YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሱዳን ከአሜሪካ የሽብር መዝገብ ስሟ እንዲፋቅ በዩኤኢ ልትወያይ ነው!

የሽግግር ምክርቤቱ ኃላፊ ጄነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሃንና የፍትህ ሚኒስትሩ ከሱዳን ወደ ዩኤኢ በሚሄደው ቡድን ውስጥ ተካተዋል፡፡የሱዳን የሽግግር መንግስት ሱዳንን ከዝርዝሩ ለማስጠፋት እየጣረ ሲሆን ይህም ሀገሪቱ የውጭ ብድር ልታገኝ የምትችልበትን እድል ያመቻችላታል ተብሏል፡፡

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa
የሱልጣን ሐንፍሬ ዓሊሚራህ አስክሬን አፋር ሰመራ ሲገባ አቀባበል ተደረገለት!

ባደረባቸው ህመም ትላንት ህይወታቸው ያለፈው የአፋሩ ሱልጣን ሐንፍሬ ዓሚራህ ሀነፍሬ አስክሬን ዛሬ ረፋድ ሰመራ ከተማ ገብቷል።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ እና ሌሎች የፈደራል እና የክልሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትም አስሬኑን አጅበው አፋር ገብተዋል።የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባና ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናትም አስክሬኑ ሰመራ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርስ አቀባበል አደርገውለታል።የሱልጣን ሐንፍሬ ዓሊሚራህ ስርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በአሳይታ ከተማ ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
በትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ትምህርት ለመጀመር ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሆነ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ!

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለ 7 ወራት የተቋረጠውን መደበኛ ትምህርት ለማስቀጠል ትምህርት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡መንግስት በትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣ የውሃ እና የእጅ ማፅጃ አቅርቦቶችን በማሟላት እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን የማፅዳት ስራዎችን በማከናወን መደበኛ ትምህርት እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ትምህርት ቤቶች ሲከፈቱ ተማሪዎች እንደየ ደረጃው ወደ ክፍል ገብተው ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ የገለፁ ሲሆን ትምህርት ሲጀመርም በአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚጀመር መሆኑን እና በቀጣይም ሌሎች የትምህርት ክፍሎች ወደ መደበኛ ትምህርቱ እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የተቀመጡ ጥንቃቄዎች ሙሉ በሙሉ የሚተገበሩ መሆኑን እና የትምህርት አሰጣጡ ሂደትም በፈረቃ የሚሰጥ መሆኑንም ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡

የፈረቃ ስርዕቱም እንደየአካባቢው ሁኔታ ከ 2 እስከ 3 ሊሆን እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በትምህርት ቤት ውስጥ መምህራኖች ትልቁን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን ወላጆችም ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ሲልኩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።መደበኛ ትምህረቱም መንግስት ውሳኔ እንዳሳለፈ እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመተግበር ትምህርት ቤቶችን መክፈት እንደሚቻል ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ምክረ ሃሳብ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

[MoE]
@YeneTube @FikerAssefa
የቻይናውን መተግበሪያ ዊቻት አሜሪካ ለማገድ ያደረገችውን ጥረት ፍርድ ቤት አስቆመ።

ዳኛ ሎረል ቤለር፤ አሜሪካ ዊቻትን ለማገድ መሞከሯ ሕገ መንግሥቱ የደነገገውን የንግግር ነጻነትን ይጻረራል ብለዋል።የአሜሪካ የንግድ ተቋም፤ ዊቻት በአገሪቱ የመተግበሪያ መጫኛዎች ላይ እንዳይገኝ ውሳኔ አስተላልፏል።ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ መተግበሪያው ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት ነው ብለዋል። መተግበሪያው የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃ ለቻይና መንግሥት አስተላልፎ ይሰጣል ሲሉም ተደምጠዋል።ቻይና እና የዊቻት ድርጅትም ክሱን አጣጥለዋል። ዊቻትን የሚያስተዳድረው ቴንሴንት አሜሪካ መተግበሪያውን ለማገድ ማሰቧ አሳዛኝ ነው ብሏል።

ውሳኔው የተላለፈው ቲክቶክ ሥራውን መቀጠል እንዲችል ከአሜሪካዎቹ የቴክኖሎጂ ተቋሞች ኦራክል እና ዋልማርት ጋር ከተስማማ በኋላ ነው።
ትራምፕ ዊቻትን ለማገድ ሲወስኑ፤ አሜሪካ የሚገኙ የዊቻት ተጠቃሚዎች ክስ መስርተዋል።የአሜሪካ የፍትሕ ተቋም የትራምፕን ውሳኔ ማገድ ፕሬዝዳንቱ የአገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ትግል ያደናቅፋል ብሏል።ሆኖም ግን የሳን ፍራንሲስኮው ዳኛ “ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሆኑ የቻይና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በተመለከተ የቀረበው ማስረጃ የሚያስኬድ ቢሆንም ስለ ዊቻት ግን የተሟላ ማስረጃ አልቀረበም” ብለዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ጉባኤ በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2012 የስራ ዘመን ኮሮናን ለመከላከል ያከናወኗቸው አበይት ተግባራትና ያስገኙት ውጤት ይገመገማል።ትናንት በተጀመረው በዚሁ ጉባኤ የዘንድሮ ትምህርት በሚጀመርበት ሁኔታ ላይ ጉባኤው እንደሚመክርና መረሃ ግብሩ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።ከጉባኤው ጎን ለጎን ኮሮናን ለመከላከል በዩኒቨርስቲዎች የተሰሩ የፈጠራ ምርቶችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ በጅማ ዩኒቨርሲቱ ዋናው ግቢ ተከፍቷል።የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምር፣ በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ያከናወኗቸውን አበይት ተግባራት ይዘው መቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል ።

@YeneTube @FikerAssefa
በተያዘው አመት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር መታቀዱ ተገለጸ!

በተያዘው አመት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ማቀዱን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ገለፀ፡፡የፌዴራል የከተሞች የስራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በ2013 በጀት አመት እቅዱ ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዶክተር መስፍን አሰፋ በተያዘው አመት 1∙5 ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር መታቀዱን አስታውቀዋል።ከሚፈጠረው የስራ እድል ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነው በቋሚነት እንደሚሆን ነው የገለፁት።በሌላ በኩል 72 ተጨማሪ ከተሞችን በምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ለማካተት መታቀዱን አስታውቀዋል።ይህም ከዚህ በፊት በምግብ ዋስተና የተካተቱ 11 ከተሞችን ወደ 83 በማሳደግ በሁሉም ክልሎች ከ472 ሺህ በላይ ዜጎች በአካባቢ ልማት፣ ለ152 ሺህ ዜጎች በቀጥታ ልማትና 22 ሺህ ልዩ ድጋፍ የሚሹ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተመላክቷል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
እነ አቶ ጃዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባና ሀምዛ አዳነን ጨምሮ 18 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ተመሰረተባቸው!

እነ አቶ ጃዋር መሀመድ፣ በቀለ ገርባና ሀምዛ አዳነን ጨምሮ 18 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ተመስርቶባቸዋል።ተከሳሾቹ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ህገ መንግስትና ጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሱ ደርሷቸዋል።ፍርድ ቤቱ ማንነታቸውን የማረጋገጥ ስራ የሰራ ሲሆን፥ በዚህም አቶ ጃዋር እድሜያቸው 34 መሆኑን የፖለቲካ አመራር መሆናቸውን እና ባለትዳርና 1 ልጅ አባት መሆናቸውን እንዲሁም በሂዩማን ራይት ማስተርስ መያዛቸውን በአዲስ አበባ ኗሪ መሆናቸውን አስመዝግበዋል።አቶ በቀለ ገርባም የአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪ መሆናቸውን፤ መምህርና እድሜያቸው 60 ዓመት እንደሆነ እንዲሁም ባለትዳርና የ6 ልጆች አባት መሆናቸውን አስመዝግበዋል።

ሌሎችም በተመሳሳይ ማንነታቸውን አስመዝግበዋል።ከምክትል ኢንስፔክተር እስከ አምሳ አለቃ ደረጃ ማእረግ ያላቸው 6 ግለሰቦችም ማእረጋቸው በክሱ ባለመካተቱ ማረጋቸው እንዲመዘገብ አድርገዋል።በሌላ ክስ ተመስርቶባቸው ማረሚያ ቤት የሚገኙት አቶ ደጀኔ ጣፋ እና መስተዋርድ ተማም በችሎቱ አልቀረቡም።እንዲሁም አቶ ደጀኔ ጉተማ፣ ብርሀነ መስቀል አበበ፣ ፀጋዬ አራርሳ ያልቀረቡ ሲሆን፥ በችሎት ለተጠራው የኦ.ኤም.ኤን ተወካይ የሆነ እኔነኝ ብሎ ያስመዘገበ ሰው የለም።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ ላይ እንደየተሳትፏቸው በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 240 በመተላለፍ ብሔርን እና ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ አንዱ ወገን በሌላው ወገን ላይ እንዲነሳሳ በማድረግ፣ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012፣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 761/2004 እና የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1177/2012 በመተላለፍ በፈፀሙት ወንጀል ነው መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 260215 አስር ተደራራቢ ክሶች ያስከፈተው።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በመተከል ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ከተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ ተሳተፈዋል የተባሉ እስካሁን 358 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ አበራ ባያታ፣ በቅርቡ በመተከል ዞን የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ለማረጋጋት እና በቀጥታም ሆነ በተለያዩ መንገዶች በተዘዋዋሪ ተሳትፎ ባደረጉ አካላት ላይ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የክልሉና የፌዴራል መንግስት በትኩረት እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ከሰሞኑ በመተከል ዞን ቡለን እና ወምበራ ወረዳ አንዳንድ ቀበሌዎች ከነበረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ አየተሠራ ባለው የሕግ ማስከበር ሥራ የተለያዩ ተሳትፎዎችን አድርገዋል የተባሉ ተጨማሪ 30 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አቶ አበራ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ተሳትፎ የነበራቸው 328 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር ያስታወሱት አቶ አበራ፣ ሰሞኑን በ2ቱ ወረዳዎች እየተሠራ ባለው የሕግ ማስከበር ሥራ ተጨማሪ 30 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል፡፡እስካሁን በተሠራው የህግ ማስከበር ሥራም 358 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታዬ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡

[የዞኑ መ/ኮሙኒኬሽን]
@YeneTube @FikerAssefa
"አቶ እስክንድር ነጋ በእስር ቤት ሆነውም ቢሆን የባልደራስ-መኢአድ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በሙሉ ድምጽ ወስኗል" - የባልደራስ - መኢአድ ጋራ ምክር ቤት

የባልደራስ-መኢአድ የጋራው ምክር ቤት በ09/01/2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የቅንጅቱን ፕሬዚዳንት ፣ ም/ል ፕሬዚዳንት እና ሥራ አስፈፃሚውን በሙሉ ድምፅ መርጧል፡፡የጋራ ምክር ቤቱ መስከረም 12/01/2013 ይፋ ባደረገው ጋዜጣዊ መግለጫው "በሀገራችን ኢትዮጵያ ለሶስት አስርት ዓመታት በተደረገው መራራ ትግል ውስጥ አቶ እስክንድር ነጋ አድልዎንና ኢፍትሃዊነትን በብዕራቸው በመታገል የሚታወቁት ናቸው። ነገር ግን ዛሬም እንደገና ለእስር የተዳረጉ ሲሆን ይህ ውንጀላና እስር በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ እንደሆነ የሚያምነው የባልደራስ -መኢአድ ከፍተኛው ምክር ቤት ጥልቅ ውይይት ካካሄደ በኋላ ክቡር አቶ እስክንድር ነጋ በእስር ቤት ሆነውም ቢሆን የባልደራስ-መኢአድ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ እኚህን የህዝብ ልጅና መሪ መንግስት በፍጥነት ከእስር እንዲለቅም ምክር ቤቱ በጽኑ አሳስቧል" ሲል የአቶ እስክንድርን በእሥር እያሉ በፕሬዚደንትነት መመረጥ አስታውቋል።

አያይዞም "ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ሰፊ ተሳትፎ የነበራቸውና በተደጋጋሚ ለእስር የተዳርጉትን የነፃነት ታጋዩን አቶ ማሙሸት አማረን በምክትል ፕሬዚዳንትነት የመረጠ ሲሆን አቶ ማሙሸት አማረ ለህግ የበላይነት ለዴሞከራሲ ስርአት ግንባታ የከፈሉትን ወደር የሌለው መስዋእትነትና ቁርጠኝነት የቅንጅቱ ምክር ቤት ያደነቀ ሲሆን በቀጣይነት ትግሉን በመምራት ቅንጅቱ በአሸናፊነት እንዲወጣ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርጉ ምክር ቤቱ እምነቱን ገልጿል" በማለት የምርጫ ውጤቱን ገልጧል።

[SBS Amharic]
@YeneTube @FikerAssefa
ከ24ቱ ተከሳሾች ውስጥ አቶ ጃዋር መሐመድ ብቻ በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ተገለፀ!

እነ አቶ ጃዋር መሐመድ በዛሬው ዕለት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ቀርበው የክስ ወረቀት ደርሷቸዋል፡፡በክሱ መሰረት ከ24ቱ ተከሳሾች አቶ ጃዋር መሐመድ ብቻ በሽብር ወንጀል መከሰሳቸውን በክሱ ላይ ተመልክቷል፡፡አቶ ጃዋር የሽብር ወንጀልን ለመፈፀም መሰናዳት በሚል ከቀረበባቸው ክስ በተጨማሪ፣ የብሔር ግጭት ማስነሳት፣ሕገ ወጥ የጦር መሳያ ይዞ መገኘትና በቴሌኮም ማጭበርበር የሚሉ ጭብጦችም በክሱ ላይ ይገኙበታል፡፡

በአቶ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አዳነን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾች ላይ የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳትና ህገ ወጥ የጦር መሳያ ይዞ በመገኘት በሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን፣8 ተከሳሾች ደግሞ በእርስ በርስ ግጭት ውስጥ ማነሳሳት እና መሳተፍ በሚል ክስ እንደቀረበባቸው የክስ ወረቀቱ ያሳያል፡፡የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኦ ኤም ኤን) የእርስ በርስ ግጭት ማስነሳትና በድርጅቱ ውስጥ ሕገ ወጥ የጦር መሳያ ይዞ መገኘት በሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡

ተከሳሾቹ የክስ ወረቀቱን ከተቀበሉ በኋላ በችሎቱ ከመነበቡ በፊት የተከሳሽ ጠበቆች ከደንበኞቻው ጋር በመምከር አጭር ቀጠሮ እንዲፈቀድ በመጠየቃቸው ክሱን ለማንበብና እና ተያያዥ ትዕዛዞችን ለመስጠት ለመስከረም 14፣2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡በችሎቱ ያልቀረቡ 3 ተከሳሾችን የፌደራል ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርብ እና በሌላ መዝገብ ጉዳያቸው እየታየ ዛሬ ያልቀረቡ ተከሳቾችን በቀጠሮው ዕለት እንዲቀርቡ ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡በተጨማሪም የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ተወካይ ለሐሙስ በተያዘው ተለዋጭ ቀጠሮ ቀን እንዲቀርቡም ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ጃዋር መሐመድ "ክስ የተመሠረተብን በምርጫ እንዳንሳተፍ ነው" አለ!

በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተደራራቢ ክሶች ከቀረቡባቸው ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ጃዋር መሐመድ ለሁለተኛ ጊዜ በሽብር መከሰሳቸው በቀጣዩ ምርጫ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ታስቦ መሆኑን ለፍርድ ቤት ተናገሩ።ዐቃቤ ሕግ ባሳለፈው ቅዳሜ አቶ ጃዋርን ጨምሮ በ24 ግለሰቦች እንዲሁም በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦኤምኤን) ላይ የሽብር ክስን ጨምሮ በአስር ተደራራቢ ወንጀሎች እንደከሰሳቸው ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።ክሱ ከተመሰረተባቸውና በእስር ላይ ከሚገኙት ሰዎች መካከል የተወሰኑት ዛሬም [ሰኞ] በተገኙበት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦባቸዋል።ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ጃዋር መሐመድ በዛሬው ችሎት "ለሁለተኛ ጊዜ በሽብር በመከሰሴ ኩራት ይሰማኛል" ሲሉ ለፍርድ ቤት ተናግረዋል። አቶ ጃዋር ከአገር ውጭ እያሉ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።

አቶ ጃዋር ጨምረውም ክሱ የተመሰረተባቸው በአገራዊ ምርጫው እንዳይሳተፉ ለማድረግ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፤ ገዢው ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል እሸነፋለሁ ብሎ በመስጋቱ የሽብር ክስ እንዲመሰረትብኝ ተደርጓል ሲሉ በችሎቱ ተናግረዋል።ክሱ እሳቸውን ብቻ ሳይሆን "አቶ እስክንድር ነጋም በአዲስ አበባ ምርጫው ያሸንፋል ተብሎ ተፈርቶ እንጂ፤ ወንጀል ሰርቶ አይመስለኝም" ሲሉም አቶ ጃዋር ሌሎችም ላይ የቀረበው ክስን ጠይቀዋል።በተጨማሪም አቶ ልደቱ አያሌውን ጠቅሰው ለእስር የተዳረጉት የሽግግር መንግሥት ይቋቋም የሚለው ሃሳባቸው ተሰሚነት እያገኘ ስለነበረ ነው ሲሉ አቶ ጃዋር ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።ክሱ የተመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች ዛሬ ዝርዝሩ በጽሑፍ የተሰጣቸው ሲሆን ችሎቱ ክሱን ለመስማት ለፊታችን ሐሙስ መስከረም 14/2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

[ቢቢሲ]
@YeneTube @FikerAssefa
👆👆
በእነ ጃዋር መሃመድ መዝገብ የተከሰሱ 24 ተከሳሾች ዝርዝር ።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በጎፋ ዞን የዘንድሮ መስቀል በዓል በአደባባይ እንደማይከበር ተገለጸ!

የጎፋ እና ኦይዳ ብሔረሰቦች ዘንድ በድምቀት የሚከበረዉ የመስቀል በዓል ዘንድሮ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በአደባባይ እንደማይከበር ተገለጸ፡፡የጎፋ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ድንበሩ ድርቤ የዘንድሮውን የ2013 ዓ.ም የ"ጎፋ ጋዜ ማስቃላ" እና የ"ኦይዳ ዮኦ ማስቃላ" ወይም የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ ለዞኑ ነዋሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።አቶ ድንበሩ በጎፋ እና ኦይዳ ብሄረሰቦች ዘንድ በደማቅ ባህላዊ ክዋኔዎች ከሚከበሩ በዓላት አንዱ የሆነዉ የመስቀል በዓል ዘንድሮ በአደባባይ ስለማይከበር እያንዳንዱ ሰው በያለበት ሆነዉ በዓሉን እንዲያከብሩ አሳስበዋል።

ምንጭ፡ ጎፋ ዞን መንግስት ኮምዩኒኬሽን መምሪያ
@YeneTube @FikerAssefa
ከአዋሽ ወደ ድሬዳዋ የሚዘልቀው መንገድ ዳግም ለተሽከርካሪ ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን አሳውቋል።

ከትላንትና በስተያ ከድሬዳዋ 15 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በካራሚሌ እና ቦረዳ መሃል አይፎክሩ በሚባል መስመር ላይ ክሬሸር የጫነ ሎቤድ ከባድ የጭነት መኪና ለማለፍ ሲሞክር በጭቃ ሳቢያ በመያዙ መንገዱ ለተወሰነ ሰዓታት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል።የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የድሬዳዋ ዲስትሪክት መንገዱን ክፍት ለማድረግ ባከናወናቸው ስራዎች መስመሩ ዳግም ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።በቀጣይም ከመንገዱ መልክአ ምድራዊ አቀማመጥና ከተፈጥሮ የመሬት መንሸራተት ጋር ተዳምሮ መስተጓጎል እንዳያጋጥም ቀጣይ ስራዎች እየተከናወኑ ነው።የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ይህን የመሰሉ ችግሮች ሲያጋጥም ፣እንዲሁም ችግሮቹ እልባት እስከሚያገኙ ድረስ በትዕግስት ለሚጠባበቁት የመንገዱ ተጠቃሚዎች እና አሽከርካሪዎች ምስጋናውን አቅርቧል።

[ERA]
@YeneTube @FikerAssefa
አዋሽ ባንክ አዲሱን የብር ኖት በኤትኤም (ATM) አገልግሎት ማቅረብ ጀመረ !

አዋሽ ባንክ ነባሮቹን የብር ኖቶች በአዲሶቹ የመቀየር አገልግሎት በቅርንጫፎች ከመስጠቱ ጎን ለጎን በኤትኤም (ATM) አገልግሎቱን ማቅረብ ጀመሯል፡፡በመሆኑም ደንበኞች አዳዲሶቹን የብር ኖቶች በኤትኤም (ATM) ማሽን አማካኝነት በቅርበት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ባንኩ አሳውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሀይማኖት በዳዳን በመግደል ወንጀል የተከሰሰው ደግነት ወርቁ የተጠየቀበትን ወንጀል ክዶ ተከራከረ!

ተከሳሽ ደግነት ወርቁ ግንቦት 17/2012 የ2ኛ ዲግሪ የመመረቂያ ምርምር ስራዎች በማከናወን ላይ የነበረችው ሃይማኖት በዳዳን በግምት ከቀኑ 8 ሰዓት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል 4ኛ ፎቅ ላይ የነበረችበትን ክፍል ከውስጥ ቆልፎ በስለት ወግቶ ገድሏታል በሚል ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የነፍስ ግድያና ከባድ ውንብድና ችሎት በከባድ ውንብድና የተከሰሰው ግለሰቡ በእለቱ ከፈጸመው ግድያ ወንጀል ባሻገር የሟችን አይፎን ሞባይል፣ ላፕቶፕ፣ የ5 ሺህ ብር ቼክ እና ጥሬ ብር ፓስፖርት እና የቤት ቁልፍ ዘርፏል የሚለውን በአቃቤ ህግ ክስ ተካቷል።ወንጀሉ እንደተፈፀመ እያወቀ ከተዘረፈው የሟች ንብረት ተጋራ የተባለው ምህረቱ ሚጣ የተባለው ግለሰብም በከባድ ሙስና ወንጀል ተከሷል።ሁለቱም ተከሳሾች ወንጀሉን አልፈጸምንም በማለት ክደው መከራከራቸውን ተከትሎ ችሎቱ የዐቃቤ ህግ ምስክር ለመስማት ለህዳር 23/2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
በተያዘው የመስከረም ወር ስድስት የድንበር ኬላዎች ይከፈታሉ - የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ

ኢትዮጵያ ስድስት የድንበር ኬላዎችን እስከተያዘው ወር መጨረሻ ድረስ እንደምትከፍት የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ።የሚከፈቱት ስድስቱ የድንበር ኬላዎች በቤንሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ በሶማሌ እና በደቡብ ክልሎች መሆናቸውንም የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ኡበቱ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተርሩ ኢትዮጵያ ካላት የድንበር ስፋት አንጻር አሁን ያሏትን 12 የድንበር ኬላዎች ቁጥር መጨመር አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።በተለይም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ከተለያዩ የውጭ አገራት ድንበሮችን አቋርጠው በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡትን ለመቆጣጠር የድንበር ኬላዎች እንዲከፈቱ አቅጣጫ መቀመጡን አስታውሰዋል።

በመሆኑም ኤጀንሲው ከክልሎች ጋር በመሆን የድንበር ኬላዎችን በጥናት ለመክፈት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።በጥናት ከተለዩ የድንበር ኬላዎች ውስጥ ስድስቱ እስከዚህ ወር መጨረሻ ድረስ ሙሉ ለሙሉ ክፍት ይሆናሉ ብለዋል፡፡እንዲሁም ካላቸው ጠቀሜታ አንጻር አንዳንዶቹ በይፋ ባይመረቁም በአሁኑ ወቅት ሥራ እንዲጀምሩ መደረጉን ተናግረዋል።ኬላዎቹ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ጠብቀው አገልግሎት እንዲሰጡ መሰረተ ልማት የማሟላት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አንስተዋል።

[ENA]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በማእከላዊና ምእራብ ጎንደር 280 መኖሪያ ቤቶችን ሊገነባ ነው!

በማእከላዊና ምእራብ ጎንደር ዞኖች ተፈጥሮ በነበረ ግጭት መኖሪያ ቤታቸው ለተቃጠለባቸው አርሶ አደሮች በ24 ሚሊዮን ብር ወጪ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታወቀ።ማህበሩ በሁለቱ ዞኖች የሚገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በጎንደር ከተማ ከአጋር አካላት ጋር የምክክር መድረክ ዛሬ አካሂዷል።የማህበሩ ምክትል ዋና ፀሐፊ አቶ እንግዳ ማንደፍሮ በምክክር መድረኩ ላይ እንዳሉት ማህበሩ በአዲሱ አመት 280 መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ዝግጅቱን አጠናቋል።፡መኖሪያቸው ከተቃጠለባቸው አርሶ አደሮች በተጨማሪ አቅመ ደካሞች፣ ደጋፊ የሌላቸው ሴቶችና አካል ጉዳተኞችም የመኖሪያ ቤት ግንባታው ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ተናግረዋል።

ማህበሩ የሚገነባቸው መኖሪያ ቤቶች የግል መፀዳጃ ቤት ጭምር እንደሚኖራቸው ጠቁመው፤ ህብረተሰቡም በጉልበትና በቁሳቁስ ጭምር አስተዋጽኦ በማድረግ የሚሳተፍበት እንደሆነ አስረድተዋል።

“ማህበሩ የቤቶቹን ግንባታ ከመጭው ጥቅምት ወር 2013 ዓ/ም በማስጀመር በዓመቱ መጨረሻ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ነዋሪዎቹ እንዲረከቡ ይደረጋል”ብለዋል።በተጨማሪም በሁለቱ ዞኖችና በምእራብ ትግራይ ሁለት ወረዳዎች የህብረተሰቡን የግልና የአካባቢ ንጽህና ለመጠበቅ የሚያግዝ የጤና አጠባበቅ ፕሮጀክት እንደሚተገብርም ተናግረዋል።ለፕሮጀክቶቹ ማስፈጸሚያ የሚውለውን በጀትም ማህበሩ ከአሜሪካን አለምአቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት /ዩኤስ አይ ዲ/ በድጋፍ እንዳገኘም አስታውቀዋል፡፡ የማእከላዊ የሰሜንና የምእራብ ጎንደር ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ሃላፊ አቶ አታለል ታረቀኝ በበኩላቸው ማህበሩ ባለፈው አመት በማእከላዊና ምአራብ ጎንደር ዞኖች ቤታቸው ለተቃጠለባቸው ወገኖች 120 መኖሪያ ቤቶችን ሰርቶ አስረክቧል።

[ኢዜአ]
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮምያ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ተፈሪ መኮንን ዛሬ ለጋዜጠኞች በቢሮአቸው እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ ባወጣው መመሪያ መሰረት የሒሳብ አካውንት በውክልና ማንቀሳቀስ የሚችሉት ከመስከረም 4,2013 ዓ.ም በፊት ውክልና የተሰጣቸው ብቻ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ለአንድ መቶ ሺህ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር የ20 ሚሊየን ብር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ፡፡

ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን 20 ሚለየን ብር በጀት የያዘለትንና በ7 ኢንድስትሪ ፓርኮች ውስጥ አንድ መቶ ሺ ወጣቶች የስራ እድል እንዲያገኙ እንዲሁም ሙሉ የመረጃ ሲስተም ለመዘርጋት የሚያስችለውን ስምምነት ከኢትዮጲያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ዛሬ ተፈራርሟል፡፡ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ብሪጅስ በተሰኘው ፕሮጀክቱ በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ የተሰማራ ሲሆን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በ7 ኢንድስትሪ ፓርኮች ላይ የሰራተኞች ምልመላ፣ ቅጥር ፣ስልጠና እና የሙሉ መረጃ ሲስተም ለመዘርጋት የሚያችለውን ስምምነት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የብሪጅስ ፕሮግራም ቡድን መሪ አቶ ሚካኤል አዲሱ እንዳሉት ፕሮጀክቱ 100 ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች በ7ቱ ኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ የስራ እድል የሚገኙ ሲሆን 30 ሺህ ያህል ወጣቶች ደግሞ ከኢንድስትሪ ፓርኮች ስራ ጋር በተያያዘ የክህሎት ስልጠና ያገኛሉ ብለዋል፡፡

የኢንድስትሪ ፓርክ ስራዎችን ለማግኘት ከተላያዩ አካቢዎች የሚጎርፉ ወጣቶች ስለ ኢንድስትሪ ፓርኩ ሙሉ መረጃን ስለማያገኙ የሚጠብቁትና የሚያኙት ሳይሰማማ ቀርቶ ለብዙ እንግልት ይዳረጉ ነበር፡፡በፕሮጀክቱ መሰረት ግን ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ 100 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ያሉ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ያሉትን የስራ እድሎች፣ ጥቅሞቹን፣ ለስራው ማሟላት ያለባቸው መስፈርት ምን እንደሆነና ሌሎችም መረጃዎችን የሚያገኙበት ሲስተም ስለሚዘረጋ ችግሩን ለመቅረፍ ያስችላል ብለዋል፡፡ፋውንዴሽኑ ድጋፍ የሚደርግባቸው ኢንድስትሪ ፓርኮችም በአዳማ፣ ድሬደዋ ፣ባህርዳር፣ ደብረ ብርሀን፣ሀዋሳ፣ መቀሌ እና ኮምቦልቻ የሚገኙት ሲሆኑ በቀጣይ 3 ኢንድስትሪ ፓርኮች ላይም ድጋፍ እንደሚደርግ ተሰምቷል፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa