YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል "ከፌዴራል መንግስት ጋር ያለው ጦርነት ቆሞ ድርድር ቢሞከር ጥሩ ነገር" አሉ

ሬዊተርስ ማምሻውን ይዞ በወጣው ፅሁፍ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል "ከፌዴራል መንግስት ጋር ያለው ጦርነት ቆሞ ድርድር ቢሞከር ጥሩ ነገር "ብለዋል።

Via:- Fidel Post
@Yenetube @Fikerassefa
ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በ97 ዓመታቸው አረፉ

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በጎንደር ክፍለ ሀገር በደብረ ታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ልዩ ስሟ መገንታ ቍስቋም በተባለች ደብር ከቄስ ወርቅነህ ትኩና ከወይዘሮ አንጓች አታሌ በ1916 ዓም ነበር የተወለዱት።

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ከፍተኛ የሃይማኖት ትምህርትን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ተምረው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሙሉ እድሚያቸውን ያገለገሉ አባት ነበሩ።ጥቅምት 28 ቀን 2013ዓም በ97 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መፅናናቱን አብዝቶ ይስጣችሁ።

ምንጭ:—EOTC TV
@Yenetube @Fikerassefa
ትናንት በምስራቅ ሀረርጌ ኮምቦልቻ ወረዳ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በሸኔ ላይ በወሰደው እርምጃ አንድ የቡድኑ አባል ሲገደል፣ አንድ ቆስሎ 16ቱ ተማርከዋል።በሀረሪ ክልል ኮሎኔል ፒሳ ከሚባል አካባቢ ከአንድ ቤት 36 ፈንጂዎች እና 6 አሸባሪዎች ተይዘዋል።

Via Taye Dendea
@YeneTube @FikerAssefa
"በነበሩን ጥቂት ጊዜያት ለዘመናት መሠረት የሚሆኑ ስራዎችን እንደሠራን አምናለሁ።" -አቶ ተመስገን ጥሩነህ

"የክልላችንን ህዝብ ስነልቦና አብሮ ለትልቅ ግብ ስኬት እንዴት መጓዝ እንዳለብን ለማስተማር አይዳዳኝም። በሀገራችን አሻራ ላይ ግዙፉን አብሮነት በተግባር ያረጋገጠ ማህበረሰብን ማገልገል በራሱ ትልቅ ትምህርትና መታደል ነው።በአማራ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራርነት ሳገለግል ለራሴ ያሳመንኩት ይህንኑ በመርህ እና ተግባር የጸናውን አብሮነት ባህል በአመራርነት ጥበባችን በማስረጽ መተጋገዝ እንደሚገባን ነው።ሁላችንም ለቆምንለት አላማ ለተሰጠን ሀላፊነት የጦር ጀነራል ነን በሚል ዋናው ስራችን ላይ ማተኮርን መምረጥ ይገባናል።በአማራ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንትነት የነበረኝ ቆይታ እጅግ መልካም የሚባል ነበር።ቆይታዬ መልካም እንዲሆን ያገዛችሁኝ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮችና መላው የክልሉ ህዝብ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በቀጣይም በብዙ ሐላፊነቶች እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ።
ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ድልና ሰላምን እመኛለሁ። አመሰግናለሁ።"

@YeneTube @FikerAssefa
የካቶሊኩ ጳጳስ የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም አማራጭ እንዲወስድ ጠየቁ!

የካቶሊኩ ጳጳስ ፍራንሲስ በኢትዪጵያ የፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልላዊ መንግስት መካከል የተጫረውን ግጭት በአፅንኦት እየተከታተሉ እንደሆነ በትላንትናው እለት በሰጡት መግለጫ የገለፁ ሲሆን አክለውም በግጭቱ ላይ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ከጦርነት ይልቅ የሰላምን አቅጣጫ እንዲመርጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።በትላንትናው እለት ከዘወትር የፀሎት መርሀግብራቸው በኋላ መግለጫውን የሰጡት ጳጳሱ የግጭት አማራጭ ለየትኛውም ወገን አይበጅም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በትግራይ ክልል እና በፌደራል መንግስታት መካከል በወቅቱ በተከሰተው ግጭት በክልሉ እና በክልሉ ዙርያ የሚገኙ ከዘጠኝ ሚልዮን በላይ ኢትዮጵያውያን የመፈናቀል አደጋ እንደተጋረጠባቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የገለፀ ሲሆን የትግራይ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ባሳለፍነው እሁድ ከፌደራል መንግስት ጋር ያላቸውን ቅራኔ በውይይት መፍታት እንደሚፈልጉ በትግራይ ቲሌቭዥን በሰጡት መግለጫ መናገራቸው የሚታወስ ነው። በክልሉ የተከሰተው ግጭት ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከተጀመረ ወዲህ አምስተኛ ቀኑን ዛሬ እንደያዘ የሚታወስ ነው።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ካሉ የመንጃ ማሰልጠኛ ተቋማት መካከል መስፈርቱን ያሟሉት 40 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከዘርፉ አመራሮች ከአሽከርካሪ ማሰልጠኛ እና ከተሽከርካሪ ምርመራ ተቋማት ባለሀብቶች ጋር በአዲስ አበባ በመምከር ላይ ይገኛል።ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ፣ኦሮሚያ፣አማራ እና ትግራይ ክልሎች በመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛዎች ጥራት ዙሪያ ያካሄደውን ጥናት ዛሬ ይፋ አድርጓል።በዚህ ጥናት መሰረትም በሀገር አቀፍ ደረጃ ካሉ 550 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ውስጥ መስፈርቱን አሟልተው እየሰሩ ያሉት 40 በመቶዎቹ ያህሉ ብቻ ናቸው ተብሏል።

የተሽከርካሪ መመርመሪያ ማሽኖች ደረጃቸውን ያልጠበቁ ሆነው አገልግሎት የሚሰጡ እንዳሉ በጥናቱ ታውቋል።የመብራት ሲስተም የሚሰራ ተሽከርካሪ ያላቸው የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት 63 በመቶዎቹ ብቻ ናቸውም ተብሏል።ከ20 አመት በላይ በሆናቸው መኪኖች የሚያሰለጥኑ ተቋማትም እንዳሉ በግኝቱ ተረጋግጧል።የአሽከርካሪ ምርመራ ተቋማትን በተመለከተ የምርመራ ቦታ በመስፈርቱ መሰረት ያሟሉ ቁጥራቸው አነስተኛ ሲሆን ይህም የሚያሳየው ህጋዊ ሳይሆኑ ፍቃድ እያገኙ ነው።የማሽን እርማት (ካሊብሬሽን) የሚሰሩ አንድም የአሽከርካሪ ምርመራ ተቋማት የሉም ሲሉም ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ ከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ ላለማጓጓዝ የወሰነውን ውሳኔ ማሰረዙን የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር አስታወቀ።

ማህበሩ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባካሄደው ስብሰባ መንግስት እስከ ዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የትራንስፖርት ታሪፍ የማይሻሻል ከሆነ ተሽከርካሪዎቻችንን እናቆማለን ብሎ ነበር።ነገር ግን አሁን ባለው የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታና ከመንግስት አካላት ጋር ባደረግነው ስምምነት እስከ ጥቅምት 30 አስቀምጠነው የነበረውን ውሳኔ አንስተናል ሲሉ የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጸጋ አሳመረ ተናግረዋል፡፡ምንም እንኳን በኪሳራ ውስጥ ብንሆንም አገር የባሰ ጉዳት እንዳይደርስባት ስንል ስራችንን ለመቀጠል ፈቅደናል ብለዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ አዲስ የነዋሪዎች መታወቂያ መሰጠት ቆመ፡፡

ሸገር ከከተማዋ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ እንደሰማው አዲስ የነዋሪዎች የመታወቂያ ምዝገባ እና አሰጣጥ እንዲሁም የመሸኛ አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ መሰጠት ቆሟል፡፡

የኤጀንሲው የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ዳይክተሩ አቶ ዮናስ አለማየሁ እንዳሉት አዲስ የነዋሪነት መታወቂያና የመሸኛ መሰጠቱ ላልተወሰነ ጊዜ ቢቋረጥም እድሳትና ምትክ መስጠት ግን አልተቋረጠም ብለዋል፡፡

ኤጀንሲው መታወቂያ መስጠቱን ያቆመው ከወቅታዊው አገራዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ አዳዲስ መታወቂያዎች ተሰጥተው ለተለያዩ እኩይ ዓላማ መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ቁጥጥር ለማድረግ መሆኑን አቶ ዮናስ አለማየሁ ተናግረዋል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ በመልበስ ለስራ ጉዳይ በሚል ምክንያት ወደተለያዩ መኖሪያ ቤቶች እና ተቋማት የሚሄዱ ግለሰቦችን ማንነት መለየት እና ማረጋገጥ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ፡፡

በዚህ በኩል የሚጋጥሙ ችግሮችን ለመከላከል የከተማችው ነዋሪዎች የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ በመልበስ ለስራ ጉዳይ በሚል ምክንያት ወደተለያዩ መኖሪያ ቤቶች እና ተቋማት የሚሄዱ ግለሰቦችን ማንነት በትክክልም የፀጥታ አካል ስለመሆንና አለመሆናቸው የተቋማቸውን የስራ መታወቂያ ጠይቀው መለየት እና ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡

ፖሊስም ሆነ ሌሎች የፀጥታ አካላት የስራ መታወቂያ እንዲያሳዩ በተጠየቁ ጊዜ የማሳየት ግዴታ እንደተጣለባቸው ያስታወሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መታወቂያቸውን ለማሳየት ፈቃደኛ ያልሆኑ ሲያጋጥሙ በመጠራጠር መረጃና ጥቆማውን በየአቅራቢያቸው ለሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች በአካልም ሆነ በስልክ በማድረስ የከተማው ነዋሪዎች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

[Addis Ababa Police Commission]
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የኮሚኒኬሽን ቡድን ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለካፒታል ጋዜጣ እንደገለፁት አሁን በሀገሪቷ የተፈጠረው ሁኔታ ከጦርነት ይልቅ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ወንጀለኞችን ለፍርድ የማቅረብ ኦፕሬሽን ነው ብለዋል፡፡

ጎረቤት ሀገራትም የኢትዮጲያ መንግስት ሁኔታን በመረዳት ለመንግስት ድጋፍ እንደሚያደርጉ የገለፁት አምባሳደር ሬድዋን ጅቡቲ፣ ሱዳን እና ኤርትራ ከመንግሥት ጎን ቆመዋል፡፡በዚህም ኤርትራ ራሷን ወደ ጦርነት በማስገባት ተሳታፊ እንደማትሆን ገልፀው ነገር ግን ድንበር አልፈው ለሚመጡ ንፁሃን ዜጎችን እንደምትቀበል ገልፀዋል፡፡ በጅቡቲ በኩልም ማንኛወም የጦር ወንጀለኛ ወደ ጅቡቲ የሚያሸሹ ካለ ለኢትዮጲያ መንግስት ለማስረከብ ቃል በመግባት እየሰሩ ሲሆን በተጨማሪም ገቢ እና ወጪ እቃዎች ላይ ጉዳት እንዳደርስ ተገቢውን ጥበቃ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

ሱዳን በበኩሏ በትግራይ በኩል የሚያዋስናትን ድንበር ህገወጥ መሣሪዎችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ሲባል ድንበሯን ዘግታለች፡፡በተጨማሪም አምባሳደር ሬድዋን መንግሥት ባለፉት ጊዜያት ወደ ውይይት በመምጣት ነገሮችን ለማረጋጋት ሙከራዎችን ቢያደርግም ውጤት አላመጣም ሲሉ ከአሁን በኋላ ግን በውይይት ለመፍታት አንደማይሰራ ይግልፃሉ ይልቁንስ አሁን የተፈጠረው ሁኔታ ሀገርን መካድ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያልታሰበ ጥቃት በማድረስ ጉዳት ማስከተልና መሳሪያዎችንም መንጠቅ ሲሆን ቡድኑን ወደ ህግ በማምጣት ህገ መንግሥቱን ማስከበር እስካልተቻለ ድረስ በእጁ የገቡትን መሣሪያዎች ማጥፋት እስካልተቻለ ድረስ ለሀገር ህልውና አስጊ ነው ይላሉ፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል ጥቃቶችን ለመሰንዘር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 16 የታጠቁ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ክልሉ አስታወቀ።

የአፋር ክልሉ ሰላምና ደህንነት ሃላፊ አቶ ኢብራሂም ኡመድ እንዳሉት በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ከነ ትጥቃቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።እነዚህ የታጠቁ ሃይሎች በሰመራ-ሎጊያ መውጫ 6፣በአፋር እና ራያ በኩል ባለው ቦታዎች ላይ 8 እንዲሁም በአፋር ዞን አራት እና አንድ ላይ ሁለት በድምሩ 16 ታጣቂዎች ከነ ትጥቃቸው በአፋር የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል።እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በአርብቶ አደሮች ጥቆማ እና እገዛ እንደሆነም ሃላፊው ተናግረዋል።

"ተጠርጣሪዎቹ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ፣ከባድ መሳሪያ የታጠቁ እና ትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ናቸው" ያሉት ሃላፊው ተልዕኮ ተሰጥቷቸው በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ መያዛቸውን ተናግረዋል።ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ ሌሊት ስድስት ሰዓት ላይ 6 አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪዎች ተከታትለው ወደ ትግራይ ለመሄድ ሲሞክሩ በጸጥታ ሃይሉ በቁጥጥር ስር ውለው ምን እንደጫኑ እና ማን እንዳሰማራቸው ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም ሃላፊው ተናግረዋል።የአፋር አርብቶ አደሮች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በንቃት የክልሉን ደህንነት በመጠበቅ ላይ መሆናቸውንም አቶ ኢብራሂም ገልጸዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በትናትናው ዕለት የኢትዮጵያ ተዋጊ አውሮፕላን በትግራይ ተመቶ ወድቋል በሚል የተሰራጨው ዘገባ ከእውነት የራቀ ነው ሲል የኢፌዲሪ የአገር መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ አስታወቁ።

'በከሀዲው የህወሓት ቡድን' ላይ ህግ የማስከበር እርምጃ እየወሰደ ያለው የአገር መከላከያ ሰራዊት በትግራይ የተመረጡ ቦታዎች ላይ የአየር ድብድባ እየፈጸመ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚህ ግዳጅ የተላኩ ተዋጊ አውሮፕላኖች እሥካሁን ያጋጠማቸው ችግር እንደሌለ አስታውቀዋል።

በ'ከሀዲው ቡድን' ተዋጊ ጀት መተን ጥለናል በሚል የሀሰት ፕሮፓጋንዳ መሰራጨቱን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የዚህ ቡድን መረጃ አስቀድሞ ይናገር የነበረውን አደረኩ ለማለት ብቻ ያሰራጨው የሀሰት ዘገባ ነው ብለዋል።

ህብረተሰቡ ከዚህ ቡድን ከሚወጡ የሀሰት መረጃዎች እንዲጠበቅ ያሳሰቡት ዋና ዳይሬክተሩ፤ 'ከሀዲው ቡድን' ተዋጊ አውሮፕላን መቶ ጥሎ ከሆነ የቪዲዮ መረጃ መልቀቅ ይችላል ብለዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በንጹኃን ዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲያደርሱ ከነበሩት ውስጥ 16 ሽፍቶች ተደምስሰዋል ተባለ፡፡

ሽፍቶቹ የተደመሰሱት በአካባቢው ዘላቂ ሠላምን ለማምጣት እየሠሩ የሚገኙት የሀገር መከላከያ፣ የፌዴራል ፖለስ እና የክልሉ የጸጥታ ኃይል በወሰዱት እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።በመተከል ዞን በተለይም የሕወኃትን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብሎ በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት እያደረሰ የሚገኘውን የጸረ-ሠላም ኃይል ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ እና አካባቢውን ወደ ዘላቂ ሠላም ለመመለስ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት መርሃ ግብር:

ማክሰኞ ሕዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፡-
• በወርቁ ሰፈር፣ በደራርቱ ት/ቤት፣ በአየር ኃይል ካንፕ፣ በመንገድ ትራንስፖርት እና አካባቢዎቻቸው፣

በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡30 ድረስ፡-
• በመነን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒዓለም ቤተ-ክርስተያን፣ በላዛሪስት፣ በሀምሌ 19 መናፈሻ፣ በፈረንሳይ ኤምባሲ፣ በጉራራ፣ በፊልም ማዕከል፣ በራስ ካሳ ክሊኒክ፣ በአቦ ቤተ-ክርስተያን፣ በእንጦጦ ኪዳነምህረት ቤተ-ክርስተያን፣ በጎሮ፣ በሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ፣ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ፣ በሰሚት ኪዳነምህረት ቤተ-ክርስተያን እና አካባቢዎቻቸው፤

ረቡዕ ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 7፡30 ድረስ፡-
• በመነን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒያለም ቤተ-ክርስተያን፣ በላዛሪስት፣ በሀምሌ 19 መናፈሻ፣ በፈረንሳይ ኤምባሲ፣ በጉራራ፣ ፊልም ማዕከል፣ በራስ ካሳ ክሊኒክ፣ በአቦ ቤተ-ክርስተያን፣ በእንጦጦ ኪዳነምህረት ቤተ-ክርስተያን፣ በኦሎፒያ፣ በፍላሚንጎ፣ በደንበል፣ በኦሮሚያ ቢሮ፣ በሰንሻይን ጀርባ እና አካባቢዎቻቸው፤

በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ፡-
• በጎሮ፣ በሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ፣ በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ፣ በሰሚት ኪዳነምህረት ቤተ-ክርስተያን፣ እና አካባቢዎቻቸው፤

በተጨማሪም ሐሙሰ ህዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ፡-
• በቦሌ ሚካዔል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማህበር እና አካባቢዎቻቸው፤

በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ9፡30 ድረስ፡-
• በቀጨኔ 8 ቁጥር ማዞርያ፣ በአመሃ ደስታ ት/ቤት፣ በመቀጠያ፣ በታቦት ማደርያ፣ በገርጂ ዩኒቲ ኮሌጅ፣ በቦሌ ሆምስ፣ በቦሌ ሲቪል አቬሽን፣ በጎሮ አለማየው ህንፃ፣ በጃክሮስ፣ በቦሌ መድሀኒያለም ቤተ-ክርስተያን፣ በአያት ሆስፒታል፣ በብራስ ሆስፒታል፣ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ በቦሌ ሚኒ፣ በቼራሊያ ፋብሪካ፣ በገነት መናፈሻ ኮንደሚኒየም፣ በማሩ ብረታ ብረት፣ በወህይኒ ቤት ጀርባ፣ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እና አካባቢዎቻቸው፤

በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ፡፡

[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]
@YeneTube @FikerAssefa
አሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ከቀረጥ ነፃ የሆኑ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ጠየቁ!

አሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ለስልጠና የሚጠቀሙበትን እና ከጊዜው ጋር አብረው ሊሄዱ የሚችሉ ከቀረጥ ነፃ የሆነ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም እንደ ሲሙሌተር ያሉ የማሰልጠኛ ግብአቶች የሚያገኙበት እድል እንዲመቻችላቸው ጠየቁ።የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከዘርፉ አመራሮች ፣ከአሽከርካሪ ማሰልጠኛና ከተሽከርካሪ ተቋማት ባለቤቶች ጋር በካፒታል ሆቴል በመከረበት ወቅት ነው ይህን የጠቁት።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለማጓጓዝ ከዓለም አቀፍ መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች ጋር በመምከር ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኮሮና ቫይረስ ክትባት ተመርቶ ወደ ገበያ መግባት ያልጀመረ ቢሆንም ምርቱ ሲጠናቀቅ ለመላው አለም በጥንቃቄ እና በፍጥነት ለማጓጓዝ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡የአየር መንገዱ አለም አቀፍ በረራ አገልግሎት ዳሬክተር አቶ ለማ ያደቻ እንደተናገሩት ሀገራት የኮቪድ-19 ክትባትን በስፋት ለማምረት ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ገልፀው ክትባቱ በሚደርስበት ወቅት ደግሞ ለመላው የአለም ሀገራት ማከፋፈል የራሱ የሆነ ጫና ይፈጥራል፡፡ይህንን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ክትባቱን በስፋት ወደ ማምረት ሲገባ ጥንቃቄ በተሞላበትና በተቀላጠፈ ሁኔታ ለአለም ሀገራት ለማሰራጨት በቂ ዝግጅት አድርገናል ብለዋል፡፡

አለምን ከኮቪድ ለመታደግ የሚሰራውን ክትባት ለማጓጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተመራጭ በመሆን አለምን እንደሚታደግ ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉም ተናግረዋል፡፡አየር መንገዱ እስካሁን ለሙከራ እየተመረቱ የሚገኙትን ክትባቶች ከተለያዩ ሀገራት እያጓጓዘ ሲሆን ወደ ትልቅ ስምምነት ያልተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡የኮቪድ-19 ክትባት ማጓጓዝን በተመለከተ አለም ላይ ካሉ ትልልቅ የካርጎ አንቀሳቃሾች ጋር በጋራ እየሰራን ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከእነርሱ ጋር የጠበቀ የስራ ውል እንዳለውም አብራርተዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ ስታንዳርድ ኤዲተር የሆነው መድሃኔ እቁባሚካኤል ቅዳሜ ዕለት በፖሊስ መወሰዱን ሚዲያው አስታወቀ!

ጋዜጠኛው ከትናንት ብስቲያ ከቤቱ ተይዞ የታሰረ ሲሆን በወቅቱ ወዴት እንደተወሰደ አይታወቅም ነበር፣ መድሃኔ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ፖሊስ "ህገመንግስቱን በሃይል ለመናድ መስራት" በሚል እንደከሰሰውና ፖሊስ አስፈላጊውን ማጣራት እንዲያደርግ 14 ቀን እንደተሰጠው ተሰምቷል።ጋዜጠኛው በአሁኑ ሰዓት ፒያሳ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ እጅ እንደሚገኝ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ለአስር አመታት ግድም በሙከራ ደረጃ የነበረው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

በተለያየ አጋጣሚ በአዋጅ ይደነገጋል ተብሎ የቆየው እና መላውን የህብረተሰብ ክፍል በመድን ሽፋን የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችለው ህግ እስከ ባለፈው ሳምንት ለፓርላማ ሰይቀርብ ቆይቷል፡፡ሆኖም በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በ771 ወረዳዎች በሙከራ የቆየው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን በህግ ከተደነገገ ሁሉም ዜጋ ሽፋን ማግኘት የሚያስችለው ይሆናል፡፡በስርአቱም ሰፊ ሃብት ሊሰበሰብ ስለሚችል በመሰረተ ልማት እና አገልግሎት ጥራት ከፍተኛ እድል እንደሚፈጠር ረቂቅ አዋጁን በመደገፍ የቀረበው የማብራሪያ ሰነድ ይገልፃል፡፡በአዋጁ መሰረትም የመድን ፈንድ ይቋቋማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ጥንቃቄ ለአዲስ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ፈላጊ ደንበኞች!

በአንዳንድ አካባቢዎች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሠራተኛ መስለው የኤሌክትሪክ ቆጣሪ እናስገባለን በማለት በህገወጥ መንገድ ከህብረተሰቡ ገንዘብ የሚቀበሉ ግለሰቦች እንዳሉ መረጃዎች ከህብረተሰቡ ደርሰውናል፡፡

በመሆኑም አንዳንድ ደንበኞች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ እንደነዚህ ዓይነትና መሰል ህገወጥ ድርጊቶች የሚያከናውኑ ግለሰቦች መጠቀሚያ ከመሆን እራሳቸውን እንዲጠብቁ እና መሠል ተግባራት በሚያጋጥማቸው ወቅትም በትክክል የተቋሙ ሠራተኞች መሆናቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ወይም የስራ ትእዛዝ ደብዳቤ መያዛቸውን ማረጋገጥ ይገባቸዋል፡፡

አዲስ የደንበኝነት ጥያቄን ጨምሮ ሌሎች ማንኛውም የኤሌክትሪክ አገልግሎቶች ሲፈልጉ በአቅራቢያዎ ወደሚገኘው አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ የተቋሙ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በመከተል አገልግሎቱን ማግኝት መብታቸው ነው፡፡

እንዲሁም ማናቸውንም የተቋሙን አገልግሎት ለማግኘት ለሚከፍሉት ገንዘብ ተቋሙ ያዘጋጀውን ህጋዊ የገንዘብ መሠብሰቢያ ደረሰኝ መቀበል ይገባዎታል::የሚያጠራጥር ሁኔታ ካለ በተቋሙ 905 ነፃ የጥሪ ማዕከል በመደወል ወይም በአቅራቢ ከሚገኝ የተቋሙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመሄድ ጥቆማ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተቋሙ ያሳስባል፡፡

[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል እንዳሻው ጣሰው ወደ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግለት ተመደቡ።

ኮሚሽነር ጄነራሉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በቆዩበት ወቅት በቁርጠኝነት በሰጡት አመራር ኮሚሽኑን ለመቀየር ባደረጉት ጥረት በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ ፖሊስ እንዲፈጠር ሪፎርሙን በመምራት በአጭር ጊዜ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን መስራታቸው በየደረጃው ያሉ የኮሚሽኑ አመራሮች በሰጡት አስተያየት ተናገረዋል።ኮሚሽነሩም የተሰጡትን አስተያየቶች ተቀብለው በሪፎርሙ ያልተጠናቀቁ ስራዎች ነቅሰው በማውጣት በምትካቸው ለተሾሙት ኮሚሽነር ጀኔራል እንደሚያስረክቡና በጅምር ላይ ያሉ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ባሉበት መስሪያ ቤት ሆነው እገዛ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

[ፌደራል ፖሊስ]
@YeneTube @FikerAssefa