YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዓለም ለሚቀጥለው ወረርሽኝ በአግባቡ መዘጋጀት አለባት- የአለም ጤና ድርጅት

የአለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በትናንትናው እለት ሀገራትን በህብረተሰብ ጤና ላይ አተኩረው እንዲሰሩ በጠየቁበት ወቅት፣ ዓለም ለሚቀጥለው ወረርሽኝ በሚገባ መዘጋጅት እንዳለባት ተናግረዋል፡፡እስካሁን ሮይተርስ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ በሽታ በፈረንጆቹ 2019 በቻይና ከተገኘበት ጊዜ ጀምሮ አዘጋጀሁት ባለው መረጃ መሰረት ከ27 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሲሆን 888 326 ሰዎችደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ዶክተር ቴድሮስ ይሄ የመጨረሻው ወረርሽኝ አይደለም ብለዋል፡፡ “ታሪክ እንደሚያስተምረን ወረርሽኞች የሚኖሩ ናቸው፤ስለሆነም ዓለም ከአሁን በላይ መዘጋጀት” እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ሱር ኮንስትራክሽን ዋና ቢሮውን ወደ ትግራይ ክልል አዘዋወረ!

በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ባለቤትነት ስር የሚተዳደረውና በርካታ የልማት ድርጅቶችን አቅፎ በያዘው የትግራይ መልሶ ማቋቋም (ኤፈርት) ተብሎ በሚጠራው ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ሱር ኮንስትራክሽን ዋና ቢሮውን ወደ መቐለ ማዘዋወሩ ተገለፀ።

አዲስ ማለዳ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው የኮንስትራክሽን ድርጅቱ ቦሌ ሸዋ ዳቦ አፍሪካ ጎዳና አካባቢ ባስገነባው የራሱ ህንፃ አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ወደ ትግራይ ክልል ማዘዋወሩ ተገልጿል።

በሱር ኮንስትራክሽን ውስጥ ከሚሰሩ ሰራተኞች መሃል ለአዲስ ማለዳ የተናገሩት እንዳሉት ኮቪድ 19 ከገባ ከጥቂት ቀናት በኋላ ዋና መስሪያ ቤቱ ወደ መቐለ መዛወሩን የተናገሩ ሲሆን በዚህም አዲስ አበባ የሚገኙ ሰራተኞች ፈቃድ እንደሰጠና ለዚህም ምክንያቱ ኮቪድ 19 ኢትዮጵያ መግባቱ መሆኑ እንደተገለፀላቸው ተናግረዋል።

ድርጅቱ ይህን ይበል እንጂ ከቀናት በኋላ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ሰራተኞች የተገለፀው ፈቃደኛ ሆነው ትግራይ ክልል መቀሌ ገብተው መስራት ከፈለጉ እንደሚችሉ እና ካልሆነ ግን በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን እንደለቀቁ እንደሚወሰድ እንደተነገራቸው አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ አረጋግጣለች።ከዚህ ጉዳይ ጋር ጋዜጣው ያነጋገራቸው የሱር ኮንስትራክሽን ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ታደሰ የማነ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ከሆነ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ ያለው ሱር ኮንትራክሽን ከዚህ ቀደም የነበረውን ዋናውን ቢሮ አለመልቀቁን እና ቅሬታውም ከእውነት የራቀ ነው በማለት ተናግረዋል።

ዋና ስራ አስኪያጁ እንደሚሉት ከዚህ ቀደም የሱር ኮንስትራክሽን ዋና ቢሮ የሚገኝበት ደምበል አካባቢ ከሜጋ ህንፃ ጎን እንደሆነ እና አሁንም እዛው እንዳለ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።ታደሰ ጨምረውም አሁን ደምበል አካባቢ የሚገኘው ቢሯቸው አገልግሎት እየሰጠ ያልሆነበት ምክንትን ሲጠቅሱ፤ በትግራይ ክልል ከ30 በላይ ፕሮጀክቶች በመጀመራቸው እና ሱር ኮንስትራክሽንም ለስራው ቅርብ መሆን ስላለበት አንዳንድ ዋና ዋና የስራ ኃላፊዎች ወደዛው መቅረብ ስላለባቸው መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ነገር ግን ይላሉ በፕሮጀክቱ ላይ ለመሳተፍ ምን ያህል ሰራተኞች እንደሄዱ በቁጥር እንደማያውቁ እና አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋናው ቢሮም ምንም አይነት ሰራተኛ በእረፍት ላይ አይገኝም ሲሉ አስተባብለዋል።ሱር ኮንስትራክሽን በኤፈርት ስር ከሚገኙ ወደ 14 የሚጠጉ ድርጅቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከሦስት ሺሕ በላይ ቋሚ እና ከሰባት ሺሕ በላይ ደግሞ ቀን ሰራተኞችን በስሩ ሚያስተዳደር ግዙፍ ኩባንያ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።

ከ20 ዓመታት በፊት በ108 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተመሰረተው ሱር ኮንስትራክሽን በሕወሓት ባለቤትነት በሚመራው ኤፈርት ኩባንያዎች አንዱ አካል እንደሆነም ይታወቃል።ሱር ኮንስትራክሽን በአገር ውስጥ ካሉ ኮንስትራክሽኖች ደረጃ አንድ ግንባታ ድርጅት ሲሆን፤ ሀይድሮፓወር ፕሮጀክቶች እና የመኖሪያ ቤት ግንነባታዎችም ላይ በስፋት እንደሚሳተፍም ይታወቃል።ከተሳተፈባቸው ፕሮጀክቶችም መካከል በከፍተኛ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የዛሬማ ሜይዴይ ግድብ አንዱ ሲሆን በአገር በቀል ድርጅቶች ይህን የሚያክል ከፍተኛ በጀት ያላቸውን ፕሮጀክቶች በዋና ተቋራጭነት በመሳተፍ ሱር ቀዳሚው ድርጅት ነው።በተመሳሳይም በመቐለ ከተማ መኖሪያ መንደርም በመገንባት ስራ ላይም ተሰመራርቷል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
ኮሮና ቫይረስ በአውሮፓ በድጋሚ እያንሰራራ መሆኑ ተገለጸ!

ስፔን በምዕራብ አውሮፓ ግማሽ ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎችን በመመዝገብ የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች፡፡በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ525 ሺ የበለጠ ሲሆን ይህም የሆነው ትምህርት ቤቶች እንደገና ከመከፈታቸው ጋር በተያያዘ ቫይረሱ ለሁለተኛ ጊዜ በማገርሸት ላይ በመሆኑ ነው፡፡

በሌሎች የአውሮፓ ሀገራትም በተመሳሳይ ቫይረሱ በድጋሚ በማንሰራራት ላይ ይገኛል፡፡ ፈረንሳይ በየቀኑ የተጠቂዎች ቁጥር “አሳሳቢ” በሆነ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን ያሳወቀች ሲሆን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እለት ተእለት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ ከ 5,000 በላይ መድረሱን ይፋ አድርጋለች፡፡

የተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረባት ባለችው በሌላኛዋ አውሮፓዊት ሀገር ዩናይትድ ኪንግደም የአገር ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ከወጣቶች የተያያዘ ስለመሆኑ ዘ ናሺናል ዘግቧል፡፡በመላው ዓለም እስካሁን የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ 27.4 ሚሊዮን በላይየደረሰ ሲሆን ከ 896,000 በላይ የሚሆኑት ህይወታቸው አልፎ ከ 19 ሚሊዮን የሚበልጡት አገግመዋል፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች በበዓሉ ዋዜማ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳይጠቀሙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳሰበ!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2013 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚኖረው የኃይል ፍልጎት ለማሟላት የቅድመ ጥንቃቄ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በበአሉ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የኃይል መዋዠቅንና መቆራረጥ ለመቀነስ የድንጋይና እህል ወፍጮ፣ የፕላስቲክ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የብረታ ብረት፣ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ የኬሚካልና ሌሎች ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ከጳጉሜ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 4፡00 ድረስ ከግሪድ የሚያገኙትን የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳይጠቀሙ የተለመደ ትብብራቸውን አንዲሰጡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳስቧል።

በዋዜማና በበዓሉ ቀን የኤሌክትሪክ ኃይል ሳይቆራረጥና ሳይዋዥቅ ለማቅረብ እንዲሁም ችግሩ ከተከሰተም በተገቢው መንገድ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑንንም ነው ተቋሙ የገለፀው፡፡በተደጋጋሚ ጊዜ የኃይል መቆራረጥ የሚስተዋልባቸውን አካባቢዎች በመለየት በመካከለኛና በዝቅተኛ መስመሮች ላይ ጭነት የማመጣጠንና የቅድመ መከላከል ጥገና ስራዎች በመሰራት ላይ መሆኑንንም አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጋራ በመሆን ከኃይል ማመንጫ ጀምሮ እስከ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችንና ትራንስፎርመሮች ብልሽቶች ሲያጋጥሙ በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውም ተገልጿል፡፡

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአምስት ቋንቋዎች የተሰናዳ የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ሥርዓት መተግበሩን አስታወቀ!

በኢትዮጵያውያን የተሠራና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያስገኛል የተባለና ‹‹ጉዞ ጐ›› የተባለ በአምስት ቋንቋዎችና በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የተሠራ የኤሌክሮኒክስ ክፍያ ሥርዓት መተግበሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ፡፡

ጉዞ ጐ የተሰኘው የበረራ ትኬት ሽያጭ ማከናወኛ ሶፍትዌር በአማርኛ፣ በኦሮሚኛ፣ በትግሪኛ፣ በሶማሊኛና እንግሊዝኛ ወይም እንዲተገበር ያደረገው ሶልጌት ትራቭል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባደረገው ስምምነት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በረራ ካላቸው አሥር አየር መንገዶች ጋር የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ዘዴውን በመተግበር፣ በባንኩ በኩል የአየር ትኬት ሽያጭ በኦንላይን መጀመሩን የሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች ነሐሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. የስምምነት ሰነድ በመፈጸም ትግበራውን ይፋ አድርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዮሐንስ ሚሊዮን፣ አዲስ የተተገበረውን የኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴን በሚመለከት እንደገለጹት፣ የክፍያ ሥርዓትን ከማዘመን አንፃር ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ ሶልጌት ትራቭል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ያበለፀገው ጉዞ ጐ ዲጂታላይዝ የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መተግበሪያ፣ የአየር በረራ ትኬቶችን የመቁረጥና ለደንበኞች ቀልጣፋ አገልግሎት የሚያገኙበት አሠራር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለ1 ሺህ 29 የአየር ኃይል መኮንኖች የማእረግ እድገት ሰጠ!

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለ1 ሺህ 29 የአየር ኃይል መኮንኖች የማእረግ እድገት ሰጠ።
የማእረግ እድገቱኑን የሰጡት የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ በስነ-ስርአቱ ላይ እንደተናገሩት የማእረግ እድገቱ ለተጨማሪ ኃላፊነት የሚጋብዝ በመሆኑ መኮንኖቹ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት እንዳለባቸው አሳስበዋል።በእለቱ የአየር ኃይል ከፍተኛ አመራሮችን ሀብት ማስመዝገብ፣ የተቋሙ የድህረ ገፅ ምርቃት እና የአብራሪዎች ትጥቅ ትውውቅ ተደርጓል።በዝግጅቱ ላይ ሰራዊቱ “ለገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶችም የአንድ ወር ሙሉ ደሞዛቸውን እንደሚሰጡ ተገልጿል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፖሊስ በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ ያቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ይግባኝ የወንጀል ችሎት ፖሊስ በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ ያቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።ፖሊስ የአሥራት ጋዜጠኞች በዋስትና ከእስር ቢፈቱ መረጃ ያጠፉብኛል ቢልም ፍርድ ቤቱ ይግባኙን አልተቀበለውም።ፖሊስ ከአራቱ የአሥራት ጋዜጠኞች መካከል በበላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ላይ ይግባኝ ጠይቆ የነበር ሲሆን በዋነኛነት ከኢመድኤ / INSA፣ ከሆስፒታል እና ከብሮድካስት ባለስልጣን መረጃ እንደሚያመጣ ጠቅሶ ከእስር ከወጡ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስለሆኑ መረጃ ያጠፉብኛል ብሏል ማለቱን አስራት ሚዲያ በፌስ ቡክ ገጹ ይፋ አደርጓል።

ይሁንና ፍርድ ቤቱ መረጃ ይመጣባቸዋል ከሚባሉት ተቋማት መረጃ ማጥፋት ሆነ ማዛባት እንደማይቻል ገልፆ የእስር ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ ፖሊስ መረጃ እንዲታቀርብ ቀጠሮ ከሰጠ በኋላ ጋዜጠኞቹ በዋስትና እንዲለቀቁ ማድረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብሎታል።የአሥራት ጋዜጠኞች በአራዳ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋስትና እንዲወጡ ከተወሰነላቸው በኋላ እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር የከፈሉ ሲሆን ፖሊስ በሕገወጥ መንገድ በእስር እንዳቆያቸው ጠበቃቸው መግለፃቸው ይታወቃል።

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
የድምጽ ብክለትን ለመቆጣጠር የምሽት የቁጥጥር ሥራ ሊጀመር ነው!

በተለያዩ ሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች ፣በመንገድ ላይ፣ በልብስ መሸጫ (ቡቲክ) እና በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚስተዋለውን የድምጽ ብክለት ለመቆጣጠር ከዚህ በፊት ይተገበር ያልነበረው የምሽት የቁጥጥር ስራ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ለመጀመር ማቀዱን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ለአዲሰ ማለዳ አስታወቀ።የቁጥጥር ስራው ቅዳሜ እና እሁድን በመጨመር ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ተግባዊ እንደሚሆንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
በጉራጌ ዞን እኖር ኤነር ወረዳ ሚስቱን የገደለው ተከሳሽ የሞት ፍርድ ተፈረደበት።

የዞኑ ኮሙንኬሽን እንዳስታወቀው ድርጊቱ ፈፃሚ አቶ በሀሩ ወንድም አገኝ ጉባሞ በጉራጌ ዞን እኖር ኤነረ ወረዳ የባረዋ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን ለባለቤቱ እንደሚገድላት በተደጋጋሚ እየዛተባት ነበር።በእለተ ሀሙስ በቀን 24/07/2012 በግምት ከንጋቱ 12:00 ሟች አፀደ ዘመድአገኝ በባለቤቷ እንደዛተባትም በአሰቃቂ ሁኔታ በዱላ ጭንቅላቷንና ማጅራቷን ደብድቦ ከገደላት በኋላ ወንዝ ላይ ጥሏት መሄዱ ተገልጿል።ይህንን አሰቃቂ ድርጊት የሚገልፅ የምርመራ መዝገብ የደረሰው የጉራጌ ዞን ዐቃቤ ህግ መምሪያ የልዩ ልዩ የወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ የምርመራ መዝገቡ በአግባቡ በመመርመር በተከሳሹ ግለሰብ ላይ የኢ ፌ ዲ ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 539 (1)(ሀ )ላይ የከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ክስ መስርቶበታል።

ክሱ የደረሰው የወልቂጤ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ በቀን 02/13/2012 ዓም በዋለው ችሎት የተከሳሹ ድርጊት እጅግ አደገኛና ነውረኛ መሆኑን ከግምት ውስጥ አስገብቷል።በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ከዚህ ቀደም በ1999 ዓም በሀዋሳ ከተማ የቀድሞ ባለቤቱ በተመሳሳይ ሁኔታ ገድሎ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ከሁለት አመት በፊት በይቅርታ ተለቆ መውጣቱን በቅጣት ማክበጃነት ይዟል።በመሆኑም ሰው መግደል ልማድ አድርጎ የያዘ በመሆኑ: ከዚህ በኋላ እስራት ያስተምረዋል ተብሎ ስለማይታሰብና የኢ ፌ ዲ ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 117 መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ የሚያሟላ በመሆኑ በአጠቃላይ ሌላው የህብረተሰብ ክፍል ሊያስተምር ይችላል ያለውን የሞት ቅጣት ውሳኔ ወስኖበታል ተብሏል።

[ኢትዮ ኤፍ ኤም]
@YeneTube @FikerAssefa
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መርሃ-ግብሮች ያስተማራቸውን ከ 1000 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

በ1999 ዓ.ም የተመሰረተውና የሁለተኛ ትውልድ ዩኒቨርስቲ የሆነው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መርሃግብሮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 79 ተማሪዎችን ዛሬው ዕለት ለ12 ኛ ጊዜ ባካሄደው የምረቃ ስነስርዓት አስመርቋል። የምረቃ-ስነስርዓቱም በኮቪድ-19 ወረረሽኝ ምክንያት በበይነ-መረብ በሚተፈላለፍ የቀጥታ ስርጭት ተካሂዷል፡፡ዩኒቨርሲቲው በድህረ ምረቃና በቅድመ ምረቃ በመደበኛ፣ በሳምንቱ መጨረሻ እና በክረምት መርሀግብር በማሰልጠን በዛሬው ዕለት ካስመርቃቸው 1 ሺህ 79 ዕጩ ምሩቃን 493ቱ ሴቶች ሲሆኑ ከኒዚህም ውስጥ 51ዱ በተለያዩ የትህርት መስኮች በድህረ ምረቃ ዕጩ ምሩቃን ናቸው፡፡

[የወላይታ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት]
@YeneTube @FikerAssefa
በወልቃይት እና ራያ አካባቢ ደርሷል የተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ ሊካሔድበት ነው!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በወልቃይት እና ራያ አካባቢ በሕወሓት እየደረሰ ነው የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊመረምር መሆኑን ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።በኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መከሰቱን ምክንያት በማድረግ 6ኛው አገራዊ ምርጫ መራዘሙን ተከትሎ በገዥው ፓርቲ ብልጽግና እና በህወሓት መካከል የተፈጠረው የፖለቲካ ልዩነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ትግራይ ክልል ምርጫውን በክልል ደረጃ ምርጫ ለማካሄድ ጫፍ ደርሷል ይሄኑ መነሻ በማድረግ በአማራ ክልልና በትግራይ ክልል አዋሳኝ በወልቃይትና በራያ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች ህወሓት የግድ ትምርጣላችሁ በማለት ለእስር፣ድብደባ እና ለአፈና ተዳርገናል ሲሉ አቤቱታቸውን አቅርበዋል።

ተጨማሪ👇👇👇
https://telegra.ph/-09-08-449
የትግራይ ክልል ምርጫውን ለመታዘብ የጠየቀ አንድ ተቋምን ማገዱ ተገለጠ!

«ሰብ ሕድሪ ሲቪል ማሕበረሰብ ትግራይ» የተባለ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀስ ነፃ ተቋም በትግራይ ምርጫ ለመታዘብ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ እንደተደረገበት ገለፀ፡፡

ሰብ ሕድሪ ሲቪል ማሕበረሰብ ትግራይ ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው ተቋሙ «ታሪካዊ» ባለው የትግራይ ምርጫ በታዛቢነት ለመሳተፍ 300 ገደማ አባላቱን ለታዛቢነት አዘጋጅቶ ነበር። ቢሆንም የትግራይ ምርጫ ኮምሽን ከሦስተኛ ወገን በቀረበለት ቅሬታ ከታዛቢነት እንዳገደው ዐስታውቋል፡፡ሰብ ሕድሪ ሲቪል ማሕበረሰብ ትግራይ በትግራይ ምርጫ ኮምሽን የተላለፈውን የእግድ ውሳኔ «ተገቢነት የሌለው» ብሎታል፡፡

የትግራይ ምርጫ ኮምሽን በበኩሉ ሲቪል ተቋሙ በምርጫው ከሚወዳደር ፓርቲ ቅሬታ ስለቀረበበት ነገ ይካኼዳል በተባለው ምርጫ ተሳታፊ እንዳይኾን መወሰኑን ገልጧል፡፡ሰብ ሕድሪ ሲቪል ማሕበረሰብ ትግራይ ሰኔ 2010 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን፤ በትግራይ «ዴሞክራታይዜሽን» እና ክብሮች ዙርያ የሚሠራ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ይኽ በእንዲህ እንዳለ፦ የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ለ61 የሀገር ውስጥ ተቋማት ምርጫውን እንዲታዘቡ ፍቃድ መስጠቱን ዐስታውቋል፡፡

በትናንትናው እለት አራት ጋዜጠኞችን ጨምሮ የትግራይ ክልል ምርጫን ለመከታተል ወደ መቀሌ በአየር ሊጓዙ የነበሩ ዐሥራ ኹለት ሰዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንደታገዱ ተነግሯል። ከታገዱት መካከል የሀገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች እንደሚገኙበትም ተዘግቧል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ብሄራዊ ባንክ ለ15 ተከታታይ አመታት ያልተንቀሳቀሱ ሂሳቦችን ወደ መንግስት እንዲገባ የሚያደርገውን የብሄራዊ ባንክ የባንክ ስራ አዎጅ ማስፈጸሚያ መመሪያ አወጣ!

በመመሪያው መሰረት ከ12 አመት በፊት የወጣውን የባንክ ስራ አዋጅ አንቀፅ 52 ማስፈፀሚያ የሚሆነው መመሪያ በባንኮች ለተከታታይ 15 አመት ያልተንቀሳቀሱ ከ5 ብር ጀምሮ ያሉ ሂሳቦች ወደ ብሄራዊ ባንክ መግባት አለባቸው፡፡ሆኖም ብሄራዊ ባንክ ቢደረግለትም ባለንብረቱ ወይም ህጋዊ ወራሽ ከመጣ ብሄራዊ ባንክ በማንኛውም ጊዜ ወለድን ሳይጨምር ገንዘቡን ይመልሳል፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
የትምህርት ቤት ክፍያ ላይ አላስፈላጊ ጭማሪ ያሚደረጉ ትምህርት ቤቶች ላይ እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ትምህርት ሚኒስቴር አስጠነቀቀ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከተማሪ ወላጆች የሚመጡ ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን መሰረት በማድረግ ነው እርምጃ እንደሚወሰድ ይፋ ያደረገው፡፡የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቲዎስ ከቀጣይ አመት ትምህርት ጋር በተያያዘ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ሚኒስትር ዴኤታው የግል ትምህርት ቤቶች ቀድመው ሲሰሩበት ከነበረው የአከፋፈል ስርዓት ውጪ ምንም አይነት ጭማሪ ማድረግ እንማይችሉ አስስበዋል፡፡

ቀድመው ከሚሰሩበት አሰራር ውጭ ተጨማሪ ክፍያ በሚያስከፍሉ ትምህርት ቤቶች ላይ ትምህርት ቤቶቹን እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችልም ትምህር ሚኒስቴር አስጠንቅቋል፡፡በቀጣይ ትምህርት ሲከፈት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ትምህርት ቤቶች በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20 እስከ 25 ተማሪ ብቻ ለማስተማር የሚያስችላቸውን ዝግጅት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

‹‹የግል ትምህርት ቤቶች ይህንን ለማድረግ አይቸገሩም ወይ?›› ተብለው ከጋዜጠኞች ጥያቄ የተነሳላቸው ሚኒስትር ዴኤታው ሚሊየን ማቲዮስ ቀጣዩ የትምህርት ስርዓት ወደ አዲስ አሰራር የሚሸጋገርበት በመሆኑ ራሳቸውን ለዚህ ዝግጁ ማድረግ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት፡፡የመንግስት ትምህርት ቤቶችም ተመራጭ እንዲሆኑ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ተብራርቷል::ትምህርት ሲጀመር የሚኖረው የትምህርት አሰጣጥ ሂደትም በአንድ ከፍል የሚማሩ የተማሪዎችን ቁጥር የሚወስን ይሆናል፡፡

[MoE]
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ባንክ ለ4 የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት አዲስ ዳይሬክተር ሾመ!

የዓለም ባንክ አቶ ኬት ሃንሰንን የኬንያ፣ ርዋንዳ፣ ሶማሊያ እና ኡጋንዳ ዳይሬክተር አድርጎ ሾመ፡፡ልማትን የተመለከቱ የ30 ዓመታት ልምድ ያላቸው ሃንሰን የ13 ቢሊዬን ዶላር ዋጋ ያላቸው እና በ4ቱ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የተሚተገበሩ 100 ፕሮጄክቶችን ይመራሉ ተብሏል፡፡ትኩረታቸው በኮሮና ወረርሽኝ ላይ አድርገው ሃገራቱ የጀመሩትን የዘላቂ ልማት ጉዞ እንደሚደግፉም ነው የተገለጸው፡፡ከአሁን ቀደም አፍሪካን ጨምሮ ደቡብ አሜሪካን በመሳሰሉ የተለያዩ ክፍለ አህጉራት በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉት ሃንሰን የባንኩ የሰብዓዊ ልማቶች ምክትል ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉም ሲሆን ዋና ስራ አስፈጻሚውን ያማክሩም እንደነበር የህይወትና የስራ ልምድ ማስረጃዎቻቸው ያሳያሉ፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ በመተከል ዞን ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ነጋ ጃራ ለቢቢሲ እንደገለጹት "ፀረ ሠላም" ያሏቸው ኃይሎች በወንበራ ወረዳ መልካ በምትባል ቀበሌ ሠላማዊ ሰዎችን በማገት፣ የጦር መሣሪያዎችን በመቀማትና በአካባቢው ማኅበረሰብ ንብረት ላይ ዘረፋ ፈጽመዋል ብለዋል።በትላንትናው ዕለትም [ሰኞ] በቡለን ወረዳ ኤጳር በምትባል ቀበሌ እነዚሁ ኃይሎች በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የአፈናና የግድያ ወንጀል ከመፈጸማቸው በተጨማሪ የተለያዩ ጉዳቶችን ማድረሳቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቢቢሲ በአካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን ጠይቆ እንደተረዳው በተለያዩ ጊዜያት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በሚፈጸመው ጥቃት የተነሳ የዕለት ከዕለት ተግባራቸውን በስጋት ውስጥ ሆነው እንደሚያከናውኑ ተናግረዋል።በሚፈጸሙት ጥቃቶችም በሰው ህይወት፣ አካልና ንብረት ላይ ጉዳት እየደረሰ በመሆኑ እንቅስቃሴያቸው መገደቡንና ክስተቱም ሁሉም በነጻነት እንዳይንቀሳቀስ በማድረጉ በአካባቢዎቹ ባለው ሥራ ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የወረዳው የመንግሥት ሠራተኛ ተናግረዋል።

ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከአካባቢው ነዋሪዎች በተጨማሪ የጤናና ግብርና ባለሙያዎችን ለማፈን ከመሞከራቸውም በላይ በመንግሥት መዋቅር ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከሩ መሆኑን ጠቅሰው ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ወደ ሌላ ወረዳ መሸሻቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት ተከትሎ በወጣው መረጃ መሰረት የአካባቢው ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ ልዩ ኃይል በጋራ በመሆን ወደ ወረዳዎቹ በመግባት ጥቃቱን ለማስቆምና ፈጻሚዎቹን ለመቆጣጠር በቅንጅት እየሠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ነጋ ጃራ በወረዳዎቹ እንደሚሉት ጉዳት እያስከተለ ያለው ጥቃት የሚፈጸመው ስሙን ለጊዜው መጥቀስ ባልፈለጉት "የተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድን አባላት" መሆኑንና በቁጥጥር ስር እያዋሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ እስካሁን የታገቱ እና የሞቱ ሰዎች ቁጥር በተመለከከተ "በቁጥር ደረጃ በዝርዝር አልተለየም" ያሉት ኮማንደር ነጋ፤ መረጃው ተሰባሰቦ ሲያልቅ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ በክልሉ ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች እየተፈጸመ ካለው ጥቃት ጋር በተያያዘ "ፀረ ሠላም" ያሏቸው ኃይሎች ከውጪ አገር ጭምር ድጋፍ እንደሚደረግላቸው መረጃ መገኘቱን ጠቅሰው "ወጣቶችን ለመመልመል እንደሚንቀሳቀሱም" ጨምረው ተናግረዋል።ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከቀናት በፊል መልካን በሚባል ቀበሌ 30 ሰዎችን አፍነው የነበረ ሲሆን አሁን እነሱን መልቀቃቸውን አመልክተው፤ የያዟቸውን ሰዎች ቡድኑን እንዲቀላቀሉ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በተለያዩ ጊዜያት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ማንነታቸው ያልተገጹ ቡድኖች በነዋሪዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ከማድረሳቸው ባሻገር በተደጋጋሚ ሰዎችን እያገቱ እንደሚወስዱ ሲዘገብ ቆይቷል።ይህንንም ለማስቆም የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ከአገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለመቆጣጠርና ድርጊቱን ለማስቆም እየጣሩ መሆኑ ተገልጿል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በሶሪያ እስር ቤቶች የነበሩ 3 ኢትዮጵያውን እና በሊባኖስ እስር ቤት የነበረች አንዲት ኢትዮጵያዊት ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል!

3 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ በሶሪያ አቋርጠው ወደ ሌሎች አገራት ለመሻገር ሲሞክሩ ተይዘው በሶሪያ እስር ቤቶች ታስረው የነበሩ ዜጎቻችንን ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ በቤይሩት ከሚገኘው የሶሪያ ኤምባሲ ጋር በመቀናጀት የኮሮናቫይረስ PCR ምርመራ አድርገው ዛሬ ጷጉሜ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረግ ተችሏል፡፡ሌሎች 2 በሶሪያ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በመጭው ሳምንት ወደ አገር ቤት ይመለሳሉ፡፡ቀደም ሲል በተመሳሳይ 12 ኢትዮጵያውያን (ከአንድ ህጻን ጋር) ከሶሪያ እስር ቤቶች ተለቀው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም በሊባኖስ እስር ቤት የነበረች አንዲት ኢትዮጵያዊትም ወደ አገር ቤት ተመልሳለች፡፡

[Ethiopian Counsulate in Beirut]
@YeneTube @FikerAssefa
ጥረት ኮርፖሬት ሥያሜውንና የመለያ ምልክቱን ሊቀይር ነው!

በቀድሞው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) እና በአሁኑ አማራ ብልጽግና ስር የሚተዳደረው የልማት ድርጅት ጥረት ኮርፖሬት መለያ ስያሜውንና የመለያ ምልክቱን ለመቀየር በኮርፖሬቱ ቦርድ ወሳኔ ማስተላለፉንና ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ፡፡ጥረት ኮርፖሬት ሥያሜውንና የመለያ ምልክቱን ሊቀይር ነውበቀድሞው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) እና በአሁኑ አማራ ብልጽግና ስር የሚተዳደረው የልማት ድርጅት ጥረት ኮርፖሬት መለያ ስያሜውንና የመለያ ምልክቱን ለመቀየር በኮርፖሬቱ ቦርድ ወሳኔ ማስተላለፉንና ወደ ስራ መግባቱን አስታወቋል፡፡

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
ነገ በትግራይ ይደረጋል ለተባለው ምርጫ 2672 ድምፅ መስጫ ጣብያዎች መዘጋጀታቸው የትግራይ ምርጫ ኮምሽን ዐስታወቀ፡፡

በነገው ድምፅ የመስጠት ስነ ስርዓት 2 ነጥብ 7 ሚልዮን ህዝብ ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡በመቐለ የተለያዩ አካባቢዎች የድምፅ መስጫ ጣብያዎች በየአካባቢው ምርጫ አስፈፃሚዎችና ወጣቶች እየተዘጋጁ ነው፡፡ በከተማዋ የፀጥታ ሐይሎች ጥብቅ ቁጥጥር እያደረጉም ይገኛሉ፡፡ከዛሬ ምሽት ጀምሮም የብስክሌቶች፣ የሞተር ሳይክሎች፣ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጆች) እንቅስቃሴ በጊዜያዊነት መከልከሉ የትግራይ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል፡፡ነገ ጳጉሜ 4 ቀን፣ 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማታ 12 ሰዓት መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ፡ ተብሎ ይጠበቃል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1136 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 14,815 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 1136 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

307 ሰዎች ሲያገግሙ 16 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

እስካሁን በአጠቃላይ 60,784 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 22,677 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን የ949 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa