YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አብርሃ ደስታ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ!

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ማካተቱን እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
"በክልሎች መካከል እየታየ ያለው የብሽሽቅ ፖለቲካ ስንጥቅ ሊደፈን የሚችለው ኃላፊነት የሚሰማው ውሳኔ እስከተወሰነ ድረስ ብቻ ነው" ሲሉ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ ተናገሩ።

"ቃላትን ከሰው ህይወት መጥፋት በላይ በሚመነዝር የፖለቲካ ገበያ ውስጥ ቀውስ መቆጣጠር የሚችል ገለልተኛ የአመራር አቅምና አሰላለፍ ይኖራል ብሎ ማሰብ ከብሳና ዛፍ አፕል ለመቁረጥ መሞከር ነው"፣ ስለሆነም የፌዴራል መንግስት የቀውስ ጊዜ አስቸኳይ አመራር ካላረጋገጠ በስተቀር ማንነትን ለይቶ የሚፈጸም ጥቃት ድህረ ትህነግ አገሪቷን የማትወጣበት ቅርቃር ውስጥ ሊያስገባት እንደሚችል ማወቅ አለበት።" ብለዋል።

[የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
"በክልሎች መካከል እየታየ ያለው የብሽሽቅ ፖለቲካ ስንጥቅ ሊደፈን የሚችለው ኃላፊነት የሚሰማው ውሳኔ እስከተወሰነ ድረስ ብቻ ነው" ሲሉ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብርሃም አለኸኝ ተናገሩ። "ቃላትን ከሰው ህይወት መጥፋት በላይ በሚመነዝር የፖለቲካ ገበያ ውስጥ ቀውስ መቆጣጠር የሚችል ገለልተኛ የአመራር አቅምና አሰላለፍ ይኖራል ብሎ ማሰብ ከብሳና ዛፍ አፕል ለመቁረጥ መሞከር ነው"፣…
ሃላፊው ይህንን ያሉት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ ታኅሣሥ 6 ባወጣው መግለጫ ‹‹በሕገ መንግሥት የተደራጀ ክልል ውስጥ ከፌደራል መንግሥት ዕውቅና ውጭ ገብቼ እዋጋለሁ ብሎ በተደጋጋሚ ዛቻ እና ማስፈራሪያ አዛል ቃላት ጭምር በመጠቀም መግላጫ መስጠት በሕዝቦች መካከል ግልፅ ጦርነት ማወጅ ነው›› ሲል በከሰሰ ማግስት ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
አንጋፋው የጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ በ84 አመት እድሜአቸው ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2013 ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ አትክልት ተራ በአዲሱ የገበያ ማዕከል ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በሰጡት መግለጫ ጃንሜዳ የሚገኘው ጊዜያዊ አትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ የገበያ ስፍራ የከተማው አስተዳደር ባዘጋጀው የገበያ ማዕከል እንዲዘዋወሩ በተወሰነው መሰረት የዕጣ ማውጣት ስርዓቱ ተጠናቆ ውል መዋዋል ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ተጠናቆ ከነገ ጀምሮ ጃንሜዳ የነበረው አትክልት ተራ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ በተገነባው የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ገበያ ማዕከል ተዘዋውሮ ስራ የሚጀምር መሆኑን ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አብርሃ ደስታ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ! የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ማካተቱን እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡ [Al-ain] @YeneTube @FikerAssefa
አቶ አበርሀ ደስታ ስለሹመቱ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ገለፀ!

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ሆኖ መሾሙን የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

አዲስ ዘይቤ ለአዲሱ ተሿሚ በመደወል ስለሹመቱ ጥያቄ አቅርቤ «ምንም የማውቀው ነገር የለም፡፡ የነገረኝም ሰው የለም» ብሎኛል ሲል ዘግቧል።

አቶ አብረሃ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር እና የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር ነው፡፡

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በዘር ለሚተላለፍ በሽታ አዲስ ሕክምና ሊጀምር ነው!

በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በተፈጥሮ ከእናት እና ከአባት በዘር የሚተላለፍ ‘ Cystic fibrosis’ የተባለ የመተንፈሻ አካላትን የሚጎዳ በሽታን ለመመርመር ሥራ ሊጀምር መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊንየም ሕክምና ኮሌጅ አስታወቀ።

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሕክምናውን ለመመርመር የሚያስችል ምንም ዓይነት የመመርመሪያ መሣሪያ አገር ውስጥ እንዳልነበር እና በአሁኑ ወቅት ግን መሣሪያውን ከመካከለኛው ምስራቅ ‘ Cystic fibrosis’ ማኅበር በእርዳታ መልክ ማግኘታቸውን እና በአሁኑ ሰዓትም መሣሪያው በሆስፒታሉ እንደሚገኝ አሳውቋል።

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የኢህዴሪ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈፀመ!

የቀድሞው የኢህዲሪ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የቀብር ስነ ስርዓት ነገ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ከጳጉሜን 5 ቀን 1979 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 29 ቀን 1982 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉ ናቸው።ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የተወለዱት ሐምሌ 7 ቀን 1937 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተለምዶ ቀጨኔ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ነው።

በተለያዩ የሥልጣን እርከኖች አገራቸውን ያገለገሉት ፍቅረሥላሴ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ (ኢሰፓ) አደራጅ ኮሚቴ እና የደርግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነበሩ።"እኛና አብዮቱ እና እኔና አብዮቱ” በሚል ርዕስ ሁለት መጽሐፍት ጽፈው ለአንባቢያን አድርሰዋል።ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የሁለት ሴት እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት እንደነበሩ የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
#FactCheck
Via @EthiopiaCheck

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ አቋረጠ፣ ግማሹን ቀነሰ ወዘተ የሚሉ መረጃዎች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ቼክ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ሀላፊ የሆኑትን አምባሳደር ዮሀን ቦርግስታምን በጉዳዩ ዙርያ አነጋግሯል።

አምባሳደሩ እንደሚሉት ህብረቱ ለኢትዮጵያ ከ2014 እስከ 2020 እአአ ላለው ግዜ 1.4 ቢልዮን ዩሮ መድቧል። ከዚህ ውስጥ 500 ሚልዮን ዩሮ ገደማው ለመንግስት በጀት ድጎማ ይውላል ያሉ ሲሆን 90 ሚልዮን ዩሮ ያክሉ የበጀት ድጎማ ግን አሁን ላይ ክፍያው እንዲዘገይ መደረጉን አረጋግጠዋል።

የአውሮፓ ህብረት ለምን 90 ሚልዮን ዩሮ የበጀት ድጎማውን እንዲዘገይ እንዳረገ ሲያስረዱ በትግራይ ክልል ካለው ሁኔታ ጋር እንደሚያያዝ ጠቅሰው "ሁሉም አካላት የሲቪሎች ደህንነትን እንዲጠብቁ፣ ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዲቆም፣ ስደተኞች ከለላ እንዲደረግላቸው፣ ቦታዎች ለሰብአዊ እርዳታ ክፍት እንዲሆኑ፣ ክልሉ ለሚድያዎች ክፍት እንዲሆን እንዲሁም መንግስት የጀመረው የተቋረጡ መገናኛዎች የመመለስ ስራ እንዲሰራ ህብረቱ ይፈልጋል" ብለዋል።

ህብረቱ ሙሉ ለሙሉ ድጋፉን እንዳቋረጠ እየተነገረ እና እየተፃፈ ያለው ግን ስህተት እንደሆነ ለኢትዮጵያ ቼክ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በ782 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ተባለ!

በኦሮሚያ ክልል ከሕወሓት ቡድን ጋር በመቀናጀት ግጭቶች ሲያስነሱና ግድያ እና ዝርፊያ ሲፈጽሙ ነበሩ የተባሉ 782 የኦነግ ሸኔ 'የጥፋት ኃይሎች' ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ባልቻ ሰሞኑን በሆሮ ጉዱሩ ወለጋና በሌሎች ዞኖች ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭት እንዲቀሰቀስ በማድረግ ግድያ በፈጸሙ የህወሓት ተላላኪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንም ገልጸዋል፡፡

ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ ህግን ማስከበር ባቃታቸውና ከኦነግ ሸኔ ቡድን ጋር በመሆን በንጹሃን ዜጎች ላይ የጥፋት ተግባር ሲፈጽሙ በነበሩ የመንግስት አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱም ተገልጿል፡፡

በተደረገው ሕግ የማስከበር ስራ ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቶ ጌታቸው ገልጸዋል፡ ከዚህ በኋላም ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶችን ለመቀስቀስ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ሃይሎችን የክልሉ መንግስት እንደማይታገስም አስረድተዋል፡፡

[ዋልታ]
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ አንድነት ፓርክ የሚወስደው መንገድ አዲስ በሚገነባ የውስጥ ለውስጥ የዋሻ መንገድ ግንባታ ምክንያት ከነገ ጀምሮ ለአንድ ወር እንደሚዘጋ ተገለፀ።

በታላቁ ቤተመንግስት ወደ አንድነት ፓርክ የሚወስደው መንገድ የውስጥ ለውስጥ የዋሻ መንገድ ግንባታ ስለሚጀመር አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።የታላቁ ቤተመንግስት እና አንድነት ፓርክን ያለ ትራፊክ መጨናነቅ መጎብኘት የሚያስችል የውስጥ ለውስጥ የዋሻ መንገድ ግንባታ ምክንያት ከነገ ህዳር 08/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር የተወሰኑ መንገዶች ዝግ እንደሚሆኑ ኤጀንሲ አስታውቋል።

ከሂልተን ሆቴል ተነስቶ ወደ ቀኝ የሚታጠፉ ተሸከርካሪዎች እና ከካሳንችስ ወደ 4 ኪሎ የሚያስወጣው መንገድ ከነገ ህዳር 08/2013 ዓ.ም ጀምሮ የሚዘጋ በመሆኑ አሽከርካሪዎችም ኢንተርኮንትኔታል ሆቴል፣ በንግድ ሚንስቴር፣ በሂልተን ሆቴል ወደ 4 ኪሎ እና ከካሳንቺስ መለስ አካዳሚ ሴቶች አደባባይ አቧሬ አድርገው ወደ 4 ኪሎ መውጣት እንደሚችሉ ኤጀንሲው መግለፁን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪ መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
አብን ሥልታዊ የዘር ማፅዳትና ማጥፋት እንቅስቃሴዎች እየታዩ ነው አለ!

የአማራና የአገው ሕዝብ ሲፈጸሙበት ከቆዩት ሰፊ ዘር ተኮር ጥቃቶች ሳያገግም፣ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ፣ በአማራ ጠልነት መንፈስ ሥልታዊ የዘር ማፅዳትና ማጥፋት እንቅስቃሴዎች እንደ አዲስ ተጠናክረው እየታዩ መሆኑን መገንዘቡን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አስታወቋል፡፡

ዘገባው የሪፖርተር ነው ተጨማሪ ለማንበብ: http://bit.ly/34mc078

@YeneTube @FikerAssefa
በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የሕወሃት የፈጸመው ጥቃት ለሀገሪቱ ከእንግዲህ አሳሳቢ እንደማይሆን መከላከያ ሚንስትር ቀንዓ ያዴታ ትናንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት መናገራቸውን ሪፖርተር አስነብቧል።

መያዣ የወጠባቸው የአማጺው ሕወሃት አመራሮች ለምን እስካሁን እንዳልተያዙ ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ተፈላጊዎቹ ያሉበት ቦታ የታወቀ ቢሆንም፣ ቀድመው ካዘጋጁዋቸው ጉድጓዶችና መደበቂያዎች በየጊዜው ስለሚቀያይሩ ይዞ ለማቅረብ አዳጋች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

‹‹የሕዝቡን ፍላጎት የምንረዳው ቢሆንም በእኔ ግምገማ ሠራዊቱ ቶሎ ይዞ አላቀረበም የሚለው ትችት የፈጠነ ነው፤›› ሲሉ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

‹‹ዝም ብሎ እንደተቀመጠ ዕቃ ከሆነ ቦታ አንስቶ ማምጣት አይደለም፡፡ ወይም ደግሞ ከሆነ ጓሮ እንደ ጎመንና ካሮት ተቆርጦ የሚመጣ ነገር አይደለም፤›› በማለት ለፓርላማ አባላቱ ሒደቱ አስቸጋሪና ጊዜ የሚፈልግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም ሥራው ሌት ተቀን እየተከናወነ እንደሆነና የሚፈለጉት ሰዎችም መያዛቸው እንደማይቀር አስታውቀዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከደምበል (ዝዋይ) ሐይቅና ከቆቃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ላይ እንቦጭን የማስወገድ ዘመቻ ነገ ይጀምራል!

ከደምበል (ዝዋይ) ሐይቅና ከቆቃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ላይ ለ30 የስራ ቀናት የሚቆይ እንቦጭን የማስወገድ ዘመቻ ከነገ ከታህሳስ 08/2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሔድ የውሃ ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በጣና ሐይቅ ላይ በተካሔደው ዘመቻ ላይ 85 በመቶ የሚሆነውን እንቦጭ ማስወገድ እንደተቻለ የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ በቀጣዩ ዘመቻ የጣና ተሞክሮ እንደሚተገበር አስታውቋል፡፡ከሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት እና ከኦሮሚያ ክልል መዋቅር ጋር በመሆን የእምቦጭ አረሙን በሰው ጉልበት ለማስወገድ በሞዴል ደረጃ በ980 ሄ/ር ቦታ ላይ የዘመቻ ስራው እንደሚሰራ ሚኒስቴሩ በፌስቡክ ገጹ ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች ከባለፈው እሁድ አንስቶ በተለያዩ ስፋራዎች ባደረሱት ጥቃት የአማራ ተወላጆች ሕይወት ማለፉን የአካቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።

በዞኑ አሙሩ ወረዳ ጃቦ ዶበን ቀበሌ ውስጥ ከስድስት በላይ ሰዎች ከትናንት በስትያ አንስቶ እስከ ትናንትናው ዕለት ድረስ በታጣቂዎች መገደላቸውን አቶ ያሲን የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ ለዶይቸ ቬለ በስልክ ገልጸዋል።ከሟቾቹ መካከል አምስቱ «በካራ እና በጥይት» መመታታቸውን በዛሬው እለትም ስድስት ሰዎች መቅበራቸውን ገልጠዋል።

አጋምሳ በተባለ እና ሀሮ በተባሉ ስፋራዎችም ጥቃቶች መድረሳቸውንና በሰው ላይ ጉዳት መድረሱን ነዋሪው አክለዋል።አሙሩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት እና ከዞኑ አስተዳዳሪ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በስልክ የተደረገው ጥረት አልተሳካም።ከምዕራብ ወለጋ የሸሹ የዐይን ምስክሮች እንደሚናገሩት ጥቃቱ በተደጋጋሚ የሚከሰት ነው።በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሁለት ቀናት ቢያንስ በሁለት ዞኖች ብቻ 19 ንፁሃን ዜጎች በታጣቂዎች ጥቃት ተፈፅሞባቸው መሞታቸውን የክልሉ መንግስት ዛሬ አረጋግጧል፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ዛሬ ለብዙኃን መገናኛ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ከትናንት በስቲያ እና ለሌት ለትናንት አጥቢያ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በ13 የአማራ ተወላጆች፤ በምዕራብ ወለጋ ነጆ ወረዳ ደግሞ በ6 የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የጅምላ ግድያ "ኦነግ ሸኔ" ባሉት ታጣቂ ቡድን ግድያ ተፈጽሟል፡፡በ782 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ ደግሞ እርምጃ መወሰዱን ሃላፊው መግለፃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

[ዶይቸ ቬለ]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 464 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,451 የላብራቶሪ ምርመራ 464 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,818 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 1,662 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 97,969 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 118,006 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ፣ ደሴ (ኮምቦልቻ) እና ሰመራ ተቋርጦ የነበረውን የበረራ አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ።መንገደኞች የአየር መንገዱን ድረ ገጽና የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም ግዜያቸውን በመቆጠብና በረራቸውን በማቀላጠፍ እንዲጓዙ አየር መንገዱ ጥሪ አቅርቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከግልገል በለሰ ማረሚያቤት «ለማምለጥ የሞከሩ» የተባሉ እስረኞች በፈጠሩት ረብሻ ቁጥሩ ያልታወቀ ሰዉ መሞቱ ተነገረ።ዶይቸ ቨለ የዓይን ምስክሮችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ በአካባቢዉ ከፍተኛ ተኩስ ይሰማ ነበር።ለማምለጥ የሞከሩ ከተባሉት እስረኞች ቢያንስ ሁለቱ ክፉኛ ቆስለዉ ሆስፒታል ሲደርሱ ሞተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ጥቃት ተፈጸመብኝ አለ!
 
የሱዳን ጦር ባወጣው መግለጫ የሀገሪቱ ታጣቂ ኃይሎች የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ እና በሱዳን ላይ የሚያስከትለውን መዘዝ በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። እነዚህም የስደተኞች ወደ ሱዳን ግዛቶች መግባት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው ድንበር ላይ ያለው አለመረጋጋት መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

የሀገሪቱ ታጣቂ ኃይል በኢትዮጵያ በነበረው ውጊያ የፌዴራል መንግሥትም ይሁን የትግራይ ተዋጊዎች የሱዳንን መሬት እንዳይጠቀሙ ሲጠብቅ መቆየቱን አንስቷል።ይሁንና ትናንት ማክሰኞ ታህሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ የኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች ወደ ሱዳን ግዛት ገብተው ጥቃት እንደፈጸሙ የሱዳን ጦር ገልጿል።

ሚሊሺያዎቹ 'ጃባል አቡጢዩር' በተባለ አካባቢ አድብተው እንደፈጸሙት በተገለጸው ጥቃት የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን እና በንብረትም ላይ ጉዳት መድረሱን መግለጫው ያትታል። የቆሰሉ ሰዎችም መኖራቸው ቢጠቀስም፣ ምን ያክል ሰዎች እንደተገደሉ እና እንደተጎዱ ግን አልተገለጸም።

ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በአካባቢው የነበሩ የሱዳን ታጣቂዎች እና ነዋሪዎች ለመከላከል ጥረት ማድረጋቸውን በመግለጽ ጦሩ ሀገሪቱን ከጥቃት እና ከወረራ ለመከላከል የገባውን ቃል እንደሚፈጽም አስታውቋል።ከሰሞኑ በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ አለመረጋጋት ስለመኖሩ ጭምጭምታዎች ቢሰሙም ሁለቱም ሀገራት በይፋ ችግሮች ስለመኖራቸው ሳይገልጹ ቆይተዋል። በሱዳን በኩል በሀገሪቱ ጦር ምሽት ላይ ስለቀረበው ወቀሳ በኢትዮጵያ በኩል ወዲያው የተሰጠ ምላሽ የለም።

Via Al-ain
@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት በትግራይ ክልል ባሉ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የህግ ታራሚዎችን ሰብስቦ በመቀሌ ከተማ ውስጥ በመልቀቅ ዝርፊያ እንዲፈጸም አድርጓል ሲሉ የመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተናግረዋል።“በበርካታ ወንጀሎች ተይዘው የነበሩ ሰዎች መቀሌ ላይ ተሰብስበው እንዲለቀቁ ስለተደረገ የግለሰቦች ሱቅ ጭምር እንዲዘረፉ ተደርጓል” ብለዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa