YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
'ጁንታው' ለዓመታት ያዋጋኛል ብሎ የቆፈረውን ምሽግ ጀግናው ሠራዊት በመሰባበር ድል አድርጓል ሲሉ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜ/ጄ ዘውዱ በላይ ተናገሩ!

ጁንታው ለዓመታት ያዋጋኛል ብሎ የቆፈረውን ምሽግ ጀግናው ሠራዊታችን በመሰባበር ከጁንታው ብቻ ሳይሆን አስቸጋሪ ከሆነ መልክአ ምድር ጋር ተፋልሞ ድል አድርጓል ሲሉ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ በላይ ገለጹ።ህዝብና መንግስት የሚሠጠውን ተልዕኮ በአስተማማኝ ሁኔታ የሚፈፅም መከላከያ ሠራዊት መገንባቱንም የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ በላይ አስታውቀዋል።

ከጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥና ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ አይበገሬው የሚል ስያሜ የተሠጣቸው ሜጀር ጄኔራሉ ÷ “በህግ አልዳኝ ብሎ ግጭት የመረጠውን ጁንታ ሠራዊታችን በአጭር ግዜ ውስጥ ከሀገር ወዳዱ የትግራይ ህዝብ በመነጠል ሙሉ በሙሉ ከስራ ውጭ አድርጎታል” ብለዋል ።

ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ በላይ ሠራዊቱ “ ከቢሶ በር - ጨርጨር ፣ መኾኒ ፣ አዲቀይህ ፣ አዲመስኖ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ለዓመታት ያዋጋኛል ብሎ የቆፈረውን ምሽግ ጀግናው ሠራዊታችን በመበጣጠስ ከጁንታው ብቻ ሳይሆን በጣም አስቸጋሪ ከሆነ መልክአ ምድር ጋር ተፋልሞ ድል አድርጓል” ብለዋል።“ህዝብና መንግስት ለቀጣይም ቢሆን በየትኛውም ግዜና ቦታ ለሚሠጠን ግዳጅ ደከመኝ ፣ ሠለቸኝ የማይል ብቃት ያለው ሰራዊት እንዳለን በነበሩት የህግ ማስከበር ዘመቻዎች ተረጋግጧል” ሲሉም መግለጻቸውን ኢዜአ ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ አስመልክቶ የሶስት ክለቦች (መቐለ 70 እንደርታ፣ ስሑል ሽረ እና ወልዋሎ አዲግራት ) ክለብ ከታህሳስ ሶስት በፊት የሚመጡ ከሆነ የምንቀበላቸው ሲሆን ከዚህ ቀን በኋላ የሚመጡ ከሆነ ተቀባይነት የማያገኙ እና በውድድሩ የማይካፈሉ መሆናቸውን መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ገልጸዋል።ሆኖም ግን በ 2014 የውድድር ዓመት እንደ ፕርሚየር ሊጉ አካል አድርገን እንካትታቸዋለን ብለዋል።

Via Hatrick Sport
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 26 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለፀ!

በአፋር ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከነገ ታህሳስ 26 እስከ 28/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ ሁመድ በክልሉ በኮሮና ወረርሺኝ ምክንያት ተላልፎ የነበረው የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 26-28/2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ተገልጿል።ፈተናውን የሚወስዱት በ271 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 7 ሺህ 984 ተማሪዎች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ 4 ሺህ 837 የሚሆኑት ወንዶች፣ 3 ሺህ 147 ደግሞ ሴት ተፈታኞች መሆናቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በታጣቂዎች ከታገቱ ዛሬ አንድ ዐመት ሞልቷቸዋል። መንግሥት ከጥቂት ወራት በፊት 17 ያህል ተጠርጣሪ አጋቾችን በቁጥጥር ስር አውሎ ለፍርድ ቤት አቅርቧቸው የነበረ ቢሆንም፣ ታጋቾቹ በሕይወት ይኑሩ አይኑሩ ግን እስካሁን የሰጠው መረጃ የለም።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ጦርነት ሸሽተው ወደ ሱዳን የተሰደዱትን ኢትዮጵያዊያን ለመመለስ ከሱዳን መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

ስደተኞቹ የት ይገኛሉ፣ እነማን ናቸው፣ ስንት ናቸው ፣ በምን ደረጃ ላይ ናቸው የሚለውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኃላፊነት ተሰጥቶት እየተከታተለ መሆኑና በአጭር ጊዜ ውስጥም ተጣርቶ እንደሚመለሱ ተነግሯል። ወደ ትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ የተባበሩት መንግሥታት ድጋፍ ሰጪ ቡድን መጓዙን የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ውጤቱ በቀጣይ ቀናት ይፋ ይሆናል ብለዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአመታዊው “አለም አቀፍ የጉዞ ሽልማት” (World Travel Awards) ስታር አሊያንስ “የ2020 ምርጥ የአየር መንገዶች ህብረት” ሽልማት አሸናፊ ሆኗል። በተመሳሳይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የ2020 ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ሽልማትን ተቀዳጅቷል። ይህ አመታዊ ሽልማት በአቪየሽኑ ዘርፍ ለታዩ ድንቅ አፈፃፀሞች እና ለተመዘገቡ ስኬቶች እውቅና እና ማበረታቻ የሚሰጥበት ነው።

https://www.worldtravelawards.com/award-africas-leading-airline-2020

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያዊቷ ታዳጊ በአሳዛኝ ሁኔታ ከጎረቤት በተተኮሰ ጥይት ህይወቷ አለፈ!

ኢትዮጵያዊቷ የ 12 ዓመት ታዳጊ ከጎረቤት በተተኮሰ ጥይት በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቷ አለፈ።በአሜሪካ ኮሎምበስ ነዋሪ የሆነችው ታዳጊ ሊዲያ ከቤተሰቧ ጋር በምትኖርበት አፓርትመንት ውስጥ እንዳለች በድንገት ከጎረቤት ቤት የተተኮሰ ጥይት አንገቷን መቶ ለሞት እንዳበቃት ፖሊስ ተናግሯል።

የመሳሪያው ባለቤት ተገቢውን ጥንቃቄ ባለማድረጉ አሳዛኙ ድርጊት መፈፀሙን የተናገረው ፖሊስ ጠበቅ ያለ የመሳሪያ ቁጥጥር የሚያስፈልገው እንዲህ አይነቱን አደጋ ለመከላከል ነው ብሏል።

ሊዲያና ቤተሰቧ ወደዚህ አፓርትመንት ገብተው ኑሮ ከጀመሩ ገና አንድ ወራቸው እንደሆነ ተወርቷል።ታዳጊዋ ሊዲያ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወቷ ማለፉን ተከትሎ ለቀብር ስነ ስርዓት ማስፈፀሚያ በተከፈተው የ GoFundMe አካውንት ገንዘብ እየተሰበሰበ ነው።

[Fidel post]
@YeneTube @FikerAssefa
ከቄለም ወለጋ አንፊሎ ወረዳ በፀጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ጋምቤላ መሸሻቸውን አንዳንድ ግለሰቦች ገለፁ። ከተፈናቀሉት መካከል የሸሸነው ታጥቀው ከሚንቀሳቀሱ የኦነግ ሸኔ አባላት ጥቃት ለማምለጥ ነው ብለዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
ኢዜማ ባዘጋጃቸው 7 የፖሊሲ ሰነዶች ላይ ውይይት እያካሄደ ነው!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ባዘጋጃቸው 7 የተለያዩ ረቂቅ ፖሊሲዎች ላይ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።ፓርቲው የማክሮ ኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንት፣ የንግድ፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ የኢንዱስትሪ፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የማህበራዊ ከለላ ረቂቅ ፖሊሲዎችን በማዘጋጀት ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ይገኛል።በውይይቱ ላይ የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፖለቲካ የአጭር ጊዜ ጩኸት ሳይሆን ሰፊውን ህዝብ የሚጠቅም የረጅም ጊዜ ተግባር ነው ብለዋል።የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ምርጫ ከመሄዳቸው በፊት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተደራጀ ሃሳብ አቅርበው ውይይቶችን በማካሄድ ለሀገራቸው የሚጠቅሙ ሀሳቦችን ማቅረብ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ከጊዜ ኋላ ሲራመድ የነበረውና ከስህተቱ ለመማር ያልቻለው ሕወሓት በመጨረሻም የዘራውን መረራ ፍሬ እየሰበሰበ ነው አሉ፤ የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በአልጀዚራ ላይ ባሰፈሩት ሀተታ እንደ ሕወሓት ያሉ ፓርቲዎች የመጨረሻ እጣ ፈንታም ከዚህ እንደማያልፍ ነው የጠቀሱት፡፡‹‹በኢትዮጵያ ያለው ግጭት እና የሕወሓት ከመጠን ያለፈ ብሔርተኝነት›› በሚል ርዕስ የወጣው የሙስጠፌ ጽሑፍ፤ ከሕወሓት አፈጣጠር ጀምሮ የነበሩ ብልሽቶችን ዳሷል፡፡
ሕወሓት የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ በጋብቻ፣ በንግድ፣ በሃይማኖትና በባሕል እጅግ የተሳሰረ የመሆኑን እውነታ በመካድ የማይታረቅ ልዩነት እንዳላቸው አድርጎ ሲሰብክ ኖሯል ሲሉ ነው የከሰሱት፡፡ በዚህም አጥፊና ከፋፋይ የሆነውን ‹‹የእኛ እና እነሱ›› ትርክትን ፈጥሯል ይላሉ፡፡

ሀተታው ሲቀጥል የትግራይ ሕዝብ በጠላት እንደተከበበ አድርጎ በመስበክ በሚያስተዳድራቸው የመገናኛ ብዙኃን በኩልም ተከታታይ የጦርነት ዘጋቢ ፊልሞችን ሲያሳይ ስለመክረሙ አስታውሷል፡፡
ሕወሓት ራሱን የብሔር፣ ብሔረሰቦች ሰላም ብቸኛ ጠባቂ አድርጎ ሲያስፈራራ መኖሩንም ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ሙስጠፌ ያነሱት፡፡ሕወሓት ለዓመታት በበላይነት ይዞት የነበረውን የማዕከላዊ መንግሥቱን ሥልጣን በ2010 ካጣ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተጀመሩ አገራዊ ማሻሻያዎችን ለመቀልበስ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል ሲልም ጽሑፉ ይነበባል፡፡ በመላ አገሪቱ ግጭቶችን በተለያዩ መንግዶች ሲደግፍ እንደነበር በመክሰስ፤ በአገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ኢትዮጵያ ሕግ ወደማስከበሩ ዘመቻ መግባቷንም ያስታውሳል፡፡

አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ በሶማሊያ የሚገኙ ወታደሮቿን ልታስወጣ ነው።700 ገደማ ይሆናሉ የተባለላቸው ወታደሮቹ የሚወጡት ተመራጩ ፕሬዝዳንት ባይደን ወደ ነጩ ቤተመንግስት ከመግባታቸው 5 ቀናት በፊት ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ኢ-መደበኛና ታጣቂ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ ባቀረብኩት ጥሪ እስካሁን እጅ የሰጠ ታጣቂ የለም አለ፡፡

ከሰሞኑ የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ‹43 የፀረ ሰላም ኃይሎች እጃቸውን ሰጥተዋል› በሚል ያቀረቡት መረጃ ትክክለኛ እንዳልሆነም የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መለሰ በየነ ለአሐዱ ቴሌቪዥን ገልፀዋል፡፡ምክትል ኮሚሽነሩ በተለይም ‹በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂ ቡድኖች እጃቸውን ሰጥተዋል› ማለታቸው አይዘነጋም፡፡አካባቢውን ወደ ሰላም ለመመለስ የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የክልሉ ልዩ ኃይልና የፌደራል ፖሊስ በኮማንድ ፖስት ተቀናጅተው እየሰሩ ነው፤ ያሉት ኃላፊው ወደ ታላቁ ኅዳሴ ግድብ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለጊዜው በግልገል በለስ ከተማ እንዲቆሙ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ስለምክንያቱ የጠየቃቸው ኃላፊው ጉባ ወረዳን ጨምሮ በመተከል ዞን በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የፀረ ሰላም ኃይሎችን ለመደምሰስ እርምጃ በመጀመሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ሆኖም ከእሁድ ኅዳር 27 ጀምሮ የቆሙት ተሽከርካሪዎች ወደ ግድቡ በመንቀሳቀስ መደበኛ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በመተከል ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የንፁሃን ግድያ፣ ማፈናቀልና ንብረት ማውደም በተደጋጋሚ የሚከሰት ጥቃት ሲሆን የክልሉ መንግሥትም አፋጣኝ እርምጃ እየወሰደ አይደለም በሚል ወቀሳዎች እየተነሱበት ይገኛል፡፡

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube @FikerAssefa
በህውሃት ቡድን የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን ትምህርት ለማስጀመር 50 ሚሊየን ብር በጀት መያዙን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ እንደገለጹት፡ በትግራይ ክልል 'በከሃዲው ቡድን' የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን ትምህርት ለማስጀመር 50 ሚሊየን ብር በጀት መያዙን ተናግረዋል።በአማራ ክልል አጎራባች አካባቢዎች በህግ ማስከበር ሂደቱ የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን በመጠገን ወደ ስራ ለማስገባትም እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰው፣ ለትግራይ ክልል ከ700 ሺህ በላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መዘጋጀቱንም ገልፀዋል፡፡በሰላም ማስከበር ወቅት የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን የመማር ማስተማሩ ስራ በሁሉም ቦታ ትምህርት ይጀምራል ብለዋል፡፡ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት በሁሉም አካባቢ እንዲጀመር ለማድረግ እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ጸሐዬና ጌታቸው ረዳ በአንድ ቦታ ለይ መሆናቸውን በሰሜን ዕዝ የ31 ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ አስታወቁ፡፡

አዛዡ ኮሎኔል ሻምበል በየነ ከፍተኛ አመራሮቹ ያሉበት ቦታ መታወቁን ገልጸው በተምቤን፣ አቢ አዲ እና ወርቃምባ ይገኛሉ ብለዋል ለኢቲቪ በሰጡት መግለጫ፡፡አመራሮቹ የሚገኙበት ስፍራ ከሃገር መከላከያው በቅርብ ርቀት ላይ እንደሚገኝ እና የሰራዊቱ አባላት የቅርብ ክትትል እያደረጉ እንደሚገኙም ነው አዛዡ የተናገሩት፡፡

ኮሎኔል ሻምበል አመራሮቹ በተምቤን አቢ አዲ እንዲሁም የሀውዜንና አድዋ መገንጠያ በሆነችው ወርቃምባ ከተማ ውስጥ መሆናቸውን ማየት ተችሏል ብለዋል፡፡ወርቃምባ ከሰራዊቱ በ10 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የምትገኝ ነች እንደ ኮሎኔሉ ገለጻ፡፡

በልዩ ጥበቃ ማለትም በኮማንዶ ጭምር እተየተጠበቁ እንደሆነ የተናገሩት አዛዡ ከአራቱ ባለስልጣናት ውጭ ሌሎች ብዙም በሕዝብ የማይታወቁ ባለስልጣናት በስፍራው እንዳሉ ስለማየታቸው ተናግረዋል፡፡አሁን ላይ የትግራይ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ፈርሷል ያሉት ክፍለ ጦር አዛዡ ሰራዊቱን ከድተው ለህወሃት የወገኑ አባላትን የመያዝ ስራ ይሰራል ብለዋል ከፍተኛ አመራሮቹን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ ጥቂት ቀናትን ብቻ እንደሚወስድ በመጠቆም፡፡

ሙሉ ዘገባው👇👇👇
https://am.al-ain.com/article/four-senior-tplf-leaders-including-dr-debretsion-are-said-to-be-in-the-town-of-workamba

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ተጨማሪ ሦስት ወደቦችን ለመገንባት ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡

ድርጅቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ የደረቅ ወደቦችን በማስፋፋት ከውጪ ሀገራት ለሚገቡ እቃዎች ጊዜያዊ ማረፊያ እንዲሆኑ አገልግሎት መስጠት ነው፡፡

ከሦስቱ ደረቅ ወደቦች መካከል የሁለቱ ጥናት በተያዘው ዓመት ተሠርቶ እንደሚጠናቀቅ የድርጅቱ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አሸብር ኖታ ተናግረዋል፡፡ የወደብ አገልግሎት ለማግኘት ከተለያዩ አካላት የሚነሱ ጥያቄዎች መኖራቸውን ያመላከቱት አቶ አሸብር ወደቦቹ ሊሠሩ የሚችሉበት አካባቢ በጥናት እንደሚለይ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ የወረታ ደረቅ ወደብና ተርሚናል ማስፋፊያ ጥናት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

[AMMA]
@YeneTube @FikerAssefa
በቶኬ ኩታዬ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የተገኘ 96 ኩንታል ቡና ተያዘ!

በምዕራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ 96 ኩንታል ቡና ጭኖ በህገ ወጥ መንገድ ሲያጓጉዝ የተገኘ አሽከርካሪ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኮማንደር ይገዙ ገብረሚካኤል እንደተናገሩት፤ አሽከርካሪው የተያዘው ንግድ ፈቃድም ሆነ ሌላ መስረጃ ሳይኖረው ቡናውን ከጅማ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ለማሳለፍ ሲሞከር ነው።

ቡናው በወረዳው ጉደር ከተማ ንግድ ባንክ አካባቢ ትናንት ሌሊቱ ስምንት ሰዓት ተኩል አካባቢ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-64936 አዲስ አበባ በሆነ ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ እንደተጫነ በህብረተሰብ ጥቆማ መያዙን ገልጸዋል።አሽከርካሪው የፖሊሶቹን እንቅሰቃሴ እንዳየ ለማምለጥ ቢሞክርም በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ረዳት ኮማንደሩ አስረድተዋል፡፡

[ENA]
@YeneTube @FikerAssefa
አርጀንቲና በኮሮናቫይረስ ሰበብ ባለሀብቶች ላይ አዲስ ግብር ጣለች!

አርጀንቲና ለኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ሕክምና የሚያስፈልጉ የሕክምና አቅርቦቶችን ለማሟላትና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላትን ወጪ ለመሸፈን ሀብታም ዜጓቿ ላይ አዲስ ግብር ጣለች።ይህ አንድ ጊዜ የሚከፈለውና "የሚሊየነሮች ግብር" የተባለውን ታክስ ለመጣል የወጣው ረቂቅ ለአርጀንቲና ምክር ቤት አባላት ቀርቦ 26 እንደራሴዎች ቢቃወሙትም የ42ቱን ድጋፍ በማግኘቱ ጸድቋል። ይህ ግብር ይመለከታቸዋል የተባሉት የአርጀንቲና ባለጸጋዎች ሀብታቸው ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሲሆን ብዛታቸውም 12 ሺህ እንደሚሆኑ ታውቋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያዊቷ ዶ/ር ውለታ ለማ ዓለም አቀፉን የቴክኖሎጂ የስራ ፈጠራ ውድድር አሸነፉ!

የላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ዓለም አቀፉን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ አዲስ የስራ ፈጣራ ውድድር አሸነፉ።ኢትዮጵያዊቷ በየዓመቱ የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን ፒአይቲሲኤች (PITCH) አዲስ የስራ ፈጠራ ውድድር በትላንትናው እለት ማሸነፉቸው ይፋ ሆኗል። 

በውድድሩ 2500 ስራ ፈጣሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ወደ መጨረሻው ዙር ያለፉት ደግሞ 700 የሚሆኑ አዲስ ፈጣሪዎች ነበሩ።ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ(ዶ/ር) በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያቀረቡት አዲስ የስራ ፈጠራ በቅርበት ተፎካካሪ ከነበሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ የስራ ፈጣሪዎችን በመብለጥ የዓመቱ ውድድር አሸናፊ ሆኗል።

ውለታ ለማ (ዶ/ር) ለውድድሩ ያቀረቡት የስራ ፈጠራ አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ህክምና ዘርፍ ያለውን ሰፊ የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታል በመቀየር ስራን የሚያቀልና የሚያቀላጥፍ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚያስቀር የሥራ ፈጠራ ነው ተብሏል።"የአፍሪካን የጤና ዘርፍ ስርዓት ለማዘመን ለ28 ዓመታት ሰርቻለሁ ፤ እናም ውድድሩን በማሸነፌ በጣም ተደስቻለሁ" ሲሉ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የማታ ፕሮግራም ተማሪዎች (ከ1ኛ አመት ጀምሮ ለሆኑ) ጥሪ አደረገ!

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠዉ የ2012 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት ለማስጀመር የመልሶ ምዝገባ በሚከተለዉ መሠረት ይካሄዳል፡፡

-የማታ ተማሪዎች ምዝገባ ታህሳስ 10 እና 11 2013 ዓ.ም

-የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ታህሳስ 19 እና 20 2013 ዓ.ም ሲሆን ተመዝጋቢዎች ከኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች በመገኘት የኮርስ ምዝገባ ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሀይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኙ ተማሪዎች በጥሩ ደህንነት ላይ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡

ተማሪዎቹ በአሁን ሰዓት የትምህርት አገልግሎት ቢቋረጥም በሰላማዊ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል።በሀይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአሁን ሰዓት የህክምናና ተመራቂ የጤና ሳይንስ ተማረዎች ይገኛሉ፡፡ከዚህ ባሻገር በተለያዩ የትምርህት ዘርፍ ስፔሻላይዝድ ለማድረግ የገቡ የህክምና ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን÷ በአሁን ሰዓት ሁሉም በሆስፒታሉ ቅጥር ጊቢ እንዳሉ ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ከዚህ ቀደም ከጊቢው ውጪ ይኖሩ የነበሩ የስፔሻሊቲና ሰብ ስፔሻሊቲ ተማሪዎች ወደ ጊቢ ገብተው የመኝታ ክፍል አግኝተው በጥሩ ደህንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡በዩኒቨርሲቲው በቂ የውሃና የመብራት አቅርቦት እንደሌለም ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa