YeneTube
አዲሱን የብር ለውጥ አስመልክቶ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ከኢቲቪ ጋር ያደረጉት ቆይታ Size: 11mb @YeneTube @FikerAssefa
አሮጌው የብር ኖት በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ በአዲስ እስከሚቀየር ድረስ ሁለቱም ጎን ለጎን ስራ ላይ እንደሚውሉ ብሔራዊ ባንክ ገለፀ!
አሁን በገበያ ውስጥ ያለውን ገንዘብ በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚቀየር የብሔራዊ ባንክ ገዥው ዶ/ር ይናገር ደሴ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናገሩ፡፡ ዶ/ር ይናገር እንደገለጹት ገንዘቡን የመቀየር ሂደቱ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚጀመርም አስታውቀዋል፡፡አብዛኛው የመቀየር ስራዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ የተገለፀ ሲሆን በአዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ የተካተቱ መለያዎች አመሳስሎ ገንዘብ ለማተም የሚደረጉ ሕገ-ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል፡፡
አብዛኛው የሕትመት ሥራ ተገባዶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግምጃ ቤት እንደሚገኝ እና የስርጭት ስርዓት እና ዕቅድ ተዘጋጅቶ በሚመለከታቸው አካላት አማካኝነት የሚተገበር እንደሚሆንም ዶ/ር ይናገር ገልጸዋል፡፡ይህንን የሥርጭት ሂደት በበላይነት የሚያስተባብር ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እና ከፌደራል ፖሊስ የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት እንደሚቋቋም ተገልፆ አሁን ላይ ግን አሮጌውንና አዲሱን የብር ኖት ጎን ለጎን መጠቀም እንደሚቻልም የብሔራዊ ባንክ ገዥው አስታውቀዋል።
[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa

በተያዘው ወር ከሳዑዲ ዓረቢያ ጅዳ ከተማ 1 ሺህ 440 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ መስፍን ገብረማርያም ከመስከረም 6 እስከ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ዜጎችን ከጅዳ ለመመለስ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል።በዚህም የፊታችን ረቡዕ 300 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ብለዋል።በቀጣይም ቀሪዎቹ ስደተኞች እንደሚመለሱ ያስታወቁት አቶ መስፍን፤ ተመላሾቹ በሕገ ወጥ መንገድ በቀይ ባህር በኩል ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ የገቡ፤ በእስር ቤትና በሕገ ወጥ ስደተኞች ማቆያዎች ውስጥ እንደነበሩ አመልክተዋል።ዜጎቹ ወደ አገራቸው የሚመለሱት በሚኒስቴሩ፣ በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት እና የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ከዓለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም(አይ ኦ ኤም)ጋር በመተባበር እንደሆነም ጠቅሰዋል።
ባለፈው ሳምንት በሳዑዲ ዓረቢያዋ ሪያድ ከተማ ይኖሩ የነበሩ 147 ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አቶ መስፍን አውስተዋል።በቀጣይም በሪያድ የሚገኙ 334 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ዳይሬክተር ጄኔራሉ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።በተጨማሪም ሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም በሊባኖስ መዲና በቤይሩት ወደብ በደረሰው ፍንዳታ ምክንያት ችግር ላይ የወደቁ 132 ኢትዮጵያውያን የፊታችን ሐሙስ ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።ዜጎቹ በደረሰባቸው ችግር በመጠለያ ውስጥ የሚገኙና የቲኬት ወጪያቸውም በበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ግለሰቦችና ቡድኖች እንደተሸፈነም ተጠቁሟል።
[FBC]

ኢትዮጵያ በቅርቡ ለምትቀይራቸው የብር ኖቶች 3ነጥብ6 ቢሊዮን ወጪ አወጣች!
ኢትዮጵያ ለ23 ዓመታት ያህል ስትጠቀምባቸው የነረበሩትን የብር ኖቶችን መቀየሯ ይፋ ተደርጓል።በዚህም 262 ቢሊየን መጠን ያላቸው የብር ኖቶች የታተሙ ሲሆን ለህትመቱም 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ለኢትይዮጵያን ቢዝነስ ሪቪው መጽሔት (EBR) ገልጸዋል።
[Addis Maleda]

ሳልሳይ ወያነ(ሳወት) ቅሬታ አሰምቷል!
የትግራዩ ተቃዋሚ ፓርቲ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ዛሬ [ሰኞ ጠዋት] በሰጠው መግለጫ፣ በምርጫው ሂደት በተወዳዳሪዎቹና በታዛቢዎቹ ላይ "ማስፈራርያና ጫና" ይደርስ እንደነበረ አስታወቀ።ፓርቲው እንዳለው ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች ከምርጫው ቀን በፊት አንስቶ ይስተዋሉ እንደነበር ጠቅሶ፤ በዚህም የገዢው ፓርቲ አባላት ከምርጫው በፊት ቤት ለቤት እየዞሩ "ምልክት የምታደርጉት እዚህ ላይ ነው" በማለት በመራጮች ላይ ጫና ሲያሳድሩ እንደነበር ገልጿል።በተጨማሪም ሳልሳይ ወያነ ትግራይ በመግለጫው ላይ እንዳለው በተወዳዳሪዎቹ እና ታዛቢዎቹ ላይ "ማስፈራርያና ጫና" እንደደረሰም አመልክቷል።"የወረዳና የቀበሌ መዋቅሮችን በመጠቀም፣ በእጩ ተመራጮቻችን እና ቤተሰቦቻቸው ላይ ማስፈራርያ ይደርስ ነበር፤ በሕዝብ እንደ ጠላት እንዲታዩና እንዲሸማቀቁም ሲደረግ ነበር" ብሏል።
[BBC]

የዱለቻ - አዋሽ አርባ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ግንባታ ተቋረጠ!
የአዋሽ ወንዝ ሙላት ያደረሰው የጎርፍ ማጥለቅለቅ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተቋራጭነት በግንባታ ላይ የሚገኘውን የዱለቻ አዋሽ አርባ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሥራ መቆሙን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ።በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች በተለይም በአፋር ክልል የክረምት ዝናብ በመብዛቱ ከፍተኛ የሚባል የጎፍ መጥለቅለቅ አጋጥሞ እስካሁንም ድረስ ብዙ ዜጎች ተጎጅ ሆነዋል።በዚሁ የጎርፍ መጥለቅለቅ በአፋር ክልል በአዋሽ ተፋሰስ አካባቢ እየተገነባ ያለው የዱለቻ አዋሽ አርባ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከነሀሴ 26/2012 ጀምሮ የግንባታ ስራው እንደተቋረጠ የኢትዮጵያ ኮንስትራክ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የህዝብ ግነኙነት ኃላፊ ጥንፉ ሙጬ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ከስልጣን መነሳታቸው ተሰማ!
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት በመሆን ሲሠሩ የቆዩት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ፣ ከቅዳሜ መስከረም 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን የሪፖርተር ምንጮች አረጋገጡ፡፡ከባንኩ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከመስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ አቶ ኃይለየሱስ ኃላፊነት ያለባቸው ውሳኔዎችን ከማስተላለፍ የታገዱ ሲሆን፣ ምንም ዓይነት አዲስ ብድር እንዳይፈቅዱ፣ የተፈቀደ ብድር ካለም እንዳይለቀቅ መታገዱን የባንኩ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ፕሬዚዳንቱ ለምን እንደተነሱ ለማወቅ ከባንድ ቦርድ አመራር እንዲሁም ከአቶ ኃይለየሱስ ለመረዳት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡ የሪፖርተር ምንጮችም የፕሬዚዳንቱ መነሳት ምክንያቱን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ የመነሳታቸው ጉዳይ ግን ውስጥ ውስጡን ሲነገር መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡
አቶ ኃየለየሱስ የቀድሞው የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ፕሬዚዳንት በመሆን ሠርተዋል፡፡ ባንኩ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲጠቀለልና ህልውናው ሲያበቃ በንግድ ባንክ ውስጥ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ጥቂት ጊዜያት አገልግለዋል።
በእሳቸው ምትክ የቀድሞው የብሔራዊ ባንክ ዋና የኢኮኖሚ ባለሙያና ምክትል ገዥ ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) እንደሚሾሙ ከልማት ባንክ የቦርድ አባላት ምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡ዮሐንስ (ዶ/ር) የባንኩ የቦርድ አባል በመሆናቸው አባልነታቸው እንዲነሳ ተደርጎ ሹመታቸው በብሔራዊ ባንክ እስኪጸድቅ ድረስ ያለው የአካሄድ ጉዳይ ካሀልሆነ በቀር፣ የልማት ባንክ ቦርድ አባላት እሳቸው እንዲሾሙ ተነጋግረው መወሰናቸው ታውቋል፡፡በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ልማት ፖሊሲ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆን እያገለገሉ ነበር፡፡
[Reporter]

Photo
ኦነግ ሰላማዊ ትግልን ብቸኛ አማራጨ አድርጌያለሁ አለ!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሰላማዊ ትግልን ብቸኛ አማራጩ አድርጎ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡የድርጅቱ ሊቀ-መንበር የነበሩትን የአቶ ዳውድ ኢብሣ ከስራ መታገድ እና በቀጣይ ሰላማዊ ትግል መምረጡን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡በመግለጫው የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ለ21 ዓመታት በሊቀ-መንበርነት የመሩትን አቶ ዳውድ ኢብሣ ከስራ ማገዱን አስታውቋል፡፡በአቶ ዳውድ የስልጣን ዘመን ድርጅቱ ሶስት ጊዜ የመከፋፈል አደጋ እንደደረሰበትና በተያዘለት ጊዜ ጉባኤ ሲያደርግ እንዳልነበር በድርጅቱ አመራሮች ተገልጿል።የድርጅቱ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ እንዳሉት "ኦነግ ሰላማዊ ትግልን መርጦ አገር ቤት ከገባ በኋላም አንዳንድ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ጫካ ካለውና የትጥቅ ትግል ከመረጠው አካል ጋር ሲሰሩ ነበር፤ የአመጽ ጥሪም ሲያስተላልፉ ቆይተዋል"።
አቶ ዳውድ በድርጅቱ ህገ-ደንብ መሰረት ከተቋቋመው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጋር የመስራት ፍላጎት የላቸውም ያሉት ቃል አቀባዩ "የፓርቲውን ንብረት በህገ-ወጥ መንገድ ለራሳቸው ሲሰበስቡ ነበር" ሲሉም ተናግረዋል፡፡"ድርጅቱ በአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭነት የሚመራና በግለሰቦች ፍላጎት የሚነዳ አይደለም" ብለዋል።"አቶ ዳውድ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ጠቅላላ ጉባኤው እስኪሰበሰብ ታህሳስ 2013 ድረስ ከድርጅቱ ሊቀ-መንበርነት ታግደዋል" ነው ያሉት አቶ ቶሌራ።በምትካቸው ምክትል ሊቀ-መንበሩ አቶ አራርሶ ቢቂላ ድርጅቱን እንደሚመሩ ተገልጿል።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አገር ቤት ሲገባ በገባው ቃል መሰረት ሰላማዊ ትግልን ብቸኛ አማራጩ አድርጎ ይቀጥላል ብለዋል።ድርጅቱ ውስጥ ሆነው ሰላማዊና የትጥቅ ትግልን አማራጭ የሚያደርጉ አካላትን የማጥራት ስራ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡የድርጅቱ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ አራርሶ ቢቂላ "ኦነግ በአንድ ግለሰብ የተመሰረተ ባለመሆኑ በአንድ ግለሰብ ሊፈርስ አይችልም" ብለዋል፡፡"በተለያዩ አገራት በመሆን ድርጅቱን እና አገሪቱን ለማተራመስ የምትሰሩ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ"ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ለበርካታ ዓመታት ተቀማጭነቱን በውጭ አገራት አድርጎ የቆየው ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከሁለት ዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ይታወቃል።
[OBN]

በኢትዮጵያ ከ150 በላይ አትሌቶች ከዛሬ ጀምሮ የአበረታች ቅመሞች ወይም የዶፒንግ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡
ፅ/ቤቱ ከአለም አትሌቲክስ የኢንተግሪቲ ዩኒት ጋር በመተባበር ዛሬና ነገ ምርመር የሚያደርግላቸው ከ150 በላይ አትሌቶች በግላቸውም ይሁን አገራቸውን ወክለው በተለያዩ አለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ላይ የሚሳተፉ ኤሊት አትሌቶች ናቸው፡፡ከ22 በላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት የምርመራ ባለሞያዎችእና የምርመራ አስተባባሪዎችም ምርመራውን በማድረግ ሂደት ተሳታፊ ናቸው ተብሏል፡፡በ2013 ዓ.ም ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ መድረክ ጨምሮ በተለያዩ ውድድሮች ተሳትፎ ዝግጅት ለሚያደርጉ አትሌቶች ክትትል አንደሚደረግላቸው የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡
[ETV]

ተማሪ ሃይማኖት በዳዳን በመግደል ወንጀል ምርመራ ሲደረግበት የነበረው ደግነት ወርቁና 2ኛ ተከሳሽ ምህረቱ ሚጣ ላይ ክስ ተመሰረተ!
ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በቤተ ሙከራ ክፍል ውስጥ ተማሪ ሃይማኖት በዳዳን በመግደል የወንጀል ምርመራ ሲደረግበት የነበረው ደግነት ወርቁ በውንብድና ወንጀል እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ ምህረቱ ሚጣ ላይ ደግሞ በከባድ የመሸሸግ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።ክሱ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የከባድ የውንብድና ወንጀል ችሎት የተመሰረተ ሲሆን፥ በተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መዝገቡ ታይቷል።የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በሁለቱ ተከሳሾች ላይ ሁለት ክስ ነው እንደተሳትፏቸው መጠን ክስ የመሰረተው።
የዐቃቤ ህግ ክስ እንደሚያመላክተው 1ኛ ተከሳሽ ደግነት ወርቁ የወንጀል ህግ 671 ንኡስ ቁጥር 2 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላላፍ በከባድ ውንብድና ወንጀል ለመፈጸም እና የማይገባ ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለሌላ አካል ለማስገኘት በማሰብ በግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ ስፔሻላየዝድ ሆስፒታል መግባቱ በክሱ ተመላክቷል።በእለቱም ወደ ኬሚስትሪ ላብራቶሪ ለመግባት ከሞከረ በኋላ ተማሪ ሃይማኖት በዳዳ እጇ ላይ ቦርሳ አንጠልጥላ ወደ ፋርማሲ ላብራቶሪ ስትገባ በመመልከቱ ፕሮፖዛል የያዘ በማስመሰል ነጭ ወረቀት ይዞ ገብቶ በር ከውስጥ መዝጋቱ በክሱ ተጠቅሷል።
ወደ ሟች ሃይማኖት በመጠጋት ያለሽን አምጪ ማለቱን በክሱ የጠቀሰው ዐቃቤ ህግ ቢላ አውጥቶ በማስፈራራት በእጇ የያዘችውን አይፎን ስልክ እንድትሰጠውና ፓተርን እንድትከፍትለት ሲጠይቋት አልከፍትም አልሰጥም ማለቷን ተከትሎ ገፍትሮ መሬት ላይ በመጣል እራሷን ለመከላከል ስትሮጥ እጇ ላይ ጉዳት ካደረሰ በኋላ ጭካኔ በሞላበት ሁኔታ በአንገቷ ላይ ጥቃት በማድረስ ህይወቷን ማጥፋቱን ዐቃቤ ህግ በክሱ አመላክታል።በዛው ሰአት ማስረጃ የማጥፋት ስራ መስራቱን የገለጸው ዐቃቤ ህግ ከቦርሳዋ ውስጥ 400 ብር፣ የ5 ሺህ ብር ቼክ፣ ላፕቶፕ እና አይፎን ሞባይል ስክል በመውሰድ ከውጭ በሩን ቆልፎ መውጣቱን በክሱ ተገልጻል።በ2ኛ ክስ ደግሞ የወንጀል ህግ 683/ሐ’ን በመተላለፍ በከባድ መሸሸግ ወንጀል ክስ የተመሰረተበት 2ኛ ተከሳሽ ምህረቱ ሚጣ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር በአንድ ቤት ወስጥ ተከራይተው እንደሚኖሩ ዐቃቤ ህግ በክሱ ጠቅሷል።
በእለቱ 1ኛ ተከሳሽ ወደዚህ ቤት በመሄድ ለ2ኛ ተከሳሽ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሰው አስሬ ነው የመጣሁት ብሎ በመግለጽ የወሰደውን ስልክ፣ ላፕቶፕ እና ቼክ እንዲሁም 400 ብሩን በመናገር የወሰደውን የ5 ሺህ ብር ቼክ ከአዋሽ ባንክ በመመንዘር 2 ሺህ ብር ለ2ኛ ተከሳሽ ሲሰጠው አንድ ሞባይል ገዝቶ ሲጠቀም በመያዙ በመሸሸግ ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።ተከሳሾቹ ክሱ የደረሳቸው እና ያቀረቡትን ዋስትና ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ፍርድ ቤቱ ጠበቃ ለማቆም አቅም የለንም ማለታቸውን ተከትሎ የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲመደብላቸው እና ተማክረው እንዲቀርቡ ክሱን ለማንበብ ለመስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቷል።እስከዚያው በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ አዟል።

በኢትዮጵያ ከ217 ሺህ በላይ ዜጎች በጎርፍ ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡- የሰላም ሚኒስቴር
በኢትዮጵያ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት እስካሁን ከአምስት ክልሎች ከ217 ሺህ በላይ ዜጎች በጎርፍ ምክንያት ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል አስታወቁ።በኢትዮጵያ የተከሰተውን የጎርፍ አደጋ በሚመለከት የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።በኢትዮጵያ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ በአምስት ክልሎች በሚገኙ 23 ዞኖች ላይ ጎርፍ የተከሰተ ሲሆን 580 ሺህ ዜጎች የጎርፍ አደጋ ተጋርጦባቸዋል።
በጎርፍ አደጋ የተጎዱ ዜጎችን ለመደገፍ አስቸኳይና ዘላቂ ተግባራት ተለይተው እየተሰሩ መሆኑንም ሚኒስትሮቹ ገልፀዋል።ከአጭር ጊዜ መፍትሄ አንፃር ደራሽ ምግብና ምግብ-ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች አደጋው ለደረሰባቸው ዜጎች እየቀረቡ መሆኑንም ነው የገለጹት።የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢኒጂነር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው በበጋው ወቅት በአዋሽ ተፋሰስ ብቻ 136 ሚሊዮን ብር በማውጣት 130 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የጎርፍ ጥበቃ ስራ መከናወኑን ገልጸዋል።ከአጭር ጊዜ መፍትሄ አንጻርም በቀጣዩ የበጋ ወቅት መሰል የጎርፍ መከላከል ስራ ተጠናክሮ እንሚቀጥል ሚኒስትሩ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

እስራኤል እስከ ቀጣዩ የፈረንጆች ዐመት 2 ሺህ ቤተ እስራዔላዊያንን ከኢትዮጵያ ለማስወጣት 51 ሚሊዮን ዶላር እንደመደበች ታይምስ ኦፍ እስራዔል ጋዜጣ በድረገጹ ዘግቧል፡፡ በጀቱ የተያዘው 2 ሺህ ቤተ እስራዔላዊያንን ለማስወጣት ነው፡፡ ጉዞውን በመጠባበቅ ላይ ያሉት ቤተ እስራዔላዊያን በአዲስ አበባ እና ጎንደር ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በጎረቤት አገራት ከፍተኛ ብር አለ ይህ ከፍተኛ ብር መምከን ነው ያለበት:- የብሄራዊ ባንክ ገዥ
አሁን አመሻሽ ለሚዲያ ስለ ገንዘብ ለውጡ መግለጫ እየሰጡ የሚገኙት የብሄራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ በጎረቤት አገራት ከፍተኛ ብር መኖሩን ገልፀው ወደ አገር እንዳይገቡ የፀጥታ መዋቅሩ ይሰራል ብለዋል።ይህ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን መምከን አለበትም ሲሉ አክለዋል።ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ከነበረው ስብሰባ በተጨማሪ ዛሬ ከሰአት የብሄራዊ ባንክ መሪዎች ከባንክ ፕሬዝደንቶች ጋር በባንኩ ተጨማሪ ስብሰባ እንደነበራቸው ታውቋል።
[Capital]

ክንደያ ገብረህይወት ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትነታቸው ተነሱ!
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ክንደያ ገብረህይወት (ፕ/ር) ከሃላፊነት መነሳታቸውን አስታወቀ፡፡ፕሬዝዳንቱ ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ ለነበራቸው አበርክቶ ያመሰገኑት ሚኒስትሩ ሳሙዔል ኡርካቶ (ዶ/ር) ከነገ ጀምሮ መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ የተሰጣቸው ኃላፊነት መነሳቱን በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡
“…ኃላፊነቶ የተነሳሎት መሆኑን አስታውቃለሁ” በሚል ነው በሚኒስትሩ የተጻፈው ደብዳቤ የሚነበበው፡፡
ፕሮፌሰሩ በምን ምክንያት ከኃላፊነታቸው ሊነሱ እንደቻሉ ግን በደብዳቤው የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡ደብዳቤውን በተመለከተም ሚኒስቴሩ በማህበራዊ ገጾቹም ሆነ በድረግ አድራሻው የሰጠው ይፋዊ መግለጫም ሆነ ማስታወቂያ የለም፡፡ሆኖም ፕሬዝዳንቱ ከሚኒስቴሩ የደረሳቸውንና የተሰጣቸው ኃላፊነት መነሳቱን የሚገልጸውን ደብዳቤ በስማቸው ባለ የትዊተር የማህበረሰብ ትስስር ገጽ ለጥፈዋል፡፡
ከደብዳቤው ጋር አያይዘው ባሰፈሩት ጽሁፍ ዩኒቨርስቲውንና ህዝባቸውን ማገልገል በመቻላቸው ያመሰገኑ ሲሆን የሃላፊነት ዘመናቸው ከተጠናቀቀ ለጥቂት ጊዜም ቢሆን መቆየቱን እና ይህንንም ለሚመለከታቸው ባለስልጣናት ማስታወቃቸውን ገልጸዋል፡፡ሆኖም የተሰጣቸው ኃላፊነት የመነሳቱ ነገር በቅርቡ የተካሄደውን የትግራይ ክልል ምርጫ ለመታዘብ እንደመጡ አስታውቀው ከነበሩት ከኖርዌያዊው ኬይቲል ትሮንቮል ጋር “መገጣጠሙ አስገርሞኛል” ብለዋል፡፡
[Al Ain]

ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) የተባለው ፓርቲ በትግራይ ክልል ምክር ቤት አንድ መቀመጫ እንደሚኖረው የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ። ቀሪዎቹ 189 መቀመጫዎች በገዢው ህወሓት ተይዘዋል። ባይቶና በክልሉ ምርጫ በ20,839 ሰዎች ተመርጦ ነበር።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 485 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው 350ው ደግሞ አገግመዋል እንዲሁም የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 9 ሺህ 256 የላቦራቶሪ ምርመራ 485 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 64 ሺህ 786 ደርሷል።
በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 350 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 25 ሺህ 333 ሆኗል።
ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉ በመረጋገጡ በአጠቃላይ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 22 ደርሷል።
በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 38 ሺህ 429 ሰዎች መካከል 344ቱ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
በአገሪቱ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊዮን 147 ሺህ 268 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።
@Yenetube @Fikerassefa

የቀድሞው የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ተቋም ዋና ዳይሬክተርነት ነበሩ።
Via Fortune Newspaper
@Yenetube @Fikerassefa
Via Fortune Newspaper
@Yenetube @Fikerassefa
ፍርድ ቤት ተከሳሽ ሚሻ ጭሪን በዋስ ከለቀቀ በኋላ ፖሊስ ተከሳሹን እስር ቤት የማቆየት ምንም ዓይነት ስልጣን ስለማይኖረው እርምጃ ከመወሰዱ በፊት ህግና ህገ መንግስቱን ጭምር በማክበር ፍ/ቤቱ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት በአስቸኳይ እንዲለቅ ታዟል ሲል ከፍተኛ ፍ/ ቤት ገለጸ።ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተሰጠው ትእዛዝ የማይፈጸም ከሆነ የሚመጣውን ሃላፊነት ለመውሰድ ጭምር ተከሳሹን ይዛቹ እንዲትቀርቡ በጥብቅ ታዟል ብለዋል።
[OMN]
@YeneTube @FikerAssefa
[OMN]
@YeneTube @FikerAssefa
ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ አዲስ ባንክ እያቋቋሙ ነው!
በበየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ቦርድ ሰብሳቢነት የሚቋቋመው ሆሳዕና ባንክ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያወጣውን ደንብ እና መርሆዎች በመከተል በኹለት ቢሊየን ብር የተፈረመ ካፒታል በምስረታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ። በዋነኝነት በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ የደቡብ ክልል ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን አነሳሽነት በምስረታ ላይ የሚገኘው ይህ ባንክ በአገራችን ያለውን ውስን የፋይናንስ ዘርፍ በማጠንከር ስራ ላይ የራሱን የሆነ አስተዋፅዎ እንደሚያበርክት ተገልጿል።