YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ከመጭው ሀገራዊ ምርጫ በፊት አባሎቹ እንዲፈቱ ጠየቀ!

ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በሀገሪቱ ዶሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ የበኩሉን ሲያበረክትና በተለያዩ ምርጫዎች ሲሳተፍ መቆየቱን አመለክቷል።ኦፌኮ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫን ለማካሄድ በምርጫ ቦርድ በኩል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ገልጾ፤ በመጭው ዓመት 2013 በሚካሄደው ምርጫም ለመሳተፍ እንደሚፈልግ አመልክቷል።ይሁን እንጅ ምርጫው በታቀደለት ጊዜ ተዓማኒነት ባለውና በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲካሄድ ከተፈለገ፤መንግስት ከምርጫው በፊት የታሰሩ አመራሮች እንዲፈቱ፣በመንግስት ሀይሎች የተዘጉ ፅ/ቤቶች እንዲከፈቱና በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት እንዲከበርና የፖለቲካ ምህዳሩ እንዲሰፋ ጠይቋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ለመከላከያ ሠራዊት እና ለተጎዱ ዜጎች ማቋቋሚያ የሚውል የ200 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ድጋፉን ለመከላከያ ሠራዊት የውጭ ግንኙነት ሓላፊ ኮሎኔል የኑስ ሙሉ አስረክበዋል።በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በክብር እንግድነት ተገኝተው ባንኮች ስላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።ድጋፉን ያደረጉት የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር አባል የሆኑ 18 ባንኮች ናቸው ተብሏል።

ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 100 ሚሊየን ብር ያበረከተ ሲሆን፣ አዋሽ፣ ዳሸን፣ አቢሲንያ፣ ሕብረት፣ ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እያንዳንዳቸው 10 ሚሊየን፣ ንብ ኢንተርናሽናል፣ ዘመን፣ አንበሳ ኢንተርናሽናል፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል እና ብርሃን ባንክ እያንዳንዳቸው አምስት ሚሊየን ብር እንዲሁም ወጋገን፣ ዓባይ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል፣ እናት፣ ቡና ኢንተርናሽናል እና ደቡብ ግሎባል ባንክ እያንዳንዳቸው 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በበኩሉ ለመከላከያ ሠራዊት የአምስት ሚሊየን ብር ድጋፍ አስረክቧል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ህወሃት ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የእዙ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ተለቀቁ።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ህወሃት ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የእዙ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ተለቀቁ። Via ENA @YeneTube @FikerAssefa
ህወሃት ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክሉ የእዙ የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ተለቀቁ።

የህወሃት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ለግብዣ በሚል ጠርቶ አግቷቸው ከነበሩት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያህል የሰሜን እዝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖችን የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በሰሩት የጋራ አሰሳ አስለቀቁ።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሃመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት የህውሃት ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ የእራት ግብዣ ብሎ ከጠራ በኋላ አፍኖ በመውሰድ አግቷቸው ቆይቷል።የጁንታው ሃይል መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖችን በሸሸበት ቦታ ሁሉ ይዟቸው ሲጓዝ ቆይቶ በቀድሞው የትጥቅ ትግል ወቅት የማዘዣ ቤዝ በነበረው አዴት በሚባል ቦታ አግቷቸው እንደነበርና የጁንታው ታጣቂ ሃይል መደበቁ በአሰሳና በጥናት ተደርሶበታል።

በዚሁ መሰረት የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ባደረጉት የጋራ አሰሳ እና እርምጃ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከጁንታው አስለቅቀዋል።ሰራዊቱ ያስለቀቃቸው 1 ሺህ ያክል የመስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች አሁን ላይ ሰራዊቱን መቀላቀላቸውን ሜጀር ጀነራል መሀመድ ገልጸዋል።ሰራዊቱ ከጁንታው ካስለቀቃቸው መካከል የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋደል ጀነራል አዳምነህ መንገስቴም ይገኙበታል።

የጁንታውን አባላት የማደን ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጹት ሜጀር ጀነራል መሀመድ፤ የመጨረሻ ምእራፍ በሆነው ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ምእራፍ የተደበቀውን ጁንታ አስሶ የመያዙ ስራ በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ የጋራ ቅንጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።ወደፊትም የጁንታውን ቡድንና ወንጀለኞቸን ለህግ የማቅረብና የማደን ስራ ውጤት በየጊዜው ለህዝብ እንደሚገለፅ ጨምረው ገልጸዋል።

(ኢዜአ)
@YeneTube @FikerAssefa
የልዩ ዕድል ሎተሪ ወጥቷል!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የልዩ ዕድል ሎተሪ ህዳር 3 0/2013 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡

👉1ኛ. 20,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር -------1705090
👉2ኛ.10,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር-----0729356
👉3ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር -----1206064
👉4ኛ. 3,000,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር -------0923071
👉5ኛ. 1,500,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር -------1877734
👉6ኛ. 750,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር -------0340162
👉7ኛ.300, 000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር ------1510522
👉8ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 20,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------- 31075
👉9ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------34772
👉10ኛ. 20 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-----5632
👉11ኛ.200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 2,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-------1071
👉12ኛ.200 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------345
👉13ኛ.2, 000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር-----065
👉14ኛ.20, 000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 300 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------87
👉15ኛ. 200,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 100 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር------ 5 ሆኗል፡፡

@YeneTube @FikerAsse
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ሰሞኑን ባደረገዉ ፍተሻ «ሕገ ወጥ» ያላቸዉን ከአራት መቶ የሚበልጡ ሽጉጦችና ሌሎች የጦር መሳሪዎች መያዙን አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ የኮሙኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ እንደተናገሩት ከሽጉጦቹ በተጨማሪ ክላሺንኮቭ ጠመንጃዎች፣ ቦምቦችና የጦር ሜዳ መነፅሮች ተይዘዋል።የጦር መሳሪዎቹን በመደበቅ ወይም በመያዝ የተጠረጠሩ ከ350 በላይ ሰዎችን ፖሊስ እየመረመረ መሆኑንም ኢንስፔክተር ቶሎሳ አስታዉቀዋል።የድሬዳዋዉ ወኪላችን የመሳይ ተክሉ ዘገባ መሳሪያዎቹ የተያዙበትን ትክክለኛ ቀንና ሥፍራ አልጠቀሰም።በሌላ በኩል እዚያዉ ምስራቅ ሐረርጌ ዉስጥ በየጊዜዉ መንገድ የሚዘጉ የመንግስት ተቃዋሚዎች መኖራቸዉን ኢንስፔክተር ቶሎሳ ገልጠዋል።የኢትዮጵያ መንግስት ያሰራቸዉን ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እንዲለቅ በመጠየቅ መንገድ የሚዘጉት ወገኖች አሁንም ለገና በዓል መንገድ ለመዝጋት ዝተዋል።የፖሊስ ኃላፊዉ ግን የተቃዋሚዎቹ ዓላማ «ከሽፏል» ባይናቸዉ።

[ዶቸ ቬለ]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በሚቀጥለው ሳምንት የመድረክ ቴአትሮችን ለተመልካች ማቅረብ ሊጀምር ነው!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የኮቪድ-19 መከላከል መመሪያን ተግባራዊ ባደረገ መልኩ በሚቀጥለው ሳምንት የመድረክ ቴአትሮችን ለተመልካች ማቅረብ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።ኮቪድ-19 ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎችን በመተግበር መድረኩን ለተመልካቾች ክፍት ለማድረግ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የቴአትር ክፍል ዳይሬክተር ደስታ አስረስ ገልጸዋል።ቴአትር ቤቱ በአንድ ጊዜ 1 ሺህ 200 ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ቢኖረውም አሁን ላይ በአንድ ጊዜ 300 ተመልካቾች ብቻ ይስተናገዳሉ ነው ያሉት።

“ተመልካቾች ወደ ቴአትር ቤት ሲመጡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማድረግ፣ ሳኒታይዘር በመጠቀም እና ተራርቆ በመቀመጥ እንዲመለከቱ ይገደዳሉ” ብለዋል።የመድረክ ትወና አቅራቢዎችም ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግና ከንክኪ በመራቅ ዝግጅታቸውን ለታዳሚ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።“ለቴአትር ሥራ የሚውሉ ቁሶችም ቴአትሩ ከመጀመሩ በፊት በሳኒታይዘር ይፀዳሉ” ብለዋል።የቴአትር መጀመር በኮቪድ-19 ምክንያት የተቀዛቀዘውን ባለሙያ ወደ ስራ የሚያስገባ መሆኑንም ገልጸዋል።ከታህሣሥ 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ቴአትር ቤቱ ለተመልካች ክፍት ሆኖ በሳምንት ሶስት ቴአትሮችን ለማሳየት ዝግጅት መደረጉንም ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

(ኢዜአ)
@YeneTube @FikerAssefa
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በመተባባር ያለማውን የሰው ሃብት አስተዳደር ሲስተም አስመረቀ!

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢ.መ.ደ.ኤ) ጋር በመተባባር ያለማውን የሰው ሀብት አስተዳደር ሲስተም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንዲሁም የኢ.መ.ደ.ኤ ዋና ዳይሬክተሮች ዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ እና አቶ ይድነቃቸው ወርቁ በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።
የተመረቀው የሰው ሀብት አስተዳደር ሲስተም የተቋሙን የሰው ሃብት አስተዳደር መረጃዎች በሶፍትዌር ለማደራጀት እና ፈጣን እና ጥራት ያለው የሰው ሃይል አስተዳደር ስርዓት እና ውሳኔ አሰጣጥን ለመተግበር የሚያስችል ሲሆን ተቋሙ የሚሰጠውን አጠቃላይ የሰው ሃይል አገልግሎት በአውቶሚሽን ለመስጠት የሚረዳም ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሀብታም አገራት ያላግባብ የኮሮናቫይረስ ክትባት እያከማቹ እንደሆነና ይህም ድሀ አገራት ክትባቱን የሚያገኙበትን እድል እንደሚያጠበው ተገለጸ።

ለክትባት ፍትሐዊ ስርጭት የቆመው "ዘ ፒፕልስ ቫክሲን አልያንስ" የተባለው ስብስብ እንዳለው፤ ወደ 70 የሚጠጉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራች ከአስር ዜጎቻቸው ለአንድ ሰው ብቻ ነው ክትባት መስጠት የሚችሉት።ኦክስፎርድ እና አስትራዜንካ በጥምረት ከሚሠሩት ክትባት 64 በመቶውን በታዳጊ አገራት እንደሚያከፋፍሉ አስታውቀዋል።ክትባቱ በፍትሐዊ መንገድ ለመላው ዓለም እንዲከፋፈል እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው።ኮቫክስ የተባለው ጥምረት 700 ጠብታ ለ92 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት ለማከፋፈል ተስማምቷል።

"ዘ ፒፕልስ ቫክሲን አልያንስ" ውስጥ አምንስቲ፣ ኦክስፋምና ሌሎችም የመብት ተሟጋቾች ይገኙበታል።ይህ ስብስብ እንዳለው፤ ከሆነ በቂ ክትባት ባለመኖሩ መድኃኒት አምራቾች በርካታ ክትባት እንዲመረት የቴክኖሎጂ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።ሁሉም ክትባቶች ፍቃድ ካገኙ፤ ሀብታም አገራች ለመላው ዜጎቻቸው ከሚበቃው ሦስት እጥፍ ጠብታ ለመግዛት ከወዲሁ መስማማታቸው ተጠቁሟል።

ለምሳሌ ካናዳ ለእያንዳንዱ ዜጋዋ አምስት እጥፍ ክትባት ለማግኘት አስቀድማ ትዕዛዝ አስተላልፋለች።ሀብታም አገራች ከመላው ዓለም 14% ብቻ ቢሆኑም 53% ክትባት ገዝተዋል።የኦክስፋም የጤና ፖሊሲ ኃላፊ አና ማርዮት "ማንም ሰው ሕይወቱን የሚያተርፍ ክትባት ሊከለከል አይገባም።ክትባት ማግኘት እና አለማግኘት በአገር የገንዘብ አቅም መወሰን የለበትም" ብለዋል።አሁን ያለው ሁኔታ ካልተለወጠ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባት ላያገኙ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።"ዘ ፒፕልስ ቫክሲን አልያንስ" ሁሉም መድኃኒት አምራቾች የኮቪድ-19 ክትባት ሂደትና ቴክኖሎጂውን በማጋራት ጠብታው በቢሊዮኖች እንዲመረት ጥሪ አቅርቧል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከሃገር የሸሹና በሃገር ውስጥ የተደበቁ በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን ለማስመለስ መዘጋጀቱን ገለፀ።

ተቋሙ እንዳሳወቀው በዋናነት በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን ለማስመለስ የሚያስችል የጥቆማ መቀበያ ስርአት እየዘረጋ ነው፡፡

ይህ እየተዘረጋ ያለው የጥቆማ መቀበያ ሰርአት በወንጀል የተገኙ ሃብቶችን በማጣራት ማስመለስ የሚያስችል ነው።

ተቋሙ በአሁን ወቅት በኢሜይል እና በነጻ የስልክ ጥሪ ጥቆማ መቀበል የሚያስችለውን አሰራር መዘርጋቱን አሳውቋል፡፡

ይህም በህገወጥ መንገድ በግለሰብ የተያዙ የህዝብ ሃብትን በሚሰጥ በወንጀል የተገኙ ሃበቶችን አጣርቶ ለማስመለስ ያሰችላል ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለሚዲያ አመራሮች ስልጠና እየሰጠ ነው!

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አዘጋጅነት ለአገር ውስጥ የሚዲያ አመራሮች በግጭት አዘጋገብ እና ለሰላም ከመቆም ጋር የተያያዘ ሥልጠና እና ውይይት እየተካሄደ ነው።የመገናኛ ብዙኃን ማሕበረሰብን ከማገልገል አኳያ ትልቅ ባለድርሻ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የምክክር መድረኩ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ካቢኔ በፈረንሳይ ጽንፈኛ እስላማዊነትን ይገታል ያሉትን አዲስ ሕግ አረቀቁ።

በቅርቡ ፈረንሳይ በጽንፈኞች ተደጋጋሚ ጥቃትን ስታስተናግድ ቆይታለች።ረቂቅ ሕጉ ሰዎች በሃይማኖት ጉዳይ የተሰማቸውን እንዲገልጹ የሚፈቅድ ከመሆኑም በላይ ታዳጊዎችን በቤት ማስተማር ላይ ጥብቅ ክልከላዎችን ይጥላል ተብሏል።የፈረንሳይ መንግሥት ሃይማኖትን ለማጥቃት ያወጣው ሕግ ነው በማለት በርካቶች ረቂቅ ሕጉን ተችተዋል።

የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንሰትር ጄን ካስቴክ ግን ሕጉ ሙስሊሞችን ከጽንፈኞች ነጻ የሚያደርግ ሕግ ነው ብለዋል።"የሪፐብሊካን መርሆችን" ይደግፋል የተባለው ረቂቅ ሕግ፤ በኢንተርኔት የሚፈጸሙ የጥላቻ ንግግሮች በጥብቅ እንዲመረመሩ ያዛል እንዲሁም በኢንተርኔት አማካይነት የሰዎችን ግላዊ መረጃ ማጋለጥን ይከለክላል።

ከሳምንታት በፊት የነብዩ መሐመድን የካርቱን ምስል ለተማሪዎቹ ማሳየቱን ተከትሎ የተገደለው ሳሙኤል ፓቲ፤ በኢንተርኔት አማካኝነት ዘመቻ ተፍቶበት ነበር ተብሏል።ፈረንሳይ ይህን መሰል ሕግ ለማውጣት ስታጤነው የቆየችው ጉዳይ ቢሆንም በቅርቡ በፈረንሳይ የደረሱ ጥቃቶች ሕጉ በፍጥነት እንዲወጣ አስገድደዋል።በቅርቡ በፓሪስ እና በመዲናዋ አቅራቢያ በጽንፈኛ ሙስሊሞች የተፈጸሙት ጥቃቶች የአገሪቱን ዜጎች አስቆጥተዋል።ፈረንሳይ ወደ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊሞች የሚኖሩባት አገር ናት።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
እነ ብርጋዴር ጀነራል ገብረመድህን ፍቃዴ (ወዲነጮ) ጨምሮ ሰባት የመከላከያ ከፍተኛ የጦር መኮነኖች ላይ መርማሪ ፖሊስ ባከናወነው በርካታ ማስረጃ ለወንጀሉ መፈጸም የሚያመላክቱ ማስረጃዎች በመኖራቸው 12 ተጨማሪ ቀናትን ፈቀደ፡፡

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በይደር ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ተጠርጣሪዎቹን አስቀርቦ መርማሪ ፖሊስ ሰፊ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎቹን መሰብሰቡን ነው የገለጸው፡፡ስለሆነም ቀሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልጋል ሲል ለመርማሪ ፖሊስ 12 ቀናት የፈቀደው ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎች ትናንት ባቀረቡት የስኳር ህመም መመርመሪያ የህክምና መሳሪያ ይግባልኝ ጥያቄ ተቀብሏል፡፡

በዚህም መሰረት መመርመሪያ ኪት እንዲገባላቸው አሊያም በማረፊያ ቤታቸው የህክምና ክትትል እንዲደረግላቸው አዟል።በተጨማሪም ችሎቱ ትናንት የቀረበው የባንክ ሂሳብ እግድ ይነሳልን ጥያቄያቸውን መርምሮ እግዱን ያገደው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እግዱን ያገደበት ምክንያት አስተያየቱን እንዲያቀርብ አዟል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
አብዛኞቹ የትግራይ ከተሞች እስከ እሁድ ድረስ መብራት እንዲያገኙ እየተሰራ ነው!

በትግራይ ክልል ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያዎችን ወደ ቀደመው አገልግሎታቸው እንዲመለሱ በማድረግ የክልሉ አብዛኞቹ ከተሞች እስከ መጪው እሁድ መብራት እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንዳስታወቀው በህወሓት አማካኝነት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የኃይል ማስተላለፊያዎች በአፋጣኝ ጥገና እየተደረገላቸው እንደሆነ እና አንዳንድ አካባቢዎች ላይም በከፊል መጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባለፈው አንድ ወር ውስጥ 370 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መደምሰሳቸው ተገለጸ!

የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ የህወሃት ጁንታ ተላላኪ በሆነው ኦነግ ሸኔ ላይ ሲወስድ በነበረዉ እርምጃ 370 መደምሰሳቸው ተገልጿል፡፡ 176 ታጣቂዎች ደግሞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲውሉ 154 ደግሞ በህዝቡ ተይዘዋል፡፡በዚሁ ወቅት ትጥቅና ስንቅ ለሽፍታዉ ሲያቀርቡ የነበሩ 183 የሕወሓት አባላትም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡በሎጂስቲክ በኩል 4 ብሬኖችን ጨምሮ 1,585 ጠመንጃዎች፣ 10,902 ጥይቶች፣ 605 ከብቶች፣ 353 ፍየሎች፣ 54 አህዮች፣ 48 ግመሎች፣ 682,680 ብር እና 204,000 ሀሰተኛ ገንዘብ መያዙንም ፓርቲው አስታውቋል፡፡

[OPP/Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የደረሰበትን ሪፖርት ይፋ አደረገ!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ በባህርዳር ፣ጎንደር ፣ዳንሻ ፣ሁመራና ማይካድራ በመገኘት በህወሓት ቡድን የተፈጸመውን ጥቃትና ያደረሰውን ውድመት እንዲሁም አሁን ያለበትን አጠቃላይ ሁኔታ ተመልክቶ የደረሰበትን ሪፖርት ይፋ አድርጓል። በተፈጸመው ጥቃት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች በጎንደር አካባቢ ተጠልለው እንደሚገኙና አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ቦርዱ ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታውቋል።

የህወሓት ቡድን የፈፀመው ተግባር አሰቃቂ፣ ጭካኔ የተሞላበትና በዓለም አቀፍ ወንጀል የሚያስጠይቅ ነው ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርዱ ገልጿል።ቦርዱ አሁን አካባቢዎቹ ላይ አንጻራዊ መረጋጋት በመኖሩ አስፈላጊ የሚባሉ መሰረታዊ ነገሮች እንዲሟሉና በቀጣይም ትኩረት ቢሰጥባቸው ያላቸውን ምክረ ሀሳቦች ለሚመለከታቸው አካላት ማስታወቁን ጠቅሷል።በዚህም የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ማቋቋምና ሰብአዊ ድጋፎችም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መርማሪ ቦርዱ በሪፖርቱ ማመላከቱን ነው የገጸው።

(ኢዜአ)
@YeneTube @FikerAssefa
ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል ስንዴ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዘ መሆኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በዛሬው እለትም ከ12 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴ የጫኑ 30 ተሽከርካሪዎች መቐለ ከተማ መግባታቸውንም ነው ኮሚሽኑ የገለፀው።በአዳማ እና ኮምቦልቻ ከሚገኙ መጋዘኖች የተጫነው ስንዴ በዕለት ደራሽ እርዳታ ትራንሸዠስፖርት በኩል ነው እየጓጓዘ ያለው።በቀጣይም ተጨማሪ የሰብአዊ ድጋፎች ወደ ትግራይ ክልል ለማድረስ እየተሰራ ነው መሆኑንም አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በትናንትናው እለት ወደ ሽሬ ከተማ በ44 ከባድ የጭነት መኪና የተላከው ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች መድረሳቸውንም ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

በአሁኑ ሰአትም እርዳታውን ለማከፋፈል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ይገኛል።በተመሳሳይ ባለፉት አምስት ቀናት ወደ አላማጣ ከተማ የተላከው የእለት ደራሽ እርዳታ በመከፋፈል ላይ መሆኑን ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው።

በተጨማሪም 15 ሺህ ሜትሪክ ቶን የእርዳታ እህል ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የብሔራዊ የአደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ አስታውቀዋል።በአሁኑ ወቅት እየተደረገ ያለው ድጋፍ በመንግስት ብቻ መሆኑን ጠቁመው፤ እርዳታው ሩዝ፣ ዱቄትና ሌሎች ምግብ ነክና ተያያዥ ቁሳቁሶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሕወሓት ታማኝ ታጣቂዎች ከከፈቱባቸዉ ጥቃት ያመለጡ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ባልደረቦች ወደ አማራ ክልል መግባታቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።

የሰሜን ጎንደር ዞን የበየዳ ወረዳ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት እስካሁን ድረስ ከጥቃቱ ያመለጡ 5000 ያክል ወታደሮች በየዳ ገብተዋል።የወረዳዉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ባለስልጣናት እንዳሉት የወረዳዉ መስተዳድር ለወታደሮቹ ጊዚያዊ ርዳታ እያደረገ አስተማማኝ ቦታ አስፍሯቸዋል።ወታደሮቹ በየዳ የደረሱት ከትግራይ ክልል የተከዜ በረሐን ጨምሮ ረጅሙን ርቀት በእግር ሲጓዙ ሰንብተዉ ነዉ።ባለፈዉ ጥቅምት 24 የትግራይ ልዩ ኃይል፣ሚሊሺያና ከሰሜን ዕዝ ያፈነገጡ የጦሩ ባልደረቦች ድንገት ከከፈቱባቸዉ ጥቃት ያመለጡ ከአንድ ሺሕ በላይ ወታደሮች ከዚሕ ቀደም አማራ ክልል ዋግ ሕምራ ዞን ሰቆጣ መግባታቸዉን ባለፈዉ ሳምንት ዘግበን ነበር።በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር በሕወሓት ታጣቂዎች ታግተዉ የነበሩ 1000 የሰሜን ዕዝ መኮንኖችን ማስለቀቁን የኢትዮጵያ መንግስት የሚቆጣጠራቸዉ መገናኛ ዘዴዎች ትናንት ዘግበዋል።መገናኛ ዘዴዎቹ የመከላከያ ሚንስቴር መግለጫን ጠቅሰዉ እንደዘገቡት የሕወሓት ታጣቂዎች አንድ ብርጌድየር ጄኔራልን ጨምሮ ባለፈዉ ጥቅምት ያገቷቸዉን 1000 ከፍተኛና መስመራዊ መኮንኖችን አዴት በተባለዉ የቀድሞ የሕወሓት ወታደራዊ ማዘዢያ ጣቢያ ሸሽገዋቸዉ ነበር።የኢትዮጵያ ጦር መኮንኖቹን ያስለቀዉ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በጋራ በከፈተዉ ዘመቻ ነዉ።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል የኢትዮ ቴሌኮምን የመቀሌ ጠባቂ በማባረር አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉ በደህንነት ካሜራ በተቀረፀ ምስል ተረጋግጧል ተባለ!

የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በጥቅምት መጨረሻና ህዳር መጀመሪያ ሳምንታት አካባቢ የስልክ አገልግሎትን በድምጽ ለመስጠት የሚያስችል ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ ተጀምሮ ነበር ብለዋል፡፡

በክልሉ የነበረውን የቴሌኮም አገልግሎት ያቋረጠው ኩባንያው ነው በሚል ሲሰጡ የነበሩ መላ ምቶች ነበሩ፡፡ አገልግሎቱ በምን ምክንያት ሊቋረጥ እንደቻለ ሳይታወቅም ቆይቷል፡፡

ሆኖም በኩባያው የተቋረጠ ነው የሚለውን መላ ምት ያስተባበሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ምክንያቱ መታወቁን ዛሬ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ አብራርተዋል፡፡

አገልግሎቱ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም መቀሌ ስራ ላይ የነበሩትን የኩባንያውን የጥበቃ ሰራተኛ በክልሉ ልዩ ኃይል እንዲባረሩ በማድረግ ነው መቋረጡንም ነው ወ/ሪት ፍሬሕይወት የገለጹት፡፡

ይህም መቀሌ ካለው የተቋሙ የደህንነት ካሜራ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡ከደህንነት ካሜራው የተገኘው ተንቃሳቃሽ ምስል የትግራይ ልዩ ኃይል አባላትን ደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች የመስሪያ ቤቱን ጥበቃ በሃይል በማስወጣት አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ሲያደርጉ ያሳያል፡፡ በዚህም መሰረት የክልሉ የቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፡፡

በተመሳሳይ በ14 ቀናት ውስጥ 39 ነጥብ 8 ቢሊዮን የሳይበር ጥቃቶች መፈጸማቸውንም ነው የገለጹት፡፡ ሆኖም ሀገር አቀፉን የቴሌኮም ስርጭት ለማቋረጥ በማሰብ የተፈጸሙትን እነዚህን ጥቃቶች ለማክሸፍ ተችሏል፡፡ሙከራዎቹ በሃገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የፋይናንስ፣ የትምህርት፣ የብሮድካስት እና ሌሎችንም ስርዓቶች ለማናጋት በማሰብ ጭምር የተፈጸሙ ነበሩም ብለዋል።

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኤርትራ ወታደሮች በትግራዩ ግጭት ተሳትፈዋል ብላ አሜሪካ እንደምታስብ ሮይተርስ ከአንድ የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣን እና ከ5 የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ዲፕሎማቶች ሰምቻለሁ በማለት ዘግቧል።ኤርትራ ጦሯን ስለማስገባቷ የአሜሪካ መንግሥት ግንዛቤ ያገኘው፣ ከሳተላይት ምስሎች፣ ከተጠለፉ የመልዕክት ልውውጦች እና ከትግራይ ክልል ከሚወጡ ሪፖርቶች እንደሆነ ዘገባው ገልጧል።የአሜሪካ መንግሥት እዚህ ድምዳሜ ላይ ስለመድረሱ…
የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የኤርትራ ወታደሮች በትግራዩ ውጊያ ተሳትፈዋል ለሚለው ውንጀላ ማስረጃ አላገኘንም ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ ጋር በነበረን ቆይታም ስለዚህ ጉዳይ ጠይቄያቸው ነበር ያሉ ሲሆን የኤርትራ ወታደሮች ፈፅሞ ድንበር እንዳልተሻገሩ ነግረውኛል ብለዋል፣ ወታደሮቹ የነበሩት ከዚህ በፊት በሰላም ስምምነት ለኤርትራ ተወስኖ ሳለ በውዝግብ ላይ በነበሩ አካባቢዎች ነው፣ ያንን አልፎ ወደ ኢትዮጵያ መሬት የገባ አንድም የኤርትራ ወታደር እንደሌለ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ እንደነገሯቸው ገልፀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa