YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዐቢይ አህመድ የኢጋድን ‘የእናሸማግላችሁ’ ጥያቄ ሳይቀበሉ ቀሩ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የቀረበውን የሽምግልና ጥሪ ሳይቀበሉ ቀሩ፡፡የቀጣናዊው ተቋም መሪ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በ4 የተለያዩ ጊዜያት ስልክ በመደወል የኢትዮጵያ አቻቸውን ለማግባባት ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ሱዳን ትሪቢውን የሃምዶክን ቢሮ አጣቅሶ የዘገበውን ሂቃያት ጋዜጣን ዋቢ አድርጎ በድረ ገጹ እንዳሰፈረው ዘገባ ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉዳዩ ዓለም አቀፋዊ መልክ ሊይዝ የማይገባው የሃገር ውስጥ ጉዳይ ነው፡፡

ሃምዶክ ባለፈው ዓመት የኢጋድ ሊቀመንበር ሆነው ዐቢይ አህመድን መተካታቸው ይታወሳል፡፡“የህወሀት ጁንታ ቡድን ትላንት የቀረቡለትን የድርድር እና የውይይት እድሎች ሁሉ አምክኖ ግብአተ መሬቱ ሊፈጸም ሲቃረብ የአደራዳሪ ያለ ብሎ መጮህ ጀምሯል” ሲል መግለጫ ያወጣው ብልጽግና ፓርቲ “አሁን ሰአቱ የድርድር ሳይሆን የፍርድ ሆኗል” ብሏል፡፡“ትዕግስት ሊቀይረው ያልቻለው ጁንታ”ያለውን ህወሓትን “በህግ አግባብ ተጠያቂ ማድረግ ግዴታ የሆነበት ሰአት ላይ” እንደደረሰም ነው የገለጸው፡፡

“የተጀመረው ጉዞ ጦርነት ሳይሆን የህግ ማስከበር ስርአት ነው” ያለም ሲሆን “በአጭር ጊዜ ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ በማቅረብ” እንደሚጠናቀቅም አስታውቋል፡፡ብልጽግና ህወሓት ድርድን እናስቀድም የማለቱ ዋና ዓላማ “ሰላምን ማውረድ ሳይሆን በድርድር ምክንያት ጊዜን መግዛት ነው” ሲል ትናንት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡“ኢትዮጵያ ወደ ትርምስ ትገባለች የሚለው ስጋት የሃገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ካለመረዳት የመነጨ ነው” ሲሉ በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “አሁን እየተካሄደ ያለው ህግ የማስከበር ስራ ሰላምንና መረጋጋትን በማስፈን ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ ያለመ ነው ይህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል” ሲሉ መልዕክት ማስፈራቸውም አይዘነጋም፡፡

Via Al ain
@YeneTube @FikerAssefa
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በታጣቂዎች ታግተው ከነበሩ የጤና ባለሙያዎች ውስጥ ስምንቱ ተለቀቁ።

የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ በየነ እንደተናገሩት በክልሉ ዳንጉር ወረዳ ጉብላክ ቀበሌ ባሳለፍነው እሁድ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም 5 ወንድ 7 ሴት 1 አሽከርካሪ እና 1 መካኒክ በድምሩ 14 ሰዎች በታጣቂዎች ታግተው ነበር።በታጣቂዎቹ ታግተው ከነበሩት የጤና ባለሙያዎች መካከል ስምንቱ ተለቀዋል ተብሏል።

ባለሙያዎቹ የተለቀቁት የአገር መከላከያ ሰራዊት በአጋቾቹ ላይ ባደረገው እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።ከተለቀቁት ውስጥ አንደኛዋ የጤና ባለሙያ እንደተናገረችው የተቀሩት ታጋቾች ከመከላከያ ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ አምልጠው ጫካ ገብተው ነው እንጂ በጸረ ሰላም ሀይሉ አልተያዙም ብላለች።አቶ መለስ ግን ይሄንን እርግጠኛ ልንሆን ስለማንችል ወደ ቦታው መከላከያ ሚሊሻና ፌደራል ፖሊስ በመላክ እየተፈለጉ ነው ብለዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ አማጺ ሃይል እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በተቀሰቀሰው ውጊያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱ ሮይተርስ የመንግሥት ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ባካባቢው ያሉ ዘጋቢዎቼ፣ በጭነት መኪናዎች የተጫኑ የተጫኑ በርካታ ሚሊሽያዎች እና መትረጊሶች የተጠመዱባቸው ፒካፕ ተሸከርካሪዎች ወደ ውጊያው ግንባር ሲጓዙ ተመልክተዋል ብሏል ሮተርስ፡፡ በትግራይ እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ ድንበር ቅራቅር በተባለ ቦታ በተደረገ ውጊያ 500 ያህል የትግራይ ታጣቂዎች እንደተገደሉ ካንድ የአማራ ክልል ወታደራዊ ሃላፊ መስማቱንም ገልጧል፡፡ በምዕራብ ትግራይ ዳንሻ አካባቢ በተደረገው የመጀመሪያው ውጊያ፣ ከመንግሥት ወገን በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች እንደሞቱ መስማቱንም ዘግቧል፡፡

[Reuters/Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የአዲስ ስታንዳርድ ኤዲተር የሆነው መድሃኔ እቁባሚካኤል ቅዳሜ ዕለት በፖሊስ መወሰዱን ሚዲያው አስታወቀ! ጋዜጠኛው ከትናንት ብስቲያ ከቤቱ ተይዞ የታሰረ ሲሆን በወቅቱ ወዴት እንደተወሰደ አይታወቅም ነበር፣ መድሃኔ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ፖሊስ "ህገመንግስቱን በሃይል ለመናድ መስራት" በሚል እንደከሰሰውና ፖሊስ አስፈላጊውን ማጣራት እንዲያደርግ 14 ቀን እንደተሰጠው ተሰምቷል።ጋዜጠኛው በአሁኑ ሰዓት…
ትናንት በስቲያ በፖሊስ የታሰረው የአዲስ ስታንዳርድ መጽሄት አዘጋጅ መድኀኔ ዕቁባሚካዔል ዛሬ እንደተለቀቀ መጽሄቱ አስታውቋል፡፡ፖሊስ መድኀኔን ያሰረው፣ ሕገ መንግሥቱን በማፍረስ ወንጀል ጠርጠሬዋለሁ በማለት ነበር፡፡ ፖለስ ጋዜጠኛውን ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቦ የ14 ቀናት ምርመራ ጊዜ እንደተፈቀደለት መጽሄቱ ቀደም ሲል ዘግቦ ነበር፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 307 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 3,889 የላብራቶሪ ምርመራ 307 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ7 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,530 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 944 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 60,710 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 99,982 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በሞዛምቢክ ጽንፈኛ ኢስላማዊ ታጣቂዎች በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ከ50 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን 'አንገት መቅላታቸውን' የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ።

ታጣቂዎቹ በአንዲት መንደር የሚገኝ የእግር ኳስ ሜዳ ውስጥ ሰዎቹን የገደሉ ሲሆን ሟቾቹ እጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን የሚጠቁሙ ሌሎች ሪፖርቶችም እየወጡ ይገኛሉ።በሌላ መንደር ደግሞ በተመሳሳይ የበርካታ ሰዎች አንገት እንደተቀላ መገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሀገር መከላከያ ሰራዊት "ዘራፊው የህውሓት ቡድን ከጠላት ጋር ጥምረት በመፍጠር ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት ነበር" ያለውን የሁመራ ኤርፖርት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ገለፀ።

በርካታ ህውሓት ያደራጃቸው የልዩ ኃይል፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን እየሰጡ ነውም ብሏል የመሃል ሀገር መገናኛ ብዙሃን።

ሰራዊቱ "የህውሓት ቡድን ያደረሰበትን ድንገተኛ ጥቃት በመመከት የመልሶ ማጥቃት ስራ እየሰራ ነው" የተባለ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ከዳንሻ ጀምሮ በርካታ ቦታዎችን እየተቆጣጠረ ነውም ተብሏል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተመረተ ያለው ሲሚንቶ መጠን ከባለፈው ወራት ጋር ሲነጻጸር ከ 17 በመቶ በላይ መጨመሩን የኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ግብአቶች ኢንዱስትሪ ልማት ተቋም ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

በተቋሙ የሲሚንቶ እና ተዛማጅ የኢንዱስትሪ ልማት ምርምርና ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር ስመኝ ደጉ እንደተናገሩት በመስከረም ወር ከስድስት መቶ ሺሕ ቶን ሲሚንቶ የተመረተ ሲሆን በጥቅምት ወር ግን ሰባት መቶ ሺሕ ቶን ምርት መመረቱን እና ምርቱ መጨመሩ አገራችን ያለባትን የሲሚንቶ እጥረት ከማስቀረት አንፃር ትልቅ ለውጥ ያመጣል ሲሉ ተናግረዋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
አማራ ባንክ መሥራች ጉባዔውን በውክልና ሊያካሂድ ነው!

በምሥረታ ላይ የሚገኘው አማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር፣ የምሥረታ ጉባዔውን በውክልና ለማካሄድ መወሰኑን፣ እንዲሁም ባለአክሲዮኖች ለ34 አደራጆች ውክልና እንዲሰጡ ጠየቀ፡፡የባንኩ አደራጅ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፈንታ ሐሙስ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ ቁጥራቸው ከ155 ሺሕ በላይ የደረሰው ባለአክሲዮኖችን በአንዴ ለመሰብሰብ ስለማይቻል፣ የምሥረታ ጠቅላላ ጉባዔን በውክልና እንዲያካሄድ መወሰናቸውን ገልጸዋል፡፡ለዚህም አስፈላጊ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን አስታውቀዋል፡፡

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
እስራኤል የአንበጣ ተከላካይ ግብረ ሀይሏን ወደ ኢትዮጵያ ላከች።

የበረሀ አንበጣን ለመከላከል የሚያግዝ ግብረ ሀይል እስራኤል ወደ ኢትዮጵያ መላኳን በኢትዮጵያ የእስራኤል ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።ከጥቂት ወራት ጀምሮ ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የአንበጣ መንጋን እየተጋፈጠች እንደሆነ ይታወቃል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋቢ አሽካንዚ ግብረ ሀይሉ እንዲመጣ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

የእስራኤል ኤምባሲም ተልዕኮውን በመምራት ከኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይሰራል።ግብረ ሀይሉ 2 ቶን የሚመዝን የአንበጣ መከላከያ መሳሪያ ያመጣ ሲሆን በ2 ሳምንት ውስጥም ስራውን ለማጠናቀቅ አቅዷል።ከ200 በላይ የአንበጣ መከላከያ ላይ የሚሰሩ ሀገር በቀል ተቋማትም ስልጠና እንደሚሰጣቸው ታውቋል።ይሄ ተልዕኮ የሁለቱን ሀገራት ረዘም ያለ መልካም ግንኙነት ያሳያልም ተብሏል

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
"የሶስቱ ቀናት ፈታኝ ተጋድሎ በጀኔራሉ አንደበት!"

ዳንሻ ከተማ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ አምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር ካምፕ ጊቢ ውስጥ የመከላከያ መኪናዎች በጥይት ተበሳስተው ይታያሉ፡፡መስታወታቸው ረግፏል፤ዛፎቹም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፤ መጥረቢያ እንጂ የጥይት ውርጅብኝ የቆረጣቸው አይመስሉም።የግንብና ቆርቆሮ ቤቶች እንደ ወንፊት ተበሳስተዋል፡፡የጥይቶች ቀላሃ እንደ ጠጠር ተብትኗል፡፡

ዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2013ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት አካባቢ በዳንሻ ከተማ ያልተጠበቀ፣አሳዛኝ፣አስደጋጭ ድርጊት ነው የተፈጸመው፡፡በከተማዋ የሚገኘው የሰሜን ዕዝ የአምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር የተደገሰለትን ጥቃት አያውቅም።በመካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ስታፍ ውስጥ የሚሰሩት መደበኛ ስራቸውን ከውነው እንቅልፍ ላይ ናቸው፡፡

የሰሜን ዕዝ የአምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቆይታ፣

👇👇
https://telegra.ph/Brigadier-Gen-Mulalem-11-10
በአዲስ አበብ ከ700 ሺህ በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች የዲጅታል መታወቂያ ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ።

እስካሁንም ለ140 ሺ የከተማዋ ነዋሪዎች ይህ ዲጂታል መታወቂያ መሰጠቱን የከተማዋ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታውቋል።የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነትና ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር ዶክተር ታከለ ነጫ እንዳሉት ይህንን ዲጅታል የነዋሪዎች መታወቂያ በ96 ወረዳዎች ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።ኤጀንሲው ባለፉት ሶስት ወራት ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብንም አስታውቋል።

አሰራሩን ለማዘመን የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ፣የፎርጅድ ሰነዶች መበራከት፣እንዲሁም በየወረዳው ያሉ አንዳንድ የኤጀንሲው ሰራተኞች ህገ ወጥ ተግባር ላይ መሳተፍ ለወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገልግሎቱ እንቅፋት መሆኑ ተነግሯል ።

በተጨማሪም በከተማዋ በአንድ ሰው መኖሪያ ቤት ከ50 ሰው በላይ የነዋሪነት መታወቂያ እንደሚወጣም ተነግሯል።በከተማዋ የሚገኙ አንዳንድ ነዋሪዎች በየመኖሪያ ቤታቸው ያሻቸውን መታወቂያ ያለ ገደብ በማሶጣት የነዋሪነት መታወቂያውን የገቢ ምንጭ ማድረጋቸውም ተሰምቷል።የነዋሪነት መታወቂያውን ከ 2 ሺ ብር ጀምሮ እስከ 7 ሺ ብር ድረስ በህገ ወጥ መንገድ ሲሰጡ የነበሩ ግለሰቦች መያዛቸውንም ዶክተር ታከለ ተናግረዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በፋግታ ለኮማ ውረዳ በሉሊስታ ቀበሌ በደርሰዉ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰዉ ሂወት አለፈ፡፡

የፋግታ ለኮማ ውረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ላለም ጥላሁን እንደገለፁት በቀን 1/3/2013 ዓ/ም ከጥዋቱ 1፡00 አካባቢ መነሻዉን ኮሶበር ያደረገ ኮድ 3 ሰሌዳ ቁጥር 20763 ሀይሩፍ ተሽከርካሪ መነሻዉን ባህርዳር ካደረገ ኮድ 3 ሰሌዳ ቁጥር 18266 አባዱላ ተሸከርካሪ በተፈጠረ ግጭት የአንድ ሰዉ ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ የዘጠኝ ሰዎች ከባድና ቀላል ያካል ጉዳት ደርሶባቸዉ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝ ኃላፊዉ አስረድተዋል ፡፡የአደጋዉ መንስኤም ከልክ በላይ ማሽከርከር እንደሆነ ገልፀዋል ።

ምንጭ: ፋግታ ኮሙዩኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
የአለም የምግብ ድርጅት በምስራቅ አፍሪካ ሁለተኛ የአንበጣ ወረርሺኝ ሊከሰት እንደሚችል አስጠነቀቀ!

የአለም የምግብ ድርጅት በቅርቡ ከነበረው ከፍተኛ ዝናብ የተነሳ የበረሀ አንበጣ በከባቢው በድጋሚ መራባቱን ተከትሎ ሁለተኛ ዙር የበረሀ አንበጣ ወረርሺኝ በምስራቅ አፍሪካ ሊከሰት እንደሚችል በትላንትናው እለት በትዊተር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት አስጠነቀቀ።

ድርጅቱ አክሎም በቀጠናው የሚገኙ አገራት ካለፉት ጊዜያት ይልቅ ወረርሺኙንና ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል የተሻለ አቅም አላቸው ያለ ሲሆን ይህም የበረሀ አንበጣ በቀጠናው ከሰኔ 2011 ዓ.ም አንስቶ ከተከሰተ ወዲህ የቀጠናው አገራት ከድርጅቱ ጋር በቅርበት በመስራታቸው እንደሆነ ድርጅቱ ተናግሯል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ በምስራቅ አፍሪካ በሚገኙ አገራት የተከሰተውን የበረሀ አንበጣ ወረርሺኝ ለመከላከል ከአገራቱ መንግስታት ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ ያስታወሰው ድርጅቱ አክሎም ከላይ የተጠቀሰውን መደምደምያ ላይ ለመድረስ ከየአገራቱ በየወቅቱ የሚላኩ የቁጥር መረጃዎችን እንደተመለከተ ገልጿል።

የበረሀ አንበጣ ወረርሺኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ወዲህ በአገሪቱ የምግብ ዋስትና ላይ ትልቅ ጫና በመፍጠር ላይ የሚገኝ ሲሆን የአለም የምግብ ድርጅት ባሳለፍነው ሰኞ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ወረርሺኙ በምስራቅ አማራ፣ ትግራይና አፋር ክልሎች የመረጋጋት ሁኔታ እንደሚታይበት መግለፁ ይታወሳል።

ድርጅቱ በሪፖርቱ አክሎም በአንፃሩ በድሬዳዋና በጅጅጋ አካባቢዎች አሁንም ሙሉ በሙሉ ያላደገ የበረሀ አንበጣ መንጋ (Immature Swarms of Desert Locusts) እንደሚገኝ ገልጿል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
ወትሮም የመጠጥ ውሃ ችግር የነበረባት የመቀለ ከተማ አሁን ችግሩ በርትቷል።

ከዚህ ቀደም በተንቀሳቃሽ ቦቴ መኪናዎች እና በሌሎች ዘዴዎች ውሃ ያገኙ የነበሩ ነዋሪዎቸ አሁን ላይ የግንኙት መስመሮች በመቋረጣቸው ውሃ ለማግኘት መቸገራቸው ይናገራሉ።በመቀለ ከተማ በስልክ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ውሃ ያቀርቡ የነበሩ ድርጅቶች አሉ።በአሁኑ ወቅት ግን የስልክ ግንኙነት ባለመኖሩ ውሃ በትዕዛዝ ማግኘት ከባድ ነው ሲል ሪፖርተራችን ይናገራል።

በሳምንት አንድ ጊዜ ትመጣ የነበረው የቧንቧ ውሃ ሳትመጣ መቅረቷ ችግሩን አባብሶታል ይላል ሪፖርተራችን።በመቀለ ከተማ በተለያዩ ስፍራዎች ውሃ ማከፋፈያ ስፍራዎች አሉ። ከእነዚህ ማከፋፈያ ስፍራዎች በአሌክትሪክ ኃይል ተስበው በውሃ መጫኛ ቦቴዎች ነበር የሚጓጓዙት።በአሁኑ ወቅት የአሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ የውሃ እደላ የማካሄድ ሥራውን ከባድ ማድረጉን የቢቢሲ ጋዜጠኛ ይናገራል።

በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይል መካከል ግጭት ከተከሰተ ዛሬ 7ኛ ቀኑን አስቆጥሯል።ሕይወት በጦርነት ቀጣና ውስጥ በምትገኘው መቀለ ከባድ ሆኗል። የቢቢሲ ዘገቢ በመቀለ እና አከባቢዋ ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት መኖሩን እንዲሁም የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ተናግሯል።ባንኮችም እንዲዘጉ መደረጉ ነዋሪዎች ሕይወት እንዲከብዳቸው ሌላው ምክንያት ሆኗል ይላል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ
👇👇👇
https://bbc.in/3khQwNC

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ አዲስ የነዋሪዎች መታወቂያ መሰጠት ቆመ፡፡ ሸገር ከከተማዋ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ እንደሰማው አዲስ የነዋሪዎች የመታወቂያ ምዝገባ እና አሰጣጥ እንዲሁም የመሸኛ አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ መሰጠት ቆሟል፡፡ የኤጀንሲው የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ዳይክተሩ አቶ ዮናስ አለማየሁ እንዳሉት አዲስ የነዋሪነት መታወቂያና የመሸኛ መሰጠቱ ላልተወሰነ ጊዜ ቢቋረጥም እድሳትና ምትክ…
አስቸኳይ ጉዞ ላላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መታወቂያ እንደሚሰጥ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ አዲስ መታወቂያ ማውጣት፣ማደስ እና መሸኛ መስጠት መታገዱ ይታወሳል።ይህ እገዳ የሚቀጥለው አሁን ያለው ሃገራዊ ሁኔታ እስኪረጋጋ ድረስ ብቻ ይሆናል ተብሏል።በቀጣይ የተሻለ መፍትሄ እስኪገኝ ደረስ አሁን ባለው ሁኔታ እንደሚቀጥል የከተማዋ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታውቋል።ይሁንና ለአስቸኳይ ሁኔታ እንደ ህክምና፣ የውጪ ሃገር ጉዞ፣ለትምህርት እና መሰል ሁኔታዎች ላላቸው እና ለነዚህ ማስረጃ ማቅረብ ለሚችሉ ዜጎች አገልግሎቱ ይሰጣል ተብሏል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በጉጂ ዞን የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ!

በጉጂ ዞን ባለፉት ሁለት ሳምንታት የጸጥታ አካላት ከህዝቡ ጋር በመተባበር የጽንፈኛው ህወሃት ተላላኪ የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል፡፡በተወሰደው እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተገድለዋል፣ 13 በቁጥጥር ስር ውለዋል፣ ከ17 በላይ የሚሆኑ ደግሞ መቁሰላቸው የጉጂ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ኡዶ ገልጸዋል፡፡

የጸጥታ ኃይሎች በጉጂ ዞን ወረዳዎችና ከተሞች በተለያዩ ቦታዎች ባደረጉት ልዩ ፍተሻ በዞኑ የሽብር ተግባራትን ለመፈጸም ከጽንፈኛው ህወሃት ተልዕኮ ወስደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 3 ግለሰቦች ከ100 ሺህ ብር ጋር በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የጉጂ ዞን የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወልዴ ዱጎ መግለጻቸውን የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በትግራይ ክልል ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ፡፡

የፌደራሉ እና የክልሉ መንግሥት ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ወደ ንግግር እንዲመለሱ ሊቀመንበሩ ሙሳ ፋኪ ማህማት ጠይቀዋል፡፡ግጭቱን ለመፍታት የሚደረግን ማንኛውም ጥረት ለማገዝ የአፍሪካ ኅብረት ዝግጁ መሆኑን ሊቀመንበሩ በመግለጫቸው ገልጸዋል፡፡ኢትዮጵያ ወደ የዕርስ በዕርስ ግጭት እንዳታመራ ኅብረቱ ጣልቃ እንዲገባ የክልሉ ገዢ ፓርቲ ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ባለፈው እሁድ ጥሪ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እየተወሰደ ያለው ሕግን የማስከበር እርምጃ ሕገ ወጡ ቡድን ትጥቁን ሲፈታ፣ ለሕግ ሲቀርብና በክልሉ ሕጋዊ አስተዳዳር ሲቋቋም ያበቃል ብለዋል፡፡በትግራይ እየተካሄደ ያለው ጦርነቱ ከተጀመረ ዛሬ 7ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፤ መከላከያ ሠራዊት የሁመራ ኤርፖርትን በቁጥጥሩ ስር ማዋሉን አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትና ትግራይ ክልል መንግስት መካከል እየተካሄደ በሚገኝ ጦርነት በቀጥታ መሳተፍ ጀመረ ሲሉ የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ዶ/ር ደብረፅዮን ተናገሩ።በዚህም ጦርነቱ "ወደ ተለየ ምዕራፍ ተሸጋግሯል" ብለዋል።

Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa
ወቅታዊ የሀገሪቱን ሁኔታ ምክንያት በማድረግ ያለ ህጋዊ ደረሰኝ እና ያለ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ሲነግዱ ፣የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ፣ ህገ-ወጥ የምርት ያከማቹ እና የደበቁ በጠቅላላው የተለያዩ የንግድ ህግ ጥሰት በፈፀሙ 159 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa