YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ፖሊስ አንድ ጥቁር አሜሪካዊን መግደሉን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ የሰዓት እላፊ አዋጅ በፊላደልፊያ ግዛት ተጥሏል።

የተገደለው አፍሪካዊ አሜሪካዊ ዋልተር ዋላስ ቤተሰቦች የአዕምሮ ጤና ህመም እንዳለበት ገልፀው ፖሊሶችም ተኩሰው ገድለውታል ብለዋል።ፖሊስ በበኩሉ የያዘውን ቢላ አልጥልም በማለቱ ነው የተኮስነው ይላል።የ27 አመቱ ዋላስ 'ባይፖላር ዲስኦርደር' የሚባል የአዕምሮ ጤና መታወክ እንዳለበትም ለፖሊሶቹ ባለቤቱ ቀድማ ብትናገርም በጥይት ተኩሰው እንደገደሉት ቤተሰቡን ወክሎ ጠበቃው ተናግሯል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ደቡብ ክልል የበረሃ አንበጣ የመከሰት እድሉ በጣም ከፍተኛ መሆኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ገለጸ።

ባለፈው አመት በአብዛኛዎቹ የክልሉ አካባቢዎች በ400ሺ ሄክታር መሬት ላይ አንበጣ ተከስቶ እንደነበር ቢሮው ጠቁሟል።ቢሮው የደቡብ ክልል የአንበጣ መንጋ መከላከልና መቆጣጠር ግብረ ሃይል በችግሩ ዙሪያ ውይይት ሲያካሂድ እንደገለጸው የአንበጣ መንጋው እስከ አሁን መከሰቱ ባይረጋገጥም በቀጣይ የመከሰት እድሉ እጅግ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ አስታውቋል።አሁን ላይ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ሰፊ ጉዳት ያደረሰው ይህ የአንበጣ መንጋ በደቡብ ክልልም የመምጣት እድሉ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተነስቷል።

ክልሉ ከፍተኛ የአንበጣ መንጋ ስጋት እንዳለበት የቢሮው ሃላፊና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አንተነህ ፈቃዱ ጠቁመዋል።የዚህ ስጋት መነሻም በአሁኑ ወቅት በሶማሌ ክልል፣በኬንያ፣ሶማሊያና ሱዳን እየተራባ ያለው የአንበጣ መንጋ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።ይህን ሰፊ ስጋት የሚመጥን ቅድመ ዝግጅት ሊደረግ እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።በክልሉ ታህሳስ ወር ላይ ሊመጣ ይችላል የሚል ትንበያ እንዳለም አቶ አንተነህ ገልጸዋል።

Via SRTA
@YeneTube @FikerAssefa
በፈረንሳይ ኒስ ከተማ በአንድ ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ሁለት ሰዎች በስለት ተወግተው ሲሞቱ በርካቶች ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል። የከተማዋ ከንቲባ ክርስትያን ኤስቶሪ ድርጊቱን የሽብርተኝነት ተግባር ነው ብለው መግለጻቸውን ኤን ቢ ሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት በክልል ደረጃ መዋቀር አለበት በሚልና ሌሎች ጥያቄዎች ምክንያት አለመግባባት ውስጥ የነበሩት የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እርቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ መኮንንም ለቢቢሲ እንደገለፁት ለመታረቅ መንገድ መጀመራቸውን ነው።የሚስማሙባቸውን…
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእነ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ላይ አስተላልፋው የነበረውን እገዳ ማንሳቷን አስታወቀች።

የፓትሪያርክ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ቤተክርስቲያኗ የኦሮሚያ ቤተክህነትን ለማቋቋም በሚል በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩት ላይ እገዳ አስተላልፋ ነበር።ይሁንና እነዚህ ሰዎች ከቤተክርስቲያኗ ጋር ባደረጉት የእርቅ ስራ በእነ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ላይ አስተላልፋው የነበረውን እገዳ ማንሳቷን አስታውቃለች።እገዳው ተላልፎባቸው የነበሩት ሰዎች በቤተክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ ሆነው ሥራ እንዲሰሩም ውሳኔ ተላልፏል ተብሏል።በመሆኑም እነቀሲስ በላይ በእርቁ ላይ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ይሰጣሉ ተብሏል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
189 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ከቤሩት ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡ ዛሬ ከቤሩት ወደ ሃገራቸው የተመለሱት 189 ኢትዮጵያውያን ሰነድ አላባ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ሰነድ አልባ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለሱ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ከቤሩት የኢትየጵያ ቆንስላ ጄኔራል ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ150 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባውን የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ በዛሬው እለት መርቀው ከፍተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በድሬዳዋ ከተማ በ150 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውን የኢንዱስትሪ ፓርክ መርቀዋል።የኢንዱስትሪ ፓርኩ ለ1 ሺህ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር 20 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
በቀሲስ በላይ መኮንን እና በቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የነበረው የዕርቅ ሂደት መጠናቀቁ ተገለጸ!

በኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጽህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ መኮንን እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ መካከል እየተካሄደ የነበረው የዕርቅ ሂደት መጠናቀቁን ሂደቱን ሲመሩ የነበሩ ሽማግሌዎች ገለጹ።ቀሲስ በላይ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት እንደሚያቋቁሙ መግለጻቸውን ተከትሎ ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።

ቤተ ክርስቲያኒቱ ባለፉት ጥቂት ቀናት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ስታደርግ ከተነሱ ነጥቦች አንዱ በቀሲስ በላይና በሲኖዶሱ መካከል ዕርቀ ሰላም ማውረድ እንደሆነ መገለፁ አይዘነጋም።የዕርቅ ሂደቱን ሲመሩ የነበሩ አባቶች ዛሬ ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ. ም. በሰጡት መግለጫ፤ "በመጀመሪያ ቋሚ ሲኖዶስ፣ በመቀጠልም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ባጸደቀው መሠረት የዕርቅ ሂደቱ ተጠናቋል" ተብሏል።

ለሙሉ ዘገባው👇👇👇
https://bbc.in/31SZomI

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ማእከሉን መቐለ ላደረገው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ አዲስ የተመደቡ አንድ አዛዥ ዛሬ መቐለ ከደረሱ በኃላ በክልሉ የፀጥታ ሐይል እንዲመለሱ መደረጉ ተገለፀ።የትግራይ ክልል መንግሥት "የፌደራል መንግስት ሰራዊቱን ማዘዝ አይችልም" ይላል።

Via Million HaileSelasie
@YeneTube @FikerAssefa
አብን ለረቡዕ በጠራው ሰልፍ ላይ መንግሥት ስለፈጠረበት ችግሮች ከመንግሥት ባለስልጣናት ጋር እንደመከረ በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ለተፈጠረው መስተጓጎል መንግሥት ይቅርታ እንደጠየቀም ንቅናቄው አክሎ ገልጧል፡፡ የታሰሩ የንቅናቄው አመራሮች እና ደጋፊዎችን ማስፈታት መቻሉንም ገልጧል፡፡ አብን ውይይት ያደረገው ከአማራ ክልል ጋር ወይንስ ከፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ስለመሆኑ መግለጫው አላብራራም፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 481 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7,773 የላብራቶሪ ምርመራ 481 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ6 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,457 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 867 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 50,753 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 95,301 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ  በታጠቁ ሀይሎች  ሁለት ሰዎች መገደላቸውን  የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ጥቃቱ  በአካባቢው በሚኖሩ አርሶ አደሮች ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ እንደነበረም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።በወረዳዋ ከመሰከረም ወር ጀምሮ ተመሳሳይ ጥቃቶች ሲደርሱ እንደነበርም ነው ነዋሪዎቹ ያመለከቱት።የአሙሩ ወረዳ ፖሊስ በበኩሉ ጥቃቱ መድረሱን አረጋግጦ ነገር ግን ማንነትን መሰረት ያደረገ አይደለም ሲል ክሱን አስተባብሏል።  

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በኮቪድ-19 ማዕከላት የሚሠሩ የጤና ባለሙያዎች የተገባልን ቃል አልተፈጸመም አሉ!

በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሥር በሚተዳደሩ እና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በተቋቋሙ የሕክምና መስጫዎች ውስጥ የሰሩ እና የሚሰሩ የሕክምና ባለሙያዎች በተለያየ ጊዜ የተገባላቸው ቃል እንዳልተፈጸመ በመግለጽ ቅሬታቸውን አቀረቡ።ኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በኢትዮጵያ መገኘቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ መንግሥት በሕክምና ባለሙያዎችን ላይ የሚኖረውን ጫና ከግምት በማስገባት ከባለሙያዎቹ ጎን እንደሚቆም አስታውቆ ነበር።

በዚህ መሠረትም የሚንስትሮች ምክር ቤት ግንቦት 14/2012 ዓ. ም ባካሄደው 83ኛ መደበኛ ስብሰባ የኮቪድ-19 ወረርሽንን በመከላከል እና የህክምና አገልግሎት በመስጠት በቀጥታ ለሚሳተፉ የጤና ባለሙያዎች ልዩ አበል እንዲከፈላቸው ውሳኔ ማሳለፉን ባለሙያዎቹ ለቢቢሲ አስረድተዋል።ምክር ቤቱ እንደሙያቸው እና ሥራቸው ሁኔታ ከ1ሺህ150 ብር ጀምሮ እስከ 300 ብር በየቀኑ እንዲከፈላቸው ነው የወሰነው።

በዚህ መሠረትም በፌደራል ደረጃ የሚተዳደሩት እንደ ኤካ ኮተቤ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል እና ሚሊኒየም ሆስፒታል ያሉት የጤና ተቋማት እና አንዳንድ ክልሎች ወሳኔውን መሠረት በማድረግ ለባለሙያዎቻቸው ልዩ አበል እንደከፈሉ ባለሙያዎቹ አስታውቀዋል።ሆኖም በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሥር ከሚተዳደሩ ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች መከካከል የተወሰኑት የኮሮናቫይረስ ህክምና መስጫ ማዕከል ሆነው እያገለገሉ ቢሆንም ለባለሙያዎች እስካሁን ምንም ዓይነት ከፍያ እንዳልተፈጸመ የጤና ባለሙያዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮን ምላሽ ጨምሮ ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ👇👇👇
https://bbc.in/3eblOo7

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
160 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከቤይሩት ወደ አገራቸው ተሳፈሩ!

በ9ኛ ዙር ወደ አገራቸው ለመሳፈር ተመዝግበው ከነበሩ ሰነድ አልባ ዜጎች መካከል ዛሬ ጥቅምት 20 ቀን 2013፣ 160 ዜጎች ወደ አገራቸው ተሳፍረዋል፡፡

Via Ethiopian Consulate In Beirut
@YeneTube @FikerAssefa
140 ስደተኞች ሴኔጋል አቅራቢያ ሰጥመው ሞቱ!

የተባበሩት መንግሥታት ወደ 200 የሚጠጉ ስደተኞችን ጭና ወደ አውሮፓ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ሴኔጋል አቅራቢያ ሰጥማ 140 ስደተኞች መሞታቸውን አስታወቀ።ጀልባዋ ማቡር ከምትባለው የሴኔጋል ከተማ ከተነሳች በኋላ በእሳት ተያይዛ መስጠሟን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አረጋግጧል።አደጋው የደረሳው ባለፈው ቅዳሜ ነበር።ከአደጋው 60 ሰዎች በሕይወት መትረፍ መቻላቸው ተጠቁሟል።

[IOM/BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራና የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡የምክክር መድረኩ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና የምክክር ባህል ማጎልበት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ውይይቱ ዛሬ መካሄድ የጀመረ ሲሆን እስከ ነገ የሚቀጥል ይሆናል፡፡በመድረኩ የፖለቲካ አመራሮችና የፓርቲ ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ላይ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ፣ የህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት፣ የሀገር ግንባታ ድርሻ፣ ሰላማዊ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባህል ግንባታ ላይም ይመከራል፡፡ኢትዮጵያ ባሳለፈቻቸው የነገስታት፣ የወታደራዊ ደርግ፣ ኢህአዴግ፣ የለውጥ ጉዞና የወደፊት የፖለቲካ አቅጣጫ ላይም ይመከራል ተብሏል፡፡

ዘገባው የፋና ሲሆን የትኞቹ ፓርቲዎች በውይይቱ ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ያለው ነገር የለም

@YeneTube @FikerAssefa
65 በመቶ ኢትዮጵያዊያን ለዜጎቹ ተጥያቂ የሆነ መንግሥት እንዲኖር ይፈልጋሉ!

አፍሮ ባሮሜትር የተሰኘ የጥናት እና ምርምር ተቋም በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲን እና ተጠያቂነትን በሚመለከት ባደረገው የዳሰሳ ጥናት 65 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ሳያማክር በራሱ ከሚወስን መንግሥት ይልቅ ለዜጎቹ ተጠያቂ የሆነ መንግሥት እንዲኖር ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቋል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ከክልል ፕሬዚዳንቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

ውይይቱ በሃገሪቱ የጸጥታ ጉዳይና ባጋጠሙ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ሃገራዊ ምርጫ የፊታችን ግንቦት ወይም ሰኔ ወር ላይ ለማካሄድ ማቀዱን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ሃገራዊ ምርጫ ከኮቪድ 19 ወረረሽኝ ጥንቃቄ በማድረግ ማካሄድ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚዲያ አካላትና የሲቪክ ማህበራትን በማሳተፍ እየመከረ ነው፡፡ቦርዱ ለውይይት ባቀረበው መነሻ ሃሳብም 6ተኛው ሃገራዊ ምርጫ በግንቦት ወር የመጨረሻ ሁለት ሳምንታት አልያም የሰኔ ወር የመጀመርያ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ለማካሄድ እቅድ እንዳለው አስታውቋል፡፡የጊዜ ሰሌዳውን በተመለከተ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦችን እንደሚያካትትም ቦርዱ ገልጿል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ሃገራዊ ምርጫ የፊታችን ግንቦት ወይም ሰኔ ወር ላይ ለማካሄድ ማቀዱን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛውን ሃገራዊ ምርጫ ከኮቪድ 19 ወረረሽኝ ጥንቃቄ በማድረግ ማካሄድ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚዲያ አካላትና የሲቪክ ማህበራትን በማሳተፍ እየመከረ ነው፡፡ቦርዱ ለውይይት ባቀረበው መነሻ ሃሳብም 6ተኛው ሃገራዊ ምርጫ በግንቦት ወር የመጨረሻ ሁለት…
ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ከታህሳስ እስከ ጥር ባሉት ጊዜያት የመራጮች ምዝገባ እንደሚካሄድ ተገለጸ!

ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ከታህሳስ እስከ ጥር ባሉት ጊዜያት የመራጮች ምዝገባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።ቦርዱ ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ በሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ከሲቪክ እና ከመገናኛ ብዙሃን አባላት ጋር እየመከረ ነው።በምክክር መድረኩ መክፈቻ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንደተናገሩት ከታህሳስ እስከ ጥር ወር 2013 ዓ.ም ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች መዝግባ ይካሄዳል።

"ከጥር የመጀመሪያው ሳምንት እስከ የካቲት አጋማሽ ደግሞ የእጩዎች ምዝገባ እንዲሁም ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ የምረጡኝ ቅሰቀሳ ይጀመራል" ሲሉም ተናግረዋል።በምክክር መድረኩ ላይ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ እና በምርጫ ሂደት ስለሚወሰዱ የኮቪድ-19 የጥንቃቄ እርምጃዎችን በተመለከተ ከሲቪክ ማህበራት እና ከመገናኛ ብዙሃን አባላት ጋር በመወያየት ግብዓት ይወሰዳል ተብሏል።በተጨማሪም ሲቪክ ማህበራት አና መገናኛ ብዙሃንን የሚመለከቱ ዋና ዋና የምርጫ እንቅስቃሴዎች እና ዝግጅቶች ላይ ውይይት እንደሚደረግም ነው የተገለጸው።

እንደ ወይዘሪት ብርቱካን ገለጻ፣ መድረኩ የተዘጋጀው የሲቪክ ማህበራት እና የመገናኛ ብዙሃን የሚያነሷቸውን ሀሳቦች በመጨረሻ ለሚወጣው የምርጫ ጊዜ ሰለዳ እና የአፈጻጸም ዕቅድ ላይ በግብዓትነት ለመጠቀም ታስቦ ነው።በመድረኩ በምርጫ ሂደት የሚተገበሩ የኮቪድ-19 የጥንቃቄ መመሪያ መነሻ ሀሳቦች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።በተጨማሪም ዋና ዋና የምርጫ ተግባራት በሚተገበሩበት ጊዜ የሲቪክ ማህበራት እና የመገናኛ ብዙሃን ያላቸውን ሚና የተመለከቱና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
ህዳሴ ግድብን ከደለል ለመታደግ የአባይ ተፋሰስን በቆላ ቀርከሀ ለማልማት ስምምነት ተፈረመ!

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ከደለል ለመታደግ የአባይ ተፋሰስን በቆላ ቀርከሀ ለማልማት ተቋማት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ስምምነቱን የተፈራረሙት የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን፣ የአካባቢና ደን ምርምር ኢንስቲትዮት፣ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲና ሰላሌ ዩኒቨርስቲ ናቸው፡፡በመጀመሪያ ዙር በቆላ ቀርከሀ ለማልማት የታሰበው የደጀንና የጎሀፅዮን የአባይ ተፋሰስ ቆላማ አካባቢዎችን ነው ተብሏል፡፡የአካባቢና ደን ምርምር ኢንስቲትዩትም የቆላ ቀርከሀ ዛፍ ችግኞችን እያባዛ መሆኑን ገልጿል፡፡እስካሁን ድረስ 10 ሺህ ችግኞችን ማባዛቱን ኢንስቲትዩቱ ጠቅሶ በቀጣይም 500 ሺህ ለማባዛት ማቀዱን ጠቁሟል፡፡የቆላ ቀርከሀ የአባይ ተፋሰስ በደለል እንዳይሞላና ሥነ-ምህዳሩ እንዲያገግም ከማድረግ ባለፈ ለአካባቢው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa