YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በዘረፋ ወንጀል የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር አዲስ ቅዳም ከተማ በትላንትናው ዕለት ለእቁብ የተሰበሰበን አንድ ሚሊዮን ሰባ ሶስት ሽህ ብር ወደ አባይ ባንክ ለማስገባት ሲወስዱ በነበሩ ሰዎች ላይ በተተኮሰ ጥይት የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል።

ጥይቱ የተተኮሰው የባንክ ሰራተኛውንና የተከተለውን የጥበቃ ሰራተኛ ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ዘራፊዎቹ ብሩን ይዘው መሰወራቸው ነው የተነገረው።ለዘረፋ የተጠቀሙባትን መኪና ጥለው የጠፉ ዘራፊዎችን ለመያዝ የፀጥታ አካሉ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ የፋግታ ወረዳ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
የገቢዎች ሚኒስቴር በወላይታ ሶዶ ከተማ በመርካቶ የገበያ ማዕከል በእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ከ40 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ድጋፉን ለወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ለዶክተር እንድሪያስ ጌታ አስረክበዋል፡፡ድጋፉ የምግብ ዘይት፣ ስኳር አልባሳት እና መሠል ቁሳቁስን እንደሚያካትት ከደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
በቅርቡ የንግድ ስሙን ከ ኢን ኤንድ አውት በርገር (In-N-Out Burger) ወደ ኢን ጆይ በርገር የቀየረው የፈጣን ምግብ አቅራቢ የአሜሪካው In-N-Out Burger በከፈተበት ክስ ተረታ፡፡

ሁለቱ ድርጅቶች በንግድ ምልክት ያለአግባብ በመጠቀም ላለፉት 6 አመታት ሲነታረኩ ቆይተው ነበር፡፡ባሳለፍነው ሃሙስ ጉዳዩን ሲመለከት የነበረው የፌደራል ፍርድ ቤት ልደታ ሰሚ ችሎት በቅርቡ ስሙን ወደ ኢን ጆይ በቀየረው ፈጣን ምግብ ድርጅት ላይ ስምን ያለአግባብ የመጠቀም የጥፋተኝነት ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን፡፡ ድርጅቱም ከአሁን በኋላ ስሙን እንዳይጠቀም በይኗል፡፡በተጨማሪም ድርጅቱ ያላግባብ In-N-Out Burger የሚለውን ስም ተጠቅሞ ለአመታት በመስራቱ የ 150 ሺ ብር ካሳ ለአሜሪካው ድርጅት እንዲከፍል ውሳኔ አሳፏል፡፡

የኢን ጆይ ጠበቃ አቶ ሞላልኝ መለሰ ለካፒታል የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደሚቃወሙ ተናግረው፡ ይግባኝ እንላለን ብለዋል፡፡አቶ ሞላልኝ እንዳሉት የአሜሪካው ድርጅት የንግድ ምልክት ያለአግባብ ጥቅም ላይ ውሎብኛል እንጂ ብሎ የከሰሰው በንግድ ስያሜ አደለም ብለዋል፡፡

“እኛ የንግድ ስያሜያችንን ከንግድ ሚኒስቴር በተሰጠ ፈቃድ In-N-Out Burger ብለን ሰየምን እንጂ የንግድ ምልክታችን In-N-Out Burger አይደለም ሆኖም ፍርድ ቤቱ ከሳሽ ባልከሰሰበት ነው የፈረደብን በመሆኑም አቤት እንላለን፣” ብለው አክለዋል፡፡የአሜሪካው In-N-Out Burger የንግድ ምልክቱን በአምሯዊ ፅህፈት ቤት የንግድ ምልክቱን ከእ.ኤ.አ 2011 አንስቶ ያስመዘገ ሲሆን፤ እ.ኤ.አ በ1948 በካሊፎርንያ የተመሰረተ ድርጅት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊው ድርጅት ደግሞ ላለፉት 10 አመታት በፈጣን ምግቦች ማቅረብ በመሰማራት ቅርንጫፎቹንም በማስፋት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡

[Capital]
@YeneTube
ምርጫ ቦርድ በምርጫ ሂደት የኮሮናቫይረስ ለመከላከል ያወጣውን መመሪያ ለሕዝብ አስተያየት ክፍት ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀጣዩን ስድስተኛ ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የተለያዩ መመሪያዎችን እያፀደቀ ነው፡፡ከእነዚህ የምርጫ መመሪያዎች አንዱ የሆነውን በምርጫ ሂደት ወቅት የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ አውጥቶ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የሕዝብ አስተያየት ክፍት ማድረጉን አስታውቋል፡፡ የረቂቅ መመሪያው ዋና ዓላማ በቅድመ ምርጫ፣ በድምፅ መስጫ ቀን እና በድህረ ምርጫ ወቅት ከምርጫ ጋር ተያያዥ ተግባራት ሁሉ የቫይረሱን ስርጭት እንዳይጨምር ማድረግ ነው ተብሏል፡፡ረቂቅ መመሪያው ለቦርዱ፣ ለምርጫ ባለድርሻ አካላት እና አስፈፃሚዎች ኮሮናቫይረስን ለመከላከል ያስፈልጋሉ በሚባሉ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ረቂቅ መመሪያውን ከሕዝብ በሚሰበሰብ ገንቢ አስተያየት ለማዳበር ይረዳ ዘንድ ለአንድ ሳምንት ለሚቆይ ጊዜ ክፍት ተደርጓል፡፡ረቂቅ መመሪያው ከዛሬ ጀምሮ ለሕዝብ አስተያየት ክፍት መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በረቂቁ ዙሪያ ለሚኖር ሀሳብና አስተያየት በኢሜል አድራሻ legal@nebe.org እንዲሁም በቦርዱ ገጽ መልዕክት ማስቀመጫ አማካኝነት መላክ እንደሚቻል አስታውቋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ:- ረቂቅ መመሪያውን ለማግኘት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም መጫን ይቻላል፡፡
https://bit.ly/3ofdkAn

@YeneTube @FikerAssefa
ከፍተኛ ገንዘብ በመቀበል በህገወጥ መንገድ ወደ ውጪ ሀገር ሲልኩ የነበሩ የኢምግሬሽን አመራሮችና ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

ህጋዊውን መንገድ ማሟላት ካልቻሉ ዜጎች ከፍተኛ ገንዘብ በመቀበል በህገወጥ መንገድ ወደ ውጪ ሀገር ሲልኩ የነበሩ የኢምግሬሽን አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም በህጋዊ አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ስም የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለኢቲቪ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅርንጫፍ የሚሰሩ አመራሮችና ሰራተኞች በህጋዊ መንገድ ሰዎችን ወደ ውጪ ሀገር ለመላክ ከተቋቋሙ አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር የጥቅም ትስስር በመፍጠርና በመመሳጠር ህጋዊ ሂደቶችን ያላሟሉና ከሀገር መውጣት የማይገባቸውን ግለሰቦች በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሲያስወጡ ነበር፡፡

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ቡድን ጋር ባደረጉት የተቀናጀ ክትትልም በህገወጥ ድርጊቱ ሲሳተፉ እንደነበር የተጠረጠሩ 21 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርገዋል፡፡የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መግለጫ እንዳብራራው፤ በአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ስም ተደራጅተው በዚህ ተግባር የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ህጋዊ መንገዱን አሟልተው ከሀገር መውጣት ካልቻሉ ዜጎች ከፍተኛ ገንዘብ በመቀበል ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ከሚሰሩና በጥቅም ከተሳሰሯቸው አመራሮችና ሰራተኞች ጋር በመከፋፈል ሰዎች በህገወጥ መንገድ ከሀገር እንዲወጡ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በሶስት ተጠርጣሪ የኢምግሬሽን ባለሙያዎች ቤት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻም ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ እንዲሁም የተለያዩ የባንክ ደብተሮችና ሰነዶች መገኘታቸውን ያመለከተው መግለጫው፤ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ከተጠረጠሩ ሶስት በአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ስም ከሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ቤትም የሌሎች ሰዎች ሰባት ፓስፖርቶች ተይዘዋል፡፡በአጠቃላይ በተጠርጣሪዎች ቤት በተደረገ ፍተሻ 37 የባንክ ደብተሮችና ለህገ ወጥ ስራቸው የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ ቁሳቁስ የተገኙ ሲሆን፤ ተጨማሪ የማጣራት ስራዎችም እየተከናወኑ ነው፡፡

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት ሊያካሂዱት ታስቦ የነበረው የበይነ-መረብ ስብሰባ ሱዳን ባለመገኘቷ ምክንያት ሳይካሄድ መቅረቱ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት ሊያካሂዱት ታስቦ የነበረው የበይነ-መረብ ስብሰባ ሱዳን ባለመገኘቷ ምክንያት ሳይካሄድ መቅረቱን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።ሚኒስቴሩ የሕዳሴው ግድብ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የዕለቱ ሰብሳቢ የሆነችው ኢትዮጵያ ባስተላለፈችው ጥሪ መሰረት የግብጽ ልዑክ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች እና ታዛቢዎች መገኘታቸውን ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰየማቸው ባለሙያዎች ባዘጋጁት ሰነድ ላይ ያሏትን የልዩነት ሃሳቦች ለአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክርቤት ሊቀመንበር በማሳወቅ ሰነዱን ለሶስትዮሽ ድርድር እንደግብዓት ለመጠቀም መስማማቷን ያስታወሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ ሆኖም የልዩነት እና አንድነት ሃሳቦችን ለማጠናቀር የታሰበው የዛሬው ስብሰባ በሱዳን አለመገኘት ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል ብሏል፡፡ይኸው ለአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክርቤት ሊቀመንበር በኢትዮጵያ በኩል መገለጹንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ከነበሩ 269 አንቡላንስ በአሁኑ ጊዜ 31 አንድ ብቻ እንዳሉ የግዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሃላፊ ሃላፊ አቶ ገብረመስቀል ገለፁ። ህውሃት የአንቡላንሶቹ ሳይረን በመንቀል ለውግያ እንደተጠቀመባቸው ይታወቃል፤ 235 አንቡላንሶች የተወሰኑት በውግያው ተሳትፈው ተቃጥለዋል የተወሰኑ ተዘርፈዋል የቀሩትም የት እንዳሉ አይታወቅም።

[አማን ሚካኤል መስፍን]
@YeneTube @FikerAssefa
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የእገታ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ፡፡

በዞኑ ጣቁሳ ወረዳ ሮቢት ቀበሌ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 11፡30 አንደበት አዘነው የተባለውን ተከሳሽ ለጊዜው በቁጥጥር ስር ካልዋለው ግብር አበሩ ጋር በመሆን መንገድ ዘግቶ በተሸከርካሪ ይጓዙ ከነበሩ ሶስት ግለሰቦች መካከል አንዱን በማገት እንድ ሚሊዮን ብር ጥይቋል፡፡

አጋቹ ግለሰብ በድርድር ሁለት መቶ ሽህ ብር ከታጋቹ ቤተሰቦች ከተቀበ በኋላ የታገተውን ግለሰብ ለቀውታል።ይህ መረጃ የደረሰው የጣቁሳ ወረዳ ፖሊስም ባደረገው ክትትል ወንጀል የፈፀመውን እንደበት አዘነውን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማጣራት መዝገቡን ለጣቁሳ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ልኳል፡፡መዝገቡን የተመለከተው የጣቁሳ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ አንደበት አዛነውን በ14 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

መረጃው የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ዋና ክፍል ነው፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን ለትግራይ ስደተኞች በገዳሪፍ ክፍለ ሀገር አልቲንደባ የተባለ አዲስ መጠለያ እንዳቃቋመች ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡ ባለሥልጣናቱ ሐሻባ እና ሐምዳይት ከተሰኙት የጠረፍ ጊዜያዊ መቀበያ ጣቢያዎች ወደ አዲሱ ጣቢያ ስደተኞችን ማጓጓዝ ጀምረዋል፡፡ አዲሱ መጠለያ ጣቢያ 30 ሺህ ስደተኞችን ማስተናገድ ይችላል ተብሏል፡፡ ኡም ራኩባ በተባለው ስደተኞች ጣቢያ ደሞ ኮሮና ቫይረስ እንደገባ ተሰምቷል፡፡

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም የላቀ ስኬት ባለቤት በመባል በቢዝነስ፣ በፖለቲካና በስነ ጥበብ መስኮች ድንቅ ውጤት ካስመዘገቡ 100 ተፅእኖ ፈጣሪ አፍሪካውያን መካከል አንዱ በመሆን ለሁለተኛ ጊዜ እውቅናን ተቀዳጅተዋል።

https://100.newafricanmagazine.com/#leaders

Via Ethiopian Airlines
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
TOP book series 📚ቶፕ የተማሪዎች አጋዥ መፅሀፍት

📌ከ 1-12 ክፍል በ ተለያዩ ቋንቋ የተዘጋጀ
📌በ ኦሮምኛ
📌በ አማርኛ
📌በ እንግሊዘኛ በሁሉም አይነት ትምህርት የተዘጋጀ
- maths chemistry biology physics ...
📌ለ 8 እና 12ኛ ክፍል ፈተና የሚያዘጋጁ
📌ለ ልጆችም 20 አይነት ተረት መጽሀፍት ታትሞዋል

❗️❗️በሁሉም መፅሀፍት ቤት ይጠይቁ
 
ዋና አከፋፋይ : ኤደን መጽሀፍት ቤት  
* * መገናኛ ሀይሌ ህንፅ ፊት ለ ፊት
📞 0911238057
0912732493

@TOPBOOkSERIES
Forwarded from YeneTube
🎓🌎✈️


📣Hope Travel Agents and Consultants📣

የውጭ ሀገር የትምህርት ዕድል ለማግኘት አቅድዋል ?
መልስዎ አዎ ከሆነ እና ህልሞን ለማሳካት የሚሹ ከሆነ HOPE የትምህርት ጉዳዮች አማካሪ የእርስዎን ህልም ለማሳካት ከጎናችሁ ነው ።

መሀል አውሮፓ አንቱታን ባተረፋ ዩኒቨርሲቲዎች በመማር አለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው ትምህርት ከ ዕውቀት ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት ከፈለጉ መፍትሄው እኛ ጋር አለ።

የብዙዎችን ህልም ዕውን አድርገናል እርሰዎም መተው ይቀላቀሉን።

አድራሻ

☎️+48 739667468
@Dagides

https://tttttt.me/studymeeurope - join our channel
Forwarded from Nadi market™️ (BT)
🏷CHEKICH
🏷TURKEY
🏷Size: 41 42 43 44
🏷️Price: 2700 ETB
🏷Free Delivery
🏷contact @babeyos
🏷call +251955352406
📞+251904180418
BABYO BRAND|always unique
በትግራይ ክልል ከውቅሮ ከተማ የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ወጣ ብሎ በሚገኘው ጥንታዊው የአል ነጃሺ መስጅድ እንዲሁም በአንድ ቤተክርስቲያን ላይ ጉዳት እንደደረሰ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በውቅሮ አል ነጃሺ መስጂድ እና በአማኑኤል ምንጉዋ ቤተክርስትያን ላይ ጉዳት መድረሱን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ጄይላን ከድር በመስጂዱ ላይ ስለደረሰው ጉዳት መረጃ እንዳልደረሳቸውና ከሁለት ቀናት በኋላ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ረዳት ፕሮፌሰር አበባው ለቢቢሲ እንደተናገሩት የአል ነጃሺ መስጂድ ጉዳት እንደደረሰበት መስማታቸውን ገልጸው፤ መስሪያ ቤታቸውም ወደ ሥፍራው የሚሄድ ሁለት የጥናት ቡድን እንዳዘጋጀ አመልክተዋል።ይህ የጥናት ቡድን ወደ ትግራይ ወደ ስፍራው የሚሄደው በዕምነት ቤቶቹ ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን አጣርቶ ለጥገና የሚሆን መረጃ ለማሰባሰብ እንደሆነ ገልፀዋል።የእስልምና ጉዳዮች ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአካባቢው ካሉ የሐይማኖት አባቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ ስላለው ሁኔታ ለማወቅ ባለመቻሉ ስለጉዳቱ ለማረጋገጥ እንዳልቻለ ዶ/ር ጄይላን ለቢቢሲ ገልፀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያን ከጂቡቲ የሚያገናኝ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ለመዘርጋት፣ ዓለም አቀፍ ጨረታ እንደሚወጣ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ። 

ሚኒስቴሩ ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ የጋዝ ማስተላለፊያ መስመሩ በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ለውጭ ገበያ ለማጓጓዝ የሚውል ነው።ሪፖርተር ያነጋገራቸው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ አቶ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)፣ የሚዘረጋው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ፣ በውጭ ኩባንያ የሚገነባ ቢሆንም ንብረትነቱም ሆነ የሚተዳደረው በመንግሥት እንደሚሆን ገልጸዋል። 

በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ በድሬዳዋ ለሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ በግብዓትነት ለመጠቀም ፕሮጀክት የተቀረፀ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ ያለውን የተፈጥሮ ጋዝ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ መታቀዱን ተናግረዋል።በዚህ ዕቅድ መሠረትም ፖሊጂሲኤል የተባለ የቻይና ኩባንያና ኒውኤጅ የተባለ ሌላ የእንግሊዝ ኩባንያ የተፈጥሮ ጋዙን የማልማት ሥራ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።የእንግሊዝ ኩባንያ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ከሚኒስትሩ የተገኘው መረጃ የሚያመለክት ሲሆን፣ የቻይናው ኩባንያ ፖሊጂሲኤል የተወሰነ መዘግየት እንደሚታይበት ጠቁመዋል።

[ሪፖርተር]
@YeneTube @FikerAssefa
ሱዳን በሕዳሴው ግድብ ሙሌትና ቀጣይ ሥራ ላይ ዛሬ [ሰኞ] በተካሄደው የሦስትዮሽ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ቅሬታ እንዳላት የሱዳን ዜና አገልግሎት ሱና የአገሪቱን መስኖና ውሃ ሀብት ሚኒስቴርን ጠቅሶ ዘግቧል።

እሁድ የተካሄደውን ውይይት መሰረት አድርጎ ከሚኒስቴሩ የወጣው መግለጫ እንዳለው ሱዳን በዚያው ዕለት ከአፍሪካ ሕብረት ባለሙያዎች ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባ ለማድረግ ብትጠይቅም ምላሽ ሳታገኝ የቀጥታ የሦስትዮሽ ድርድር ላይ እንድትሳተፍ ጥሪ ቀርቦላታል ብሏል።ይህም ሱዳን በተሳትፎዋ ላይ ያላትን ቅሬታ ይፋ እንድታደርግ እንዳደረጋት ያመለከተው መግለጫ "ሱዳን የአፍሪካ ሕብረት ባለሙያዎች ድርድሩን በማስተባበር በኩል ሰፋ ያለ ሚና እንዲሰጣቸው ያላትን ጽኑ አቋም ታረጋግጣለች" ሲል አጽንኦት መስጠቱን ሱና ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጡት ለማጥባት ምቹ የሆኑ ጤና ተቋማት ዕውቅና ተሰጣቸው!

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበረ ባለው ጤና ተቋማትን ለጡት ማጥባት ምቹ የማድረግ ኢንሼቲቭ ጥሩ አፈፃፀም ላሳዩ 14 የጤና ተቋማት ዕውቅና ተሰጥቷል።ዕዉቅና ከተሰጣቸው 14ተቋማት መካከል 5ቱ ከአፋር፣ 4ቱ ከሶማሌ፣ 3ቱ ከኦሮሚያ፣ 1ከአማራ እና 1ከደቡብ ክልል ናቸው።

[MoHE]
@YeneTube @FikerAssefa
የግብጽ የስለላ መሥሪያ ቤት ዳይሬክተር ወደ ኻርቱም ተጉዘው ከጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ፣ የሉዓላዊ ምክር ቤቱ ሊቃነ መናብርት እና የሱዳን አቻቸው ተወያይተዋል። በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ላይ ዛሬ ከተደረገው ድርድር ሱዳን መቅረቷ አይዘነጋም።ሜጀር ጄኔራል አባስ ካመል ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ተገናኝተዋል። ዳጋሎ እንዳሉት ውይይታቸው በሁለቱ አገሮች ግንኙነት ላይ ያተኮረ ነበር።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በኮንትሮባንድ ሲዘዋወር የነበረ 71 ካርቶን መድኃኒት እና 57 ካርቶን ሽቶ መያዙን ገለፀ።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው እፎይታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ገደማ ፖሊስ ፍተሻና ቁጥጥር በሚያደርግበት ወቅት ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ ጊዜያት በሀገር ክህደት ወንጀል ተጠርጥረው መያዣ ትዕዛዝ ከአወጣባቸዉ አመራሮችና የጦር መኮንኖች መካከል በቁጥጥር ስር በዋሉት ምርመራ እያካሄደባቸው መሆኑንና በየጥሻውና በየጉድጓዱ የተደበቁትንም በማደን ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

በዚህም እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ከፍተኛ መኮንኖች መካከል፡-

1. ሜ/ጀኔራል ገ/መድህን ፈቃዱ ሀይሉ
2. ሜ/ጀኔራል ይዳው ገ/መድህን
3. ብ/ጀኔራል ገ/ህይወት ሲስኖስ ገብሩ
4. ብ/ጄኔራል ኢንሱ እጃጆ እራሾ
5. ብ/ጄኔራል ፍስሃ ገ/ስላሴ
6. ኮ/ል ደሳለኝ አበበ ተስፋዬ
7. ኮ/ል እያሱ ነጋሽ ተሰማ
8. ኮ/ል መብራቱ ተድላ ወ/ሚካኤል
9. ኮ/ል ባራኪ ጠማሎው ገብሩ
10. ኮ/ል ሀይላይ መዝገብ ማሾ
11. ኮ/ል ፍሰኃ ግደይ ወ/ማርያም
12. ሌ/ኮ/ል ሙዘይ ተሰማ ስዩም
13. ሌ/ኮ/ል ፍሰሃ በየነ ገ/ኪዳን
14. ሌ/ኮ/ል ምሩጽ ወ/አረጋይ ገ/መስቀል
15. ሌ/ኮ/ል ምሩጽ በርሄ አበራ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸዉ ይገኛል፡፡

እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል፡-

1. ኮ/ል ተስፋዬ ገ/መድህን
2. ኮ/ል የማነ ገ/ሚካኤል
3. ሌ/ኮ/ል ሀዲሽ ገ/ጻዲቅ
4. ኮ/ል ማዕሾ
5. ኮ/ል አለም ገ/መድህን የተባሉት እንደሚገኙበት ተረጋግጧል፡፡

የኢፌዲሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
ታህሳስ 27/ 2013 ዓ/ም
አዲስ አበባ
@YeneTube @FikerAssefa