በኢትዮጵያ ከጥቂት አካካቢዎች በቀር በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋረጠ!
በአገሪቱ ከጥቂት አካባቢዎች በቀር በሁሉም ቦታዎች በሚባል ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡንየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ፡፡
ኃይል የተቋረጠው ዛሬ ህዳር 15/2013 ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት እንደሆበ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
በቴክኒክ ችግር የተቋረጠውን ኃይል ለመመለስ የቴክኒክ ክፍል የሥራ ባልደረቦች በሥራ ላይ መሆናቸውም ሞገስ ጠቁመዋል።
@YeneTube @FikerAssefa

የቀድሞው ጠ/ሚር ሃይለማርያም ደሳለኝ የፌዴራል መንግስትና የህወሓት አመራሮች ለመደራደር የሞራል እኩልነት የላቸውም አሉ።
የህወሓት አመራሮች ጦርነቱን ያስጀመሩት አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማደራደር በሚገባበት ጊዜ ከዚህ በፊት ሲፈፅሙ ከነበረው አሁንም እየፈፀሙ ካሉት ወንጀል ራሳቸውን ለማስመለጥ እንደሆነ እንደሚያምኑ ለፎሬይን ፖሊሲ መፅሔት በፃፉት አምድ ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ችግሩ በውይይት እንዲፈታ የሚያደርገው ውትወታ የችግሩን ምንጭ በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ ነው ብለዋል።
የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ስቦ የፌዴራል መንግሥት ለድርድር እንዲቀመጥ ከማድረጉ ውጭ የህወሃት አመራሮች በጦርነት እንኳን ቢሆን የመከላከያ ሠራዊትን የመርታት አቅም አለን ብለው ያስቡ እንደነበር፣ ይህም ሃሳባቸው ከዚህ በፊት ጦርነትን ማሸነፍ በመቻላቸው አሁንም ያ ታሪክ ይደገማል የሚል እምነት ስለነበራቸው እንደነበር፣ ይህም ሳይሆን እንደ ቀረ አሁን እየተመለከትን ነው ብለዋል።
ሌላኛው የህወሓት አላማ ግጭቱን አለማቀፋዊ መልክ ማስያዝ የነበረ ሲሆን ይህም ወደ አስመራ ሮኬት በመተኮስ ቢሞከርም ትኩረት ከመሳብ ይልቅ ውግዘትን እንዳስከተለባቸው ተናግረዋል።
እንደ አቶ ሃይለማርያም ገለፃ እስካሁን ለህወሓት እየሰራለት የሚገኘው ከተለያዩ አካላት የሚሰነዘረው የችግሩ በውይይት ይፈታ ውትወታ ነው። ነገር ግን ይህ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የማይሆን መንገድ መሆኑን አንስተው መንግስት የሚወስደውን እርምጃ በፍጥነትና ንፁሃን ዜጎችን በማይጎዳ መልኩ ከውኖ ወንጀለኞችን ለህግ ማቅረቡ ብቸኛ አማራጭ ነው ብለዋል።

#NewsAlert
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥቅምት 30 በማይካድራ ከተማ የነበረው የሰዎች ግድያ “በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅር እና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን” የተፈጸመ መሆኑን ገለጸ። ድርጊቱንም “ግፍና ጭካኔ የተሞላበት፤ በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል” ሲል ጠርቶታል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

YeneTube
#NewsAlert የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥቅምት 30 በማይካድራ ከተማ የነበረው የሰዎች ግድያ “በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅር እና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን” የተፈጸመ መሆኑን ገለጸ። ድርጊቱንም “ግፍና ጭካኔ የተሞላበት፤ በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል” ሲል ጠርቶታል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) @YeneTube @FikerAssefa
በማይካድራ የተፈጸመው የግፍ ግድያ የጦር ወንጀል የመሆን እድል እንዳለው ኢሰመኮ አስታወቀ።
በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን በምትገኘው የማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን የተፈጸመው ጥቃት፤ ግድያ፣ ጉዳትና ውድመት፤ ጠቅላላ ድርጊቱና ውጤቱ ግፍና ጭካኔ የተሞላበት በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል (atrocious crime of massacre against civilians) መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው ኮሚሽኑ ከሕዳር 5 እስከ ሕዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በማይካድራ ከተማ እንዲሁም በአብርሀጅራ፣ በሳንጃ፣ በዳንሻ፣ በሁመራ እና በጐንደር ከተማ ተዘዋውሮ ባደረገው ምርመራ የደረሰበትን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት የመጀመሪያ ደረጃ ቀዳሚ ሪፖርት ነው፡፡ይህ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል (crimes against humanity) እና የጦር ወንጀል (war crime) ሊሆን እንደሚችል የሚያመለክት ስለሆነ ኮሚሽኑ ዝርዝር ማስረጃዎቹን እና ወንጀሉን የሚያቋቁሙትን የሕግና የፍሬ ነገር ትንተና በሙሉ ሪፖርቱ ላይ በዝርዝር አጣርቶ የሚያቀርብ መሆኑን አሳውቋል፡፡
በቀዳሚ ሪፖርቱ እንደተመለከተው በአካባቢው የነበረው የሚሊሽያና የፖሊስ ጸጥታ መዋቅር በፌዴራሉ አገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃ ሸሽቶ አካባቢውን ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት ሳምሪ ከተባለ መደበኛ ያልሆነ የትግራይ ወጣቶች ቡድን ጋር በማበርና በመተባበር በተለይ ‹‹አማሮችና ወልቃይቴዎች›› ያሏቸውን የአካባቢው ነዋሪ ሲቪል ሰዎች ከቤት ቤት እየዞሩና በየጐዳናው ላይ በገመድ በማነቅ፣ በስለት በመጥረቢያ በዱላ በመደብደብ ገድለዋል፣ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፣ እንዲሁም ንብረት አውድመዋል፡፡
ኢሰመኮ ከአካባቢው ምንጮች እስከ አሁን ባገኘው መረጃ በአነስተኛ ግምት እስከ 600 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ትክክለኛው ቁጥር ከዚህ ሊበልጥም እንደሚችል በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡
ሳምሪ የሚባለው የትግራይ ወጣቶች ቡድን በዚህ ከባድ ወንጀል ላይ ቢሰማራም፤ በአንጻሩ የትግራይ ብሔረሰብ ተወላጅች የሆኑ ሌሎች የአካባቢው ነዋሪዎች አጥቂው ቡድን ሲያሳድዳቸው የነበሩ ሲቪል ሰዎችን በቤታቸው፣ በቤተክርስቲያን እና በእርሻ ቦታ ደብቀው በመሸሸግ ሕይወታቸውን እንዳተረፉላቸው ኢሰመኮ ያነጋገራቸው ምስክሮች አረጋግጠዋል፡፡
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ‹‹በማይካድራ ከተማ በአነስተኛ ጽንፈኛ ቡድን የተፈጸመው በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ እጅግ ዘግናኝ ኢሰብዓዊ ወንጀል ልብ ሰባሪ ቢሆንም፤ በአንጻሩ ኢትዮጵያውያን በብሔር ሳይለያዩ አንዱ የሌላው ጠባቂ ሆነው መታየታቸው ልብ ይጠግናል፤ ስለ ወደፊት በሰላም አብሮ መኖርም ተስፋ ይሰጣል›› ብለዋል፡፡ አክለውም ‹‹የተጐዱ ሰዎችን እና አካባቢዎችን መልሶ ከማቋቋምና ከመጠገን በተጨማሪ፤ በዚህ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተሳተፉ በየደረጃው ያሉ ጥፋተኞችን በሕግ ፊት ተጠያቂነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡
Via Capital

በኢትዮጵያ ከጥቂት አካካቢዎች በቀር በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋረጠ! በአገሪቱ ከጥቂት አካባቢዎች በቀር በሁሉም ቦታዎች በሚባል ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡንየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ፡፡ ኃይል የተቋረጠው ዛሬ ህዳር 15/2013 ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት እንደሆበ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር…
#update
በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ከሁለት ሰዓት በላይ ተቋርጦ የነበረውን ኃይል በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማገናኘት ተጀምሯል።
ደረጃ በደረጃ የተቀሩትን አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ የማድረግ ስራም በመከናወን ላይ ይገኛል።
[EEPCo]
@YeneTube @FikerAssefa
በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ከሁለት ሰዓት በላይ ተቋርጦ የነበረውን ኃይል በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማገናኘት ተጀምሯል።
ደረጃ በደረጃ የተቀሩትን አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ የማድረግ ስራም በመከናወን ላይ ይገኛል።
[EEPCo]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል "በግፍ ተፈጽመዋል የተባሉ ወንጀሎችን" የሚያጣራ የምርመራ ቡድን ወደ ስፍራው በማቅናት ስራ መጀመሩን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በትግራይ ክልል እየተወሰደ ያለውን የሕግ ማስከበር እርምጃ አስመልክቶ ለውጭ አገራት ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ማይካድራን ጨምሮ በትግራይ ክልል "በግፍ ተፈጽመዋል የተባሉ ወንጀሎችን" የሚያጣራ የምርመራ ቡድን አካባቢው ላይ ደርሷል ብለዋል።የሕወሓትን አመራሮች በከባድ ወንጀል ሊያስጠይቁ የሚችሉ ወንጀሎችን መፈጸማቸውን ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አብራርተዋል።
በተለይም የሰሜን እዝ ካምፖች ላይ የተፈጸመው ድርጊት የአገር የመከላከያ ሃይልን በማጥቃት የተፈጸመ በመሆኑ በከባድ ወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።በባህርዳርና በጎንደር ከተሞች የተፈጸሙት የሮኬት ጥቃቶችም በሽብርተኝነት ተግባር የሚያስጠይቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።በሰሜን ዕዝ ላይ በተፈጸመው ጥቃት እጃቸው አለበት የተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ፌዴራል ፖሊስና ጠቅላይ ቃቤ ህግ በፍርድ ቤት በኩል የእስር ማዘዣ እንዲወጣባቸው አድርጓል ብለዋል።እስካሁን በተደረገው ምርምራ ተጥርጣሪ ተብለው የተለዩ ሰዎች ቁጥር 167 መድረሱንም ገልጸዋል።
የሕግ ማስከበር እርምጃው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ እየተከናወነ ስለመሆኑም አብራርተዋል።የግል ድርጅቶች ሆነው ለህወሃት ቡድን የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ አድርገዋል የተባሉ 34 ተቋማት የባንክ ሒሳብ ጨምሮ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረታቸው ከሕዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መታገዱን ገልጸዋል።ተቋማቱ ብሔር ተኮር ጥቃትና የሽብር ድርጊት እንዲፈጸም የገንዘብ ድጋፍ በማቅረብ፣ ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ከሚንቀሳቀሰው የሕወሓት ቡድን ጋር ግንኙነት ፈጥረዋል ተብለው በመጠርጠራቸው መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ አቅርበዋል።
በግንኙነቱ ወቅት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ደመቀ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል የተጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስረድተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንቴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የጀመረችው ህግ የማስከበር እርምጃ በኃላፊነት እና በጥንቃቄ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል።
Via Walta

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር ሞያሌ አካባቢ ሶመሬ በምትባል ቦታ ህብረተሰቡ ባደረገው ጥቆማ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተያዙ፡፡
ከተያዙት ውስጥ አምስቱ መቁሰላቸውን የሞያሌ ወረዳ ኮምኒኬሽን ፅህፈት ቤት ገልጿል።የክልሉ ፖሊስ ግለሰቦቹን ለሚያዝ ጥረት ሲያደረግ በወሰደው እርምጃ 4 የኦነግ ሸኔ አባላት ገደላቸውን አዲስ ዘይቤ አረጋግጫለው ብላለች።
ምንጭ: @addiszeybe
@YeneTube @FikerAssefa
ከተያዙት ውስጥ አምስቱ መቁሰላቸውን የሞያሌ ወረዳ ኮምኒኬሽን ፅህፈት ቤት ገልጿል።የክልሉ ፖሊስ ግለሰቦቹን ለሚያዝ ጥረት ሲያደረግ በወሰደው እርምጃ 4 የኦነግ ሸኔ አባላት ገደላቸውን አዲስ ዘይቤ አረጋግጫለው ብላለች።
ምንጭ: @addiszeybe
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከተማ ለአካባቢ ጥበቃ የተለዩ 632 ቦታዎች ላይ ህገወጥ ወረራና ግንባታ መፈፀሙ ገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ህገወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ ላይ ያሉ ችግሮችን በሚመለከት ያስጠናውን ጥናት ማጠቃለያ ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን፣ 632 ቦታዎች ላይ በህገወጥ ወረራና ግንባታ ተፈፅሞ መገኘቱን አስታውቋል።ለሁለት ወራት የተደረገው ጥናቱ ለአካባቢ ጥበቃ የተለዩ ቦታዎችን በህገወጥ በመውረር መያዝ፣ የሪልስቴት አልሚዎች በህጋዊ መንገድ ከተሰጣቸው ቦታ ውጪ በህገወጥ አስፋፍቶ መያዝ፣ መሬት ባንክ የገባ መሬት በህገወጥ መንገድ ጥቅም ላይ መዋላቸውን የጥናት ግኝቶች አመላክተዋል።
“ህገወጥ የመሬት ወረራንና ግንባታን በመከላከል በአቋራጭ መክበርን እናስቁም” በሚል የጥናቱ ግኝትና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ መለሰ አለሙ እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።ምክትል ከንቲባዋ በዚህ ወቅት እንዳሉት የተስፋፋው ህገወጥ የመሬት ወረራ በመዲናዋ ለስራ አጥነት መስፋፋትና ኢ-ፍትሐዊ ለሆነ የሀብት ክፍፍል መዳረጉን አንስተዋል።በመሆኑም እርምጃ ለመውሰድና ችግሩ እንዳይቀጥል ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካል በአንድ ሊቆም ይገባል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ለአካባቢ ጥበቃ የተለዩ 632 ቦታዎች ላይ ህገወጥ ወረራና ግንባታ መፈፀሙ ገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ህገወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ ላይ ያሉ ችግሮችን በሚመለከት ያስጠናውን ጥናት ማጠቃለያ ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን፣ 632 ቦታዎች ላይ በህገወጥ ወረራና ግንባታ ተፈፅሞ መገኘቱን አስታውቋል።ለሁለት ወራት የተደረገው ጥናቱ ለአካባቢ ጥበቃ የተለዩ ቦታዎችን በህገወጥ…
በአዲስ አበባ ከተማ ከ1352 ሄክታር በላይ መሬት በህገወጥ መንገድ መያዙን እና ከ79ሺህ በላይ ቤቶች ደግሞ በህገወጥ መንገድ መገንባታቸው ተገለፀ።
ከህገወጥ የመሬት ወረራ እና ግንባታ ችግሮችን ለማጥራት ሲካሄድ የነበረው የጥናት ግኝት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ይፋ ሆኗል።ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት በከተማዋ መሬት አንዱና ዋነኛው ሀብት በመሆኑ በመረጃ እና በስርዓት ተገቢውን ግልጋሎት እንዲሰጥ ማድረግ ይገባል ብለዋል።በከተማዋ በመሬት ላይ የሚደረገው ህገወጥ ተግባራት ለስራ እድል ፈጠራ እና ለፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲሁም በአጠቃላይ የከተማዋ እድገት ማነቆ እንደሚፈጥር ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል ።
በቅርቡ በአስሩም ከፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች በተካሄደው ከህገወጥ የመሬት ወረራ እና ግንባታ ችግሮችን ለማጥራት የጥናት ግኝት መሰረት በ632 ቦታዎች ከ1352 ሄክታር በላይ መሬት በህገወጥ መንገድ መያዙን ግኝቱ አመላክቷል።በተጨማሪም 79ሺህ 112 ቤቶች በህገወጥ መንገድ መገንባታቸውን በጥናቱ ተመላክቷል።
በሪል ስቴት ስም በህጋዊነት ከተሰጣቸው ቦታ ውጪ ሌላ ቦታ መውረር እና ማስፋፋት እንዲሁም ለሌሎች ግለሰቦች ማስተላለፍ ፣ወደ መሬት ባንክ የገቡ እና ለአረንጓዴ ስፍራ ተብለው የታጠሩ ቦታዎችን በቡድን ፣ በግለሰቦች እንዲሁም በባለሀብቶች መሬት የማስወረር ዝንባሌዎች እንደሚስተዋሉ ተገልጿል።በተጨማሪ በእምነት ተቋማት ስም ፣በጋራ መኖሪያ ቤቶች እና ማስፋፊያ አካባቢዎች በከተማ ግብርና ስም መሬት መውረር እና ግንባታ ማካሄድ ፣ለጥቃቅንና አነስተኛ ተብለው የተወሰዱ ቦታዎችን ለግለሰቦች ማስተላለፍ እንዲሁም በመሀል ክፍለከተሞች የመንግስት ቤቶችን በማፍረስ ለግለሰቦች ካርታ የማድረግ ህገወጥ ተግባራት ተፈጽመዋል ።
የአርሶአደሮችን መሬቶች በርካሽ ዋጋ የመግዛት ፣የመሬት ደላሎች ከባለሀብቶች እና ከመንግሥት አካላት ጋር በመመሳጠር እና የመሬት ማኔጅመንት አሰራሮችን በመጣስ መሬት መውረር እና ቤቶችን መገንባት እንደሚስተዋል በጥናት ግኝቱ ተገልጿል።የቀረበውን የጥናት ግኝት በተመለከተ ከከተማ አስተዳደሩ እና ከፌደራል ተቋማት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የተለያዩ ሀይማኖት ተቋማት ተወካዮች የመሬት ወረራ መንስኤ እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
Via Mayor Office

የህወሓት ቅጥረኞች የተዛባ መረጃን የማሰራጨት ተልዕኮን ተቀብለው ወደ ሱዳን ከሸሹ ዜጎች ጋር እንደ ተቀላቀሉ ተአማኒ መረጃን አግኝተናል ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማት ከእነዚህ ቡድኖች የሚቀበሉትን መረጃ በሚገባ እንዲፈትሹ እና እንዲያጣሩ አሳስቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማት ከእነዚህ ቡድኖች የሚቀበሉትን መረጃ በሚገባ እንዲፈትሹ እና እንዲያጣሩ አሳስቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
የህወሃት ታጣቂ ሃይል በማይካድራ የፈጸመውን ጭፍጨፋ በመቀሌ ለመድገም ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ደርሰንበታል ሲሉ የመከላከያ ኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ተናገሩ።
ቡድኑ ድርጊቱን የሚፈጽመው ልዩ ቡድን አዘጋጅቶና በአልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ያዘጋጀውን የመከላከያንና የኤርትራ ሰራዊት ዩኒፎርሞችን በማልበስ እንደሆነም ነው የጠቆሙት።ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማ ይህን ያሉት ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።
የ'ህወሃት የጥፋት ሃይል' ያሰበው ሴራ ሁሉ እየከሸፈበት መሆኑን ጠቅሰው፤ አሁን ላይ ደግሞ አዲስ የጥፋት እቅድ ማውጣቱን ደርሰንበታል ብለዋል ሜጀር ጀነራል መሀመድ።በዚህም በማይካድራ ንፁሃን ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋ በመቀሌ ለመድገም ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጸው ድርጊቱን ለመፈጸም ደግሞ ልዩ የገዳይ ቡድን ማዋቀሩንም ነው የተናገሩት።
የገዳይ ቡድን አባላቶችን በአልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ያዘጋጀውን የኢፌዴሪ መከላከያ እና የኤርትራ ሰራዊት ዩኒፎርሞችን በማልበስ ጭፍጨፋውን ለመፈጸም ተዘጋጅቷል ብለዋል።ቡድኑ ይህን የሚያደርገው የኢትዮጵያና የኤርትራ ሰራዊት በጋራ በመሆን ንፁሃንን እንደጨፈጨፉ በማስመሰል ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ ለማግኘት መሆኑንም ገልጸዋል።
(ኢዜአ)

ሱዳን የግጭት ቀጠና ከሆነው የኢትዮጵያው ትግራይ ክልል ለሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ድንበሯን እንደማትዘጋ መግለጧን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡
ይህን ማረጋገጫ ለጋዜጣው የሰጡት የሀገሪቱ ምድር ጦር ዋና አዛዥ ጀኔራል ኢሳም ሞሐመድ ሐሰን ካራር ናቸው፡፡ ከትግራይ ክልል ግጭት ከተቀሰቀሰ ወዲህ 45 ሺህ ያህል ስደተኞች ሱዳን እንደገቡ ዐለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች ተናግረዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከሕወሃት ጋር በእኩል ይደራደር ማለት ሀገሪቱን የሚበታትን አማራጭ ነው ሲሉ የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኡመር ጌሌህ ለአፍሪካ ሪፖርት መጽሄት በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡ ሕወሃት የተባለው ድርጅት ፌደራል መንግሥቱን በሃይል ለማንበርከክ ራሱን ያደራጀ ሃይል ነው- ብለዋል ፕሬዝዳንት ጌሌህ፡፡ ዐቢይ ከድርድር ይልቅ ሕወሃትን የመቅጣት አማራጭ መከተላቸው ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነ በሚጠቁም መልኩ፣ ማንም ሰው ራሱን በዐቢይ ጫማ ውስጥ አስቀምጦ ችግሩን ማየት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#የጥፋት_አርበኞች
#አዲስ_መጽሐፍ_በገበያ_ላይ
አንዳንድ ሀገሮች የመፈራረስ ዕጣ ፈንታ የገጠማቸው በጥፋት አርበኞች የጀብደኝነት ተግባር እንደሆነ ያውቃሉ? እኛስ እያጋጠመን ያለው ይሄው እጣፈንታ ይሆን?
የጥፋት አርበኞች የሚንቀሳቀሱት ከንቃተ ህሊናቸውን ጋር በተፋቱ ስሜቶቻቸውና በተሳሳቱ እምነቶች እንጂ በምክንያት አይደለም! መመሪያቸው አረመኔያዊነት፣ ተግባራቸውም እንሰሳዊነት ነው ይላል፡፡ #የጥፋት_አርበኞች_ልክ_የበሰበሰ_ሬሳ_ላይ_እንደሚራኮቱ_ምስጦች_የሚተባበበሩት_ለጥፋት_ነው፡፡
#ይሄ_መፅሐፍ_ደግሞ_ብዙ_ የጥፋት_ሚስጥራቸውን_ይገልጥልናል፡፡
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።
ይቀላቀሉን 👉http://tttttt.me/teklutilahun

#መልካም_ሰዎች_ለምን_ይሰቃያሉ?
#ሁለተኛው_ዕትም_በገበያ_ላይ
መልካም ሰዎች ላይ መጥፎ ነገር የሚደርሰው ለምንድን ነው? መከራን የሚቀበሉትስ ለምን ይሆን? ከዚህ ሁሉ ጥያቄ በኋላ እኛ ያላወቅነው ምስጢር ይኖር ይሆን?
ይህ መጽሐፍ ‹‹ፈጣሪ ለምንድነው ይሄን ሁሉ በእኔ ላይ ያመጣብኝ?›› ለምንለው ነገር ሁሉ ምላሽ አለው!!!
“በሃሳቦች የተሞላ፣ በተዋጣላቸው አመክንዮዎች የተተነተነ፣ የመንፈሳዊ ጥንካሬ መመሪያዎችን የያዘ ድንቅ መጽሐፍ!!”
#ዘ_ዋሽንግተን_ፖስት
“ይህ ላዘኑ መጽናናትን፣ ማባሪያ በሌለው ፍርሃት ለተተበተቡት ሰዎች ደግሞ ሰላምን የሚሰጥ የሃሳብ እድገት መጽሐፍ ነው!”
#ስፕሪችዋሊቲ_ኤንድ_ሄልዝ
“ይህ ለሰው ልጆች ሁሉ አስፈላጊ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ በመከራ የተሞሉ የህይወትን ውጣ ውረዶችን ለመረዳትና ፈጠራ በተሞላበት ጥብበ ለመወጣት ይጠቅማል!”
#ኖርማን_ቪንሰንት_ፒል
#ሁለተኛውን_ዕትም_በየመጽሐፍት_መደብሩና_በአዟሪዎች እጅ ያገኙታል።
👉 ይቀላቀሉን http://tttttt.me/teklutilahun

TOP book series 📚ቶፕ የተማሪዎች አጋዥ መፅሀፍት
📌ከ 1-12 ክፍል በ ተለያዩ ቋንቋ የተዘጋጀ
📌በ ኦሮምኛ
📌በ አማርኛ
📌በ እንግሊዘኛ በሁሉም አይነት ትምህርት የተዘጋጀ
- maths chemistry biology physics ...
📌ለ 8 እና 12ኛ ክፍል ፈተና የሚያዘጋጁ
📌ለ ልጆችም 20 አይነት ተረት መጽሀፍት ታትሞዋል
❗️❗️በሁሉም መፅሀፍት ቤት ይጠይቁ
ዋና አከፋፋይ : ኤደን መጽሀፍት ቤት
* * መገናኛ ሀይሌ ህንፅ ፊት ለ ፊት
📞 0911238057
0912732493
@TOPBOOkSERIES
📌ከ 1-12 ክፍል በ ተለያዩ ቋንቋ የተዘጋጀ
📌በ ኦሮምኛ
📌በ አማርኛ
📌በ እንግሊዘኛ በሁሉም አይነት ትምህርት የተዘጋጀ
- maths chemistry biology physics ...
📌ለ 8 እና 12ኛ ክፍል ፈተና የሚያዘጋጁ
📌ለ ልጆችም 20 አይነት ተረት መጽሀፍት ታትሞዋል
❗️❗️በሁሉም መፅሀፍት ቤት ይጠይቁ
ዋና አከፋፋይ : ኤደን መጽሀፍት ቤት
* * መገናኛ ሀይሌ ህንፅ ፊት ለ ፊት
📞 0911238057
0912732493
@TOPBOOkSERIES
ስናፕቻት ስኬታማ ደንበኞቼን በየቀኑ 1 ሚሊዮን ዶላር እሸልማለሁ አለ!
ከማኅበራዊ የትስስር ገጾች አንዱ የሆነው ስናፕቻት ‹ስፖትላይት› በተሰኘው አዲስ ገጽታው ላይ እጅግ ተወዳጅ ቪዲዮ ሰርተው ለሚያጋሩ ተጠቃሚዎቹ በየቀኑ አንድ ሚሊዮን ዶላር እሸልማለሁ አለ።ስናፕቻት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከቲክቶክ ጋር ከፍተኛ የገበያ ውድድር ላይ ስለሚገኝ ነው።ስፖትላይት የተሰኘው የስናፕቻት አዲስ ገጽታ የአልጎሪዝም ቀመርን በመጠቀም ብዙ ሰዎችን ያነጋገረና ብዙዎች መድረስ የቻለ ቪዲዮ ሲኖር ተጠቃሚዎቹ እንዲመለከቱት ይጋብዛል።ይህም የሚሆነው የተጠቃሚውን የፍላጎት አዝማሚያዎችን መሠረት በማድረግ ነው። አንድ ተጠቃሚ እንዲመለከታቸው የሚጋበዘው ቪዲዮ የሕይወት ዝንባሌውን መሠረት ባደረገ መልኩ ነው።
ይህ በየቀኑ አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚያሸልመው አዲስ አሰራር በስናፕቻት ከፍተኛ ተከታይ ያላቸው ኮከብ ደንበኞቹን ብቻ ሳይሆን ማንኛውም የስናፕቻት ተጠቃሚን የሚያካትት ነው።በየቀኑ አንድ ሚሊዮን ዶላር የመሸለሙ ነገር እስከዚህኛው የፈረንጆች ዓመት ማብቂያ የሚዘልቅ ነው።ነገር ግን ደንበኞችን በመሳብ ረገድ የተፈለገውን ውጤት ማምጣቱ ከተረጋገጠ በ2021 ሊቀጥል እንደሚችል ተጠቁሟል።
ተሸላሚ የሚሆኑት ደንበኞች ሰርተው የሚያጋሩት ቪዲዮ ተወዳጅ መሆን ብቻም ሳይሆን በከፍተኛ ፍጥነት መዛመት የሚችል እንዲሆን ይጠበቅበታል።ስናፕቻት በየቀኑ 1 ሚሊዮን ዶላር የሚሸልመው ሆኖም ቪዲዮው በስንት ሰዎች ሲወደድ እንደሆነ አላስቀመጠም።
ሽልማቱ ለስንት ሰዎች እንደሆነ፣ ይህ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ስንት ሰዎች እንደሚካፈሉትም አልተብራራም።ሆኖም በዚህ ውድድር ለመታቀፍ ተጠቃሚዎቹ ዕድሜያቸው 16 እና ከዚያ በላይ መሆን ግድ ይላል።የሚጋሩት ቪዲዮዎች አደገኛ እጽና አልኮል መጠጦችን የሚያበረታቱ መሆን የለባቸውም።የስናፕሻት ደንብና ግዴታዎችም ተፈጻሚ ይሆናሉ።ስናፕቻት ኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ በቀን የተጠቃሚዎች ቁጥር 250 ሚሊዮን ደርሶልኛል ይላል።ሆኖም የቢዝነስ ተወዳዳሪዎቹ ኢንስታግራምና ቲክቶክ ከፍተኛ የደንበኛ ቁጥር በማስመዝገባቸው ስናፕቻት ተወዳዳሪ ሆኖ ለመዝለቅ ይህን ከፍተኛ መጠን ያለውን ሽልማቱን እንዳዘጋጀ ተነግሯል።
[BBC]

Audio
በማይካድራ ተገኝተው ምርምር ያደረጉ አጥኚን የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ አነጋግሯል!
በማይካድራ ከተማ በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 600 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ትናንት ማስታወቁ ይታወሳል።ኮሚሽኑ ትናንት ይፋ ባደረገው የፈጣን ምርመራ ግኝት፤ ከጥቃቱ በኋላ ወደ ስፍራው የምርመራ ቡድን በመላክ ዘግናኝ የሆነ የሰባዊ መብት ጥሰት መፈፀሙን ማረጋገጡን ገልጿል።
ጥቃቱም የተፈፀመው በትግራይ ሚሊሺያ አስተባባሪነት በሚታገዙና በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅር እና ‘ሳምሪ’ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን መሆኑንም ይፋ አድርጓል።
በሌላ በኩል አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተሰኘው ዓለም አቀፍ ተቋም የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ “ህወሓት” በሚያካሂዱት ጦርነት፤ ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ሰላማዊ ዜጎች ደህንነት እንዲጠብቁ አሳሰቧል።
በተጨማሪም መንግሥት የሰብዓዊ ረድኤት አቅራቢዎች ወደ ሥፍራው ገብተው ድጋፍእንዲሰጡ ሁኔታውን እንዲያመቻች ጥሪ አቀረቡ።
ወደ ማይካድራ፣ አብርሀጅራ፣ በሳንጃ፣ በዳንሻ፣ በሁመራ እና በጐንደር በመዟዟር ጥናት ካካሄዱት የኢሰመኮ አጥኒዎች መካከል አንዷ የሆነችውን ሃይማኖት አሸናፊን እና የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች አጥኚ ፍሰሐ ተክሌን የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ያነጋገራቸው ሲሆን ዝርዝርሩን ከላይ ተያይዟል።

የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የ15 አፍሪካ አገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ ከመጓዛቸው በፊት ተመላሽ የሚሆን እስከ 15ሺህ ዶላር በቦንድ መልክ ማስያዝ አለባቸው የሚል አዲስ ጊዜያዊ ሕግ አውጥቷል።
ይህ ሕግ ተፈጻሚ መሆን የሚጀምረው ከአንድ ወር በኋላ ሲሆን ለስድስት ተከታታይ ወራት ከዘለቀ በኋላ ውጤታማ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
ይህ ሕግ ተፈጻሚ የሚሆንባቸው አገራት፤ አንጎላ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ቻድ፣ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ጋምቢያ፣ ጊኒ-ቢሳው፣ ላይቤሪያ፣ ሊቢያ፣ ሞሪታኒያ፣ ሱዳን፣ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ፣ ኬፕ ቨርዴ እና ቡሩንዲ ናቸው።
አገራቱ የተለዩት ወደ አሜሪካ ካቀኑ ዜጎቻቸው 10 በመቶ እና ከዛ በላይ የሚሆኑት ዜጎቻቸው በተሰጣቸው ቪዛ መሠረት ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በአሜሪካ በመቆየታቸው ነው ተብሏል።
የእነዚህ አገራት ዜጎች እንደየ ሁኔታው ለጉብኝትም ይሁን በሥራ ጉዳይ ወደ አሜሪካ ከመጓዛቸው በፊት 5ሺህ፣ 10ሺህ ወይም 15ሺህ ዶላር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ተሰናባቹ ፕሬዝደንት ትራምፕ በዋይት ሃውስ በነበራቸው የአራት ዓመት ቆይታ የኢሚግሬሽን ጉዳዮችን አስተዳደራቸው በትኩረት ሲያስፈጽመው የቆየ ጉዳይ ነው። ተመራጩ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የሪፓብሊካኑን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በርካታ የኢሚግሬሽን ፖሊሲዎች እንደሚቀይሩ ቃል ገብተዋል።
@YeneTube @Fikerassefa