YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከግልገል በለሰ ማረሚያቤት «ለማምለጥ የሞከሩ» የተባሉ እስረኞች በፈጠሩት ረብሻ ቁጥሩ ያልታወቀ ሰዉ መሞቱ ተነገረ።ዶይቸ ቨለ የዓይን ምስክሮችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ በአካባቢዉ ከፍተኛ ተኩስ ይሰማ ነበር።ለማምለጥ የሞከሩ ከተባሉት እስረኞች ቢያንስ ሁለቱ ክፉኛ ቆስለዉ ሆስፒታል ሲደርሱ ሞተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ጥቃት ተፈጸመብኝ አለ!
 
የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫ የሀገሪቱ ታጣቂ ኃይሎች የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ እና በሱዳን ላይ የሚያስከትለውን መዘዝ በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። እነዚህም የስደተኞች ወደ ሱዳን ግዛቶች መግባት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው ድንበር ላይ ያለው አለመረጋጋት መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

የሀገሪቱ ታጣቂ ኃይል በኢትዮጵያ በነበረው ውጊያ የፌዴራል መንግሥትም ይሁን የትግራይ ተዋጊዎች የሱዳንን መሬት እንዳይጠቀሙ ሲጠብቅ መቆየቱን አንስቷል።ይሁንና ትናንት ማክሰኞ ታህሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ የኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች ወደ ሱዳን ግዛት ገብተው ጥቃት እንደፈጸሙ የሱዳን ጦር ገልጿል።

ሚሊሺያዎቹ 'ጃባል አቡጢዩር' በተባለ አካባቢ አድብተው እንደፈጸሙት በተገለጸው ጥቃት የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን እና በንብረትም ላይ ጉዳት መድረሱን መግለጫው ያትታል። የቆሰሉ ሰዎችም መኖራቸው ቢጠቀስም፣ ምን ያክል ሰዎች እንደተገደሉ እና እንደተጎዱ ግን አልተገለጸም።

ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በአካባቢው የነበሩ የሱዳን ታጣቂዎች እና ነዋሪዎች ለመከላከል ጥረት ማድረጋቸውን በመግለጽ ጦሩ ሀገሪቱን ከጥቃት እና ከወረራ ለመከላከል የገባውን ቃል እንደሚፈጽም አስታውቋል።ከሰሞኑ በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ አለመረጋጋት ስለመኖሩ ጭምጭምታዎች ቢሰሙም ሁለቱም ሀገራት በይፋ ችግሮች ስለመኖራቸው ሳይገልጹ ቆይተዋል። በሱዳን በኩል በሀገሪቱ ጦር ምሽት ላይ ስለቀረበው ወቀሳ በኢትዮጵያ በኩል ወዲያው የተሰጠ ምላሽ የለም።

Via Al-ain
@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት በትግራይ ክልል ባሉ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የህግ ታራሚዎችን ሰብስቦ በመቀሌ ከተማ ውስጥ በመልቀቅ ዝርፊያ እንዲፈጸም አድርጓል ሲሉ የመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተናግረዋል።“በበርካታ ወንጀሎች ተይዘው የነበሩ ሰዎች መቀሌ ላይ ተሰብስበው እንዲለቀቁ ስለተደረገ የግለሰቦች ሱቅ ጭምር እንዲዘረፉ ተደርጓል” ብለዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን እስካሁን 280 ታጣቂዎች ተደምሰዋል ተባለ!

በመተከል ዞን ለወራት በቀጠለው የጸጥታ መደፍረስ ከተሳተፉት ታጣቂዎች ውስጥ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ 284ቱ መደምሰሳቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ለአዲስ ዘይቤ ተናግሯል፡፡

በዞኑ ህግ ለማስከበር የተቋቋመው ኮማድ ፖስት በወሰደው እርምጃ ከተደመሰሱት ታጣቂዎች በተጨማሪ 1001 ከማህበረሰቡ ጋር ተደባልቀው ለተጣቂዎች መረጃ ሲያቀብሉ ነበር የተባሉ እና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በዞኑ ለተፈጠረው ችግር መንስዔ የሆኑ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ከእነዚህ ውስጥ 66 አመራሮች፣ 32 የፖሊስ አባላት 35 የጸረ ሽምቅ አባላት ይገኙበታል ተብሏል፡፡በተጨማሪም 227 የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ፅህፈት ቤቱ ገልጿል፡፡

ለወራት በቆየው የጸጥታ ችግር እስካሁን 22 ሺህ 789 የህብረተሰብ ክፍሎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን አዲስ ዘይቤ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል፡፡የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ ለማረጋጋት 2ሺ 679 የሚሊሻ አባላት መሰልጠናቸውንም የአዲስ ዘይቤ መረጃ ያሳያል፡፡

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ኬኒያ ውስጥ በህገወጥ መንገድ በመገኘታቸው 10 ኢትዮጵያን ታሰሩ!

የኬኒያው ኔሽን አፍሪካ ድህረ ገፅ እንደዘገበው ማዉዋ በተባለችው ከተማ ያለ ህጋዊ ፈቃድ በመገኘታቸውና ወደሌላ ስፍራ ለመጓዝ ዝግጅት ውስጥ እንደነበሩ ተገልጿል። ሰዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበው የ6 ወር እስር የተፈረደባቸው ሲሆን እስሩ ወደ ገንዘብ መቀጮ እንዲቀየርላቸው ከፈለጉ እያንዳንዳቸው 100,000 የኬኒያ ሽልንግ መክፈል ይጠበቅባቸዋል ተብሏል። ድህረ ገፁ የታሳሪዎቹን ስም ዝርዝር ያወጣ ሲሆን ፣ ኢያሽ አዶሬ፣ ጃሚሉ ታደሰ፣ ደፈፈ አበረ፣ ምንተስኖት አበራ፣ ሰዒድ ከድር፣ አዲሴ ጴጥሮስ ፣ ታሪኮ ሶማኖ፣ መስፍን ቦቢቾ፣ ሲያን ዱማ እና እሸቱ ዶቢቶ የሚባሉ ሰዎች መሆናቸውን ጠቅሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ከታህሳስ 12/2013 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ መደበኛ እና የመጀመሪያ ሳይክል የገፅ ለገፅ ትምህርት መሰጠት እንደሚጀመር የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ ከመጪው ሰኞ ታህሳስ 12/2013 ዓ.ም ጀምሮ በ5ኛው ዙር መርሃ ግብር በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ሳይክል (ከ1-4) ትምህርት የሚጀመር ሲሆን በሁሉም የግል ትምሀርት ቤቶች ደግሞ የቅድመ መደበኛ (የመዋለ ህፃናት) ትምህርት እንደሚጀመር እና ለዚህም አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ት/ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ በተለይም ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአንጋፋው የጥበብ ሠው እና መምህር ረ/ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ የክብር ሽኝት ስነስርዓት ዛሬ ታህሳስ 8/2013 ከአራት ሰዐት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል። ከቀኑ በስምንት ሰዓት ተኩል በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ስነስርዓት ይፈፀማል።

Via Arts TV
@YeneTube @FikerAssefa
መቐለ ዩኒቨርሲቲ 3‚291 ተማሪዎችን አስመረቀ!

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን 3‚291 ተማሪዎች አስመርቋል።ዩኒቨርሲቲው 3‚290 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ፤ አንድ ተማሪ ደግሞ በሦስተኛ ዲግሪ ያስመረቀ መሆኑ ታውቋል።ከጠቅላላ ተመራቂዎች 30 በመቶው፣ እንዲሁም በጤና መስክ ከተመረቁት መካከል ደግሞ 38 በመቶው ሴቶች መሆናቸውን ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች የአንበጣ መንጋ መከሰቱ ተገለጸ፡፡

በደቡብ ክልል በም/ርዕሰ-መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ክለስተር አስተባባሪና የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ እንደገለጹት በደቡብ ኦሞ ዞን ሀመር ወረዳ ታህሳስ 06/2013 የአንበጣ መንጋ ተከስቷል፡፡እንደ አቶ አንተነህ ገለጻ የበረሀ አንበጣው የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር አውሮፕላን ወደ ክልሉ በማስገባት የኬሚካል ርጭት በማድረግ መቆጣጠር መቻሉንም አስረድተዋል፡፡

ደቡብ ኦሞ ዞን እንዲሁም አጎራባች ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ታህሳስ ወር የበረሃ አንበጣ ሊከሰት እንደሚችል የተተነበየ በመሆኑ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ለማከናወን በቂ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል፡፡የበረሃ አንበጣ በኬንያና በኢትየጵያ ድንበር ቦረና ዞን በሚገኝ ማዮ የሚባል አካባቢ እንዲሁም ተልተሌ ወረዳ መኖሩንና የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ እየተከናወነ እንደሆነ ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያስረዳል፡፡

[ደቡብ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማክሮን በኮሮና ቫይረስ ተያዙ!

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ዛሬ ጠዋት ይፋ አድርጓል፡፡ፕሬዚዳንቱ ምልክቶችን ካሳዩ በኋላ ባደረጉት ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ነው ጽ/ቤቱ የገለጸው፡፡ከዛሬ ጀምሮ ለሰባት ቀናት ራሳቸውን እንደሚያገሉም ስካይ ኒውስ ዘግቧል ፡፡ይሁንና ስራቸውን እንደሚቀጥሉ ተገልጿል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
እነ ጃዋር መሀመድ ‘በአቅራቢያችን ችሎት ጉዳያችን ይታይልን’ ብለው ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ሆነ!

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የህገ መንግስትና የፀረ ሽብር ወንጀሎች ጉዳይ ችሎት የእነ ጃዋር መሀመድን ጉዳይ ዛሬ ተመልክቷል፡፡ከዚህ በፊት አቶ ጃዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሀምዛ አዳነ እና ሸምሰዲን ጠሀ ባቀረቡት የጽሁፍ አቤቱታ ለደህንነታችን ስለምንሰጋ ችሎቱ በአቅራቢያችን ይሁንልን ሲሉ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ይህንን የመረመረው ችሎቱ ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ በዚሁ ችሎት ጉዳያቸው እንዲታይ አዝዟል፡፡ለጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ዛሬ አራቱ ተጠርጣሪዎች በችሎቱ ያልተገኙ ሲሆን በመዝገባቸው ስር የተካተቱ ቀሪዎቹ ግን ተገኝተዋል ሲል የኤፍቢሲ ዘገባ አመልክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የሕዝብ ንባብ አገልግሎት መስጠት እጀምራለሁ አለ።

አጀንሲው እነደተናገረው ከሆነ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እየተከላከለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቋል።በሕዝብ ንባብ ቤቱ ከአሁን ቀደም በአንድ ጊዜ ከ1000 በላይ አንባቢዎችን ያስተናግድ እንደነበር የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ዳይሬክተሩ አቶ ያሬድ ተፈራ ተናግረዋል።አሁን ግን ከግማሽ በላይ በመቀነስ 326 ሰዎች ይስተናገዳሉ ብለዋል።አንባቢዎች የተጠቀሙባቸው መጻሕፍትም ከ3 እስከ 5 ቀናት ከንክኪ ርቀው ተለይተው ይቆያሉ ተብሏል።

ለዚሁ ሲባል 1 ክፍል ማዘጋጀቱን ነው ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ የተናገረው።የቤተ መጻሕፍቱ ተገልጋዮች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የንባብ አገልግሎት ማግኘት ትችላላችሁ ተብላችኋል።የወረርሽኙን ስርጭት ለመከላከልም ብርቱ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ሲልም ኤጀንሲው ጥሪ አቅርቧል።ለአጥኚዎችና ተመራማሪዎች ከነሐሴ 15፣ 2012 ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱንም ተሰምቷል።ቀስ በቀስ ሙሉ የንባብ ቤቶቹን አገልግሎት ወደመስጠት እንደሚያሸጋግርም ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ እወቁት ብሏል።

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
የምስራቅ አፍሪካ አገሮች ሌላ ዙር ከባድ የበረሃ አንበጣ ወረራ እንደሚያሰጋቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጠ፡፡

ማስጠንቀቂያውን የሰጠው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡የመንም የበረሃ አንበጣ ወረራው ሰለባ እንደምትሆን በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

እንደ ፋኦ ማስጠንቀቂያ በቀይ ባሕር ማዶ ለማዶ የበረሃ አንበጣው ዕጭ በመፈልፈል ላይ ይገኛል፡፡አመቱም ለመስራቅ አፍሪካ በ70 ዓመታት ውስጥ እጅግ ከባዱ የበረሃ አንበጣ ወረራ ጊዜ ሆኖ ማለፉን መረጃው አስታውሷል፡፡የበረሃ አንበጣው በቀዳሚው ወረራውም ከፍተኛ ጥፋት ማድረሱ ለትውስታ ተነስቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የደራሲና ተዋናይ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ስርዓተ ቀብር በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ የተለያዩ መፅሃፍትን የደረሱ ሲሆን በተለያዩ ፊልሞች እና ድራማዎች ላይም በተዋናይነት ተሳትፈዋል።ዛሬ ረፋዱን በብሄራዊ ቴአትር ቤት የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተካሄዷል፡፡በርካታ ተውኔቶች ላይ የትወና ችሎታቸውን ያስመሰከሩት ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ አጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞቻቸው በሩሲያኛ ተተርጉመው ታትመዋል፡፡ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ መተከዣ (ግጥምና ቅኔ)፣ ጥላሁን ግዛው፣ ዕቃው፣ የሺህ፣ አባትና ልጆች፣ ላቀችና ደስታ፣ ተሐድሶ የተሰኙ ተውኔቶችን ደርሰዋል።እንዲሁም የዑመር ኻያምን ልብወለዳዊ የሕይወት ታሪኩና ሩብ አያቶቹ የትርጉም መፅሃፍ ለአንባቢያን አድርሰዋል።ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር እና ጥበባት ኮሌጅ ለበርካታ ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል።በሐረርጌ በ1929 ዓ.ም የተወለዱት ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ በ84 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ሱዳንና ኢትዮጵያ በሚዋሰኑበት የድንበር አካባቢ የተከሰተው ግጭት በስፍራው ባለ የሱዳን መንግሥት መዋቅር ውስጥ በተከሰተ ችግር ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ።

በድንበር አካባቢ ስለተከሰተው ጉዳይ በቢቢሲ የተጠየቁት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ "የተወሰኑ የሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ተሻግረው የአርሶ አደሩን ንብረት ለመውሰድ ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት ለመከላከል የተደረገ ክስተት ነው" ሲሉ ግጭቱን ገልፀውታል።ማክሰኞ ታህሣሥ 6/2013 ዓ.ም ምሽት ላይ የሱዳን ወታደሮች በድንበር አካባቢ ቅኝት አድርገው ሲመለሱ "ወደ ሱዳን ግዛት ገብተው አድፍጠው በነበሩ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል" ሲሉ የሱዳን መገናኛ ብዙሃንን በመጥቀስ ሮይተርስ ዘግቦ ነበር።

አምባሳደር ዲና ስለክስተቱ ጨምረው እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ "የአርሶ አደር ማሳ ውስጥ ገብተው አንዳንድ ነገሮችን የመውሰድ፣ ወደዚያ የማስፋፋትና ከሕግ አግባብ ውጪ የመሄድ ሁኔታ ስለታየ ይህንን ነገር መመለስ ስለሚያስፈልግ እርምጃ ተወስዷል" ብለዋል።ግጭቱን ተከትሎ የሱዳን መገናኛ ብዙሃን በጥቃቱ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን ጨምሮ አራት የሱዳን ወታደሮች መሞታቸውን ዘግበዋል።የሱዳን ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጦሩ ጎን መሆኑን እና ድጋፍ እንደሚያደርግ የዘገቡት መገናኛ ብዙሃኑ፤ የሱዳን ታጣቂ ኃይሎች የአገሪቱን ዳር ድንበር የመጠበቅ እና ማንኛውንም ጥቃት የመከላከል አቅም እንዳለው እምነታቸውን ገልጸዋል ብለዋል።

ዘገባው የቢቢሲ ነው፣ ተጨማሪ ለማንበብ:- https://bbc.in/3ao5Tmq

@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካው ጉግል ኩባንያ ከሥራ ስላባረራት የሰው ሰራሽ ልህቀት ተመራማሪዋ ትምኒት ገብሩ ማብራሪያ እንዲሰጥ 9 የአሜሪካ ሕግ አውጭ ምክር ቤቶች አባላት ጠይቀዋል፡፡ ሕግ አውጭዎቹ በጻፉት ደብዳቤ፣ ኩባንያው ለቀረቡበት ቅሬታዎች ምን እርማት እንደሚወስድ፣ የሰው ሰራሽ ልህቀት ምርምሩ ስነ ምግባር ደንብ አድሏዊ ላለመሆኑ እና ስለ ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ማብራሪያ እንዲሰጥ ነው፡፡ ትምኒት ከኩባንያው በተባረረችበት ሁኔታ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ሕግ አውጭዎቹ አልሸሸጉም፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ከአካባቢ ሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡

"ሁለቱ ሀገራት እንዲህ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ሁሌም የውይይትን አማራጭ የሚከተሉ በመሆናቸው ክስተቱ የሁለቱን ሀገራት ጥብቅ ትስስር አያላላውም" ብለዋል ጠቅላይ ሚስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት አስተያየት፡፡
"ክስተቱን እንደ መልካም አጋጣሚ ወስደው በማራገብ ልዩነትን ለማስፋት የሚጥሩ አካላት የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ትስስር ያልተረዱ ናቸው" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲግራትና ውቅሮ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት ዛሬ ማምሻውን ጀምሯል።

በህወሃት የወደሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች በአፋጣኝ ወደ አገልግሎት ለመመለስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሲሰራ ቆይቷል።

የውቅሮና አዲግራት ከተሞች የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና በመጠናቀቁ የፍተሻ ስራ ተከናውኖ ከተሞቹ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል።

የሽሬ፣ አክሱምና አድዋ ከተሞች ኃይል እንዲያገኙም በቅንጅት በመሰራት ላይ ነው።

[EEPCo]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎትን የዲጂታል አሰራር የማሻሻል ስራ ሊጀመር ነው።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከጀርመን የኢኮኖሚ ጉዳዮች እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር የኢትዮጵያ ፖስታ አገልገሎት የዲጂታል አሰራርን ለማዘመን በጋር ለመስራት ተስማምተዋል።በስምምነቱ መሰረት የጀርመን የኢኮኖሚ ጉዳዮች እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ድጋፎችን ያደርጋል።በሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያቤቶች በተደረሰው ስምምነት መሰረት የድጋፍ ስራው በየካቲት ወር መጀመሪያ የሚጀመር ይሆናል፡፡

በውይይቱ ላይ ከሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያቤት የስራ ሃላፊዎች ፣የጀረመን ፖስታ አገልገሎት እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልገሎት ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ኢትዮጵያ ያፀደቀችው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የኢኮሜርስ አገልግሎትን ማስፋፋት ነው፡፡ኢኮሜርስን ለመተግበር ደግሞ ዘመናዊ የፖስታ አሰራር ወሳኝ ድርሻ አለው፡፡ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎትን የዲጂታል አሰራርን የማሻሻል ስራ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂው ስኬት ወሳኝ ድርሻ አለው፡

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
በናይጀርያ ቦኮሐራም አግቷቸው ከነበሩ ተማሪዎች 344የሚሆኑት መለቀቃቸው ተሰማ!

በናይጀርያ ሰሜናዊ ምእራብ ከሳምንት በፊት ከካስቲና ት/ ቤት በበኮሐራም ታግተው ከነበሩ ተማሪዎች ውሰጥ 344 ተማሪዎች መለቀቃቸውን የናይጀርያ ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ።
ትናንት በተለቀቀ ቪዲዮ አጋቾቹ ተማሪዎቹን ለመልቀቅ መንግስትን ገንዘብ መጠየቃቸው የሚታወስ ሲሆን መንግስት ተማሪዎችን ለማስለቀቅ ገንዘብ ይክፈል አይክፈል በውል የታወቀ ነገር የለም።

አንደ አንዳንድ የናይጀርያ ጋዜጦች ዘገባ አሁንም ቢሆን አጋቾቹ ጋር ከ50 በላይ ተማሪዎች ይገኛሉ ሲሉ ፅፈዋል።

@YeneTube @FikerAssefa