YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የማህበር ቤቶች የቤት ግንባታ አማራጭ የ2005 ዓ.ም ተመዝጋቢዎችን ቅድሚያ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተገለጸ!

የማህበር ቤቶች የቤት ግንባታ አማራጭ ፍላጎት ያላቸውን የ2005 ዓ.ም የ20/80 እና 40/60 ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።የማህበር ቤት ግንባታዎቹ ከዚህ በፊት የታዩ ክፍተቶችን ለመድፈን በመሀል ከተማ እንዲገነቡ መሬት እየተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው 30ኛ ስብሰባው የማህበር ቤቶች የቤት ግንባታ አማራጭ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።የቢሮው ኃላፊ ኢንጅነር ሰናይት ዳምጠው በውሳኔው ዙሪያ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።የቤት አቅርቦት እና ፍላጎቱ ባለመጣጣሙ እንዲሁም ግንባታው በሚፈለገው ፍጥነት እና ብዛት ልክ እየተካሄደ ባለመሆኑ አማራጭ የቤት ልማት መርሃ ግብሮችን ለመንደፍ ሲጠና መቆየቱን ኃላፊዋ ተናግረዋል።

በማህበር ተደራጅተው ቤት ለመገንባት ፍቃደኛ ለሆኑ መንግሥት ከባንኮች ጋር የማስተሳሰር ስራን ያከናውናል፣ መሬትን ያቀርባል፣ መሰረተ ልማቶችን ያሟላል ነው የተባለው።መኖሪያ ቤትን በስፋት ለማቅረብ ከማህበር ቤት ግንባታ በተጨማሪ ሪል እስቴትን ማልማት እና የኪራይ ቤቶችን ግንባታ ማስፋፋትን ጨምሮ ሌሎች አማራጮች ተግባራዊ እንደሚሆኑ የተገለጸ ሲሆን ነባር የ1997 ዓመተ ምህርት ተመዝጋቢዎች አሁን መንግሥት እያከናወናቸው ባሉ የቤት ልማት ስራዎች የሚስተናገዱ መሆናቸውም ነው የተመላከተው።በሁለቱ ዙሮች ተመዝግበው መረጃዎቻቸው በአስተዳደሩ ቋት ውስጥ የሚገኝ ነዋሪዎች ከመርሃ ግብሩ ሳይወጡ በትዕግስት እንዲጠባበቁም ኃላፊዋ ማሳሰቧን አሳስበዋል።

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት ለአመታት ሲጓተት የነበረ የተቋራጮችን ክፍያ መፈፀሙን አስታወቀ!

ለ7 አመታት ክፍያ ተጠይቆባቸው የነበሩ የመንገድ ስራ ፕሮጀክቶችን ክፍያ ባለፈው በጀት አመት መፈፀሙን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ባለፈው በኢኮኖሚ መስክ በርካታ እመርታዎ መምጣታቸውን የተናገሩት እዮብ (ዶ/ር) ከነዚህም መካከል ሲጓተቱ የቆዩ ክፍያዎችን ማጠናቀቅ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
ለ7 አመት ግድም ሲጓተቱ የነበሩ የ6 ቢሊየን ብር ግድም የሚሆኑ ክፍያዎች ተፈፅመዋል ብለዋል፡፡ፕሮጀክት በግዜ ቢያጠናቅቁም በክፈፍያ መዘግየት በተለይ የውጭ ተቋራጮች ቅሬታ ሲያሰሙ ይታያል፡፡ ይሄን ቅሬታ ለመቅረፍ ክፍያን በወቅቱ መፈፀም ለፕሮጀክት አፈጻፀም አብይ ጉዳይ መሆኑን ባለሞያዎች ያስረዳሉ፡፡

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
👆👆

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ለ2013 በጀት ዓመት ያጸደቀው በጀት ዝርዝር

ምንጭ፡ የደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ
@YeneTube @FikerAssefa
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለኦሜን ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ የፈቀደለትን ዋስትና ዛሬ ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንዳጸና አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ ፖሊስ እስከዛሬ ሰኞ ድረስ በተጠርጣሪው ላይ ክስ እንዲመሰርት ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም ክስ ሳይመሰርት ቀርቷል፡፡ በኦፌኮ አመራር ደጀኔ ጠፋ ላይ ግን ዐቃቤ ሕግ ነገ ክስ እመሰርታለሁ ብሎ ችሎቱ ፈቅዶለታል፡፡ በኦሜን ኮምፒውተር ባለሙያ ሚሻ አደም ላይ ደሞ፣ ዐቃቤ ሕግ እስከ መስከረም 3 ክስ እንዲመሰርት ታዟል፡፡

[AS & Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ 8 ባህላዊ መድሃኒቶች የኮቪድ-19 ለመከላከልና ለማከም ፈዋሸነታቸው እየተገመገመ ነው

በኢትዮጵያ ኮቪድ-19ን ለማከምና ለመከላከል የሚረዱ ስምንት ባህላዊ መድሃኒቶች ፈዋሽነታቸውን በሳይንሳዊ ዘዴ ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።
የአፍሪካ የባህል መድሃኒቶች ቀን በየዓመቱ ነሃሴ 25 ቀን ታስቦ የሚውል በመሆኑ 18ኛው አህጉር አቀፍ የባህል ህክምና ቀን እየተከበረ ነው።

በዓሉን በማስመልከት የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣንና የባህላዊ የህክምና አዋቂዎች ማህበር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የምርት ደህንነት ዳይሬክተር ወይዘሮ አስናቀች አለሙ እንዳሉት ኮቪድን ለመከላከልና ለማከም ”የባህላዊ መድሃኒቶች ጊዚያዊ ጋይዳንስ” ተዘጋጅቶ የሙከራ ጥያቄዎችን በማስተናገድ ላይ ናቸው።

በሂደቱ ስምንት የሚሆኑ ኮቪድን ለማከምና ለመከላከል የሚያግዙ የባህላዊ መድሃኒቶች ቀርበው በሰው ላይ ሙከራ እንዲደረጉ የሚያስችል የሰነድ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል።
የባህል ህክምና አዋቂዎች እነዚህ መድሃኒቶች በተለያዩ የሙከራ ዘዴዎች በማለፍ ውጤት አገኝተንበታል ብለው እውቅና እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቅርበዋል።

Via:- Ethiopia News Agency
@Yenetube @Fikerassefa
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መመሪያ የኮሮና ቫይረስ እለታዊ ሪፓርት

ዛሬ በላብራቶሪ የተመረመሩ ብዛት :- 338
ዛሬ የተያዙ :- 7
ዛሬ ህይወታቸው ያለፈ :- 0
ዛሬ ከበሽታው ያገገሙ :- 31
_____________________________
በአጠቃላይ የተመረመሩ :- 9896
በበሽታው የተያዙ :- 1011
በአሁን ሰዕት ህክምና ላይ ያሉ :- 531
ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ያገገሙ :- 470
@Yenetube @Fikerassefa
በአማራ ክልል ተጨማሪ 75 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ 88 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,009 ሰዎች በኮሮና ሲያዙ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,364 የላብራቶሪ ምርመራ 1,009 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 612 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 52,131 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 809 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 18,994 ደርሷል። በፅኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር 344 መድረሱን ጤና ሚኒስተር ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ትናንት ተጠናቋል፡፡ ጳጉሜ 4 2012 ድምፅ ሊሰጥ መርሐ ግብር ለወጣለት ምርጫ 2.7 ሚልዮን ድምፅ ሰጪዎች ተመዝግበዋል ሲል የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።ከዚህ ሌላ በምርጫው የሚወዳደሩ ፓርቲዎች  በየአካባቢው የሚወዳደሩትን እጩዎቻቸውን ይፋ እያደረጉ ነው። የምረጡኝ ዘመቻና የቀጥታ የቴሌቪዥን ክርክርም በሂደት ላይ ነው፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
ሩስያ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ከመስከረም ወር ጀምሮ በስፋት ልታሰራጭ መሆኑን አስታወቀች!

ሩስያ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ከመስከረም ወር ጀምሮ በስፋት ለማሰራጨት ማቀዷን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ሚኻኤል ሙራሽኮ አስታወቁ።ሩስያ ከ25 ሚሊየን በላይ የዓለም ህዝብ ላጠቃው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማግኘቷን በቅርቡ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።ይህንንም ተከትሎ የጤና ሚኒስትሩ በመጀመሪያ ዙር የሚከተቡት የጤና ባለሙያዎችና መምህራን መሆናቸውን ተናግረዋል።ክትባቱም ሙሉ ለሙሉ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም አንስተዋል።ሞስኮታይምስን ጠቅሶ ኤፍ.ቢ.ሲ እንደዘገበው፤ የጤና ሚኒስትሩ የክትባት ምርት እየተከናወነ ጎን ለጎን ደግሞ ፈዋሽነቱ እየተፈተሸ ነው ብለዋል።

እስከ አሁን ለሦስተኛ ደረጃ ሙከራ ከተመዘገቡ 40 ሺህ በጎ ፈቃደኞች መካከል 2 ሺህ 500 ሰዎች መመረጣቸውንም አስታውቀዋል።

በአንጻሩ ምዕራባውያን የክትባቱ ፈዋሽነት ላይ የተዓማኒነት ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፦ ሩስያ በበኩሏ ጥያቄውን ውድቅ አድርገዋለች።በተጨማሪም ሩስያ ከ20 ሀገራት በላይ 1 ቢሊየን መጠን የያዘ ስፑትኒክ ቪ ክትባት እንዲመረትላቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።ሆኖም ግን የዓለም ጤና ድርጅት በክትባቱ ዙሪያ ከሩሲያ ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገረ መሆኑንም በትናንትናው እለት ማስታወቁ አይዘነጋም።የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የሩሲያ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ለመመዘንም ከሀገሪቱ በቂ መረጃ እንዳላገኘም ነው በመነገር ላይ የሚገኘው።

@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የመደበችውን 130 ሚሊዮን ዶላር እንዳይሰጥ በጊዜያዊነት እንዲታገድ መወሰኗ ተረጋገጠ።

በዋሽንግተን ውሳኔ ላይ ማብራሪያ ማግኘታቸውን ያሳወቁት በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ "ጉዳዩ Temporary Pause እንደሆነ ተረድተናል" ሲሉ በፌስ ቡክ ገፃቸው አስነብበዋል:: በኅዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር በግብፅ ጋባዥነት ወደ ታዛቢነት መድረኩ ከመጣ በኋላ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ማሳደር የጀመረው የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የኢትዮጵያ ፍትሐዊ የተጠቃሚነት መርህ አልተዋጠለትም።

በተለይም ኢትዮጵያ ድርድሩ ወደ አፍሪካ ኅብረት እንዲመለስ ማድረጓ ያበሳጨው የትራምፕ አስተዳደር አሜሪካ ለኢትዮጵያ ትሰጥ ከነበረው እርዳታ የተወሰነውን ማገድ ሌላው የጫና መፍጠሪያ ስልት አድርጎ አምጥቶታል። ስለጉዳዩ የጻፉት አምባሳደሩ ፍፁም በበኩላቸው "ግድቡ የኛ ነው! ተባብረን እንጨርሰዋለን! በጥረታችን ኢትዮጵያችን በብርሃን ትደምቃለች!" ብለው ማስፈራቸውን አሀዱ ቴሌቭዥን ዘግቧል።

[FidelPost & Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa
መንግስት ለታሰሩ ጋዜጠኞች አፋጣኝ ፍትህን እንዲሰጥ ማህበሩ አሳሰበ!

ተጠርጥረው ለታሰሩ የአስራት ቴሌቪዥን እና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ጋዜጠኞች መንግስት አፋጣኝ ፍትህን እንዲሰጥ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ማህበር አሳስበቧል።

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ከወርቅ ማዕድን 198 ነጥብ 3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለፀ!

በተጠናቀቀው 2012 በጀት ዓመት ከባህላዊ አምራቾችና ከኩባንያዎች ለውጭ ገበያ ከቀረቡ የወርቅ ማዕድናት 198 ነጥብ ሶስት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገቢ መገኘቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ።የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደተመለከተው፤ በበጀት ዓመቱ በኩባንያዎች 849 ኪሎ ግራም ወርቅ ለማምረትና 32 ነጥብ 75 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 678 ነጥብ 39 ኪሎ ግራም ወርቅ በማምረት 36 ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ተገኝቷል።

በባህላዊ ወርቅ አምራቾች 115 ነጥብ 74 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ ሶስት ሺህ ኪሎ ግራም ወርቅ ለማቅረብ ታቅዶ ሁለት ሺህ 397 ነጥብ 857 ኪሎ ግራም ወርቅ ማቅረብ መቻሉን መግለጫው አስታውቋል።በሌሎች አቅራቢዎች 108 ነጥብ 55 እና በኮንትሮባንድ ከተያዘው 14 ነጥብ 246 ኪሎ ግራም ጋር በድምሩ ሁለት ሺህ 520 ነጥብ 653 ወይም የዕቅዱ 84 ከመቶ ለባንክ ሊያቀርብ መቻሉን መግለጫው አስታውቋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
የእነ ጃዋር መሐመድን የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ የሚመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት፤ በዛሬ ማክሰኞ የችሎት ውሎው፤ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የእስረኛ አስተዳደር ኃላፊ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።ፍርድ ቤቱ ማስጠንቀቂያውን የሰጠው፤ በፖሊስ ኮሚሽን ቁጥጥር ስር ላሉ 3 ተጠርጣሪዎች የኮሮና ምርመራ ተደርጎ፣ ውጤት እንዲቀርብ የሰጠው ተደጋጋሚ ትዕዛዝ ባለመፈጸሙ ነው።ፍርድ ቤቱ የእስረኛ አስተዳደር ኃላፊው ለዛሬ ታስረው እንዲቀርቡ አዝዞ ነበር።

ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 26፤ 2012 ችሎት ፊት የቀረቡት የኮሚሽኑ እስረኞች አስተዳደር ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አራጌ እሸቴ "በቴሌቪዥን በተላለፈው መሰረት መቅረብ ስላለብኝ ቀርቤያለሁ። ማንም አስሮ ያስገደደኝ አካል የለም" ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር ላሉ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በነሐሴ ወር ለ3 ጊዜያት ምርመራ እንደተደርገላቸው የተናገሩት የእስረኛ አስተዳደር ኃላፊው፤ የምርመራ ውጤታቸውን ለፍርድ ቤት እንዲቀርብ "ማንም የነገረኝ ወይም የጠየቀኝ የለም" ብለዋል። "እኛ ማቅረብ የምንችለው የራሳችንን እስረኞች ውጤት ነው" ያሉት ዋና ኢንስፔክተር አራጌ እሸቴ፤ የሶስቱን ተጠርጣሪዎች የምርመራ ውጤት ማቅረብ ያለባቸው "የፌደራል እስረኛ አስተዳደር ኃላፊዎች ነው" ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
በናይጀሪያ ሌጎስ ከተማ ትምህርት ቤቶች በቀጣይ ወር ሊከፈቱ ነው።

በናይጄሪያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በመቀነሱ በሀገሪቱ የንግድ ከተማ በሆነችው ሌጎስ ከቀጣይ ወር ጀምሮ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፈቱ የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።በሌጎስ ኮሌጆች በመጪው መስከረም 14 የሚከፈቱ ሲሆን አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም ከ መስከረም 21 ጀምሮ ክፍት እንደሚሆኑ ተገልጿል።በዚህ ወር ናይጄሪያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዋች የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፈተና እንዲወሰድ ትምህርት ቤቶችን መክፈቷ ይታወሳል።

ምንጭ - ሲጂቲኤን/MoE
@YeneTube @FikerAssefa
ኢዴፓ በፍርድ ቤት ነጻ የተባሉትን አቶ ልደቱ አያሌው ከእስር ባለመለቀቃቸው "አካልን ነጻ የማድረግ" ክስ ሊመሰርት መሆኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ እንደገለጹት አቶ ልደቱ አያሌው የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት መዝገቡን ዘግቶ ነጻ መሆናቸውን ቢያሳውቅም እስካሁን ከእስር አልተፈቱም።

ፖሊስ አቶ ልደቱን እንዲፈታ እና የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለምን አይከበርም ብለን ስንጠይቅ ይሄ አሰራራችን ነው የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል የሚሉት አቶ አዳነ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፖሊስ የፍርድ ቤቶችን ትዕዛዝ አለማክበር እየተለመደ መጥቷል ብለዋል።

በዚህም መሰረት አቶ ልደቱ አያሌውን ከእስር ለማስፈታት " አካልን ነጻ ማውጣት" የተሰኘ ክስ ለአዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሊያስገቡ መሆኑንን ሊቀመንበሩ አስታውቀዋል።ፓርቲው ክሱን ለመመስረት በዛሬው እለት ከህግ ባለሙያዎቻችን ጋር በመነጋገር ላይ ነን ሲሉም ተናግረዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ግብርና ሚኒስቴር በኮሮና ቫይረስ የሚጠቁ ሰራተኞች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ሰራተኞች እስከ መስከረም ድረስ በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ አደረገ።

እስካሁን ድረስ 70 ሰራተኞች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

በቫይረሱ ከተጠቁ ሰራተኞች መካከልም የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሁሴን የጥበቃ እና ፕሮቶኮል ሰራተኞችን ይጨምራል።አቶ ኡመር ሁሴን ጠባቂዎቻቸው በቫይረሱ መጠቃታቸው በምርመራ መረጋገጡን ተከትሎ ራሳቸውን አግልለው በቤታቸው ቆይተው አሁን ላይ በተደረገላቸው ምርመራ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን ሰምተናል።

በቫይረሱ የተያዙ ሰራተኞቹ ቁጥር መጨመሩ ያሳሰበው ሚኒስቴሩም ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ከወጪ ንግድ ጋር የተያያዙ አስቸኳይ ስራዎችን ከሚያከናውኑ ውስን ሰራተኞች ውጪ ቀሪዎቹ በቤታቸው እንዲቆዩ እና ስራቸውን በኢንተርኔት እንዲያከናውኑ ማድረጉ ተገልጿል።

የግብርና ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አበራ ለማ በበኩላቸው 90 በመቶ የሚኒስቴሩ ሰራተኞች ስራቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው እያከናወኑ መሆኑን ገልጸው በቫይረሱ የተጠቁ ሰራተኞች ቁጥር መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የፖሊስ ደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል ሲፈጽሙ የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች በተደረገ ተኩስ ልውውጥ በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የማቻክል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ኮማንደር አምሳል ሰውነት በሰጡት መግለጫ የአዲስ አበባ ፖሊስ መለያ በመልበስ በ21/12/2012 ዓ.ም በወረዳው የደፋስ ቀበሌ ተፈላጊ ወንጀለኛን ለመያዝ እንደመጡ የማታለያ ቃል በመጠቀም መሳሪያ ለመንጠቅና የግድያ ወንጀል ሊፈጽሙ ሲሉ ህብረተሰቡ ባደረገው ጥቆማ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸው ተጠርጣሪዎች ህብረተሰቡን በመደብደብ፣በመግደልና በማታለል መሳሪያ በመንጠቅ ወንጀል ላይ የሚሳተፉ መሆናቸውን በመግለጫቸው አስታውሰው ፖሊስ፣የሚሊሻ አባላት እና በህብረተሰቡ የተሳለጠ ቅንጅት ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በአንድ ተጠርጣሪ ላይ ቁስለት መድረሱን ገልጸዋል፡፡ሀላፊው አያይዘው ተጠርጣሪዎች ከደብረ ኤሊያስ ወረዳ ከነጠቁት ክላሽ ጋር በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ህብረተሰቡን ፖሊስ ነን በማለት በማታለል ወንጀል የሚፈጽሙ ወንጅለኞችና ጸጉረ ልውጥ ሰዎችን በሚያይበት ጊዜ ለጸጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ በማቅረብ የተጠርጣሪዎችን የምርመራ ውጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡

[የወረዳው መንግስት ኮምኒኬሽን]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የአዲስ አበባ የመሬት ወረራና የኮንዶሚኒየም እንደላ ህገ-ወጥነትን ተከትዬ ባደረኩት ጥናት መሰረት የወንጀል ይጣራልኝ አቤቱታ አቅርቤያሁ አለ፡፡

የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ለሸገር እንደተናገሩት ግኝታችንን መሰረት አድርገን የወንጀል ይጣራልን አቤቱታ ለ3 ተቋማት አቅርበናል ይላሉ፡፡

ኢዜማ ከቀናት በፊት ጉዳዩን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ጥሪ ቢያደርግም ህጋዊውን አካሄድ አላሟላህም ተብሎ መከልከሉ የሚታወስ ሲሆን በተመሳሳይ ትንናትና የጠራው መግለጫም ባለመፈቀዱ ግኝቴ ያለውን ከቢሮው ሆኖ ሪፖርት አድርጓል፡፡

ኢዜማ የአዲስ አበባ ጉዳይ አሳስቦኛል የመሬትና የኮንዶሚኒየም ህገ-ወጥ እደላው ነገርም አሳሳቢ ከሆኑ ነጥቦች መሀከል አንዱ ነው ሲል ተናግሯል፡፡የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ ምንም በህገ-ወጥ መንገድ የተሰራ ስራ የለም በሚል በህጋዊነቱና በአሰራሩ ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎችም መልስ ሲሰጥ ተሰምቷል፡፡

ኢዜማ የወንጀል ይጣራልኝ አቤቱታ ያቀረብኩት ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ለፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽንና ለፌዴራል ፖሊስ ነው ሲልም ለሸገር ነግሯል፡፡

[Sheger FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በትናንትናው እለት በኢዜማ አማካኝነት ይፋ በተደረገው የመሬት ወረራና የህገወጥ ኮንዶሚኒዬም እደላ የጥናት ውጤትን በተመለከተ የሚከተለውን ጽሑፍ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው አስፍረዋል።
👇👇

<<በሀሰተኛ መረጃ ሀገር ማፍረስ ይቻል ይሆናል እንጂ ሀገር አይገነባም -የፖለቲካ ትርፍም የለውም!!

ለዚህ ምላሽ ለመስጠት ተገቢው ቦታ ላይ ባልገኝም ከዚህ የመጓተት ፖለቲካ አስተሳሰብ መውጣት አለመቻል ግን ትልቅ ህመም እንደሆነ ይሰማኛል።የመሬት ወረራን በተመለከተ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ጠንካራ የሆነ እርምጃ ስንወስድበት የቆየንበት ጉዳይ ነው።በተለያዩ ጊዜዎች የወሰድናቸው እርምጃዎችም ህያው ምስክሮች ናቸው።እኛ ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል እርምጃ ስንወስድ የዛሬ ተቺዎች የሰብአዊ መብት ተነካ፣ ዜጎች ተፈናቀሉ ብለው ዘመቻ ከከፈቱብን ውስጥ ነበሩ።

ለ20ሺህ አርሶአደሮች የተሰጡ የኮንዶሚኒየም ቤቶች በተመለከተም ከአንድ አመት ተኩል በፊት በካቢኔ የተወሰነና የተተገበረ ነው።በድብቅ የተተገበረም ሳይሆን በመንግስት ሚዲያም በይፋ የተገለፀ ነበር።ከመሬታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ከወደቁ በራሳቸው መሬት ላይ በተሰራ ህንጻ ዘበኛ እና ተሸካሚ ሆነው ከቀሩ 67 ሺህ አባወራዎች መሃል የከፋ ችግር ላይ ለወደቁት 20 ሺህ ኮንዶሚንየም ቢያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም።

ከዚህ ውጭ በህገወጥ መንገድ የተሰጠ ምንም አይነት ቤት የለም።ይህ ሥራችን በተደጋጋሚ በይፋ ስንናገር እንደነበረው የምናፍርበት ሳይሆን የምንኮራበት ነው።በግፍ የተገፋን፣ በግፍ ከመሬቱ የተፈናቀለን አርሶ አደር መካስ ያኮራናል!
በዙሪያዋ ካሉት አርሶ አደሮች ጋር በፍቅር ተሳስባ የምትኖር የተሰናሰለች ከተማ እንጂ በዙሪያዋ ካሉት ህዝቦች ጋር የተቀያየመች ከተማ እንድትኖር አንሻም ነበርና።ይህ ደግሞ የከተማዋ ነዋሪዎች ፍላጎት መሆኑንም እንገነዘባለን።

አንድም ቀን በግፍ ለተፈናቀሉ አርሶአደሮች የመቆርቆር ስሜት አሳይቶ የማያውቅ ቡድን ዛሬ የአርሶአደሮችን ጉዳት ለተቀባይነት ማግኛ መጠቀሚያ ሲያደርገው ማየት ያሳዝናል።ነገር ግን በሃሰተኛ እና በተጋነነ መረጃ ጠንካራ መምሰል እንጂ መሆን አይቻልም።
በሀሰተኛ መረጃ ድካማችንና ስራችንን ለማጠልሸት ቢሞከርም ስራችን ይናገራልና ፍርድ የህዝብ ነው!>>

©Takele Uma Banti
@YeneTube @FikerAssefa