YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ደራሲ አዘጋጅ እንዲሁም ተዋናይት ባዩሽ አለማየሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

በቴአትር ልምምድ ላይ እያለች ትንሽ አሞኛል ብላ በዛው የቀረችው ደራሲ፤አዘጋጅ፤ተዋናይት ፤ገጣሚ እና ተራኪ ባዩሽ አለማየሁ ዛሬ ታህሳስ 23/2013 ዓም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በህክምና ስትረዳ በቆየችበት በየካቲት 12 ሆስፒታል ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

[ሸገር ታይምስ]
@YeneTube @FikerAssefa
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በነገው እለት ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ያስመርቃል!

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በነገው እለት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ያስመርቃል።ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በማታ እና በእረፍት ቀናት መርሀግብሮች ያሰለጠናቸውን 6ሺህ 263 ተማሪዎች ነው በነገው እለት የሚያስመርቀው።ከተመራቂዎቹ መካከል 2ሺህ 144ቱ ሴቶች መሆናቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት አምስት አመታት ከወደሙ ፍብሪካዎች ውስጥ አንሰራርተው ወደ ስራ መግባት የሚችሉት 1% ቱ ብቻ ናቸው።

ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረው የፀጥታ ችግርና አመፅ ከ400 በላይ ፍብሪካዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የወደሙ ሲሆን ወደ ስራ መግባት የሚችሉት ከአንድ ፐርሰንት ወይም ከአራት አንደማይበልጡ የኢትዮጵያ አንቪስትመንት ኮሚሽንን ጠቅሶ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል።ይሄ ቁጥር በትግራይ የወደሙ ፋብሪካዎችን አይጨምርም።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች በዚህ ዓመት በታኅሣስ ወር ብቻ በርካታ የእሳት አደጋዎች ደርሰዋል። በዚህም የተነሳ በሚሊዮኖች ብሮች የሚገመት ንብረት ወድሟል።

እነዚህ አብዛኞቹ የእሳት አደጋዎች የደረሱት በተለይ በገበያ ሥፍራዎች ላይ ሲሆን በመኖሪያ አካባቢዎች ላይ ደረሱና ጥቂት የማይባሉ ነዋሪዎች የተፈናቀሉባቸውም አጋጣሚዎች አሉ።
ቢቢሲ ከተለያዩ የዜና ዘገባዎች ካሰባሰባቸው የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች ውስጥ ባለንበት የታኅሣስ ወር ያጋጠሙት በቁጥር በርከት ይላሉ። ምክንያቱን ግን ለመገመት አስቸጋሪ ነው።

በዚህ ወር ብቻ አደጋዎች የደረሱበት:

1.ታኅሣስ 8/2013 ዓ.ም ሐረማያ

2.ታኅሣስ 8/2013 ዓ.ም ቡራዩ

3.ታኅሣስ11/2013 ወላይታ ሶዶ

4.ታኅሣስ 13/2013 ባሕርዳር

5.ታኅሣስ 14/2013 ጅግጅጋ

6.ታኅሣስ 14/2013 መቅደላ ወረዳ

7.ታኅሣስ 18/2012 ሀላባ ዞን

8.ታኅሣስ 18 እና 19/2013ሀዲያ ዞን

9.ታኅሣስ 19/2013ምዕራብ ኦሞ ዞን

10.ታኅሣስ 22/2010 በደብረ ማርቆስ

በዚህ ዙሪያ ቢቢሲ ያዘጋጀው ጥንቅር👇👇

https://bbc.in/3b0VvBt
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ማሰባሰቢያ የባንክ ሒሳብ ቁጥር ይፋ ሆነ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ላይ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የተሰየመው የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000261313301 ይፋ አድርጓል።
በመሆኑም "ለወገን ደራሽ ወገን ነውና" ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የተቻለውን ድጋፍ እንዲያደርግ የክልሉ መንግሥት ጥሪ ማቅረቡን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@Yenetube @Fikerassefa
የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች የመመረቂያ ትምህርታቸውን በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ እንዲያደረጉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እና በቻይናው ተቋራጭ CCECC ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱ ሀገራዊ የባቡር መስመርን አዋሽ ከሚገኘዉ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዲፖ ጋር የሚያገናኝ ሲሆን ለመጫንና ለማራገፍያ አገልግሎት የሚያስፈልጉ የፋሲሊቲዎች ግንባታንም ያካትታል። ፕሮጀክቱ የአዲስ አበባ - ጅቡቲ የባቡር መስመርን ከአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሀራገበያ የባቡር መስመር ጋር ከማገናኘት አንጻር ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

የኮንትራት ስምምነቱ ከዲዛይን እስከ ግንባታ ያለዉን የሚያጠቃልል ሆኖ 54.93 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (2.018 ቢሊዮን ብር) የሚሸፍን ሲሆን ወጪዉ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ይሆናል።

95% ነዳጅ ወደ ሀገራችን የሚገባዉ በጅቡቲ ወደብ እንደመሆኑ መጠን ፕሮጀክቱ በተሽከሪካሪ ብቻ የሚመጣዉን የነዳጅ በባቡር የትራንስፖርት አማራጭ እንዲገባ በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅን በመቀነስ የሚያገለግል ከመሆኑም በላይ ከአዋሽ ነዳጅ ማጠራቀሚያን የሚገኘዉ የነዳጅ ወደ መሃል ለማድረስ ያገለግላል።

የትራንስፖርት ወጪን ከመቀነስ በዘለለ የነደጅ ስርቆት አደጋን እንዲሁም የአየር ብክለትን ከመቀነስ ረገድም ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

የአዋሽ ብሔራዊ የነዳጅ ዲፖ እስከ 130ሺ ኩዊብክ ሜትር ነዳጅ የመያዝ አቅም እንዳለዉ ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ከአዲስ አበባ እስከ ጅቡቲ የባቡር መስመር ወደ 110 የሚሆኑ ለነዳጅ ማመላለሽ የሚሆኑ ዋገኖች ቀድመዉ የተዘጋጁ በመሆናቸዉ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በቀጥታ ወደ ሥራ መግባት የሚቻል መሆኑ ታዉቋል።ፕሮጀክቱ በአንድ አመት ዉስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው!

የወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 4 ሺህ 238 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ነው።ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን ለ12ኛ ዙር የሚያስመርቅ ሲሆን፣ ከተመራቂዎቹ መካከል 1 ሺህ 522 ሴቶች ሲሆኑ፣ 2 ሺህ 716ቱ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡ከነዚህም በመጀመሪያ ዲግሪ 3 ሺህ 920፣ ሁለተኛ ድግሪ 185 እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ 133 ሲማሩ የቆዩ ተማራቂዎች መሆናቸውን ዋልታ ከስፍራው ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል በሚገኘው ታሪካዊው አል ነጃሺ መስጂድ ላይ ጥቃት ተፈፅሟል !!ጥቃቱን ያደረሰው አካል እስካሁን አልተገለፀም።

[Fidelpost]
@YeneTube @FikerAssefa
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 6263 ተማሪዎች አሰመረቀ፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 34 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።ከተመራቂዎቹ መካከል 6ቱ በዶክትሬት ዲግሪ፣ 514ቱ በማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም 5626ቱ ደግሞ በመጀመሪያ ዲግሪ ለመመረቅ በቅተዋል ሲል ደሬቴድ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 6 ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ340 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ::

የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደተናገሩት ባለፉት 6 ወራት ከ340 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡

ገቢው የተገኘው ከ4112 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ፣26.97 ቶን ታንታለም፣1625 ኪሎግራም ጥሬ ኦፓል 37.8 ኪ.ግ እሴት የተጨመረበት ኦፓል እና 2123ኪ.ግ ሌሎች የጌጣጌጥ ማዕድናት ለውጭ ገበያ ማቅረብ ተችሏል፡፡

ለሀገር ውስጥ ገበያ ከቀረቡ የኢንዱስትሪና የኮንስትራክሽን ማዕድናት 1.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዘርፉ ለ48,785 ዜጎች የስራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን ሚኒስቴር መ/ቤቱ፣ ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልሎችና ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የቀጣይ ስድስት ወራት የዕቅድ አቅጣጫዎች ተቀምጧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዝግጅቶች ሲጠናቀቁ ክትባቱን መስጠት ይጀመራል - ጤና ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባት ማስገባት የሚያስችሉ የላቦራቶሪና ሌሎች ዝግጅቶችን ሲጠናቀቁ ለ20 በመቶ ዜጎቿ ክትባት መስጠት እንደሚጀመር የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ ገለጹ።ክትባቱ መስጠት ሲጀመር ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የሕክምና ባለሙያዎችና ዳር ድንበር የሚጠብቁ የሕብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ ያገኛሉ ብለዋል።የተለያዩ አገራት እስካሁን ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳይንሳዊ መፍትሔዎችን እያፈላለጉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ክትባትን እንደ አንድ መፍትሔ በመውሰድ ለሕዝቦቻቸው ተደራሽ እያደረጉ ነው።

ሚኒስትር ዴኤታ ኢትዮጵያም ሳይንሳዊ ሁኔታዎችን ተከትላ ክትባቱን ለማስገባት ስትዘጋጅ መቆየቷን ገልፀው ይህንን ታሳቢ በማድረግ ክትባቱን መፈተሻ ላቦራቶሪ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት እየተገጣጠመ ይገኛል ብለዋል።ክትባቱ ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት የላቦራቶሪ ፍተሻዎችን ሲያልፍ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ይደረጋል ነው ያሉት።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
የአርቲስት ባዩሽ አለማየሁ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ!

የደራሲ አዘጋጅና ተዋናይት ባዩሽ አለማየሁ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ።የአርቲስት ባዩሽ የቀብር ሰነ ስርዓት ወዳጅ ፣ ዘመዶቿ እና አርቲስቶች እንዲሁም አድናቂዎቿ በተገኙበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።ባዩሽ አለማየሁ በሃገር ፍቅር ቴአትር ቤት በተዋናይትነት ለረጅም አመታት አገልግላለች።በርካታ አጫጭር ተከታታይ ድራማዎችን፣ የመድረክ ትያትሮች ላይም በተዋናይነት እንዲሁም በአዘጋጅነት ስትሰራ ቆይታለች፡፡

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
ህንድ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የተዘጋጀው የኮሮና ክትባት ግልጋሎት ላይ እንዲውል ፈቀደች!

ህንድ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ተዘጋጅቶ አስትራ ዜናካ በተባለው መድሃኒት አምራች ኩባንያ የተመረተው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ግልጋሎት ላይ እንዲውል ፈቀደች፡፡ክትባቱ ፍቃድ ማግኘቱን የመረጃ ሚኒስትሩ ፕራካሽ ጃቫዴካር ተናግረዋል፡፡ከአሜሪካ በመቀጠል በርካቶች በቫይረሱ በተጠቁባት ህንድ የአገልግሎት ፍቃድን ያገኘ የመጀመሪያው ክትባት ነው፡፡የራሽያውን ስፑትኒክ ቪን ጨምሮ በሃገር ውስጥ የተዘጋጁ ሌሎች ሁለት ክትባቶች እንዲሁ የአገልግሎት ፍቃድ ለማግኘት እየተጠባበቁ ይገኛሉ እንደ ሮይተርስ ዘገባ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከ11 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ 150 አዳዲስ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ግዥ መፈፀሙን አስታውቋል።

ከቻይና ግዢ የተፈጸመባቸው ተሽከርካሪዎቹ እያንዳንዳቸው ከ400 ኩንታል በላይ የመጫን አቅም እንዳላቸው የድርጅቱ የኮርፖሬት አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንድሙ ደንቡ ገልጸዋል፡፡ተሽከርካሪዎቹ የገቢና ወጪ ጭነቶችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማጓጓዝ እና የድርጅቱን የሎጅስቲክስ አቅም ለመገንባት የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ግዥ እንደተፈፀመ ተነግሯል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በጅማ ሹፌሮች በቤንዚን እጥረት ተቸግረዋል!

በጅማ ከተማ ከማክሰኞ 20፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ባጋጠመው የቤንዚን እጥረት ምክንያት ከ11 የነዳጅ ማደያዎች መካከል አንዱ ብቻ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡በዚህም በጣም  መቸገራቸውን በከተማው የሚገኙ የባጃጅ ሾፎሮች ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል፡፡

«ቤንዚን ለመቅዳት ወረፋው ብዙ ነው ፤ግዜዬን እያባከነብኝ ነው፡፡ እዚህ ከተማ ካሉ 11 የነዳጅ ማደያዎች መካከል ሰሞኑን የቤንዚን እጥረት ካገጠመ ጀምሮ ዲና ቶታል የሚባል የነዳጅ ማደያ ብቻ አገልግሎት እየሰጣ ይገኛል፡፡ሌሎቹ የነዳጅ ማደያዎች እጥረት አለ በሚል ሰበብ በህገወጥ መንገድ በችሪቻሮ ለሚነግዱት አትርፎ ይሸጣሉ፡፡

በማደያ 22.50 ብር የሚሸጠው አንድ ሊትር ቤንዚን ለቸርቻሪዎች በ25.50 ብር ይሸጣል፤ በበርሜል ሲሆን ደግሞ በጣም ይጨምራል፡፡አንዴ ቢንዚን ለመቅዳት ከሶስት ሰዓት በላይ ተሰልፌ መጠበቅ አለብኝ፡፡እኔም የልጆች አባት ስለሆንኩኝና መስራት ስላለብኝ አንዳንዴ ሰዓቴን ላለማባከን በችርቻሮ የሚሸጠውን በ35 ብር ለመግዛት ተገድጃለሁ፡፡» ይላል ቅሬታውን ያቀረበ የባጃጅ ሹፌር

ሌላኛው የባጃጅ ሾፌር ደግሞ “በጅማ ከተማ የቤንዚን እጥረት ተከሰተ የሚባለው በጣም በተደጋጋሚ ግዜ ነው፡፡አንዳንዴ ነዳጅ ማደያዎች አውቀው የለም በማለት በድብቅ ዋጋውን ጨምሮ ለሚቸረችሩ ግለሰቦች ይሸጣሉ፡፡የከተማው ንግድ ቢሮም ጠንካራ የሆነ ክትትልና እርምጃ ሲወስድ አይታይም፡፡

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የፋይዘር ክትባቶች ለድንገተኛ ግልጋሎቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተፈቀደ!

የዓለም ጤና ድርጅት በፋይዘር/ባዮንቴክ የተመረቱ የኮሮና ክትባቶች ለድንገተኛ አገልግሎቶች እንዲውሉ ፈቀደ፡፡ፍቃዱ በማደግ ላይ ያሉ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሃገራት ዜጎቻቸውን መከተብ እንዲጀምሩ መንገድ የሚጠርግ ነው ተብሏል፡፡ክትባቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በእንግሊዝ ነበር ፍቃድ ያገኘው፡፡ ከዚያም አሜሪካ፣ካናዳ እና አውሮፓ ግልጋሎት ላይ እንዲውል ፈቅደው ዜጎቻቸውን መከተብ ጀምረዋል፡፡በዓለም አቀፉ ተቋም የተሰጠው ፍቃድ የክትባቶቹን ፍቱንነት የመፈተሽ አቅም የሌላቸው ሃገራት ክትባቱን እንዲገለገሉ ለማድረግ የሚያስችል ነው፡፡በደሃና በሃብታም ሃገራት መካከል የሚነሳውን የፍትሃዊ ተደራሽነት ጥያቄ አንጻራዊ ምላሽ ለመስጠት እንደሚያስችልም ይገመታል፡፡ሲኤንኤን እንደ ዘገበው ከሆነ የድርጅቱ የክትባት ሙያተኞች የፊታችን ማክሰኞ ተሰብስበው ክትባቱ በስፋት ጥቅም ላይ ስለሚውልበት ሁኔታ ይመክራሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

Al-ain
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ አውሮፓ ለማቋረጡ ሲሞክሩ የሰጠሙ ስደተኞች ሳይሆኑ አይቀሩም የተባሉ ሰባት ሰዎች አስከሬኖች ከአልጄሪያ የባሕር ዳርቻ ወድቀው መገኘታቸውን የአገሪቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተናገሩ።

አስከሬኖቹ የሶስት ወንዶች እና የአራት ሴቶች መሆናቸውን የገለጹት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች መበስበስ በመጀመራቸው ማንነታቸውን መለየት አዳጋች እንደሆነ ተናግረዋል።

ለስደተኞች ቤተሰቦች የሚቆሙ አንድ ጠበቃ እንደተናገሩት ባለፉት ሳምንታት ከአልጄሪያ ወደቦች በመነሳት የሜድትራኒያን ባሕርን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።ፍሮንቴክስ የተባለው የአውሮፓ የድንበር ቁጥጥር ኤጀንሲ የቅርብ ጊዜ መረጃ እንደሚያሳየው በጎርጎሮሳዊው 2020 ዓ.ም. የመጀመሪያ አምስት ወራት ብቻ ከ3,7000 በላይ ስደተኞች ምዕራባዊ ሜድትራኒያን ባሕርን አቋርጠዋል። ከእነዚህ መካከል ግማሽ ያክሉ አልጄሪያውያን ናቸው።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ለ600 አርሶ እና አርብቶ አደሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት እውቅና እና ሽልማት ይሰጣል፡፡

በክላስተር በማልማት ምሳሌነት ያለው ስራ ላከናው 600 አርሶ እና አርብቶ አደሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት እውቅና እና ሽልማት የመስጠት መርሀ ግብር በአዳማ አባገዳ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሔደ ነው፡፡

ሽልማት እና እውቅና ከሚሰጣቸው መካከል 357 ቱ አርሶ እና አርብቶ አደሮች ፣ 29 ባለድርሻ አካላት ፣ 12 ደግሞ የግብርና ምርቶችን እና የእንስሳት ተዋፅኦችን ለውጥ ገበያ የሚያቀርቡ ነጋዴዎች ፣ በወረዳ ደረጃ በክላስተር በማልማት ሞዴል የሆኑ 32 ወረዳዎች ናቸው፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ፣ የክልሉ መንግስት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳባ ደበሌ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

[OBN]
@YeneTube @FikerAssefa
የመቐላ ዩንቨርስቲ 2012 ዓ/ም ተመራቂዎች ሆናችሁ በወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ላልተመረቃችሁ ተማሪዎች የመማር ማስተማር ሂደቱን ካቋረጣችሁበት በመቀጠል እና በመጨርስ እንድትመረቁ የአጭር ግዜ ልዩ ፕሮግራም ስለተዝጋጀ ጥር 5/2013 ዓ/ም በአካል ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን ።

Via:- Mekelle University
@Yenetube @Fikerassefa