YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በማይካድራ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል በሚል በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የተገለጸው የሟቾች ቁጥር ስህተት እንዳለበትና ከተጠቀሰውም በላይ እንደሆነ ተገለጸ።

የህወሃት ቡድን በልዩ ሃይሉ አማካኝነት በአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በሰሜን ኢትዮጵያ የህግ ማስከበር ዘመቻ ከተጀመረ 18ኛ ቀኑ ላይ ደርሷል።የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በማይካድራ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ ቦታው ላይ በነበረው የመንግስት አስተዳድር ወይም በትግራይ የጸጥታ ሃይል አጋዥነት እና ሳምሪ በተሰኘ የወጣቶች ቡድን መፈጸሙንም በያዝነው ሳምንት ማሳወቁ አይዘነጋም።ኮሚሽኑ በዚህ አሰቃቂ እና ማንነትን መሰረት ባደረገ የግድያ ወንጀል በማይካድራ 600 ንጹሀን ዜጎች መገደላቸውን ገልጿል።የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል የገለጸው ኮሚሽኑ ክስተቱ የጦር ወንጀል የመሆን እድሉ የሰፋ ሊሆን እንደሚችልም በቅድመ ምርመራ ሪፖርቱ ጠቁሟል።

ይሁንና በቦታው ያሉ የህክምና ባለሙያዎች በኮሚሽኑ የተጠቀሰው ቁጥር ስህተት አለበት ሲሉ የህክምና ባለሙያውን ቡድን የመሩት ዶክተር ስምኦን ደሳለኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።እንደ ዶክተር ስምዖን አስተያየት ከሆነ በአካባቢው በተፈጠረው ጦርነት የተጎዱ ሰዎችን ለማከም ወደ አካባቢው ማምራታቸውን ተናግረው በማይካድራ ሆን ተብሎ ግድያ የተፈጸመባቸው ሰዎች ከ750 በላይ እንደሆነ በአይናቸው ማየታቸውን እና ይሄንን አሃዝም የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ላሰማራቸው መርማሪዎች መናገራቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በበኩላቸው ጉዳዩን ለመመርመር ወደ ሰፍራው ያቀናው የምርመራ ቡድን መረጃዎችን ሐኪሞችን ጨምሮ በአካባቢው ካሉ የተለያዩ አካላትን ጠይቀው መመለሳቸውን ተናግረዋል።በምርመራው የተገኘውን መረጃ ከተለያዩ ቦታዎች ስለምንቀበል በራሳችን መመዘኛ አጣርተን ነው ይፋ የምናደርገው ሆኖም ግን በዚህ አሰቃቂ ግድያ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች ቁጥር 600 ብቻ ነው ብለን አልገለጽንም በቀጣይ ተጨማሪ እና ዋናው ሪፖርት ሲሰራ ትክክለኛው የሟቾች ቁጥር ይታወቃል ሲሉም ዶክተር ዳንኤል ምላሽ ሰጥተዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ የትምህርት ሥልጠና ጥራት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ባለሥልጣን የተቀመጠውን ዝቅተኛ መስፈርት አላሟሉም ያላቸውን 23 ትምህርት ቤቶች የሥራ ፈቃድ መንጠቁን ተናገረ።

የእውቅና ፈቃዳቸው የተወሰደባቸው 15 መዋዕለ ሕፃናት፣ 7 የመጀመሪያ ደረጃ እና 1 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸው።ባለሥልጣኑ የእውቅና ፈቃዳቸውን የሰረዝኩት ከተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ በኋላ ነው ብሏል።ትምህርት ቤቶቹ በዚህ የትምህርት ዘመን ማስተማር እንደማይችሉ የባለሥልጣኑ ሥራ አስኪያጅ ሸዊት ሻንካ ተናግረዋል።ሥራ አስኪያጇ አክለውም፤ ለ60 ትምህርት ቤቶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል ብለዋል።

በሌላ በኩል ለ574 ትምህርት ቤቶች የእውቅና ፈቃድ የታደሰላቸው ሲሆን 93 አዲስ ትምህርት ቤቶችም ወደሥራ እንደሚገቡ ሥራ አስኪያጇ ተናግረዋል።ወላጆች ልጆቻቸውን ሲያስመዘግቡ በቅድሚያ ትምህርት ቤቶች ፈቃድ ስለማግኘታቸው ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

ፈቃዳቸው የተሰረዘባቸውን ትምህርት ቤቶች በስም እንዲጠቅሱልን የጠየቅናቸው የባለሥልጣኑ ኃላፊዎች፣ ለየትምህርት ቤቶቹ በደብዳቤ የተነገራቸው መሆኑን እና ይህንኑም ራሳቸው ትምህርት ቤቶቹ ለማኅበረሰቡ እንዲያሳውቁ የተነገራቸው መሆኑን ተናግረዋል።በከተማዋ በአጠቃላይ ከ1,590 በላይ የግል ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሏል።

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
Today is the last day of Virtual Agrofood & Plastprintpack Africa 2020. It has indeed become a truly global event with a clear Africa focus. Considering that the event includes not only the core period from 23 - 26 November, but also a bonus period until 03 December, one can well imagine that the event will become a great success.

Only on the first day:
No fewer than 904 attendees have already become active users, out of the 2,001 meanwhile registered from 81 countries. The attendees networked with each other and of course with the

64 exhibitors from 17 countries participating
4,522 messages were exchanged
444 attendees attended the conference sessions
a total of 2,022 contacts were made
444 participants attended the panel sessions, presentations and product demos
The opening talk on how exhibitors, attendees & speakers can best benefit from the event was followed by 172 participants

You can still be part of this trade fair Today! Register now as an attendee here;, it's free of charge
የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ በተጠረጠሩ 7 የጄኔራል መኮንኖች ላይ ፖሊስ የጠየቀባቸው ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ!

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የልዩ ቀጠሮ ችሎት በሀገር ክህደት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚገኙት እነ ሜ/ጄ ገብረመድህን ፈቃዱን ጨምሮ 7 ግለሰቦች ፖሊስ የጠየቀባቸው ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜን ፈቀደ።በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ ቡድን እነ ሜ/ጄ ገብረመድህን ፈቃዱ፣ ሜ/ጄ ይርዳው ገብረመድህን፣ ብ/ጄ ኢንሱ ኢጳጆ ኢንሱ ኢጳጆ ረሾን ጨምሮ 7 መኮንኖችን በሀገር ክህደት ብሎም ሕገ-መንግሥቱን እና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ በመጣል ወንጀል ነው የጠረጠራቸው።

ተጠርጣሪዎቹ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ ላይ የተደረገውን ጥቃት በመጠንሰስ ትልቅ ሚና እንደነበራቸው የምርመራ ቡድኑ ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የልዩ ቀጠሮ ችሎት ባቀረበው ማመልከቻ ላይ ጠቅሷል።

የሰሜን ዕዝ የሬዲዮ መገኛ ተቋርጦ የጥቃት ሰለባ እንዲሆን፣ በሠራዊቱ መካከል መከፋፈል እንዲፈጠር የተለያዩ የወንጀል ተግበራትን መፈፀማቸውን የምርመራ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ መጥቀሱ ይታወቃል።ዛሬ ሁሉም ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ የምርመራ ቡድኑ በቀጣይ የምርመራ ሥራ 14 ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው አመልክቷል። ተጠርጣሪዎችም የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው አመልክተዋል።የግራ ቀኙን ክርክር የተከታተለው ችሎቱ 13 ቀን በመፍቀድ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለኅዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በልደታ ክፍለ ከተማ ከ55ሺ ብር በላይ ሀሠተኛ ባለ200 የብር ኖቶች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

ከተያዘው የብር ኖት ባለፈ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል።

ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ተግባረድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ ግለሠብ አዲሱን ባለ200 የብር ኖቶ በመቶ ብር ለመቀየር በማፈላለግ እያለ ከህብረተሰቡ ለፖሊስ በደረሠው ጥቆማ መሠረት ግለሰቡ ከ7 ሺህ 400 ሀሠተኛ ባለ2መቶ የብር ኖት ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።

በፖሊስ ከተያዘው አንድ ተጠርጣሪ መረጃ በመነሳት በተደረገው የክትትልና የኦፕሬሽን ስራ ከተያዘው ተጠርጣሪ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሶስት ተጠርጣሪዎች እና 48ሺህ 200 ሀሠተኛ ባለ2መቶ የብር ኖት በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ ዋና ሳጅን በእምነት ግርማ ተናግረዋል።

ከአዲሱ የብር ኖት ቅያሬ ጋር ተያይዞ በርካታ አዲስ ሀሠተኛ የብር ኖቶች ተመሳስለው እየተሰሩ ወደ ህብረተሠሰቡ እየተሠራጩ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሊሰጥበት እንደሚገባ ዋና ሳጅን በእምነት ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ ግብይት በሚያከናውኑበት ወቅት በአጭበርባሪ ግለሰቦች እንዳይታለልና እንዳይጭበረበር ጥንቃቄ ማድረግና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት አራት ወራት ከወጪ ንግዱ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ተገኘ!

የንግድና ኢንዱስትሪ በለፉት 4 ወራት ከወጪ ንግዱ 1ነጥብ7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 1ነጥብ1 ቢሊዮን እንዲሁም በጥቅምት ወር 280 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 258 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገልጸዋል፡፡

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
እስር ላይ የሚገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ሥነ-ባህሪ ኮሌጅ ዲን፣ እንዲሁም የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል ዶ/ር ሁሴን ከድር የለገጣፎ ወረዳ ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸዉን ቢጠብቅም እስካሁን እንዳልተለቀቁ ተነገረ።

ዶ/ር ሁሴን ከድር የተከሰሱት ከአርቲስት ሃጫሉ ግድያ ማግስት በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የተቀሰቀሰውና ለበርካታ ህይወትና ንብረቶች ውድመት በሃሳብና ድርጊት ረድተዋል የሚል ነው። ፍርድ ቤቱ ትናንት በዋለው ችሎት ላለፉት አምስት ወራት በማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ዶ/ር ሁሴን ከድር በ10 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ፈቅዶ ነበር፡፡ይሁንና እስከ ዛሬ ማምሻ ድረስ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት ዶ/ር ሁሴን አለመለቀቃቸውን ጠበቃቸው አቶ ከድር ቡሎ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ሁሴን ከዚህ ቀደም በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳያቸው ሲታይ በቆየበት ወቅትም ፍርድ ቤት በዋስትና መብት ቢለቃቸውም ፖሊስ በሌላ ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ በሚል ዳግም በለገጣፎ ክስ እንደመሰረተባቸው አቶ ከድር ተናግረዋል።በኦሮሚያ ክልል የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በተፈጠረው ሁከት የ170 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከፍተኛ ግምት ያላቸው ንብረቶችም ጉዳት ደርሶባቸው በዚሁ የተጠረጠሩ ከ9000 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው አይዘነጋም፡፡

(DW)
@YeneTube @FikerAssefa
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ ጋር በሰላምና ደህንነት መስኮች የነበራቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ!

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ በሰላምና ደህንነት መስኮች እንዲሁም ሽብርተኝነትን በጋራ ለመከላከል ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ የሞሳድ ቢሮ ኃላፊ ጋር በዛሬው ዕለት ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሞሳድ ጋር ትብብሩን በማጠናከር በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት፣ በቴክኖሎጂ፣ በአቅም ግንባታ ሥልጠና ዘርፍ ይበልጥ ተባብረው ለመሥራት ማቀዳቸው ተገልጿል።የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሞሳድ የሚደረግለትን ሁሉን አቀፍ የአቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ ድጋፎች በመጠቀም ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመከላከል እና ከሥሩ በመንቀል ረገድ ያላት አቋም ጠንካራ መሆኑን የጠቀሱት የእስራኤል የሞሳድ ዳይሬክተር ጀነራል ሚስተር ዮሴፍ ኮ`ን ልዩ መልዕክተኛ እንዲሁም በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ የሞሳድ ቢሮ ኃላፊ የህዝቦች የጋራ ጠላት የሆነውን ሽብርተኝነትን በተቀናጀ ሁኔታ ለመከላከል ሞሳድ ከኢትዮጵያ አቻ የመረጃና ደህንነት ተቋም ጋር በትብብር እንደሚሰራና ድጋፋኑም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኮንሶ የተፈናቀሉ እርዳታ እየተጠባበቁ ነው!

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ባለፈው ሳምንት የታጠቁ ሀይሎች አደረሱት በተባለው ጥቃትና ግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን ገለጹ።ከዞኑ ሰስት ወረዳዎች ተፈናቅለው በተለያዩ ቀበሌያትና በአጎራባች ወረዳዎች ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ እንዳሉት ከቀያቸው ከወጡ ቀናትን ቢያስቆጥሩም እስከአሁን ግን ያናገራቸውም ሆነ ድጋፍ ያደረገላቸው አካል የለም።የኮንሶ ዞን የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው ከዞኑ ለተፈናቀሉ ከ94 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የቀለብና የአልባሳት ድጋፍ እንዲቀርብ ለደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በማቅረብ ምላሽ እየጠበቁ እንዳሉ ተናግረዋል።ተፈናቅለዋል በሚል ከዞኑ የቀረበው ቁጥር የተጋነነ ነው የሚሉት የደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጋንታ ጋሞአ በበኩላቸው የተረጂዎችን ትክክለኛ ቁጥር በባለሙያዎች እየተለየ ይገኛል ብለዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በኤልቲቪ ቴሊቪዥን ጣቢያ ታቀርባቸው በነበሩ አነጋጋሪ ቃለ መጠየቆቿ የምትታወቀው ቤተልሔም ታፈሰ፤ የስራ እና የግል ህይወቷን የተመለከቱ ማስታወሻዎችን ያሰፈረችበት መጽሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

Via Ethiopia Insider
@Yenetube @Fikerassefa
በቄለምና ምዕራብ ወለጋ የተወሰኑ ስፍራዎች የኢንተርኔትና ስልክ መቋረጥ!

በቄለም ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ዞን የተወሰኑ ስፍራዎች የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ከጠፋ ከሁለት ሳምንት በላይ ሆኖታል።

የግምቢ እና ነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ባለመኖሩ ከዘመዶቻቸው ጋር መገናኘት እንዳልቻሉ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

የምዕራብ ወለጋ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያስ ኡመታ በዞናቸው ስር  ስምንት በሚደርሱ ወረዳዎች የሞባይል ስልክ አገልግሎት መቋረጡን እና ችግሩን ለመቅረፍ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እየተነጋሩ እንደሆነ አስረድተዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮምዩንኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው አገልግሎቱ ስለመቋረጡ ምክንያት እንደማያውቁ ገልጸው በጸጥታ ችግርም ሆነ በሌላ ምክንያት የቴሌኮም አገልግሎት እንዲቋረጥ የተላለፈ ውሳኔም በመንግስት በኩል የለም ብለዋል። 

ባለፈው ዓመትም  ከታህሳስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ወራት ያህል በወለጋ ዞኖችና በተወሰኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወረዳዎችም  የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱ የክልሉ መንግስት የአካባቢውን የጸጥታ ችግርን ለመቅረፍ ሲባል መቋርጦ ገልጾ ነበር።

(DW)
@Yenetube @Fikerassefa
ዋልታ ቴሌቪዥን ሰበር ዜና ይኖረናል ካለ አንድ ሰዓት አልፎታል።
የዋልድባው መነኩሴ ነጻ ወጥቷል ወዳሉት ገዳም መመለሳቸውን ተናገሩ!

ከትላልቆቹ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተከርስቲያን ገዳማት የዋልድባ ገዳም ተወካይ የነበሩት አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያምን ዋልድባ ገዳም ነጻ በመውጣቱ ወደ ገዳሙ መመለሳቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

አባ ገብረየሱስ በቀደመው መንግሥት እስርና እንግልት የደረሰባቸው መሆኑን የገለጹልን ሲሆን፣ አካባቢው ነጻ በመውጣቱ፣ ከተባረሩበትና እንዳይገቡ ተከልክለው ወደ ነበረበት የዋልድባ ገዳም ሰሞኑን የተመለሱ መሆኑንም አጫውተውናል፡፡

የዋልድባ ገዳም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተከስቲያን ከአሏት ታላላቅ ገዳማት አንዱ መሆኑ ይነገርለታል፡፡

አካባቢውንና የፌዴራል መንግሥቱን ይቆጣጠር ከነበረው፣ የቀደመው መንግሥት ጋር በተፈጠረ ግጭት፣ ከታሰሩና ከገዳሙ እንዲባረሩ ከተደረጉ መነኮሳት መካከል፣ መጋቢ ስርዓት አባ ገብረየሱስ ኪዳነ ማርያም አንዱ ናቸው፡፡ የዋልድባ ገዳም አብረንታንት ቤተ ሚናስ ተወካይ ሆነው ለዓመታት አገልግለዋል። የገዳሙን ቦታዎች ለስኳር ፋብሪካ መታሰቡን በመቃወማቸው እንደ ፖለቲካ እስረኛ በሽብር ወንጀል ተከሰው በማዕከላዊ እስር ቤትና ኋላም በቅሊንጦ ወህኒ ቤት መቆየታቸውንም ገልጸዋል፡፡ መነኩሴው አባ ኪዳነ ማርያም፣"የዋልድባና የህወሓት ፍጥጫ" የሚል መጽሀፍ አውጥተዋል፡፡

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ልዩ ኃይል ቁጥጥር ሥር ባለቸው አላማጣ ከተማ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ለህግና ማስከበርና ጸጥታ ጉዳዮች ቀዳሚ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚንቀሳቀስ አረጋገጠ፡፡

አዲስ ለተመረጠው ጊዜያዊ አስተዳደር ህዝቡ ሙሉ ድጋፉን እየሰጠ መሆኑን አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የገለጹ አመራሮች ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ቅዳሜ በአላማጣ ከተማና በዙሪያው ባሉ የገጠር ቀበሌዎች በተደረገው ውይይት የራያ አላማጣን 15 የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም የአላማጣ ከተማን አራት ቀበሌዎች በጊዜያዊነት የሚያስተዳድሩ 114 ሰዎች መመረጣቸው ይታወሳል፡፡የዚህ ዜና ዝርዝር የድምፅ ዘገባ ከላይ ተያይዟል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጆ ባይደን መሸነፋቸውነ ሊቀበሉ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ።ትራምፕ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ "ጆ ባይደን በ 'ኤሌክቶራል ኮሌጅ' የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆኑ ከተረጋገጠ መሸነፌን ልቀበል እችላለሁ" ብለዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ያለ ደረሰኝ ሽያጭ ሲያከናውኑ የነበሩ ከ22 በላይ ድርጅቶች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮ ኃላፊው አቶ ሙሉጌታ ተፈራ እንደገለጹት በከተማዋ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ላይ በተደረገ የክትትል ቁጥጥር ስራ ከ22 በላይ ድርጅቶች ያለደረሰኝ ሲሸጡ በመገኘታቸው እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡በከተማዋ የግብር ህግን አክብረው በማይሰሩ ነጋዴዎች ላይ ህግን የማስከበር ስራ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ ግብር ከፉዪ የወጣውን የግብር ህግ አክብሮ እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡ህብረተሰቡም የወጣውን የግብር ህግ አክብረው የማይሰሩ አጭበርባሪዎችን በሚመለከትበት ወቅት 7075 ነጻ የስልክ መስመር በመጠቀም ጥቆማቸውን እንዲሰጡ አቶ ሙሉጌታ ጥሪ አቅርበዋል።በተያያዘ ዜና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ቄራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የፖሊስ ልብስ በመልበስና ሀሰተኛ የገቢዎች ቢሮን በመያዝ ግብር ከፋዩን ህብረተሰብ ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በፖሊስ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም ኃላፊው ጥሪ ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
“መንግስት የሰላም ድርድር ሃሳብ ሊቀበል የሚችለው የህወሃት 'ጁንታ' ለፍርድ ከቀረበ በኋላ ነው” ሲሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።

‘ኤ ቲቪ’ ከተባለ የቱርክ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ማንኛውንም ልዑክ ተቀብሎ ያስተናግዳል።“በተለይም ከጎረቤት አገሮች ብሎም ከአፍሪካ ልዑካን የሚመጣ ሙከራና ሃሳብ እንቀበላለን፤ ሁሉንም ወዳጆቻችንን እንሰማለን” ብለዋል።ዋናው ነገር 200 ያህል የሚሆኑና የእስር ማዘዣ የተቆረጠባቸው የህወሃት ጁንታ ጋር ድርድር የሚባል ነገር አለመኖሩን መረዳት ላይ መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን ገልጸዋል።

የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የላኩት ሶስት አባል ያለውን ልዑክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተቀብለው እንደሚያስተናግዱም ጠቁመዋል።ልዑኩን ተቀብለው ቢያስተናግዱም ህዝብ ከጨፈጨፈው፣ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከፈጸመው፣ የአገር ክህደት ከፈጸመውና በአገሪቱ ሁከትና ብጥብጥ ሲያስተባብርና ሲመራ ከነበረው የህወሃት ቡድን ጋር የሚደራደሩበት ሁኔታ እንደማይኖር አምባሳደር ሬድዋን አስረግጠው ተናግረዋል።ከቡድኑ ጋር መደራደር በኢትዮጵያ ለሰርጎ ገቦች መንገድ መክፈት እና ህገ ወጥነት እውቅና እንዲያገኝ ማድረግ መሆኑንም በውይይታቸው አስምረውበታል።

በህግና ስርዓት የምትተዳደረው ኢትዮጵያ ወንጀለኛውን ቡድን ለህግ ካቀረበች በኋላ ማንኛውም ሰላም ሊያረጋግጥ የሚችል ድርድር ውስጥ ልትገባ እንደምትችል ግን ጠቁመዋል።በመሆኑም ህግን ለማስከበር የህወሃት ጁንታን ለህግ ለማቅረብ የህግ ማስከበር ዘመቻው እየተካሄደ ስለመሆኑ ገልጸዋል።የህወሓትና የትግራይ ህዝብ በፍጹም የተላያዩ መሆናቸውን የገለጹት አምባሳደር ሬድዋን፤ “ህወሃት የፖለቲካ ቡድን ሲሆን ትግራዋያን ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል ናቸው” ብለዋል።በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግስት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ መጀመሩን ገልጸው፤ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ዳሰሳ መካሄዱን አምባሳደር ሬድዋን መናገራቸውን ኢዜአ በዘገባው አመልክቷል።ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን ለመመለስ እየተሰራ እንደሆነ አንስተው፤ “እንኳንና የእኛን ዜጎች ይቅርና በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሌሎች አገሮች ዜጎችን በስደተኝነት ተቀብለን እያስተናገድን ነው” ብለዋል።

[ENA]
@YeneTube @FikerAssefa
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ኅዳር 24 እና 25 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ኅዳር 24 እና 25 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለጸ።ቢሮው ተማሪዎች በተገለጹት ቀናት ወደ መፈተኛ ጣቢያዎች በመገኘት ፈተና እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀን በማረሚያ ቤት ይከበራል!

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀን አከባበርን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ተሰጥቷል።

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀን ከታህሳስ 1 /2013 ጀምሮም ‹‹ለሰብዓዊ መብቶች ተግባራዊነት በመትጋት ዓለማችንን በተሻለ መልሰን እንገንባ›› በሚል መሪ ቃል በዓለማቀፍ ደረጃ ይከበራል።

እንዲሁም ከኀዳር 22 እስከ 30 በተለያዮ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን ዘንድሮም ለመጀመሪያ ጊዜ ቃሊቲ በሚገኘው የፌደራል ማረሚያ ቤት እንደሚከበርም ተነግሯል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት መርሃ-ግብር

ዕሁድ ህዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡30 ድረስ፡-
• በሲቪል ሰርቪስ ፊት ለፊት፣ በተባበሩት ልዩ ቤቶች፣ በሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል፣ በጃክሮስ፣ በሳሊተ ምህረት፣ በፊጋ ሆቴል እና አካባቢዎቻቸው፤

ሰኞ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 እስከ ቀኑ 5 ድረስ፡-
• በየረር፣ በጎሮ ሰፈራ፣ በጎሮ ገብርኤል፣በየረር ድልድይ እና አካባቢዎቻቸው፤

በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 7፡00 ድረስ፡-
• በምስራቀ ፀሐይ ገብርኤል፣ በተባበሩት ነዳጅ ማደያ፣ በሚካኤል ፊት ለፊት፣ በጆሞ 1 በከፊል፣ በጆሞ 3 እና አካባቢዎቻቸው፤

በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ፡-
• በሰሚት ለስላሳ፣ በሰሚት ኪዳነ-ምህረት፣ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ፣ በፍርድ ቤት፣ በአደዋ ድልድይ፣ በአቧሬ፣ በእንደራሴ ሆቴል፣ በመለስ ፋውንዴሽን፣ በልቤ ፋና ኮንደሚኒየም፣ በካዛንቺስ በከፊል እና አካባቢዎቻቸው፤

በተጨማሪም ማክሰኞ ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ፡-
• በገላን ኮንደሚኒየም በከፊል፣ በቴሌ ስቶር እና አካባቢዎቻቸው፤

በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ፡-
• በወሰን ግሮሰሪ፣ በሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል፣ በየካ አባዶ ኮንደሚኒየም፣ በሮፓክ፣ በመንን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒዓለም፣ በላዛሪስት፣ በሐምሌ 19 መናፈሻ እና አካባቢዎቻቸው፤

እንዲሁም በዚሁ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፡-
• በወሎ ሰፈር፣ በጃፓን ኤምባሲ፣ በሩዋንዳ አምባሲ፣ በካራ ማራ ድልድይ እና አካባቢዎቻቸው፤

በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ አሳውቋል፡፡

[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]
@YeneTube @FikerAssefa