!

በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠሩ ግጭቶች አማካኝነት ንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ነጋዴዎች የግብር እፎይታ ይሰጣቸዋል ተብለው ቃል የተገባላቸው ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን ግብር ካልከፈላችሁ ንግድ ፍቃድ ማደስም ሆነ ‹‹ክሊራንስ›› መውሰድ አትችሉም እየተባሉ እንደሆነ ሻሸመኔ የሚገኙ ጉዳት የደረሰባቸው ነጋዴዎች ለአዲስ ማለዳ አስረድተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሐምሌ ወር ጀምሮ በተፈጸሙ ጥቃቶች ለደኅንነታቸው በመስጋት ቤት ንብረታቸውን ጥለው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 100 ሺህ መድረሱን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

የቤንሻንጉል ከልል አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ታሲሳ እንዳሉት በቅርቡ በቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ከተፈጸመውና ጥቃት በኋላ ቀያቸውን ጥለው የሸሹትን ጨምሮ 100 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን አረጋግጠዋል።በክልሉ መተከል ዞን አምስት ወረዳዎች ከሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም ወዲህ ዳግም መፈናቀል መከሰቱን የተናገሩት አቶ ታረቀኝ፤ እነሱም ማንኩሽ፣ ድባጢ፣ ቡለን፣ ወንበራ እና ማንዱራ ወረዳዎች መሆናቸውን አመልክተዋል።በዳንጉራ፣ በኩጂ እና አዲስ ዓለም ወረዳዎች ተፈናቃዮች መኖራቸውን የተናገሩት ኃላፊው፤ ከእነዚህ መካከል ስድስ ሺህ የሚሆኑት ጉባ የሚባል አካባቢ፣ 6 ሺህ 800 የሚሆኑት ደግሞ ወንበራ፣ ማንዱራ 12 ሺህ፣ በድባጤ 14 ሺህ፣ በቡለን ደግሞ 51 ሺህ የሚጠጉ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ አብራርተዋል።

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ታኅሳስ 13/2013 ዓ. ም ንጋት ላይ በታጣቂዎች በተጸፈመ ጥቃት 207 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን በወቅቱ የአካባቢው ባለስልጣን ለቢቢሲ አረጋግጠው ነበር።የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም በጥቃቱ ስለተገደሉት ሰዎች ዝርዝር ሲገልጽ ከሟቾቹ መካከል አዋቂዎቹ 133 ወንዶችና 35 ሴቶች ሲሆኑ፤ አንድ የስድስት ወር ሕጻንን ጨምሮ 17 ሕጻናት ተገድለዋል ብሎ ነበር።አክሎም የቀሩት 20 ሰዎች ደግሞ አዛውንቶች መሆናቸው ገልጾ ነበር።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው መልዕክት አስተላልፈዋል

የገና በዓልን በማስመልከት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ የዘንድሮው በዓል ህገወጡ እና ጁንታው ሀይል የተወገደበት፣ የትግራይም ሆነ መላው የሀገራችን ህዝቦች ነጻ የወጡበት ወቅት በመሆኑ በዓሉን የተለየ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የራያ ዩኒቨርስቲ ጥር 15 እና 16 ቀን 2013 ዓ.ም የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ያካሂዳል፡፡ ስለሆነም ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ተገኝታሁ ምዝገባ እንድታካሂዱ እያሳሰበ መደበኛ ትምህርት የሚጀመረው ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ተገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa