YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በመተከል ዞን በዜጎች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ከነበሩት ታጣቂዎች መካከል 17ቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል ተባለ!

በመተከል ዞን በዜጎች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ከነበሩት ታጣቂዎች መካከል 17ቱ በህዝቡ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀረ ሽምቅና ልዩ ጥበቃ አድማ ብተና መምሪያ አስታወቀ።ከታጣቂዎቹ ጋር ከ29 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የባለ 5፣ 10፣ 50፣ 100 የሞባይል ካርዶች፣ 290 ቀስቶች፣ መድሃኒቶችና ሌሎች ቁሳቁሶችም ተይዘዋል።

በአካባቢው ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተቋቋመው ግብረ ሃይል የጸጥታና ህግ የማስከበር ስራውን ተረክቦ የተጠናከረ እርምጃ እየወሰደ ነው ተብሏል።የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጸረ ሽምቅና ልዩ ጥበቃ አድማ ብተና መምሪያም ከተቋቋመው ግብረ ሃይል ጋር በመቀናጀት ወንጀለኞችን በማደን ላይ ይገኛል።የመምሪያው ዋና አዛዥ ኮማንደር ዶሳ ጎሹ ለኢዜአ እንዳሉት ክልሉ ከግብረ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት የታጠቁ ሃይሎችንና በግድያው እጃቸው ያለበትን ወንጀለኞች በህዝቡ ትብብር በቁጥጥር ስር እያዋልን ነው ብለዋል።በህግ ማስከበሩ በርካታ ሽፍቶች እጅ እየሰጡና በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን ኮማንደሩ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ 311 ሺህ 421 ተማሪዎች ተመዝግበዋል !

በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ለሚደረገው የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና 500 ሺ ታብሌቶች ተዘጋጅተዋል።

በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተፈታኞች ምዝገባና ውጤት ጥንቅር ዳይሬክተር አቶ ዩሴፍ አበራ እንደገለጹት፤ የአጠቃላይ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ ለመስጠት መርሐግብር ተይዟል።

በዚህ መሰረት የተማሪዎች ምዝገባ መደረጉን ገልጸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል።

ምዝገባው ከትግራይ ክልል እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን በስተቀር በሁሉ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካሄዱን ገልፀዋል።

በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ካጋጠመው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ተማሪዎችን ለመመዝገብ እንዳልተቻለ አመልክተዋል።

በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ቀደም ሲል ምዝገባ የተጀምረ ቢሆንም ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ መቋረጡን አስታውሰው፤ በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎችን ለመመዝገብ የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር እየተሠራ ይገኛልም ብለዋል።

በትግራይ ክልል 80 ያህል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በመተከል ደግሞ እስከ 14 ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሎ ይገመታል፣ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ምዝገባ ከተደረገ ቁጥሩ ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትጵያ፣ሱዳንና ግብፅ መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር ዛሬ እንደሚቀጥል የውኃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዛሬው ውይይት በግድቡ አጠቃላይ ሙሌት እና አመታዊ ክዋኔ ህጎች እና መመሪያዎች ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ሚኒስትሩ ዶ/ር ስለሺ በቀለ (ኢ/ር) የዛሬው ስብሰባ የተጠራው የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር በሆነቸው ደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኑነትና ትብብር ሚኒስትር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በውይይቱም የሦስቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይና የውኃ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል፡፡

ለአንድ ወር ተቋርጦ የነበረው ይኸው ድርድር ዛሬ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባሳለፍነው ማክሰኞ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡ ድርድሩ የቆመው በሀገራቱ የውስጥ ጉዳይና ሱዳን የድርድሩ አካሄድ (ሞዳሊቲ) ይቀየር የሚል ጥያቄ በማንሳቷ መሆኑንም ቃል አቀባዩ ገልጸው ነበር፡፡ ሱዳን ወደ ድርድሩ እንደምትመለስ በቅርቡ መግለጿን ተከትሎ የዛሬው ድርድር ሦስቱንም ሀገራት አሳትፎ ነው የሚካሔደው፡፡

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አሁን ላይ ግንባታው 78 በመቶ መድረሱን ዶ/ር ስለሺ በቀለ (ኢ/ር) በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

Al-ain
@YeneTube @FikerAssefa
እስራኤል በኮሮናቫይረስ ክትባት ዓለምን እየመራች ነው

ለዜጎቿ የኮሮናቫይረስ ክትባት በመስጠት እስራኤል ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች። ሀገሪቱ እስካሁን ከ9.2 ሚሊዮን ህዝቧ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑት ክትባቱን ሰጥታለች።

@Yenetube @Fikerassefa
በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 ዩቲዩብ ላይ በርካታ ተመልካቾች ያገኙ 10 ቪዲዮዎች ዝርዝር ይፋ ተደርጓል

በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 ዩቲዩብ ላይ በርካታ ተመልካቾች ያገኙ 10 ቪዲዮዎች ዝርዝር ይፋ ተደርጓል።

በዚህም 7.05 ቢሊዮን በላይ ተመልካች በማግኘት “ቤቢ ሻርክ ዳንስ” የተሰኘው የህፃናት መዝሙር #በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ዓመቱን ሙሉ ከ7 ቢሊዮን በላይ ተመልካቾች የነበረው “ዴስፓሲቶ” እና 5.05 ቢሊዮን በላይ ተመልካቾች የነበረው “ሼፕ ኦፍ ዩ” የተሰኙት የሙዚቃ ቪድዮዎች ደግሞ በ2ኛ እና በ3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

የአሜሪካ የቪዲዮ መጋሪያ መድረክ በሆነው ዩቲዩብ፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች የሠሯቸውን ቪዲዮዎች ለተመልካቾች ያጋራሉ፤ በርካቶቹም በቪዲዮዎቹ ገንዘብ ያገኙበታል።

ዩቲዩብ እ.አ.አ በ2005 ቻድ ሐርሌይ፣ ስቲቭ ቼን እና ጃውድ ከሪም በተባሉ ሦስት የፔይፓል የቀድሞ ሠራተኞች የተመሠረተ ሲሆን ጉግል ይህን መድረክ ከተመሰረተ ከአንድ ዓመት በኋላ በ2006 በ1.65 ቢሊዮን ዶላር ገዝቶታል።

ዩቲዩብ አሁን በጉግል ባለቤትነት ሥር ይገኛል።
@Yenetube @Fikerassefa
በሕዳሴው ግድብ ላይ የሚደረገው የሦስትዮሽ ውይይት ተጀመረ!

በሕዳሴው ግድብ ላይ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል የሚደረገው የሦስትዮሽ ውይይት ዛሬ ከሰዓት በኋላ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።ውይይቱ በግድቡ አጠቃላይ የዉሃ ሙሌት ዓመታዊ ክዋኔ ህጎች እና ደንቦች ላይ ያተኮረ መሆኑን የዉሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ መግለጻቸው ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ላለፉት ዘጠኝ ወራት አንድም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና አለማድረጉን አስታወቀ።

70 የኩላሊት ህመምተኞች የግድ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ቢሆንም ሆስፒታሉ ከዛሬ ነገ ስራ ይጀምራል እያሉ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ካደረገ 9 ወራት ማስቀጠሩ ተነግሯል።ለዚህም ምክንያቱ የኮሮና ቫይረስ መሆኑ ተገልጿል፡፡በሆስፒታሉ የንቅለ ተከላ ማዕከል የነርስ አስተባባሪ የሆኑት ሲስተር ሀይማኖት ሀብተማርያም በኮሮና ምክንያት ጉዞዎች ስለተሰረዙ መደረግ ያለባቸው ምርመራዎችን ውጪ አገራት ልከን ማስመርመር አልቻልንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ህይወት ለማዳን የመጣን ሰው ህመም ሰጥተን አንሸኝም ብለን ነገሮች እስኪስተካከሉ እየጠበቅን ነው ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡የኮሮና ዳፋ ህሙማኑን በዲያሌሲስ እንዲቆዩ ያስገደዳቸው ሲሆን ይሄም ለከፍተኛ ወጪ ይዳርጋቸዋል ብለዋል ሲስተር ሀይማኖት፡፡የኩላሊት ህመምተኞች በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ በበኩላቸው በኮሮና ምክንያት ከባድ ጊዜን እያሳለፍን ነው ብለዋል፡፡

ከዚህም በላይ ደግሞ የመድሀኒት ዋጋ መጨመር ሌላው ፈተናችን ነው ብለዋል።

'መቼ መፍትሄ ይሰጠዋል?' ሲባሉ ለተጠየቁት ጥያቄ ሲስተር ሀይማኖት ሳምፕል ልከን የምናስመረምርበትን ሆስፒታል መቀየርን አማራጭ አድርገን አይተናል በቅርቡም ከውሳኔ ላይ እንደርሳለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ሲቀበሉት ግብፅ ሳትቀበለው ቀርታለች!

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ ላይ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሰየሟቸው ባለሙያዎች ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ሲቀበሉት ግብፅ ሰነዱን ሳትቀበለው ቀርታለች።በዛሬው እለት የተካሄደውን የሦስትዮሽ ድርድር አስመልክቶ የተሰጠውን መግለጫ ከላይ አቅርበን ነበር።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
 ባዕድ ነገር ጨምረው እንጀራ በመጋገር በህገወጥ መንገድ የሚያከፋፈሉ ተጠርጣሪዎች በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።

ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በታቦር ክፍለ ከተማ ከወልደአማኑኤል ዱባለ አደባባይ አለፍ ብሎ በሚገኘው መንገድ 500 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ሙሉ ግቢ ተከራይተው ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የተገኙት ተጠርጣሪዎች ህብረተሰቡ ባደረገው ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ የገለፀው።

ፖሊስ ህገወጥ ተግባር በሚፈፅሙ አካላት ላይ አስፈላጊውን ማጣራት አድርጎ በህግ አግባብ ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑንም አስታውቋል።ህብረተሰቡ መሰል ተግባር ሲያጋጥመው ጥቆማ የማድረግና አካባቢውን በንቃት የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የከተማው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጥር አቅርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የትራንስፖርት ጉዳይ አሳስቦናል እያሉ ይገኛሉ!

በቅርቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በ2012 በአዲግራት ዩንቨርስቲ ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎችን በመቐለ ዩንቨርስቲ ጊቢ አስተምሮ ለማስመረቅ ማቀዱን በማሳወቅ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል።ይህንን ተከትሎ አስተያየታቸውን ለየኔቲዩብ የሰጡ የዩንቨርስቲው ተማሪዎች በመጠራታቸው ደስተኛ ቢሆኑም የትራንስፖርት አገልግሎት አለመኖሩ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። ተማሪዎቹ እንደሚሉት በአሁኑ ሰዓት ከአላማጣ መቐለ ለአንድ ሰው እስከ 1000 ብር ይጠየቃል፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ምንም አይነት ስምሪት እየተሰጠ አይደለም። ይባስ ብሎም ጥሪው የተደረገበት ጊዜ ታህሳስ 30 እና ጥር 1 የገና በዓል ማግስት በመሆኑ አገልግሎቱን ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነ ተማሪዎቹ ገልፀውልናል። ተማሪዎቹ ይህንን ችግር መንግስት ተገንዝቦ የምንጓዝበትን የትራንስፖርት አገልግሎት ቢያመቻችልን ሲሉ ጠይቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት በመተከል ዞን የተከሰተውን አለመረጋጋት በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥና ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ተፈናቃይ ወገኞች ጠየቁ።

ከነበሩበት ቀየ ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ በመኖራቸው ከፍተኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር በመዳረጋቸው መንግስት አስፈላጊውን መፍትሄ እንዲሰጣቸው በመተከል ዞን በተለያዩ የመጠለያ ማዕከል የሚገኙ ዜጎች ጠይቀዋል።በመተከል ዞን በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ እና ሌሎች አካባቢዎች በደረሰባቸው ጥቃት ተርፈው በቡለን ከተማ ተጠልለው ይገኛሉ።በመንግስት እና በተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አማካኝነት የሰብዓዊ እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጸው ይህ በቂ ባለመሆኑ ወደ ነበሩበት ቀየ እንዲመለሱ የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራው መጠናከር እንዳለበት ተጎጅ የማህበረሰብ ክፍሎች ገልጸዋል።

በቀጠናው አንጻራዊ ሰላም እስኪሰፍን ድረስ የደረሱ ሰብሎችን ለመሰብሰብ በሚመለከተው አካል በኩል ጥበቃ እንዲደረግላቸውም አሳስበዋል።በቡለን ወረዳ ብቻ ከ40 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ከቀያቸው ተፈናቅለው የሚገኙ ሲሆን በአጠቃላይ በዞኑ ከ100ሺ በላይ ዜጎች በመጠለያ ጣቢያዎች እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።በቀጠናው የህግ የበላይነትን ለማስከበር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ሰላምን ለማስፈን እየሰራም እንደሚገኝ የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኒጀር በታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 100 ደረሰ!

ጥቃቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የመጀመሪያ ዙር ውጤት እንደተገለጸ የተፈጸመ ሲሆን ጽንፈኛ ታጣቂዎች በ100 ሞተር ሳይክሎች 2 መንደሮች ውስጥ ገብተው ነው ጥቃቱን የፈጸሙት፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በአርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ የሚመራው የዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት አንድ ሚሊዮን ብር ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ።

ከመተከል ዞን ተፈናቅለው ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ተፈናቃዮች በአርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ የሚመራው ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ከውጭ ሀገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ያሰባሰበውን አንድ ሚሊዮን ብር የምግብ ድጋፍ አድርጓል።

[አብመድ]
@YeneTube @FikerAssefa
ህንድ ለኮሮና ቫይረስ ሰራሁት ያለችው የክትባት መድሀኒት የተሟላ መረጃ የለውም በሚል ትችት እየቀረበባት ይገኛል!

ህንድ በትላንትናው እለት ባሀራት ባዮቲክ ኮቫኤክሲኢን ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ መስጠቷ ይታወሳል፡፡በህንድ የመድሀኒት ቁጥጥር መስሪያ ቤት የክትባት መድሃኒቱ ማረጋገጫ የተሰጠው ሲሆን የጠ/ሚ ናሬንድራ ሞዲ አስተዳደር ስኬት ተደርጎ ተወስዷል፡፡

ኮቫኤክሲኢን በመንግስት ተቋማት የተመረተ ሲሆን ህንድ ለቫይረሱ የክትባት መድሀኒት ከሚያዘጋጁ ተርታ ውስጥ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት ሀገር ግን አይደለችም፡፡

ልክ እንደ ህንድ ሁሉ ቻይና የሰራችው የክትባት መድሀኒት ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም በሚል ወቀሳ እየቀረበ ይገኛል፡፡በህንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና የቀድሞ ሚኒስትሮች በኮሮና ቫረስ መድሀኒት ላይ መንግስት ግልፅነት ይጎድለዋል ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
በቡሬ ከተማ የተቋቋመው የአቶ በላይነህ ክንዴ የምግብ ዘይት ፋብሪካ የሙከራ ምርት መጀመሩ ተገለጸ!

በቡሬ ከተማ የተቋቋመውንና ከ991 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የአቶ በላይነህ ክንዴ የምግብ ዘይት ፋብሪካ የሙከራ ምርት መጀመሩን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።አቶ መላኩ አለበል በቡሬ ከተማ የተቋቋመውን የአቶ በላይነህ ክንዴ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ምርት ለማምረት ላበቁት አካላት በትዊተር ገጻቸው ምስጋና አቅርበዋል::በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ ከ991 ሚሊዮን ብር በላይ ለተገነባው የአቶ በላይነህ ክንዴ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ስኬታማነት አስተዋጽዖ ለነበራቸውና ፕሮጀክቱ ሥራ እንዲጀምር ጥረት ላደረጋችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል” ብለዋል፡፡

የዘይት ፋብሪካ የሙከራ ምርት መጀመሩን አቶ መላኩ በትዊተር ገጻቸው ጠቅሰዋል፡፡ሚኒስትሩ ከዚህ በፊትም ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር 22 ሚሊዮን 500 ሺህ ሊትር ለገበያ እንደሚያቀርብ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡በቡሬ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሪችላንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ አማካኝነት የተገነባው የአኩሪ አተር ፕሮቲንና የምግብ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ ወደ ሙከራ ምርት መግባቱን ገልጸው ነበር፡፡ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባም 22 ሚሊዮን 500 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት ለሀገር ውስጥ ገበያ ያቀርባል።ለውጪ ገበያ ከሚያቀርበው የምግብ ዘይትም 61 ሚሊዮን 680 ሺህ ዶላር እንደሚያስገኝ ሚኒስትሩ መናገራቸው አብመድ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በቡሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው ከሌሊቱ 10 ሰዓት 48 ሰዎችን ጭኖ ለመንፈሳዊ ጉዞ ከደንበጫ ወደ ላሊበላ በመጓዝ ላይ የነበረ ኮድ 3 የሆነ ቅጥቅጥ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ቡሬ ከተማ በመገልበጡ የደረሰ ነው፡፡በአደጋው ሳቢያ የአራት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ15 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል።ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቡሬ አስራደ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ከቡሬ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ሕይወታቸው ከሚያልፉት መካከል ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በሀገሪቱ ውስጥ በኮሮናቫይረስ በሽታ ከተያዙ ሰዎች መካከል ከ56 እስከ 60 በመቶ የሚሆኑት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መሆኑን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የብሔራዊ ኮቪድ 19 መከላከል ሰብሳቢ አቶ አስቻለው ዓባይነህ በተለይ ለኢቲቪ ገልጸዋል።

የሞት ምጣኔ ጋር በተያያዘ በተለይ ወደ ጤና ተቋም መጥተው ከሚሞቱ ሰዎች መካከል 50 በመቶ በላይ ዜጎች አዲስ አበባ ውስጥ መሆናቸውን፣ ነገር ግን ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በደንብ ፍተሻ ቢደረግ ከዚህ መጠን ያነሰ ስርጭት አይኖርም የሚል ምልከታ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ውስጥ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ አድርጎ የመንቀሳቀስ መጠን መቀነሱን ተከትሎ ጉዳዩ አሳሳቢ በመሆኑ የሕክምና ተቋማቱን ግብዓት የማሟላት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

አዲስ አበባ ላይ በመተግባር ላይ የሚገኘው ምርመራ በጤና ተቋማት ውስጥ ከቤታቸው ውስጥ አልያም ከለይቶ ማቆያ እንዲሁም ብዙ የማኅበረሰብ ክፍል የሚገኝባቸው ማረሚያ ቤት፣ የአረጋዊያን ማእከላት እንዲሁም ሰዎች ሰብሰብ ብለው የሚኖሩባቸውን አካባቢዎች መለየት ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰዋል።34 በሚሆኑ የጤና ጣቢያዎች ላይ ምርመራ እንደሚሰጥ እና ሆስፒታሎቹ ከየተቋማቱ የተሰበሰቡ ናሙናዎችን በመመርመር በሽታውን ለመግታት ትኩረት አድርገው እየሠሩ ነው ብለዋል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በጅግጅጋ 218 ህገ ወጥ ባጃጆቸ በቁጥጥር ስር ዋሉ!

የጅግጅጋ ከተማ አስተዳድር ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ከታህሳስ 13፣2013 ዓ.ም ጀምሮ 218 ሰሌዳ ያልተሰጣቸው ባጃጆችን በቁጥጥር ስር አዋለ።በከተማዋ የሚንቀሳቀሱት ኮድ አንድ ባጃጆች ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ አውጥተው፣ በማኅበር ተደራጅተው ሳምንታዊ መርሀ ግብር ስምሪት እየተሰጣቸው የሚሠሩና ዓመታዊ የሥራ ግብር የሚከፍሉ ናቸው፡፡

ሆኖም በጅግጅጋ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የኮድ አንድ ባጃጅ ሰሌዳ በ2010 ዓ.ም፣ የኮድ ሁለት እና ኮድ ሦስት ባጃጅ ሰሌዳ ደግሞ 2011 ዓ.ም የተከለከለ ሲሆን ከዚህ በተቃራኒው ግን አዳዲስ በጃጆች በከተማው እንደበዙ የክልሉ ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሮብሌ አዋሌ ይገልፃል፡፡“በዛ ወቅት በክልሉና በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋት እና የሰላም መደፍረስ ተከስቶ ስለነበር በከተማ መስተዳድሩ ሰሌዳ ሳይሰጣቸው መስራት የጀመሩ ባጃጆች ላይ ርምጃ ለመውሰድ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡ይህም በመንግሥት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ አውጥተው በሚሠሩት እና ግብር በሚከፍሉት ላይ ከፍተኛ ችግር ይፈጥራል መንግሥትን ማግኘት የሚገባውን ግብር አሳጥተዋል” ብሏል።

እነዚህ ባለባጃጆች መንገድ እና ትራንስፖርት ካስቀመጠው ታሪፍ በላይ በማስከፈል ማኅበረሰቡን ለእንግልት እና ለብዝበዛ እንደሚዳርጉ ተናግሯል፡፡ተጠቃሚ ሲበዛ ኮንትራት ካልሆነ አለመጫን፣ በዝናብና በችግር ጊዜ መስመርን ጠብቆ አለመስራት፣ የትራፊክ ሕግን አክብሮ አለመንቀሳቀስ በባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ላይ በተደጋጋሚ የሚስትዋል ጥፋት መሆኑን የተናገረው ሃላፊው ክትትሉ እና እርምጃው እንደሚቀጥል አክሏል።

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የወርቅ ማቅለጫ ሊገነባ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ማቅለጫ እንደሚገነባ የማአድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ።ይህንን የወርቅ ማቅለጫ መገንባት እንደ ኢትዮጵያ ላለች የወርቅ ማዕድን ላላት አገር ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ የማአድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa