YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አምባሳደር አዲስ ዓለም ባሌማ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ!

የቀድሞው የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አዲስ ዓለም ባሌማ (ዶ/ር) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ሴክሬታሪያት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ፡፡

የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ የነበሩት ኬሪያ ኢብራሂምም በቅርቡ እጅ መስጠታቸውን ያስታወሱት አምባሳደር ሬድዋን ሌሎች በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦችን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

በመንግሥት ኃይል እየታደኑ የሚገኙት የቀሩት የሕወሓት አመራሮች በጥቂት ቀናት ውስጥ በቁጥጥር ስር እንደሚውሉም አምባሳደር ሬድዋን ዛሬ ለውጭ ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ጠቁመዋል፡፡

የተመድ ሰራተኞች ያልተፈቀዱ ኬላዎችን አልፈው ሲሄዱ መንግሥት እንደተቆጣጠራቸውም ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባው👇👇👇https://am.al-ain.com/article/ethiopia-announces-that-tplf-s-ambassador-addis-alem-balema-is-arrested

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል የገዳ ሥርዓት ትምህርት መሰጠት ጀመረ!

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገዳ ሥርዓት ትምህርት በአፋን ኦሮሞ በሚያስተምሩ በሁሉም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መሰጠት ጀምሯል። የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥናት የገዳ ሥርዓተ ትምህርት እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት ቢሰጥ በሕዝቡ ማኅበረ-ኢኮኖሚ ውስጥ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን በማረጋገጣቸው ትምህርቱ መጀመሩ ተገልጿል።በዚህም ከ500 ሺህ በላይ የገዳ ትምህርት የመማሪያ መጽሐፍት እና የመምህራን መመሪያ ለትምህርት ቤቶች መከፋፈላቸውን የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ተሰማ ገልጸዋል።የመማሪያ መጽሐፍቱ እንደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ሐረሪ ያሉ የኦሮሚያ አጎራባች ክልሎች መከፋፋላቸው መገለጹን ኦቢኤን ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኤርትራ ወታደሮች በትግራዩ ግጭት ተሳትፈዋል ብላ አሜሪካ እንደምታስብ ሮይተርስ ከአንድ የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣን እና ከ5 የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ዲፕሎማቶች ሰምቻለሁ በማለት ዘግቧል።ኤርትራ ጦሯን ስለማስገባቷ የአሜሪካ መንግሥት ግንዛቤ ያገኘው፣ ከሳተላይት ምስሎች፣ ከተጠለፉ የመልዕክት ልውውጦች እና ከትግራይ ክልል ከሚወጡ ሪፖርቶች እንደሆነ ዘገባው ገልጧል።የአሜሪካ መንግሥት እዚህ ድምዳሜ ላይ ስለመድረሱ ግን፣ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ማረጋገጫ አለመስጠቱን ዘገባው አመልክቷል።የኤርትራ ወታደሮች በዛላንበሳ፣ ራማ እና ባድመ ከተሞች በኩል እንደገቡ ከምንጮች መስማቱን የገለጠው ዜና ወኪሉ፣ የወታደሮቹ ብዛት እና በጦርነቱ ስላላቸው ሚና ግን መረጃ እንዳልተገኘ አክሏል።ብሉምበርግም ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ፣ የኤርትራ ወታደሮች መቀሌ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች መታየታቸውን ዘግቧል።

[Reuters/Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያስተሳስረው የሀዋሳ ሞያሌ መንገድና የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል!

ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያስተሳስረው የሞምባሳ-ናይሮቢ -አዲስ አበባ- ኮሪደር ግንባታ አካል የሆነው የሀዋሳ ሞያሌ መንገድ እና የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል።የሞንባሳ ናይሮቢ አዲስ አበባ ኮሪደር ግንባታ አካል የሆነው እና የ500 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የሃዋሳ ሞያሌ መንገድ እና የሞያሌ የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ነው ነገ የሚመረቀው።የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ እንደተናገሩት፥ ነገ የሚመረቀው መንገድ 6 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጭ የተደረገበት ነው።

ወጪው በአፍሪካ ልማት ባንክ የረጅም ጊዜ የብድር ድጋፍ የተሸፈነ መሆኑንም አስታውቀዋል።መንገዱ በመስመሩ ለሚገኙ ከተሞች የእርሻ እና የኢንደስትሪ ዞኖች እና የቱሪስት መዳረሻወች በዘመናዊ መንገድ ከማስተሳሰሩ ባለፈ የኢትዮጲያ እና የኬኒያ መንግስት የሁለትዬሽ የንግድ ልውውጥ ግንኙነትን እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።በምረቃ ስነ ስርአቱ የሁለቱ ሃገራት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
"የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ-19 ክትባትን በማጓጓዙ ሒደት ለክትባቱ የሚያስፈልገውን የቅዝቃዜ መጠን በመጠበቅ በተለመደው ቅልጥፍና እና ሙያዊ ብቃት የኮቪድ መከላከያ ግብዐቶችን በማከፋፈል ያገኘውን አለም አቀፍ እውቅና እና አድናቆት ይደግመዋል" ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ተናግረዋል።

Via Ethiopian Airlines
@YeneTube @FikerAssefa
ጃንሜዳ ለጥምቀት በዓል ዝግጁ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስተወቁ።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ተብሎ አትክልት ተራ ወደ ጃንሜዳ እንዲዘዋወር መደረጉን ያስታወሱት ወ/ሮ አዳነች፤ "አሁን ጃንሜዳን መልሶ ለጥምቀት በዓል እና ሌሎች ማሀበራዊ አገልግሎቶች ዝግጁ ላማድረግ ቦታውን ማጽዳት እና ማስተካከል ወሳኝ መሆኑን በመረዳት ዛሬ ማለዳ በቦታው በመገኘት የጽዳት ስራ አስጀምረናል"ብለዋል።በቦታው ያሉ ነጋዴዎችም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በሃይሌ ጋርመንት እና በሌሎች አካባቢዎች ወደተዘጋጁ የገበያ ማዕከላት ይዘዋወራሉና ለዚህ ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም ከንቲባዋ አሳስበዋል።"አዳዲሶቹ የአትክልት ገበያዎች የሚርቋቸው የከተማችን ነዋሪዎች ይቅርታ እየጠየኩ በገርጂ፣ ጀሞ፣ አቃቂ፣ ጉለሌ እና ሌሎች አካባቢዎች ተጨማሪ የገበያ ስፍራ እያዘጋጀን መሆኑን እና ችግሩ ጊዜአዊ እንደሆነ ማሳወቅ እወዳለሁ" ሲሉም ተናግረዋል።ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለበዓሉ አከባበር በኢትዮጵያዊ ጨዋነት፣ በመተባበር፣ በመቻቻል እና መተሳሰብ መንፈስ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

(ኢ ፕ ድ)
@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ወደቀደመ ሰላሙና መረጋጋት እየተመለሰ ነው ሲሉ የትግራይ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁልሚካኤል አስታወቁ::

በክልሉ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ 50 ሚሊዮን ብር መመደቡን ገለጹ:: አቶ ነብዩ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በህወሓት ጁንታ ወደ አለመረጋጋት ገብቶ የነበረው የትግራይ ክልል አሁን ላይ ወደቀደመ ሰላምና መረጋጋቱ እየተመለሰ ይገኛል::

ችግሩ ከተፈጠረበት ዕለት ጀምሮ ጉዳዩ ሀገራዊ ጉዳይ ተደርጎ ከፍተኛ ርብርብ እንደተደረገበት እንደሚገኝ ያስታወቁት አቶ ነብዩ ፣ የተገኘው ውጤት ነገሮች በጋራ ሲሰሩ ምን ያህል አመርቂ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል ያሳየ ነው ብለዋል ::

አሁን ላይ በክልሉ መደበኛ ሕይወት እየተጀመረ ነው፤ የፈረሰው አስተዳደር በጊዜያዊ አስተዳደር እየተተካ ነው ፤ ሕዝቡም እየተወያየ ይምራኝ የሚለው እና ራሱ የመረጠው አካል እንዲመራው እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል::

በአክሱም፣ በሽሬ ፣ በአላማጣ በአጠቃላይ ምዕራብ ትግራይና ደቡብ ትግራይ መቀሌ ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ላይም ሕዝቡ እየተወያየ መሪውን እየመረጠና ወደመረጋጋት እየተመለሰ መሆኑን አብራርተዋል::አገልግሎት ሰጭ የመንግሥት ተቋማትን ወደ ስራ እየተመለሱ መሆኑንም ገልጸዋል::

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ከዛሬ ጀምሮ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለመድረግ ወደ ኬንያ እንደሚገቡ የተገለጸ ሲሆን፤ በጉብኝታቸው ኢትዮጵያ እና ኬንያን የሚወሰኑበትን የሞያሌና የላሙ ወደብን ይጎበኛሉ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በጉበኝታቸው ከኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በመሆን የሞያሌን የድንበር መተላለፊያን በር የሚከፍቱ መሆኑ ተነገረ ሲሆን፤ በተጨማሪም የሁለቱ አገራት መሪዎች በላሙ ግዛት ግዙፉን 'ላፕሴት' ፕሮጄክትን ይጎበኛሉ።ላፕሴት (LAPSSET) የተባለው ፕሮጀክት የሚለው ምህጻረ ቃል የላሙ ወደብ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ የትራንስፖርት መተላለፊያን የሚወክል ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ከምዕራብ ወለጋ ወሊሶ ወረዳ ጋዋ ቋንቋ ሰቀጀርቢ ቀበሌ የተፈናቀሉ ወገኖች አስፈላጊውን በቂ ድጋፍ እንዲደረግልን ሲሉ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ዳስ-ጉንዶ የሰፈሩ ወገኖች ገለጹ።

የአማራ ክልል ሴቶች ህፃናት ቢሮ ከዩኒሴፉ ጋር በመተባበር ከምዕራብ ወለጋ ወሊሶ ወረዳ ጋዋ ቋንቋ ሰቀጀርቢ ቀበሌ በማንነታቸው ተፈናቅለው ለመጡ ወገኖች በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ዳስጉ-ንዶ ቀበሌ በመገኘት ድጋፍ አደረገ።የአማራ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ የዩኒሴፍ አስተባባሪ አቶ በረከት ዩሃንስ በቂ ባይሆንም ለጊዜው ማረፊያ የሚሆን ድንኳንና ለሴቶች የንፅህና መጠበቂያ የሚሆን ቁሳቁስ ድጋፉ አድርገናል በቀጣይ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት እገዛ እንድደረግላቸው ጥረት እናደርጋለን ብለዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ተወካይ ሃላፊ አቶ አበበ ሲሳይ ከዚህ በፊት ከተለያዩ አጋር አካላት የምግብ አቅርቦትና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ ቢደረግም ችግሩን የከፋ ያደረገው ሴቶችና ህፃናት መኖራቸው ነው ብለዋል።አቶ አበበ አክለውም የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ እና ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እንዲሰጥ ቢደረግ የተሻለ ነው ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።ተፈናቃዮችም 131 አባውራ አጠቃላይ በቤተሰብ ደግሞ 227 ሲሆኑ 96ቱ ህጻናት ናቸው ። እየተደረገላቸዉ ላለዉ ድጋፍ አመስግነዉ በቀጣይ መንግስት በዘላቂነት መፍትሄ እንዲሰጠን ሲሉ የተፈናቀሉ ወገኖች ጠይቀዋል።

[የመተማ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን]
@YeneTube @FikerAssefa
በመቀለ ከተማ የሚገኘው ዋነኛው የህክምና ተቋም አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሁኔታ አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር አስታወቀ።

ሆስፒታሉ መደበኛ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉት የነበሩት አቅርቦቶች በከፍተኛ ደረጃ በመሟጠጣቸው ህክምና ለሚፈልጉ ሰዎች አገልግሎቱን ለመስጠት አዳጋች ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጿል።እስከ ትናንት ባለው መረጃ አይደር ሆስፒታል ድንገተኛና ህይወት አድን የሚባሉ ለምሳሌ ቀዶ ጥገናና የፅኑ ህሙማን ህክምና ለማቋረጥ መገደዱን የዓለም አቀፉ ቀይመስቀል የምሥራቅና የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ቃለ አቀባይ ክሪስታል ዌልስ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ቃለ አቀባይዋ ለዚህ እንደ ምክንያትነትም ያስቀመጡት መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችና ነዳጅ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በማለቃቸው ነው ብለዋል።የተፈጠረውንም ችግር ለመቅረፍም ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር እየተወያዩ መሆኑንም አስረድተዋል።

"የህክምና ግብአቶችን ጨምሮ አስፈላጊ የሚባሉ ቁሳቁሶችን አዲስ አበባ ካለው ክምችታችን ወደ መቀለ እንዲሄድ ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር በመነጋገር ላይ ነን። ይህንም በቅርቡ እንደሚፈፀም ተስፋ አለን" በማለትም ተናግረዋል።ከዚህ በተጨማሪ በመቀለ ከተማ ከፍተኛ የውሃ እጥረት እንዳጋጠመ ቀይ መስቀል በትዊተር ገፁ አስታውቋል።የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበርም ጋር በመሆን ውሃ በከተማዋ ማከፋፈል መጀመራቸውን የገለፀው ድርጅቱ ይህም ሁኔታ ዋነኛው የውሃ አቅርቦት መስመር ሥራ እስኪጀመር ድረስ ይቀጥላል ብሏል።"በእርግጠኝነት ይሄ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጠውን የማኅበረሰቡን ህይወት የማዳን ተግባር ነው። ሁኔታውም አስጊ ደረጃ ላይ ነው" የሚል መልዕክት ድርጅቱ አስተላልፏል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት በትግራይ ክልል ያለ ፈቃድ በተንቀሳቀሱ የተመድ ሠራተኞች ላይ መተኮሱን ተናገረ!

እሑድ ኅዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ከተፈቀዱላቸው የመንቀሳቀሻ ሥፍራዎች ውጪ በመሄድ ሦስተኛ ኬላ ሊጥሱ ሲሞክሩ የነበሩ የተወሰኑ የተመድ ሠራተኞች ላይ የፀጥታ ኃይሎች መተኮሳቸውንና ሠራተኞቹም መታሰራቸውን የገለጹት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ቃል አቀባይ ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር) ናቸው፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዳራሽ በወቅታዊ ጉዳዮችና በትግራይ ክልል ባለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥርጭት ላይ ከብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ጋር በመሆን መግለጫ የሰጡት ሬድዋን (አምባሳደር)፣ እነዚህ ሰዎች እንዲንቀሳቀሱ ከተፈቀደላቸው ሥፍራ ውጪ ለመንቀሳቀስ ባደረጉት ሙከራ ሁለት ኬላዎችን ጥሰው ከሄዱ በኋላ ሦስተኛውን ለመጣስ ሲሞክሩ፣ ተተኩሶባቸው እንደታሰሩና ከቆይታ በኋላ እንደተፈቱ አስታውቀዋል፡፡

‹‹ይኼ ሕግ አልባና ባለቤት አልባ አገር አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ያልተገደበ መንቀሳቀሻ የሚባል ነገር በፍፁም የለም፤›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አክለውም መንግሥት የሚመራው የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲኖር ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር ስምምነት ላይ የደረሰ ቢሆንም፣ መንግሥት ድጋፍ በሚሻ ጊዜ እነዚህን ድጋፍ የሚሰጡ ድርጅቶች ያሳትፋል ብለዋል፡፡ ‹‹መቼም ቢሆን እኛ በዚህ ሥፍራ መግባት የደኅንነት ሥጋት አለው ካልን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ሆነ ሌሎች ድጋፍ አድራጊዎች ለዚህ መገዛት ይኖርባቸዋል፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

አገሪቱ መንግሥት ያላትና በሰሜኑ ክፍል ብቻ ችግር የገጠማት ሆና ሳለ፣ ‹‹እነዚህ የተመድ ሠራተኞች መግባት የማይገባቸው ሥፍራ እንዳለ ተነግሯቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ጀብዳዊ አሰሳ ለማድረግ ሲሹ ነበር፡፡ ሁለት ኬላዎችን በመጣስ በፍጥነት ሲያሽከረክሩና እንዳይሄዱ ወደ ተነገራቸው ሥፍራ ሲገሰግሱ ነበር፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ይህች ኢትዮጵያ መሆኗ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በሺዎች ዓመታት የሚቆጠሩ የአገርነት ልምድ ያላት አገር ናት፡፡ ማንም እንዳሻው መሆን አይችልም፡፡ አትሂዱ ከተባሉ አለመሄድ ነው ያለባቸው፡፡ የመንግሥትን ማሳሰቢያ ችላ በማለት በማናለብኝነት መንቀሳቀስ አይችሉም፤›› ሲሉ አስረግጠዋል፡፡

ስለዚህም ‹‹የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከኢትዮጵያ ጋር ይተባበራል በሚል ነው እንጂ ውሳኔው የኢትዮጵያ ነው›› በማለት፣ ለዚህ ስኬት ግን ድጋፍና ዕርዳታ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ‹‹ነገር የምንመራውና የምናስተባብረው እኛ ነን፤›› በማለት አስታውቀዋል፡፡ ‹‹አንዳንዶች እንዳሻቸው መንቀሳቀስ አይችሉም፣ አይፈቀድላቸውምም፤›› ሲሉም አምባሳደሩ አሳስበዋል፡፡

ይኼ ክልከላ በዋናነት ከደኅንነት ጋር የተገናኘ መሆኑን በመግለጽ፣ በተለያዩ አካባቢዎች አሁንም ድረስ ተበትነው ያሉ የልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት ተኩስ እየከፈቱ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል፡፡ ስለዚህም ጋዜጠኞችም ሆኑ ሌሎች አካላት በክልሉ ያለ ገደብ መንቀሳቀስ የሚፈቀድላቸው ሙሉ ለሙሉ ሰላም ሲፈጠርና ደኅንነት ሲረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ሀረርጌ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 19 ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሷል።

አደጋው የተከሰተው ጭሮ ወረዳ ያብዶ ቦባሳ ቀበሌ በተለምዶ ኮሎሎ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነው።የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ጽ/ቤት ለአዲስ ዘይቤ እንደገለጸው አደጋው ያጋጠመው ከአዳማ ከተማ ወደ ጭሮ ሲጓዝ የነበረ ቦቴ ከህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።በዚህም 10 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ታውቋል።

በሶማሌ ክልል ባለፉት ሶስት ወራት በደረሱ የመኪና አደጋዎች የዛሬውን ጨምሮ 37 ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን 42 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የሆነ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡በክልሉ በንብረት ላይ ደግሞ በእነዚህ ወራት ብቻ ከ19.7 ሚሊዮን ብር በላይ በትራፊክ አደጋ ምክኒያት መውደሙ ተገልጿል፡፡

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
በመታደን ላይ የሚገኙ የሕወሓት አመራሮችን መቆጣጠር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ሌ/ጄነራል አበባው ታደሰ ከግንባሩ የጦር አዛዦች ጋር መከሩ!

ሌ/ጄነራል አበባው ታደሰ ፣ ከግንባሩ የጦር አዛዦቻቸው ጋር ፣ በቀጣይ በወንጀል የሚፈለጉ የሕወሓት መሪዎችን የማደንና በቁጥጥር ስር የማዋል ተልዕኮን በሚመለከት መክረዋል፡፡

በትግራይ በተወሰነ አካባቢ ላይ "ቀደም ብለው ባዘጋጁት ጉድጓድ የተደበቁትን ከሀዲዎች" አድኖ በቁጥጥር ስር ለማዋል በሚያስችል ዝርዝር ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የሐዋሳ-ሀገረ ማርያም-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ መንገድ እና የጋራ ፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክትን ዛሬ በይፋ መርቀዋል።

500 ኪ.ሜ ርዝመት ያለውና የሞምባሳ-ናይሮቢ-አዲስ አበባ ኮሪደር አካል የሆነው መንገዱ ኢትዮጵያን ከኬንያ የሚያስተሳስር መሆኑ ተገልጿል።በመንገዱ ምረቃ መርሐ ግብር ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል ባለሥልጣናት ታድመዋል።ይኸው የሐዋሳ-ሀገረ ማርያም-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ 6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል።
የሐዋሳ-ሀገረ ማርያም መንገድ የመጀመሪያው ኮሪደር 199 ነጥብ 6 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን፣ ግንባታው ከ3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በሦስት ተቋራጮች ግንባታው ተከናውኗል።

ከሀገረ-ማርያም-ያቤሎ ያለው ሁለተኛው ኮሪደር 192 ነጥብ 3 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው እና ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ነው።በአጠቃላይ የአዲስ አበባ-ሐዋሳ-ሀገረ ማርያም-ያቤሎ-ሜጋ-ሞያሌ መንገድ ግንባታ አዲስ አበባን ከካይሮ፣ ጋቦሮኒ፣ ኬፕ ታውን እና ኬንያ-ሞምባሳ የሚያገናኝ ከመሆኑም ባሻገር ደቡብ ሱዳንን-ከኬንያ ላሙ ወደብ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል መሆኑ ታውቋል።

በሌላ በኩል ሦስተኛው እና የኢትዮጵያን መሬት አቋርጦ የሚያልፈው የትራንስ-አፍሪካ አውራ ጎዳና የመጨረሻው ኮሪደር የሆነው 109 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የሜጋ-ሞያሌ መንገድ ግንባታ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተጠናቅቆ በይፋ ተመርቋል።በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቦረና ዞን ከምትገኘው ከሜጋ ከተማ ጀምሮ እስከ ሞያሌ የሚዘልቀው ይኸው የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል የወጪ እና ገቢ ንግድን የሚያጠናክር ነው ተብሏል።

በአጠቃላይ ከሐዋሳ-ሞያሌ የሚዘልቀው 500 ኪ.ሜ መንገድ እና የጋራ ፍተሻ ኬላ የጉምሩክ፣ የኢሚግሬሽን፣ የጤና እና የደረጃ ድርብርብ ፍተሻ በማስቀረት የጉምሩክ ሥርዓቱን ግልጽ፣ ቀላል እና ቀልጣፋ እንደሚያደርግ ታውቋል።ከዚህ ባለፈ በድርብርብ የፍተሻ አሠራር የሚባክነውን ጊዜ እና ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስቀር ነው ተብሏል።መንገዱ የኢትዮጵያ እና ኬንያን የወጪ እና ገቢ ንግድ በማቀላጠፍ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ ቀደም ሲል የተጎዳ ይዞታ እንደነበረው ተጠቁሟል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በቁጥጥር ስር ስለሚገኙት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ፖሊስ እና አቃቤ ሕግ በቅርቡ ማብራሪያ እንደሚሰጡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባቦት ቃል አቀባዩ ሬድዋን ሁሴን ገለጹ፡፡

የህወሓት የቀድሞ አመራሮች አዲስአለም ባሌማ (ዶ/ር) እና ኬሪያ ኢብራሂም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው ቃላቸውን እየሰጡ እንደሚገኙም ነው ቃል አቀባዩ ለውጭ መገናኛ ብዙሃን የተናገሩት።ግለሰቦቹ በቅርቡ ስለነበሩበት ሁኔታ መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ሬድዋን ገልጸዋል።በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ምን እንደተፈፀመ ተጨማሪ መረጃ ሊገኝ እንደሚችልም ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግሥት የገለልተኛ አጣሪ ቡድን ምርመራ ያድረግን ጥያቄ እንደማይቀበል አሳወቀ፡፡

መንግሥት ለመመርመር እንዳልቻለና እንደወደቀ ሲሰማው ብቻ ገለልተኛ አጣሪ ቡድንን እንደሚጋብዝ ነው የገለፀው፡፡ኅዳር 29 ለውጭ አገራት መገናኛ ብዙኃን ማብራሪያ የሰጡት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባቦት ቃል አቀባይ ሬድዋን ሁሴን የገለልተኛ አጣሪ ቡድን ለምን ወደ ኢትዮጵያ አይገባም የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡ምላሻቸው አጭር ሲሆን ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት እንደወደቀና እንዳልቻለ ሲሰማው ብቻ የገለልተኛ አጣሪ ቡድንን ለምርመራ ይጋብዛል፤ የትኛውም ወገን እኛ እስክንጠራው መጠበቅ አለበት የሚል ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት አገርን እንዴት መምራት እንደሚችል የሚያውቅ ነው በማለትም የቅኝ ግዛት እሳቤን ለማንፀባረቅ መሞከር ቅቡልነት እንደማይኖረው ነው ያሰመሩበት።መንግሥት በማይካድራም ሆነ በአጠቃላይ ትግራይ ክልል ስለነበረው ሁኔታ የአገሪቱንና የዓለም አቀፍ መርሆዎችና ደረጃዎችን ያሟላ ምርመራ ውጤትን ለፍርድ ቤት ያቀርባል፤ ያሉት ቃል አቀባዩ የትኛውም ወገን የምርመራ ሰነዱን ካየ በኋላ ጥርጣሬ ካለው መጠየቅ ይችላል እንጂ እኛ እንመርምርላችሁ የሚለው እንደማይታሰብ ነው ያሳወቁት፡፡

አሐዱ
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከሕወሓት እና ኦነግ ሸኔ ቡድኖች የጥፋት ተልእኮ ለመቀበል የተደራጀ አንድ ለ20 የሚል ቡድን በምርመራ ማግኘቱን አስታወቀ።

በኮሚሽኑ የወንጀል ምርመራ ቢሮ አገኘሁት ያለውን መረጃ ያብራራው በእነ ሜጀር ጄነራል ገብረ መድህን ፍቃዱ 7 ተጠርጣሪዎች እና በእነ ብርጋዴር ጄነራል አሊጋዝ ገብሬ 4 ተጠርጣሪዎች የተካተቱባቸውን የምርመራ መዝገቦች ለፍርድ ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው።ፖሊስ በእነ ሜጀር ጄነራል ገብረ መድህን ፍቃዱ መዝገብ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀደም ሲል በሰጠው የምርመራ ጊዜ ከተጠርጣሪዎች አገኘሁ ካላቸው መረጃዎች አንዱ ከሕወሓት አመራሮች ተልእኮ በመቀበል የሰሜን እዝ ኔትወርክ ተቋርጦ የመከላከያ ሠራዊቱ እንዲመታ ስለማድረጋቸው የሚያስረዱ የምስክሮችን ቃል መቀበል የሚለው ይጠቀሳል።

ተጠርጣሪዎቹ ከኦነግ ሸኔ አመራሮች ጋርም ግንኙነት ሲያደርጉ እንደነበር የሚያስረዱ ምስክሮችን ቃል ስለመቀበላቸውም ተሰምቷል።በሌላ በኩል ችሎቱ የመከላከያ አካዳሚ ኮሌጅ አመራር የነበሩ እነ ብርጋዴር ጄነራል አሊጋዝ ገብሬ ላይም መሰል የምርመራ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጿል።በሁለቱም የምርመራ መዝገቦች አዲስ አበባ ውስጥ በኅቡዕ ድብቅ የፖለቲካ እና የጥፋት አጀንዳ በሚያራምደው እና 1 ለ 20 በሚል በተቋቋመው ቡድን ውስጥ ዐሥራ አንዱም ተጠርጣሪዎች የነበራቸውን ተሳትፎ ፖሊስ ለችሎቱ ገልጿል።

በሌላ በኩል በሁለቱም የምርመራ መዝገቦች የሚገኙ ተጠርጣሪዎች የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን በማንሣት የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡ፖሊስም ዋስትናውን በመቃወም ተከራክሯል።የግራ ቀኙን ክርክር የሚመራው ችሎቱ በእነ ሜጀር ጄነራል ገብረ መድህን ፍቃዱ ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለነገ ታኅሣሥ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሲይዝ በእነ ብርጋዴር ጄነራል አሊጋዝ መዝገብ ላይ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀናት 12 ቀናት ፈቅዷል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በሦስት ተጨማሪ ቋንቋዎች ሥርጭት ሊጀምር ነው!

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ባስገነባው ስቱዲዮ ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ በትግረኛ፣በኦሮምኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑንም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሙሉቀን ሰጥየ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል ።

@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን በተነሳ ግጭት 83,131 ሰዎች ሲፈናቀሉ ከመቶ በላይ ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡

የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ለካፒታል ጋዜጣ ከነገረው መረጃ በተጨማሪ ከ40 በላይ ሰዎች ሲጎዱ 6,000 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡በድንበር ይገባኛልና ዞን ለመሆን ይገባናል በሚል በተነሳው ግጭት እስካሁን ከመቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ተጠርጥረው መታሰራቸውን ተገልፃል፡፡ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን የሰዎች መፈናቅልና ሞት በገለልተኛ ቡድን ለማጣራት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ወደ ቦታው እንደላከ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ተናግረዋል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
የ"ሲንቄ/ሲቆ" ባህላዊ ስርዓት ምንነና በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ያላትን ሚና የሚዳስስ መጽሀፍ ተመረቀ።

መጽሀፉን የመረቁት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው እና የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ከበደ ደሲሳ ናቸው።በመጽሀፍ ምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በኦሮሞ ብሔር ትልቅ ቦታ ያለው የገዳ ስርዓት የዲሞክራሲ ስርዓት ሲሆን በውስጡም የ"ሲንቄ/ሲቆ" ባህላዊ ስርዓት የሴቶችን ጉልህ ድርሻ ይዞ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲያስተላልፈው የቆየ ባህላዊ ክዋኔ መሆኑ ተገልጿል።

[ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር]
@YeneTube @FikerAssefa