YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በትግራይ ክልል የተወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞንም እንዲደገም ተጠየቀ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ አባላት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ በአሶሳ ከተማ በተወያዩበት ወቅት ህወሓት የመተከልን የአስተዳደር መዋቅር በማፈራረስ በራሱ ቡድን ለመተካት ጥረት አድርጓል ብለዋል፡፡

በመተከል እየተፈጸመ የሚገኘው ግፍ በትግራይ ክልል በቅርቡ ከሆነው ጥፋት የማይተናነስ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ህወሓት በመተከል ባደረሰው ጥፋት ዋነኛ ተጠቂዎች ሴቶች እና ህጻናት እንደሆኑ በመጥቀስም ችግሩ በፍጥነት መቆም እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡የጥፋት ቡድኑ አመራሮችም በአስቸኳይ ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው አመልክተው በትግራይ ክልል የተወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ በመተከልም እንዲደገም መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሶማሊያ ከኬንያ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ገለጸች!

ሶማሊያ በአንድ ሳምንት ውስጥ ዲፕሎማቶቿ ከኬንያ እንዲወጡ አዛለች፡፡ሀገሪቱ እርምጃውን የወሰደችው የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ወደ ናይሮቢ ማቅናታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የቀብር ስነ ስርዓት ነገ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል፡፡

ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ከጳጉሜን 5 ቀን 1979 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 29 ቀን 1982 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉ ናቸው።

@YeneTube @FikerAssefa
ፑቲን በመጨረሻ ለባይደን የእንኳን ደስ አሉት መልዕክት አስተላልፉ!

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጆ ባይደንን ዛሬ በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ በመሆናቸው ለጆን ባይደን ከስድስት ሳምንት በኋላ እና የምርጫ ኮሌጁ በይፋ የባይደንን አሸናፊነትን ባረጋገጠ ከአንድ ቀን በኃላ ነው የእንኳን ደስ አሉት መልዕክት ያስተላለፉት፡፡

የምርጫው ውጤት ከታወቀ በጥቂት ቀናት ውስጥ ብዙ የዓለም መሪዎች አዲስ ለተመረጡት ፕሬዚዳንት ባይደን እንኳን ደስ አሉት ሲሉ፣ ፑቲን ግን ለአሸናፊው የእንኳን ደስ አሉ መልእክት ከማስተላለፋቸው በፊት ኦፊሴላዊ ውጤቱን መጠበቁ “ትክክል” ነው ብለው በወቅቱ ተናግረዋል ብሏል ሲኤን ኤ ኤን በዘገባው፡፡ቭላድሚር ፖቲን ለተመራጮ ፕሬዝዳንት ስኬት ተመኝተዋል፡፡በዓለም ላይ በአሁኑ ወቅት እየገጠሟት ያሉትን በርካታ ችግሮች እና ተግዳሮቶች ለመፍታት ልዩነቶች አሉ፡፡

ነገር ግን ለዓለም ደህንነት እና መረጋጋት ሲባል ይህንን ልዩ ሃላፊነት የሚሸከሙት ሩሲያ እና አሜሪካ እንደሚሆኑ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ፑቲን “በእኩልነትና በጋራ መከባበር መርሆዎች ላይ የተመሠረተ የሩሲያ-አሜሪካዊ ትብብር የሁለቱም አገራት ህዝቦች እንዲሁም የመላው ዓለም ማህበረሰብ ፍላጎቶችን የሚያሟላ ነው” ብለዋል ፡፡የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን "እኔ በበኩሌ ከእርሶ ጋር ለመተባበር እና ከእርስዎ ጋር ለመገናኘት ዝግጁ ነኝ" ብለዋል ፡፡

Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ወደ ትግራይ እየተላከ ካለው ድጋፍ 70 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ እንደሆነ የውጭ ጉ/ሚኒስቴር አስታውቋል።

ዛሬ ጠዋት ለተመድ የተለያዩ ኤጄንሲዎች በትግራይ ክልል ሁኔታ ላይ ማብራሪያ መሰጠቱ ተገለጿል፡፡በዚህም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተባበሩት መንግስታትን አመስግኗል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የልደት ካርድ ለሌላቸው ተማሪዎች ሊሰጥ ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ የልደት ካርድ ለሌላቸው ተማሪዎች ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር የልደት ካርድ ሊሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የልደት ካርድ አገልግሎት ዘርፍ ዳይሬክተር ግርማ መኮንን እንደተናገሩት የልደት ካርድ ማለት የአንድን ግለሰብ ትክክለኛ ዕድሜ ከማወቅም በዘለለ ለአንድ አገር የተስተካከለ የሕዝብ ብዛት ለማወቅ ፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሠሩ ፣ ልጁ መብቱ እንዲከበርለት የሚያስችለው ፣ ዜግነት የሚያገኙበት መሆኑን ተናግረዋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባህር ዳር እና መቀሌ ከተማዎች ለጊዜው ተቋርጦ የነበረውን የበረራ አገልግሎት እንደገና እንደሚጀምር ገለፀ። መንገደኞች በተለመደው መንገድ በመመዝገብ በረራዎቹን መጠቀም የሚችሉ መሆናቸውንም አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
👆👆

የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላን አስመልክቶ በወጣ የተዛባ መረጃ ላይ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ ማብራሪያ

@YeneTube @FikerAssefa
ተሿሚዎች፣ ተመራጮች እና የመንግስት ሰራተኞች እስከ ታህሳስ 20/2013 ዓ.ም ሀብታቸውን ሊያስመዘግቡ እንደሚገባ የአማራ ክልል ሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እንዲቻል ተሿሚዎች፣ ተመራጮች እና የመንግስት ሰራተኞች የሃብት ማሳወቅ እና ምዝገባ ስራ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰራ ይገኛል፡፡ እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ ከ65 ሺህ በላይ ሀብት አስመዝጋቢዎች የመጀመሪያ ደረጃ ምዝገባ ተከናውኗል፤ ከ15 ሺህ በላይ ደግሞ የዳግም ምዝገባ ተካሂዷል፡፡ሶስተኛው ዙር ምዝገባም መጀመሩን የአማራ ክልል ሥነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዝግአለ ገበየሁ ገልጸዋል፡፡ተሿሚዎች፣ ተመራጮች እና የመንግስት ሰራተኞች እስከ ታህሳስ 20/2013 ዓ.ም ሀብታቸውን እንዲያስመዝግቡ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በሳዑዲ ጊዜያዊ ስደተኛ ጣቢያዎች የታጎሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሁንም አያያዛቸው አስከፊ እንደሆነ ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። የስደተኛ ማቆያዎቹ በስደተኞች የተጨናነቁ ሲሆኑ፣ ጥበቃዎችም በስደተኞቹ ላይ ግርፋት፣ ግድያ እና ሌሎች የስቅየት ድርጊቶችን ይፈጽማሉ፤ ባለፉት ሁለት ወራትም 3 ስደተኞች በግርፋት ሕይወታቸው አልፏል- ብሏል ድርጅቱ በሪፖርቱ። ሳዑዲ ዐረቢያ በአስከፊ ሁኔታ የያዘቻቸውን ስደተኞች ባስቸኳይ እንድትለቅ እና እስከዚያው አያያዛቸው ሰብዓዊ ክብራቸውን በጠበቀ አኳኋን እንዲሆን ድርጅቱ በድጋሚ አሳስቧል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት አቋርጦት የነበረውን በረራ በዛሬው እለት በይፋ ጀመረ።

አየር መንገዱ በትግራይ ክልል በህወሃት ላይ ይወሰድ በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በረራውን አቋርጦ ነበር።ይሁን እንጂ የህግ ማስከበሩ ከተጠናቀቀ በኋላ በዛሬው እለት ምሽት ከአዲስ አበባ መንገደኞችን ጭኖ የመጀመሪያ
በረራውን በማድረግ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ኤር ፖርት ደርሷል።በኤርፖርት ለደረሱት መንገደኞችም የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አባል ጀነራል ዮሐንስ ገብረ መስቀልና የጊዜያዊ አስተዳደሩ አስተባባሪ አቶ ሃፍታይ ገብረ
እግዚአብሔር አቀባበል አድርገውላቸዋል።መቀሌ የደረሰው አውሮፕላን ሌሎች መንገደኞችን አሳፍሮ
ምሽቱን ወደ አዲስ አበባ መመለሱ ታውቋል።የኤርፖርቱ ሰራተኞችም በሙሉ በስራ ገበታቸው ላይ የተገኙ ሲሆን፣ በቀጣይ አየር መንገዱ በቀን ሁለት ጊዜ የሚያደርገውን በረራ ይቀጥላል በመባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍1
በደቡብ ክልል የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ፌስ ቡክ የተባለው ማህበራዊ መገናኛ ዘዴን በመጠቀም ሐሰተኛ መረጃዎችን አሰራጭተዋል ያላቸውን ሶስት ሰዎች በዘጠኝ ዓመት ፅኑ እስራት ቀጣ።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ ባዋለው ችሎት ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው በዘጠኝ ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን በፍርድ ቤት የቴፒ ምድብ ችሎት አስተባባሪ አቶ ሰራዊት ደስኖ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል ። የፅኑ እስራት ቅጣቱ የተወሰነው ያዕቆብ ተረፈ፣ ዕርቅ ይሁን መንግስቱ እና ሳሙኤል መኳንንት በተባሉ ተከሳሾች ላይ ነው። ግለሰቦቹ የእስር ቅጣቱ ሊወሰንባቸው የቻለው << የቴፒ ልጆች ብቻ >> ፣ << ለቴፒ እታገላለሁ >> እና <<ነፍጠኛው የቴፒ ጀግና በድጋሚ>> የሚል መጠሪያ ያላቸው ሀሰተኛ የፌስ ቡክ አካውንቶችን በመክፈት ያልተረጋገጡና ህዝብን የሚያሸብሩ መረጃዎችን ማሰራጨታቸው በማስረጃ በመረጋገጡ ነው ተብሏል።በመሆኑም ተከሳሾቹ የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ተላልፈው ተገኝተዋል ሲል የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማስታወቁን ዶይቸ ቬለ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የዕለት ደራሽ እርዳታ እየተዳረሰ ይገኛል ተባለ።

በመተከል ዞን በተመረጡ ቦታዎች ማለትም ማንዱራ፣ ጉባ፣ ድባጤ፣ ጋሊሴ፣ ቡለን፣ ዳንጉር እና ወንበራ ላይ ካምፖች ተመስርተው የዕለት ደራሽ እርዳታ በመከፋፈል ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ምንጭ-የሰላም ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
90 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከሊባኖስ ወደ ሀገራቸው ተመልሱ፡፡

ከመካከላቸውም ዓሥሩ ህጻናቶች መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡ ተመላሾቹን ወደ አገራቸ እንዲገቡ ለማድረግ ግሎባል አሊያን ከተሰኘ በኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎች የተመሰረተ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር መፈፀሙን ለማወቅ ተችሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት 2.3 ሚሊዮን የሚሆኑ ህፃናት ከሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ውጪ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት አስጠነቀቀ።

"ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ስደተኛና የተፈናቀሉ ናቸው።በአጠቃላይ ህፃናቱን መጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ሥራ ነው" በማለት የተባበሩት መንግሥታት የዓለም አቀፉ የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ኃላፊ አስታውቀዋል።ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሰብዓዊ እርዳታዎችን ለማድረስ ስምምነት ላይ ቢደረስም ድርጅቶቹ በክልሉ የእርዳታ አቅርቦት ለማድረስ አልተቻለም እያለ ነው።የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር የተደረገው ግጭት የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/ 2013 ዓ.ም እንደነበር ይታወሳል።የፌደራል መንግሥት ክልሉን እንደተቆጣጠረና ግጭቶች ቆመዋል ቢልም ህወሓት በበኩሉ በተለያዩ ግንባሮች ግጭቶች መቀጠላቸውን አስታውቋል።

"ለህፃናቱ የሚሰጠው እርዳታ አቅርቦት በዘገየ ቁጥር፣ ምግብ፣ በችጋር ለተጋለጡት ህፃናትን ለማደስ የሚያስፈልጉ አልሚ ምግቦች፣ ህክምና፣ ውሃ፣ ነዳጅና እና ሌሎችም አስፈላጊ ነገሮች እያጠሩ ወደ ከፋ ሁኔታ ያመራሉ" ብሏል ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ።አክሎም "አፋጣኝ፣ ዘላቂ፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማንንም ባላገለለ መልኩ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ለየትኛውም ቤተሰብ በያሉበት እንዲመቻች እንጠይቃለን" ብሏል ድርጅቱ።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀለኞች ቴክኖሎጂን በመጠቀም ፖሊስን እንደሚቀድሙ ተገለጸ!

ወንጀለኞች የተወሳሰበ እና ዘመናዊ ቴክሎጂዎችን በመጠቀም ፖሊስን እየተገዳደሩ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ፖሊስ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ቀድሞ መታጠቅና ወንጀልን ቀድሞ መከላከል ላይ ማተኮር አለበት በሚል ታቅዶ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት አቶ መስፍን አበበ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ በዓለምም ሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂን ተገን አድርገው በርካታ ወንጀሎች እየተፈፀሙ መሆናቸውን ጠቁመዋል።ይህም የፖሊስን ሥራ ፈታኝ እና በእጅጉ ጥንቃቄ በታከለበት ሁኔታ እንደሚሠራ እያስገደደ መሆኑን አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመታጠቅ ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም አሁንም ያለው በጣም ኋላቋር ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን፤ ‹‹ወንጀለኞች ቴክኖሎጂ በመታጠቅ በንፅፅር ይቀድማሉ። በሳይበር እና በሶሻል ሚዲያ የሚፈፀም ወንጀልም እየረቀቀ ነው። ለአብነት በቴሌ ላይ እየተሰሩ ያሉ ወንጀሎችን በሚሊዮኖች እና በቢሊዮኖች ኪሳራ አደረሱ ሲባል ይሰማል። ይህን ከወንጀለኞች ሰምተን እንጂ ቀድመን አውቀን የማስቀረት አቅም የለንም›› ብለዋል።

በመሆኑም እንደ ፖሊስ ቴክኖሎጂን ቀድሞ መታጠቅና ወንጀልን ቀድሞ መከላከል አለብን በሚል ታቅዶ እየተሠራ ነው ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራል መስፍን፤ ወንጀል ቢፈፀም እንኳን በፍጥነት ማወቅ አለብን ብለዋል። በቀጣይም በቴክኖሎጂ የትምህርት ክፍል የቴክኖሎጂ ፖሊሲንግ የመከፈት ውጥን ያለ ሲሆን በዚህም ምርምር ማድረግ፣ ባለሙያ የማፍራት እና ቴክኖሎጂን የመታጠቅ አስፈላጊነት ታምኖበት እየተሠራ ነው ብለዋል።

[ኢ.ፕ.ድ]
@YeneTube
ጓደኛዋን የገደለችው ግለሰብ 25 አመት ተፈረደባት!

በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ጎሮ ቀበሌ ውስጥ የሴት ጓደኛዋን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል የተከሰሰችው ሴት ላይ የ25 አመት ፅኑ እስራት ፍርድ ተላለፈ።

ሩሃማ ጀማል የተባለችው ግለሰብ ለ12 አመታት አብራት የኖረችውን ሟች ከዲራ አሊን ሀምሌ 7 ቀን 2012 ዓም ከሌሊቱ 5 ሰዓት ገደማ ባልታወቀ ምክንያት ሟች በተኛችበት በጥርሶቿ የሟችን ጆር፣ አፍንጫ ፣ጉንጯን እና ከንፈሯን ከነከሰቻት በኋላ በዱላ በመደብደብ እንዲሁም የሟችን ደም በመምጠጥ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሷን ፖሊስ በማስረጃ ማረጋገጥ ችሏል።

በወቅቱም ሟች በንክሻው ሰዓት ባሰማችው የድረሱልኝ ጥሪ ጎረቤቶቿ ፖሊስ በመጥራት በስፍራው ፖሊስ ሲደርስ ሟች ተዘርራ መመልከቱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ተጎጂዋን በፍጥነት በማንሳት ወደ አዳማ ሆስፒታል ቢያደርሷትም ነገር ግን ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ ወደ አዲስ አበባ ባልቻ ሆስፒታል ሪፈር እንደተደረገችና ባልቻ ሆስፒታል ለ15 ቀናት ህክምና ስትከታተል ቆይታ ህይወቷ መለፉን መረጃው አካቷል።

ከሳሽ አቃቤ ህግም በአሰቃቂ ግድያ ወንጀል የምርመራ መዝገብ በመክፈት ለአዳማ ከተማ ከፍተኛ ዞን ፍርድ ቤት አቀርቧል።ፍርድ ቤቱም በተከሳሽ ላይ የቀረበውን የሰው ምስክር እና የሰነድ ማሥረጃ በመመርመር ትናንት ታህሳስ 5 ቀን 2013 በዋለው ችሎት ተከሳሽ በፈፀመችው አሰቃቂ ግድያ በ25 አመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ መወሰኑን የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግኑኝነት ባለሞያ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለአዲስ ዘይቤ ገልፃለች።

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ባለ ኹለት እግር ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው!

የራሳቸውን ሰሌዳ ቁጥር ለጥፈው የሚንቀሳቀሱም ይገኙበታል።ማንኛውንም ባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪ በሰዓት ከ40ኪሜ እና ከዛ በላይ የሚጓዙ ያለ ሰሌዳ ቁጥር መንቀሳቀስ እንደማይችሉ በ2011 የወጣ መመሪያ እንዳለ እና አሁን ተሽከርካሪዎቹን በቁጥጥር ሥር እያዋሉ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለአዲስ ማለዳ አስታወቋል።

በሞተር ብቻ የሚሠሩ፣ በኤሌትሪክ ኃይል የሚሠሩ፣ በጸሐይ ኃይል የሚሠሩ እንዲሁም በፔዳል የሚሠሩትን ተሽከርካሪዎች በጠቅላላ በቁጥጥር ላይ እያዋሉ እንዳለና ይህም አግባብነት ያለው የሕግ ማስከበር ሥራ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ስጦታው አካለ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa