YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአማጺው ሕወሃት አመራሮች እንደተደበቁባት የሚነገርላት ወርቅ አምባ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ኮማንዶዎች እንደተከበበች የብሄራዊ መረጃ እና ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ጽፈው ተመልክተናል። በትግራይ ክልል ቆላ ተምቤን ውስጥ በምትገኘው ወርቅ አምባ ከተማ፣ የአማጺው ሕወሃት ሊቀመንበር ደብረ ጺዮን ገ/ሚካዔል፣ የሥራ አስፈጻሚ አባሉ ጌታቸው ረዳ፣ የቀድሞዎቹ አመራሮች ስብሃት ነጋ እና አባይ ጸሃዬ እንዲሁም ከመከላከያ ሠራዊቱ ሰሜን ዕዝ የከዱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እንደሚገኙ ተረጋግጧል- ብለዋል ተመስገን። የሕወሃት አመራሮች መጀመሪያ ከመሸጉባት ሀገረ ሰላም ከተማ ወደ ወርቅ አምባ የሸሹት ሰሞኑን እንደሆነ ታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያዊው የማር ወይን ነጋዴ የ750 ሺህ ዶላር አሸናፊ ሆነ!

በካሊፎርኒያ ሶኖማ ግዛት የሚኖረው አየለ ሰለሞን የጠጅ ባህል በማጥናት የጠጅ ጣዕም እና ሽታ ያለው የማር ወይን መጥመቅ ችሏል፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታትም ቢ ዲቫይን የተሰኘውን የማር ጠጅ በመሸጥ እና በዓለም ዙሪያ በማስተዋወቅ ላይ ቆይቷል፡፡ የኮቪድ 19 ወረሽኝ ከፍተኛ ወደሆነ ኪሳራ እና የገበያ መቀስዛቀዝ ያደረሰበት ሲሆን ይህን ችግሩን ለመቅረፍም በአሜሪካ ግዙፉ በሆነው የንግድ ውድድር ሻርክ ታንክ ውስጥ በምሳተፍ 750,000 ዶላር አሸናፊ ሆኗል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
በቆላ ተንቤን የሚገኘው የህወሓት የመጨረሻ ምሽግ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ተባለ!

በቆላ ተንቤን የሚገኘው የ'ጁንታው' የመጨረሻ ምሽግ በሀገር መከላከያ ሰራዊት በሶስት አቅጣጫ ተከቦ እርምጃ እየተወሰደበት እንደሚገኝ ተገለጸ።በቆላ ተምቤን የ'ጁንታው'ን አመራር ለመያዝ የሚደረገውን ዘመቻ እየመሩ ያሉት በመከላከያ ሰራዊት የ31ኛ ክፍለ ጦር ምክትል ኦፕሬሽን አዛዥ ኮሎኔል ሻምበል በየነ እንደገለጹት፤ ከመቀሌ ቢሮው ለቆ የሸሸው የ'ጁንታው' አመራር በቆላ ተንቤን የመጨረሻ ምሽጉ ላይ ይገኛል።

የመከላከያ ሰራዊትን የጁንታውን የመጨረሻ ምሽግ በተለያዩ አቅጣጫዎች ከቦ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።ቆላ ተምቤን ወርቅ አምባ ከተማ ላይ የመጨረሻ ምሽጉን ያደረገውን የጁንታውን አመራር ለመያዝ አሊያም ለመደምሰስ መከላከያ ሰራዊት በመረጃ የተደገፈ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ያሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ከአድዋ መስመር የመጣው ሰራዊት አካባቢውን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ እንደሆነ እና ከሃውዜን እና መቀሌ መስመር ያለውም ወደ ቦታው በከፍተኛ ወኔ እየተጠጋ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

መከላከያ ሰራዊቱ ወርህ የሚባል ትልቅ ወንዝ መሻገር አይችልም በሚል አካባቢ የ'ጁንታው' ታጣቂዎች ማጥቃት ቢፈጽምም ሰራዊቱ ወደ አካባቢው ተጠግቶ ከወርቅ አምባ 10 ኪሎ ሜትር ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል።እንደ ኮሎኔል ሻምበል ከሆነ፤ በቆላ ተምቤን ወርቅ አምባ አካባቢ የመሸገው 'ጁንታው' በምድር ከሚወሰድበት እርምጃ ባለፈ በአየር ጭምር እርምጃ ተወስዷል።በአየርና በድሮን አውሮፕላኖች በተወሰደ እርምጃ ወርቅ አምባ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ሰባት የጁንታው ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ወድመዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂ ፒ ኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ተባለ!

በኦሮሚያ በየጊዜው እያጋጠመ ለሚ ገኘው የህይወትና ንብረት ውድመት በህወሓት እና ተላላኪዎቹ የሚፈፀም መሆኑንና ይህንንም ለማስወገድ ብሎም የቡድንን ዕድሜውን ለማሳጠር በ‹ጂ ፒ ኤስ› ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መምሪያ አስታወቀ።የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር እንዳለ ቁምላቸው ለበሪሳ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የህወሓት ጁንታ እና የኦነግ ሸኔን ሴራ ለማክሸፍና ዕድሜ ለማሳጠር ‹‹ጂ ፒ ኤስ›› ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ መሆኑን አብራርተዋል።

እነዚህ አካላት ዜጎችን ለምን እንደሚገድሉ እንደማያውቁ በመጠቆም በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋልም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል።ቴክኖሎጂው እነዚህ አካላት ያሉበትን ቦታ ለመከታተል የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል።በዚህ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የኦነግ ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸውን የተናገሩት ኃላፊው፤ በሠላማዊ መንገድ እጅ ለማይሰጡና የኃይል አማራጭ ለመጠቀም የሚሞክሩት ላይ ደግሞ እርምጃ እየተወሰደባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል።

[ኢ.ፕ.ድ]
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሆስፒታል የሚገኙ የመከላከያ አባላትን ጎበኙ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት በሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላትን መጎብኘታቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ዛሬ ጠዋት ኢትዮጵያን ከራስ በላይ ያስቀመጡ በሆስፒታል የሚገኙ ሴት እና ወንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጀግኖቻችንን ጎብኝቻለሁ!አገልግሎታችሁን እናከብራለን” ብለዋል፡፡

ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ስላደረጉበት ሆስፒታል የገለጹት ነገር የለም፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በማይካድራ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የእርሻ ካምፕ ውስጥ የሕወሓት የጦር መሳሪያዎችና ማሰልጠኛ ተገኘ!

የተለያዩ ሃገራት ወታደራዊ ልብሶች፣ የአልሸባብ እና የኦነግ ሸኔ ወታደራዊ ልብሶችም መገኘታቸው ተገልጿል፡፡የሠው ማሠቃያ ሠንሰለቶች፣ መፅሐፎች፣ ካሴቶች እና ሲዲዎችም ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ከአላማጣ ወደ መቀሌ የሚሄደው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፍያ መስመር እየተጠገነ ነው!

ከአላማጣ ወደ መቀሌ የሚሄደው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፍያ መስመር እየተጠገነ ነው።በህወሓት ጁንታ ታጣቂዎች ጉዳት ደርሶበት የነበረው ይሄው የኤሌክትሪክ ሃይል መስመር በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገባ ጥገና እየተደረገለት እንደሚገኝ የኢዜአ ዘገባ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
የደብረ ብርሃን የተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ!

ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በ2012 ዓ. ም ሁለተኛው መንፈቅ አመት የመማር ማስተማር ሂደት ተቋርጦ እንደነበር ይታወቃል፡፡ስለሆነም የተቋረጠዉን ትምህርት ለማስቀጠል፣

1. በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበራችሁ ተማሪዎች ታህሳስ 1 እና 2/2013 ዓ.ም
2. ከተመራቂ ተማሪዎች ውጪ ያላችሁ ነባር ተማሪዎች በሙሉ ታህሳስ 8 እና 9/2013 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመገኘት ትምህርታችሁን እንድትጀምሩ እየገለፅን በጉዞ ላይም ሆነ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት እና ጤና ሚኒሰቴር ያወጡትን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ መመሪያን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ በማድረግ ስለሆነ አስፈላጊዉን የመከላከያ መንገዶች ዝግጅት አድርጋችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
@YeneTube @FikerAssefa
የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች በሚነሱባቸው አካባቢዎች የዜጎች መብት ሊከበር እንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አቅጣጫ አስቀመጠ።

የብጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ባከሄደው መደበኛ ስብሰባው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም በሰጡት መግለጫ ስራአስፈጻሚው ከሃዲው የህወሃት ቡድን በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ካደረሰና በአማራ ክልልም ትንኮሳ ካካሄደ በኋላ በተወሰደው የህግ ማሰከበር ዘመቻ እንደ ሀገር አኩሪ ገድል መፈፀሙ ተገምግሟል ብለዋል፡፡ህወሃት እየተሸነፈ ሲሄድ እስካሁን ባለው 1 ሺ ንጹሃንን በማንነታቸው ለይቶ ገድሏልም ተብሏል፡፡

የህግ ማሰከበር ዘመቻው በስኬት እየተጠናቀቀ ነው ያሉት አቶ ብናልፍ የቀረው መሪ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ስራ በአፋጣኝ እንዲካሄድ ስራአስፈጻሚው አቅጣጫ አስቀምጧል ብለዋል፡፡የወሰንና የማንነት ጥያቄ ዎች በሚነሱባቸው አካባቢዎች ላይ ህወሃት በሃይል ማንነትን የመንጠቅ፣ ጥያቄውን የሚያቀርቡ አካላትን የመግደል፣ የማሰርና የማፈናቀል ስራ ሲሰራ ነበር በዚህም ወደ 500 ሺ ዜጎች ተሰደዋል ያሉት አቶ ብናልፍ ጥያቄ አቅራቢወቹ ፍትህን ለ30 አመታት በሰላማዊ መንገድ ሲጠይቁ መቆየታቸውንና መብታቸውም መከበር እንዳለበት ስራ አስፈጻሚው መወያየቱን ገልጸዋል፡፡በመሆኑም ጥያቂያቸውን ህወሃት ባሰተናገደበት መንገድ ሳይሆን በሰላመዊ መንገድ ይመለሳል ምክንያቱም ነዋሪዎቹ መብታቸውን እንጅ የተለየ ስጦታ አልጠየቁም ነው ያሉት።

የተፈናቀሉ ዜጎችን የማቋቋምና በከሃዲው ቡድን የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን ስራ ማስጀመር በትኩረት እንዲሰራ ስራ አስፈጻሚው ወስኗል፡፡መሪ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ስራ እየተሰራ ቡድኑን በሽብርተኝነት የመፈረጅ ስራው በጥናትና በነባራዊ ሁኔታዎች ታይቶ ይወሰናልም ብለዋል፡፡ስራ አስፈጻሚው በሃገራዊና አለማቀፋዊ ዮፖለቲካ ሀይሎች ወቅታዊ አሰላለፍ ላይም መክሯል፡፡በሃገሪቱ ጽንፍ የወጡ አስተሳሰቦች እየተሰታወሉ ሀገር የማፍረስ አደጋ እንዳያመጡ የፖለቲካ ንቃት ላይ ይሰራል ተብሏል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገር ግንባታላይ በጎ አስተዋኦአቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል፡፡በዓለም አቀፍ ደረጃ በአባይ ፖለቲካ ላይ የሚሰሩ ፐሮፖጋንዳዎች ላይ ያሉ ስጋቶችና መልካም እድሎች ተለይተው ውይይት ተካሂዶባቿል፡፡የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ባከሄደው መደበኛ ስብሰባው በ2013 ሀጋራዊ ምርጫ ፓርቲው የሚመራበትን የዘመቻ ሰነድም አጽድቋል፡፡

[AMMA]
@YeneTube @FikerAssefa
ፋሲል ከነማ ከ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውጪ ሆነ!

በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እየተሳተፉ ይገኙ የነበሩት አፄዎቹ በሚያስቆጭ ሁኔታ በጭማሪ ደቂቃ በተቆጠረባቸው አንድ ግብ በድምር ውጤት 3 ለ 2 በመሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።ሞናስቲር ክለብ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን ተከትሎ በቀጣዩ ዙር ከ ሊቢያው አል አህሊ ትሪፖሊ ጋር ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።

[Hatrick Sport]
@YeneTube @FikerAssefa
የሰቆጣ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ምንጭ በመጥቀስ የህወሓቶች መማረክ በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ የተዘገበውን ዜና በተመለከተ የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ማምሻውን ማስተባበያ አውጥቷል።

መግለጫው:

ከመቀሌ ሸሽቶ በቆላ ተንቤን የመሸገው የጁንታው ቡድን በጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ከባድ የማጥቃት እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የውጊያውን ውጤትና የተገኘውን ድልም መንግሥት ያሳውቃል፡፡

ሁኖም ግን ህዝባችን አንዳንድ ምንጫቸው ያልተረጋገጡ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ አላስፈላጊ የሆኑ የደስታ መግለጫዎችን ከማድረግ እንዲቆጠብ እናሳስባለን፡፡

አሸባሪው ትህነግ እንዲደመሰስ ካለ የህዝባችን ፍላጎት የተነሳ ማኅበረሰባችን ደስታውን ስሜታዊ በሆነ መንገድ መግለጹ የሚጠበቅ ቢሆንም የራስንና የህዝብን ደኅንነት ለከፋ አደጋ በሚያጋልጥ መንገድ ግን መሆን እንደሌለበት ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ጥይት በመተኮስ እና በሌሎች የደስታ መግለጫዎች የሚገለጽ ድል ለህገ ወጦችና የጁንታው ርዝራዦች የተመቸ ክፍተት የሚሰጥ በመሆኑ ከዚህ ልንቆጠብ ይገባል፡፡

ስግብግቡ ጁንታና ርዝራዦቹ ተጠራርገው የህግ የበላይነት ሙሉ በሙሉ እስኪከበር ድረስ ህዝባችን ደስታውን በበለጠ ጥንቃቄ በማጀብ ለአካባቢው ሰላም አስተዋጽኦ በሚያደርግ መንገድ መግለጽ ይኖርበታል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ህዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም.
ባሕር ዳር

@YeneTube @FikerAssefa
በሕንድ በርካቶች ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ታመው ሆስፒታል ገቡ!

በሕንድ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ለ140 ሰዎች ሆስፒታል እንዲገቡ ያደረገው በሽታ ምንነት ለማወቅ ምርምራ እየተካሄደ ነው።ተመራማሪዎች በሽታው ምን እንደሆነ እና የሕመሙን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ መጀመራቸው አስታውቀዋል።አንድራ ፕራዴሽ ከሚባለው ግዛት የመጡት ታማሚዎች በርካታ የተለያዩ የሕመም ምልክቶች ሲያሳዩ የነበረ ሲሆን ማጥወልወል እና እራስን ስቶ ተዝለፍልፎ መውደቅ ደግሞ አብዛኛዎቹ ላይ የተስተዋለ እንደሆነ ዶክተሮች ገልጸዋል።

ኢሉሩ የተባለው የመንግሥት ሆስፒታል ደግሞ ምናልባት ተጨማሪ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ተማሚዎች ከመጡ በሚል በርካታ አልጋዎች ነጻ ሆነው እንዲጠባበቁም ተደርጓል ተብሏል።ሕንድ የኮሮረናቫይረስ ተጽእኖን ለመቀነስ እና ስርጭቱን ለመቆጣጠር ደፋ ቀና በምትልበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ምንነቱ ያልታወቀ ሕመም መከሰቱ በርካቶችን አሳስቧል።የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ደግሞ ሁሉም ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ታማሚዎች የኮሮናቫይረስ ምርምራ የተደረገላቸው ሲሆን ማንኛቸውም ግን በቫይረሱ አልተያዙም።

በኢሉሩ የመንግሥት ሆስፒታል የሚሰራ አንድ የጤና ባለሙያ ለኢንዲያን ኤክስፕረስ ሲናገር '' 'አይናችን አካባቢ ማቃጠል ይሰማናል' ብለው ወደ ሆስፒታላችን ከመጡት መካከል በተለይ ደግሞ ሕጻናቱ ወዲያው ማስመለስ ጀመሩ። አንዳንዶቹ እራሳቸውን የሳቱ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ቅዝቃዜ ተሰምቷቸው ይንቀጠቀጡ ነበር'' ብሏል።ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱት ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን አንዳንዶቹም ተሽሏቸው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።

የአንድራ ፕራዳሽ የጤና ሚኒስትር አላ ካሊ ካሊ ክሪሽና እንዳሉት ደግሞ ከሁሉም ታማሚዎች ላይ የደም ናሙና የተወሰደ ቢሆንም ምንም አይነት የቫይረስ ኢንፌክሽን ምልክት ግል አልታየባቸውም።''ባለሙያዎቻችን የሰዎቹን መኖሪያ አካባቢ ከጎበኙ በኋላ በምርመራችን የአየር እና የውሃ ብክለት አለመሆኑን ደርሰንበታል። ሚስጥራዊ የሆነ ሕመም ይመስላል፤ የትኛውም የላብራቶሪ ምርመራ ምክንያቱን ሊያውቀው አልቻለም'' ብለዋል የጤና ሚንስትሩ።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የስኳር ሕመምተኞች ኢንሱሊን የተባለው መድሐኒት እጥረት በመከሰቱ ታማሚዎች በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ስኳር ሕመምተኞች ማኅበር አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ መድሐኒቶች በሚፈለገው መጠን ወደ አገር ውስጥ ባለመግባታቸው ላለፉት ኹለት ወራት የኢንሱሊን እጥረት በአገር ደረጃ በመከሰቱ ታማሚዎች የሚፈልጉትን አቅርቦት እያገኙ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ስኳር ሕመምተኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶክተር አብዱረዛቅ አህመድ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት ለአገር የመከላከያ ሠራዊት በአንድ ቀን ከ21 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ አሰባሰበ!

በኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት ለአገር የመከላከያ ሠራዊት ቤተሰቦች እና ወገኖች ለመደገፍ ኅዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው የዙም ጉባኤ በአንድ ቀን ከ21 ሺህ ዶላር በላይ አሰባስቧል።በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ ዳያስፖራው በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እና በዕውቀት እያደረገ ላለው ተግባራዊ አጋርነት እና ድጋፍ አመስግነዋል።መንግሥት በአገር ውስጥም በውጭም ያሉ ወገኖችን አስተባብሮ በመላው አገሪቱ ሰላም፣ አንድነት እና ብልጽግና እንዲረጋገጥ ማንም ኢትዮጵያዊ ባይተዋር የማይሆንባት አገርን የመገንባቱ ግስጋሴ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የመንግስት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ትምህርታቸውን ዛሬ በይፋ ጀምረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
አስገዳጅ ስምምነት ሳይደረስ ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን በቀጣይነት እንድትሞላ እንደማትፈቅድ ሱዳን ገለጸች!

ቀጣዩ ሙሌት ያለስምምነት ከተከናወነ በሱዳን ላይ የደህንነት ስጋት እንደሚደቅን የዉሃ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ሱዳን አለመግባባቱን ለመፍታት ኃይል የመጠቀም ፍላጎት እንደሌላት የሀገሪቱ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

ዘገባው የአልዐይን ነው👇👇👇

https://am.al-ain.com/article/sudan-rejects-further-filling-of-ethiopia-s-renaissance-dam-if-no-agreement

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንዱስትሪያል ፓርኮችን ሙሉ በሙሉ ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር የተለያዩ ጥናቶች በመደረግ ላይ ናቸው ሲሉ የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት አማካሪ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ተናገሩ።

በኢትዮጵያ 13 ያህል ኢንደስትሪያል ፓርኮች ያሉ ሲሆን ዐሥሩ በሥራ ላይ ሲሆኑ ኹለቱ በቅድመ ምስረታ አንዱ ደግሞ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ነው። በእነዚህ ኢንደስትሪያል ፓርኮች 60 ሺሕ የሚደርሱ ሠራተኞች አሉ።አብዛኛዎቹ የኢንደስትሪ ፓርኮች በጨርቃጨርቅ ምርቶች ላይ የተሠማሩ መሆናቸውን የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነት እና የማርኬቲንግ ኃላፊ የሆኑት በኃይሉ ከበደ አስታውቀዋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
ሄሎ ታክሲ በቀጣዮቹ 15 ቀናት ዉስጥ 451 አዳዲስ መኪናዎችን ለማስገባት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለፀ።

የድርጅቱ መስራችና ባለቤት የሆኑት አቶ ዳንኤል ዮሃንስ እንዳሉት፣ ''መንግስት ባመቻቸልን የቀረጥ ነጻ እድል መሰረት ከዚህ በፊት ለ5 ሺህ ሰዎች የዘመናዊ ታክሲ አገልግሎት ተጠቃሚና ባለቤት ማድረግ እንደተቻለ አውስተዋል።አሁን ደግሞ ለደንበኞች በገባነው ዉል መሰረት አዳዲስ መኪናዎችን ወደ ሀገራችን ለማስገባት እና ለማስረከብ ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ ብሏል።

በመቀሌ ጉምሩክ 126 መኪናዎች፣ በሞጆ ደረቅ ወደብ 84 መኪናዎች፣ በጅቡቲ ወደብ 67 መኪናዎች፣ እንዲሁም በቀጣዮቹ 15 ቀናት ውስጥ የሚገቡ 174 መኪናዎች በጠቅላላው 451 መኪናዎችን ወደ ሃገራችን ለማስገባት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን አቶ ዳንኤል ተናግረዋል።

የእነዚህ ታክሲዎች ስራ መጀመር በተለይ ቱርሲቶችን ወይም የውጭ ሀገር ጎብኝዎችን በማጓጓዝ ሀገራችን በቱሪዝም ዘርፍ እውቅናና ገቢም እንድታገኝ ይረዳሉ ሲሉ ተናግረዋል አቶ ዳንኤል።በመሆኑም ሃገራችንን በዘርፉ ለማዘመን እንዲሁም በሀገራችን የተከሰተውን የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የኮቪድ 19 ያስከተከውን ኢኮኖሚያዊ ችግር ለማካካስ በሚደረገው ጥረት የድርሻችንን ለማገዝ በርትተን እንሰራለን ማለታቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል::

@YeneTube @FikerAssefa
መንግሥት በሱዳን የሚገኙ ስደተኞችን በአጭር ጊዜ እመልሳለሁ አለ፡፡

በትግራይ የተፈጠረውን ጦርነት ተከትሎ ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን በአጭር ጊዜ በመመለስ ለማቋቋም እንደሚሰራ የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት በእንግሊዘኛ ባውጣው መግለጫ ገልጿል፡፡በክልሉ በነበረው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከሚኖሩበት መፈናቀላቸውን እንዲሁም ወደ ሱዳን መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ያሳያል፡፡መንግሥት በማንኛውም ጊዜ ለዜጎች ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን የጠቀሰው የጽህፈት ቤቱ መግለጫ፤ በትግራይ ክልል ሰብኣዊ ድጋፍን ለማቅረብ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በተባበሩት መንግሥታት መካከል ስምምነት መፈረሙን አስታውሷል፡፡

በክልሉ በነበረው ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች እና በስደተኞች ካምፕ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላልሆኑ ዜጎች ሰብኣዊ ድጋፍ ለማቅረብ መንግሥት ከሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት እና ከተባበሩት መንግሥታቱ አጋሮች ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡ወንጀለኞችን ለሕግ ማቅረብ፣ ሕግና ስርዓትን መመለስ፣ ሰብኣዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ፣ ድንበር አቋርጠው የተሰደዱ ዜጎችን መልሶ ማቋቋም እና በወንጀለኛው ቡድን የወደሙና አገልግሎት ያቋረጡ የትራንስፖርትና መገናኛ መሰረተ ልማቶችን መልሶ መገንባት የፌደራል መንግሥት ዋነኛ ተግባራት መሆናቸውን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከቻይናው ሳይንስ አካዳሚ የአፕላይድ ኢኮሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር በግብርና ምርምር ዘርፍ አብሮ ለመሥራት የሚያስችል የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመተባበር የግብርና ምርምርና የልማት ስራዎችን፣ የአካባቢ እና ሥነ-ምህዳር ምርምር፣ በመስኩ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ነፃ ትምህርት ዕድል እና የገንዘብ ድጋፍ በማፈላለግ የሰው ሀይል አቅም ግንባታ ለማካሄድ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

የቻይና-ኢትዮጵያ የግብርና እና አካባቢ የምርምር ማዕከል ለመመስረት እንዲሁም በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ማዕከል ለመክፈት መታቀዱን በቻይና ከኢትዮጵያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

[ኢ.ፕ.ድ]
@YeneTube @FikerAssefa