YeneTube
Photo
በያዝነው ሳምንት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ ተገለፀ!
በኢትዮጵያ እና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊጥል እንደሚችል የምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት የልህቀት ማዕከል እጠነቀቀ፡፡ማዕከሉ እንደገለጸው በተለይም በመካከለኛው እና ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊጥል ይችላል፡፡በእነዚህ ሀገራት የሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋዎችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ የልህቀት ማዕከሉ አስጠንቅቋል፡፡
የዝናብ ትንበያው ከዛሬ ጀምሮ በሚቀጠሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የሚጠበቅ ሲሆን በምዕራብ እና መካከለኛው ኢትዮጵያ ጥቂት ቦታዎች ከ 200 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ ዝናብ ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በጎረቤት ሀገራት ደቡብ-ምዕራብ ሱዳን፣ከሰሜን-ምዕራብ እስከ ደቡብ-ምዕራብ ደቡብ ሱዳን፣በምዕራብ እና፣ሰሜን-ምስራቅ ሶማሊያ እንዲሁም በሰሜን-ምዕራብ ዩጋንዳ እና ምዕራብ ኬንያ ከ 50 እስከ 200 ሚሊ ሜትር የሆነ መካከለኛ ዝናብ ይኖራል፡፡በሰሜን፣በምስራቅ እና በደቡብ ኢትዮጵያ፣በማዕከላዊ ሱዳን፣በሰሜን ምዕራብ ኤርትራ፣በምዕራብ እና ማዕከላዊ ደቡብ ሱዳን፣በሰሜን እና በደቡብ ሶማሊያ፣በጅቡቲ የባህር ዳርቻዎች፣ በማዕከላዊ እና በምስራቅ ዩጋንዳ አንዳንድ አካባቢዎች ከ 50 ሚሊ ሜትር በታች የሆነ ቀላል ዝናብ ይኖራል ተብሏል፡፡
እንደ የምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት የልህቀት ማዕከል ትንበያ ከሆነ አብዛኞቹ፣የደቡብ ምስራቅ እና ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍሎች፤የታንዛኒያ፣ቡሩንዲ፣ሩዋንዳ ፣ደቡባዊ ኡጋንዳ ፣ከምስራቅ እስከ ሰሜን ምዕራብ ኬንያ፣ደቡብ ምስራቅ ደቡብ ሱዳን ፣ማዕከላዊ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣እና የኤርትራ ባህር ዳርቻዎች ደረቃማ የአየር ሁኔታ ያመዝናል፡፡በሌላ በኩል በማዕከሉ የሙቀት ትንበያ መሰረት በሰሜን-ምስራቅ ኢትዮጵያ አንዳንድ ክፍሎች ፤ሰሜን ሱዳን፣የኤርትራ ባህር ዳርቻዎች፣ በጅቡቲ እና የሶማሊያ ሰሜን ምዕራብ ጠረፍ ክፍሎች ከ 32 ℃ በላይ የሆነ ከፍተኛ ዕለታዊ አማካይ የሙቀት መጠን ይጠበቃል፡፡የደቡብ-ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍሎች ከ 20 እስከ 32 የሆነ መካከለኛ የሙቀት መጠን ሲጠበቅ፤አብዛኞቹ ደቡባዊ እና ሰሜን ኢትዮጵያ ክፍሎች ገድሞ ከ20 በታች የሆነ የሙቀት መጠን ይኖራቸዋል ነው የተባለው፡፡
[ENA & ICPAC]
@YeneTube @FikerAssefa

በአማኑኤል ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ አማኑኤል ከተማ በደረስ የተራፊክ አደጋ የአንድሰው ህይወት ሲያልፍ በ9ኝ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡አደጋው መስከረም 5/2013 ዓመተ ምህረት ከጠዋቱ 1፡30አካባቢ በተለምዶ ጎጃም ዱር እየተባለ በሚጠራው ቦታ ታርጋ ቁጥር 25769 ኤፍ ኤስ አር ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻና ታርጋ ቁጥር 12086 አባዱላ የሆኑ ተሸከርካሪዎች ላይ በተፈጠረ ግጭት መድረሱን የገለፁት የማቻክል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኮማነደር አምሳል ሰውነት የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ገለፀዋል፡፡
[የወረዳው መ/ኮሙኒኬሽን]

ዘመናዊው የቄራ ግንባታ በሕገ ወጥ የመሬት ወረራ ምክንያት ተስተጓጎለ!
የአዲስ አበባ የቄራዎች ድርጅት በሃና ማርያም አካባቢ ሊያከናውነው የነበረውን ዘመናዊ የቄራ ግንባታ በሕገ ወጥ የመሬት ወረራ ምክንያት ግንባታውን ለመጀመር መቸገሩን ገለጸ። ባጠናቀቅነው የ2012 በጀት ዓመት ግንባታው ለማጠናቀቅ የታቀደ ቢሆንም በሕገ- ወጥ መሬት ወረራ ምክንያት ግንባታው እስከአሁን አለመጀመሩን ድርጅቱ ለአዲስ ማለዳ አስታወቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ የቄራዎች ድርጅት በሃና ማርያም አካባቢ ሊያከናውነው የነበረውን ዘመናዊ የቄራ ግንባታ በሕገ ወጥ የመሬት ወረራ ምክንያት ግንባታውን ለመጀመር መቸገሩን ገለጸ። ባጠናቀቅነው የ2012 በጀት ዓመት ግንባታው ለማጠናቀቅ የታቀደ ቢሆንም በሕገ- ወጥ መሬት ወረራ ምክንያት ግንባታው እስከአሁን አለመጀመሩን ድርጅቱ ለአዲስ ማለዳ አስታወቋል።
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ክንደያ ገብረህይወት ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትነታቸው ተነሱ! የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ክንደያ ገብረህይወት (ፕ/ር) ከሃላፊነት መነሳታቸውን አስታወቀ፡፡ፕሬዝዳንቱ ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ ለነበራቸው አበርክቶ ያመሰገኑት ሚኒስትሩ ሳሙዔል ኡርካቶ (ዶ/ር) ከነገ ጀምሮ መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ የተሰጣቸው ኃላፊነት መነሳቱን በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡…
ፕ/ር ክንደያ ገ/ሕይወት ከመቐለ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንትነት የተነሱት የስራ ዘመናቸውን በማጠናቀቃቸው መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚ/ር እንደሚከተለው አሳውቋል:
ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት መቀሌ ዩኒቨርስቲን በፕሬዘዳንትነት ሲመሩ መቆየታቸው ይታወሳል።ሆኖም በተለመደው የዪኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ምልመላና ስምሪት መመሪያ መሠረት የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ በመሆኑ በክብር መሰናበታቸውን እንገልፃለን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ፕሮፌሰር ክንደያ በተሰጣቸው የኃላፊነት ጊዜና ከዚያም በላይ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ እያመሰገነ፣ ቀጣይ የሥራ ዘመናቸው ውጤታማ እንዲሆን ይመኛል፡፡
-የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

የቅዱስ ዻውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ አቋርጦት የነበረውን ህክምና መስጠት ጀመረ!
የቅዱስ ዻውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለ3 ወር ያህል አቋርጦት የነበረውን ህክምና መስጠት እንደጀመረ አስታውቋል።ሆስፒታሉ ወረርሽኙን በመከላከል ረገድ ምርመራዎችን ማካሄድና ታካሚዎችን ከመንከባከብ ጋር ተያይዞ ወደ 25 ሺሀ የሚጠጉ ምርመራዎችን እንዳከናወነ ነው የገለፀው።ሆስፒታሉ 270 አልጋዎችን በማዘጋጀት ከኮሮና በሽታ ጋር ተያይዞ የተለየ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ታካሚዎች በመቀበል አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበርም ተጠቅሷል።ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከ900 ሰዎችን በመቀበል 640 ድነው መውጣታቸውና አሁን ላይ ደግሞ 150 ሰዎች በህክምና ላይ የሚገኙ እንደሆኑ ተጠቁሟል።
[EBC]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አደረጉ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከክልል እና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።ውይይቱ በዋናነት በሀገራዊ መግባባት ላይ የተደረገውን ውይይት ምን እንደሚመስል መገምገም እና ቀጣይ በምን ሁኔታ ውይይቶች ይካሄዱ የሚለውን ለመወያየት ነው።አብዛኛዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደገለጹት የተደረጉ ውይይቶች በፓርቲዎች መካከል ፉክክር እንዲደረግ በር የከፈተ እና መቀራረብ የፈጠረ ነው ብለዋል።ታይተው የነበሩ ችግሮች እየተቀረፉ መምጣታቸውንም አንስተዋል።በሚቀጥለው ጊዜ ምን ይደረግ በሚለው ጉዳይ ላይም አራት ርእሰ ጉዳዮችን መርጠዋል።
እነዚህም
👉 ህገ መንግስት እና ህግ መንግስታዊነት ስር በኢትዮጵያ የቅራኔ ምንጭ ላይ ውይይት፣
👉 የፖለቲካ አደረጃጀቶች ምን መምሰል አለበት፣
👉 የፖለቲካ ፓርቲዎችን መሰባሰብ በሚመለከት እና
👉 ትክክለኛ ምርጫ ምን ማለት ነው በሚለው ጉዳይ ላይ ውይይት እንዲደረጉ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምርጫው ስርዓቱ ምን ይሁን እንዲሁም በምን መልኩ ምርጫውን ማከናውን አለበት በሚሉ ጉዳይ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ይመክራሉ ተብሏል።

በውጭ ሀገር የገንዘብ ምንዛሬ አገልግሎት የተጠረጠሩ ሱቆች ታሸጉ!
የኢትዮጵያ መንግስት አሁን በአገልግሎት ላይ የሚገኙትን የብር የገንዘብ አይነቶች እንዲሚቀይር በትላንትናው ዕለት ማስታወቁን ተከትሎ የ“ጥቁር ገበያ”ውን ለመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ ተጀመረ። በአዲስ አበባ ከባንክ ውጭ የሚደረጉ የውጭ ሀገር ገንዘብ ግብይቶችን በድብቅ ያከናውናሉ ከተባሉ ሱቆች መካከል የተወሰኑት ከትላንት ጀምሮ እንዲታሸጉ ተደርገዋል።የእርምጃው ሰለባ የሆኑት በይፋ ከሚታወቁባቸው አገልግሎቶች ባሻገር የውጭ ሀገር ገንዘቦች ምንዛሬን በተደራቢነት የሚሰጡ ሱቆች ናቸው።በኢትዮጵያ ሆቴል እና ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኙት እነዚህ ሱቆች “ታሽጓል” የሚል ጽሁፍ እና ማህተም የሰፈረባቸው ወረቀቶች በየበሮቻቸው ላይ መለጠፍፋቸውን ዛሬ ረፋዱን በቦታው የተገኘው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ ተመልክቷል።
[Ethiopia Insider]

ጋምቤላ በዐሥር ሺህዎች በጎርፍ መጥለቅለቅ ተፈናቅለዋል!
ከ18ሺህ በላይ ሰዎች ጋምቤላ ክልል ላሬ ወረዳ ውስጥ በጎርፍ መፈናቀላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ዐስታወቁ። የጎርፍ መጥለቅለቊ አደጋ የተከሰተበት ወረዳው ኢትዮጵያን ከሱዳን በሚያዋስን አካባቢ ነው፡፡ የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ ቤት ከተፈናቃዮች መካከል ወ/ሮ ኛዳክ ፓችን ጠቅሶ እንደዘገበው ሰሞኑን እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ በፈጠረው ጎርፍ ምክናያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከነቤተሰቦቻቸው በትምህርት ቤት አጥር ጊቢ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። መንግስት የአልባሳትና የምግብ አቅርቦት ባለማድረጉም ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ወ/ሮ ኛዳክ ተናግረዋል።
በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን የላሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋርዊች ቢየል በስልክ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ሱዳንንና ኢትዮጵያን የሚያዋስነው ጂካዎ ወንዝ ሞልቶ በተፈጠረው ችግር ከ18ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ የሚኖሩትም በትምህርት ቤቶች እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡ እንስሳት እንደሞቱና የግጦሽ ሜዳዎችም በጎርፍ በመሸፈናቸው እንስሳቱም ለከፋ ረሀብ መጋለጣቸውን ዋና አስተዳዳሪው አመልክተዋል፡፡ አደጋው ከጳጉሜ ጀምሮ የተከሰተ ሲሆን ከክልል ርዳታ እንዲቀርብ ሪፖርት ቢደረግም ጉዳቱን መጥቶ ከመመልከት ውጪ እስካሁን ምንም እርዳታ እንዳልተገኘ ገልፀዋል፡፡
የጋምቤላ ክልል አደጋ መከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሙያ አቶ ሰይፉ ወልዴ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ የአካባቢው ሰዎች አኗኗር ለእንደዚህ ዓይነት አደጋ እንደሚያጋልጥ አመልክተዋል። በመሆኑም ሰሞኑን በአካባቢው የጎርፍ መጥለቅለቅ መድረሱን አመልክተው የተጠቀሰው የርዳታ ፈላጊ ቁጥር ግን የተጋነነ እንደሆነ አመልክተዋል። ሆኖም ርዳታ ወደ አካባቢው ለመላክ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አመልክተዋል። በዘንድሮው ክረምት በተለያዩ አካባቢዎች የጣለው ከባድ ዝናብ በበርካታ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ጎርፍና ናዳ በመፍጠሩ በርካቶች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል።
[DW]

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዳዲስ ሹመቶች ሰጡ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተለያዩ አዳዲስ ሹመቶችን እና የስራ ምደባ መስጠታቸው ተገለጸ፡፡የተጀመረውን ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እና በተለያዩ ግዜያት የሚነሱ የህዝብ ቅሬታዎችን ለመመለስ የአመራር ሽግሽግና አዳዲስ የስራ ስምሪት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ዛሬ ለ8 አመራሮች ምደባ መሰጠቱን የከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት አስታውቋል፡፡
በዚሁም መሰረት፡-
1. አቶ ሙሉጌታ ተፈራ - የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ተፈራ ሞላ - የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ ጀማል ረዲ - የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
4. አቶ መኮንን አምባዬ - የቦሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
5. አቶ ሺሰማ ገ/ስላሴ- በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ የህዝብ አደረጃጀት አማካሪ
6. አቶ ተተካ በቀለ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ አደረጃጀት አማካሪ
7. አቶ ጥላሁን ፍቃዱ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የከንቲባ ማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ
8. አቶ የትናየት ሙሉጌታ - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ፅ/ቤት ኃላፊ
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተሿሚዎቹ የተሰጣቸው ሃላፊነት የህዝብ አገልጋይነት መሆኑን በመረዳት ህዝቡን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ እንዲሆኑ ማሳሰባቸውን ከፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የፓናማ ፖሊስ ከአንድ ኃይማኖት ጋር ግንኙነት አለው ያለውን የጅምላ መቃብር ማግኘታቸውን አስታወቀ።
ፖሊስ ምርመራ ላይ እንደሆነ ጨምሮ አስታውቋል።መርማሪዎች በሰሜን ምዕራብ የፓናማ አውራጃ ከተገኘው የጅምላ መቃብሩ የተቆፈሩ አፅሞችን እየሰበሰቡ ነው።ባለፈው ጥር አሁን የጅምላ መቃብሩ ከተገኘበት ሥፍራ ብዙም ሳይርቅ የሰባት ሰዎች አስከሬን አንድ ላይ ተቀብሮ መገኘቱ ይታወሳል።ሬሳዎቹ አንድ ሰይጣን ለማውጣት ጉልበት የተቀላቀለበት ኃይል ከሚጠቀም ኃይማኖት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሏል።አቃቤ ሕግ አዛኤል ቱግሪ፤ መርማሪዎች በተራራዎች መካከል 10 ሰዓት ያክል ተጉዘው የጅምላ መቃብሩን እንዳገኙት ያስረዳሉ።መቃብሩ ንጋቤ ቡግሌ የተሰኘ ሥፍራ ካለ አንድ ወንዝ አቅራቢያ ነው የተገኘው።የጅምላ መቃብሩ ከፓናማ ዋና ከተማ ፓናማ ሲቲ 350 ኪሎ ሜትር ርቆ ነው የሚገኘው።
አቃቤ ሕጉ በአሁን ወቅት የአስከሬን ቁጥርና ፆታ መለየት እጅግ አዳጋች ነው ሲሉ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።አፅሞቹ ተሰብስበው የሬሳ ምርመራ እንደሚደርግላቸው ታውቋል።ከቀናት በፊት ፖሊስ የኒው ላይት ኦፍ ጋድ ቤተ እምነት መሪ ነው የተባለ ሰው ወርሃ ጥር ላይ ከተገኘው መቃብር ጋር በተያያዘ ክስ በቁጥጥር ሥር አውሏል።ባለፈው ጥር የጅምላ መቃብሩ የተገኘው ሶስት ሰዎች አምልጠው በአቅራቢያው ወዳለ ሆስፒታል ሄደው ጥቆማ ከሰጡ በኋላ ነው።መቃብሩ ሲቆፈር አንዲት ነብሰ ጡር እናትና አምስት ልጆቿ እንዲሁም አንድ ታዳጊ ተገኝተዋል።ይህን ተከትሎ ፖሊስ ባካሄደው ፍተሻ በአንድ ቤተ እምነት ውስጥ አንዲት እርቃኗን ያለች ሴት፣ ገጀራዎች፣ ቢላዎች መስዋዕት የሆነ ፍየል አግኝቷል።ቤተ እምነቱ ሰይጣን ለማውጣት በሚል ኃይል የተቀላቀለበት መንገድ ይጠቀም ነበር ተብሏል።በኃይማኖቱ ቁጥጥር ሥር የነበሩ 15 ሰዎች መለቀቃቸውም በጊዜው ተዘግቦ ነበር።
[BBC]

አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባ አንድ ላይ እንዲገናኙ ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ አፈፃፀሙን ለመመልከት በተሰጠው ቀጠሮ መሰረት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ተወካይም ቀርበው ትእዛዙ መፈፀሙን አብራርቷል።እነ አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባም ትእዛዙ መፈፀሙን ገልፀዋል።የአቶ ሀምዛ አዳነ (ቦረና) እና የአቶ ሸምሰዲን ጠሃ ጠበቃ ለችሎቱ ደንበኞቹ 30 ደቂቃ ብቻ አየር እያገኙ መሆኑን በመግለፅ፤ ከ30 ደቂቃ በላይ የፀሃይ ብርሃን እና አየር እንዲያገኙ ትእዛዝ እንዲሰጥለት ጠይቋል።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎትም በቂ አየር እና የፀሃይ ብርሃን እንዲያገኙ ትእዛዝ ሰጥቷል።በሌላ በኩል በሰብአዊ መበት ጥሰት ወንጀል በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት በእነ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ የተከሰሱ ከ15 በላይ ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበው የአቃቤ ህግ ምስክር እየተሰማ ይገኛል።
[FBC]

ከአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ 8 ተሽከርካሪዎችን ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ!
በኮሚሽኑ የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ኢንስፔክተር ያሬድ አለማየሁ እንደገለፁት ከአዲስ አበባ ከተማ ተሰርቀው የተወሰዱ 8 የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ከአዲስ አበባ ውጪ በሚገኙ የተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ ይገኛል ብለዋል።
የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ቸልተኝነት እና ጥንቃቄ ጉድለት በተለይም ቁልፍ ሳይነቅሉ እና የተሟላ ጥበቃ ባለበት ስፍራ ሳያቆሙ መሄድ፣ በከተማችን የተሽከርካሪ ስርቆት ከሚፈፀምባቸው ምቹ ሁኔታዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ጉዳዮች በጉምሩክ ተይዘው የነበሩ እና ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው 4 ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ሰራተኞች ጋር በመመሳጠር እና ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ በፖሊስ በተደረገ ክትትል ተሽከርካሪዎቹ ወንጀሉን ፈፅመዋል ከተባሉት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል።
[Addis Ababa Police Commission]

በጅግጅጋ ጉምሩክ በዛሬ ዕለት ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ 200 ሺህ ብር መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በትላንትናው ዕለት በመንግሥት ይፋ በተደረገው የብር ኖት ቅያሪ ምክንያት ከሱማሌላንድ በቶጎውጫሌ በኩል በተለያየ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ የሸሸ የኢትዮጵያ 200 ሺህ ብር በአንድ ግለሰብ አማካኝነት ወደ ሀገር ሊገባ ሲል በጉምሩክ ፈታሽ አማካኝነት ከነተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር መዋሉ ነው የተገለጸው፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
በትላንትናው ዕለት በመንግሥት ይፋ በተደረገው የብር ኖት ቅያሪ ምክንያት ከሱማሌላንድ በቶጎውጫሌ በኩል በተለያየ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ የሸሸ የኢትዮጵያ 200 ሺህ ብር በአንድ ግለሰብ አማካኝነት ወደ ሀገር ሊገባ ሲል በጉምሩክ ፈታሽ አማካኝነት ከነተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር መዋሉ ነው የተገለጸው፡፡
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ከሳውዲ አረቢያ የመውጫ ቪዛ አግኝተው ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከሀገሪቱ መንግስት ጋር በመስማማት ከነሃሴ 17/2012 ጀምሮ አስፈላጊው የጉዞ ሰነድና የትብብር ደብዳቤ በመያዝ ሲሰጥ የነበረው አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ በሳውዲ ኢሚግሬሽን በኩል መቋረጡን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል። @YeneTube @FikerAssefa
በሳዑዲ እስካሁን ከታወቁት ውጭ ሌሎች በርካታ አሰቃቂ የስደተኛ ማጎሪያዎች አሉ ብሎ እንደሚገምት ቴሌግራፍ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ከመካ ከተማ አቅራቢያ ባለው አል ሹማሲ ማጎሪያ ጣቢያ ብቻ 16 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንደታጎሩ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ገልጧል፡፡ ሰሞኑን ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ያሉት ስደተኞችም፣ በሁለቱ ሀገሮች ስምምነት የመውጫ አውሮፕላን ትኬታቸውን በራሳቸው ወጭ ገዝተው ነው- ብሏል ዘገባው፡፡ ሳዑዲ ግን ይህን ስምምነት አሁን እንደሰረዘችው እና ይህም በቀጣይ ስደተኞችን መውጫ እንደሚያሳጣቸው፣ ጋዜጣው በሪያድ የኢትዮጵያ ኢምባሲን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
[Wazema]