YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአስተዳደር ወሰን፣ የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚደረገው አጠቃላይ አገራዊ የዳሰሳ ጥናት በመጪው ግንቦት ወር እንደሚጠናቀቅ የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ገለጸ።

በክልሎች መካከል የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸው ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በጥናቱ ይካተታሉ ተብሏል።ኮሚሽኑ የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ ክንውኑን በተመለከተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ዶክተር ጣሰው ገብሬ እንዳሉት፣ ኮሚሽኑ በአስተዳደር ወሰን፣ በማንነትና ራስን በራስ ማስተዳደር ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር በማቅረብ ለመንግስት ምክረ ሃሳብ ያቀርባል።

በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከ28 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ከ70 በላይ ተመራማሪዎች የሚሳተፉበት አገራዊ ጥቅል የምርምር ሥራ 40 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወል ሁሴን በበኩላቸው ÷ የአስተዳደር ወሰን የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ ዘላቂ መፍትሄ የሚመጣው ‘አንተም ተው አንተም ተው’ በሚል ሳይሆን በጥናት ላይ በተመሰረተ ውጤት ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ችግርን ለማቃለል የተከራያቸው 560 አውቶብሶች የአዋጭነት እና የግልጽነት ጥያቄ እየተነሳባቸው እንደሆነ ተሰምቷል። ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በቀድሞው ምክትል ከንቲባ ጊዜ አዋጭ አይደለም ተብሎ የተተወውን የአውቶብስ ኪራይ ከጥቅምት 9 ጀምሮ ተግባራዊ አድርገውታል።ከግል ባለሃብቶች ለተገኙት ያገለገሉ አውቶብሶቹ ኪራይ አስተዳደሩ ጨረታ ሳያወጣ ለእያንዳንዱ አውቶብስ ወርሃዊ የኪራይ ሒሳብ በማውጣት ነው ውሉ ከከተማዋ የትራንስፖርት ቢሮ ጋር የተፈጸመው። አስተዳደሩ ለሁሉም አውቶብሶች ኪራይ በወር 71 ሚሊዮን ብር ያወጣል።

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 511 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,884 የላብራቶሪ ምርመራ 511 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ8 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,445 አድርሶታል።በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 818 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 48,968 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 94,218 ደርሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ ማካሄድ ጀምረዋል!

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች የሶስትዮሽ ስብሰባ ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በቨርቿል ማካሄድ ጀምረዋል።የዛሬው ስብሰባ የተካሄደው በደቡብ አፍሪካ የዓለምአቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም ለሃገራቱ በጻፉት ደብዳቤ ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት ነው።በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ተጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።ስብሰባው በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር እየተካሄደ ያለው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የተመለከተው የሶስትዮሽ ድርድር በሚቀጥልበት ጉዳይ ዙሪያ የሚመክር እንደሚሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በድርድሩ አካሄድና ጊዜ ሰሌዳ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ተግባቡ!

ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚያደርጉት ድርድር ዛሬ የጀመረ ሲሆን ሀገራቱ በድርድራቸው፣በድርድሩ አካሄድና በጊዜ ሰሌዳ ላይ ሰምምነት ላይ ለመድረስ መግባባታቸውን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይና ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል።ሀገራቱ ልዩነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር የውጭ ጉዳይና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው እንደሚገናኙ መግለጫው ጠቅሷል።

የመጀመሪያው ስብሰባ በሱዳን ሰብሳቢነት ይካሄዳል ተብሏል። በኢትዮጵያ አለመሰማማት ምክንያት የአሜሪካው ድርድር ከተቋረጠ በኋላ ድርድሩ በሶስቱም ሀገራት ሰምምነት በአፍሪካ ህብረት መእቀፍ እየተካሄደ ይገኛል።

Via Al ain
@YeneTube @FikerAssefa
ከ14 በላይ የነዳጅ ማደያ ያላት ሐዋሳ ከተማ በነዳጅ ጥቁር ገበያ እየታመሰች ነው።

[በኢትዮ ኤፍ ኤም]

በከተማዋ አንድ ሊትር ቤንዚን እስከ 50 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው።ከተለያዩ ነዳጅ ማደያዎች በሌሊት በበርሜል እና ጀሪካን ቤንዚን በየመንደሩ እየተሸጠ በመሆኑ ከማዳያ ነዳጅ ለመቅዳት ለሰታት ሰልፍ ለመሰለፍ መገደዳቸውን አሽከርካሪዎች ተናግረዋል፡፡ከየመንደሩ እና ነዳጅ ማደያ አካባቢ ቤንዚን የመግዛትና የመጠቀም ሁኔታው በመኖሩ የባጃጅ እና የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች መንግስት ባስቀመጠው የነዳጅ ዋጋ ተመን ለመግዛት ከአቅም በላይ እንደሆባቸውም ነግረውናል።

ጠዋትም መጣን ያው ነወ ከሰዓት ይቀንሳል ብለን መጣን ያው ነው፣ ሶስት አራት ነዳጅ ማደያ ላይ ነዳጅ መኖሩን አረጋግጠናል የሚሉት እነዚህ ሾፌሮች መንግስት ህግ እንዲያስከብር ጠይቀዋል።ኢትዮ ኤፍ ኤም የአዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ብርሃኑ ለታሞን በጉዳዩ ዙሪያ ጠይቋል።በከተማዋ የነዳጅ አቅርቦት እና ማጓጓዝ ላይ ችግሮች ቢኖሩም በሕገ ወጥ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች የሚወጣውን ነዳጅ መልሰው ለጥቁር ገበያ ሚያቀርቡት እራሳቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ሾፌሬች ናቸው ብለዋል።

ሀላፊው የአጠቃቀም ችግርም መኖሩን ገልጸው ከ 6 በላይ የከተማዋ አዋሳኝ ወረዳዎች ነዳጅ ማደያ ባለመኖሩ ለጥቁር ገበያ መስፋፋት ምክንያት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡በአዋሳ ከተማ የነዳጅ አቅርቦትና ሥርጭት ላይ አዲስ የቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት ከፖሊስ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ግብረ ሐይል በማቋቋም ሕገወጦች ላይ አስተማሪ ዕርምጃዎች ለመውሰድ እየተሰራ መሆኑን አቶ ብርሃኑ ገልፀዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
በኤርትራ ቢራ በኩፖን መሸጥ ተጀመረ!

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት ምግብ ቤቶች፣ ካፌዎችና መጠጥ ቤቶቿን በዘጋችው ኤርትራ ቢራ በኩፖን (መሸመቻ ካርድ) መሸጥ መጀመሯ ተገልጿል።ብቸኛው ሜሎቲ ቢራ በሱቆች በመሸመቻ ካርድ አማካኝነት እየተሸጠ እንደሚገኝም ቢቢሲ ትግርኛ ከምንጮች ያገኘው መረጃ አመላክቷል።ደንበኞች ቢራውን ማግኘት የሚችሉት በሱቆች ብቻ ሲሆን አንድ ቢራም በአስር ናቅፋ (ወደ 25 ብር በሚጠጋ) ዋጋ እንደሚሸጥ ተገልጿል።

ኩፖኑን (የመሸመቻ ካርዱን) የያዙ ሰዎችም በአንድ ሳምንት መግዛት የሚፈቀድላቸው የቢራ ብዛት ስምንት ጠርሙስ ብቻ ነው።በኤርትራ ዳቦ፣ ዘይት፣ ስኳርና ማሽላ የመሳሰሉትን መሰረታዊ ሸቀጦች በስርጭት (በመሸመቻ) ካርድ በቀበሌዎች ሲሆን መግዛት የሚቻለው፤ መጠኑም በቤተሰብ ቁጥሩ ይወሰናል።በተለይም ዳቦ ለመግዛት በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዳቦ ቤቶች ተመዝግበውም በየእለቱ ጧት የቤተሰባቸውን ቁጥር መሰረት ባደረገ መልኩም እንዲገዙ ይፈቅድላቸዋል።ሜሎቲ ቢራም በተመሳሳይ መልኩ እንደ ዳቦና ስኳር በሱቆች በመሸመቻ ካርድ መሸጡ አንዳንድ የመጠጥ ቤት ባለቤቶችን ቅር አሰኝቷል።

በአስመራ የሚገኝ ስሜ አይጠቀስ ያለ አንድ የመጠጥ ቤት ባለቤት ነጋዴ "የንግድ ፍቃድ ያለን ሰዎች ንግድ ቤታችሁን ዝጉ ተብለን፤ ለሰራተኞች ደሞዝ ክፈሉ ተብለን ስናበቃ እኛ ልንሸጠው የሚገባ ቢራ በሱቆች እየተሸጠ ይገኛል" በማለት ለቢቢሲ ተናግሯል።ነጋዴው እንደሚለው መጠጥ ቤቶቹ የተዘጉት የሰዎችን መሰባሰብ ለመቀነስ መሆኑን ቢረዳም ቢራው በሱቆች መሸጥ ለመጀመሩ ምክንያቱ ግልፅ አልሆነለትም።መጠጥ ቤቶቹ ሱቆች አሁን እያደረጉት እንዳለው ቢራ መሸጥ ይችሉም እንደነበር ይናገራል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
 የሳዑዲ ዓረቢያን የመኖሪያ ፈቃድ ተላልፈዋል በሚል ላለፉት ሳምንታት ከልጆቻቸው ጋር ተይዘው ሪያድ ባሉ ፖሊስ ጣቢያዎች የቆዩ 82 ዜጎች እንዲፈቱ አደረገ።

እነዚህ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በከተማው ውስጥ በሚገኙ 5 ፖሊስ ጣቢያዎች በጊዜያዊነት ከሶስት ሳምንታት በላይ እንዲቆዩ ተደርገዋል፡፡በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዳስታወቀው ከሚመለከታቸው የሀገሪቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ዜጎቹ እንዲፈቱ ተደርጓል፡፡ከቤተሰቦቻቸው ጋር ታስረው የነበሩ ህፃናትም የህክምና ክትትል እና ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉንም አሳውቋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ንግግር በአገር ሉአላዊነት ላይ የተቃጣ በመሆኑ ይህንን ተከትሎ ለሚመጣ ነገር ሁሉ አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዝግጁ መሆኑን አስታወቀⵆ

የኢፌዴሪ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ንግግር ሀያል አገርን እመራለሁ ከሚል ፕሬዝደንት የሚጠበቅ አይደለም።የአንድን አገር ሉአላዊነት በንግግርም ቢሆን መጣስ ከባድ ጥፋት በመሆኑ ይህንን ተከትሎ ሊመጣ የሚችል ማንኛውንም አይነት ጥቃት ለመመከት አየር ሃይሉ ሙሉ ዝግጁነት አለውⵆ

እንደ ሜጀር ጀነራል ይልማ ገለጻ፤ ለፕሬዝዳንቱ ንግግር የአገር መሪዎችና ዲፕሎማቶች በዲፕሎማሲው መድረክ መልስ እንደሚሰጡ ሁሉ፤ አየር ሃይሉ ደግሞ ፕሬዝደንቱ ለጎሰሙት የጦርነት ነጋሪት አስፈላጊውን መልስና እርምጃ ይወስዳልⵆ

“ከአባይ ወንዝ ጋር በተያያዘ ጭቅጭቅ እያነሱ ያሉ አካላት ከ 2 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘው በእግረኛ ጦር ይዋጋሉ ብለን አናስብም፤ በመሆኑም ወደ ግጭት ከተገባም ግጭቱ በቀጥታ ከአየር ሃይል ጋር እንደሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ደረጃ እነሱ ምንድን ነው ያላቸው? የመሳሪያ የቴክኖሎጂያቸው፤ የሰው ሃይል ብቃት የስልጠና ደረጃቸው ምን ይመስላል? የሚለውን ለይተን እናውቃለን። ከዚህም ባሻገር 24 ሰዓት ዓይናችን የህዳሴው ግድብ ላይ ነው” ብለዋል አዛዡ።

የኢትዮጵያን የአየር ሃይልብቃት እኛ ከምናውቀው በላይ እነሱ ጠንቅቀው ያውቁታል፤ ስለወደዱን ወይም አቋማችንን ስለተቀበሉ ሳይሆን ሁኔታዎች ወዴት ሊሄዱ እንደሚችሉ ጠንቅቀው ያስለሚያውቁም ጭምር የሚፈጠር ጉዳይ አይኖርም ያሉት ሜጀር ጀነራል ይልማ፤ አየር ሃይሉም ለ24 ሰዓታት ለሰባት ቀናት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጣለሁ ብለዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ህዝብ ከሌለው ሀብት ላይ ቆጥቦ እየገነባው ያለው ፕሮጀክቱ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ቢሆንም፤ አየር ሃይሉ ግን በጠቅላላው የአገሪቷን መሰረተ ልማቶች የፖለቲካ የኢኮኖሚ እንዲሁም ወታደራዊ ማዕከሎችን በንቃት እንደሚጠብቅም አረጋግጠዋልⵆ

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል 127 ሺህ ዜጎች በወባ በሽታ መጠቃታቸዉን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

በአማራ ክልል ባለፉት ወራቶች የወባ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ ስርጭቱ እየጨመረ ነዉ ተብሏል፡፡በዚህም ከደሴ በስተቀር በክልሉ በሁሉም ዞኖች በሽታው መስፋፋቱ ነው የተነገረው፡፡የክልሉ የወባ በሽታ ማጥፋት ፕሮግራም አማካሪ አቶ አማረ ደስታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥም ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች በበሽታው እንደተጠቁ ነው የተናገሩት፡፡ከባለፈው የ2012 የሩብ አመት ሲነጻጸርም የአራት በመቶ ጭማሪ እንዳለውም አማካሪው ተናግረዋል፡፡

የበሽታው ስርጭት በከፍተኛ መጠን እየተስፋፋ ያለው በምእራብ አማራ ሲሆን በምስራቅ አማራ ስርጭቱ ውስን ነው ብለውናል፡፡በምእራብ አማራ ምእራብ ጎንደር፣ ሰሜን ጎንደር እና ምስራቅ ጎጃም፣ ምእራብ ጎጃም እንደዚሁም ሰሜን ሸዋ ዞንም በሽታው በስፋት መስፋፋቱ ተገልጿል።90 ከመቶ የወባ ስርጭቱ ያለው በምእራብ አማራ እንደሆነም አቶ አማረ ተናግረዋል፡፡በነዚህ ዞኖች የበሽታው ስርጭት የጨመረበት ዋነኛ ምክንያት የአካባቢው የአየር ሁኔታ ሲሆን፣ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የውሀ ማቆሪያ ቦታዎች በትክክል ባለመሰራታቸውና የወባ መከላከያ አጎበር በትክክል ካለመጠቀም ጋር በተያያዘ ነው ስርጭቱ የጨመረው ተብሏል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ሁለት የትምህርት ሚኒስቴር ባልደረቦች ለስራ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት መገደላቸውን ሚንስትር መስሪያ ቤቱ አስታወቀ!

መስሪያ ቤቱ ያወጣው የሃዘን መግለጫ የሚከተለውን ይመስላል:

"የሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የስራ ባልደረባ የነበሩት አቶ ሙላት ጸጋዩ እና አቶ አበባው አያልነህ ለስራ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት ድንገት ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡በዚህም የሚኒስቴር መስሪያቤታችን አመራሮች እና ሰራተኞች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን፡፡ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቸው እና ለ ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡"

ትምህርት ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
ፊሊፒንስ ውስጥ አንድ ፖሊስ በአውራ ዶሮ መገደሉ ተሰምቷል።

የሁለት አውራ ዶሮዎችን ጥል መመልከት የስፖርት ክዋኔን እንደመከታተል በሚቆጠርባት ፊሊፒንስ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ውድድሩ ሰውን በብዛት የሚያሰባስብ በመሆኑ ተከልክሎ ነበር። ይህን ክልከላ በመተላለፍ እየተካሄደ ያለን ውድድር ለማስቆምና ዶሮዎቹን ለመገላገል ጣልቃ የገባው ፖሊስ ነው እንግዲህ ህይወቱን ያጣው። ዶሮዎቹ በተፈጥሮ ከተሰጣቸው ጥፍሮች በተጨማሪ ከላይ በምስሉ ላይ እንደሚታየው ለቀዶ ጥገና የሚያገለግል ምላጭ አይነት ስለት እግሮቻቸው ላይ ታስሮላቸው ነው ወደ ሜዳ የሚገቡት። በዚህ ምላጭ ነው እንግዲህ ይህን ለግልግል የገባውን ፖሊስ አንደኛው አውራ ዶሮ ቆርጦት ከፍተኛ ደም ስለፈሰሰበት ህይወቱ ሊያልፍ የቻለው።የአካባቢው ፖሊስ አዛዥ ለአጃንስ ፍራንስ ፕረስ እንዳለው "ለ25 አመታት በዚህ ስራ ላይ ቆይቻለው፣ የፖሊስ ባልደረባ ላይ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሲፈጠር ግን የመጀመሪያው ነው"። ፊሊፒንስ ይህ ውድድር እንደ ባህል ከሆነባቸው ሀገራት አንዷ እንደሆነችና ከፍተኛ የሆነ ውርርድ የሚደረግበት ዘርፍ መሆኑን ጠቅሶ አር ቲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአሠሪ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞች ቅሬታ አቀረቡ!

ኤጀንሲዎች የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅን ባከበረ መንገድ እየሠሩ ባለመሆኑ የአሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞች ቅሬታ አቀረቡ።ከዚህ ቀደም ለደመወዝ ወለል፣ ለሙያ ደህንነት እንዲሁም በሠራተኞች ላይ ለሚደርሰው የመብት ጥሰት በሕግ አግባብ መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችል አዋጅ ቢጸድቅም ትግበራው ላይ ከፍተኛ ክፍተት መኖሩን ሠራተኞቹ ገልጸዋል።
ቅሬታ ያቀረቡት ሠራተኞች ከኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን እና ሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ አዋጁ ከጸደቀ በርካታ ወራትን ያስቆጠረ ቢሆንም በተለይም በሠራተኞች ደመወዝ አከፋፈል ላይ የመብት ጥሰት እንደሚፈጸም ተናግረዋል።በአዋጁ ላይ የተቀመጡትን የአሠሪ እና ሠራተኛ ደንቦች የማስከበር እና በሕግ አግባብም ተጠያቂ የማድረግ ሥራ መሠራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ራማፎሳ ወደ ለይቶ ማቆያ ገቡ!

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ በኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ስላላቸው ራሳቸውን ለይተው እያቆዩ መሆኑን የፕሬዝደንቱ ቢሮ አስታወቀ።ፕሬዝደንቱ ራሳቸውን ለይተው እንዲቆዩ ያስገደዳቸው ቅዳሜ ምሽት እርሳቸው በተገኙበት የእራት ግብዣ ላይ የተገኘ ሌላ እንግዳ በኮቪድ-19 መያዙ መረጋገጡን ተከትሎ ነው።
በእራት ግብዣው ላይ ከ35 በላይ ሰዎች ጆሃንስበርግ ከተማ በሚገኝ ሆቴል ተገኝተው ነበር ተብሏል።“ፕሬዝደንቱ የበሽታውን ምልክት እያሳዩ አይደለም። የጤና ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብን በመከተል ፕሬዝደንቱ ምልክት የሚያሳዩ ከሆነ ምርምራ ያደርጋሉ” ይላል ከፕሬዝደንቱ ቢሮ የወጣው መግለጫ።በእራት ግብዣው ላይ የተገኙ እንግዶች በሙሉ የሰውነት ሙቀታቸው ተለክቶ እንደነበረ እና አካላዊ ርቀታቸውንም ጠብቀው እንደነበረ ተጠቁሟል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ሁለት የትምህርት ሚኒስቴር ባልደረቦች ለስራ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት መገደላቸውን ሚንስትር መስሪያ ቤቱ አስታወቀ! መስሪያ ቤቱ ያወጣው የሃዘን መግለጫ የሚከተለውን ይመስላል: "የሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የስራ ባልደረባ የነበሩት አቶ ሙላት ጸጋዩ እና አቶ አበባው አያልነህ ለስራ ወደ አፋር ክልል በሄዱበት ድንገት ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡በዚህም የሚኒስቴር መስሪያቤታችን…
በአፋር ክልል በስራ ላይ እያሉ ህይወታቸውን ላጡ የትምህርት ሚንስትር ሰራተኞች ሽኝት ተደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩ ሁለት ሰራተኞች በአፋር ክልል በስራ ላይ ሳሉ ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸውን ማጣታቸውን ቀደም ሲል ዘግበን ነበር።የሰራተኞቹ አስክሬን ከአፋር ክልል ዛሬ ወደ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች ወደየአካባቢያቸው ሽኝት ተደርጎላቸዋል።የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ፒ ኤች ዲ) በሽኝቱ ላይ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን በመመኘት የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
በወቅቱ የመቁሰል አደጋ ያጋጠመው ሰራተኛም የህክምና ክትትል እየተደረገለት እንደሆነ ተገልጿል።

[MoE]
@YeneTube @FikerAssefa
በባህርዳር ከተማ በዛሬዉ እለት ሰልፍ የወጡ ነዋሪዎች በክልሉ ልዩ ሃይል ተበተኑ።

በዛሬዉ እለት በባህርዳር ከተማ በተላያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚፈጸሙትን ብሄር ተኮር የሆነ ጥቃት በመቃወም ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው እንደነበር ከስፍራዉ የደረሰ መረጃ ያሳያል። ስማቸዉን መግለጽ ያልፈለጉ የከተማዉ ኑዋሪ ለአዲስ ዘይቤ እንደተናገሩት ከሆነ በከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ በሚበዛበት ፓፒረስ ሆቴል አካባቢ የተሰበሰቡት ሰልፈኞቹ በክልሉ ልዩ ሃይል እንደተበተኑ ተናግረዋል። አያይዘዉም ምንም እንኳን ጠዋት ላይ የንግድ እንቅስቃሴዎች ቆመዉ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን በከተማዋ የተለመደዉ እንቅስቃሴ ቀጥለዋል ብለዋል። " ወደከተማዉ የሚገቡ መንገዶች ላይም የጸጥታ ሃይሎች ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉ ነበር በዛ ላይ በከተማዉም ብዛት ያለዉ የጸጥታ ሃይል ተሰማርቶ ነበር" ሲሉም አክለዋል።

Via Addis Zeybe
@YeneTube @FikerAssefa
ኳታር በተለያዩ 10 በረራዎች ለመብረር የተዘጋጁ ሴቶች በዶሃ አየር ማረፊያ 'አስነዋሪ' ፍተሻ ተደርጎባቸዋል መባሉን አጣራለሁ አለች።

"በጣም አስነዋሪ" የተባለው ፍተሻ ሴቶቹ ላይ የተደረገው በአየር ማረፊያው መጸዳጃ ቤት ውስጥ አንዲት ጨቅላ ልጅ ተጥላ መገኘቷን ተከትሎ ነበር።ሴቶቹ የተፈተሹት በቅርቡ ልጅ ስለመውለዳቸው የሚያመላክት ምልክት ለማግኘት ነበር ተብሏል።ፍተሻ ከተደረገባቸው ሴቶች መካከል ቢያንስ 18ቱ የአውስትራሊያ ዜጎች መሆናቸውን የአውስትራሊያ መንግሥት አስታውቋል።ይህን ተከትሎም የአውስትራሊያ መንግሥት ሴቶቹ ለፍተሻ ልብሳቸውን እንዲያወልቁ ተደርገዋል፤ ይህን 'በጣም አስነዋሪ' ፍተሻን በተመለከተም የኳታር መንግሥት ማብራሪያ ይስጥ ሲል ጠይቋል።

አውስትራሊያ ጉዳዩን ወደ ፌደራል ፖሊሷ መርታዋለች።የኳታር መንግሥት ለደርጊቱ ይቅርታ ጠይቆ ጨቅላዋ ደህንነቷ ተጠብቆ እንደሚገኝ አስታውቋል።ጨቅላዋ በፕላስቲክ ተሸፍና መጣሏን እና ወላጅ እናቷን ለማግኘት የተደረገ ጥረት መሆኑንም የኳታር መንግሥት አስታውቋል። ጨምሮም ፍተሻወን ማድረግ ያስፈለገው ጥፋተኛውን ሰው ለመለየት ነው፤ በዚህ ፍተሻ የተበሳጩ ሰዎችን ይቅርታ እጠይቃለሁ ብሏል።የምርመራው ውጤት ሲጠናቀቅ ውጤቱን ለሌሎች መንግሥታትም አሳውቃለሁ ብሏል የኳታር መንግሥት።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ኮኬይን የተባለውን አደገኛ ዕፅ ስታዘዋውር የተገኘች የታይላንድ ዜጋ በቁጥጥር ስር ዋለች!

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር አደገኛ ዕፅ ስታዘዋውር የተገኘችውን ታይላንዳዊት በቁጥጥር ስር አዋለ፡፡በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የኢንተለጀንስ አደገኛ ዕፅና ሬዲዮ መገናኛ ዳይሬክቶሬት ስር የሚገኘው የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ምክትል ዳይሬክቶሬት ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ትናንት ከምሽቱ አራት ሰዓት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡፡

ተጠርጣሪዋ ከአዲስ አበባ ወደ ታይላንድ ባንኮክ ጉዞ ማድረግ ላይ የነበረች ሲሆን እጅ ከፍንጅ መያዟን የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር መንግስትአብ በየነ ገልጸዋል፡፡የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዋ አደንዛዥ ዕፁን በልብስ ውጫዊ የሻንጣ አካል በመደበቅ ለማሳለፍ ሙከራ ብታደርግም ሁለቱ የፀጥታ አካላት ባደረጉት ክትትል ተጠርጣሪዋን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡በእጇ የተገኘው 2 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
የነቢዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) 1495ኛው ልደት በዓል በተመለከተ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት::

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa