ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የህወሓት ቡድን መሪዎች በእግራቸው መሸሽ ከመጀመራቸው በፊት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ከ40 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪዎች በመከላከያ ሰራዊቱ እጅ ገብተዋል ተባለ።
ቡድኑ ሰራዊቱን መቋቋም ተስኖት ወደ ገጠራማ ስፍራ በእግር መጓዝ ሲጀምር በታጣቂዎቹ በኩል ለማጥቃት ቢሞክርም እንዳልተሳካለት የ32ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ ተናግረዋል።ቡድኑ የመንገድ መሰረተ ልማት በሌለበት ከማይጨው 60 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ዴላ ወረዳ ከ40 በላይ የመንግስት እና በርካታ የግል ተሽከርካሪዎችን ይዞ ለመደበቅ ያደረገው ሙከራም መክሸፉን ነው ኮሎኔል ደጀኔ የተናገሩት።
ተሽከርካሪዎቹን ከፅንፈኛው ቡድን ሀይሎች አስጥሎ በቁጥጥር ስር ያዋለው ሰራዊቱ ባደረገው ፍተሻ በተሽከርካሪዎቹ ውስጥ መታወቂያ እና ፓስፖርቶች ተገኝተዋል።የተለያዩ ሰነዶቻቸውን ጥለው ከሸሹት መካከል የቀድሞው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት፣ የማይጨው አስተዳዳሪ የነበረው ሀፍቱ ኪሮስ እና ሌሎች የወረዳ አመራር የነበሩ ሰዎች ሰነድ ይገኝበታል።
የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ጥቆማ መሰረት ጌታቸው ረዳ በዴላ በኩል ከሸሸው ቡድን ውስጥ እንደሚገኝበትም ነው ኮሎኔል ፀጋዬ የገለጹት፡፡በመከላከያ ሰራዊቱ ከተያዙት ተሽከርካሪዎች መካከል ስድስቱ በአሻራ የሚከፈቱ እጅግ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ አራቱ ለኮሮና ወረርሽኝ መከላከል ስራ ከፌደራል መንግስቱ ለትግራይ ክልል የተበረከቱ አምቡላንሶች ይገኙበታል።ፅንፈኛው ቡድን ሲጠቀምባቸው የነበሩ የጭነት ተሽከርካሪዎች እና ቦቴዎችንም ሰራዊቱ ወደ ማይጨው ከተማ እንዲገቡ አድርጓል ብለዋል።በአሻራ የሚከፈቱትን ተሽከርካሪዎችም ከሞኤንኮ ጋር በመነጋገር ከአካባቢው ለማንሳትና ፍተሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አውስተዋል።
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa

ሰዓሊ ሚካኤል ቤተ ስላሴ ከዚህ አለም በሞት ተለየ!
ሰዓሊ እና ቀራፂ ሚካኤል ቤተ ስላሴ ፓፒዬ ማሼ (papier mâché) በተሰኘው ቅርፃ-ቅርፅ ሥራው ዓለም አቀፍ እውቅንናን ያገኘ ኢትዮጵያዊ የጥበብ ሰው ነበር።በወጥ የስዕል አይነት፣ የባለደማቅ ቀለም ውሁድ ስዕላትእና የሃውልት ቅርፅ ስራዎች ኢትዮጵያን ከሚያስጠሩት ቀደምት የጥበብ ስዎች አንዱ የነበረው አርቲስቱ ለረዥም አመታት በኖረባት የፓሪስ ከተማ በተፈጥሮአዊ ምክንያት በ69 አመቱ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
አርቲስት ሚካኤል የካቲት 8 ቀን 1943 በምስራቅ ኢትዮጵያ በምትገኘው ድሬ-ዳዋ ከተማ ውስጥ ነበር የተወለደው፡፡ሚካኤል የምድር ባቡር ተቀጣሪ ከነበሩት ከአባቱ ቤተ ስላሴ እና ከህክምና ባለሙያዋ እናቱ ተወልዶ 3 ዓመት ሲሞላው ወደ አዲስ አበባ ሄደ፡፡የመጀመርያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምርቱን የተከታተለው በሊሴ ገብረ ማሪያም ተምሯል፡፡ ከዚያም በሃያ አመቱ ወደ ፈረንሳይ በመሄድ ፊዚክስ እና ኬሚስትሪ ለሶስት አመት ተማረ፡፡
ከዚህ ፍፁም ወደተለየው ወደ ጥበብ ያዘነበለው እና ቅርፃ-ቅርፅ መስራት የጀመረው ደግሞ በ30 ዓመቱ ነበር፡፡የሰዓሊ ሚካኤል ሥራዎች በዋሽንግተን ዲሲ በብሔራዊ የአፍሪካ ሥነጥበብ ሙዚየም ውስጥ ይገኛሉ፡፡ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባው የአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስና የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ከስመ ጥር ኢትዮጵያን ጋር የጥበብ ስራዎቹንም አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡
[@addiszeybe]

ቤቶች ኮርፖሬሽን በሕገወጥ መሬት ወረራና ቤቶች ዕደላ ላይ ለመነጋገር ፈቃደኛ አለመሆኑን ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ!
የፌዴራል ዋና ዕንባ ጠባቂ ተቋም በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ አሠራር በርከት ያሉ የጋራ ቤቶች ስለመታደላቸውና የመሬት ወረራ ስለመከናወኑ በወጣው መረጃ ላይ፣ ምርመራ ለማድረግ ቢሞክርም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ኮርፖሬሽን ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለም ሲል ወቀሳ አቀረበ።
የፌዴራል ዕንባ ጠባቂ ተቋም ሪፖርቱን
መሠረት አድርጎ የችግሩን ሁኔታ
ለማጣራት ዋና ሥራ አስኪያጁን ለማነጋገርና መልስ ለማግኘት ቢጠይቅም፣ ምንም ዓይነት መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ሲል ዋና ዕንባ ጠባቂ እንዳለ ኃይሌ
(ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ: https://bit.ly/2Im5yFg

በአገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነበሩ አመራሮች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ!
ተጠርጣሪዎቹ መንግስት እና ህዝብ የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ወደ ጐን በመተው መቀመጫቸውን ትግራይ ክልል በማድረግ የህዋሃት ፀረ-ሠላም እና ፀረ-ህዝብ ከሆኑ ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል በጽንፈኝነት አስተሳሰብ በመነሣት በሀይል ወደ ስልጣን የመምጣት ፍላጎትን ካነገቡ ፀረ-ሠላም ሀይሎች ተልዕኮ በመቀበል በሀገር ውስጥ ሌሎችን በማደራጀት ሀገር የመበተን፣ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር እና ህገ-መንግስታዊ ሥርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ውስጥ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ መንገድ በመሳተፍ ህዝብ በመንግስት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው በማድረግ በአገር ክህደት እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩ በተለያዩ የአመራር ደረጃ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል፡-
1) ኮማንደር ሰለሞን አብርሃ ብስራት
2) ኮማንደር ሀይለማርያም ብርሃኔ ገ/ማርያም
3) ም/ኢ/ር ክብሮም ገብሩ ገ/እግዚአብሄር
4) ም/ኢ/ር አረጋዊ ገ/ሂወት አስፋዉ
5) ረ/ኢንስፔክተር ገዛኢ ገ/ሂወት ገ/ስላሴ
6) ረ/ኢንስፔክተር ተስፋ ኪሮስ ግደይ
7) ረ/ኢንስፔክተር አርአያ ገ/አናንያ ኪዳኑ
8)ረ/ኢንስፔክተር ሰለሞን ወላይ ወ/አብዝጊ
9) ዋ/ሳጅን ሀይላይ ወልዱ ገ/ማርያም
10) ዋ/ሳጅን ሀፍቱ ካህሳይ አብርሃ ናቸው።
በመሆኑም መላው የሃገራችን ህዝቦች በተለይም ደግሞ ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ፤ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት፤ የአገራችን የፖሊስ ሰራዊትና የደህንነት ተቋማት እነዚህን የጁንታው የህዋሃት የጥፋት ቡድን ተፈላጊዎች አባላት አድኖ ለህግ ለማቅረብ እየተደረገ ባለው ተግባር በያላችሁበት የድርሻችሁን እንድትወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ እያቀረበ፤ በቀጣይም የጁንታው ርዝራዥ ቡድን ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ የማድረግ ስራው አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እየገለፀ በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለህብረተሰቡ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአየር ሠዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል እያበለፀገ ያለውን መተግበሪያ በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ።
የባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር አቶ አብዮት ለሚታ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ መተግበሪያው ተሻሽሎ እየበለጸገ ያለው ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የአየር ሠዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል ከእጅ ንክኪ ነጻ ለማድረግ ነው።መተግበሪያውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ ምርጫ ቦርድና ብሮድካስት ባለስልጣን በጋራ እያዘጋጁት መሆኑንም ተናግረዋል።"የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ መገናኛ ብዙሃንና የተመደበውን የአየር ሠዓት ወደ ሲስተሙ በማስገባት መተግበሪያው ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው ቀመር መሰረት ለእያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲና ሚዲያ የተዘጋጀውን ሠዓት ይደለድላል" ብለዋል።
መተግበሪያው የሰው ጉልበት፣ ጊዜና ሀብት በመቆጠብ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎችና መገናኛ ብዙሀን በድልድሉ መሰረት መረጃቸውን በፍጥነት እንዲያገኙም ያስችላል።ቴክኖሎጂው መገናኛ ብዙሃን የአየር ሠዓትና የጋዜጣ አምድ ለማንና በየትኛው ሠዓት መስጠት እንዳለባቸው ጊዜ ሳይፈጁ ለማወቅ እንደሚያስችላቸውም ተገልጿል።መተግበሪያው በ2007 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን አስፈላጊው ማሻሻያ ተደርጎበት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ነው አቶ አብዮት የገለጹት።መተግበሪያው በ2007 ዓ.ም በአጭር ጊዜና በችኮላ በመዘጋጀቱ ያልተካተቱበት ክልሎችና ቋንቋዎች እንደነበሩ የኢዜአ ዘገባ አስታውሷል።

ጠ/ሚ ዐብይ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ወደ ኬንያ አቅንተው የሞያሌ የድንበር መተላለፊያ በርን ይመርቃሉ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከነገ በስቲያ ረቡዕ ጀምሮ ወደ ኬንያ ሊያቀኑ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ኬንያ የሚያቀኑት ለሁለት ይፋዊ የጉብኝት ቀናት ነው፡፡በመጀመሪያው ቀን (ረቡዕ) በመርሳቢት ግዛት ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተገናኝተው የሞያሌ የድንበር መተላለፊያ በርን ይጎበኛሉ፤ በይፋ መርቀው ይከፍታሉም ተብሏል፡፡መሪዎቹ በዚያኑ ቀን ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለውን እና የኬንያ፣ደቡብ ሱዳን እና ኢትዮጵያ የትራንስፖርት ፕሮጄክት አካል የሆነውን አዲሱን የላሙ ወደብን እንደሚጎበኙ የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ከዛሬ 2 ገደማ ዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እና ከቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር በመሆን የደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክን መመረቃቸው የሚታወስ ነው፡፡
[Al-ain]

ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ይገኙበት በነበረ ቢሮ ውስጥ ለውስጥ ከ300 ሜትር በላይ የኮንክሪት ዋሻ ተገኝቷል ሲል ፋና ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች የሚመዘገቡበት ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክ ማዕከል እንዳቋቋመ እና ወደ ሥራ እንዳስገባ የባንኩ የፋይናሻል ኢንክሉዢን ዳይሬክተር ተመስገን ዘለቀ ለአዲስ ማለዳ አስታወቁ።
ተንቀሳቃሽ ንብረቶች የሚመዘገቡበት ማዕከል ከባንኮች ብድር ለመውሰድ የሚፈልጉ ደንበኞች ያሏቸውን ተንቀሳቃሽ ንብረቶች በማስመዝገብ እና የተለየ መለያ ቁጥር ወይንም ኮድ ለንብረቱ ከተሰጠ በኋላ ባለንብረቶቹ ለመበደር ወደ መደበኛ ባንኮችም ሆነ ወደ ‹ማይክሮ›ፋይናንስ ተkማት ሲሄዱ የተመዘገበበትን ቁጥር ብቻ በመያዝ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።
[Addis Maleda]

"የፌደራል መንግስት ወይ ሀላፊነቱን ይወጣ አልያም ግዳጁን ለኛ ይስጠን" -ኮሚሽነር አበረ አዳሙ
<<ልዩ ኃይላችን የአማራ ልዩ ኃይል ተባለ እንጅ የኢትዮጵያ ልጅ (የኢትዮጵያ ሰራዊት)ነው፤
"ነፍሰጡር ሴት ሆዷ ተቀዶ ህፃኑ ወጦ የተበላበት፤
ሰው በቀስት ሆዱን ተመቶ አንጀቱ ተጎልጉሎ እዲወጣ የተደረገበት በአለም ላይ ከመተከል ውጭ የትም አልተፈፀመም፤
ይሄን ድርጊት የፌዴራል መንግስት እንዲያስቆም ወይም ግዳጁን ለኛ እንዲሰጠን እየወተወትነ ነው።
ሀገር እንዳይፈርስ፣መጥፎ ታሪክ እንዳይሰራ በማሰብ እንዲሁም ጥቂቶች ባጠፉት ሁላችንም እንዳንሳሳት እንጅ የምንታገሰው ቤኒሻንጉል እየተፈፀመ ያለው ግፍ አይደለም መሳሪያ ሌላም ነገር እንድትጠቀም የሚያስገድድ ነው።>>
የአማራ ፖሊስ ኮሚሸን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ የተናገሩት።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በኃይል ገመድና ኬብል ስርቆት መቸገሩን አስታወቀ!
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት የኃይል ገመዶች እና ኬብሎች ስርቆት መቸገሩን አስታወቀ። በዚህም ተገልጋዮቹ መንገላታቸውና ኮርፖሬሽኑም ለተደጋጋሚ ኪሳራ መዳረጉን ገለጸ።
የአገልግሎት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሙሉቀን አሰፋ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ፣የኃይል ገመዶች እና ኬብሎች በሌቦች ተቆርጠው በመወሰዳቸው ምክንያት ሰሞኑን ከመሿለኪያ ሚኒሊክ አደባባይ እና ከጦርኃይሎች ስቴዲየም ያለው መስመር በከፊል አገልግሎቱ ተቋርጧል። በዚህም ደንበኞቹ ለችግር ተጋልጠዋል።
እስካሁን 750 የሚደርሱ የኃይል ኬብሎች እና 15 የኃይል ማሰራጫ ገመዶች ስርቆት እንዳጋጠመ የገለጹት ኢንጂነር ሙሉቀን ፣ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ማበጀት ባለመቻሉ አገልግሎቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
[ኢ ፕ ድ]

የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት 23 የጸረ-ሠላም ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ!
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን 23 የጸረ-ሠላም ኃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የዞኑ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ኮሎኔል አያሌው በየነ፣ በዞኑ ዳንጉር ወረዳ ልዩ ስሙ ቁጥር 3 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሠላምን ሲያውኩ በነበሩ ኃይሎች ላይ በተወሰደው እርምጃ 23 ጸረ-ሠላም ኃይሎችን መደምሰሳቸውን ገልጸዋል።የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የክልሉ የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ ከተደመሰሱት የጽረ-ሠላም ኃይሎች በተጨማሪ ለጥፋት ሲጠቀሙበት የነበረ 3 የጦር- መሣሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋሉንም ኮሎኔሉ ተናግረዋል።
በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የጥፋት ቡድኑ በሠላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጥ በክልሉ መንግሥት ጥሪ መቅረቡን ያስታወሱ ሲሆን፣ በጥሪው መሠረት መጠቀም ካልቻለ በዋናው ጁንታ ላይ የተወሰደው የማያዳግም እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም አሳስበዋል።በጸረ-ሠላም ኃይሉ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ኮሎኔል አያሌው፣ ህብረተሰቡም እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የአካባቢውን ሠላም በተደራጀ መንገድ በመጠበቅ ረገድ የጀመረውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አገር አቀፍ ሲምፖዚየም መርሐግብር እየተካሄደ ነው፡፡
15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አገር አቀፍ ሲምፖዚየም መርሐግብር በአዲስ አበባ በመካሔድ ላይ ይገኛል።በመርሐግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮችና የብሔር ብሔረሰብ ተወካዮች እና የሐይማኖት መሪዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡መርሐግብሩ በትህነግ ቡድን ክህደት ተፈፅሞባቸው ለተሰው የሰራዊት አባላት የህሊና ጸሎት ተደርጎ ተጀምሯል።

የኩላሊት ዕጥበት ሕክምና ክፍያ በግል ሆስፒታሎች ጭማሪ አሳይቷል ተባለ
የኩላሊት ዕጥበት (ዲያሊስስ) ሕክምና የሚሰጡ ሦስት የግል ሆስፒታሎች ለአንድ ጊዜ ዕጥበት ከ 150 እስከ 800 ብር ጭማሪ ማድረጋቸውን የኩላሊት ህሙማን በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰለሞን አሰፋ ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።
ቤተዛታ ሆስቲታል 150 ብር፣ አዲስ ሕይወት ሆስፒታል 500 ብር እና ኮሪያ ሆስፒታል 800 ብር ለአንድ ጊዜ ዕጥበት እንደጨመሩ ሰለሞን ገልጸዋል። ይህ ማለት አንድ የኩላሊት ታካሚ በሳምንት ሦስት ጊዜ ሕክምናውን ሲያደርግ ከ450 ብር እስከ ኹለት ሺሕ 400 ብር ተጨማሪ ወጪ በአንድ ሳምንት ውስጥ ያወጣል ብለዋል።

በትግራይ ክልል የህግ የበላይነት በፍጥነት እንዲረጋገጥ የተመድ ዋና ጸኃፊ ጥሪ አቀረቡ!
ዋና ጸኃፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተነጋግረዋል፡፡የተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ ድጋፎችን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ዋና ጸኃፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተነጋግረዋል፡፡የተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ ድጋፎችን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የደራርቱ ቱሉ ተወዳዳሪ የነበሩት ራሳቸውን አግልለዋል እናም ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ተወዳደሪ ሆናለች።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
ለኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሁለገብ መረጃ የሚያቀርብ “የጉዞ ስንቅ” የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል፡፡
በአለም አቀፉ የስራ ድርጅት/ILO/ ተጋጅቶ ይፋ የደረገው መተግበሪያ ለስደተኞች የተሟላ መረጃ እንዲኖራቸው ያለመ ነው ተብሏል፡፡ስደተኞች መረጃ ባለማግኘታቸው ምክንያት ለእንግልት ይዳረጋሉ ያለው ድርጅቱ፣ አዲሱ የሞባይል መተግበሪያ ግን ከስደት ሕይወት ጋር በተገናኘ የሥራ ዕድል አማራጮችን፣ የየአገራት ህግጋትንና የሚደርሱ ችግሮችን በዘርፉ ከሚሰሩ ተቋማት እና ኢምባሲዎች ጋር ጭምር በማስተሳሰር መረጃዎች በማቅረብ ለስደተኞች እገዛ ያደርጋል ተብሏል፡፡መተግበሪያው በእንግሊዘኛ በአማርኛ በአፋን ኦሮሞ እና በትግረኛ ቋንቋዎች አገልግሎት እዲሰጥ ተደርጎ ነው የተዘጋጀው፡፡የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሞባይል መተግበሪያው ተደራሽ እንዲሆንም ይሰራል ብለዋል፡፡
[EBC]

የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ የተመሰረተባቸው የሙስና ክስ የሚሰማበት ጊዜ ለ2 ወር ከ15 ቀን መራዘሙን የሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ጃኮብ ዙማ ደቡብ አፍሪካን በመሩበት ዘመን በህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ህገወጥ የጦር መሳሪያ ንግድ ውስጥ እጃቸው ነበረበት በሚል እንደተከሰሱ አይዘነጋም።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
እነ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 5 ተከሳሾች ላይ ዐቃቤ ህግ ለምስክሮቼ ደህንነት ከመጋረጃ ጀርባ ይመስክሩልኝ ሲል ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆነ።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስት እና የፀረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የተከሳሾችን የክስ መቃወሚያ ተከትሎ ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ምላሽን ተመልክቶ ትዕዛዝ ለመስጠት ነበር ለዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው።ዐቃቤ ህግ ከዚህ በፊት በነበረው ቀጠሮ የማሰማቸው ምስክሮቼ ለደህንነታቸው ሲባል በምስክር ጥበቃ አዋጅ መሰረት ከመጋረጃ ጀርባ እንዲመሰክሩልኝ ሲል ማመልከቱን ተከትሎ ተከሳሾች ከመጋረጃ ጀርባ መባሉ ተገቢነት የለውም ሲሉ መቃወሚያ ማሰማታቸው ይታወሳል፡፡
ምስክሩ መስማትና ማየት እንደሚችል ማረጋገጥ ካልቻሉ የመስቀለኛ ጥያቄ ለማቅረብ አያስችልም፤ ምስክሩ ከመጋረጃ ጀርባ ሲመሰክር ተጨማሪ ሰነድ ይዞ እያነበበ ስለመሆኑ ምንም የምናውቀው ነገር አይኖርም ሲሉም ተቃውመው ተከራክረው ነበር።በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ምስክሮቼን ከመጋረጃ በስተጀርባ ላሰማ ጥያቄን ውድቅ አድርጓል።
በተያያዘ በችሎቱ ያልተገኙ 6ኛ እና 7ኛ ተከሳሾችን ከዚህ በፊት የፌደራል ፖሊስ አፈላልጎ ለችሎት እንዲያቀርብ በታዘዘው መሰረት ፖሊስ አድራሻቸውን ማግኘት አልቻልኩም በማለቱ ፍርድ ቤቱ ክሳቸው እንዲቋረጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል።ችሎቱ የተከሳሾቹን አድራሻ ማወቅ ባለመቻሉ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ክሳቸው እየተሰማ ያሉ ተከሳሾችን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታቸውን የሚያጣብብ በመሆኑ ነው ክሳቸው እንዲቋረጥ ያዘዘው።የተሻሻለውን ክስ ለመጠባበቅ ለታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
[FBC]

የተሽከርካሪ ምርመራ ሰጪ ተቋማት በትክክል እንደማይመረምሩ ተገለፀ
የትራንስፖርት ሚኒስቴር በአራት ክልሎች እና አንድ የከተማ አስተዳደር በተሸከርካሪ ምርመራ ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ተቋማት የሥራ ጥራት ችግር እንዳለባቸው እና በትክክል ላልተመረመረ ተሽከርካሪ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንደሚሰጡ ገለጸ።
በአገር ደረጃ 95 በመቶ የሚሆነው የተሽከርካሪ ምርመራ የሚያደርጉ ተቋማት አዲስ አበባ ፣ ኦሮሚያ ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሶች እና ሕዝቦች ፣ ትግራይ እና አማራ ክልል የሚገኙ ሲሆን 41 በሚሆኑ የተሽከርካሪ ምርመራ በሚያካሂዱ ተቋማት ላይ በትራንስፖርት ሚኒስቴር በተደረገው ጥናት በትክክል እንደማይመረምሩ ማረጋገጡን ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

በመተከል ጉምዝ ታጣቂዎች ግድያ ፈጸሙ!
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ቂዶ ቀበሌ ውስጥ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሰው ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት ከትናንት በስትያ አራት ሰዓት በጀመረው ጥቃት ምክንያት ከዐሥር በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉን አስረድተዋል።ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ስለ ጉዳዩ መረጃ ለማግኘት በስልክ ያደረግነው ጥረት ኃላፊው ስብሰባ ላይ ነን በማታቸው አልተሳካም።
የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት በዳንጉር ወረዳ 23 ጸረ-ሰላም የተባሉ ኃይሎች ላይ ርምጃ መውሰዱን ዛሬ የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል።በመተከል ዞን የድባጢ ወረዳ ቂዶ ነዋሪ የሆኑት አቶ ባቤን አስቻለው በአካባቢያቸው ሰላም ሰፍኗል ብለው መደበኛ የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ላይ ተሰማርተው ባሉበት የታጠቁ ኃይሎች ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጸዋል።ባለፈው እሁድ በጀመረው ጥቃትም የበርካቶች ሕይወት ማለፉን የጠቆሙ ሲሆን፤ እስከ ትናትንት ከሰዓት ድረስ የሰባት ሰዎች ስርዓተ ቀብር መፈጸማቸውን ተናግረዋል።
በቂዶ ቀበሌ በንግድ ሥራ ተሰማርተው እንደሚገኙ የነገሩን ሌላው የአካባቢው ነዋሪም የተለያዩ የሰላም ጉባኤዎችና ውይይቶች በመደረጋቸውን እንዲሁም ሰለም ሰፍነዋል ብለው ወደ ማሳቸው ያቀኑ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባ መሆናውን ጠቁመዋል።በደረሰው ጥቃት ምክንያትም የገቡበት ያልታወቀ ነዋሪዎች መኖራቸውን ገልጸው በታጣቂዎችም ተወስደው ሊሆን እንደሚችል አክለዋል።በስፋራው የሚንቀሳቀሱ ታጠቂዎችም ትጥቃቸውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመንግስት እንዲያስረክቡ በክልሉ መንግስት ጥሪ ሲቀርብ ነዋሪው በአካባቢው ሰላም ይሰፍናል የሚል እምነት እንደበረውም ተናግረዋል።ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ በድባጢ ስለነበረው ኹኔታ ተጨማሪ ማብራርያ እንንዲሰጡ በስልክ የተደረገው ጥረትም ኃላፊው ስብሰባ ላይ ነን በማለታቸው አልተሳካም።
[DW]