YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የተከዜ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰበትና ሃይል በማመንጨት ስራ ላይ እንደሚገኝ የጣቢያው ስራ አስኪያጅ ገለጹ፡፡

የጣቢያው ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ከማል አህመድ በስፍራው ለተገኙ ጋዜጠኞች እንደገለጹት፤ ከሰሞኑ መንግስት ከወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ ጋር ተያይዞ ማመንጫው ጉዳት ደርሶበታል መባሉ ሀሰት ነው፡፡የተከዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ አሁንም ሃይል እያመነጨ መሆኑን ገልጸው፤ በግድቡ ላይ የአውሮፕላን ጥቃት ደርሶበታል የሚለውን ዜና እንደማንኛውም ሰው በድምጸ ወያኔ እና በትግራይ ቴሌቪዢ የሰሙ መሆናቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

የተከዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ 300 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፤ በተጠቃሚ ማነስ ምክንያት አሁን ላይ 225 ሜጋ ዋት እያመነጨ መሆኑን ኢፕድ ዘግቧል፡፡ጁንታው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ ከተከዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የሚመነጨው ሃይል ወደ ብሔራዊ ቋት እንዳይጓዝ በማድረግ ለትግራይ ክልል ብቻ እንዲያገለግል ለማድረግ በክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ የሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ጉዳት ማድረሱንም ገልጸዋል፡፡

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ማእካላዊ ዞን የጭላ ወረዳ ከ140 በላይ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችና የጦር መሳሪያዎች ተገኙ!

በትግራይ ክልል ማእካላዊ ዞን የጭላ ወረዳ በአንድ አካባቢ ከ140 በላይ ከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎችና የተለያዩ ፈንጅዎችን ጨምሮ በርካታ የከባድ መሳሪያ ተተኳሾች ሰራዊቱ ባደረገው አሰሳ ተገኙ። ተስከርካሪዎቹ እና የጦር መሳሪያዎቹ ሕወሓት ደብቋቸው የነበሩ መሆናቸውን መከላከያ ሠራዊት በፌስቡክ ገጹ ገልጿል፡፡

በአካባቢው የተሰማራው የ11ኛ ክ/ጦር 3ኛ ብርጌድ አዛዥ ኮሎኔል ያሲን ኑርዬ እንደገለፁት፣ ህገወጡ ቡድን ሰራዊቱ አይደርስበትም ብሎ ባሰበው የጭላ ወረዳ ልዩ ስፍራው ሰረፍረፍ በተባለ አካባቢ ነው ስንቅና ትጥቅ የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎች የተገኙት፡፡የ11ኛ ክ/ጦር 1ኛ ብርጌድ አዛዥ ኮ/ል ያረጋል መኮንን በበኩላቸው ፣ አካባቢው “ከጁንታው” አባላት ሙሉ በሙሉ ነፃ በመውጣቱ ህብረተሰቡ ወደቀደመ የተረጋጋ ህይወቱ እየተመለሰ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኮትዲቯሩ ፕሬዝዳንት ኦላሳን ኦታራ በአለ ሲመት ላይ ለመገኘት ወደ ኮትዲቯር አቅንተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአፍሪካ የበሽታ የመከላከልና መቆጣጠር ማዕከል ግንባታ ዛሬ በይፋ መሰረት ድንጋይ ይቀመጣል!

በ90 ሺህ ሜትር ካሬ የሚያርፈው የአፍሪካ የበሽታ የመከላከልና መቆጣጠር ማዕከል ግንባታ በሃያ አምስት ወራት እንደሚጠናቀቅ ተጠቁሟል።የማዕከሉ ግንባታ ተጠናቅቆ ወደ ትግበራ ሲገባ የአፍሪካን የ2063 የጤና ዘርፍ መሪ ዕቅድ ለማሳካት ያግዛል ተብሏል።በመርሃግብሩ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና የቻይና ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ተገኝተዋል።

(Walta)
@YeneTube @FikerAssefa
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ መቀሌ ላይ ሆነው መግለጫ ሰጥተዋል

ከህወሐት መደምሰስ በኋላ በመላ ኢትዮጵያ ሰላም መስፈኑን የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ።

ላለፉት ሁለትና ሶስት አመታት ራሱን እያደራጃ በመላ አገሪቷ ግጭት እየለኮሰ የቆየው የህወሓት ጁንታ ከተደመሰሰ በኋላ በመላ ኢትዮጵያ ሰላም መስፈኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ዛሬ መቀሌ ላይ ሆነው በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

እንደ ጄኔራል ብርሃኑ ገለጻ፤ ጁንታው በመደምሰሱ የኢትዮጰያ ህዝብ እፎይታ አግኝቷል፤ በመላ አገሪቱ አሁን ሰላም ነው።

ቀደም ባሉት ሁለትና ሶስት አመታት በየቦታው እነሱ ግጭት ይለኩሱ እንደነበረ ያስታወሱት ጄኔራል ብርሃኑ፤ በአሁኑ ወቅት እነሱ በመመታታቸው ምክንያት ሁሉም አካባቢ እፎይታ ሰፍኗል ሲሉም ነው ያስታወቁት።

“የኢትዮጵያ ህዝብ ከእነዚህ መሰሪና በጣም አስቸጋሪ ሰዎች ተገላግሏል” ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ፤ የትግራይ ህዝብም ነጻ ወጥቷል፤ ከዚህ በሁዋላ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ማግኘት የሚገባውና በጁንታው ተቋርጠው የነበሩ የመሰረተ ልማት ስራዎች በፍጥነት ይከናወናሉ ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሙለር ሪልስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ አስረስ እና ብርጋዴር ጄኔራል አብርሃም መውጫ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

በእነ ሙለር ሪል ስቴት ባለቤት መዝገብ የተካከተ ተጠርጣሪም ከ81 ሚሊዮን ብር በላይ በአንበሳ ባንክ በኩል ለጽንፈኛው የህውሓት ቡድን ድጋፍ ለማድረግ ሲያዘዋውር እንደነበር መረጃ ማግኝቱን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ለመሬት በሚል በማህበር ተደራጅተው ከአንበሳ ባንክ በተጨማሪ በአራት ባንኮች ለፀረ ሰላም ቡድኑ ገንዘብ ሲያዘዋውሩ እንደነበር ነው የተገለጸው።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
በሽሬ የወርቅ መሸጫ ማዕከል የነበረ 369.92 ኪሎ ግራም ወርቅ በህወሓት ቡድን ስለመዘረፉ መረጃ ደርሶኛል ሲሉ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚኒስትር ታከለ ኡማ ተናገሩ፡፡

አቶ ታከለ 369.92 ኪሎ ግራም ወርቅ ከሽሬ የወርቅ መሸጫ ማዕከል በህወሓት ስለመዘረፉ በቦታው ላይ ካለ ባለሙያ መረጃ ደርሶኛል ሲሉ በማዕበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል፡፡መረጃውን የተናገረው ባለሙያ ስለ ዝርፊያው ዝርዝር መረጃ ሰጥተውናል ብለዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል ሰንደቅ አላማን ለመቀየር ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለመኖሩ ታወቀ!

አሁን በስራ ላይ ያለዉ የአማራ ብሔራዊ ክልል ሰንደቅ አላማን ለመቀየር ተጨባጭ ስራዎች እንዳልተጀመሩ ስማቸዉን መጥቀስ ያልፈለጉ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ገልፀውልኛል ሲል ለአዲስ ዘይቤ ዘግቧል፡፡

በማኅበራዊ ሚዲያ ተያያዥነት ያላቸው ወሬዎች ሲሰራጩ ቢቆዩም ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑት አመራር እንደተናገሩት የሰንደቅ አላማ ለዉጥ የህዝብም የአመራሩም ጥያቄ መሆኑን ጠቅሰው ይሁንና ለውጡን ለማለፍ የተለያዩ ሂደቶችን ማለፍ እንዳለበት አስረድተዋል። ስለ እነዚህ ሂደቶች ተጨማሪ መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡

በተጨማሪም በህገ-መንግስት እና በሰንደቅ አላማ ማሻሻል ዙሪያ ጥያቄዎች ቢነሱም ጉዳዩ በምክር ቤት ደረጃ ለዉይይት አለመቅረቡን አዲስ ዘይቤ በክልሉ ምክር ቤት ባደረገችዉ ማጣራት ለማወቅ ችያለው ብላለች።

ሆኖም እንደሃላፊዉ ገለጻ መሰረት ሰንደቅ አላማዉን የመቀየር ሀሳቡ እና ፍላጎቱም በክልሉ አመራር ዘንድ ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት የልማት ባለስልጣን /ኢጋድ/ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አስቸኳይ ጉባኤ ሊያደርግ ነው፡፡

ከትግራዩ ዘመቻ በኋላ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የመጀመሪያው የውጪ መሪ የሆኑት የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር እና የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር አብዳላ ሀምዶክ በትግራይ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ጉባኤ ለማድረግ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡ምንም እንኳን በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ማረጋገጫ ባይሰጥበትም፡፡ ሀምዶክ በአዲስ አበባ የነበራቸው ቆይታ ውጤታማ እንደነበር ለፈረንሳይ የዜና ወኪል አስታየታቸውን የሰጡ የሱዳን ከፍተኛ ሹም፤ ሁለቱ ሀገራት የሚያዋስናቸው ድንበርን ለማካለለ የተቋቁመውን የጋር ኮሚቴ ወደ ሥራ ለማስገባት መስማማታቸውንም ገልጸዋል፡፡የትግራዩን ዘመቻ ተከትሎ 50 ሺህ የመደርሱ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሱዳን የተሰደዱ ሲሆን ይህም በካርቱም ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሆነ ዘገባዎች ያሳያሉ፡፡

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል የአየር መሥመር ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡

የትግራይ ክልል የአየር መሥመር ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታውቋል፡፡በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ሂደትን ተከትሎ ተዘግቶ የነበረው የአየር ክልል ከዛሬ ታህሣሥ 5/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በሰሜን የኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ የሚያቋርጡ የአለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ የበረራ መስመሮች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታውቋል፡፡በመሆኑም አገልግሎት መሥጠት የሚችሉ ኤርፖርቶች በረራ ማስተናገድ የሚችሉ መሆኑን ኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ገልጿል::

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ገለልተኛ የብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት መመስረቱን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ምክር ቤቱ 16 ምሁራንን የያዘ ነው።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በትግራይ ክልል ጥቅምት 24 ሌሊት ላይ የቴሌኮም አገልግሎት እንዲቋረጥ ሲደረግ የሚያሳይ ከደህንነት ካሜራ የተወሰደ ተንቀሳቃሽ ምስል።

[የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማእከል]
@YeneTube @FikerAssefa
በማይካድራ የሰላማዊ ሰዎች ጅምላ ጭፍጨፋ በማስተባበር የተጠረጠረችው ታጎስ ገ/ትንሳዔ የተባለች ወታደር ዛሬ ፍርድ ቤት እንደቀረበች ፋና ብሮድካስት ዘግቧል። ተጠርጣሪዋ ጭፍጨፋው በተፈጸመበት አካባቢ በመዘዋወር ጭፍጨፋው ትክክለኛ መሆኑን ሰብካለች- ብሏል ፖሊስ። ጦር መሳሪያ ለአማጺው ሕወሃት በመሸጥ የተጠረጠሩት ጀማል አደም እና ዐለም ደስታ የተባሉ ነጋዴዎችም ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ለሁሉም ተጠርጣሪዎች ችሎቱ 14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ 473 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 1 ሺህ 335 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 778 የላብራቶሪ ምርመራ 473 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ። ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው እንደገለጹት 1 ሺህ 335 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡ እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 3 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ህወሓት ለአንበጣ መንጋ መከላከል ሥራ በሚል ወደ ትግራይ ክልል ድሮን አስገብቶ ለእኩይ ተግባር ሊያውል እንደነበረ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተናገረ፡፡

የኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ከዚህ ቀደም ህወሖት በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል በሚል ድሮን ለማስገባት ሞክሮ እንደነበር አውስተዋል።

በተደረገ ምርመራ ድሮኑ ለእኩይ ተግባር ሊውል እንደነበር የሚያሳዩ አመላካች መረጃዎች በመገኘታቸው ፈቃዱ መታገዱን ዋና ዳይሬክተሩ አስታውሰው ኤጀንሲው ይህን በማድረጉ ሊከሰት ይችል የነበረን ጉዳት ማስቀረት ተችሏል ብለዋል፡፡

ኤጀንሲው ሳምንቱን ሙሉ ለ24 ሰዓት እና ለ7 ቀናት በመስራትና የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን በመውሰድ በጥፋት ቡድኑ ሊቃጡ ይችሉ የነበሩ በርካታ የሳይበር ጥቃቶችን መከላከል እንደቻለም ዶ/ር ሹመቴ ተናግረዋል፡፡

ከጥቃቶቹ መካከልም ሀገርን ለማተራመስ የሚያስችሉ የሀሰት መረጃዎች ከማሰራጨት በተጨማሪ የደህንነት ሽፋን በሌላቸው ድረ-ገጾችን ላይ የተሞከሩ ጥቃቶች እንደሚገኙበትም ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

ቡድኑ በመንግስት የሚዲያ ተቋማት መሠረተ-ልማቶች ላይ ጉዳት በማድረስ ምንም ዓይነት የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ሥራ እንዳይሮር ጥረት ሲያደርግ እንደነበረ የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር መናገራቸውን ከኤጀንሲው ሰምተናል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ እየተዋቀረ ባለው የመንግስት አስተዳደር ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተካተቱ መሆኑን ዶ/ር ሙሉ ነጋ ገለፁ!

ከጁንታው መደምሰስ በኋላ በትግራይ ክልል እየተዋቀረ ባለው የመንግስት አስተዳደር ውስጥ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም እየተካተቱ እንደሆነ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አስታወቁ።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዶ/ር ሙሉ ነጋ እንደገለጹት፤ እየተዋቀሩ በሚገኙ አስተዳደሮች ብዙ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ ነው። መሳተፍም ብቻ ሳይሆን የሽግግሩ መንግስቱ አካል ሆነው እስከ ቢሮ ሃላፊነት ድረስ ይመራሉ።

እንደ ዶክተር ሙሉ ገለጻ፤ አረና፣ ትዴፓ እና አሲምባ የመሳሰሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በክልሉ ካቢኔ ውስጥ እንዲገቡ ተወስኗል። ከዚህ በፊት በነበረው የክልሉ ነበራዊ ሁኔታ እነዚህ አካላት በፖለቲካ አመለካከታቸው የተነሳ ሲታሰሩ፣ ሲገደሉና ሲሳደዱ ቆይተዋል።

የትግራይ ክልል ሕዝብ በአፈና ውስጥ የኖረ ሕዝብ ነው ያሉት ዶ/ር ሙሉ፤ “በአሁኑ ወቅት ግን ህዝቡ ከታች ጀምሮ እየተሳተፈ ነው፡፡ይህ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ እየሆነ ያለ ነው። ቀበሌ፣ ክፍለ ከተማ እና ሌሎቹንም የአስተዳደር እርከኖች ጭምር ሕዝቡ ነጻ ሆኖ ራሱ እንዲመርጥ ይደረጋል” ብለዋል፡፡

[ኢ.ፕ.ድ]
@YeneTube @FikerAssefa
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በዘር ጭፍጨፋ ወንጀል ሊጠየቁ ይገባል የሚል አቤቱታ ቀረበባቸው።

ከሁለት አመት በፊት የኖቤል ሰላም ሽልማት እጩ የነበረው አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት እና አክቲቪስት ዳቪድ ስቴንማን የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተሩን
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎች በማንነታቸው እንዲገደሉና አንዲሰደዱ ይሰሩበት ከነበረው መንግስት ጋር ተባብረዋል ለዚህም ሊጠየቁ ይገባል የሚል አቤቱታ ለአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ማስገባቱን አርቲ ሚዲያ ዘግቧል።

" ዶክተር ቴድሮስ ኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን በነበሩበት ጊዜ የደህነንነት ተግባራት ላይ ሚና የነበራቸው ሲሆን ይሄም የሰዎች መገደል ፣መታሰርና መገረፍን " ያጠቃልል ነበር ይላል ኢኮኖሚስቱ ለፍርድ ቤቱ ያስገባው አቤቱታ ።
" በህውሃት አባልነታቸውና በከፍተኛ የመንግስት ሀላፊነታቸውን ጉልበት አንዲኖራቸው ያገዛቸው ሲሆን በዚህ ሰዎች ያለ ክስ ሲታሰሩና ወደ እስር ቤት ሲታጎሩ የእሳቸው እጅ ነበረበት " ይላል የኢኮኖሚስቱ አቤቱታ።

አቤቱታው ዶ/ር ቴድሮስ በጋራ ሲሰሩበት ከነበረ መንግስት ጋር ፈፅመዋል ይበል እንጂ በተናጥል ይሄን ወንጀል እዚህ ቦታ የሚል አቤቱታ አላቀረበባቸውም።

አቤቱታው ተቃባይነት ካገኘ ዶ/ር ቴድሮስ በስራ ላይ እያሉ በአለም ዓቀፉ የመጀመሪያው ፍርድ ቤት የቀረቡ የመጀሪያው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣን ይሆናሉ።

ይሄ የሚሆነው ግን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ጠርቶ ያለመከሰስ መብታቸውን ካነሳ ብቻ ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት ረገጣ ከዚህ በፊት የቀረበባቸውን አቤቱታ ማጣጣላቸው ይታወሳል።

Fidelpost
@YeneTube @FikerAssefa
በአምስት ወራት ውስጥ 1 ቢሊዮን 356 ሚሊዮን 119 ሺ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል፡፡

የንግድ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግና የፀረ-ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴውን ለመጣጠር የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ባደረጉት እንቅስቃሴ ባለፉት አምስት ወራት ከሀምሌ 1 ህዳር 30/2013 ዓ/ም ግምታዊ ዋጋቸው 1 ቢሊዮን 356 ሚሊዮን 118 ሺ ብር የሆነ የወጪና የገቢ ኮንትሮባንዶችን መቆጣጠር መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
Audio
የፀሀይ ሪል እስቴት አልሚ ሚስተር ቼን ከቡና ባንክ የተበደርኩትን ገንዘብ የምከፍልበት የጊዜ ገደብ አላለፈም ሲሉ ለሸገር ነግረዋል፡፡

ቡና ባንክ በፀሀይ ሪል እስቴት አፓርትመንቶች ላይ የሀራጅ ሽያጭ ጨረታ ያወጣው እኔ ከሀገር እንደወጣሁ ስለ ተወራብኝ ነው ብለዋል፡፡

ሸገር በጉዳዩ ላይ ያነጋገረው ቡና ባንክ በበኩሉ ችግሩን ለመፍታት ከፀሀይ ሪል እስቴት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ቡና ባንክ ከፀሀይ ሪል እስቴት አልሚ ግማሽ ቢሊየን ብር እንደሚፈልግ ይታወቃል፡፡

ሸገር ኤፍ ኤም ሁለቱንም ጠይቆ ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ዘገባ አሰናድቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
"በመተከል ዞን የሰው ደም በየእርሻ ማሳው እየፈሰሰ ነው" ነዋሪዎችም የድርሱልን ጥሪ እያቀረቡ ነው!

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን አሁንም ሰው እየሞተ ነው፣ መፈናቀሉም ቀጥሏል፣ ነዋሪዎቹም የድርሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው።ቀደም ሲል ቀጣናውን ለማርጋጋት ከፍተኛ የሀገርቱ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ወደ ቦታው አቅንተው ነበር፣ አካባቢው በኮማንድ ፖስት እንዲተዳደርም ተደርጓል።ይሁን እንጂ አሁንም ሞት እና መፈናቀል እየተባበሰ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአብመድ ተናግረዋል።

በቡለን ወረዳ የሚኖሩ ዜጎች "የሰው ደም በየእርሻ ማሳው እፈሰሰ ነው፤ የሚመለከተው አካል ሊድርስልን ይገባል" ብለዋል።በዚህ ሁለት ቀን እንኳን ከጥቃት ለመዳን ሲሉ ከ300 በላይ ነዋሪዎች ቀያቸውን እንደለቀቁ ተናግረዋል።ነዋሪዎቹ ለአካባቢው የወረዳ አስተዳደር የድርሱልን ጥሪ ቢያሰሙም የሚመለከተው የጸጥታ አካል በፍጥነት ደርሶ ሕይወታቸውን መታደግ አለመቻሉንም ገልጸውልናል።ጉዳዩን በሚመለከት ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም እና ህዝብ ደኅንነት ቢሮ ቢደወልም ስልክ አይነሳም፡፡

[አብመድ]
@YeneTube @FikerAssefa