ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ ጣልቃ ለመግባት ከሚያደርገው ሙከራ እንዲቆጠብ አሳሰቡ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በእንግሊዝኛ ባወጡት መግለጫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አንቀፅ 2 ንዑስ አንቀፅ 7ን በመጥቀስ ሉዓላዊ በሆነ ሀገር ጣልቃ መግባትን እንደሚከለክል በማንሳት እንዲሁም የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት አንድ ሀገር የራሱን የውስጥ ጉዳይ ያለማንም የውጭ አካል ጣልቃ ገብነት ማከናወን እንደሚችል ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ያሳሰባቸውን ወዳጆችን አመስግነው ይህ ግን ኢትዮጵያ በራሷ ማከናወን የምትችለው ስለሆነ የማንም ጣልቃ ገብነት እንደማያስፈልግ አሳስበዋል። ሀገሪቱ እገዛ የሚያስፈልጋት ቢሆን እንኳን ራሷ ግብዣ የምታደርግ እንደሆነም ተናግረዋል። ይህ መግለጫ የወጣው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ለመወያየት በወሰነ ማግስት ነው።
@YeneTube @FikerAssefa

የቀድሞው የኒጀር ፕሬዚዳንት ማማዱ ታንጃ በ82 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰማ፡፡ማማዱ
ታንጃ ከፈረንጆቹ 1999 እስከ 2010 በስልጣን መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡ከሁለት ጊዜ በላይ በስልጣን ለመቆየት ከሞከሩ በኋላ ግን በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን መነሳታቸው ይታወሳል፡፡ከስልጣን ከተነሱ በኋላም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ወህኒ ከወረዱ አንድ ዓመት በኋላ ነጻ ወጥተውም ነበር፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በወቅታዊነት በሚከናወኑ ተግባራት የሚከሰቱ የመብት ጥሰቶችን ለመከላከል የቅሬታ መቀበያ ስልክ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
በህወሀት ቡድን ላይ መንግስት የሚወስደውን ህግን የማስከበር እርምጃን ተከትሎ በአዲስ አበባ የቡድኑ ተላላኪዎች ሊያስከትሉት የሚችሉትን ጥፋት ለመከላከል የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በጋራ ባደረገው በጥናት ላይ በተመረኮዘ አሰሳና ፍተሻ በርካታ ውጤቶች እየተገኙ መጥተዋል ተብሏል፡፡
ሆኖም በስራ አፈፃፀም ላይ የታዩ ጉድለቶች እንዲስተካከሉ ከህብረተሰቡ የሚመጡ አስተያየቶችና ቅሬታዎች በመኖራቸው መረጃዎችን ለመቀበል ቁጥሩ 011 -8-69-45-02 የሆነ ስልክ መዘጋጀቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባስተላለፈው መልዕክት የሚከሰቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ተገቢ ያልሆነ ጫና በአጠቃላይ ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር የተገናኙ ማንኛውም አይነት ቅሬታዎች አሉኝ የሚል ነዋሪ በ011-8-69-45-02 ላይ በመደወል መረጃ መስጠት እንደሚችል የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የህወሃት አባላት በመንግስት የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው እጅ እንዲሰጡ የአቶ ጌታቸው ረዳ እህት ጠየቁ!
የህወሃት ጁንታ ቡድን አባላት በመንግስት የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው እጅ በመስጠት የትግራይ ህዝብ ከተጋረጠበት አደጋ ሊታደጉት እንደሚገባ የህወሃት ጁንታ ስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት የአቶ ጌታቸው ረዳ ታናሽ እህት ዋና ሳጅን ትዕግስት ረዳ ገለጹ።"እኔ የአቶ ጌታቸው ረዳ እህት ብሆንም የፖለቲካ አመለካከት በዘር አይተላለፍም" የሚሉት ዋና ሳጅን ትግስት፤ "በበኩሌ በአፍላነት እድሜዬ ህብረ-ብሄራዊ ለነበረው ኢህዴን የታገልኩና ለሰንደቅ ዓላማዬ ዘብ የምቆም ህዝባዊ ፖሊስ ነኝ" ብለዋል።
በሰቆጣ ከተማ ለ22 ዓመታት የኖሩት ዋና ሳጅን ትዕግስት ከአሁኑ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ምንም አይነት ችግር እንዳላጋጠማቸው ገልጸው፤ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በጽኑ እንደሚያወግዙት ለኢዜአ ተናግረዋል።
"መከላከያ ሀገር ነው፤ ብሔር የለውም ዘር የለውም እሱ እንዲበተን አልፈልግም፤ ሀገርን የሚጠብቅ ሰው ሲሞት በጣም አዝኛለሁ" ያሉት ዋና ሳጅን ትዕግስት ረዳ፤ መንግስት እያካሄደ ያለው የህግ ማስከበር ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የትግራይን ወጣት ለጦርነት መማገዳቸው ለትግራይ ህዝብ ደንታ እንደሌላቸው ማሳያ እንደሆነም ጠቅሰዋል።"በወንጀል የሚፈለጉ የህወሃት አመራሮች በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ ለሁለተኛ ጊዜ በመንግስት በኩል የቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ህዝባቸውን ከተጋረጠበት አደጋ ሊታደጉት ይገባል" ብለዋል።
ወንድማቸው አቶ ጌታቸው ረዳ የህወሃት ጁንታ አመራር በመሆናቸው እንደሚያዝኑ የሚናገሩት ዋና ሳጅን ትዕግስት ረዳ፤ እሳቸው የአፍላነት እድሜያቸውን በትግል ያሳለፉት ለሀገር አንድነት ባላቸው ጽኑ እምነት መሆኑን ገልጸዋል።ለግል ጥቅም ህዝብን አደጋ ላይ የሚጥለው የህወሃት ጁንታ አመራር አባል በሆኑት ወንድማቸው ድርጊት እንደሚያዝኑም ገልጸዋል።ወንድማቸው ሁሉም ህዝብ የራሳቸው መሆኑን በመረዳት ዘብ ሊቆሙለት ይገባ እንደነበረም በመጥቀስ ወቅሰዋል። እሳቸው በትግል ቢያሳልፉም ቀድሞውኑ የትግል ተሞክሮ የሌላቸውና መምህር የነበሩት የጁንታው አመራር ወንድማቸው እስከ አሁን ለሰሩት ጥፋት ህግ እንደሚዳኛቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ከ110 በላይ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ!
በምስራቅ ሃረርጌ ዞን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።የመምሪያው ኃላፊ ኮማንደር ናስር መሀመድ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት የጦር መሳሪያዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በዞኑ 20 ወረዳዎች በተደረገው ፍተሻ ነው።
ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገው ፍተሻ 103 ሽጉጥ፣ 7 ክላሽንኮቭ ፣25 የተለያዩ ቦንቦች፣ ከ5 ሺህ በላይ የሽጉጥ፣ የክላሽንኮቭ፣ የተለያዩ ጥይቶችና የጥይት ካርታዎች መያዛቸውን ተናግረዋል።
እንዲሁም ቪንቶቭ ፣ኤስኬ ኤስና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ የተለያየዩ የሬዲዮ መገናኛዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።በዚህም 66 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው 24ቱ በፍርድ ቤት የክስ መዝገብ የተከፈተባቸው ሲሆን 42ቱ ላይ ማስረጃ እየተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል።ሌሎች 56 ግለሰቦች ደግሞ ከኦነግ ሸኔና ከጁንታው ህወሃት ቡድን ጋር አብረው እንደሚሰሩ መረጃ ተገኝቶባቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር ናስር መሀመድ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሰሜን ምእራብ ግንባር ሰራዊቱ በአጥፊው ጁንታ ቡድን ላይ ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ እያደረሰ ነው ተባለ!
በሰሜን ምእራብ ግንባር የሰራዊቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የግንባሩ የሚዲያ ስራዎች አስተባባሪ ኮሎኔል አባተ ንጋቱ ሰራዊቱ በሕወሓት ቡድን ላይ እየወሰደ ባለው ሕግን የማስከበር እርምጃ በአጥፊ ቡድኑ ላይ ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን ተናግረዋል፡፡በዘመቻውም ሰራዊቱ የጠላትን ኃይል ደምስሶ ክላሽን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ ነብስ ወከፍ እና ከ5 ሺህ በላይ የቡድን መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር አውሏል ብለዋል፡፡ከዚያም ባለፈ ጀግናው ሰራዊት ይህ ቡድን ቀደም ሲል ከሰራዊቱ ዘርፏቸው የነበሩትን ታንኮች፣ መድፎች እና ሮኬቶችንም በቁጥጥር ስር አውሏል ብለዋል፡፡ሰራዊቱ ሀገር የጣለችበትን ግዳጅ በላቀ ቁመና እየፈጸመ ነው ያሉት ኮሎኔል አባተ የስግብግብ ጁንታው አባላት ለፍርድ እስኪቀርቡ ድረስ ሕግ የማስከበር እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
Via ETV

ትናንት ምሽት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የተሰበሰበው የጸጥታው ምክር ስብሰባ ቤት ያለ ስምምነት ተጠናቀቀ።
የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ትግራይ ዉስጥ ሥለሚደረገዉ ዉጊያ ትናንት ሌሊት በመንግስታቱ ድርጅት ዋና መቀመጫ ኒዮርክ ተሰብስቦ ነበር።ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ቀደም ሲል ይዞት ለነበረዉ ቀጠሮ የአፍሪቃ ሐገራት ድጋፍ ባለመስጠታቸው ምክንያት ሰርዞት ነበር።ይሁንና በምክር ቤቱ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣን ያላቸዉን ፈረንሳይና ብሪታንያን፣ ጨምሮ የአዉሮጳ ሐገራት ዉይይቱ እንዲደረረግ ግፊት በማድረጋቸዉ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት በጉዳዩ ዙሪያ መሰብሰባቸው ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ ሶስተኛ ሳምንቱን የያዘዉ ጦርነት በርዕስነት እንዲቀርብ ከፈረንሳይና ከብሪታንያ በተጨማሪ ግፊት ያደረጉት ቤልጂየም፣ ጀርመንና የወቅቱ የጸጥታው ምክርቤት ተለዋጭ አባል የሆነችው ኢስቶኒያ ናቸዉ።
አፍሪካን ወክለው የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል የሆኑት ደቡብ አፍሪካ፣ኒጀር እና ቱኒዝያ የኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግስት ጦርና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ታጣቂዎች ሥለገጠሙት ጦርነት መረጃ የሚያሰባስብ የመልዕክተኞች ጓድ ወደ ኢትዮጵያ መሔድ አለበት በሚል ምክንያት ጉዳዩ ለዉይይት መቅረቡን ተቃውመው ነበር።ይሁንና በመጨረሻም ስብሰባው ያለ ስምምነት መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ጦርነቱ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው የትኛውም አገር በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠብ አሳስበዋል።
[ኢትዮ ኤፍ ኤም]

በደቡብ ክልል በመወቅር ምክንያት በኮንሶ ዞን፣ ደራሼ ልዩ ወረዳ፣ በአማሮ ልዩ ወረዳ እና በአሌ ልዩ ወረዳ ግጭት በቀሰቀሱ አካላት የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ ተናግረዋል።
በአቶ ጥላሁን ከበደ የተመራ ልዑካን ቡድን ኮንሶ ዞን፣ አማሮ ልዩ ወረዳ በግጭቱ ሰበብ ቤት ንብረታቸዉ የወደመባቸዉን ዜጎች እቦታዉ ድረስ በመሄድ አፅናንቷቸዋል፡፡
አጥፍዎችን ወደ ህግ በማቅረብ የህግ የበላይነትን እንዲረጋገጥ ከመቼዉም ጊዜ በላይ እንደሚሰሩ ነዉ አቶ ጥላሁን የገለጹት፡፡ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸዉ እንዲመለሱ የክልሉ መንግስት በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡በአቶ ጥላሁን ከበደ የተመራ ልዑካን ከሰዓት ቦታዎች በማቅናት ከተጎጂዎች ጋር ቆይታ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
[ደሬቴድ]

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ላደረጉት አስተዋጾ እውቅና ሊሰጣቸው ነው።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እንዳስታወቀው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ስለ ሰብአዊ መብቶች መከበርና የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን በመከላከል ላደረጉት አስተዋጽኦ እውቅና ሊሰጣቸው ነው ብሏል።የሰብአዊ መብቶች ቀን ከታህሳስ 1 ጀምሮ በኢትዮጵያ መከበር እንደሚጀምር ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ ገልጿል።አከባበሩም የተለያዩ ሁነቶች ያሉት እንደሆነ ታውቋል።የሰብአዊ መብቶችን መጠየቅን ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ በርካታ የጉዳዩ ባለቤቶች ይሳተፉበታል ተብሏል።ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምም በህይወት ዘመናቸው ላደረጉት የሰብአዊ መብት ተጋድሎ ነው ይህ እውቅና የሚሰጣቸው ተብሏል።
Via Ethio FM

ወጋገን ባንክ አዲስ ፕሬዝዳንት ተሾመለት፡፡
የቀድሞ ወጋገን ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አባይ መሐሪ በቦርድ መነሳታቸውን ተከትሎ ወ/ሮ ብርቱካን ገ/እግዚአብሔር የወጋገን ባንክ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን ተሰምቷል፡፡ወ/ሮ ብርቱካን ከዚህ ቀደም የእናት ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ከዚያም ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በአቢሲኒያ ባንክም በከፍተኛ ሀላፊነት ማገልገላቸውን ይታወቃል፡፡
ወ/ሮ ብርቱካን የወጋገን ባንክ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በቦርዱ ከታጩ በኋላ በብሔራዊ ባንክ በኩል ማረጋገጫ እስኪሰጣቸው ድረስ እየጠበቁ ቆይተዋል፡፡ብሔራዊ ባንክም ወ/ሮ ብርቱካንን የወጋገን ባንክ ፕሬዝዳንት እንደሆኑ መፍቀዱም ተሰምቷል፡፡ሸገር ወሬውን ከብሔራዊ ባንክ አረጋግጫለው ብሏል፡፡
Via Sheger FM

በጉጂ ዞን ጎሮ ዶላ ወረዳ 14 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ኦሮሚያ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የጉጂ ዞን ፖሊስ መምሪያ የአካባቢ ደህንነት ማረጋገጫ ስራ ሂደት ኃላፊ ሳጂን ጉተማ ሳፈዮ፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት እና ሌሎች የክልሉ የፀጥታ መዋቅር አባላት የህብረተሰቡ የሰላም ፀር የሆኑት የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከህወሓት ጋር የተፈጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሲጥሩ ቢቆዩም የህውሓት ሃይል ግን በተቃራኒው ቆሞ ቀውሶችን ለመፍጠር ሲዘጋጅና የጥፋት ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡ በተለይ ብሔር ላይ ተመስርተው ለሚከሰቱ ሰብአዊ ቀውሶች የህወሓት የጀርባ መሪነት አለበት፡፡ እንደዚህ አይነት አገር የማፍረስ ሁኔታዎች ሲመጡ መንግስት በቀጥታ ሊያደርግ የሚችለው ህግን የማስከበር ተግባር ነው፡፡"
የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለቢቢሲ የተናገሩት
@Yenetube @Fikerassefa
የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለቢቢሲ የተናገሩት
@Yenetube @Fikerassefa
በሰበታ ከተማ ተጠምዶ የነበረ ፈንጂ በህብረተሰቡ ጥቆማ ከሸፈ!
በሰበታ ከተማ አስተዳደር 04 ቀበሌ መስጂድ አካባቢ ተጠምዶ የነበረ ፈንጂ ጉዳት ሳያደርስ በህብረተሰቡ ጥቆማ መክሸፉ ተገለጸ፡፡ፈንጂው መሀመድ ረጃ መስጂድ አካባቢ ተጠምዶ የተገኘ መሆኑን የሰበታ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡መስጂድ አቅራቢያ ላይ መጠመዱ ነመስጂዱ ላይ ጉዳት ለማድረስ ታቅዶ የተፈፀመ መሆኑን የቀበሌው አስተዳደርና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ተሬሳ ገልፀዋል፡፡ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጥቆማ ሲደርሰው በፍጥነት ወደ አካባቢው በማምራት የማክሸፍ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡ህብረተሰቡ አካባቢውን ከጥፋት ኃይሎች በንቃት እንዲጠብቅና አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲታዘብ ጥቆማ እንዲያደርሰው የከተማው ፖሊስ ጥሪ ማቅረቡን ከሰበታ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

"ከአትክልት ተራ ተነስተው በጃን ሜዳ እንዲሰሩ የተደረጉ የአትክልት ነጋዴዎች በቅርብ ቀን ወደ ተዘጋጀላቸው የገበያ ማዕከላት ይዘዋወራሉ"ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተለያዩ አካባቢዎች በመገንባት ላይ ያሉ አዲስ እና ነባር የገበያ ማዕከላትን ጎብኝተዋል፡፡ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በጀሞ ፣በኮልፌ ፣በሃይሌ ጋርመንት እና በሌሎች አካባቢዎች በግንባታ ላይ ያሉ የአትክልት ገበያ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ከጉብኝታቸው በኃላ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት ህዝብ መተፋፈግን በመቀነስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ለመከላከል ከአትክልት ተራ ተነስተዉ በጃን ሜዳ እንዲሰሩ የተደረጉ የአትክልት ነጋዴዎች በቅርብ ቀን ወደ ተዘጋጀላቸው የገበያ ማዕከላት ይዘዋወራሉ ብለዋል።
የአዲስ የተገነቡና ነባር የገበያ ማዕከላት እድሳታቸው ተጠናቆ ቅድሚያ በጃን ሜዳ ላሉ የአትክልት ተራ ነጋዴዎች እንዲሰጡ ይደረጋል ያሉት ወ/ሮ አዳነች ለስራ ክፍት ሲሆኑም ለአምራች ፣ለነጋዴ እና ለሸማቹ የተሻለ የገበያ አቅረቦትና ትስስር እንደሚፈጥሩ አያጠራጥርም ሲሉ ገልጸዋል።
Via Addis Ababa City PS

በማይካድራ ንፁኃን በግፍ የተገደሉበት ቦታዎች እየተገኙ ነው፡፡
በማይካድራ ንፁኃን ተገድለው የተቀበሩባቸው ቦታዎች በመገኘት ላይ ናቸው፡፡የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መረጃ በትንሹ 600 ሰዎች መግደላቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ በየቦታው የተገደሉ ሰዎች ስለሚገኙ ቁጥሩ ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችልም አመላክቷል፡፡በማይካድራ ከተማ አብነትና ሴንትራል መውጫ በተባሉ ገጠራማ ቦታዎች 74 ንጹሃን የተቀበሩበት ሥፍራ ተገኝቷል፡፡56 ዜጎች በአንድ ጉድጓድ ተቀብረው ነው የተገኙት፡፡የውሃ ጉድጓድ ውስጥም የሰለባዎቹ አስክሬን መኖሩም ተረጋግጧል፡፡
የህወሓት ልዩ ኃይልና ሳምሪ በተባለው ገዳይ ቡድን በግፍ የተገደሉ ንጹኃን ከሰው እይታ ለማራቅ ነበር ይህንን ያደረጉት ይላሉ የአይን እማኞች ለአብመድ በሰጡት ምስክርነት፡፡ቡድኑ ከጅምላ ግድያው በኋላ የዘር ማጥፋቱን ወንጀል ከአለምዓቀፉ ማኅበረሰብ ለመደበቅ የግድያው ሰለባ ንፁሃንን አስክሬን ከከተማዋ አርቆ መደበቁን ከጥቃቱ የተረፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ቡድኑ ከጭፍጨፋው በተጨማሪም በከተማዋ የሚኖሩ አማራዎች በስጋት እንዲሸሹ የማድረግ ትልም እንደነበረውም ተገልጿል፡፡በገዳይ ቡድኑ ህይወታቸው ያለፉ የንፁሃን ዜጎች አስክሬን በክብር እንዲያርፍ ተደርጓል፡፡
Via AMMA

በአሶሳ ከተማ ጥቃት ለማድረስ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 152 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ!
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግስት አሶሳ ከተማ ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 152 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡በአሶሳ ከተማ በቅርቡ የሕወሓትን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉት 152 ተጠርጣሪዎች ትናንት በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አብዱልሙኒየም ኡስማን ግለሰቦቹ ከህወሃት በተቀበሉት ተልዕኮም በሰሜን እዝ ላይ የደረሰውን ጥቃት በአሶሳ ከተማና አካባቢው ለመድገም ሲዘጋጁ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን ተናግረዋል፡፡ከተጠርጣሪዎቹ ጋር የተለያዩ የባንክ ደብተሮች፣ የጦር መሳሪያ፣ ጥሬ ገንዘብና ሌሎች ማስረጃዎች ፖሊስ ማግኘቱን ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል ሲሉም ጠቅሰዋል።
አክለዉም የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የማያሰጥ መሆኑን ተከትሎ በማረሚያ ቤት ሆነው የፍርድ ሂደቱን እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል ሲሉ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ያቀረበውን የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ መፍቀዱንም አቶ አብዱልሙኒየም አስታውቀዋል፡፡
Via @addiszeybe

Forwarded from YeneTube
Virtual agrofood & plastprintpack 2020 kicked off yesterday with a brilliant start and lived up to its name: A truly global event with a clear Africa focus.
Only on the first day
- no fewer than 904 attendees have already become active users, out of the 2,001 meanwhile registered from 81 countries. The attendees networked with each other and of course with the 63 exhibitors from 17 countries participating
- a total of 2,022 contacts were made
- 4,522 messages were exchanged
- 444 participants attended the panel sessions, presentations and product demos
- The opening talk on how exhibitors, attendees & speakers can best benefit from the event was followed by 172 participants
on today's conference programme we will have 1-panel discussions, 19 presentations, and 3 product demos! Don't miss it!
Not yet registered? register today for free as an attendee right here. https://reg

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እና ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በአሁኑ ወቅት ቤተሰቦቻቸው በትግራይ ክልል የሚገኙ ወገኖችን ለማገናኘት አስቀድመው ካሳወቋቸው ተጨማሪ ሁለት አዳዲስ ቁጥሮችን ይፋ አደረጉ።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እና ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በቀድሞዎቹ ቁጥሮች 09 43 12 22 07 እና 0115 52 71 10 መረጃ እየተቀበሉ የቆዩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ነገር ግን እነዚህ ስልክ ቁጥሮች በርካታ ጥሪዎች እያስተናገዱ በመሆናቸው መረጃ ሰጪ ወገኖች እየተቸገሩ በመሆኑ፤ ችግሩን ለመቅረፍ ተጨማሪ ስልክ ቁጥሮችን ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡
ተጨማሪዎቹ ቁጥሮችም፡- 09 80 19 27 06 እና 09 80 19 27 09 ናቸው፡፡

ለታገዱት 38 ድርጅቶች ገንዘብ ገቢ ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በባንክ በኩል እንዲፈጽም ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አሳሰበ!
ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት እና ዘርን መሰረት ያደረገ ኹከት እና ብጥብጥ እንዲነሳ በማድረግ ሂደት ውስጥ እንዲሁም ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ በተፈጸመ ህገ-ወጥ ተግባር ውስጥ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በወንጀል ተግባር ተሳትፈዋል በሚል ተጠርጥረው ምርመራ የተጀመረባቸው ከህወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸው 38 ድርጅቶች መታገዳቸው ይታወቃል፡፡
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ላይ እንዳለው ‹‹የድርጅቶቹ የባንክ ሂሳብ መታገዱን ተከትሎ ለድርጅቶቹ ገቢ የሚሆኑ ገንዘቦች በባንክ በኩል መከፈሉ ቀርቶ በእጅ ለእጅ ወይም በካሽ እንዲከፈላቸው የሚጠይቁ እና የሚቀበሉ የታገዱ ድርጅቶችን አመራሮች እና ክፍያውን በዚሁ መልክ የሚፈጽሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እንዳሉ ደርሰንበታል፡፡›› ብሏል
‹‹ድርጊቱ የምርመራ ስራውን የሚያደናቅፍ፣ ለግብር ስወራ ወንጀል ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር እና ከብሄራዊ ባንክ መመሪያ ድንጋጌዎች ጋርም የሚጋጭ እና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር በመሆኑ የድርጅቶቹ አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም በዚሁ መልክ ክፍያዎችን እየፈጸማችሁ ያላችሁ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን በድርጊቱ የሚሳተፉ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን በምርመራ አጣርተን በህግ እንዲጠየቁ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን›› ሲልም ጨምሮ ገልጿል፡፡
‹‹ማንኛውም ወደ ታገዱት ድርጅቶቹ ገንዘብ ገቢ ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በባንክ በኩል እንዲፈጽም እያሳሰብን የሚኖሩትን ጥያቄዎች እና ጥቆማዎች ለተቋማችን ማቅረብ የሚችል መሆኑን አክለን እናሳውቃለን ›› ሲል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡