YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ማብራሪያ ሰጠ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርምሮ ማጽደቁን ተከትሎ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ህገ መንግስታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው ምክንያት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስተባብረው ግብረ ሃይል የተቋቋመ ሲሆን ግብረ ሃይሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ የሚኖረውን ስልጣንና ተግባር በዝርዝር ተቀምጧል፡፡

በዚህ መሰረት በመጀመሪያ በተቀመጠው በትግራይ ክልል ላይ ተፈጻሚ በሚሆነውና ለስድስት ወር በሚቆየው በዚህ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ግብረ ሃይሉ በጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ሰብሳቢነት የተቋቋመ ሲሆን ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሆን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ተናግረዋል፡፡

ግብረ ሃይሉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የማስፋትም ሆነ የማጥበብ ስልጣን የተሰጠው ሲሆን፥ ማንኛውንም የፀጥታ ሃይል በማስተባበር በአንድ ዕዝ ስር እንዲመራ ማድረግ ይችላልም ነው የተባለው፡፡በትግበራው ወቅትም ተልዕኮውን ተፈጻሚ በሚያደርግበት ጊዜ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን ድንጋጌዎች ማውጣትም ሆነ መተግበርም ይችላል ነው ያሉት፡፡
የመደበኛ የዜጎች መብት ሳይጣስ አዋጁ በተጣለባቸው አካባቢዎች ላይ ተልዕኮውን ማስፈጸም የሚያስችለውን እርምጃ መውሰድም ይችላል ነው የተባለው፡፡ከዚህ ባለፈም ፖሊስን ጨምሮ ማንኛውንም የፀጥታ ሃይል ትጥቅ እንዲፈቱ ማድረግም እንደሚችልም አስረድተዋል፡፡

የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ጨምሮ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸው ሌሎች እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብም መጣል፣ የሰአት እላፊ ገደብ የማውጣት፣ የጦር መሳሪያ እንቅስቃሴዎችን የማስቆም፣ የመገናኛ ዘዴዎች እንዲቋረጡ የማድረግ፣ ለተልዕኮ እንቅፋት ይሆናሉ ያላቸውን መግለጫዎች መከልከል፣ ህገ ወጥ በሆነ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል ብሎ የጠረጠራቸውን ግለሰቦችና ቡድኖች የመያዝና የማቆየት እንደሚችል በተግባር አፈጻጸጸሙ ላይ ተቀምጧልም ብለዋል፡፡

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተደነገገባቸው አካባቢዎች ላይ ለተልዕኮ ተፈጻሚነት ያግዙኛል ብሎ ሲያምን ሰዎችን በአንድ ቤት፣ ቦታ ወይም አካባቢ እንዲቆዩ የማድረግ ስልጣን እንዳለውም ጠቅሰዋል፡፡ቤትና አካባቢዎችን ጨምሮ መጓጓዣዎችንም በማንኛውም ጊዜ መበርበርና መፈተሽ እንዲሁም አገልግሎት ሰጭ ተቋማትና መሰረተ ልማቶችን ለተልዕኮ መሳካት ያስችሉኛል ካለ ማስቆም እንደሚችልም አስረድተዋል፡፡ግብረ ሃይሉ ለተልዕኮ ተፈጻሚነት አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ማድረግ እንደሚችልም ስልጣን የተሰጠው ሲሆን በሂደቱ ተመጣጣኝ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጠ።

የኦሮሚያ ከልል የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለፈው ቀጠሮ የተሰማውን የዐቃቤ ህግ ምስክር ማስረጃን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ በያዘው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰረት ተሰይሟል፡፡በዚህ መሰረት ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ በተከሰሱበት ወንጀል ዐቃቤ ህግ ያሰማቸውን ምስክሮች መከላከል የሚያስችል የመከላከያ ማስረጃ ካላቸው እንዲያቀርቡ ለህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ለአቶ ልደቱ በዚህ ክስ የ100 ሺህ ብር ዋስትና መፍቀዱ የሚታወስ ነው።ህገ መንግስቱን በኃይል ለማፍረስ በማሰብ የሸግግር መንግስት ሰነድ ማዘጋጀት ወንጀል ክስ ላይም አቶ ልደቱ አያሌው የጤና ሁኔታቸው አስጊ ደረጃ ላይ መሆናቸውን ገልጸው የሃኪም ማስረጃ በማቅረብ የጠየቁት የዋስትና ጥያቄን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ችሎት ለህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል 'የትግራይ የፀጥታ ኃይል የሰላም አማራጭ ረግጠው በትግራይ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጁ የሩቅና የቅርብ ጠላቶች ለመደምሰስ በሚያስችል ሙሉ ቁመና ላይ እንገኛለን' ብለዋል ሲል የትግራይ ቴሌቪዥንን ጠቅሶ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ከባድ የጦር መሳሪያ ፍንዳታ በትግራይ ክልል ይሰማ እንደነበርና አሁን ላይ ለአንድ ሰዓት ያህል እንደቆመ በኢትዮጵያ የሮይተርስ ዘጋቢ ጂውሊያ ፓራቪቺኒ ፅፋለች፣ 20 የሚጠጉ ጉዳት የደረሰባቸው ወታደሮች በትግራይና በአማራ ክልል ድንበር አካባቢ በሚገኝ የጤና ማዕከል ህክምና እያደረጉ እንደሆነም በአካባቢው የሚገኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰራተኛ የሆነን አካል ጠቅሳ ፅፋለች።

@YeneTube @FikerAssefa
ሜጀር ጀነራል አለምእሸት ደግፌ ወደ መከላከያ ሠራዊቱ እንዲመለሱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል::

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ በትግራይ ክልል አሁን ያለው ሁኔታ በድርድር እንዲፈታ የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ዛሬ ቢጠይቁም በሀሳቡ እንዳልተስማሙ ተገልጿል።የሮይተርስ ዘገባ እንደሚለው የፌዴራል ባለስልጣናት ህወሓት መደምሰስ አለበት በሚል አቋማቸው ጸንተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በተለያየ ቦታ ያለው ሰራዊት ወደ ጦርነቱ ቦታ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉ ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃነ ጁላ በብሄራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ከህወሓት ጋር ለሚደረገው ዉጊያ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍል ያለው ሰራዊት ወደ ቦታው እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡“ሀገራችን ያላሰበችው ጦርነት ውስጥ ገብታለች፤ ይሄ ጦርነት አሳፋሪ ጦርነት ነው፡፡ አላማም የለውም፤ ከውስጥ እወጋለሁ ብሎ አላሰበም ነበር” ብለዋል፡፡

ጄነራል ብርሃኑ ህወሓት “ለእኩይ አላማ ያደረጀው ሃይል ሰራዊታችን ላይ ጥቃት አድርሷል::የትግራይ ህዝብ ይህንን አውግዟል ፣ ከመከላከያ ሰራዊታችንና ከመንግስት ጋር መሆኑን አረጋግጧል ” ብለዋል፡፡“በቀበሮ ጉዳድጓድ ውስጥ ሆኖ የትግራይን ህዝብና መንግስት በሚጠብቅ ሰራዊት”ላይ ወረራ የደረሰበት ብለዋል፡፡ሰራዊቱ ለተቃጣበት ጥቃት እጅ ባለመስጠት፤ ጥቃቱን መመከት መቻሉን ጀነራል ብርሃኑ ገልጸዋል፡፡ጄነራል ብርሃኑ ጦርነቱ ወደ መሃል ሀገር ሳይመጣ በዚያው እንደሚያልቅም ተናግረዋል፡፡

[Al ain/ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልል የሞባይል አጭር መልዕክት (SMS) አገልግሎት መስራት መጀመሩን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ መቐለ ዩንቨርስቲ ግቢው ውስጥ እንዲሁም አከባቢው ሰላም መሆኑን ምግብ እና የሚያስፈልጋቸው ነገሮች እየቀረበላቸው መሆኑን ከስፍራው መረጃ ደርሶናል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል 'የትግራይ የፀጥታ ኃይል የሰላም አማራጭ ረግጠው በትግራይ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጁ የሩቅና የቅርብ ጠላቶች ለመደምሰስ በሚያስችል ሙሉ ቁመና ላይ እንገኛለን' ብለዋል ሲል የትግራይ ቴሌቪዥንን ጠቅሶ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
የትግራይ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር፣ ደብረ ጺዮን ገ/ሚካዔል፣ ዛሬ ምን አሉ?

የትግራይ ክልል ጸጥታ ሃይሎች እና የፌደራሉ መከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ ግጭት ውስጥ ከገቡ ሁለተኛ ቀናቸው ሆኗል፡፡ በክልሉ የሚካሄደው ግጭት ምን መልክ እንዳለው ግን አስተማማኝ መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ትናንት በድምጸ ወያኔ ቴሌቪዥን ባስተላለፈው መግለጫ፣ በክልሉ የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ከክልሉ ጸጥታ ሃይል ጎን እንደተሰለፈ የገለጸ ሲሆን፣ ፌደራል መንግሥቱ ግን አስተባብሏል፡፡

ዶ/ር ደብረ ጺዮን ገ/ሚካዔል ስለ ወታድራዊ ሁኔታዎች ያሉት:

የተወሰነ የፌደራሉ መከላከያ ሠራዊት በምዕራብ ትግራይ በአድያቦ በኩል ወደ ኤርትራ ገብቷል፡፡ ይህም የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግሥት ትግራይን ለማጥቃት ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተባብሮ እየሠራ መሆኑን ነው፡፡ በምዕራብ ትግራይ የሚካሄደው ውጊያ እንደቀጠለ ነው፡፡ በደቡብ ትግራይ በተለይም በአፋር ክልል በኩል ፌደራል መንግሥቱ ተጨማሪ ጦር ሠራዊት እያሰማራ እንደሆነ ተረድተናል፡፡

ትግራይን ለመውረር የሚንቀሳቀስ ማናቸውም ሃይል ግን መውጫ አይኖረውም፡፡ የተከፈተብን ግልጽ ጦርነት ነው፤ ወረራ ነው፡፡ እናም የምናካሂደው ጦርነት ፍትሃዊ እና ሕልውናችን ለማስጠበቅ የምናደርገው ጦርነት ነው፡፡ በእጃችን ያለውን ከባድ ጦር መሳሪያ በቅርብ እና በሩቅ በሚገኙ የትግራይ ጠላቶች ላይ መጠቀም እንችላለን፡፡ ከጦር ግንባር ውጭ በትግራይ ሕዝብ ላይ በየትኛውም ቦታ ጥቃት በሚፈጽሙ አካላት ላይ ባሉበት ቦታ ለመምታት የሚያስችለን አቅም ፈጥረናል፡፡ ከእንግዲህ ጠላቶቻችን ባሉበት ቦታ ሁሉ ርምጃ እንወስድባቸዋለን፡፡

በትግራይ ክልል የሠፈረው የመከላከያ ሠራዊቱ ሰሜን ዕዝ የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት ለማስከበር ከክልሉ መንግሥት ጋር ተባባሪ እየሆነ ነው፡፡ የሠራዊቱ ዕዝ ከትግራይ ጎን የቆመው ግን የፌደራል መንግሥቱን ሴራ እና እንቅስቃሴ በመቃወም እንጅ የትግራይ ጸጥታ ሃይል አስገድዶት አይደለም፡፡ በክልሉ የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊቱ ከባድ ጦር መሳሪያዎችም ጉዳት ሳይደርስባቸው ለትግራይ ሕዝብ ደኅንነት እና ጥቅም እንዲውሉ ተደርገዋል፡፡ የክልሉ መንግሥት በእጁ የገባውን ከባድ ጦር መሳሪያ ተጠቅሞ ለውስጥ እና የውጭ ወረራ የሚመክት ይሆናል፡፡ ከባድ ጦር መሳሪያዎች በእጃችን ስለገቡ እና ሕዝባችንም ጸኑ ዐላማ ስላለው፣ ከአሁን በኋላ በትግራይ ጦርነት ይኖራል የሚል ዕምነት የለንም፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
በትግራይ ክልል የሞባይል አጭር መልዕክት (SMS) አገልግሎት መስራት መጀመሩን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መቐለ ዩንቨርስቲ ግቢው ውስጥ እንዲሁም አከባቢው ሰላም መሆኑን ምግብ እና የሚያስፈልጋቸው ነገሮች እየቀረበላቸው መሆኑን ከስፍራው መረጃ ደርሶናል። @YeneTube @FikerAssefa
የመልእክት አገልግሎት #መቋረጡን አውቀናል እኛ ( @Yenetube ) መረጃውን ባጋራንበት ወቅት SMS ይሰራ ነበር ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ መቋረጡን ለማወቅ ችለናል።

በSMS ያናገርናቸው የመቐለ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች እንዲሁም የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ከተማዋ ሰላም መዋሏል ነግረውናል።

@Yenetube @Fikerassefa
በዛሬው እለት ተዋጊ አውሮፕላን በመቐለ ሰማይ ላይ ሲበር እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል።በዚህም ውጪ የነበሩ ሰዎች በስጋት ወደቤታቸው እየተጣደፉ እንደገቡ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።የትግራይ ክልል መንግስት ምንም አይነት በረራ በክልሉ መከልከሉ ይታወሳል።የትግራይ ክልል ተዋጊ አውሮፕላን እንዳለው ወይም እንደሌለው ሚታወቅ ነገር የለም። የፌዴራል መንግስት በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም።

@YeneTube @FikerAssefa
መቀሌ አካባቢ በአዉሮፕላን ቦምብ ተመታ!

የኢትዮጵያ የጦር ጄቶች ዛሬ አመሻሽ ላይ የትግራይ ርዕሠ ከተማ መቀሌ አካባቢን በቦምብ መደብደባቸዉን የትግራይ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።የክልሉ የመንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባሰራጨዉ መግለጫ ጄቶቹ መቀሌ አካባቢ ቦምብ ጣሉ ከማለት ባለፍ ትክክለኛዉን ሥፍራ አልጠቀሰም።የአዲስ አበባና የመቀሌ የዶይቼ ቨለ ወኪሎች እንደጠቀሱት መግለጫዉ፣ በጥቃቱ የደረሰ ጉዳት ሥለመኖር አለመኖሩ ያለዉ ነገር የለም።ይሁንና ጥቃቱን «የትግራይ ሕዝብን ለማንበርከክ» ያለመ ብሎታል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የጂቡቲ አምባሳደር መሃመድ ኢድሪስ ፋራ ጂቡቲ ከመከላከያ ሰራዊቱ የኮበለሉ አዛዦችን እያስጠለለች ነው የሚለው ዜና ሀሰት መሆኑን ለሮይተርስ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
መቐለ ከማክሰኞ ወዲህ-በዶይቼ ቬለ ዘጋቢ አንደበት:

የዶይቼ ቬለው የመቐለ ዘጋቢ ሚሊዮን ኃይለስላሴ እንዳለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪዎችን የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ሲጠቀሙባቸው በመቐለ ጎዳናዎች ታይቷል።ዛሬ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ በመቐለ ሰማይ የጦር ጀት ሲያንዣብብ ድምጹ መሰማቱን የተናገረው ሚሊዮን "ብዙ ሰው ወጥቶ ኹኔታውን ሲከታተል ተመልክቺያለሁ" ብሏል።

በመቐለ የአየር ድብደባ መፈጸሙ በክልሉ መንግሥት ከመገለጹ ቀደም ብሎ ከተማዋ ቀስ በቀስ ወደ ዕለት ተለት ሕይወት በመመለስ ላይ ነበረች። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩት የፌድራል መንግሥት እና ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል የሚመሩት የትግራይ ክልል ወደ ከረረ ግጭት ከገቡ በኋላ በመቐለ ከተማ "የጦርነት ድባብ" ሰፍኗል።የዶይቼ ቬለው ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ የክልሉ መገናኛ ብዙኃን "ይኸንን ነው የሚያወሩት፤ የራዲዮ ጣቢያዎቹ የትግል ዘፈኖች ነው የሚያዘፍኑት" ሲል በከተማው የረበበውን ስሜት ይናገራል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጨምሮ በመቐለ ከተማ የሚገኙ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር ካምፖች በትግራይ ልዩ ኃይል ጥበቃ ሲደረግ መመልከቱን ሚሊዮን አስረድቷል። "በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የጦር ካምፖችም ከዚህ በፊት ይጠበቁ የነበረው በሀገር መከላከያ ሠራዊት ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ነበር። አሁን ደግሞ ተቀይሮ የልዩ ኃይል ሠራዊት ነው ቦታውን እየተጠበቀ የሚገኘው" ብሏል። ሚሊዮን እንዳለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪዎችን የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ሲጠቀሙባቸው በመቐለ ጎዳናዎች ታይቷል። ዛሬ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ በመቐለ ሰማይ የጦር ጀት ሲያንዣብብ ድምጹ መሰማቱን የተናገረው የዶይቼ ቬለው ሚሊዮን ኃይለስላሴ "ብዙ ሰው ወጥቶ ኹኔታውን ሲከታተል ተመልክቺያለሁ" ብሏል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ በመከላከያ ቁጥጥር ስር ነዉ ተባለ!

ረቡዕ ውጊያ ሲካሄድበት የነበረው የአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ ቅራቅር አካባቢ ዛሬ ሰላማዊ ሆኖ መዋሉን ነዋሪዎቹ ተናገሩ፣ በሌላ በኩል በዚሁ ዞን ምድረ ገነት ወይም አብደራፊ በተባለ አካባቢ ሌል ግጭት መፈጠሩን የአካባቢው ነዋሪ አመለከቱ፡፡ በትግራይ ልዩ ኃይልና በፌደራሉ መንግስት የፀጥታ ኃይል መካከል ትናንት የተፈጠረው ግጭት በአንዳንድ ቦታ ጋብ ሲል በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ ግጭቶች መፈጠራቸውን የየአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡  

ትናንት ረቡዕ ግጭት ከነበረባቸው አካባቢዎች አንዱ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ ቅራቅር አካባቢ ሲሆን አካባቢውን የመከላከያ ሰራዊት በመቆጣጠሩ ግጭቱ መቆሙን የአካባቢው ነዋሪ አመልክተዋል። ሰራዊቱ ወደ ትግራይ ፀገዴ በመግባትም የወረዳውን ዋና ማዕክል ከተማ ንጉስን መቆጣጠሩንም እኝሁ ነዋሪ ገልፀዋል።ግጭቱ ከመፈጠሩ በፊት ከበፊቱ የተለየ ነገር እንዳልነበር የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ ክስተቱ ድንገተኛ እንደነበር አስረድተዋል፡፡አንዳንድ ተቋማትን ከመጠበቅ የተለየ ነገር አልነበረም ብለዋል፡፡ አስተያየት ከሰጡት አንደኛው እንዳሉት በፀጥታ ችግር ምክንያት መንገድ ዝግ ስለነበር ለአንድ አመት ያህል 2 ሰዓታ የሚወስደውን የቅራቅር ጎንደር መንገድ በሌላ መንገድ ዞን ስለምንሄድ ረጅም ጊዜ ይስድብን ነበር ሲሉ አስረድተዋል።

 ሌላው የዚሁ አካባቢ ነዋሪ እንዳሉት አሁን አካባቢው ሰላም በመሆኑ የአካባቢው ሚሊሽያ ከሚተኩሰው የደስታ ጥይት በስተቀር ምንም ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።ዛሬ አነጋጉ ላይ በአማራ ክልል አብደራፊ ምድረ ገነት አካባቢ ግጭት እንደነበር ደግሞ አንድ አስተያየት ሰጪ አመልክተዋል፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ከቀኑ 10 ድረስ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ ቢሆንም እየራቀ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ አንድንድ አስተያየት ሰጪዎች ችግሩ እየሰፋ ሄዶ ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት ከመድረሱ በፊት አሁንም ሁለቱ አካላት ለድርድር ዝግጁ እንዲሆኑ ጠይቀዋል።የግንኙነት መስመሮች ሁሉ ዝግ በመሆናቸው ከትግራይ ክልል በኩል ያለውን ሁኔታ አስተያየት ማካተት አልተቻለም።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በሰሜን ኢትዮጵያ የነገሰው ውጥረት ያለምንም ቅድመሁኔታ እንዲረግብ ራሺያ ጥሪ አቀረበች!

ከሰሞነኛው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የራሺያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመረጃ እና የፕሬስ መምሪያ መግለጫ አወጣ።ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ የህወሓት ጦር አባላት በክልሉ ሰፍሮ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ካምፕ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ከአዲስ አበባ የሚወጡ መረጃዎች አሳይተዋል ያለው መምሪያው ጥቃቱን ተከትሎ በሰሜን የሃገሪቱ ክፍል አካባቢ ውጥረት መንገሱን ገልጿል።በሁለቱ አካላት መካከል በተካሄደው ከባድ ውጊያ ምክንያት ብዙ ሰብዓዊ አደጋዎች ማጋጠማቸውንም ነው ያስታወሰው።

አደጋው የሃገሪቱን ውስጣዊ የፖለቲካዊ ይዞታና መረጋጋት በማናጋት ከፍተኛ ስጋትን ከመፍጠር በዘለለ የንጹሐንን ህይወት እና የውጭ ሃገራት ዜጎችን አደጋ ላይ እንደሚጥል በማሳሰብ ሁለቱም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውጥረቱን እንዲያረግቡ ጥሪ አቅርቧል።ችግሩ በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በድርድር በጠረጴዛ ዙሪያ ይፈታል የሚል እምነት እንዳለውም ገልጿል።ሁኔታው ተሻሽሎ ኢትዮጵያ ወደ ቀደመ ሰላማዊ እና ህገመንግስታዊ ሁኔታዋ እንደምትመለስ ተስፋ ማድረጉንም በኢትዮጵያ የራሺያ ኤምባሲ ማህበራዊ ገጽ የሰፈረው መረጃ አመልክቷል።

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
#እባካችሁ

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ላይ #የውሸትዜናዎች እንዲሁም ያልተረጋገጠ መረጃዎችን ሆን ብላችሁ እየለቀቃችሁ ተከታዮቻችሁን አታስደንግጡ።

የቻናላችን ቤተሰቦች እንዲህ አይነት ቻናል ሲያጋጥማችሁ Report ማድረጋችሁን አትርሱ!!
@Yenetube @Fikerassefa
መቐለ ከተማ መብራት መመለሱን ከBBC ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ ተመልክተናል።

@Yenetube @Fikerassefa
ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን
በሰሜን የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው የአየር ክልል ለማንኛውም በረራ የተዘጋ በመሆኑ ይህንን ማሳሰቢያ ተላልፎ በረራ የሚፈጽም ማንኛውም አውሮፕላን እንዳይኖር አሳስቧል።

ከጥቅምት 25/2013 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በሰሜን የኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ የሚያቋርጡ የአለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ የበረራ መስመሮች ለማንኛውም የበረራ አገልግሎት የተዘጉ መሆኑን ለሁሉም አለም አቀፍ አገሮች ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa