በአፍሪካ ቀንድ አዲስ የበረሃ አንበጣ እየተራባ እንደሚገኝ ተነገረ!
አዲስ የበረሃ አንበጣ መንጋ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ እየተራባ እንደሚገኝ ተገልጿል።የአንበጣ መንጋው ወደ ኬኒያም እንደሚዛመት ተመላክቷል።እስከ ታህሳስ አጋማሽም አዲስ እየተራቡ ያሉት የአንበጣ መንጋዎች ወደ መንጋነት እንደሚሰፉ ነው የተጠቆመው።የዓለም ምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) የአንበጣ መንጋው የሚከሰትባቸው አገሮች የቅድመ መከላከያ ዝግጅት፣ ቅኝትና ሰፊ የቁጥጥር ስራ ማከናወን እንዳለባቸው ማሳሰቡን ብሉምበርግ ዘግቧል።ከሰባ አመታት ወዲህ ታይቶ አይታውቅም በተባለው የአንበጣ መንጋ በኢትዮጵያና በቀጠናው አገሮች ላይ ሰፊ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።
Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa

የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ስያሜ ሊቀየር ነው ተባለ!
የመንግስት ተቋም ሆኖ ወደ ሥራ የገባው መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ስያሜው ሊቀየር መሆኑን የአካዳሚው ሰራተኞች አስታወቁ፡፡የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ እንደገለጸው የአካዳሚውን ተልዕኮ የሚመጥን ስያሜ ለመስጠትም ስራ ሲሰራ እንደነበር አስታውቋል፡፡
እስካሁን መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ሲባል የነበረው የመንግስት ተቋም የኢትዮጵያ አመራር አካዳሚ እንዲባል ሀሳብ መቅረቡ አል ዐይን ከተቋሙ አረጋግጧል፡፡ ይሁንና ሀሳቡ ገና በሕግ አጽዳቂው አካል እንዳልጸደቀ ተገልጿል፡፡
ሙሉውን የአል ዐይን ዘገባ ለማንበብ👇👇
https://am.al-ain.com/article/meles-zenawi-academy-to-change-its-name

የኦሮሞ ነጻነት ገንባር ኦነግ በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ግድያዎችን አወገዘ።
ኦነግ በተለይ ከለውጡ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ ድንገተኛ ጥቃቶች ግድያዎች እና ከባድ ዝርፊያዎች መበራከታቸውን አስታውቋል።ይህ በምንም መስፈርት ተቀባይነት የለውም ያለው ኦነግ፤መንግስት በቅድሚያ የዜጎችን የመኖር መብት እንዲከበር የማድረግ ግዴታ አለበት ብሏል።የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ እንዳሉት ማንኛውም ዜጋ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን ሲገደል ጥቃቱ የሁላችንም እንደሆነ ሊሰማን ይገባል ብለዋል፡፡
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየደረሱ ያሉት ጥቃቶች መፈናቀሎችና ግድያዎችን ማውገዝ ለአንድ ወገን ብቻ የሚሰጥ ሳይሆን በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር የሚንቀሳቀስ የትኛውም የፖለቲካ ፖርቲ ግዴታው መሆኑን ተናግረዋል፡፡በማይታወቁ ሰዎች እና በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ስለሚገደሉት ዜጎቻችን ሁሌም ቢሆን እንሟገታለን የሚሉት አቶ ቀጀላ የዚህ ግድያ ሰለባዎች የመንግስት አመራሮች ጭምር በመሆናቸው ችግሩ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ መንግስት ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡መንግስት ጸጥታን በማስከበር ህብረተሰቡን ከስጋት ነጻ የሆነ ህይወት እንዲኖረው የማድረጎ ስራ ለዛሬና ለነገ የሚሰጠው ስራ እንዳሆነም ነው የሚናገሩት፡፡
Via Ethio FM
Photo: DW

YeneTube
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላም አስከባሪ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሥልጠና እየወሰዱ ነው! በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላም ለማስጠበቅ በተለያዩ ዘርፎች ተመድበው የሚሰሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሥልጠና እየወሰዱ ነው፡፡በ45 ዩኒቨርሲቲዎች እና በ15 ቅርንጫፍ ካምፓሶች የሚመደቡ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለሚፈጠሩ ግጭቶች ህግ ለማስከበርና በጤና ሚኒስቴር…
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመድበው ለሚያገለግሉ የፓሊስ አባላት ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
የስልጠናው ዓላማ በሀገሪቱ ባሉ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የህግ ማስከበር ስራ እንዲጠናከርና ሰላምና ደህንነት እንዲረጋገጥ ብሎም ዩኒቨርሲቲዎች የታለመላቸውን ዓላማ በነፃነት እንዲያሳኩ ለማስቻልና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ሰላምና ደህንነት ተጠብቆ ተግባራት በውጤታማነት እንዲያከናውኑ ለማስቻል ነው።
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ በማድረግ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ እንዲሁም የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆን የፓሊስ ስነምግባር መርሆዎችን በመላበስ የህግ የበላይነት መረጋገጥ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።
ተሳታፊዎችም ከተለያዩ የጸጥታ መዋቅር እና ከተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር ተቀናጅተው በመስራት የህግ የበላይነት ማስከበር ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
Via MoP

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት 1ሺህ 495ኛው የነብዩ መሐመድ የመውሊድ በዓል በታላቁ አንዋር መስጊድ ውስን ዓማኞች በተገኙበት እንደሚከበር ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጁ ዑመር በመልዕክታቸው ምዕመኑ የመውሊድ በዓልን የሚያከብረው የነቢዩ መሐመድን አስተምህሮ በመተግበርና ተምሳሌታዊነቱን ለማስቀጠል ጭምር መሆኑን ተናግረዋል።እንዲሁም የመውሊድ በዓልን ቀኑን ለማክበር ሳይሆን በዛን ጊዜ ለሰው ልጆች ፈጣሪ የዋለውን ውለታ ለማወደስና ለማመስገን ነው ብለዋል።በተጨማሪም በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሼህ አሊ መሃመድ ሺፋ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በዚህ ወቅት በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ ለሚበልጡ ነዋሪዎች የማዕድ ማጋራት ስነ ስርዓት ተካሄዷል፡፡ምክር ቤቱ በዓሉን በተለያዩ ደማቅ ስነስርዓቶች ለማክበር ቢያስብም በሃገሪቱ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከ5 ሺህ ያልበለጠ ሰው በሚታደምበት ለማክበር መገደዱንም ነው የተናገሩት፡፡አያይዘውም አሁን በሀገሪቱ እየገጠሙ ያሉ ተፈጥሯዊ ችግሮች መልካቸውን እየቀያየሩ ፈተና እንዳይበዛ እና አሁን ያለውን አንበጣና ሌሎችንም ችግሮቸ ለመቋቋም ዱዓ ማድረግና ሶደቃ ማብዛት ይገባልም ነው ያሉት፡፡በመልዕክታቸው ሁሉም የሀገሪቱ ዜጋ የሀገሩን ሰላምና አንድነት እንምዲሁም ልማትን ማስቀጠል ላይ ያለምንም ልዩነት ሊረባረብና ሊሰራ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።
Via FBC

ዛሬ በአማራ ክልል ሊካሄድ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በኢትዮጵያ መንግሥት መታገዱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አውግዟል፡፡መንግሥት ሰልፉን ማገዱ አስደንጋጭ እንደሆነበትም ገልጧል አምነስቲ፡፡ ጸጥታ ሃይሎች የሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ደኅንነት መጠበቅ እንጅ ሰልፍ መበተን ወይም ማገድ የለባቸውም- ብለዋል የድርጅቱ የምስራቅ አፍሪካ ሃላፊ፡፡መንግሥት የሰዎችን በሕይወት የመኖር መብት መጠበቅ ብሎም የዜጎችን የመሰብሰብ እና የመናገር ነጻነት ማክበር አለበት፤ ሰዎች ሃሳባቸውን ስለገለጹ ብቻ ሊገደሉ እና ሊታሰሩ አይገባም በማለትም አሳስቧል ድርጅቱ በመግለጫው፡፡በምሥራቅ አፍሪካ የሂውማን ራይትስ ዎች ሃላፊ ላቲሻ ባድርም በተመሳሳይ የመንግሥትን ርምጃ አውግዘዋል፡፡
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በቀጣዮቹ ቀናት በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል!
አርብ ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ፡-
•በኮተቤ ላምበረት፣ በመገናኛ፣ በየካ ሚካዔል፣ በሾላ ገበያ፣ በትምህርት ስርጭት፣ በእግዚአብሔር አብ ቤተ-ክርስትያን፣በሜጋ እና አካባቢዎቻቸው፣
በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ፡-
•በቼራሊያ ፋብሪካ፣ በገነት መናፈሻ ኮንደሚኒየም፣በማሩ ብረታ ብረት፣በወህይኒ ቤት ጀርባ፣ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት፣ በቦሌ ሚካዔል፣ በቦሌ ካርጎ፣ በማዕድን ማህበር እና አካባቢዎቻቸው፤
እንዲሁም እሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ-
•በሳሚት ኮንደሚኒየም፣ በፍየል ቤት፣ በጊዮርጊስ ቤተ-ክርስትያን እና አካባቢዎቻቸው፤
በተጨማሪም ሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ፡-
•በኮተቤ ላምበረት፣ በመገናኛ፣ በየካ ሚካዔል፣ በሾላ ገበያ፣ በትምርት ስርጭት፣በእግዚአብሔር አብ ቤተ-ክርስትያን፣ በሜጋ፣ በኮተቤ ብረታ ብረት፣ በኮተቤ ኪዳነ ምህረት ቤተ-ክርስትያን፣ በአንቆርጫ ሰፈር፣ በእፎይታ ሰፈር፣ በጎተራ ላንቻ፣ በግሎባል ሆቴል፣ በጨርቆስ ቤተ-ክርስትያን እና አካባቢዎቻቸው፤
በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ፡-
•በኦሎምፒያ፣ በፍላሚንጎ፣ በደንበል፣ በኦሮምያ ቢሮ፣ በሰንሻይን ጀርባ እና አካባቢዎቻቸው፤
በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 602 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 6,290 የላብራቶሪ ምርመራ 602 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ6 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,451 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 918 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 49,886 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 94,820 ደርሷል፡፡

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከዩንቨርስቲዎች መከፈት ጋር በተያያዘ ለተማሪዎች ደህንነት አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ተካሂዷል የተባለው የመሬት ወረራ ሪፖርት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ተባለ!
በአዲስ አበባ ተካሂዷል የተባለው የመሬት ወረራ ሪፖርት በመጠናቀቅ ላይ በመሆኑ ውጤቱ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ተባለ።በከተማዋ ያለዉን የመሬት ወረራ ጥቆማ እና ቅሬታዎች ለማጣራት የተቋቋመውን ግብረ ኃይል የስራ አፈፃፀም እና ግኝቶች ዛሬ ተገምግሟል። ግምገማው የተካሄደው የከተማ አስተዳደር መረጃዎችን እና በመሬት ላይ ያለውን እውነታ ማወቅ፣ ማረም እና ተጠያቂነት ማረጋገጥን ታሳቢ በማድረግ ነው ተብሏል።አጠቃላይ ሪፖርቱ በአንድ ሳምንት ውስጥ ተጠናቆ ግኝቶቹም ለህዝባችን ይፋ ይደረጋል ሲሉ ምክትል ከንቲባ አዳናች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ ተቋርጦ የነበረው የመሬት ነክ አገልግሎት እገዳም ይነሳል ብለዋል።
Via EPA

ከሶማሊ ክልል መንግሥት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ!
ሰሞኑን በሶማሊ ክልል እና አፋር ክልል አዋሳኝ አከባቢ በተፈጠረው ግጭት አስከትሎ የ27 ንፁሃን ዜጎች ህይወት ያለፈ ስሆን ከእነኝህ መካካል በትናንትናው ዕለት በሲቲ ዞን ገረብ ኢሴ የሞቱት 10 ስዎች ይገኝበታል።
በአካባቢው በተከሰተው ግጭት ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ የክልሉ መንግሰት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ፣ለቤተሰቦቻቸዉና ለመላው የሶማሊ ህዝብ መፅናናትን ይመኛል።
እንዲህ አይነት ድርጊት ተደጋጋሚ ከመሆናቸው አና የሰው ህይወት መጥፋት ከማሰከተላቸዉ በተጨማሪ ከባድ የንብረት ውድመቶች እያደረሱ ይገኛሉ።ስለዚህ የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግሰት ጋር ግንኝነት እያደረገ ስሆን ለተጎጂዎች አስቸኳይ እርዳታ ለማድረስ እየተሰራ ነው።
የሁለቱም ክልሎች ስላም ጥያቄ ዉሰጥ በማስገባት የሁለቱ የወንድማማች ህዝቦች ግንኙነት እንዳይፈርስም እየተሰራበት ይገኛል።የዚህ ድርጊት መነሻ፣ የደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት በዝርዝር በመመርመር መፈትሔ ለማበጀት የክልል መንግስት እየሰራበት እንደሆነ እናሳውቃለን። ምርመራው እንዳለቀም ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል።
የሶማሊ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከጎዴ ቀላፎ ፈርፈር ሎት ያለውን የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በይፋ አስጀመሩ!
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንባታውን ያስጀመሩት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ጋር ዛሬ በጎዴ ከተማ በመገኘት ነው፡፡
የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ የአገሪቱን የወጪና ገቢ ንግድ በእጅጉ እንደሚያሳልጥ ታምኖበታል፡፡
Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንባታውን ያስጀመሩት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ጋር ዛሬ በጎዴ ከተማ በመገኘት ነው፡፡
የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ የአገሪቱን የወጪና ገቢ ንግድ በእጅጉ እንደሚያሳልጥ ታምኖበታል፡፡
Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
1495ኛው የነብዩ መሀመድ የልደት በዓል እየተከበረ ይገኛል!
የ1495ኛው የነብዩ መሀመድ የልደት በዓል ወይንም መውሊድ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዓሉ በተለይ በአዲስ አበባ በአኑዋር መስጅድ ሲከበር የሃማኖቱ ተከታዮችና እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ሲሆን በበዓሉ ላይ ሃይማኖታዊ መልእክቶች እየተላለፉ ነው፡፡ ሙሰሊሙ ህብረተሰብ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ በየመስጅዱ በመሄድ በዓሉን እያከበረ ነው፡፡የዘንድሮው የመውሊድ በዓል የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተው ወዲህ ሲሆን የእምነቱ ተከታዮች ጥንቃቄ በማድረግ እንዲያከብሩ መልእክት ተላልፏል፡፡
[አል ዐይን]

በኢትዮጵያ ያሉ ኤርትራውያን ስደተኞች መድልዎ እየደረሰባቸው እንደሆነ ገለፁ!
በመቶ ሺዎች የሚሆኑ ስደተኞችን በመጠለያ ማዕከላት በምትቀበለው ኢትዮጵያ ወደ አገሪቷ የሚገቡ ኤርትራውያን ስደተኞች መድልዎ እየደረሰባቸው እንደሆነ ቅሬታቸውን አሰሙ።ኤርትራውያን ስደተኞቹ "ወታደሮችና የመንግሥት ሰራተኞች" ያልሆናችሁ ወደ ስደተኞች ካምፕ አትገቡም በሚል ተከልክለናልም እያሉ ነው።ከኤርትራ በተለያዩ ምክንያቶች ጠፍተው የመጡና የኢትዮጵያ ድንበርንም አቋርጠው የገቡ ስደተኞች በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል በሚገኙ የድንበር ከተሞች ተጠልለውም ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ይናገራሉ።
በዓዲግራት፣ ዛላምበሳ፣ ሽራሮ፣ ዓዲ ነብር፣ ራማ እና ገርሁስርናይ በሚባሉት ከተሞችም ስደተኞቹ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው እንዳሉም ቢቢሲ ለመረዳት ችሏል።ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መሰረት ወደ ኢትዮጵያ ተሻግረው የሚገቡ ኤርትራውያን ስደተኞች በድንበር አካባቢ በሚገኙ ጊዜያዊ መጠለያዎች ውስጥ እንዲቆዩ ይደረግ ነበር።ከባለፈው አመት ጥር ወር ጀምሮ እነዚህ ጊዜያዊ ማቆያ ማዕከላት የተዘጉ ሲሆን የስደተኞችና ከስደት ተመላሽ ጉዳዮች ኤጀንሲ ሰራተኞች ኤርትራውያን ወደሚገኙበት የለይቶ ማቆያ ቦታ በመሄድም የምዝገባና የማጣራት ስራ እያከናወኑ ይገኛሉ።በዓዲግራት ዩኒቨርስቲ የለይቶ ማቆያ ጊዜያቸውን ጨርሰው በአሁኑ ወቅት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ኤርትራውያን ስላሉበት ፈታኝ ሁኔታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
Via BBC

በአዲስ አበባ መጪዎቹ 3 ወራት ውስጥ 400 አዲስ አውቶቢሶችን ወደስራ እንደሚያስገባ ማስገባት እየሰራ መሆኑን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከዚህ ቀደም 560 አውቶቢሶችን ወደስራ ማሰማራቱን ገልፆ በመጪዎቹ 3 ወራት ውስጥ ተጨማሪ 400 አዲስ አውቶቢሶችን ለማስገባት እየሰራ መሆኑን ነው የገለፀው፡፡ባሳለፍነው ሳምንት 560 አውቶቢሶች ወደስራ ይገባሉ ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም በቅድሚያ 420 የሚሆኑ አውቶቢሶች ብቻ ነበሩ ስራ የጀመሩት፡፡
ቀሪዎቹ ከዉል ጋር ተያይዞ በነበረ ችግር ምክንት የዘገዩ ሲሆን አሁን ላይ ሁሉም ወደስራ መግባታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ጉዳች ዳይሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ ገልፀዋል፡፡አቶ አረጋዊ አክለውም የትራንስፖርት ችግሩን ለመፍታት ከዚህ አመት ጀምሮ 3 ሺህ ባሶችን ወደ ስራ ለማስገባት በሂደት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡አሁን ላይ ወደስራ የገቡ አውቶቢሶችን አፈፃፀም በማየት በሂደት ላይ ካሉት 3 ሺህ አውቶቢሶች መካከል 400 ዎቹን እስከ ቀጣዩ ታህሳስ ወር ድረስ ተገጣጥመው ያለቁ አውቶቢሶች ካሉ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ነው የገለፁት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከጎዴ ቀላፎ ፈርፈር ሎት ያለውን የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በይፋ አስጀመሩ! ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንባታውን ያስጀመሩት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ጋር ዛሬ በጎዴ ከተማ በመገኘት ነው፡፡ የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ የአገሪቱን የወጪና ገቢ ንግድ በእጅጉ እንደሚያሳልጥ ታምኖበታል፡፡ Via ENA @YeneTube @FikerAssefa
በሶማሌ ክልል የጎዴ ከተማን የልማት ማዕከል ለማድረግ የሚያስችሉ የመንገድ ፕሮጀክቶች ተጀመሩ!
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሶማሌ ክልል የጎዴ ከተማን የልማት ማዕከል ለማድረግ እና የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችሉ የመንገድ ፕሮጀክቶችን አስጀመሩ።
ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የሚደረግባቸው እነዚህ ፕሮጀክቶች 4 አመታት ውስጥ የሚጠናቀቁ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልፀዋል።
ዛሬ በሶማሌ ክልል ከ300 ኪ.ሜ. የሚበልጥ ርዝማኔ ያላቸውን መንገዶች ግንባታ አስጀምረናል።
ከእነዚህም ውስጥ ከ270 ኪ.ሜ. በሚበልጥ ርዝማኔው የጎዴ -ቀላፎ ሎት -1 ፣ የጎዴ -ሐርጌሌ ሎት እና የያአሌ -ዳና ሎት -3 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ያካተተ ነው።

የታዋቂው ሰአሊ ሎሬት ሻምበል የክብር ዶክተር አርቲስት ለማ ጉያ የቀብር ስነስርዓት በቢሾፍቱ ከተማ እየተከናወነ ይገኛል።
ፎቶ: OBN
@YeneTube @FikerAssefa
ፎቶ: OBN
@YeneTube @FikerAssefa