YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሱዳን ከትግራዩ ግጭት ሸሽተው ወደ ግዛቷ የገቡ 50 ወታደሮችን እና ፖሊሶችን ለኢትዮጵያ አሳልፋ እንደሰጠች ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንድ ኮሎኔልን ጨምሮ 31ዱ የጦር ሠራዊት አባላት ሲሆኑ፣ 13ቱ ፌደራል ፖሊሶች፣ 6ቱ ደሞ የጉምሩክ ባልደረባዎች ናቸው ተብሏል፡፡ አባላቱ ተላልፈው የተሰጡት በመተማ በኩል ሲሆን፣ መቼ እንደሆነ ግን አልተገለጸም፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ እና አማራ ክልሎች መካከል ለረጅም ጊዜ የዘለቀው የመሬት ባለቤትነት ውዝግብ የሚፈታው የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን በሚያቀርበው ጥናት መሠረት ብቻ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

በሁለቱ ክልሎች መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየ የመሬት አከላለል ውዝግብ መኖሩን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፣ መፍትሄ የሚሰጠውም መሰል ጉዳዮችን የማጥናት ኃላፊነት ያለበት የአሥተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን በሚያቀርበው ጥናት መሠረት የሕግ አግባብን በተከተለ መንገድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ቀጣዩን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተም በዛሬው ዕለት ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተናግሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመጪው ምርጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ካወጣቸው ሕግጋት በተጨማሪ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ደንብ ማዘጋጀቱንም ተናግረዋል፡፡ፓርቲያቸው ደንቡን ያዘጋጀው ሁሉም የፓርቲው አባላት ነጻ እና ፍትኃዊ ምርጫ እንዲያከናውኑ ለማስቻል ነው ተብሏል፡፡

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን መቐለ ከተማ ገባ!

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ልዩ ኮማንዶና የወንጀል ምርመራ ቡድን ዛሬ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም መቐለ ከተማ መግባቱን አስታውቋል።የፌዴራል ፖሊስ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የጁንታውን ተፈላጊ ወንጀለኛ ቡድን ማደን መጀመሩንም ነው ያስታወቀው።የኮማንዶ ቡድኑ በከተማዋ በሚያደርጋቸው አሰሳዎችና የተለያዩ ኦፕሬሽኖች እንዲሁም በወንጀል ምርመራ ቡድኑ የሚገኙ ውጤቶችን በቀጣይ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተሰየመው ቤተ መጻሕፍት በጅማ ተገንብቶ ተጠናቀቀ!

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፣ ጅማ ዞን ጥሮ አፈታ ወረዳ በጠቅላይ ሚንስተር ዐቢይ አሕመድ የተሰየመ የመጀመሪያ የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት በ2.2 ሚሊዮን ብር ተገንብቷል፡፡የጥሮ አፈታ ወረዳ አስተዳዳሪ፣ አቶ ሃይደር አባመጫ እንደተናገሩት ዘርፈ-ብዙ የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት በወረዳው የህዝብ ተነሳሽነት የተሰራ ሲሆን አከለውም “የተማረና ያነበበ ትውልድ ሁሉንም ማሸነፍ እንደሚችል” ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለአለም ማሳየታቸውን ለማዘከር በስማቸው እንደተሰየመ ተናግረዋል፡፡2.2 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተረገበት እና በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ውስጥ መጠናቀቁ የተነገረው ቤተ-መጽሐፍት ሙሉ በሙሉ በወረዳው የህዝብ ተሳትፈው የተሰራ ሲሆን በሁሉ ደረጃ ላይ የሚገኙ አንባቢዎችን ለማገልገል ታስቦ እንደተሰራም አቶ ሃይደር ለአዲስ ዘይቤ አሰረድተዋል፡፡

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ዋናው የህግ ማስከበር ስራ መጠናቀቁንና ተፈላጊ የ'ጁንታው' አመራሮችም በጥቂት ቀናት ውስጥ በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስተወቁ!

ዋናው የህግ ማስከበር ስራ መጠናቀቁንና ቀሪ ተፈላጊ የጁንታው አመራሮችም በጥቂት ቀናት ውስጥ በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።በአሁኑ ወቅት በርካታ የጁንታው ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስራ መዋላቸውን ከቲአርቲ ወርልድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የጠቀሱት አምባሳደሩ፤ በተለይም ከከሀዲው የህወሓት ዘጠኝ የስራ አስፈጻሚዎች መካከል አንደኛዋ እጃቸውን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት መስጠታቸውን ገልጸዋል።

'ጁንታው' የሚያስተዳደርውን አካባቢ ሙሉ በሙሉ በሶስት ሳምንታት የህግ ማስከበር ዘመቻ አማካኝነት ከቁጥጥሩ ውጭ እንደሆነ የጠቀሱት አምባሳደር ሬድዋን፤ ከዚህ በኋላ ጁንታው ፊት ለፊት ከመንግስት ጋር ሊታኮስ የሚችልበት አቅም እንደሌላው አብራርተዋል።'ጁንታው' ወደሽምቅ ጥቃት ሊገባ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ የተጠየቁት አምባሳደሩ፤ ከዚህ በኋላ 'ጁንታው' በእጁ ያሉ መሳሪያዎች በአብዛኛው በመደምሰሳቸው እና በመማረካቸው እንዲሁም ዓለም ስለጁንታው ትክክለኛ ማንነት በአግባቡ በመረዳቱና ፊታቸውን ስላዞሩበትም ጭምር የተባለውን አይነት ጥቃት ሊፈጸም አይችልም ሲሉ ተናግረዋል።

ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ለምን ወደስፍራው አይገቡም በሚል የተጠየቁት አምባሳደር ሬድዋን፤ ከጁንታው ነጻ በወጡ አካባቢዎች ያለው ሰላም እና ጸጥታ አስተማማኝ ከሆነ በኋላ ጋዜጠኞች እንደሚገቡ ተናግረዋል።ክልከላው ለጋዜጠኞች ደህንነት ሲባል የተደረገ ሲሆን፤ የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞችም በተመሳሳይ እየተስተናገዱ መሆኑን ገልጸዋል።ከስደተኞች ጋር ተያይዞም አምባሳደር ሬድዋን መንግስት አስፈላጊወን ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል አቅም እንዳለውና አስቸኳይ እርዳታ ባልደረሰባቸውና የእርዳታ ምግቦች በጁንታው በተዘረፈባቸው አካባቢዎች መንግስት ለማቅረብ ዝግጁ መሆኑን፤ በጥቂት ቀናት ውስጥም ወደስፍራው እንደሚላክ አብራርተዋል።

ወደሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን በተመለከተም መንግስት ከዚህ ቀደም በውስጥ ግጭት ምክንያት እስከ ሶስት ሚሊዮን ዜጎችን ወደቀያቸው መመለስ ያስቻለ አቅምና ልምድ እንዳለው በመግለጽ፤ አሁን ላይ ወደ ሱዳን ሄደዋል የተባሉትን 40 ሺ አካባቢ የሚጠጉ ዜጎች ወደ ቀያቸው መመለስና ማቋቋም የሚያስችል አቅሙም ዝግጅቱም እንዳለው አምባሳደር ሬድዋን ተናግረዋል።ፈቃደኛ የሆኑ ዜጎች መመለስ እንደሚችሉ የተናገሩት አምባሳደር ሬድዋን፤ መንግስት ዜጎቹን ለመመለስ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሆነና አገሪቷ ከ'ጁንታው' መወገድ በኋላ ምንም የሚያሰጋ ነገር እንደሌላት የማስረዳት ስራ እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል።

[ኢ ፕ ድ]
@YeneTube @FikerAssefa
አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለው ግብጽ በሞት የምትቀጣቸው ፍርደኞች ብዛት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል።ሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ግብጽ ባለፉት ጥቅምትና ኅዳር ወራት ብቻ 57 ሰዎችን በስቅላት ቀጥታለች።ይህም በፈረንጆች 2019 በስቅላት ከተቀጡ ጠቅላላ ሰዎች እጥፍ በ2 ወራት ብቻ መፈጸሙን ያሳያል።ግብጽ በአምነስቲ ዘገባ ላይ ያለችው ነገር የለም።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከወልቃይትና ራያ አካባቢዎች ታፍነው የተወሰዱ ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ ተገለፀ!

በጦርነት የተሸነፈው ህወሓት ሲያስተዳድራቸው ከነበሩት ከወልቃይትና ራያ አካባቢዎች አፍኖ የወሰዳቸው በ10 ሽዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች የደረሱበት አለመታወቁን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።

በማይካድራ ንፁሃን ዜጎችን ጨፍጭፈው ወደ ሱዳን የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ያመሩ ወጣቶች በህግ እንዲጠየቁም ሁኔታዎችን እያመቻቸሁ ነው ብሏል የክልሉ መንግሥት።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉ ታፍነው ተወስደዋል በተባሉ ንፁሀን ዜጎች ላይ መረጃው እንደደረሰውና በቀጣይ እንደሚያጣራ ገልጿል።በማይካድራ የተጨፈጨፉ ዜጎች ቁጥር እንደሚጨምርም ኮሚሽነሩ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት በአዲስ አበባ እና በጋምቤላ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ!

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት በአዲስ አበባ እና በጋምቤላ ውስጥ ከሌሎች አካባቢዎች በተሌ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ።የፌደራል የኤችአይቪ ኤድስ የመከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ኮምንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል በትረ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ ከፍተኛ የቫይረሱ ስርጭት የተመዘገበው በሁለቱ አካባቢዎች መሆኑን አመልክተዋል።እንዲሁም በሶማሌ ክልል፣ ደቡብ ክልል፣ ኦሮሚያ ክልል እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ውስጥ ደግሞ የቫይረሱ የስርጭት መጠን በአንጻራዊነት ዝቅተኛ እንደሆነ ተገልጿል።

አቶ ዳንኤል ጨምረው እንዳሉት፤ በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ669 ሺህ በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤ የቫይረሱ አገር አቀፍ የስርጭት መጠን ደግሞ 0.93 በመቶ ነው።የኤችአይቪ/ኤድስ የስርጭት ሁኔታ ከክልል ክልል የተለያየ እንደሆነው ሁሉ ልዩነቱ በከተሞችና በገጠር አካባቢዎች ይስተዋላል። በዚህም መሠረት በከተሞች አካባቢ የበሽታው ስርጭት ከፍተኛ ነው።አቶ ዳንኤል እንዳሉት የበሽታው ስርጭት መጠን በከተማና በገጠር ሲነጻጸር፤ በከተማ 3 ከመቶ ሲሆን በገጠር ደግሞ 0.4 በመቶ ነው።የስርጭት መጠኑ ከአንዱ ክልል በሌላው እንዲሁም በየማኅበረሰቡ እንደሚለያይ የገለጹት አቶ ዳንኤል፤ "በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ፣ የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች እና ተንቀሳቃሽ ሠራተኞች አካባቢ የስርጭት መጠኑ ከፍተኛ ነው" ብለዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው!

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነው እያካሄደ የሚገኘው፡፡በስብሰባው የምክር ቤቱን 6ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ  እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡ከዚህ ባለፈም በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክርም ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ መሰጠት ተጀመረ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ዛሬ እና ነገ ይሰጣል።በወጣው መርሐ ግብር መሠረት የዛሬው ፈተና ተማሪዎች በየተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች መሰጠት ተጀምሯል።

@YeneTube @FikerAssefa
አርቲስት መላከ ገብሬ ከዚህ አለም በሞት ተለየ!

የዋልያስ ባንድና የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማህበር መሥራች አርቲስት መላከ ገብሬ ባደረበት የካንሰር ህመም በህክምና ሲረዳ ከቆየ በኋላ ትናንት ሕይወቱ አልፏል።የቀብር ስነ ስርአቱ አርብ እለት በ Virginia USA እንደሚፈፅም ልጁ ሚካኤል መላከ በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል፡፡

በ1949 ዓ.ም የተወለደው አርቲስቱ በ60ዎቹ ዓ.ም መጀመርያ ላይ ነበር ቀድሞ አብረውት በቬነስ ባንድ ከነበሩት አጋሮቹ ጋር ዋልያስ ባንድን የመሰረቱት፡፡

እስከ 80ዎቹ አጋማሽ ድረስ የቆየው ባንዱ ከበርካታ አንጋፋ ሙዚቀኞች ጋር እጅግ ብዙ ዜማዎችን ለህዝብ ጆሮ አድርሷል፡፡ኢትዮጲያ ዉስጥ ያሉ የአርቲስቱ አዲናቂዎችና ወዳጆች በተገኙበት የሽኝት ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ ኅዳር 26 ቀን ከ ቀኑ በአምስት ሰዓት በብሄራዊ ቲያትር እንደሚደረግለት ሚካኤል መላከ ገልጿል፡፡

[@addiszeybe]
@YeneTube @FikerAssefa
ሕብረት ባንክ ዘንድሮ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኔ 34.7 ቢሊዮን ደርሷል አለ።

ባንኩ በ2019/20 የበጀት ዓመት፤ ከግብር በፊት ከመጠባበቅያ ተቀናሽ በኋላ 1.13 ቢሊየን ብር ትርፍ አግኝቻለሁ ብሏል።ባንኩ ያገኘሁትን ትርፍ ከባለፈው ዓመት ጋር ሳነጻጽረው የ19.45 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ብሏል።ከወለድ ነፃ በሰጠሁት የባንክ አገልግሎትም 1.23 ቢሊየን ብር መሰብሰብ ችያለሁ ብሏል።

የሕብረት ባንክ የተከፈለ ካፒታል ባለፈው ዓመት ከነበረበት 2.26 ቢሊዮን የ41 በመቶ ጭማሪ አድርጎ 3.12 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል።ባንኩ ሙሉ በሙሉ በተከፈለበት አክስዮን ላይ የ20.51 በመቶ የትርፍ ክፍፍል ይደረጋል ማለቱ ተሰምቷል።የሕብረት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኢየሱስወርቅ ዛፉ በባንኩ 23ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ የአገልግሎት ዘመን ላይ ማሻሻያ ተደረገ፡፡

ቀደም ሲል የከተማዋ የነዋሪዎች መታወቂያ ሊያገለግል ይችል የነበረው 2 ዓመት ሲሆን አሁን ወደ 4 ዓመት ከፍ እንዲል መደረጉን ተሰምቷል፡፡4 ዓመት የአገልግሎት ጊዜ የሆነ የነዋሪነት መታወቂያ ከዛሬ ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን የተናገሩት የከተማዋ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ የአገልግሎት ክፍያው ላይም ማሻሻያ ተደርጓል ብለዋል፡፡በዚህም ከዚህ በፊት መታወቂያ ለመወሰድ ይከፈል የነበረው ክፍያ 20 ብር ቀርቶ ለአዲስ ማኑዋል መታወቂያ 80 ብር፣ ለዲጂታል መታወቂያ ደግሞ 100 ብር ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የዲጂታል መታወቂያውን በሚፈለገው መጠን ለመስጠት አንደኛው ችግር የኔትወርክ መቆራረጥን መሆኑን ሀላፊው ተናግረዋል፡፡ሌላኛው ደግሞ ኤጀንሲው የራሱ የሆነ የዳታ ሴንተር የሌለው መሆኑን የተናገሩት አቶ ዮናስ ይህንን ችግር ለመፍታት ዘንድሮው ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቶ ኤጀንሲው የራሱን ዳታ ማዕከል እንዲኖረው ለማድረግ መታሰቡን፤ ለዚህም 40 ሚሊዮን ብር መበጀቱን ተናግረዋል፡፡ይህም ለነዋሪነት መታወቂያ ብቻ ሳይሆን የልደት፣ የጋብቻ ፣ የፍቺ ፣የላገባ የምስክር ወረቀቶች በአሻራና በዲጂታል ምዝገባ እንዲሆኑ ያግዛል ብለዋል፡፡

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ የብድርና ዕርዳታ ስምምነት ተፈራረሙ!

በኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ መካከል የ512 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የብድርና ዕርዳታ ስምምነት ተፈረመ፡፡ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴና የዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ዑስማን ዲዮን ተፈራርመውታል፡፡በስምምነቱ መሰረት 312 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላሩ ዕርዳታ ሲሆን 200 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ ብድር ነው፡፡ገንዘቡ በኢትዮጵያ እየተከናወነ የሚገኘውን የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር ለማጠናከርና ከዚህ ቀደም በመርሃ ግብሩ ያልተካተቱ ተጨማሪ ቦታዎችን ለማገዝ ይውላል ነው የተባለው፡፡መርሃ ግብሩ በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚገኙ የገጠር አካባቢዎችን እና በድርቅ ምክንያት ለምግብ ዕጥረት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በየሳምንቱ ለምርመራ ከሚመጡ ዜጎች ውስጥ ከ120 እስከ 150 የሚጠጉ ዜጎች በካንሰር እንደሚያዙ ነው የተገለጸው፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስቱ ዶ/ር አይናለም አብርሀ ካንሰር እና የጨረር ህክምና በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስል ማብራርያ በሰጡበት ሰአት ነው ይህንን የተናገሩት፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ የካንሰር በሽታ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝም ነው ዶ/ር አይናለም የተናገሩት፡፡

ለዚህም እንደምክንያት ያስቀመጡት የህዝቡ የአኗኗር ሁኔታ የህክምና እጥረት እና የአመጋገብ ባህሪያችን ዋነኞቹ ምክንያት እንደሆኑ ነው የተናገሩት፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በአጠቃላይ ከሚፈጠረው የካንሰር መጠን ወደ 33 ከመቶ የሚሆነው የጡት ካንሰር እንደሆነም ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡

በሴቶች ላይ 30 ከመቶ የሚሆነው የጡት ካንሰር አንደኛ ደረጃን ሲይዝ፣ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ የአንጀት ካንሰር እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡ በወንዶች ላይ ደግሞ በአንደኛ ደረጃ የትልቁ አንጀት ካንሰር፣ በሁለተኛ ደረጃ የፕሮስቴት ካንሰር እና ከተለያዪ እጢዎች የሚነሱ የካንሰር አይነቶችን ይጠቀሳሉ።

በኢትዮጵያካንሰር በርካቶችን በዋናነት ለህልፈት ከሚያበቁ ተላላፊ ያልሆኑ አራት በሽታዎች አንዱ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይገልፃል። በሀገሪቱ ትክክለኛ ምዝገባ ባለመኖሩ ምን ያህል ሰው በካንሰር እንደተያዘ ለማወቅ አደጋች እንደሆነ ነው የተነገረው

Via EthioFM
@Yenetube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል ሰሞኑን በተካሄደው ግጭት አራት የረድኤት ሰራተኞች ተገድለዋል ተባለ!

ሮይተርስ የዜና ወኪል ከናይሮቢ እንደዘገበው በትግራይ ክልል በተካሄደው ዉጊያ በኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ለሁለት የተለያዩ የውጭ ድርጅቶች ይሰሩ ነበር የተባሉ አራት ኢትዮጵያዊያን ተገድለዋል።ዜና አገልግሎቱ አክሎ የዕርዳታ ሰራተኞቹ መገደላቸውን ትናንት ረቡዕ ከባልደረቦቻቸዉ ከረድኤት ሰራተኞችና ከዲፕሎማቲክ ምንጮች አረጋግጫለሁ ብሏል።ሟቾቹ ኤርትራውያን ስደተኞች ከሠፈሩባቸዉ አራት ካምፖች ውስጥ በአንዱ ይሰሩ የነበረ ሲሆን የሞቱበት ሁኔታ ግን ግልፅ አለመሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡የሟቾቹ ቀጣሪዎች የሆኑት የዕርዳታ ድርጅቶች አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውንም ዘገባው አያይዞ ገልጿል።የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስትና የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ታጣቂዎች ለ3 ሳምንት ተኩል በገጠሙት ዉጊያ ስለጠፋ ሕይወትና ንብረት በግልፅ የተነገረ ነገር የለም።የርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ስለመገደላቸዉም ሁለቱም ወገኖች እስካሁን በይፋ ያስታወቁት ነገር የለም።

[Reuters/DW]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው! የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነው እያካሄደ የሚገኘው፡፡በስብሰባው የምክር ቤቱን 6ኛ አመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ  እንደሚያጸድቅ…
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኑክሌርን ለሰላማዊ አገልግሎት የማዋል ስምምነት ረቂቅ አዋጅን አፀጸደቀ!

ረቂቅ አዋጁ የፀደቀው ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት እያካሄደ በሚገኘው 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ኒውክሌርን ለሰላማዊ ዓላማ የማዋል ስምምነት ረቂቅ አዋጅን የሚመለከት ነው። ስምምነቱ የዕውቀት ሽግግርን ለመፍጠር የሚያግዝ፣ ለአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ የሚያደርግ እና ይህን የሚደግፉ አሰራሮች የማበጀት ግዴታ የሚጥል ነው።በተጨማሪም አዋጁ ሀገሪቱ የሀይል አማራጭ እንዲኖራት የባለሙያወችን አቅም ለመገንባት እና ልምድ ለመለዋወጥ እንደሚረዳ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ የሚገነባው የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል በ 2 ሳምንታት ይጠናቀቃል ተባለ!

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ እየተገነባ ያለው የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል የግንባታ ሥራ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ፡፡የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ወደ አንድ ቢሊዮን ብር በሚጠጋ የኮንትራት ዋጋ እየገነባ የሚገኘውን ተለዋጭ የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ አስታውቋል፡፡

የገበያ ማዕከሉን በሁለት ምዕራፍ ከፋፍሎ እየገነባ የሚገኝ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ 14 የገበያ ሼዶች፣ በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ የፓርኪንግና የአረንጓዴ ቦታዎች፣ መጋዘኖች፣ የአስተዳደር ህንጻዎች እና ሌሎች የግንባታ ስራዎች ይከናወናሉ።የገበያ ማዕከሉ 80 ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ሲሸፍን፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ የሚገነቡት 14 ሼዶች ውስጥ 588 የመገበያያ ሱቆች እንዳሏቸው የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት መረጃ ያመለክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ቤተ እስራኤላውያኑ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው!

ትናንት ወደ እስራኤል ያቀኑት 316 ቤተ እስራኤላውያን ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ቤተ እስራኤላውያኑ እስራኤል በደረሱ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን ጨምሮ ምክትል የደህንነት ሚኒስትሩ ጋዲ ይባርከን እና ሌሎችም ከፍተኛ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል፡፡ከአውሮፕላን በወረዱ ጊዜ ባሳዩት የተለየ የደስታ አገላለጽ መገረማቸውን የገለጹት ኔታንያሁን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክትን አስተላልፈዋል፡፡በነገው ዕለት ተጨማሪ 100 ቤተ እስራኤላውያን ይመጣሉም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፡፡ምክትል የደህንነት ሚኒስትሩ ጋዲ በበኩላቸው የረዥም ዓመታት የወሰደው ልፋት ፍሬ ማፍራቱን ገልጸዋል፡፡ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ከነበሩት የስደተኛ እና ስደት ተመላሾች ሚኒስትሯ ፕኒና ታመነ ጋር ወደ ያቀኑት ቤተ እስራኤላውያኑ በቀጣዮቹ 2 ወራት ውስጥ ወደ እስራኤል እንደሚያቀኑ ከሚጠበቁት 2 ሺ ቤተ እስራኤላውያን መካከል ናቸው፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ አቅርቦት በነበረው የክስ መዝገብ ላይ ምስክሮችን አሰማ!

በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ዙሪያ ክስ በተመሰረተባቸው 1ኛ ጥላሁን ያሚ፣ 2ኛ ከበደ ገመቹ፣ 3ኛ አብዲ አለማየሁ፣ 4ኛ ላምሮት ከማል ላይ ዓቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለፍርድ ቤት አሰምቷል፡፡የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብር እና ህገ-መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ባስቻለው ችሎት ዓቃቤ ህግ ተከሳሾች በክሱ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸማቸውን ያስረዱልኛል በሚል ያቀረባቸውን 12 ምስክሮች አሰምቷል፡፡በስተመጨረሻም ምስክሮቹን ያዳመጠዉ ችሎት የምስክሮችን ቃል መርምሮ ብይን ለመስጠት ለየካቲት 10/ 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተከሳሾቹ ላይ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀፅ 3/2 ስር ክስ መመስረቱ ይታወሳል፡፡

[AG]
@YeneTube @FikerAssefa