የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ነገ መደበኛ ስብሰባውን ማካሔድ ይጀምራል!
የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ነገ አርብ ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ.ም መደበኛ ስብሰባውን ማካሔድ ይጀምራል።ኮሚቴው በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@YeneTube @FikerAssefa

በትግራይ ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው ተባለ!
ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዛሬ እንደዘገበው የዕርዳታ ቁሳቁስ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እየተጓዙ ቢሆንም አሁንም ድረስ በአካባቢው ጦርነት መቀጠሉን ገልጿል።የዜና ምንጩ አንድ የዕርዳታ ሰራተኛን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በሚኖርባት መቀሌ ከተማ ደቡባዊ እና ምዕራባዊ ክፍል ዛሬም ጦርነት እየተካሄደ ነዉ።መንግስት «ሕግ የማስከበር» በሚለው ዘመቻ ከሦስት ሳምንት በላይ በተካሄደዉ ጦርነት 45 ሺህ ሰዎች ወደ ጎረቤት ሱዳን መሰደዳቸውንም ዘገባው አመልክቷል።
[Reuters/DW]

🔥1
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላይ ለመሠረተው ክስ፣ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሃ ብሄር ችሎት ታሕሳስ 1 ብይን ለመስጠት ዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ እንደሰጠ ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል። ኢዜማ በከተማዋ አስተዳደር ላይ የመሠረተው ክስ፣ "የመሰብሰብ ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ይከበር፤ ሁከትም ይወገድልን" የሚል ነው። አስተደርሩም በፖሊስ ያሳገደው የፓርቲው የውይይት ስብሰባ ሕጋዊ ፍቃድ እንዳልነበረው ጠቅሶ፤ "ጉዳዩን መመልከት ያለበትም የከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤት መሆን አለበት" በማለት ባለፈው ኅዳር 22 ለክሱ ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 595 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤9 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸው አልፏል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 522 የላብራቶሪ ምርመራ 595 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 111 ሺህ 579 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።ከዚህ ባለፈ የ9 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 724 መድረሱንም ሪፖርቱ ያመላክታል።
በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 1 ሺህ 318 ሰዎች ከኮሮና ቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 77 ሺህ 385 መድረሱም ተገልጿል።ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 652 ሺህ 517 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 111 ሺህ 579 ደርሷል።አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 32 ሺህ 468 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 317 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

❗ዛሬ በገንዘብ ሚኒስቴር አካባቢ ምንድነው የተፈጠረው?❗
👉ዛሬ ረፋድ አካባቢ ገንዘብ ሚኒስቴር በሚገኝበት ስፍራ በርከት ያሉ ሰዎች ተሰባስበው፤ እንዲሁም ፌደራል ፖሊስ እነዚህኑ ሰዎች ወደ መሥሪያ ቤቱ እንዳይገቡ ሲከላከሉ ተስተውሏል፡፡
👉ሸገር ጉዳዩ ምን ይሆን? ሲል በአካባቢው ተገኝቶ ለማጣራት ሞክሯል፡፡
👉ከ150 በላይ የሚሆኑ መኪና አስመጪዎች መኪናዎቻችን ያለ አግባብ ጨረታ እንዲወጣባቸው ተደርገዋል የሚል ቅሬታ ያላቸው ወገኖች መሆናቸውን ሰማን፡፡
👉ባለጉዳዮቹ፣ ‹‹መንግሥት ያገለገሉ መኪናዎችን ለማስመጣት በሰጠው የ6 ወር ጊዜ መሠረት መኪናዎቹን ያስመጣን ቢሆንም፤ በኮቪድ 19 መከሰትና በመርከብ ላይ በደረሰ የተፈጥሮ አደጋ የጊዜ ገደቡ ሊጓተትብን ችሏል›› ብለዋል፡፡
👉‹‹ይህን ከግምት ያላስገባው መንግሥት ዘግይተውም ቢሆን የገቡ ንብረቶቻችንን ለጨረታ እንዲቀርቡ አድርጓልና፤ ይህን ቅሬታችንን ለማሰማት ነው እዚህ የተገኘነው›› ሲሉ ለሸገር ተናግረዋል፡፡
👉በመሆኑም እነዚህ መኪኖች በመታገዳቸው ምክንያት መንግሥት እና እናንተ ምን ያህል ኪሳራ ያጋጥማችኋል? ብለን ጠይቀናቸው፣ ከ6 እስከ 20 ቢሊየን ብር ድረስ የሚጠጋ ኪሳራ ሊያጋጥም ይችላል ብለውናል፡፡
👉150 የሚሆኑት እነዚሁ መኪና አስመጪዎች ከ180 በላይ መኪኖች እንደተያዙባቸው ተናግረዋል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ነው።
@YeneTube @Fikerassefa

አዲስ አበባ ለጎብኚዎች ተመራጭ መዳረሻ ዝርዝር ውስጥ ተካተተች!
በአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት፣ለጎብኚዎች ተመራጭ መዳረሻዎች ናቸው ከተባሉ ከተሞች ስም ዝርዝር ውስጥ አዲስ አበባ ተካተተች፡፡
Condé Nast Traveler የተሰኘ መፅሄት በ2021 አዲሱ የፈረንጆች ዓመት፣ለጎብኚች ጥሩ መዳረሻዎች ናቸው ሲል ከዘረዘራቸው 21 ከተሞች ውስጥ የአዲስ አበባ ስም ይገኝበታል፡፡
መፅሄቱ፣በከተማይቱ የሚገኙትን እንደ አንድነት እና እንጦጦ ያሉ ፓርኮችን ቀዳሚ የጎብኚዎች መዳረሻ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡
ሙዚየሞችን ጨምሮ፣ቦሌ ዓለም-አቀፍ አየር ማረፊያ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ስፍራዎች ለጎብኚዎች ጥሩ መዳረሻዎች መሆናቸውን መፅሄቱ ጠቁሟል፡፡
ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ፤ ኒውዮርክ ፣ ኦስሎ እና ኪዮቶ-ጃፓን በዚህ በስም ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ከተሞች ናቸው፡፡
ይህን ለጎብኚዎች ጥሩ-መዳረሻዎች የሆኑ ከተሞችን ስም ዝርዝር ያወጣው Condé Nast Traveler የተሰኘዉ መፅሄት ዋና መቀመጫዉን በአሜሪካ ኒውዮርክ ያደረገ ሲሆን ፤ በወር ከ5 ሚልየን የማያንሱ አንባቢዎች አሉት፡፡
ምንጭ:-ብስራት ራዲዮ
@Yenetube @Fikerassefa

ትምህርት ሚኒስቴር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እስከ ታህሳስ 30 ተሰጥቶ ይጠናቀቃል አለ!
የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው የግዜ ሰሌዳ መሰረት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሁሉም ክልሎች እስከ ታህሳስ 30 ተሰጥቶ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።ይህንንም ተከትሎ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየትና አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ፈተናውን በተያዘለት የግዜ ገደብ ለመስጠት የራሳቸውን የግዜ ሰሌዳ እያወጡ ይገኛሉ።በዚህም መሰረት የሀረሪ ክልል ከ ታህሳስ 7-9፣ የአማራ ክልል ከታህሳስ 12-14 ፈተናውን ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።ሌሎች ክልሎችም በቀጣይ ቀናት ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ይፋ የሚያደርጉ ይሆናል።በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከትላንት ጀምሮ መሰጠት መጀመሩ ይታወሳል።
[MoE]

በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ ፓርክ በ70 ሚሊዮን ዩሮ ካፒታል ወደ ስራ የገባው የሶፍሌት ማልት ኢትዮጵያ መጋቢት ወር ላይ ምርት ይጀምራል ተባለ!
በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ ፓርክ በ70 ሚሊዮን ዩሮ ኢንቨስትመንት ካፒታል ወደ ስራ የገባው የሶፍሌት ማልት ኢትዮጵያ ፋብሪካ መጋቢት ወር ላይ ምርት ይጀምራል ተባለ፡፡ፋብሪካው በፈረንሳይ ቀዳሚ የጥራጥሬ ሰብሳቢ ሲሆን በ70 ሚሊዮን ዩሮ ኢንቨስትመንት ካፒታል ወደ ስራ ገብቷል፡፡ተቋሙ በ10 ሄከታር ላይ የሚያርፍ የብቅል ፋብሪካ እየገነባ ያለ ሲሆን ከጅምሩ ከ25ሺ አርሶ አደሮች ጋር የምርት ትስስር ፈጥሮ እየሰራ ይገኛል፡፡
በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር ትስስሩን ወደ 40 ሺ ለማሳደግ አቅዶ እየሰራ እንዳለ ከኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ሙሉ በሙሉ የሀገር ውስጥ የግብርና ምርትን ተጠቅሞ ከመቶ ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ ብቅል በአመት የማምርት አቅም ያለው ይህ ፋበሪካ በመጋቢት 2013 ዓ.ም ወር ምርት ይጀምራል ተብሏል፡፡
[FBC]

ኦባማ፣ ቡሽና ክሊንተን በቲቪ መስኮት እየታዩ ሊከተቡ ነው!
የቀድሞዎቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንቶች ባራክ ኦባማ፣ ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ እና ቢል ክሊንተን በቴሌቪዥን መስኮት እየታዩ የኮቪድ-19 ክትባት ለመወጋት ቃል ገብተዋል።ሶስቱ የቀድሞ መራሄ መንግሥታት ክትባቱ በአሜሪካ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ፈቃድ ካገኘ በኋላ ክንዳችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል ብለዋል።ሁለቱ ዴሞክራቶች ኦባማና ክሊንተን እንደሁም ሪፐብሊካኑ ቡሽ በጤና ሙያ ጥርሳቸውን የነቀሉ ሰዎችን ይሁንታ ካገኙ በኋላ ነው የሚከተቡት።የቀድሞዎቹ መሪዎች ይህን ለማድረግ የቆረጡት ሕዝቡ በክትባት ላይ ያለው እምነት እንዲፀና በማሰብ ነው።
[BBC]

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዳማ ከተማ አስተዳድር የመሬት ይዞታን ለማዘመን 940 ህገወጥ ቤቶች ትናንት ማፍረስ ተጀምሯል፡፡
የአዳማ ከተማ የመሬት አስተዳደር ሃላፊ አቶ ደስታ መርጋ ስራዉ ከነዋሪዎቹ ጋር በመነጋገር እና በመተባበር መሳካቱን ገልፆ ቤት ለፈረሰባቸው ነዋሪዎችም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ችግሩን በማስተካከል አዲስ ቦታ ከነካርታ እና ፕላን እንደሚያስረክቡ አክሏል።ቤት የፈረሰባቸው ነዋሪዎችም ይህ ተግበራ እስኪጠናቀቅ ድረስ አቅም ያላቸው ሰዎች በኪራይ እንዲቆዩ አቅም የሌላቸው ደግሞ በላስቲክ ቤት ተጠልለው በመቆየት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ካርታ እና ፕላን እንደሚረከቡ ገልፀዋል።
[@addiszeybe]

በሃገሪቱ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ልጆች በነጻ ለማስተማር ቃል እየገቡ ነው፡፡
ከሁለት ዓመታት በፊት በሃገሪቱ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች በቻሉት መጠን ለሃገር ክብር ዘብ የቆሙ የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ልጆች እንዲያሰተምሩ በጋዜጠኛ ባሪያስ በዛብህ የግል ተነሳሽነት በተጠየቁት ጥያቄ መሰረት በመጀመሪያ ጉዞው በሀዋሳና ሻሸመኔ ከተሞች የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለው የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ልጆችን በነጻ ለማስተማር ቃል ገብተዋል፡፡በሀዋሳና ሻሸመኔ የሚገኙና ይህንን ዓላማ ለመደገፍ ቃል የገቡ የግል ትምህርት ቤቶችም እንዳላቸው የቅርንጫፍ ብዛት ተማሪዎችን ተቀብለው እንደሚያስተምሩ ነው ለትምህርት ቤቶቹ ጋዜጠኛ ባሪያስ በዛብህ የቀረበው ይህ ጥያቄ ተቀባይነት ሊያገኝ የቻለው፡
ጋዜጠኛ ባሪያስ በዛብህ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገረው በሻሸመኔ የሚገኘው ሉሲ ትምህርት ቤት ባሉት አምስት የማስተማሪያ ቅርንጫፎች አንድ አንድ ተማሪ ለመቀበል ቃል ገብተዋል፡፡የመከላከያ ሰራዊት አባላት ልጆችን ተቀብለው በነጻ ለማስተማር ቃል ከገቡ የክልል ከተሞች ትምህርት ቤቶችም በሃዋሳና ሻሸመኔ የሚገኙት ቢኤንቢ፣ ሉሲ፣ ዩኒየን ማውንት፣ ኦሊቭና ኤስ ኦኤስ ትምህርት ቤቶች ናቸው።ይህንን መልካም ተግባር በአዲስ አበባና በክልል ከተሞችም እንዲቀላቀሉ የማስቀጠል እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ጋዜጠኛ ባሪያስ በዛብህ አስታውቋል፡፡
Via Ethio FM

በአዲስ አበባ ከተማ በአንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል!
ቅዳሜ ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ፣
• በኮተቤ ብረታ ብረት፣ በኮተቤ ኪዳነምህረት ቤተ-ክርስትያን፣ በአንቆርጫ እና አካባቢዎቻቸው፣
በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ፣
• በግብፅ ኤምባሲ፣ በስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ፣ በየካቲት ሆስፒታል፣ በቅድስተ ማርያም ቤተ-ክርስትያን ጀርባ፣ በእሪ በከንቱ፣ በፒያሳ፣ በቀይ ባህር ኮንደሚኒየም፣ በተፈሪ መኮንን ጀርባ፣ በአፍንጮ በር፣ በናይጄሪያ ኤምባሲ፣ በችሎት፣ በጉቶ ሜዳ እና አካባቢዎቻቸው፣
ሰኞ ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ፣
• በላምበረት፣ በመገናኛ፣ በየካ ሚካኤል፣ በሾላ ገበያ፣ በትምህርት ስርጭት፣ በእግዚአብሄር አብ ቤተ-ክርስትያን፣ በሜጋ እና አካባቢዎቻቸው፣
በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡30 ሰዓት ድረስ፣
• በሃና ማርያም፣ በኃይሌ ጋርመንት፣ በቆጣሪ ኮንደሚኒየም፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ በማንጎ ሰፈር፣ በወሰን ግሮሰሪ፣ በወንድይራድ ት/ቤት፣ በባድሜ ሰፈር እና አካባቢዎቻቸው፣
በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ክቡራን ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ አሳውቋል፡፡
[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
አደጋው በድሎ ሬጴ ቀበሌ ውስጥ ትናንት ማምሻውን መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽንናና ሚዲያ ሃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ ተናግረዋል፡፡በዚህም አሽከርካሪውን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ህይወት ወደያውኑ ማለፉን አስታውቀዋል።አደጋው የደረሰው ከቡታ ጅራ ወደ ባቱ እየተጓዘ የነበረ ሚኒባስ የህዝብ ማመላለሻ 16 ሰዎች ጭኖ በፍጥነት ሲጓዝ በመገልበጡ መሆኑን ኮማንደር አስቻለው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።በአደጋው ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች በተጨማሪ አምስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶ በአዳማ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።ከአደጋው አራት ህፃናት ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው መትረፉቸውን ኮማንደር አስቻለው አመልክተዋል።
[ENA]

ሠራተኛ እና አሠሪን በቀጥታ ሊነጋገሩበት የሚያስችል አሠራር ተዘረጋ!
ደረጃ ዶት ኮም ከኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ከማስተር ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ለተመራቂዎች ተማሪዎች የሥራ እድልን ለመፍጠር፤ ሠራተኛና አሰሪ በቀጥታ የሚገናኙበትን የበይነ መረብ መድረክ መዘርጋቱ በዛሬው እለት ይፋ ተደርጓል።
[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
ደረጃ ዶት ኮም ከኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ከማስተር ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ለተመራቂዎች ተማሪዎች የሥራ እድልን ለመፍጠር፤ ሠራተኛና አሰሪ በቀጥታ የሚገናኙበትን የበይነ መረብ መድረክ መዘርጋቱ በዛሬው እለት ይፋ ተደርጓል።
[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
አቢሲንያ ባንክ ለሠማይ ጠቀስ መንትያ ህንጻዎች ግንባታ አለም አቀፍ ጨረታ አወጣ!
አቢሲንያ ባንክ ከሚድሮክ ተነጥቆ በምትክ በተሠጠው 10,329 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ሠማይ ጠቀስ መንትያ ህንጻዎች ለመገንባት ረቡዕ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱ ተገለፀ።ባንኩ ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ መሰረት ከፍታቸው 50 እና 60 ወለል የሆኑ መንትያ ህንጻዎችን ለመገንባት በዲዛይን ቢውልድ (design build) ቀመር ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ኮንትራክተሮች ግብዣ አድርጓል።አቢሲንያ ባንክ ያቀደው ግንባታ እውን ከሆነ መንትያ ህንጻዎቹ በከተማው ረጃጂሞቹ ህንጻዋች ከመሆናቸው ባሻገር፣ ዋና መስሪያ ቤታቸውን ለመገንባት ዕቅድ ለያዙ የፋይናንስ ተቋማት መነሻ (ቤንች ማርክ) ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ቦታው በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ፋይናንሻል ዞን ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል ጎን የሚገኝ ደረጃ አንድ ቦታ ነው። ይህንን ቦታ ለማግኘት በርካታ ባንኮች ቢረባረቡም ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ቦታው አቢሲንያ ባንክ እጅ ውስጥ መግባቱም ተገልጿል።ይህ ቦታ ለዓመታት በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ስር በነበረው ሁዳ ሪል ስቴት ተመዝግቦ ቆይቷል። በከተማው አምስት ከንቲባዎች እየተፈራረቁ ቦታውን ሲነጥቁ ሲመልሱ፣ ካርታ ሲያመክኑ እና ውል ሲያድሱ ቢቆዩም፣ ያለምንም ግንባታ ለሁለት አስርት ዓመታት ቦታው ታጥሮ ቆይቷ ተብሏል።በከተማው ታሪክ ጉልህ ውሳኔዎችን ከሰጡ ጥቂት ከንቲባዎች አይረሴ የሆኑት ታከለ ኡማ፣ ስልጣን በተረከቡ ማግስት ይህንን ጨምሮ 154 ጦማቸውን የከረሙ ቦታዎችን ወደ መሬት ባንክ አስገንብተዎል።
አቢሲንያ ባንክ ይህን የብዙዎች አይን ያረፈበትን ቦታ ሊያገኝ የቻለው በምትክ እንደሆነም ተነግሯል። በአፍሪካ ጎዳና (ቦሌ መንገድ) ፍላሚንጎ አካባቢ የሚገኘው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ግዙፍ ግንባታዎችን ለማካሄድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል።አስተዳደሩ ለክልሉ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት 70 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ የፈቀደ ሲሆን፣ እዚህ ቦታ ላይ የአቢሲንያ ባንክ ሦስት ይዞታዎች ጨምሮ በርካታ የንግድ እና መኖርያ ቤቶች የመነሳታቸው ጉዳይ እርግጥ ሆኗል።በዚህ መሠረት የአቢሲንያ ኃላፊዎች ከከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ጋር በጥልቀት በመነጋገር፣ የተወሰዱበት ሦስት ቦታዎች በአንድ ያጠቃለለ ቦታ፣ ቦታውም ከዋቢ ሸበሌ ጎን ያለው እንዲሆን ምክረ ሀሳብ አቅርቦ ተቀባይነት አግኝቷል።ከዚህም ሌላ፣ ባንኩ በምትክ ከሚሰጠው 7,280 ካሬ ሜትር ቦታ በተጨማሪ ፣ 3,049 ካሬ ሜትር ቦታ ብልጫ ያለው በድምሩ 10,329 ካሬ ሜትር ቦታ ለማግኘት መቻሉን አዲስ ማለዳ ዘግቧል።

በሰላም ማስከበር ወቅት የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን የመማር ማስተማሩ ስራ በሁሉም ቦታ ይጀምራል - የትምህርት ሚኒስቴር
በትግራይ ክልል የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን በመጠገን ትምህርት ለማስጀመር 50 ሚሊየን ብር በጀት መያዙን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሚሊየን ማቲዎስ ገለጹ።በአማራ ክልል አጎራባች አካባቢዎች በህግ ማስከበር ሂደቱ የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን በመጠገን ወደ ስራ ለማስገባትም እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል። ለትግራይ ክልልም ከ700 ሺህ በላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መዘጋጀቱንም ጠቁመዋል።ሚኒስቴሩ ትምህርት በሁሉም አካባቢ እንዲጀመር ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ይታወሳል።
Via MoE

በባሕር ዳር ከተማ ውሃ ተበክሏል በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት መሆኑን አገልግሎቱ ገለጸ፡፡
በከተማዋ ውሃ ተበክሏል በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት መሆኑን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት አስታውቋል፡፡ከዚህ በፊትም የከተማውን ሕዝብ ሰላም ለመንሳት በተደጋጋሚ ውሃ እንደተበከለ ተደርጎ በሀሰት ይወራ እንደነበር የአገልግሎቱ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በሪሁን አለሙ ተናግረዋል፡፡ይሕ የበሬ ወለደ ወሬ የወራሪው፣ ተስፋፊውና አሸባሪው ወያኔ ቅጥረኞች የሕዝቡን ሰላም ለመንሳት የፈጠሩት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡ዛሬም በከተማ አስተዳደሩ ውሃ እንደተበከለ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ ፍጹም ሀሰት መሆኑን ነው ያስታወቁት፡፡
አቶ በሪሁን እንዳሉት የከተማ አስተዳደሩ የውሃና ፍሳሽ ባለሙያዎች በየዕለቱ በሁሉም ቦታዎች (ታንከር ላይ፣ መሥመር ላይና ቤት ለቤት በመዞር) የፊዚካል፣ ባዮሎጂካልና የኬሚካል ናሙና ምርመራ ይደረጋል፡፡ዛሬና ትናንት በተደረገ የናሙና ምርመራ ምንም ችግር እንደሌለ መረጋገረጡንም ገልጸዋል፡፡
በተለይ ዛሬ ውሃ ተበክሏል በሚል ሥጋት ጥቆማ በተደረገባቸው የከተማዋ አካባቢዎች ናሙና ተወስዶ ምንም አይነት ችግር አለመኖሩ ተረጋግጧል ነው ያሉት አቶ በሪሁን፡፡የከተማው ውሃ በቀላሉ የሚበከል አለመሆኑን ያስታወቁት አቶ በሪሁን በተለይም አጠራጣሪ በሆኑ አካባቢዎች የተጠናከረ ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በኋላም የጥበቃ ሥራው መጠናከሩን ተናግረዋል።በመሆኑም ሕዝቡ እውነቱን ተገንዝቦ ያለምንም መረበሽ የእለት ተዕለት ተግባሩን እንዲከውን መክረዋል፡፡
[AMMA]

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያየ!
የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ም/ቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የምስክርነት ማዳመጥ ውይይት አደረገ፡፡በኮሚቴው የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኬረን ባስ ውይይቱ በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ግፊት የተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡‹‹ኢትዮጵያ ሰላም እና አንድነቷን እንድታገኝ በማገዝ ረገድ ዩናይትድ ስቴትስ ጠቃሚ ሚና እንዲኖራት እንፈልጋለን›› ብለዋል ሰብሳቢዋ፡፡ለኮሚቴው የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡት የአዲስ ስታንዳርድ መጸሄት ዋና አዘጋጅ ፀዳለ ለማ ባለፉት 2 ዓመታት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶጦች መፈጸማቸውን አስታውሰዋል፡፡በመሆኑም ነጻና ግልጽ ምርመራ ማድረግ የሚችል ገለልተኛ የተባበሩት መንግስታት አጣሪ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊሰማራ ይገባል ብለዋል፡፡
የፍሪደም ሀውስ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ዮሴፍ ባድዋዛ፤ በዚህ ዓመት ከሚካሄደው ምርጫ አስቀድሞ የኢትዮጵያ መንግስት እና ፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉን ዐቀፍ ምክክር እንዲያደርጉ ዩናትድ ስቴትስ ጫና እንድታደርግ ጠይቋል፡፡በምክር ቤቱ ባለሙያ የሆኑት ሎረን ብላንቻርድ በበኩላቸው አሁን ላይ በትግራይ ክልል ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ የመረጃ እጥረት መኖሩን ነው የገለፁት፡፡ምክር ቤቱ ያደረገው የምስክርነት ማዳመጥ ውይይት የመጨረሻ እንደማይሆን ተጠቁሟል፡፡አሐዱ ቴሌቪዥን የጠየቃቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ በወቅታዊው ሁኔታ ላይ ሀሰተኛና ሚዛናዊ ያልሆነ መረጃ የሚያቀርቡ መኖራቸውን በመጠቆም የኮሚቴውን ስብሰባ አጣጥለውታል፡፡የኢትዮጵያ ኢሜባሲዎች ‹‹ከእንቅልፋቸው ነቅተው›› እውነታውን ለዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ በማሳወቅ በኩልም ከፍተኛ ርብርብር እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡
[አሐዱ ቴሌቪዥን]
@YeneTube

የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ የሚያገለግል የህክምና ቁሳቁስ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ተገለጸ!
የጁንታው ቡድን የፈጸመውን የአገር ክህደት ተከትሎ የተጎዱ ወገኖችንና የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ የሚያገለግል የህክምና አቅርቦት አዲስ አበባ መድረሱን የአለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ አስታወቀ ድጋፉ የድንገተኛ ጊዜ የህክምና ቁሳቁስና የኮቪድ መከላከያዎችንም ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል።አሁን የመጡት የህክምና ቁሳቁሶች በትግራይ ክልል ለሚሰጠው ድጋፍ እገዛ እንደሚያደርግ ኢዜአ ከአለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ መረጃ ያሳያል።